News amharic

News amharic Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from News amharic, Media/News Company, .

15/04/2022
23/03/2022

በጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የፌስ ቡክ ገፅ “ማንን ምን እንጠይቅልዎ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ለከተማዋ ዕድገት ተቆርቋሪ ከሆኑ ግለሰቦች በኦላይን ላይ ነፃ የህዝብ አስተያየትና ጥያቄዎችን አሰባስባናል፡፡

ነፃ የህዝብ አስተያየትና ጥያቄ አቅራቢዎች የመንግስት ተቋማት ሊያሻሻሏቸው ይገባቸዋል ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች በግልፅ አቅርበዋል፡፡

ስለዚህ በገፁ “ማንን ምን እንጠይቅልዎ” የነፃ አስተያየት መስጫ ላይ ለቀረቡ ጥያቄዎች የመንግስት ተቋማት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጡ እናደርጋለን።

በ“ማንን ምን እንጠይቅልዎ”በሚል ጭብጥ ለከተማዋ ዕድገት ተቆርቋሪ የሆኑ ግለሰቦች የመንግስት ተቋማት ሊያሻሻሏቸው ይገባቸዋል ያሏቸውን አስተያየቶችና ጥያቄዎች በግልፅ ጠይቀዋል።
በዚህ ነፃ ሀሳብ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ
 ጎንደር ከተማ ላይ በመንግስት ካፒታል ወጪ በቅርቡ የተሰሩ መሠረተ ልማቶች አሉ ወይ? ካሉ የተገነቡ የመሰረተ ልማቶችን ዘርዝረው ቢያስረዱን ወይም ቢያሳዩን?
 ሪክሬሽን ግቢ ውስጥ የተጀመረው የወጣቶች መዝናኛ ግንባታ ፕሮጀክት ግንባታው ለምን አቆመ?
 በ2009 ዓ.ም በማህበር ተደራጅተን 105ሺህ ብር ቆጥበን ለ6 ዓመታት ከዛሬ ነገ እንመራለን እያልን በተስፋ እየኖርን ነው፡፡አሁን በቤት ኪራይ እየተሠቃየን እንኛለን ስለዚህ ለምን መፍትሔ አይሰጠነም?
 የመንገድ ዳር መብራቶች በሌቦች እየተሰረቁ ስለሆነ የአካባቢውን ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር በባለቤትነት እንዲጠብቃቸው ለምን አልተደረገም እንዲሁምየከተማዋን መንገዶች የውሃ ማፋሰሻ ተብለው የተሰሩ ኮንክሪቶች እየፈረሱ ብረት ሲሰረቅ በዝምታ ይታለፋል? ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው ?
 የእግረኛ መንገዶች በተለይ ለአካል ጉዳተኞች አስቸግረዋል ለምን አይጠገኑም ?
 አዘዞ ተክለሀይማኖት አካባቢ ከማደያው ወደ ኤርፓርት የሚወስደው ቀጥ ያለ መንገድ ላይ ድሬኔጅ ለመስራት ተብሎ የምንወጣ የምንገባበት መንገድ ከተቆፈረ ድፍን አምስት ወር ሞላው ብዙ ሽማግሌዎች ለማለፍ ሲሞክሩ ተስብረዋል ፣ ህጻናት ወድቀዋል ። ይሰራል በሚል ተስፋ ብንቆይም መልስ የሚስጥ የለም። ለምን ?
