New Ethiopia

New Ethiopia For new Ethiopian space innovation technology and Future health modern agriculture and so on.....no

ታይም መጽሔት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ካላቸው አንዱ ቅዱስ አስፋውበታይም መጽሔት ከዓመቱ የአየር ንብረት ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን 100 ሰዎች መካከል አንዱ በመሆን ተመርጧል፤ ቅ...
01/12/2023

ታይም መጽሔት የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ፈጣሪ ካላቸው አንዱ ቅዱስ አስፋው

በታይም መጽሔት ከዓመቱ የአየር ንብረት ተጽዕኖ ፈጣሪ የዓለማችን 100 ሰዎች መካከል አንዱ በመሆን ተመርጧል፤ ቅዱስ አስፋው።

የአካባቢ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆነው ኩቢክ መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆነው ቅዱስ ‘የአየር ንብረት መሪዎች’ ተብለው ዝርዝሩ ውስጥ ከተካተቱት የዓለም የቢዝነስ መሪዎች አንዱ ነው።

ቅዱስ ያቋቋመው ድርጅት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ዝቅተኛ የካርበን ሕንጻዎች በመቀየር ከአካባቢ ለማስወገድ የሚሠራ ነው።
https://bbc.in/3Rxhkxz

ወንጪ ሀይቅ ፕሮጀክት   | አሁናዊ ገጽታ - በፎቶ
30/11/2023

ወንጪ ሀይቅ ፕሮጀክት

| አሁናዊ ገጽታ - በፎቶ

30/11/2023

I am a child, not a bride!

In the drought-stricken Afar region of Ethiopia, UNICEF is conducting awareness-raising sessions to ensure that young girls can study and fulfill their potential. 🧕🎒📚

ኤችአይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ   | 24 ሺህ ተጠቃሚዎች የተካተቱበት ጥናት መድኃኒቱ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጧል።ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነ...
30/11/2023

ኤችአይቪን የሚከላከለው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ

| 24 ሺህ ተጠቃሚዎች የተካተቱበት ጥናት መድኃኒቱ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጧል።

ዌልስ ውስጥ በሙከራ ላይ የነበረውና በሰውነት ውስጥ የኤችኤይቪ ቫይረስ ሥርጭትን የሚገታው መድኃኒት ውጤታማ መሆኑ በጥናት ተረጋገጠ።

የመድኃኒቱ ውጤታማነት የተረጋገጠው በመላው እንግሊዝ ከተውጣጡ እና በጥናቱ በተካተቱ ከ24 ሺህ በላይ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ላይ ምርመራ ከተካሄደ በኋላ ነው።

በእንግሊዝ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፒአርኢፒ የተሰኘውን ይህን መድኃኒት ከሥነ ተዋልዶ ጤና ክሊኒኮች እየወሰዱ ይገኛሉ።

ከቼልሲ እና ዌስትሚኒስትር ሆስፒታል ጋር በመሆን የመድኃኒቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተደረገውን ሙከራ የመራው የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና ደኅንነት ኤጀንሲ፣ ጥናቱ በዓይነቱ ከዚህ ቀደም ከተሰሩ ጥናቶች ሰፊ መሆኑን ገልጿል።

ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ጥቅምት 2017 እስከ ሐምሌ 2020 ባሉት ጊዜያት እንግሊዝ ውስጥ በሚገኙ 157 የሥነ ተዋልዶ ጤና ተቋማት ላይ ተካሂዷል።

ይህ ጥናት ‘ፕሪ ኤክስፖዠር ፕሮፍላክሲስ (ፒአርኢፒ)’ የተባለው መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን መድኃኒቱ በኤችአይቪ የመያዝ ዕድልን በ86 በመቶ ይቀንሳል።

በክሊኒክ የተደረጉ ሙከራዎች እንዳመለከቱትም መድኃኒቱ 99 በመቶ ውጤታማ ነው።

የዩኬ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲ የመድኃኒቱ ውጤታማ መሆን የአገሪቷ መንግሥት በ2030 የኤችአይቪ ሥርጭትን ዜሮ ለማድረስ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳል ብሏል።

