Dessie.com

Dessie.com To encourage and prove democracy in our community.
ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ!

የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ መስራች ጉባኤው አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አካላትን በእጩነት አቅርቧል።እጪዎችንም ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አቅርበዋል።1ኛ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ...
30/09/2021

የአማራ ክልል ምክር ቤት በ6ኛ መስራች ጉባኤው አዲስ የሥራ አስፈጻሚ አካላትን በእጩነት አቅርቧል።
እጪዎችንም ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ አቅርበዋል።
1ኛ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀበር (እጩ ዶክተር)
2ኛ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ ሰማ ጥሩነህ (ዶክተር)
3ኛ በምክትል ርእሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስተባባሪ ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ
4ኛ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማኀበራዊ ጉዳዮች ክላስተር አስተባባሪ አቶ ስዩም መኮንን
5ኛ የክልሉ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ጥላሁን መሃሪ
6ኛ የሥራና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ አቶ አረጋ ከበደ
7ኛ የፍትሕ ቢሮ ኀላፊ አቶ ገረመው ገብረ ጻዲቅ
8ኛ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ወይዘሮ አስናቁ ድረስ
9ኛ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኀላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
10ኛ የውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው
11ኛ የጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ
12ኛ የማዕድን ቢሮ ኀላፊ አቶ ኀይሌ አበበ
13ኛ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ማተቤ ታፈረ
14ኛ የግብርና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ኀይለማርያም ክፊያለው
15ኛ የአስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ሜጀር ጀኔራል መሰለ በለጠ
16ኛ የንግድ ቢሮ ኀላፊ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ
17ኛ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኀላፊ ወይዘሮ ባንቸዓምላክ ገብረ ማርያም
18ኛ የመንገድ ቢሮ ኀላፊ አቶ መሃመድ ያሲን
19ኛ የወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኀላፊ አቶ አማኑኤል ፈረደ
20ኛ የገቢዎች ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ፀጋ ጥበቡ
21ኛ የመሬት ቢሮ ኀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ
22ኛ የቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ አቶ ጣሂር ሙሃመድ
23ኛ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኀላፊ አቶ ተስፋሁን አለምነህ
24ኛ የፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ አንሙት በለጠ
25ኛ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ቢያዝን እንኳሆነ
26ኛ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ
27ኛ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኀላፊ ዶክተር ኢንጂነር ዳኝነት ፈንታ
ከቀረቡት እጪዎች መካከልም 75 በመቶ የሚሆኑት አዲስ የሥራ ኀላፊዎች መሆናቸውን ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) ገልጸዋል።

የተከበሩ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንኳን ደስ አለዎ ‼በኢትዮጲያ ታሪክ የመዲናችን የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ መሆንዎ ሴቶች በሃላፊነት ቦታ ላይ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚ...
28/09/2021

የተከበሩ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እንኳን ደስ አለዎ ‼
በኢትዮጲያ ታሪክ የመዲናችን የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ መሆንዎ ሴቶች በሃላፊነት ቦታ ላይ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ነው ‼
መልካም የስራ ዘመን ይሁንልዎ ‼

መስከረም 16 ቀን 2014"የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው... "- የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ ።አሸባሪ...
26/09/2021

መስከረም 16 ቀን 2014
"የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው... "
- የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጄኔራል አበባው ታደሰ ።
አሸባሪዎቹ ህወሓቶች ከጦርነቱ በፊት ከጀርባ ይዘውት የነበረው ዓላማ የእነሱን ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ መጫን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ካለ አብሮ ለመስራትና የኢትዮጵያን ህዝብና መንግስት በጉልበት ጠምዝዘው የራሳቸውን ፍላጎት ማሟላት የሚል ነው፤ ይሄ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ዓላማቸው፤
ለዚህ ዓላማ መሳካት ደግሞ ወታደር ያስፈልገናል ብለው ልዩ ሀይልን እንደ ሽፋን ተጠቅመው ከ200 ሺህ በላይ ሰው ያለበት ሀይል አደራጅተው ነበር፤
የጀመረው ጦርነት ዓላማውም ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው፤ እኛ ደግሞ የተከተልነው ስትራቴጂ ኢትዮጵያን ከብተና የማዳን ነው፤ የጦርነቱ ፍትሀዊነት የሚመነጨውም ከዚህ ነው፤
የጦርነቱን ዋነኛ ማዕከል መቀሌን አድርገን በፍጥነት በመሄድ ከሁለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ መቀሌን መቆጣጠር አለብን ካልሆነ አደጋ ነው ብለን አንድ ሰው እንደ አስር እየተዋጋ በፍጥነት ጨርሰናል፤
በሰው ሀይል ማደራጀት እነሱ ይበልጡን ነበር፤ ነገር ግን የእነሱ ትልቁ ሀይል ዘር ሲሆን የእኛ ትልቁ ሞተራችን ኢትጵያዊነት ነው፤
የኢትዮጵያዊነቱ መንፈስ እንደገና ደግሞ ዩኒፎርም ለብሰህ ዩኒፎርም የለበሰ ጓደኛህ ከኋላህ ሲመታህ የሚፈጥረው መንፈስ አለ ። ያንን ጉልበት ይዘን ነው የተዋጋነው፤
ከሰራዊት አንጻር ያስቀመጥነውን ግብ አሳክተናል፤ የታገቱብንን አባሎቻችንን አስለቅቀናል፤ የተወሰዱብንን የጦር መሳሪያ እና ተተኳሽ አስመልሰናል፤ ኢትዮጵያን አድነናል፤
ህወሓትን እንደ ድርጅት በትነነዋል፤ የሚደመሰሰውን ደምስሰናል፤ ኢትዮጵያን ሊያፈርስ የነበረውን የድርጅቱን አስኳል በትነን ለሰባትና ስምንት ወራት ዋሻ ውስጥ ከተናል፤ የቀረውን ደምስሰናል፤
ኢትዮጵያን ሁሌም የሚወጋት የእኛ የራሳችን ሰው ከውጭ ሃይል ጋር በመሆን ነው፤
የውጭ ሃይል ቀጥታ አይመጣም፤ የውስጥ ሰውን እየያዘ ነው እየተዋጋን ያለው፤ ከውጭ የሚመጣው ጠላት በግልጽ ቢመጣማ ኖሮ ምንም ችግር አልነበረም፤
ኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሰው የፈለገውን አስተሳሰብ፣ የትኛውንም እምነት ይከተል፤ የትኛውንም ፖለቲካ ይከተል እኛ አያገባንም፤
ኢትዮጵያን ከነኩ ግን ከውጩ ሰው ሳይሆን የምንጀምረው ከራሱ ነው፤ የራሳችንን ቤት ቆሻሻ ካላጸዳን ኢትዮጵያን ማቆም አንችልም፤
በአሁኑ ወቅት መከላከያ በስፋት ነው እየተጠናከረ ያለው በትጥቅ፣ በአየር ሃይላችን፣ በእግረኛ ሃይላችን፣ ሊገመት በማይችል አይነት መልኩ ነው እየተዘጋጀን ያለነው፤
መከላከያን ማጠናከር ለማንኛው ኢትዮጵያዊ በሩ ክፍት ነው፤
ማንም ሰው መከላከያን መቀላቀል ይችላል፤ መደገፍ ይችላል፤ ማረም ይችላል ምክንያቱም የራሱ ሀብት ነው፤
የውስጥ እና የውጭ ስጋት አለብን፤ የውስጥ ስጋቱ ጊዜ የሚፈጅ አይደለም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚስተካከል ነው፤
ለውጩ ስጋት ጠንክረን መዘጋጀት አለብን፤ በዚህ ሁለት አመት መከላከያ ፍጹም ሙሉ ለሙሉ ይቀየራል፤
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ይሄ ጊዜ መለማመጃችን ይሆናል፤
እኛ የሚያስፈልገን ዘር አይደለም፤ ሰውነታችን ነው፤ ሰውነታችን ካለ አገር አለ!
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

