Kembatta Voice-KV-ድምፀ ከምባታ

  • Home
  • Kembatta Voice-KV-ድምፀ ከምባታ

Kembatta Voice-KV-ድምፀ ከምባታ we will make a difference by providing approprate information for rational decisions

ይሳካልህ!!
26/06/2020

ይሳካልህ!!

20/06/2020

በአሁን ሰአት ክልልነት የተከለከለ ዞን ምን ይላል መሰላችሁ??
can't breathe

13/06/2020

የከምባታ ህዝብ የልማት ጥያቄ የመኖር እና ያለመኖር እንጂ የቅንጦት ጉዳይ አይደለም!!

12/06/2020

ነጻነት ያለ ዳቦ አንፈልግም!!!
ክልል እንሁን ስንል ስሙን ብቻ አይደለም ስሙንና ተግባሩን ነው እንጂ።
ባለፉት 27 አመታት ህዝቡና ልጆቹ የበይ ተመልካች ሆነው መሰንበታቸውን ሙሉ ክልሉ የሚያውቀው ሃቅ ነው። ከዚህ በፊትም ባዶ ዞን ሆነን ነበር የግለሰቦች መቦረቂያ - ባዶ ዎና!!
የከምባታ ህዝብ ሆሳእናን ካለማ በዋላ ወደ ዱራሜ ሲባረር አንድ ዞን ማስጠበቅ ያለበትን የህዝብ ጥቅማ ጥቅሞችን አስከብሮ አልሄደም። ኢፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ነበር ጭራሽ ምንም ይዞ አልወጣም ማለት ይቻላል። ምን አልባት ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን እና የስልጣን ጥማቸውን አርክተውበት ይሆናል። የሆነው ሆኖ አልፏል አሁን ግን ተመሳሳይ ስህተት መደገም አለበት ብዬ አላምንም ።

ከምባታ የተገፋው ከአብራኩ በወጡ ልጆቹ በስልጣን ጥመኞች በመንግስት በጀት ልማት መስራት ባቃታቸው ሌቦችና ተላላኪዎች ነው።
እንድህ ነበር ታሪኩ:
የከምባታ አውራጃ ከዚያ
የከምባታ እና የሃዲያ አውራጃ ከዚያ
የሃዲያ ዞን ከዚያ
ከምባታ ጠምባሮ ዞን - 27 አመት ሙሉ ባለሰልጣን እየተቀያየረ ጋጣት እንጂ ምንም አልተቀየረችም።
የከምባታ ህዝብ የክልልነት ጥያቄ በውስጡ የያዛቸው አያሌ ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ:
፩ የመልካም አስተዳደር እጦት
፪ የሙስና መንሰራፋት
፫ የህዝብ ድምፅ አፈና
፬ የልማት ጥያቄ
፭ የፍትህ እጦት እና የመሳሰሉት በዋቢነት ይጠቀሳሉ

ቸር እንሰንብት!!

10/06/2020

የከምባታ ህዝብ ጥያቄ ለምን አልተመለሰም??? በአሜን ሀንዳ እንደተጻፈ

የከምባታ ህዝብ በዘመናት ታሪኩ ውስጥ የዜግነት መብቱን ብቻ ነው ጠይቆ የሚያውቀው ከሌሎች የተለየ ነገር ይደረግልኝ አላለም!!
ለዋቢነት ያክል፡
፩: የመሰረተ ልማት ጥያቄ - መንገድ ፣መብራት፣ውሃ
፪: ለወጣቶች ስራ አጥነት ቅነሳ
፫: የህክምና ተቋማት ግብአት
፬: ኢንዱስትሪ
፭: የኑሮ ውድነት መቀነሻ ንድፈ ሃሳቦች እና የመሳሰሉትን ነው ።

ታድያ የከምባታ ህዝብ ጥያቄ ለምን አልተመለሰም???