 ጎንደር ከተማ ከቀበሌ 01 እስከ ቀበሌ 20 ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአስር አመት በላይ ተጀምረው የቀሩ ህንፃዎች አሉ፡፡ የህንፃዎች አለመጠናቀቅ የአካባቢ ውበት ከመቀነስ ባሻገር ህፃዎችና ሆቴሎች ሲጠናቀቁ ለስራ እድል ይፈጥሩም ነበር:: ይህም አልሆነም ግብርም ለመንግስት ያስገቡ ነበር ሆኖም ይህ ሁሉ ሊሆን አልቻለም፡፡ምክንያቱ ምንድን ነው ? ብዙ ህንፃዎች ቁመው የቀሩት ወይ ባለቤቱ ሙቶ ወይ ብድር አጥቶ ወይ ብድር በዝቶበት ወይ የግንባታ ማቴሪያል አጥቶ ሊሆን ይችላል። እየሰራ እንዲከፍል የባንክ ብድር ማመቻቸት የበዛ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ካለ መቀነስ ያስፈልጋል።
 የከተማዋ የውስጥ ለውስጥ መንገድ መሻሻል ፡፡ከንቲባውን ጨምሮ የከተማው አመራሮች ለምን በየጊዜው የመስክ ጉብኝት አታደርጉም ቢሮ ቁጭ ማለት ምን ያደርጋል ለናንተም ለጤናችህ ጥሩ ነው የማትቀሳቀሱ በየጎሬው እየገባችህ በአካል ችግር የማታዩ?
 ከፍተኛ የመልካም አስዳደር ችግር በየክፍለ ከተሞች ይታያል በተለይ ደግሞ መሬት ነክ ጉዳዮች ያለ ክፍያ ማስተናገድ ቀርቷል ትልቅ ሰንሰለት አለው ሰንሰለቱን ለምን መበጠስ አልተቻለም ?
 ለአባውራ 500 ካሬ ሜትር ለልጆች 250 ካሬ መሬት ለተነሽ አርሶ አደሮች የተነሽ ትክ ከአሁን በፊት ሲሰጥ ነበር አሁን ግን አይሰጥም ተብሏል ለምን?
 ኮብል ስቶን መንገድ ተገንብቶ ለምን መፋሰሻ አይገነባለትም?
 የተጀመሩ ድልድዮች ለምን አይጠናቀቁም?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሰላምና ህዝብ ደህንነት መምሪያ
 የዜጎች በሰላምና በህይዎት የመኖር መብታቸው እየተጠበቀ አይደለም ስለዚህ አስፈፃሚው አካል ተቀዳሚ ተግባሩ ተደረጎ ለምን አይሰራም እንዲሁምይሄን የማይሰራ ካብኔ ካለ ለምን ከሃላፊነቱ እንዲነሳ አታደርጉም ?
 ለሰዎች ደህንነት ሲባል የጥይት ተኩስ በከተማ መሳሪያ ይዞ መዞር በተለይ ገንፎ ቁጭ አካባቢ መንግስት ያለ አይመስልም፡፡ስለዚህ ለከተማዋ ሰላም ሲባል ለምን በትኩረት አይሰራም?
 መሳሪያ ይዘው ግሮሰሪ ለግሮሰሪ የሚዞሩ ሰላማችንን እያወኩት ነውስለዚህ በወጣው መመሪያ መሰረት ተግባራዊ ለምን አይደረግም?
 የመንገድ ዳር መብራቶች ሲሰረቆ የአካባቢው ጥቆማ እንዲሰጣቹህ አድርጋቹህ በወንጀለኞች ላይ እርምጃ ለምን አይወሰድም ?
 የማልጠይቀውን ጠይቁኝ መቼ ነው ሙተን ከመገኘት የምንገላገለው እፎይ ብለን ከስጋት ነጻ የሆነ ኑሮ የምንኖረው መቼ ነው የውስጥ ባንዳወችን እጅና ጓንት ሁነን መንጥረን አጋልጠን የምንገላገላቸው መቼ ነው ጎበዝ ሰላም እድገት እንደናፈቀን የበይ ተመልካች ሁነን እስከመቼ ?
 ህገ ወጦች ታጥቀው የመንግስት መሬት ከመንጠቅ አልፈው በኢንቨስትመንት በተሰማሩት ባለሀብቶችን እያጠቁ መሆኑን በአካል ተመልክቻለሁ። በዚህ ሁኔታ ከአምስት በላይ ኢንቨስተሮች ያላቸውን ቅሬታ ከነመረጃና ማስረጃው ተመልክቻለሁ። ጉዳዩ ከቀበሌ እስከ ከከፍለ ከተማ አልፎ እስከ ከፍተኛ የከተማው ኃላፊዎች እየታወቀ ግን መፍትሔው የታጣለት ጉዳይ ሆኗል ለምን ? ባለ ሀብቶች በኢንቨስትመንት በተሰጣቸው ቦታ የሚፈፀም ወረራ ኢንቨስትመንቱን አይጎዳውም ወይ? ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ ብሎም ወደ ክልሉ ለስራ ለመስራት እንዳይመጡ እየከለከለ ነው፡፡ለዚህ ችግር መፍትሔ አይሰጥም ወይ?