መስከረም-14-2014የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከ12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ ።የሰዎች ለሰዎች ድርጅት 12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ከ14 አይነት በላይ ድጋፎች ማድረጉን የድርጅቱ ሀገ...
24/09/2021

መስከረም-14-2014
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ከ12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ አደረገ ።
የሰዎች ለሰዎች ድርጅት 12 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ከ14 አይነት በላይ ድጋፎች ማድረጉን የድርጅቱ ሀገር አቀፍ ተጠሪ ይልማ ታየ ገለጹ፡፡
ድጋፎቹ በወሎ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የተበረከቱ ሲሆን÷ አልባሳት የምግብ እህል ና የንጽህና መጠበቂያዎችን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡
አሁን የተደረገው በቂ አለመሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የሰዎች ለሰዎች ድርጅት የበጎ ፈቃድ አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ለወገን ደራሽ ወገን በመሆኑ ሁሉም ሊረባረብ ይገባል ብለዋል፡፡
እኛ እያለን ወገን አይራብም ያሉት ሻለቃ አትሌት ሀይሌ÷ አሁንም ድጋፎች ይቀጥላሉ ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰይፉ ሰይድ ለተደረገው ድጋፍ አመሰግንዋል።
Fbc

ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ያደረጉት ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ለደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ 7 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገቡ፡፡ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በደሴ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃ...
17/09/2021

ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ያደረጉት ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ለደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ 7 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገቡ፡፡
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በደሴ ከተማ የተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖችን ጎብኝተዋል። ለተፈናቃዮችም የ25 ሚሊዮን ብር የምግብና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በተጨማሪም የተፈናቀሉ ወገኖችን ወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ መልሶ ለማቋቋም 100 ሚሊዮን ብር መመደባቸውን እንደገለጹ ይታወቃል፡፡
ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ እየተሳተፈ ለሚገኘው የደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ 7 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
አሁን ደግሞ ለደሴ ከተማ እግር ኳስ ክለብ 7 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል የገቡ ሲሆን በቀጣይም ክለቡን ለማጠናከር ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡

17/09/2021

An Open Letter to President Joseph R. Biden Jr.
From Ethiopian PM Abiy Ahmed
Dear Mr. President,
As I write this open letter to you, it comes at a time when innocent civilians including women, children and other vulnerable groups in the Afar and Amhara regions have been violently displaced, their livelihoods disrupted, their family members killed, and their properties as well as service giving institutions destroyed intentionally by TPLF.
This letter comes at a time when our children in the Tigray region are being used as cannon fodder by remnants of an organization recently designated as ‘terrorist’ by our House of People’s Representatives. Children of a post-war generation that have held high hopes in the possibility that their lives would be distinctly different from that of their parents, whose lives have been marred by the terror of war with the DERG regime and a cross border conflict with Eritrea in the late 1990s instigated by the TPLF.
As the rest of their peers in the country pursue their studies and lives, our children of Tigray have been held hostage by a terrorist organization that attacked the State on November 3, 2020 exposing them to various vulnerabilities. While the use of children as soldiers and participation in active combat is a violation of international law, the terrorist organization TPLF has proceeded unabated in waging its aggression through the use of children and other civilians. The cries of women and children in the Amhara and Afar regions that are displaced and suffering at the hands of TPLF’s enduring ruthlessness continues under the deafening silence of the international community.
Unfortunately, while the entire world has turned its eyes onto Ethiopia and the Government for all the wrong reasons, it has failed to openly and sternly reprimand the terrorist group in the same manner it has been chastising my Government. The many efforts the Ethiopian Government has undertaken to stabilize the region and address humanitarian needs amidst a hostile environment created by the TPLF have been continuously misrepresented. The mounting and undue pressure on a developing African country, with limitless potential for prosperity, has been building up over the past months. This unwarranted pressure, characterized by double standards, has been rooted in an orchestrated distortion of events and facts on the ground as it pertains to Ethiopia’s rule of law operations in the Tigray region. As a long-time friend, strategic ally and partner in security, the United States’ recent policy against my country comes not only as a surprise to our proud nation, but evidently surpasses humanitarian concerns.
For almost three decades, Ethiopians in all corners have been subjected to pervasive human rights, civil and political rights violations under TPLF’s regime. Various identities under the Ethiopian flag were exploited by a small clique that appropriated power to benefit its small circle at the expense of millions, including the impoverished of the Tigray region. The suppression of political dissent, egregious human rights violations, displacements, suffocation of democratic rights and capture of State machinery and institutions for the aggrandizement of a small group that ran a country of millions with no accountability for 27 years has been met with little to no resistance by various Western nations, including the US.
The period 2015-2018 that marked Ethiopia’s awakening where the TPLF was deposed from power in a popular uprising, is telling of the stance that millions throughout this great country took against a criminal enterprise that subjugated Ethiopians to oppression and stripped citizens of agency. TPLF’s track record of pitting one ethnic group against the other for its own political survival did not end in 2018 when my administration took over the helms of power. It rather mutated and intensified in form, putting on the robe of victimhood, while financing elements of instability throughout the country.
Now, the destructive criminal clique, adept at propaganda and spinning international human rights and democracy machinations to its favor, cries wolf while it leaves no stone unturned in its mission to destroy a nation of more than a 3000-year history. Although this hallucination will not come to pass, history will record that the orchestrated turbulent period Ethiopia is going through at the moment is being justified by some Western policy makers and global institutions under the guise of humanitarian assistance and advancing democracy.
In a demonstration of my people’s aspiration to democratize and unprecedented in Ethiopia’s modern history, close to 40million of my country folk went out to vote on June 21, 2021 in this country’s first attempt at a free and fair election. In spite of the many challenges and shortcomings the 6th National Election may have been faced with, the resolute determination of the Ethiopian people for the democratic process was displayed in their commitment to a peaceful electoral period. Against the backdrop of previous electoral periods in which the choice of the people was snatched through rigged processes by the former regime, the 2021 elections came on the heels of the democratic reforms processes we embarked upon three years ago. The significance of our 2021 elections is in its peaceful conclusion, demonstrating Ethiopia’s new trajectory amidst the global warnings that the elections would be violent.
With the Ethiopian people having spoken and affirmed their faith in Prosperity Party to lead them through the next five years in a landslide victory, my Party and administration with this responsibility at hand, are ever more determined to unleash the potential for equitable development these lands are blessed with. We are even more resolute in granting our people the dignity, security and development they deserve within the means we have and without succumbing to various competing interests and pressures. And we will do this by confronting the threats to democracy and stability posed by any belligerent criminal enterprise.
While threats to national, regional and global security continue to be a key component of US interests in many parts of the world, it remains unanswered why your administration has not taken a strong position against the TPLF – the very organization the US Homeland Security categorized as qualifying as Tier 3 terrorist organization for their violent activities in the 1980s.
In the same manner that your predecessors led the global ‘war on terror’, my administration supported by the millions of Ethiopians thirsty and hungry for their right to peace, development and prosperity, are also leading our national ‘war on terror’ against a destructive criminal enterprise, which poses a threat to both national and Horn region stability. Ethiopia has remained the US’s staunch ally in fighting the terrorism threat of Al Shabab in the Horn. It is our expectation that the US would stand by Ethiopia as a similar terrorist organization with hostility towards the region threatens to destabilize the Horn.
Mr. President,
The American people that have supported the US government’s global interventions under the pretext of democratization would be hard-pressed to know that a small impoverished but culturally, historically and naturally rich nation in East Africa embarked on its own democratization path three years ago. However, the American people and the rest of the Western world are being misguided by the reports, narratives and data distortions of global entities many believe were driven to help impoverished countries like mine, yet have in the past months portrayed victims as oppressors and oppressors as victims through partisan narratives and bankrolled networks. History always smiles upon those who have stood for truth. And so, I am certain that truth will shine upon this proud nation Ethiopia!
Many Ethiopians and Africans looked with optimism at your ascent to the Presidency earlier this year. This optimism has been rooted in the belief that a new dispensation for Africa – US relations will materialize in 2021, and that your Presidency would usher in respect for the sovereignty of African nations and nurture partnerships based on mutual growth and in depth reading of context.
African nations that have broken free from the shackles of colonialism starting from the 1950s have continued to resist the chains of neocolonialism that is manifesting itself in various overt and covert ways. Despite escaping the yokes of colonialism, Ethiopia now struggles with its mutation. As a founding member of the United Nations and the Organization for African Unity (now African Union), Ethiopia remains a proud nation that through its sons, daughters and kinship with other African nations, is determined to meet our current challenges with the resilient and indomitable spirit that defines this great nation.
Developing nations, like Ethiopia, have been expectant that a new course in the US’s foreign policy will be charted, departing from the influence of individuals that have entrenched themselves into the politics of other nations. A foreign policy that can extricate itself from decisions made based on key policymakers and policy influencer’s friendships with belligerent terrorist groups like the TPLF and the narrative distortions of lobby groups. We have seen the consequences and aftermaths of hurried and rash decisions made by various US administrations that have left many global populations in more desolate conditions than the intervention attempted to rectify.
It is essential to point out here that Ethiopia will not succumb to consequences of pressure engineered by disgruntled individuals for whom consolidating power is more important than the well-being of millions. Our identity as Ethiopians and our identity as Africans will not let this come to pass. The humiliation our ancestors have faced throughout the continent for centuries will not be resuscitated in these lands upon which the green, gold and red colors of independence have inspired many to successfully struggle for their freedom!
God bless Ethiopia and its people!
September 17, 2021