የከምባታ ህዝብ ጥያቄ በዞኑ ባለሰልጣናት በመታፈኑ ምክንያት ነው። የህዝቡን ጥያቄ የጥቂት ግለሰቦች ጥያቄ ነዉ እያሉ ካድሬዎችን በጎጥ እያደራጁ እነሱ ግን ቤቶቻቸውን ይሰራሉ፣ ዘመዶቻቸውን ይቀጥራሉ፣ ያስቀጥራሉ ፣ ለበላይ አለቆች እያጎበደዱ ይሾማሉ።

የዞኑ መንግስት ለመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ ከመክፈል ባሻገር ለህዝቡ ምን ሰራ??
ህዝቡን በዘር ከፋፍሎ ከማጣላት ምን አተረፈ??
የከምባታ ጠምባሮን ዞን ከሌሎች ዞኖች ይቅር እና ከወረዳ ከተሞች በታች አድርጓታል

አንድ ቀን እሄ ኩሩ ህዝብ አሻፈረኝ ያለ እለት መግቢያህ ወዴት ይሆን ??? ቀን ሳለ ህዝብህን በቅንነት አገልግል።

መገኑ አሱ
ጡሙ በርጉን

ይናገራል ፎቶ !!
07/06/2020

ይናገራል ፎቶ !!

02/06/2020

የ65 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ማርገዛቸውን ሳያውቁ ወንድ ልጅ ተገላገሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑት 65 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋዋ ወይዘሮ ስንዱ ሰውነት ማርገዛቸውን ሳያውቁ ወንድ ልጅ በምጥ ተገላገሉ።

ወይዘሮዋ በጠላና በአነስተኛ ጉልት አትክልቶችን በመሸጥ የሚተዳደሩ ናቸው፤ ከብዙ ዓመታት በፊት ባጋጠማቸው ውርጃ ሳቢያ ልጅ ወልደው ለመሳም ሳይታደሉ ዕድሜያቸው መግፋቱን ይናገራሉ።

ልጅ ወልዶ ለመሳም ባለመታደላቸው ፈጣሪያቸው ልጅ እንዲሰጣቸው ሌት ተቀን ሲማፀኑ መኖራቸውንና በኋላም ተስፋ መቁረጣቸውን የሚናገሩት ወይዘሮ ስንዱ 'የወር አበባ ማየት ካቆምኩኝ ረጅም ጊዜ ተቆጥሯል' ይላሉ።

ግንቦት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ወይዘሮ ስንዱ ሆዴን አሞኛል፣ ይቆርጠኛል ሲሉ ወደስራቸው ለሄዱት ባለቤታቸው በስልክ ይናገራሉ።

ባለቤታቸው የተለመደ የጨጓራ ህመም እንዳለባቸው የሚያውቁት አባወራ "ፈሳሽ ነገርም አየሁ" ማለታቸው ቢያሰጋቸው ጎረቤቶቻቸው ወደ ጤና ጣቢያ እንዲወስዷቸው ያሳስባሉ።

ጎረቤቶችም ወይዘሮ ስንዱን ገርጂ አካባቢ ወደሚገኘው ድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ይወስዷቸዋል።

ምርመራ ያደረጉላቸው ሐኪሞች ወይዘሮዋ ነፍሰ ጡር እንደሆኑና ህመሙም ምጥ እንደሆነ በማስረዳት ዘጠኝ ወር ሙሉ ለምን የሕክምና ክትትል እንዳላደረጉ ይጠይቃሉ የወይዘሮዋ ምላሽ "ነብሰ ጡር መሆኔን አላውቅም" ነበር።

በዚህ ጊዜ የድል ፍሬ ጤና ጣቢያ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል የላካቸው ወይዘሮ ስንዱ በሆስፒታሉ ማዋለጃ ክፍል ወንድ ልጅ በምጥ ይገላገላሉ።

በአራስ ቤት ወንድ ልጃቸውን የታቀፉት ወይዘሮ ስንዱ ስለ ነብሰጡርነታቸው የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ በመሆኑ እስከወለዱበት ዕለት ድረስ ከባድ ስራዎችን ይሰሩ እንደነበር ነው የተናገሩት።

