ኖሎት ቲዩብ nolot tube

  • Home
  • ኖሎት ቲዩብ nolot tube

ኖሎት ቲዩብ nolot tube ስለ እውነት እንሰራለን!! እውነት መርሀችን ነው ።

 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መሰበር አደጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የ258 ተማሪዎች ስም ዝርዝር።
10/10/2022



በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው የድልድይ መሰበር አደጋ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የ258 ተማሪዎች ስም ዝርዝር።

https://youtu.be/b9rriowUoac
27/09/2022

https://youtu.be/b9rriowUoac

ከድምጻዊ ማዲንጎ ሞት ጀርባ ያለው ማነው በጠዋት ለሚኩራ ለምን ሄደ አንድ የግል ክሊኒክ በመሄድ የህመም ማስታገሻዎችን እና ሌሎች መድኃኒቶችን ወስዶ እንደነበርና ሕይወቱ ያለፈው ረፋድ ...

https://youtu.be/lizIuJZZ7vg
06/06/2022

https://youtu.be/lizIuJZZ7vg

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

https://youtu.be/ZPJFHceb16M
25/05/2022

https://youtu.be/ZPJFHceb16M

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

እባካችሁ በቻልነው አቅም እንርዳው!   | ዳንኤል ታለጌታ ይባላል የ35 አመት ወጣት ነው የታክሲ ሹፌር ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቶቹ አይሰሩም በብዙ ስቃይ ላይ ነው ያለው  ፥ ኩላሊት ለጋሽ ያገኘ...
18/03/2022

እባካችሁ በቻልነው አቅም እንርዳው!
| ዳንኤል ታለጌታ ይባላል የ35 አመት ወጣት ነው የታክሲ ሹፌር ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቶቹ አይሰሩም በብዙ ስቃይ ላይ ነው ያለው ፥ ኩላሊት ለጋሽ ያገኘ ሲሆን ውጭ ሀገር ሄዶ ለመታከም 60ሺ ዳላር ያስፈልገዋል። በእናቱና በእህቱ ስም አካውንት ተከፍቷል የቻልነውን እንርዳው ጸሎታችሁም አይለየው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000460568645
https://www.gofundme.com/f/g347nq-for-kidney-disease...
ከኢትዮጵያ ዉጭ ያላችሁ
https://www.gofundme.com/f/g347nq-for-kidney-disease...
* በኢትዮጵያ ያላችሁ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፍሬህይወት ታለጌታ እና ከበቡሽ ገ/ፃድቅ
የሒሳብ ቁጥር 1000460568645
ለበለጠ መረጃ :-0913010159 ዳንኤል ታለጌታ
አይዞህ ወንድሜ !

https://www.youtube.com/watch?v=GhXUk54-Dx8
17/03/2022

https://www.youtube.com/watch?v=GhXUk54-Dx8

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

አይተን ዝም ማለት ስለማይሆንልን ሼር እናረጋለን አይታችሁ ዝም ማለት የማትችሉ "የወንድሜ ህመም የኔ ም ህመም ነው"  የምትሉ ሼር አርጉለት ማንን ጌታ እንደሚጠቀም አናውቅምና ወንጌልን በታማ...
14/03/2022

አይተን ዝም ማለት ስለማይሆንልን ሼር እናረጋለን አይታችሁ ዝም ማለት የማትችሉ "የወንድሜ ህመም የኔ ም ህመም ነው" የምትሉ ሼር አርጉለት
ማንን ጌታ እንደሚጠቀም አናውቅምና
ወንጌልን በታማኝነት እያገለገለ በገንዘብ እጦት ማንም በስቃይና መኖር የለበትም
የ37 አመቱ የወንጌል አርበኛ ብዛየሁ በፎቶ ላይ እንደሚታዩት ይህ እባጭ ወደ ካንሰር ተቀይሮበት
ለ5 አመታትእጅግ እያሰቃየው ይገኛል በቶሎ ህክምና ካላገኘ ለህይወቱ አስጊ ነው በሀገር ውስጥ አምስት ጊዜ ሰርጀሪ አድር ጎ ውጤት አላመጣም ከሀገር ወጥቶ ተገቢውን ህክምና ለማድረግ 1.5 ሚሊዮን ብር ያስፈልገዋል። በቀን በቀን በፊታችሁ እየቆምን እንዳስቸገርን ይገባናል ግን ወንገሌልን አገልግሎ ማንም ሊጣል እንዳይገባና እግዜርም ሰዎችንን እንደሚያስነሳለት አምነንን ይኸው ዛሬም ልንለምን ደፈርን ተባረኩ ሳትሰለቹ ከኛ ጋር ስለምትቆሙ ብርታት ሆናችሁኗል
https://www.gofundme.com/.../help-pastor-bezuayehu-ayele...
1000270322259(ንግድ ባንክ)
ብዙአየሁ ታደለ
1000414574491(ብርሐን ባንክ)
ብዙአየሁ ታደለ
መስጠት ባትችሉ ሼር ማድረግ እርዳታ ነው ሼር!
Via Bethelehem Tessemma