መስከረም-01-2014በድንጋይ ስድስት ክላሽ የማረኩት የድሬ ሮቃው ጀግና።ስማቸው ሲራጅ ዲቢል አሊ ይባላሉ፡፡ በሀብሩ ወረዳ 024 ድሬ ሮቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ወ...
11/09/2021

መስከረም-01-2014
በድንጋይ ስድስት ክላሽ የማረኩት የድሬ ሮቃው ጀግና።
ስማቸው ሲራጅ ዲቢል አሊ ይባላሉ፡፡ በሀብሩ ወረዳ 024 ድሬ ሮቃ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ ከሰሞኑ አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ወደ ቀበሌያቸው ለመግባት ሲሞክር ቀበሌያቸውን ባለማስደፈር ታላቅ ጀብዱ ሰርተዋል፡፡
በሚኖሩበት ድሬ ሮቃ ቀበሌ ግንባር ላይ በመሰለፍ አንድ የአሸባሪው ቡድን አባል በወገን ጦር ላይ ጥቃት ለመፈፀም ሲሞክር በድንጋይ አንገቱን ብለው የያዘውን ክላሽ ማርከውታል፡፡ ከዚያም ሌሎች አምስት የአሸባሪው ቡድን አባላት ጓደኛቸውን ለማንሳት ሲመጡ አምስቱንም በመግደል የያዙትን አምስት ክላሽ በመማረክ በአጠቃላይ 6 ክላሽ ከአሸባሪው ትህነግ ወራሪ ቡድን መማረክ ችለዋል፡፡
በሃይማኖቴ እና በኢትዮጵያዊነቴ አልደራደርም የሚሉት አቶ ሲራጅ ወጣቱ የሀገሩን ሰላም እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን በርካታ ሕዝብ አሰልፎ ድሬ ሮቃን ለመያዝ ቢመኝም በቀበሌው ነዋሪዎችና በመከላከያ ሠራዊት ጥቃት ህልም ሆኖበት ወደመጣበት ተመልሷል ብለዋል፡፡
የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ ሸህ ሀሰን ከረሙ አሸባሪ ቡድኑ እኛን አልፎ እንዲሄድ አንፈቅድለትም፣ በቀጣይም ለሀገራችን መስዋእትነት እንከፍላለን ብለዋል፡፡
@አሚኮ

ለአዲሱ አመት (2014) እንኳን አደረሳችሁ ‼አዲሱ አመት የእድገት፣ የብልፅግና፣ የስኬት ያድርግልን ‼አዲሱ አመት ከጁንታውና ከአስተሳሰቡ ነፃ የምንሆንበት ዓመት ይሁንልን ‼መልካም አዲስ አ...
10/09/2021

ለአዲሱ አመት (2014) እንኳን አደረሳችሁ ‼
አዲሱ አመት የእድገት፣ የብልፅግና፣ የስኬት ያድርግልን ‼
አዲሱ አመት ከጁንታውና ከአስተሳሰቡ ነፃ የምንሆንበት ዓመት ይሁንልን ‼
መልካም አዲስ አመት ‼

ጳጉሜ-4-2013ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖር እናደርገዋለን-ሌ/ኮ ታየ ተክሌለደሴና ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖ...
09/09/2021

ጳጉሜ-4-2013
ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖር እናደርገዋለን-
ሌ/ኮ ታየ ተክሌ
ለደሴና ለወሎ ህዝብ ደጀናዊ ፍቅር ከነፍስ በላይ የሚከፈል መሥዋእትነት ቢኖር እናደርገዋለን ሲሉ ሌተናል ኮሎኔል ታየ ተክሌ ተናገሩ።
በወሎ ውጫሌ ግንባር እነ ፍስሀ ዳኜ እና ጓደኞቻቸው ግንባታ ህብረት ስራና ሽርክና ማህበር ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የምሳ እና የሙዚቃ መዝናኛ መርሀ ግብር አከናውነዋል።
ከደሴ ከተማ ከ60 ኪሎ ሜትር በላይ ተጉዘው ለሠራዊቱ ምሳ ባበሉበት እና ቀስቃሽ የሙዚቃ ዝግጅት ባቀረቡበት ወቅት ፥ሌተናል ኮሎኔል ታየ ተክሌ የወሎ ህዝብ የደጀንነት ፍቅር ከህይወት መሥዋአትነት በላይ ሊከፍሉለት የሚገባ ነው ብለዋል።
በግንባሩ ካለን ጀምሮ ደጀን ህዝቡ ስላልተለየን ምስጋናችን የላቀ ነው ነው ብለዋል።
ሠራዊቱ የህዝቡን ፍቅር እና የሚያሳየውን የመከላከያ ሰራዊት አክብሮት በመመልከት ይበልጥ በስነ ልቦና ምልኡ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።
የእነ ፍስሀ ዳኜ የግንባታ ህብረት ስራና ሽርክና ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ፍስሀ ዳኜ በበኩላቸው፥ ደጀንነታችን አያቋርጥም ከሰራዊቱ ጋር ኢትዮጵያን ለማዳን እንቀጥላለን ብለዋል።
በዛሬው የምሳ ግብዣ እና የሙዚቃ ባንድ ዝግጅት ማህበሩ ከ300 ሺህ ብር በላይ ወጭ ማድረጉንም ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
Fbc