ስለ ባለቤታቸው እርግዝና የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረ የገለጹት ባለቤታቸው አቶ ሀብታሙ ገላን ሳያስቡት አባት በመሆናቸው ደስታቸውን ገልጸዋል።

የተወለደው ልጅ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ልጃቸውን በስስት እየተመለከቱ ነው የተናገሩት።

የእኚህ ሴት ልጅ የማግኘት ጉጉት የጎረቤቶቻቸውን ልጆች እንደራሳቸው ልጆች እንዲንከባከቡ አድርጓቸዋል። ከልጆች ጋር ያላቸው ቅርበትም የልጆቹን ልዩ ፍቅር አስገኝቶላቸዋል፤ ለዚህ ጎረቤቶቻቸውም ምስክሮች ናቸው።

ጎረቤቶቻቸው ወይዘሮ የሺ ጌታቸው እና አቶ ንጉሴ መኮንን ልጅ በጣም ይፈልጉና ይጓጉ ለነበሩት ወይዘሮ ስንዱ ፈጣሪ በመስተመጨረሻ ስለሰጣቸው በእጅጉ መደሰታቸውን ነው የተናገሩት።

ወይዘሮ ስንዱ የእርሳቸው የዕድሜ እኩያ መሆናቸውን የገለጹት የ64 ዓመቱ ተስፋ ሊቃውንት ተስፋ መስፍን ደግሞ በዚህ ዕድሜያቸው መውለዳቸውን "የፈጣሪ ድንቅ ስጦታ ነው" ብለውታል።

ምንጭ፡- ኢዜአ


የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዘናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

01/06/2020

የመሰረት ድንጋይ ከማስቀመጥ በቀጥታ ወደ ማስጀመር ላሸጋገረን አምላክ ክብር ምስጋና ይግባው።
#አላባ-አንጋጫ- አመቾ መንገድ
ማስጀመሪያ ዝግጅት መጀመሩን ሰማን

30/05/2020

Awesome kmabatta music video

29/05/2020

የአላባ-አንጋጫ- አመቾ መንገድ ጉዳይ ላይ ትዝብት አለኝ( ከደስታ ባለፈ)

ብዙ የደከሙ ዝም አሉ
አድፍጠው የጠበቁ እኛ ነን አሉ

ደግሞ ዞባዎች ተረሱ
እንዳልተቀጠቀጡ ድንጋይ እንዳልንተራሱ

ደግሞ ሌሎች አሉ
እየተዘጋጁ ምን እንደሚሉ

እሽ ቀጥሉ ደስኩሩን መቼስ ጆሮ ከመስማት አይሞላም።

እኔና ሕዝቤ ግን ለአምላክ ምስጋና አለን!!

ሰናይ ምሽት

የከምባታ ወርቅ - ሎዛ አበራGet to know Loza Abera የሎዛ አበራና ድንቅ ብቃትEthiopian national, Loza Abera's Birkirakara club goalscoring s...
26/05/2020

የከምባታ ወርቅ - ሎዛ አበራ

Get to know Loza Abera የሎዛ አበራና ድንቅ ብቃት

Ethiopian national, Loza Abera's Birkirakara club goalscoring statistics.
30 league goals in 14 matches
3 goals in Super Cup final
1 goal in international friendly
Total- 34 goals in 16 matches
(2.125 goals/game)

25/05/2020
25/05/2020

አላማችን የጭቁኖች ድምፅ መሆን ነው!! KV

25/05/2020

ፍትህና ርትዕ ስጎድል ለሕዝብና መንግስት እንጠቁማለን!! ቅር የሚለው ካለ ሕዝብንና መንግሥትን በትጋት ያገልግል!!

25/05/2020

ስለ ከምባታ ሕዝብ ግፍ እና ኢፍትሀዊነት ዝም አንልም!!

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kembatta Voice-KV-ድምፀ ከምባታ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share