 በፖሊስ ጣቢያ ሰው በጣም የማጉላላት ባህሪ አለ ጉዳዩን በፍጥነት መጨረስ ያልተቻለው ለምንድን ነው? ለምንስ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን አትፈትሹም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኢንቨስትመንት
 በከተማችን ቀደም ሲል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ ፋብሪካዎች አሁን ግን በተለያየ ምክኒያት አገልግሎት የማይሰጡ የጥጥና የዘይት ፋብሪካ ችግራቸው ምንድን ነው?
 1ኛ ጎንደር ከተማ ያለዉ ታሪካዊዉ ደስ የጥጥ መዳመጫ ደረጃዉን አሳድጎ ዘመናዊ የጨርቃ ጨርቅ ማምረቻ ማድረግ ለምን አልተቻልም? በመተማ በአርማጭሆ፣ በቋራ፣ በጠገዴ፣ በወልቃይት የሚገኙ አራሾች የሚያመርቱትን ጥጥ ወደ ጨርቃጨርቅ መቀየር እየተቻለ አዲሱ የጎንደር ጋርመንት በሚያሳዝን ሁኔታ ከአልመዳ ጨርቅ ገዝቶ ሰፍቶ ይሸጣል፣ የእኛ አርሶ አደር ያመረተዉ ጥጥ ገዢ ያጣ በማስመሰል ወያኔ በርካሽ እየወሰደ እዛ ይጠቀምበት ነበር። እሄን በምን መልኩ ለማስተካከል አስባችኋል?
 2ኛ ጎንደር እና አካባቢዉ ከፍተኛ የሆነ የቅባት እህል የሚመረትበት አካባቢ ነዉ የአካባቢዉ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች በየአመቱ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የቅባት እህል ያመርታሉ። በአካባቢዉ የሚረከባቸዉ ስለሚያጡ ዋጋው ከፍና ዝቅ እያለ ይቸገራሉ። ሲፈልጉ ኤክስፖርት ሲፈልጉ ለፋብሪካ እያቀረቡ መሸጥ እንዳይችሉ ሆነዋል።ከዚህ በመነሳት በጥንቱ ጊዜ የተቋቋመው የጥንቱ ዘይት ፋብሪካ ከንቲባ በተቀያየረ ቁጥር ጉዳዩ እየተንከባለለ ዛሬም ድረስ መፍትሄ አጥቶ ይገኛልእሄን በምን መልኩ ለማስተካከል አስባችኋል? ከዚህ በተጨማሪ የዘይት ፋብሪካ አንድ የጥጥ ፋብሪካ በአክሲዮን እንዲቋቋም ማድረግ ለምን አቃታችሁ? ሀብቱ እያለን ጅማሮዉና ልምዱ እያለን ለምን ተኛችሁ? እነዚህ ሁለት ፋብሪካዎች ሲቋቋሙ አምራቹ ምርቶቹን ለፋብሪካዎች ስለሚሸጥ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡ ከተማችን ዉስጥ የሚገኙ ወጣቶች ስራ ያገኛሉ፡፡ ህዝባችን ምርት ያገኛል፡፡ እሄ ሲሆን ለሰላም የሚኖረው አስተዋጾ በጣም ብዙ ነው ስለዚህ ትኩረት ቢሰጠው፡፡
 ህገ ወጦች ታጥቀው የመንግስት መሬት ከመንጠቅ አልፈው በኢንቨስትመንት በተሰማሩት ባለሀብቶችን እያጠቁ ነው፡፡በዚህ ሁኔታ ከአምስት በላይ ኢንቨስተሮች ያላቸውን ቅሬታ ከነመረጃ ማስረጃው ተመልክቻለሁ።ጉዳዩ ከቀበሌ ፣ከከፍለ ከተማ አልፎ እስከ ከፍተኛ የከተማው ኃላፊዎች የታወቀ ግን መፍትሔው የታጣለት ጉዳይ ሆኗል ለምን ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ህብረት ስራ ማህበራት
 እኛ በ2009 ዓ.ም በማህበር ተደራጅተን 105 ሺ ብር ቆጥበን ለ6 ዓመታት ከዛሬ ነገ እንመራለን እያልን በተስፍ እየኖርን እና በቤት ኪራይ እየተሠቃየን እንገኛለን
የህብረተሰባችን የቤት ችግር እንዳለበት እየታወቀ ለቤት ማህበራት የቤት መስሪያ ቦታም ይሁን የማህበራት የአፖርታማ ቦታ የማይሰጥበት ምክንያት ምንድን ነው?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