እናታችንም ጀግናችንም የሆኑት ዶ/ር ማህተመ ሃይሌ በወሎ ግንባር ተገኝተው ጀግኖች ልጆቻቸውን አበረታተዋል!ዶ/ር ማህተመ ሃይሌ ብልፅግና ፓርቲን ወክለው በህዝብ ድምፅ ሙሉ ቅቡልነት ያገኙ የደ...
08/09/2021

እናታችንም ጀግናችንም የሆኑት ዶ/ር ማህተመ ሃይሌ በወሎ ግንባር ተገኝተው ጀግኖች ልጆቻቸውን አበረታተዋል!
ዶ/ር ማህተመ ሃይሌ ብልፅግና ፓርቲን ወክለው በህዝብ ድምፅ ሙሉ ቅቡልነት ያገኙ የደሴ ከተማ ተመራጭ መሆናቸው የሚታወስ ነው።
#እንወድሻለን እናታችን!!

እንኳን ደስ አላችሁ !!! ጳጉሜ-02-2013በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ዋሊያዎቹ በሜዳቸው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድንን በአስቻለው ታመነ ብቸኛ ጎል 1ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድላ...
07/09/2021

እንኳን ደስ አላችሁ !!! ጳጉሜ-02-2013
በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር ጨዋታ ዋሊያዎቹ በሜዳቸው የዚምባብዌ ብሔራዊ ቡድንን በአስቻለው ታመነ ብቸኛ ጎል 1ለ0 በማሸነፍ የመጀመሪያ ድላቸውን አስመዝግበዋል ።

ወራሪው ቡድን ተሁለደሬ ወረዳ የሰራው፦ሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በሚገኙት 017 ሰግለንና 027 ሙጢበልግ ቀበሌዎች ሰርጎ ገብቶ የነበረው የወራሪው፣ ጨፍጫፊው፣ ዘራፊውና አሸባሪ...
06/09/2021

ወራሪው ቡድን ተሁለደሬ ወረዳ የሰራው፦
ሰሞኑን በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ በሚገኙት 017 ሰግለንና 027 ሙጢበልግ ቀበሌዎች ሰርጎ ገብቶ የነበረው የወራሪው፣ ጨፍጫፊው፣ ዘራፊውና አሸባሪው የትግራይ ኃይል የአርሶ አደሩን ጓዳ ሰብሮ በመግባት ጭምር ከፍተኛ ውድመት አድርሷል፡፡
ይህ ወራሪና ዘራፊ የትግራይ ኃይል ወደ አካባቢው ከገባበት ውስን ቀን ጀምሮ በጀግኖቹ የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የሚሊሻ አባላትና የወሎ ህዝብ እየተገረፈ እስከወጣበት ዕለት የአካባቢው ነዋሪ አርሶ አደሮች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዳደረሰ የፓርቲያችን ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ በቦታው በመገኘት መመልከት ችሏል።
ወሮበላው ቡድን በተሁለደሬና ወረባቦ ወረዳዎች ንጹሃን ዜጎችን ዘግናኝ በሆነ መልኩ ገድሏል፡፡ ህጻናት፣ ሴቶችንና እናቶችን ለስቃይ ዳርጓል፡፡ የግለሰቦችንና የአገልግሎት ሰጭ ተቋማትን ሀብትና ንብረት የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን በማውደም አማራ ጠልነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡
ያነጋገርናቸው የ027 ሙጢበልግ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ሠይድ ቡሽራ እንደገለጹት ጨፍጫፊና አሸባሪው ቡድን የአካባቢውን ነዋሪ እንስሳቶች (ግመል፣ በሬ፣ ላም፣ በግና ፍየል በማረድ በልቷል፣ የተረፈውንም በየቦታው በመዝራት የክፋት ጥጉን አሳይቷል ብለዋል፡፡
የጠመንጃ አፈ ሙዝ ደቅነው የአመራር፣ የሚሊሻና የመንግስት ሠራተኞችን ቤት አሳዩን እያሉ ሲያሰቃዩ እንደነበር አርሶ አደር ሠይድ ቡሽራ አስረድተዋል!!

ጳጉሜ-01-2013"በእምነቴ፣ በአማራነቴና በኢትዮጵያ አልደራደርም" የድሬሮቃው አርሶ አደሩ ጀኔራል ሸህ ሐሰን ከረሙ።በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ የድሬሮቃ ቀበሌ በተግባር ተፈትና ውጤት አም...
06/09/2021

ጳጉሜ-01-2013
"በእምነቴ፣ በአማራነቴና በኢትዮጵያ አልደራደርም" የድሬሮቃው አርሶ አደሩ ጀኔራል ሸህ ሐሰን ከረሙ።
በሰሜን ወሎ ዞን ሃብሩ ወረዳ የድሬሮቃ ቀበሌ በተግባር ተፈትና ውጤት አምጥታለች። የዚህች ቀበሌ ሊቀመንበር ጀግና መሪ እና ትጉህ አባት ሸህ ሐሰን ከረሙ ናቸው። የቀበሌያቸው ሕዝብ ባሳዩት ጀግንነት የጄኔራል ማዕረግ ሰጥቷቸዋል። ድንቅ የጦር መሪነታቸውን የተረዱ ከተሜዎችም ይህን ማዕረግ አፅድቀው "ጀኔራል ሐሰን" ሲሉ ይጠሯቸዋል።
አርሶ አደሩ ጀኔራል ሸህ ሐሰን ከረሙ አሸባሪው፣ ወራሪውና አማራ ጠሉ የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ጦር ሰብቆ ወደቀያቸው ሲዘልቅ ወጣቶችንና የአካባቢያቸውን ታጣቂዎች አቀናጅተው የመሩ፤ ለቀናት ተዋግተው ወራሪውን ቡድን በመቅበር ቀያቸውን ያላስደፈሩ ድንቅ መሪ ናቸው።
አሸባሪው ቡድን ማንነታቸውን፣ ክብራቸውን እና ሀገራቸውን መድፈሩ ያንገበገባቸው እኒህ ድንቅ መሪ ወደመከላከል ሲገቡ ከቀየው የነበረው የተሻለ መሳሪያ አንድ ስናይፐርና አንድ መትረየስ ብቻ ሲሆን የግለሰብ ክላሽን ጨምረው በመጠቀም ወራሪውን ቡድን እንዲደመሰስ ከፍተኛ ትግል አድርገዋል።
የድሬሮቃው አርሶ አደር ጀኔራል ሸህ ሐሰን ከረሙ የወጣቱን ቅንጅት አድንቀዋል፡፡ ጀኔራል ሸህ ሐሰን እንደሚሉት በፊት ለፊት ውጊያ ድል የተደረገው ወራሪው ቡድን በመርሳ ዞሮ ሲመጣ የፊት በር ጠባቂ በማስቀመጥ የቀያቸውን ወጣት እና ፋኖውን አቀናጅተው በጮቢ በር በማዝመት በሁለት ቀን ትግል ከአንድ ብርጌድ በላይ የወራሪውን ቡድን ደምስሰዋል።
"ጌታቸው ረዳ ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለን ሲል በራዲዮ ሰምቸዋለሁ" ያሉት የድሬ ሮቃው ጀግና "እኒህ ወራሪዎች የመጡት ለበቀል እና ሀገር ለማፍረስ እንጅ ሀገር ለመምራት አይደለም፤ እኔ በሕይወት እያለሁ ሕዝቤ አይንገላታም፣ ሴቶች አይደፈሩም፣ መንደሬ አይዘረፍም፣ በተለይም አማራነቴን የሚነካ ያንገበግበኛል፤ በእምነቴ፣ በአማራነቴና፣ በኢትዮጵያዊነቴ አልደራደርም" ብለዋል።
የአሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን እጅግ የተጎዳና የተራበ ነው፤ አሸባሪ ቡድኑ በሐሰት ፕሮፖጋንዳ ሕዝብ መሸበር የለበትም ነው ያሉት።
በሕዝብ ኀይል የሚጠፉ ድኩማን ናቸው ነው ያሉት።
ጀግናው ሸህ ሐሰን ከረሙ "እኔ ባለኝ እውቀት እንኳ ይህን ያህል ወራሪ ቡድን ከእኛ ቀየ ሲቀበር የትግራይ እናትና አባት ምን ያህል ጧሪ አልባ እየሆኑ እንደሆን አስባለሁ፤ አዕምሮዬም ረፍት ያጣል፤ ያሳዝኑኛል፤ የትግራይ ሕዝብ ለልጆቹ ሲል የትህነግን ሽብርተኛ ቡድን በቃችሁ ሊላቸው ይገባል" ብለዋል።
ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ክብር መሞቱ አዲስ አይደለም ያሉት የድሬሮቃው ጀግና ሸህ ሐሰን ከረሙ በተለይም አማራን ሊበቀል የመጣን ወራሪ ምድራችንን እሾህ ልናደርግበት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
@አሚኮ