የስግዴት አይነት ስንት አይነት ስግዴት አለ?1.የአምልኮት ስግዴት ለአምላክ ሁሌ የሚሰገድ በሚሰገድበት ጊዜ ከታች ንፁህ ቦታ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ መስቀል ወይም የቅዱሳት መጻሕፍት መቀመጥ አለበ...
14/03/2022

የስግዴት አይነት
ስንት አይነት ስግዴት አለ?
1.የአምልኮት ስግዴት ለአምላክ ሁሌ የሚሰገድ
በሚሰገድበት ጊዜ ከታች ንፁህ ቦታ ላይ መጽሐፍ ቅዱስ መስቀል ወይም የቅዱሳት መጻሕፍት መቀመጥ አለበት ሰጋጁ አይኑን ገልጦ ሲሆን የሚሰግዴው ግንባሩ መጽሐፍ ቅዱሱን መስቀሉን ወይም የቅዱሳን መጻሕፍትን ማስነካት አለበት።
ለአብ እሰግዳለሁ፣
ለወልድ እሰግዳለሁ፣
ለመንፈስ ቅዱስ እሰግዳለሁ፣
ምስጋና ይሁን ለአብ፣
ምስጋና ይሁን ለወልድ፣
ምስጋና ይሁን ለመንፈስ ቅዱስ፣
በረከቱን ለሰጠን፣
ሀይሉን ላበዛልን፣
በዚህ ሰዓት ላቆመን፣
በቸርነቱ መንገድ ለመራን፣
በዚህ ሰዓት በጸጋ ለጠበቀን፣
በብርሃኑ ሐይል ለመራኸን፣
ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል፣
ሃሌሉያ ለአብ፣
ሃሌሉያ ለወልድ፣
ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ፣
ቅዱስ እግዚአብሔር፣
ቅዱስ ሐያል፣
ቅዱስ ሕያው፣
ቅዱስ ኤልሻዳይ፣
ቅዱስ አዶናይ፣
ቅዱስ ያህዌ፣
ቅዱስ ፀባኦት፣
ቅዱስ ኢየሱስ፣
ቅዱስ ክርስቶስ፣
ቅዱስ አማኑኤል፣
የድንግል ማርያም ልጅ፣
2. የፀጋ ስግዴት
ቅዱስ ገብርኤል ፀጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እንዳለት እኛም እንዲሁ እያልን ለእመቤታችን የፀጋ ስግዴት እንሰግዳለን።
ስንሰግድ ድንግል ማርያም ክብር ምስጋና ይገባሻል እያልን (21 ጊዜ) እንሰግዳለን።
3.የንስሐ ስግዴት
ኪሪያላይሶን ኢየሱስ፣
ኪሪያላይስን ክርስቶስ፣
ኪሪያላይስን አማኑኤል፣
ኪሪያላይስ ኤልሻዳይ፣
አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን፣
አቤቱ አምላክ ሆይ ማረን፣
አቤቱ መድኃኔአለም ሆይ ማረን፣
አቤቱ የድንግል ማርያም ልጅ ሆይ ማረን። እያልን እንሰግዳለን።
4.የክብር ስግዴት
ለቅዱሳን መላእክት ለቅዱሳን ጻድቃን ለሰማእታት የሚሰገዱ።
ለምሳሌ 12 ጊዜ (6 ሰዓት) በቅዱስ ሚካኣል እሰግዳለሁ እና ለቅዱስ ሚካኤል እሰግዳለሁ እንዲሁም በወርኃዊ በአል ጊዜ ኦ፡ ቅዱስ ገብርኤል እያልን የአክብሮት ስግዴት እንሰግዳለን።
ክብረ በአል ከሆነ
ለምሳሌ በ12 የቅዱስ ሚካኤል ቀን፣ በ19 የቅዱስ ገብርኤል ቀን፣ በ21 የማርያም ቀን)
ስብአት ለአብ፣ ፣
ስብአት ለወልድ፣
ስብአት ለመንፈስ ቅዱስ፣
ቅዱስ እግዚአብሔር፣
ቅዱስ ሀያል፣
ቅዱስ ህያው፣
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ። እያልን እጣን እያጨስን እንሰግዳለን።
የጀመርነውን ፆም በሰላም ያስፈጽመን ዘንድ የድንግል ልጅ መድኃኔአለም ቅዱስ ፈቃድ ይሁን