መንገዶች ባለስልጣን
 የአዘዞ አሰፓልት መንገድ ግንባታ ዘግይቷል፡፡ለምን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ችግሩ ለምን አይፈታም?
 የጎንደር መንገድ ገበጣ ሁኗል እሰኪ ዞር ዞር ብላቹህ ለማየት ሞክሩ ጥገናስ የማይደረግበት ምክንያት ምንድን ነዉ ?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የጎንደር ከተማ ቤቶች ልማት ጽ/ቤት
 የቀበሌ ቤቶች በአመራርና በባለ ሀብት ተይዟል፡፡ድሃው ህብረተሰብ ግን ተጠቃሚ መሆን አልቻለም ለምን?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ትምህርት መምሪያ
 የ12ኛ ክፍል ውጤት በተለይ የአማራን ህዝብ ያልተማረ ለማድረግ የታሰበ ሰለሆነ ትምህርት ሚኒስትር መጠየቅ አለበት፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

የገቢዎች መምሪያ
 የንግዱን ማህበረሰብ ተረጋግቶ እንዳይሰራ ያደረገውን ምክኒያት የገቢዎች መዋቅር ጉዳይ ለምን ችግሩ አይፈተሸም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ንግድና ገቢያ ልማት መምሪያ
 .የኑሮውድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል፡፡እየተወሰደ ያለው እርምጃ ለውጥ አላመጣም፡፡ለምን ለውጥ የሚየመጣ ስራ መስራት አልተቻለም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

መሬት ማኔጅመንት
 በጎንደር ከተማ እና ዙሪያ የህገ ወጥ መሬት ወረራ መርን ለቆል ስለዚህ ለምን መፍትሔ አይፈለግም?
 ከፍተኛ የመልካም አስዳደር ችግር በየክፍለ ከተሞች ይታያል፡፡ በተለይ ደግሞ መሬት ነክ ጉዳዮች ያለክፍያ ማስተናገድ ቀርቷል ትልቅ ሰንሰለት አለው ቢበጠስ መልካም ነው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ትራንስፖርት መምሪያ
 የትራንስፖርት ታሪፍ ወጥቶ ቁጥጥር የማይደረገው ለምንድነው?
 በአንድ ታክሲ 24 ሰው መጫን ይታያል፡፡ይህ ለምን ቁጥጥር አይደረግበትም?

