25/07/2023
#እመን
ጓዶቻቸዉ ቤተ መንግስት ገብተዉ የአማራ ህዝብ ተስፋ የጣለበትን ድርጅት አብንን በጥቅም ፈረቃ ተጣልተዉ ያፈረሱት እነ ዘሪሁን ገሰሰና ጓዶቻቸዉ፣ አሁን ከሀገር የተሰደዱት እነ ሙሉጌታ አንበርብር እና መሰሎቻቸዉ አሁን አማራ ክልል ዉስጥ ያለዉ ትግል ሙሉ በሙሉ ዉጤታማ ይሆናል ብለዉ ሲገመግሙ ስናይ የእነዚህ አካላት የመሪነት ብቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን ተረድተን እንኳንም ቤተ መንግስት አልገቡ እንድንል ሳያስገድደን አልቀረም።እነዚህ አካላት አማራዉ ወንድም ወንድሙን እየገደለ የነፃነት ዉጤት ይመጣል ብለዉ የሚያስቡ የዋሆች ናቸዉ።ትግልና ዉጤቱ ሳይምታታባቸዉ የቀረ አይመስለኝም።ሌላዉ ቢቀር ከቅርብ ጊዜዋ ድንፋታም ህወሓት መማር ነበረባቸዉና።ትህነግ ያላትን ገንዘብና ግዛቷን ይዛ ጉልበተኛ ነኝ ብላ ባትንቀዣቀዥ ኖሮ የአማራዉ እርስቶች የሆኑት ወልቃይትና ራያ ወደ ባለቤታቸዉ አማራ ይመለሳሉ ብል ማሰብ ከባድ ነዉ።ግን የእዉነት አምላክ አንቀዣቀዣትና ሀብቷም ወድሞ በስልጣኗ የወሰደቻቸዉ ግዛቶች ወደ ባለቤታቸዉ ተመልሰዉ ሀያል ነኝ ባይ የነበረችዉ አቅመ ቢስ ሆና ያለ ክራንች የማትንቀሳቀስ ሽባ ሆናለች።ምንም እንኳ የእነሱ የአላማ ቁርጠኝነታቸዉና አንድነታቸዉ ሳይደነቅ የማይታለፍ ቢሆንም።አሁን የአማራ አንድነትን ሳይሆን መከፋፈልን እየሰበኩ ነፃ እናወጣለን የሚሉ አካላትን ስናይ ቃቃ ጨዋታ እየተጫወቱ ዜጋን መስዋትነት እያስከፈሉ የትኛዉን ነፃነት እንደሚያጎናፅፉ ማወቅ ከባድ ሆኗል።ትግል መነሻ፣መድረሻ፣የትግሉ ደጋፊወችና አካላት ከተለዩ ዉጤታማ ይሆናል።ትናንት ሞቶ ወልቃይትንና ራያን ወደ ባለቤቱ ያስመለሰን ፖሊስ ዛሬ ከቤትህ ወጥተህ ባንዳ ብለህ ገድለህ በአስከሬኑ ላይ የምትሸልል የዋህ ትግል ያልገባህ በወንድምህ አስከሬን ተረማምደህ የምታመጣዉ ዉጤት ለመገመት አዳጋች ነዉ።ወረዳን ተቆጣጠርኩ ወዘተ እያልክ ትግል ዉጤቱ ፕሮፖጋንዳ ብቻ ከመሰለህ ተሳስተሀል።የተቆጣጠርከዉን ወረዳ ህዝብ በየትኛዉ በጀትና ቀመር እንደምታስተዳድረዉ አላሰብክምና።ትግልህ መሀል ላይ ምን እንደሚገጥመዉ አልገመትክም አላሰብክምና እሰብ።
ይህን ስል ትግሉ አላስፈላጊ ነዉ ለማለት አደለም።ብአዴናዊነት ቀንበር ህዝቡን መልቀቅ እንዳለበትም አምናለሁ።ትግሉ ግን ሁሉን ያማከለ በስሌት የሚመራ ወንድማዊ መገዳደል የሌለበት ትርፍና ኪሳራዉን ያገናዘበ ትግል እንዲሆን ስለምመኚ እንጅ።የአሁኑ አካሄድ ግን ክልሉ ዉስጥ ሙሉ ስርአት አልበኝነትን ከመዉለድ ዉጭ የሚዪመጣዉ ለዉጥ እንደሌለም ስለማምን ጭምር ነዉ።
ስለዚህ በዉይይት የታጀበ አሳዳጅና ተሳዳጅ የሌለበት የትግል መስመር መፍጠር ለዉጤት ያበቃል።