https://www.youtube.com/watch?v=0sArlpAr_6c
14/03/2022

https://www.youtube.com/watch?v=0sArlpAr_6c

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

https://www.youtube.com/watch?v=Z8fhZXW61Zg
14/03/2022

https://www.youtube.com/watch?v=Z8fhZXW61Zg

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

https://www.youtube.com/watch?v=iU7N9Xc-25w
14/03/2022

https://www.youtube.com/watch?v=iU7N9Xc-25w

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

https://www.youtube.com/watch?v=JfX89iERkT8
14/03/2022

https://www.youtube.com/watch?v=JfX89iERkT8

ኖሎት ቱዩብ Nolot tube is achannel which provides News, Entertaining Videos, Documentary, Sport & many more.We’re here for one reason to provide fair and unbia...

ወንጪ ሃይቅ የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ ተመረጠ========== #==========ወንጪ ሃይቅ የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ በተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ድርጅት መመረጡ ...
16/11/2021

ወንጪ ሃይቅ የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ ተመረጠ
========== #==========

ወንጪ ሃይቅ የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ተብሎ በተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ድርጅት መመረጡ ተገለፀ፡፡

ድርጅቱ በቀጣዩ ወር በዲሴምበር 2፣2021 ስፔን ላይ በሚያካሄደው 24ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የውድድሩን አሸናፊ ይፋ እንደሚያደርግ ተነግሯል፡፡

በእሳተ ጎሞራ ከተፈጠሩ ሀይቆች መካከል የሆነው እና የሰከነው ወንጪ ሀይቅ በመንግስት የገበታ ለአገር ከሚለሙት ፕሮጀክቶች አንዱ ነው፡፡

ወንጪ ሀይቅ ለውድድር እንዲቀርብ ብርቱ ጥረት ያደረገው የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ሲሆን ባለፈው ዓመት የውድድሩን ማመልከቻ ማስገባቱን ሸገር ራድዎ ሰምቻለሁ ሲል ዘግቧል።

“የአፍሪካ ስዊዘርላንድ” በሚል ቅፅል ስሙ በጎብኚዎች ዘንድ የሚታወቀው ወንጪ ሀይቅ የተፈጥሮ ደን፣ ሞቃት ውሃ እና ፏፏቴ እንዲሁም የተፈጥሮ ጠበል እና ተወዳጅ የማር ምርት በውስጡ የያዘ ነው።

የአለም ምርጥ የቱሪዝም መንደር ውድድርን ማሸነፉ የተነገረለት ወንጪ ሃይቅ ከማን ጋር ተወዳደረ? ሽልማቱስ ምንድን ነው? የሚለውን እና ዝርዝር ሂደቱን በተመለከተ መንግስት ማብራሪያ ለመስጠት እየተዘጋጀበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡
addismaleda

በተመሳሳይ ጊዜ ተወልደዉ የአንድ እናት ጡት ጠብተዉ ያደጉ ጓደኛማቾች በ95 ዓመታቸዉ በሰዓታት ልዩነት ህልፈታቸዉ መሰማቱ አስገራሚ ሆኗልፍቅር እስከ መቃብር እንዲሉ አቶ ዳቲኮ መጋሮ እና የል...
14/11/2021

በተመሳሳይ ጊዜ ተወልደዉ የአንድ እናት ጡት ጠብተዉ ያደጉ ጓደኛማቾች በ95 ዓመታቸዉ በሰዓታት ልዩነት ህልፈታቸዉ መሰማቱ አስገራሚ ሆኗል

ፍቅር እስከ መቃብር እንዲሉ አቶ ዳቲኮ መጋሮ እና የልብ ጓደኛዉ አቶ ዘለቀ ሐስማ ህይወት ታሪክ እጅግ ይለያል ነዉ የተባለዉ፡፡

ሁለቱ የልብ ጓደኛማቾች በዲራሼ ልዩ ወረዳ ያይቤ ቀበሌ በ1919 ዓ.ም የተወለዱ ሲሆን፤ የአቶ ዘለቀ ሐስማ እናት ገና እንደወለዱ በሞት በመለየታቸዉ የአቶ ዳቲኮ መጋሮን እናት ጡት ተጋርተዉ ማደጋቸዉ ይነገርላቸዋል፡፡