ጳጉሜ-1-2013አሸባሪው ህወሓት በወሎ ግንባር ያሰለፈው ሃይል ተዳክሟል፡- ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም************************ያለ የለለ ሀይሉን በወሎ ግንባር ያሰለፈው አሸባሪው...
06/09/2021

ጳጉሜ-1-2013
አሸባሪው ህወሓት በወሎ ግንባር ያሰለፈው ሃይል ተዳክሟል፡- ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም
************************
ያለ የለለ ሀይሉን በወሎ ግንባር ያሰለፈው አሸባሪው ህወሀት በወገን ጦር በተወሰደበት እርምጃ መዳከሙን የወሎ ግንባር የኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም ተናገሩ።
በጋይንት እና በጭፍራ አካባቢዎች የደረሰበትን ሽንፈት በወሎ ግንባር አካክሳለሁ ብሎ በርካታ ሀይል አሰልፎ የነበረ ቢሆንም ሙት እና ቁስለኛውን እንኳን ሳያነሳ ወደኋላ እየሸሸ ነው ብለዋል።
በተለይም የውጫሌ ግንባርን ለመስበር ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊት ተመቶ ወደኋላ በመሸሽ ሌላ ሀይሉን ደግሞ በተሁለደሪ ሰግለን እና በወረባቦ አካባቢዎች የውጊያ ግንባርን ፈጥሮ ነበር ብለዋል ጀነራሉ፡፡
ይህም እቅዱ የወገን ጦርን አቅጣጫ ለማስቀየር በመሆኑ የተወሰነው ሰራዊት እና ልዩ ሀይሉ እንዲሁም ሚሊሻው እና የአካባቢው ፖሊስ ተቀናጅተው በመመከት ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰውበታል ብለዋል ሌ/ጀኔራል ሀሰን ኢብራሂም።
ጠላት ከፍተኛ የሰው ቁጥር በማሰለፍ የወሎ ግንባር ለመስበር ተደጋጋሚ ማጥቃት ቢያደርግም በመከላከያ ፣በልዩ ሀይል ና በሚሊሻው በሚወሰድበት እርምጃ ወደኋላ መሸሽን ተያይዞታል ነው ያሉት።
የአሸባሪው ሀይል በወገን ጦር በከፍተኛ ሁኔታ ተመቶ በጊራና አካባቢ ወደኋላ ሲሸሽም ትዋጋለህ አልዋጋም በሚል በከባድ መሳሪያ የታገዘ የርስ በርስ ውጊያ ውስጥ ገብቶ እንደነበርም ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ በሸሸበት ሁሉ በመከታተል እርምጃ እየተወሰደበት መሆኑንም ሌተናል ጀኔራል ሀሰን አስታውቀዋል።
በይመር አደም

ደሴ ከተማ አንድም የእርዳታ ድርጅት ሳይመጣ፣ አንድም የመንግስት ተቋም ሳይረዳ ለ19 ቀን ያክል 183,000 ተፈናቃዮችን በህብረተሰቡ ትብብር ብቻ እንግዶቿን እያስተናገደች ትገኛለች።አሁንም ...
05/09/2021

ደሴ ከተማ አንድም የእርዳታ ድርጅት ሳይመጣ፣ አንድም የመንግስት ተቋም ሳይረዳ ለ19 ቀን ያክል 183,000 ተፈናቃዮችን በህብረተሰቡ ትብብር ብቻ እንግዶቿን እያስተናገደች ትገኛለች።
አሁንም ደግሞ የእርዳታ አጋሮች ደርሰዋል፤ እርዳታው ይቀጥላል።

 #የድል ዜና፡-ጁንታው በወሎ ምድር ተሸንፏል!!የወሎ ህዝብ ለፍቅር እንጅ፡ በእብሪት የተሸነፈበት ታሪክ የለውም።ጁንታው የወሎን ምድር በውል ባለመገንዘብ ዘሎ ገብቶ፡ እንደ ቡና አሮ እየተቆላ...
05/09/2021

#የድል ዜና፡-ጁንታው በወሎ ምድር ተሸንፏል!!
የወሎ ህዝብ ለፍቅር እንጅ፡ በእብሪት የተሸነፈበት ታሪክ የለውም።
ጁንታው የወሎን ምድር በውል ባለመገንዘብ ዘሎ ገብቶ፡ እንደ ቡና አሮ እየተቆላ ነው። በመጣበት እግሩም ዘሎ እንዳይመለስ በየመንገዱ እየተቀበረ ነው።
በዚህም ጀግናው የወሎ ህዝብ፡ ሚኒሻው፡ ወጣቱ፡ፖሊሱ፡ ቆራጥ አመራሮቻችን በየደረጃው ባደረጉት የጀግንነት ተጋድሎ፡ የምንጊዜም ኩራታችን በሆነው የመከላከያ ሰራዊታችን፡ልዩ ሃይላችን ታሪክ ሰሪነት ጁንታው በወሎ ምድር ተሸንፎ ወደ ኋላ በመሸሽ ላይ ይገኛል።
ስለሆነም በጀግናው የወሎ ወጣት፡ ሚኒሻ፡ ህዝብ ተሸንፎ መውጫ መግቢያ ያጣውን ጁንታ በየመንገዱ ከበህ በመማረክና በመግደል የያዙትን የጦር መሳሪያ እየቀማህ ታጠቅ!!
ለጌታቸው ረዳ መልስ በተግባር ይሉሃል እንድህ ነው።
By; Seid Mohammed Hussein

ነሀሴ 30 ቀን 2013  via ENDFየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊታችን ፣ የጀመረውን ሽብርተኛውን ጠራርጎ የመደምሰስ ማጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ።የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት እንዳስታወ...
05/09/2021

