07/09/2022
አሁንም ድረስ ብዙ ሰው አልነቃም እየተበላ ነው
ከፌስ ቡክ መንደር ሲዘዋወር ነው ያገኘዉት እና ያላወቁት እንዲጠነቀቁ ነው በቻላችሁት መጠን ሼር አድርጉት
እባካችሁ በፍጥነት ሼር በማድረግ ማህበረሰባችንን ከዚህ ጥፋት እንታደግ! የጥንቃቄ መልእክት ለሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች በሙሉ!
አጭበርባሪዎች ሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ የሆኑ ግለሰቦችን ስልክ ቁጥር በተለያየ መንገድ ካገኙ በኋላ ፤ የባንክ ቁጠባ እድለኞች ሽልማት የደረሳቸው በማስመሰል ሜሴጅ ይልካሉ ፤
በተጨማሪም ወድያውኑ በስልካቸው ደውለው እርስዎ የወሩ የባንካችን እድለኛ ነዎት በመሆኑም በሽልማት የደረሰዎት 300,000 ሺ ብር በአካውንትዎ ገቢ እንዲሆንልዎ መጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚ ከሆኑ *889 # ብለው ያስገቡ በመቀጠል ስንደውልልዎ የራስዎን ሚስጥር ቁጥር (pin code) ያስገቡ በሚል አጭበርባሪወች እራሳቸው የባንክ ሰራተኛ መስለው ካልኩሌሽኑን በስልክ ይመራሉ ።
በመቀጠል በግለሰቦች አካውንት ያለውን ገንዘብ በሙሉ ወደ እራሳቸው አካውንት በማዞርና ወዲያውኑ ገቢ ያደረጉትን ገንዘብ በማውጣት እየተሰወሩ ከፍተኛ ዘረፋ እየፈፀሙ ስለሆነ ፤ ማንኛውም ሰው ባንክ እየገባ ትክክለኛነቱን ሳያረጋግጥ በስልክ ጥሪ ብቻ እየተታለለ ገንዘቡን እንዳይበላና ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ እናሳስባለን ።
✅✅✅ #ያወቁትን ማሳወቅ ብልህነት ነው!✅✅✅
በጎነት መልሶ ይከፍላል