በጥናቱ ላይ የተሳተፉት የሥነ ተዋልዶ ጤና እና ኤችአይቪ አማካሪ ጆን ሳንደርስ እንዳሉት ሙከራው መድኃኒቱ ኤችአይቪን ለመከላከል ውጤታማ መሆኑን ይበልጥ ያሳየ ነው።

ይህም ቀደም ብለው ከተሠሩ ጥናቶች በበለጠ መድኃኒቱ በሽታውን የመከላከል አቅሙን ለመጀመሪያ ጊዜ አሳይቷል ብለዋል።

ትሬንስ ሂጊንስ ኤችአይቪ የተባለው ግብረሰናይ ድርጅትም ጥናቱ መውጣቱን በበጎ ተቀብሎ፤ ነገር ግን ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ስለመድኃኒቱ ግንዛቤ ለመስጠት ብዙ ሊሠራ እንደሚገባ ጠቁሟል።

የድርጅቱ የፖሊሲ ጉዳዮች ኃላፊ ደቢ ላይኮክ መድኃኒቱ በመድኃኒት ቤቶች እና በበይነ መረብ (ኦንላይን) ተደራሽ እንዲሆንም ጠይቀዋል።

ዶ/ር ሳንደርሰን እንዳሉት ምንም እንኳ ምርምሩ የመድኃኒቱን ውጤታማነት ከማረጋገጡ ባሻገር ጥናቱ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሚያስረዱ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ይፋ አድርጓል።

“መጀመሪያ ምን ያህል ሰዎች መድኃኒቱን እንደሚፈልጉ እንዲሁም ለምን ያህል ጊዜ መድኃኒቱን ሲወስዱ እንደቆዩ አናውቅም ነበር። አሁን ላይ ግን መድኃኒቱ ለማን መታዘዝ እንዳለበት ተረድተናል። በመሆኑም ብዙ ሰዎችን ለመድረስ ከክሊኒኮች ጋር መሥራት እንችላለን” ብለዋል ሳንደርሰን።

ፒአርኢፒ ቀደም ብሎ የነበሩትን ቴኖፎቪር ዲሶፕሮክሲል እና ኢምትሪሳይታቢን የተባሉ የኤችአይቪ መድኃኒቶችን የያዘ ሲሆን፣ የኤችአይቪ ቫይረስ ወደ ሰውነት እንዳይገባ እና በሰውነት ውስጥ ከገባም በኋላ ራሱን እንዳያባዛ ያደርጋል።

መድኃኒቱ በክኒን መልክ በቀን አንዴ መወሰድ አሊያም ከወሲብ ግንኙነት ቀደም ብሎ መወሰድ ይችላል።

ይህንን መድኃኒት እንደ አውሮፓውያኑ በ2020 በእንግሊዝ በስፋት እንዲሰራጭ የተደረገው ቀደም ብሎ በተሠሩ ጥናቶች ውጤት ላይ በመመሥረት ነበር።

አሁን ላይ የጥናቱ ውጤት በላንሴት ኤችአይቪ ላይ የታተመው ሰፋ ያለ ናሙና ስለተወሰደ እና ጥናቱን ሌሎች ተመራማሪዎች ሰፊ ጊዜ ሰጥተው ስለተመለከቱት ነው ተብሏል።(BBC)

16/12/2022
02/12/2022

Japan 🇯🇵❤️

02/12/2022

Vincent Aboubakar received a second yellow card for taking his shirt off whilst celebrating his 93rd minute goal against Brazil 💔

🇨🇲 Cameroon respect
02/12/2022

🇨🇲 Cameroon respect

06/11/2022

ከ 50 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ አሻራ ያሳረፈው የኦሮምኛ ሙዚቃ ተጫዋች

ክቡር ዶክተር አርቲሰት አሊ ቢራ ፤
ነፍስ ይማር 🙏

ለመላው ቤተሰቦቹ ፣አድናቂዎችና ወዳጆቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን !!