ነሀሴ 30 ቀን 2013 via ENDF
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊታችን ፣ የጀመረውን ሽብርተኛውን ጠራርጎ የመደምሰስ ማጥቃት አጠናክሮ ቀጥሏል ።
የመከላከያ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት እንዳስታወቀው ፣ ሰራዊታችን ሰፊ የፀረ-ማጥቃት እርምጃውን አጠናክሮ ቀጥሏል ።
አሸባሪው ህወሃት የመንግስትን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔን እና ለትግራይ ህዝብ የተሰጠውን የጥሞና ጊዜ አሻፈረኝ በማለት በአማራና አፋር ክልል ወረራ በመፈፀም እጅግ ዘግናኝ ግፎችን ሲፈፅም ቆይቷል።
የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ እንዳስታወቁት ፣ የመከላከያ ሰራዊታችን እስትራቴጂክ ቦታዎችን ይዞ በመከላከል ቁመና ራሱን ለቀጣይ ግዳጅ ሲያዘጋጅ ቆይቷል።
አሁን ላይ ከመከላከል ቁመና ወደ ፀረ-ማጥቃት በመሸጋገር ሽብርተኛው ወረራ ከፈፀመባቸው ቦታዎች ሁሉ ጠራርጎ ለማውጣትና ለመደምሰስ ጀግናው ሠራዊታችን ማጥቃት ጀምሯል።
በዚህ ፀረ-ማጥቃት ፣ በአሸባሪው የህወሃት ኃይል ላይ የሚወሰደውን እርምጃ በየቀኑ እየተከታተልን ዘገባዎችን/ዜናዎችን የምናስተላልፍ መሆኑን ለመላ ህዝባችን ማብሰር እንወዳለን።
ኢትዮጵያ በልጆቿ መሰዋትነት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች! እናሸንፋለን !
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

ነሀሴ 29 ቀን 2013 via ENDFበከሃዲው ብ/ጀ ምግበ ኃይለ የሚመራው አርሚ አንድ የተሰኘው አሸባሪው የህወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/...
04/09/2021

ነሀሴ 29 ቀን 2013 via ENDF
በከሃዲው ብ/ጀ ምግበ ኃይለ የሚመራው አርሚ አንድ የተሰኘው አሸባሪው የህወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀ ባጫ ደበሌ ገለፁ።
ሌ/ጀ ባጫ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፣ ቀደም ሲል መንግስት በተናጠል የተኩስ አቁም ስምምነት ቢያደርግም አሸባሪው ህወሃት አሻፈረኝ በማለት ያለ የሌለ ኃይሉን በማሰለፍ በአማራና አፋር ክልሎች ላይ መጠነ ሰፊ ወረራ ማድረጉን ገልፀዋል።
ይህ አሸባሪ ኃይል በምዕራብ ኢትዮጵያ አድርቃይ እና ማይጠብሪ አካባቢ ዳባትና ደባርቅን በመቁረጥ ጎንደርን በመያዝ ሁመራን ተቆጣጥሮ ከውጪ የሚጋልቡት ጌቶቹ የሚሰጡትን ዕርዳታ ማስገቢያ ቀዳዳ ለማስከፈት ጥረት አድርጓል ብለዋል።
ይሁን እንጂ ይህንን ተልዕኮ ለማስፈፀም የተሠለፈው እና ብ/ጀ ምግበ በሚባል ከሃዲ ግለሰብ የሚመራው አርሚ አንድ የተሰኘው ኃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን ሌ/ጀ ባጪ ደበሌ ገልፀዋል።
በ3 ክፍለ ጦሮች የተደራጀው ይህ የአሸባሪ ኃይል በእያንዳንዱ ክፍለ ጦር ስር ሶስት ኮሮችን ያቀፈ ሲሆን ሰሞኑን በተደረገ ውጊያ ከ5 ሺ 600 በላይ ሙት ከ2 ሺ 300 በላይ ደግሞ ቁስለኛ ሲሆኑ ፣ 2 ሺ አባላቱ ተማርከው ቀሪዎቹም ተበታትነውበታል።
ይህ ኃይል ከደረሰበት ሰብዐዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ በተጨማሪ ወደ ሱዳን ያስወ፤ጣኛል ያለው መንገድም ሙሉ በሙሉ ተዘግቶበታል።
በጋሸና ግንባር የተሰለፈው እና በሃገር ላይ ክህደት በፈፀመው ሜ/ጀ ዮሐንስ ወ/ጊዮርጊስ የሚመራው አርሚ ሁለትም ከክምር ድንጋይ ጀምሮ ደብረዘቢጥ እና ኮኪት የነበረው ኃይሉ ተመቶ ከፍላቂት ወደጋሸና እየፈረጠጠ ሲሆን ፣ በዚህ አርሚ ስር ካሉት ኮሮች መካከል የአንዱ ኮር ሁለት ክ/ጦሮች ተደምስሰዋል።
በዚሁ መሠረት ከ4 ሺ 100 በላይ ሙት ከ2 ሺ300 በላይ ደግሞ ቆስለዋል ። ቀሪዎቹ ጦርነቱን መቋቋም አቅቷቸው በሽሽት ላይ ናቸው።
ሌላው ሰሞኑን መተማን ወደ ቀኝ በመተው በሽንፋ በኩል ወደ ጎንደር በመግባት ከቅማንት ቅጥረኛ ቡድን ጋር በመተባበር ለሽብር ተግባር ተልኮ የነበረው ኃይልም 90 አባላቱ ሲገደሉ ቀሪዎቹ ወደ መጡበት ሸሽተው ተመልሰዋል።
በውጪ ከሚያደራጃቸው ከሃዲው ሜ/ጀ ፍሰሃ ተልዕኮ የሚቀበለው ይህ ኃይል ከዚህ በፊትም ሁለት ጊዜ በቤንሻንጉል ጉሙዝ በኩል በመግባት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ስራን ለማስተጓጐል ጥረት ቢያደርግም ያሰበውን ሳያሳካ ተመቶ መመለሱን ሌ/ጀ ባጫ ደበሌ ገልፀዋል።
በአጠቃላይ በጦርነቱ ከ10 ሺ በላይ የአሸባሪው ኃይል መደምሰሱን ያወሱት የመከላከያ ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጀ ባጫ ደበሌ ፣ ከሃዲው ህወሃት የሚማግዳቸው ህፃናት ከሁለት ቀን ያልበለጠ ስልጠና የወሰዱ ከመሆናቸውም በላይ መሸሽ እንዳይችሉ ከኋላ ገዳይ ኃይል በመመደብ ጭምርም መሆኑን ተናግረዋል።
ጀነራል መኮንኑ ጦርነቱ አሁንም የቀጠለ መሆኑን በማውሳት በተገኘው ድልም ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አብዮት ዋሚ
ፎቶግራፍ እጸገነት ዴቢሳ

ጀነራል ባጫ ደበሌ ዝምታቸውን ሰበሩ!*****************************አሸባሪው ህወሓት በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል!!ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ*********...
04/09/2021

ጀነራል ባጫ ደበሌ ዝምታቸውን ሰበሩ!
*****************************
አሸባሪው ህወሓት በሶስት አቅጣጫ ያሰለፈው ቡድን ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል!!
ሌ/ጀነራል ባጫ ደበሌ
*****************************
በጀነራል ምግበይ የሚመራው አርሚ አንድ ተብሎ የሚጠራው ሃይል ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን የመከላከያ ሚኒስቴር የሠራዊት ግንባታ ዋና አስተባባሪ ሌተናል ጀኔራል ባጫ ደበሌ ገልጸዋል፡፡
ሌተናል ጄነራል ባጫ ደበሌ የሰራዊቱን ግዳጅ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በጀነራል ምግበይ የሚመራው እና አርሚ አንድ የሚባለው ሃይል በሁመራ አካባቢ ደባርቅ እና ዳባትን በመቁረጥ ጎንደርን ለመያዝ ቢፈልግም ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል ብለዋል ጀነራሉ፡፡

