19/08/2022
የኢትዬጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አመራሮች የቱርክ ኤምባሲ የሐይማኖት ጉዳይ ዳይሪክቶሬትን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ የሀይማኖት ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት ከሆኑት ከጀሚል ኢብራሂም ጋር በፅህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል
በውይይቱ ላይ ከፕሬዝደንቱ በተጨማሪ ምክትል ፕሬዝደንቱ ሼይኽ አብደልአዚዝ አብድል ወሌ እና የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ፀሃፊ ሼይኽ ሐሚድ ሙሳ ተካፍለዋል::
በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ የሀይማኖት ጉዳዮች ዳይሪክቶሬት ሚስተር ጀሚል ኢብራሂም ከጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ጋር ትውውቅ ያደረጉ ሲሆን በሐይማኖታዊ እና በሌሎች በሁለትዬሽ ጉዳዮች ላይ በስፋት አብረው መስራት እንደሚፈልጉ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል::
ሚስተር ጀማል ኢብራሂም በኢትዬጵያ የቅዱስ ቁርዓን የአማርኛ ትርጉምን በስፋት ለህዝቡ ተደራሽ እንዲሆን ለማስቻል በበርካታ ኮፒ አሳትመው ለማሰራጨት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር አብረው መስራት እንደሚፈልጉ የገለፁ ሲሆን በተጨማሪም የቅዱስ ቁርዓንን በኦሮምኛ ቋንቋ ትርጉም በመጅሊሱ በኩል ተዘጋጅቶ እንዲሰጣቸው እና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ በሚፈለገው ብዛት አሳትመው ለህዝቡ ለማድረስ ቢሯቸው ዝግጁ መሆኑን ለጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራሮች ገልፀውላቸዋል::
በጠቅላይ ምክር ቤቱ አመራር በኩልም ሙስሊሙን የሚጠቅሙ ማንኛውንም ስራዎች በትብብር እና በመተጋገዝ ለመስራት ሁሌም ዝግጁ መሆናቸውን እና በራቸው ክፍት መሆኑን የገለፁ ሲሆን ከቱርክ ኤምባሲ የሐማኖትን ጉዳይ ዳይሪክቶሬት ጋር በቀጣይም በስፋት በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመስራት ከስምምነት በመድረስ ውይይታቸውን አጠናቀዋል::