ዕድሜያቸዉ ለሥራ ሲደርስ በዕለት ተዕለት ተግባራቸዉ ሳይለያዩ በአንድ ግቢ በአንድነት ለበርካታ ዓመታት ኖረዋል፡፡

ሁለቱ ጓደኛማቾች በአካባቢያቸዉ አለመግባባቶች ሲፈጠርም ችግሮችን በመፍታትና በማስታረቅ የሚታወቁ ናቸዉ ተብሏል፡፡

አቶ ዳቲኮ መጋሮ ጥቅምት 03/2014 ዓ.ም ምሽት አንድ ሰዓት ከዚህ በሞት ሲለዩ፤ አቶ ዘለቀ ሐስማ በሰዓታት ልዩነት ከለሊቱ 9 ሰዓት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ አስገራሚ ክስተት ሆኗል ነዉ የተባለዉ፡፡

12/11/2021

ኢትዮጵያ በ2022 ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ የ700 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት ትጀምራለች
በርካታ አፍሪካውያን እየተሳተፉበት የሚገኘው እንደጎርጎሳውያን አቆጣጠር የ2021 የአፍሪካውያን የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል በአውታረ ውሂብ እየተካሄደ ነው።
በፌስቲቫሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ መልዕክት አስተላልፈዋል።
እንደ ክብርት ሁሪያ ኢትዮጵያ አገር በቀል የኢኮኖሚ እድገት አቅጣጫን የተከተሉ የኢኮኖሚ ለውጦችን በዲጂታል ኢኮኖሚ ለማገዝ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ግንባታ ስርዓት ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚከወኑ ዘርፎች ይጠቀሳል።
ክብርት ሁሪያ አክለውም፥ ለዲጂታል ኢኮኖሚና የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓት ግንባታ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ወሳኝ መሆኑን መንግስታቸው ይረዳል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በ2022 (እ.ኤ.አ) ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ 700 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ማምረት ስለምትጀምር ለዘርፉ ማደግ እና የኢትዮጵያን ብልጽግና ለማብሰር ትልቅ እመርታ ያስገኛል ብለዋል።

12/11/2021

የቦይንግ ኩባንያ በኢትዮጵያ ለተከሰከሰው 737 ማክስ ጄት አውሮኘላን አደጋ ኃላፊነቱን ለመቀበል ተስማማ።
ቦይንግ እ.ኤ.አ. በ 2019 በኢትዮጵያ ለደረሰው 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ኃላፊነቱን ለመቀበል እና በአደጋው ከሞቱት 157 ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ቤተሰቦች ለተሳካላቸው የካሳ ጥያቄ ሀላፊነቱን ለመውሰድ ተስማምተዋል።
በፌዴራል ፍርድ ቤት በትላንትናው እለት በቀረበው ውል መሰረት ቦይንግ በአውሮፕላኑ ላይ እስካለፈው አመት ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲታገድ ባደረገው አደጋ ተጠያቂነቱን ይቀበላል እና ለወደፊቱ ለተጎጂ ቤተሰቦች ለሚደርሰው የካሳ ክፍያ ብቸኛ ሀላፊነቱን ይወስዳል። የጉዳት ሰለባ ቤተሰቦች ከቦይንግ የቅጣት ካሳ ላለመጠየቅ ተስማምተዋል ተብሏል።
ቦይንግ ዋና መሥሪያ ቤቱ ባለበት ኢሊኖይ ውስጥ ለደረሰው ጉዳት ለማካካሻ ጉዳት ቤተሰቦች ክስ ካቀረቡ ጉዳዮቹን ወደ ሌላ ቦታ ለመውሰድ እንዳይሞክር ተስማምቷል ፣ ይህም በግዛቱ ውስጥ ላሉት ቤተሰቦች ድል ነው ሲል ኒዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

12/11/2021

የግል መገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊሰሩ እንደሚገባ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አሳሰበ።
ለንግድ አገልግሎት የተቋቋሙ አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት አገሪቷ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ሳያገናዝቡ እየሰሩ መሆኑን ባለስልጣኑ ጠቅሷል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ብዙዎቹ የግል መገናኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ተገንዝበው ለዚህም የሚመጥን ሥራ እየሰሩ አይደለም፡፡
መገናኛ ብዙኃኑ ከዚህ በፊት ከተለመደው አሰራር እና የአዘጋገብ ስልት ወጥተው ኢትዮጵያና ዜጎቿን ከገጠሙት ወቅታዊ ችግሮች ሊያሻግሩ በሚችሉ ዘገባዎች ላይ ሊያተኩሩ ይገባል ብለዋል።
ኢዜአ

በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።የሲዳማ ክልል ፖ...
31/08/2021

በሃዋሳ ከተማ አስተዳደር ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር በማተም በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበራ አሬራ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ረፋድ ላይ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተካሄደ አሰሳ በሃዋሳ ከተማ በጥቁር ገበያ ለማዘዋወር ታቅዶ የነበረና የህትመት ሂደቱ ያላለቀ ከ186 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካ ዶላር መገኘቱን አስታውቀዋል።
በዚህ የወንጀል ድርጊት የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸውን ለማጣራት ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና 12 ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበው የአትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።ሻምፒዮናው ...
24/08/2021

በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው በዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና 12 ሜዳሊያዎችን ያስመዘገበው የአትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።
ሻምፒዮናው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን 3 ወርቅ፣ 7 የብር እና 2 የነሃስ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ከዓለም 4ኛ ሆኖ ጨርሷል።

ተዋቂው ሙነሽድ የመሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ኮልፌ የሙስልሞች መቃብር ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተከናውኗል፡፡በ1958 ዓ.ም በደሴ የተወለደው መሀመድ አወል በዛው በሚገኙ መድረሳ...
24/08/2021

ተዋቂው ሙነሽድ የመሀመድ አወል ሳላህ የቀብር ሥነ-ስርዓት ኮልፌ የሙስልሞች መቃብር ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት ተከናውኗል፡፡
በ1958 ዓ.ም በደሴ የተወለደው መሀመድ አወል በዛው በሚገኙ መድረሳዎች መንፈሳዊ ትምህርቱን የተከታተለ ሲሆን ወደ ብሔራዊ ውትድርና ተቀላቅሎ ሀገሩን ማገልገሉን የህይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

ከሲዳማ  ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገኙት የሲዳማ አባቶችም የመከላከያ ሠራዊትን የመደገፍና ህወሃትን በሚቃወመው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ስለ ኢትዮጵያ ሀያልነትና ስለ ህዝቡ ጀግንነት በ...
20/08/2021

ከሲዳማ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የተገኙት የሲዳማ አባቶችም የመከላከያ ሠራዊትን የመደገፍና ህወሃትን በሚቃወመው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ስለ ኢትዮጵያ ሀያልነትና ስለ ህዝቡ ጀግንነት በቄጠላ ስነ ስርዓት ላይ በዜማ በማጀብ ድጋፋቸውን ገለፁ

የኔ እናት ዘንዬ ቸሩ መድሀኒአለም በምህረት እጆቹ ይዳስሽ🙏🏽በቻልነው ተባብረን እንድረስላት🙏🏽🙏🏽ዘነቡ ገሠሠ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር100000578147809 11 85 99...
02/08/2021

የኔ እናት ዘንዬ ቸሩ መድሀኒአለም በምህረት እጆቹ ይዳስሽ🙏🏽
በቻልነው ተባብረን እንድረስላት🙏🏽🙏🏽
ዘነቡ ገሠሠ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
1000005781478
09 11 85 99 91
by Addisalem Getaneh የጌታነህ ልጅ

11/03/2021

Visit the post for more.

 #ሀገር-በፍቅር-መተሳሰር-ነው።   ዶ/ር ምህረት ደበበዶ/ር ምህረት ደበበ የጋሞ አባቶች የኢትዮጲያ አባቶች ናቸው። መስከረም 14/2013 ዓ.ም ዶርዜ በመገኘት ዮ....ዮ ማስቃላ የእርድ ስ...
26/09/2020