አራቱ ወንድማማች የኢትዮጵያ ዘማቾች******************(ኢ.ፕ.ድ)አራቱ የጋሽ ኑር ልጆች እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም ብለው ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ገብተው ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ይ...
04/09/2021

አራቱ ወንድማማች የኢትዮጵያ ዘማቾች
******************
(ኢ.ፕ.ድ)
አራቱ የጋሽ ኑር ልጆች እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም ብለው ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ገብተው ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፤ ወንድማማቾቹ ቃሲም ኑር፣ ኤዳሶ ኑር፣ ታጁ ኑር እና ዘይኑ ኑር ይባላሉ።
አራቱ ወንድማማቾች ጁንታው ሀገር ሊበትን ቢያስብም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች እያለን ይህ እንዴት ይሆናል ብለው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት መዝመት እንዳለባቸው ተነጋግረውና መክረው ስልጠናቸውን በሚገባ እየተከታተሉ እንደሚገኙ በሥፍራው ለሚገኙት የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘጋቢዎች ነግረዋቸዋል።
አባታቸው ጋሽ ኑር 11 ወንድ ልጆች እና 6 ሴት ልጆች አሏቸው። ወደማሰልጠኛው የገቡት አራቱ ወንድማማቾች "አባታችን በሀገር ፍቅር ስሜት እና ወኔ ነው አንጾ ያሳደገን። በዚህም ምክንያት አገር ጥሪ ስታቀርብ መርቆና በአባገዳዎች አስመርቆ ሸኝቶናል" ነው ያሉት ሰልጣኞቹ የኢትዮጵያ ወታደሮች።
"ጁንታውን ሳንቀብር ደግሞ ወደቤታችን አንመለስም" ብለዋል ወንድማማቾቹ።
ወንድማማቾቹ ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ የመጣ እራሱ ይፈርሳል እንጂ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታ ትኖራለች የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም (ብርሸለቆ)

 #ወደፊት ብቻ ‼እኔ እያለሁ  #ሃገሬን፣  #ከተማየን፣  #ቤተሰቤን፣  #ንብረቴን፣  #እኔነቴን አላስደፍርም ‼ #ድሉ ከእኛ ጋር ነው ‼
04/09/2021

#ወደፊት ብቻ ‼
እኔ እያለሁ #ሃገሬን፣ #ከተማየን፣ #ቤተሰቤን፣ #ንብረቴን፣ #እኔነቴን አላስደፍርም ‼
#ድሉ ከእኛ ጋር ነው ‼

 #ወደፊት ብቻ ‼ ‼ #ድሉ ከእናንተ ጋር ይሁን ‼
04/09/2021

#ወደፊት ብቻ ‼ ‼
#ድሉ ከእናንተ ጋር ይሁን ‼

 !!ነሃሴ-28-2013**********የጁንታው ጦር ዋና ዋና ወታደራዊ አዛዦች የሆኑት ጀነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይና ጀነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) በዛሬው እለት ተገደሉ። ሁለቱ አዛዦች ዛ...
03/09/2021

!!
ነሃሴ-28-2013
**********
የጁንታው ጦር ዋና ዋና ወታደራዊ አዛዦች የሆኑት ጀነራል ጻድቃን ገ/ተንሳይና ጀነራል ታደሰ ወረደ (ወዲ ወረደ) በዛሬው እለት ተገደሉ። ሁለቱ አዛዦች ዛሬ በተደረገ ከፍተኛ ስብሰባ ስሙ ለጊዜው ባልታወቀ የሌ/ኮሎኔል ማዕረግ ባለው ወታደራዊ አመራር በተኮሰባቸው ጥይት ተመትተው ወደ ሆስፒታል ቢሄዱም ሊተርፉ አልቻሉም። ሌሎች የተመቱ አዛዦች ያሉ ሲሆን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን።
ምንጭ፡ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት- Tigray prosperity party

ነሀሴ 28 ቀን 2013   via ENDF #የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ማህበር ከአንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሽህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ በወሎ ግንባር ለተሰለፈው መከላከያ ሃይላችን ትኩስ ምግቦችን ...
03/09/2021

ነሀሴ 28 ቀን 2013 via ENDF
#የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ማህበር ከአንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሽህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ በወሎ ግንባር ለተሰለፈው መከላከያ ሃይላችን ትኩስ ምግቦችን አቅርበዋል ።
የምግብ አቅርቦቱ መጭውን የዘመን መለወጫ በአል ምክንያት በማድረግ ለሰራዊቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ለማስተላለፍ ታስቦ የቀረበ ነው።
ማህበሩ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለሰራዊቱ ለማቅረብ መዘጋጀቱን የገለፁት የድጋፉ ዋና አስተባባሪ አቶ ከበደ ወልደሩፋኤል ፣ ሃገራችን በአዲስ አመት ዋዜማ ላይ በምትገኝበት በዚህን ወቅት ከህዝብ አብራክ የፈለቀው መከላከያ ሃይላችን የሃገሩን ህልውና ለማስከበር ሲል በአልን በጦርነት ውስጥ ሲያሳልፍ የበአል ድባብ የሚፈጥሩ ትኩስ ምግቦችን ይዘን ከአጠገቡ ስንቆም የፈጠረልን የደስታ ስሜት ወደር የለውም ብለዋል ።
በእለቱ የምግብ ግብዥ ስነ-ስርዓት ላይ የታደሙ የደሴ ከተማ የሃይማኖት አባቶች ለሰራዊቱ ባስተላለፉት መልእክት ፣ ሰራዊታችን ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር የሚያካሂደው ጦርነትና የሚከፍለው ቅዱስ መስዋእት ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የሚያስመሰግነው ነው ብለዋል ።
ለሰራዊቱ የተበረከተለትን የምግብ አቅርቦት የተረከቡት በግንባሩ የሚገኝ ሻለቃ አዛዥ ተወካይ እንዳሉት ፣ ህዝባችን ለሰራዊቱ እያደረገ ያለው ድጋፍ የዝግጁነት አቅማችን ላይ ተጨማሪ ግብአት በመሆን ለበለጠ ድልና አሸናፊነት የሚያበቃን ነው ብለዋል ።
ኤፍሬም አድማሱ (ከግዳጅ ቀጣና)
ፎቶግራፍ ታጠቅ ንጉሴ

ነሀሴ 28 ቀን 2013  via ENDFዛሬ በማይጠብሪ ግንባር ለማጥቃት የመጣው የከሀዲው ኮ/ል ኪሮስ ገ/ኪዳን ክፍለጦር እሱን ጨምሮ ወርቅ አምባ፣ ቡና ሜዳ እና ዝንጆሮ አፋፍ አካባቢዎች ተደ...
03/09/2021