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሰቪል ሰርቪስና የሰው ሀይል መምሪያ
 ከላይ እስከ ታችኛው ያለው የመንግስት መዋቅር በአግባቡ ህዝብ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም፡፡ስለዚህ ይታሰብበት፡፡
 የመንግስት ሰራተኞች የስዓት አጠቃቀም ችግር አለ፡፡ይህን ለምን ማስተካከል አልተቻለም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ደንብ ማስከበር
 በህዝብ ሀብት የተሰሩ አስፓልቶች የመኪና ማጠቢያና ጋራጅ ሆነዋል፡፡ ለእግረኛ የተሰሩት መንገዶች ለነጋዴወች ዕቃ መሸጫ ሆነዋል፡፡ሰራተኞች ህዝብን ለማገልገል ያላቸው ዝግጁነት አናሳ ነው፡፡ለምን ማስተካከል አልተቻለም?
 የጫኝና አውራጅ ያላግባብ ክፍያ መጨመር ይታያል፡፡ይህ ለምን አይስተካከልም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ኮሙኒኬሽን ጉደዮች ጽ/ቤት
 ጎንደር የብዙ የታሪክና የንግድ ማዕከል የነበረችው እያየናት የህገ-ወጦች መፈንጫ የጉልበተኞች ከተማ ሆናለች፡፡የኮምኒኬሽን ስራ ከሁሉም ስልጣን በላይ አቅም አለው ስልጣናችሁን ተጠቅማችሁ የከተማዋን ችግር እንዲፈታ ለምን አታደርጉም?
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
አጠቃላይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለከንቲባ ኮሚቴ
 ከተማችን ጎንደር ሰላሟ እንዲከበር፣ ባህሏና ታሪኳ እንዲጠበቅና እንዲዘከር ከማድረግ ባሻገር ሌሎች የልማት ስራዎች ለምን አይሰሩም?
 የተጀመሩ መሰረተ ልማቶችን በወቅቱ ከመጨረሰ አኳያ ፣የሰዎች ከደህንነትና ሰላምን ከመጠበቅ አንፃር ምን እየተሰራ ነው?
 በከተማዋ የተለያዩ ፋብሪካዎችን እንዳይኖሩ የተደረገበት ምክንያት ምንድን ነው?
 መገጭ ፕሮጀክት ስንት ገንዘብ ፈሶበት ስራው ለምን ዘገዬ?
 አጠቃላይ የአማራ ህዝብ ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ምን ማድረግ አለብን?
 በከተማዋ የመልካም አስተዳደር ችግር የወንጀል መበራከት የውስጥ ባንዳዎችን እጅና ጓንት ሁነን መንጥረን አጋልጠን የምንገላገላቸው መቼ ነው ?
 ጎንደር ከተማ ከቀበሌ 01 እስከ ቀበሌ 20 ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአስር አመት በላይ ተጀምረው የቀሩ ህንፃዎች አሉ፡፡የህንፃዎች አለመጠናቀቅ የአኣባቢ ውበት ማምጣት አልተቻለም ህፃዎች ሆቴሎች ሲጠናቀቁ ለስራ እድል ይፈጥሩም ነበር ይህም አልሆነም ግብርም ለመንግስት ያስገቡ ነበር ሁኖም ይህ ሁሉ ሊሆን አልተቻለም ለምን?
 ከንቲባውን ጨምሮ የዞን አመራሮች ለምን በየጊዜው የመሰረተ ልማትና ሌሎች የልማት ስራዎች የመስክ ጉብኝት አይደረግም፡፡
 በአገር አቀፊ ደረጃ ከመንግስት በጀት ውጭ በሆነ ገንዘብ ከባለ ሀብት ከህዝብ ከበጎ ፊቃደኞች ገንዘብ እየተሰበሰበ ቢሮዎች በሚያምሩ ደረጃ እየታደሱ ነው ስለዚህ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ፅ/ቤት በጣም የሚያሳፊር ነው ህንፃው ጥሩ እያለ ረጅም ጊዜ ስላገለገለ እንዲታደስ ማድረግ ያስፈልጋል ምን አስባችኃል?
 የህብረተሰባችን የቤት ችግር እንዳለበት እየታወቀ ለቤት ማህበራት ቦታም ይሁን የማህበራት የአፖርታማ ቦታ እማይሰጥበት ምክንያት ምንድን ነው፣
 በጎንደር ከተማና ዙሪያ የህገ ወጥ መሬት ወረራ አደጋ መረን ለቆ ተመልክቻለሁና ለምን መፍትሔ አይፈለግም ።
 ህገ ወጦች ታጥቀው የመንግስት መሬት ከመንጠቅ አልፈው በኢንቨስትመንት በተሰማሩት ባለሀብቶችን እያጠቁ ለመሆኑን በአካል ተመልክቻለሁ። በዚህ ሁኔታ ከአምስት በላይ ኢንቨስተሮች ያላቸውን ቅሬታ ከነመረጃ ማስረጃው ተመልክቻለሁ። ጉዳዩ ከቀበሌ ፣ከከፍለ ከተማ አልፎ እስከ ከፍተኛ የከተማው ኃላፊዎች የታዋቀ ግን መፍትሔው የታጣለት ጉዳይ ሆኗል ።ለምን መፍትሄ አይፈለግም
 ባለ ሀብቶች በኢንቨስትመንት በተሰጣቸው ቦታ የሚፈፀም ? ወረራ ኢንቨስትመንቱን አይጎዳውም ወይ ? ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ ብሎም ወደ ክልሉ ስራ ለመስራት እንዳይመጡ አያደርግም ወይ?
 የቀበሌ ቤቶች በአመራር እና በባለሀብት ተይዘዋል ድሆች አይስተናገዱም
 የክ/ከተማ አመራር ሹመት በሰንሰለት ነው (በዘመድ አዝማድ እና በአበልጅነት) ለምን አይስተካከልም?
 በከተማው የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች ክትትል አይደረግም
 የከተማው ውሀ አገልግሎት ፕሮግራም በማውጣት ቢያስተናግድ
 የትራንስፖርት ታሪፍ ወጥቶ ቁጥጥር የማይደረገው ለምንድነው?
 የመብራት ሃይል ክፍያ በጣም ከፍተኛ ስለሆነ ህዝቡን ለምሬት ዳርጎታል፡፡
 የአይራ ዞናል ሆስቲታል ለምን ወደ ስራ አይገባም?
 የተቋማቱና የፓለቲካ ድርጅቱ በእውቀት እና በችሎታ ከመመራት ይልቅ በሰፈር፣ በትወውቅ፣ በዝምድና በወንዜና መንደረኝነት መንፈሰ ከድሮወ ሰርዓት የተጋባበት በመሆኑ ለዘረፈ ብዙ የችግረ ምንጭ ነው::ይህን ችግር ለመፍታት ምን እየተሰራ ነው፡፡
 በጎንደረ ከተማ ገፅታ የሚያበላሹ ብዙ ተግባራት እየተፈፀሙ ይገኛሉ፡፡ መሬት ወረራ እና ዝርፋያ:መልካም አሰተዳደር ችግርች :የሃብት ብክነት:ወሃ እጥረት መሰል ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ለእነዚህ ችግሮች መፍትሔ መፈለግ ይኖርበታል፡፡
 ስለጎንደር ነዋሪዎች በእኩልነት የሚያገለግል ለሰላሟ የሚጨነቅየመንግስት ኃላፊ ካለ ስለ ጎንደር የሚመክር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጣ ለጥቅም ያልተቋቋመ ልክ እንደ ደባርቅ 7 ከዘራ ዓይነት ኮሚቴ ሊዋቀር ይገባዋል፡፡
 የዜጎች በሰላምና በህይዎት የመኖር መብታቸው የአስፈፃሚው አካል ተቀዳሚ ተግባሩ ነው ይሄን የማይፈፅም ተሿሚ ከሃላፊነቱ እስከማንሳት ሊደርስ የሚችል እርምጃ ሊወሰድ ይገባል፡፡ግን ይህ እየሆነ አይደለም፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