#ሀገር-በፍቅር-መተሳሰር-ነው።
ዶ/ር ምህረት ደበበ

ዶ/ር ምህረት ደበበ የጋሞ አባቶች የኢትዮጲያ አባቶች ናቸው። መስከረም 14/2013 ዓ.ም ዶርዜ በመገኘት ዮ....ዮ ማስቃላ የእርድ ስነ-ስነስርዓት በተካፈሉበት ወቅት "ሀገር ምንድነው "? ለሚለው ጥያቄ በጋሞ ህዝቦች ዘንድ ትልቅ ቦታ ባላቸው በተለያዩ እሴቶች መልስ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ምህረት ሀገር ማለት"ጥጥ" ነው። ጥጥ ጥሩ ፈታይ ካላገኘ ሊበጠስ ይችላል፤ ጥሩ ፈታይ ካገኘ ግን ሊበጠስ አይችልም ፤ ይጠነክራል ሲሉ ሀገርን በጥጥ መስለዋል። በሌላ መልኩ ሀገር "ቀርከሃ" ነው። ቀርከሃ ለቤት ሰሪ እርስ በርሱን በማጠላለፍ ቤት ይሰራበታል፤ ነገር ግን ለማንደድ ከተፈለገም በቀላሉ ይጋያል። ሀገር"እንሰት "ነው። እንሰት ምግብ ነው እንሰት መሠሰሪያ፣ እንሰት መግመጃ ነው። ሀገር በፍቅር መተሳሰር ነው፤ ጋሞ የኢትዮጵያ ማሰሪያ ነው።

ከ ዶ/ር ምህረት በፊት መልዕክት የማስተላለፍ ዕድል ያገኘው የሰባዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆን የጋሞ ምድሩ ብቻ ሳይሆን የሰውም ልቡ ለምለም ነው፤ በሐይቆቹ መሀል ያለው ተራራ የእግዜር ድልድልይ ትላላችሁ ፤ እናንተ(ጋሞ) ለኢትዮጵያ የእርቅና የይቅርታ ድልድይ ናችሁ። ኢትዮጵያ መሪ ትፈልጋለች፣ ሽማግሌ ትፈልጋለች ይኼ በጋሞ ይገኛል። ሰው ማለት ገብቷችዋል መጀመሪያ ሰው ተፈጠረ እንጂ ብሔር አልተፈጠረም! በማለት ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኝተው ምርቃት ያቀረቡና እንግዶችን የተቀበሉ የጋሞ አባቶች ፍላጎታችን ጠንካራ መንግስትና ሰላም ነው በማለት ለሀገር ሰላምን ቀመመኘት መንግስት ጠንካራ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።
ጋሞ-ኢትዮጵያ 💚💛❤

የሐረማያ ሃይቅ ውሃ መያዙን ተከትሎ ዘላቂ እንዲሆን የማፅዳት ስራ ተከናወነሐረማያ ሃይቅ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ደርቆ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡የካቲት 1996  ሙሉ ለሙሉ የደረቀው  ሐ...
13/09/2020

የሐረማያ ሃይቅ ውሃ መያዙን ተከትሎ ዘላቂ እንዲሆን የማፅዳት ስራ ተከናወነ

ሐረማያ ሃይቅ ከአስራ አምስት ዓመታት በላይ ደርቆ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

የካቲት 1996 ሙሉ ለሙሉ የደረቀው ሐይቁ በዚህ ክረምት በጣለው ዝናብ ከፍተኛ መጠን ያለው ውሃ በመያዙ የመመለስ ተስፋ ማሳየቱ ተነግሯል፡፡

ይህን ሐይቅ በዘላቂነት ጠብቆ ለማቆየት ይቻል ዘንድ የሐረማያ ከተማ ነዋሪዎች የተሳተፉበት በሃይቁ ዳርቻና ወደ ሃይቁ ውሃ የሚያስገቡ ተፋሰሶችን የፅዳት ዘመቻ አድርገዋል።

በፅዳት ዘመቻው ያገለገሉ ፕላስቲክ የውሃ ኮዳዎች ተወግደዋል ተፋሰሱንም የማፅዳት ስራ ተከናውኗል።

በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉት የሐረማያ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙለታ ቡሽራ ለረዥም ዓመታት ደርቆ የነበረው የሐረማያ ሃይቅ ዳግመኛ የመመለስ አዝማሚያ በማሳየቱ ዘላቂ እንዲሆን የፅዳት ዘመቻው ወሳኝነት እንዳለው ተናግረዋል፡፡

ሐይቁን ጠብቆ ለማቆየት የተለያዩ ፕላስቲኮችን መወገዳቸው ለሐይቁ ህልውና ወሳኝነት አለው ብለዋል።

የሐረማያ ሃይቅን በዘላቂነት ለማስጠበቅ በሚያስችለው የፅዳት ዘመቻ ላይ የሐረማያ ከተማ ነዋሪዎችና የሐረማያ ሆስፒታል ሰራተኞች ተሳትፈዋል።

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኖሎት ቲዩብ nolot tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share