ነሀሴ 28 ቀን 2013 via ENDF
ዛሬ በማይጠብሪ ግንባር ለማጥቃት የመጣው የከሀዲው ኮ/ል ኪሮስ ገ/ኪዳን ክፍለጦር እሱን ጨምሮ ወርቅ አምባ፣ ቡና ሜዳ እና ዝንጆሮ አፋፍ አካባቢዎች ተደምስሰዋል፡፡
በማይጠብሪ ግንባር ከሚመሩት አዛዦች መሀል አንዱ እንደተናገሩት ፣ ትላንት ለሊት 10 ሰዓት እና ዛሬ ረፋድ ላይ በከሀዲው ኮ/ል ኪሮስ ገ/ኪዳን የሚመራው ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ እሱን ጨምሮ የጁንታው አመራሮች ከሆኑት መካከል ሌ/ኮ ገ/ፃዲቅ ምሩፅ መደምሰሱን አረጋግጠዋል ፡፡
በተደረጉት አውደ ውጊያዎች አሸባሪው የህውሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረው ከ27 ሺ በላይ የተለያዩ ጥይቶች ፣ ዲሽቃ፣ ብሬን ፣ ስናይፐር፣ መገናኛ ሬድዮ እንዲሁም ህዝብን መደናገሪያ ሊጠቀምበት የነበረውን የሀሰት የአማራ ክልል ማህተም መማረክ ተችሏል ብለዋል፡፡
አዛዥ እንደገለፁት ፣ ይህ ድል በምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት፣ በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በጋራ የተገኘ ድል ነው ፡፡
በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሠራዊቱ ጎን በመሆን አሁን በግንባር ተሰልፈው የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ አመልክተዋል ።
ፍፁም ከተማ ( ከግዳጅ ቀጣና )
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

ዛሬ ጀግናው የአማራ ክልል ሃይል ለቀናት በትህነግ አሸባሪ ተይዞ የነበረውን የሰቆጣ ከተማ ተቆጣጥሮታል።ለሰቆጣ ወጣቶች ና ለመላው የዋግ ጀግኖች ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ታላቅ የክብር ምስጋና...
03/09/2021

ዛሬ ጀግናው የአማራ ክልል ሃይል ለቀናት በትህነግ አሸባሪ ተይዞ የነበረውን የሰቆጣ ከተማ ተቆጣጥሮታል።
ለሰቆጣ ወጣቶች ና ለመላው የዋግ ጀግኖች ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ታላቅ የክብር ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ትህነግ ይደመሰሳል!!! እናሸንፋለን !!
አቶ አገኘሁ ተሻገር

ነሀሴ 28 ቀን 2013 via ENDFየሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ተደምስሷል።በዚህ ...
03/09/2021

ነሀሴ 28 ቀን 2013 via ENDF
የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል በጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ተደምስሷል።
በዚህ ተልዕኮ ሀምሳ የሽብር መልዕክተኞች ተደምስሰዋል ፡፡ ከሰባ በላይ ቀስለዋል ፡፡
የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ ፣ ቅጥረኛው የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል ሲሉ ተናግረዋል።
ጠላት አሳቻ ስአት ጠብቆ አካባቢውን ለማተራመስ ቢቀሳቀስም የጠላትን እንቅስቃሴ ከመነሻው በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊታችን ክፍሎች ተቀናጅተው እርምጃ ወስደውበታል ።
የጠላት ሃይል የቻለውን ያክል መከላከል ቢሞክርም በጀግናው ሰራዊታችን የበላይነት ተወስዶበት የተረፈው ሃይል አግሬ አውጪኝ በማለት መፈርጠጥ አማረራጭ ማድረጉን ኮ/ል ሰይፈ ተናግረዋል።
የጥፋት ሃይሉ ሲጠቀምባቸው እና ለእኩይ ስራው ሲያዘጋጃቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ፣ ፈንጂዎች የወደሙ ሲሆን የተቀሩት በጀግናው ሰራዊታችን ቁጥጥር ስር ገብተዋል ፡፡
አሸባሪው የሕወሃት ቡድን በግንባር ድል አልቀና ሲለው አብዛኝው ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል አቅንቷል በሚል ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ተቀናጅቶ የህዳሴ ግድባችንን ስራ ለማስተጓጎል ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ነው የተናገሩት ።
በአሁኑ ስአት በአካባቢው ጀግናው የመከላከያ ሃይላችን ፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ሐይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ኮ/ል ሰይፈ አረጋግጠዋል።
ኩራባቸው ግርማ
ፎቶግራፍ ፍቃዱ በቀለ

የደሴ ከተማ ወጣቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተሁለደሬ ላይ ደጀን ሆነዋል!*****የደሴ ከተማ ወጣቶችና የንግዱ ማህበረሰብ በተሁለደሬ ግንባር ላይ ለተሰለፈው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ አማራ...
02/09/2021

የደሴ ከተማ ወጣቶች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተሁለደሬ ላይ ደጀን ሆነዋል!
*****
የደሴ ከተማ ወጣቶችና የንግዱ ማህበረሰብ በተሁለደሬ ግንባር ላይ ለተሰለፈው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት፣ አማራ ልዩ ሃይል ሚሊሻና ፋኖ የሎጅስቲክ ድጋፋ እና ግንባር ድረስ በመዝመት ደጀንነታቸውን በተገግባር አሳይተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ ታቸንፋለች!

ትኩረት  #ለወረባቦ ‼  ‼
02/09/2021

ትኩረት #ለወረባቦ ‼

ነሀሴ 26 ቀን 2013 via ENDFደባርቅና ዳባት ~ የጁንታው መቀበሪያበከሃዲው ጄኔራል ምግበይ ሀይለ እየተመራ በማይጠብሪ ግንባር በደባርቅና ዳባት ወረዳዎች አዋሳኞች በጫንቅ ፣ ጭና እና ...
02/09/2021

ነሀሴ 26 ቀን 2013 via ENDF
ደባርቅና ዳባት ~ የጁንታው መቀበሪያ
በከሃዲው ጄኔራል ምግበይ ሀይለ እየተመራ በማይጠብሪ ግንባር በደባርቅና ዳባት ወረዳዎች አዋሳኞች በጫንቅ ፣ ጭና እና ወቅን አካባቢዎች የእነ ወዲ ረዳን ሒሳብ የማወራረድ ስሌት ይዞ የመጣው ዘራፊው የትህነግ ሀይል ድባቅ ተመቷል።
ከግንባሩ ጦር አዛዦች መካከል አንዱ ኮ/ል ሀብታሙ ምህረቴ ፣ በትንታጎቹ የሠራዊታችን አባላት መሪነት በግንባሩ ከተሰለፈው የወገን ሀይል ጋር በሳምንቱ ጠላት የከፈተውን ተደጋጋሚ ማጥቃት በመመከትና ወደ ማጥቃት በመሸጋገር ድል መቀዳጀት መቻሉን ተናግረዋል።
በወቅን ጭና የተሰለፈው የወገን ሀይል በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጁንታው ሀይል የተደመሰሰና የተማረከ ሲሆን ፀረታንክ ፣ ዲሽቃ ፣ ብሬን ፣ ላውንቸር እና ስናይፐርን ጨምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች ከ15ሺህ 600 በላይ የተለያዩ ጥይቶች ፣ የመገናኛ ሬዲዮና የእጅ ስልኮች እንዲሁም የብር ኖቶች ጋር ከጠላት ተማርከዋል።
የአገራችን ህዝቦች የአንድነት ነቀርሳ የሆነው ከሃዲ ጁንታ እንዲደመሰስና ለድሉ መገኘት የደጀኑ ህዝብ እስከ ግንባር እያደረገው ያለው ድጋፍ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑን ኮ/ል ሀብታሙ ምህረቴ ተናግረዋል ።
መላክ በቃሉ (ከግዳጅ ቀጣና)
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie.com posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share