18/03/2022

የቀድሞዉ ህዳሴ ግድብ ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘዉ አባት አባ በቀለ አይናለም አረፉ።
======================

የአባ በቀለ የቅርብ ሰዉና አስታማሚ አቶ አስረሳ አባተ እንደገለፁት የአባ በቀለ የትዉልድ ቦታቸው በቀድሞዉ በወገራ አዉራጃ ዳባት የተወለዱ ሲሆን የአንድ ልጅ አባት ናቸዉ ፤እሱም ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ነበሩ።

አባ በቀለ አይናለም ለረጅም ጊዜ በቀድሞዉ በአዉራ ጎዳና መስሪያ ቤት ሲሰሩ ነበር።
አባ በቀለ በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ ሊሻላቸዉ ባለመቻሉ በዛሬው ዕለት በ96 ዓመታቸዉ አርፈዋል።

የአባ በቀለ አይናለም የቀብር ስነ ስርዓት በጎንደር ከተማ አስተዳደር በፋሲል ክፍለ ከተማ በሳይና ሳቢያ ቀበሌ በሸንበቂት ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ነገ መጋቢት 10/2014 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ስዓት በኦርቶዶክስ እምነት መሰረት ይፈፀማል ።

31/07/2021

ካሳ ሀይሉ ነበር
ያ የቋራ ጀግና
ቴዎድሮስ ተባለ
ጎንደር ተቀባና
ቴዲም የ ካሳሁን
ድምፀ መረዋዉ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ
ብሎ ያልሰለቸው
ጎንደር ጎንደር ብሎ
ካሳን ቢያወድሰዉ
ጎንደሬ ደግ ነዉ
ክብር አለበሰዉ
Via- @ EP

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when News amharic posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share