02/11/2022
እንኳን ደስ አለን!ስምምነቱ ተፈርሟል፤ ሰላም ወዳዶች ደስ ብሎናል። ተግባራዊነቱ ሳይዘገይ እንጠብቃለን። It is so!!!
02/11/2022

እንኳን ደስ አለን!
ስምምነቱ ተፈርሟል፤ ሰላም ወዳዶች ደስ ብሎናል። ተግባራዊነቱ ሳይዘገይ እንጠብቃለን። It is so!!!

The official kick-off of PanAfricon AI 2022   at the newly inaugurated Science Museum in     with a keynote speech by th...
04/10/2022

The official kick-off of PanAfricon AI 2022 at the newly inaugurated Science Museum in with a keynote speech by the guest of honor PM Abiy.

The newly inaugurated science museum in Addis Ababa, Ethiopia.
04/10/2022

The newly inaugurated science museum in Addis Ababa, Ethiopia.

በመዲናችን አዲስ አበባ ዛሬ በተመረቀው የሳይንስ መዚየም ዘመኑ የደረሰባቸውን ስማርት ሆም፣ ኤዱኬሽን፣ ትራፊክ፣ አግሪካልቸር፣ ፋክቶሪ፣ ቨርቹዋል ሪያሊቲ እና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች አው...
04/10/2022

በመዲናችን አዲስ አበባ ዛሬ በተመረቀው የሳይንስ መዚየም ዘመኑ የደረሰባቸውን ስማርት ሆም፣ ኤዱኬሽን፣ ትራፊክ፣ አግሪካልቸር፣ ፋክቶሪ፣ ቨርቹዋል ሪያሊቲ እና ሌሎችም የቴክኖሎጂ ትሩፋቶች አውደ-ርዕይ

04/10/2022
10,000 ሲኒ 35 ሜትር ጠረንጴዛ 100 ቡና አፍይዎች 100 ኪሎ ግራም ቡና
02/10/2022

10,000 ሲኒ
35 ሜትር ጠረንጴዛ
100 ቡና አፍይዎች
100 ኪሎ ግራም ቡና

27/08/2022

ሰርቢያኖች ሰለ ጦርነት አስከፊነት ሲገልጹ እንደዚህ ይላሉ...

ጦርነት ሲጀመር ፓለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ።ባለጠጎችም ምግብ ይሰጣሉ።ድሃዎች ግን ልጆቻችውን ይለግሳሉ።ጦርነቱም ሲያበቃ ፓለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ።ባለጸጎችም ከጦርነቱ በተረፈው ገንዘባቸዉ ሀብት ማካበታቸዉን ይቀጥላሉ።ድሆች ግን የልጆቻችውን መቃብር ስፍራ ሲፈልጉ ይኖራሉ።

ሰላም ለኢትዮጵያ

14/03/2022
ሰርቢያኖች ስለ ጦርነት ያላቸው ድንቅ አባባል~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ትንሽዬዋ የደቡብ ምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር የሆነችው ሰርብይ ስለ ጦርነት አስከፊነት ትልቅ የሆነ መልእክት ያለው...
01/03/2022

ሰርቢያኖች ስለ ጦርነት ያላቸው ድንቅ አባባል
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ትንሽዬዋ የደቡብ ምስራቅ አውሮፓዊቷ ሀገር የሆነችው ሰርብይ ስለ ጦርነት አስከፊነት ትልቅ የሆነ መልእክት ያለው አባባል አላቸው። እሱም ....

...

ፓለቲከኞች ጥይት ያቀብላሉ። ባለጽጎችም ምግብ ይሰጣሉ። ድሆች ግን ልጆቻችን ይለግሳሉ።

...

ፓለቲከኞች ቀሪ ጥይቱን ይሰበስባሉ። ባለጸጎችም ከጦርነቱ በተረፈው ሐብታቸው ማደግ ይጀምራሉ፤ ድሆች ግን ልጆቻቸውን በመቃብር ሥፍራ ይፈልጋሉ። //

ይህ ነው የጦርነት ዶሴው

ሠላም ለምድራችን !

Kune Demelash Kassaye

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when New Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to New Ethiopia:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share