TAZA ታዛ

TAZA ታዛ This is Taza's Magazine official page.

በደራሲ ጥላሁን ጣሰው የተጻፈው ``Emperor Menilik 2nd – The military strategist and diplomat who changed the course of history`` የተባ...
14/10/2020

በደራሲ ጥላሁን ጣሰው የተጻፈው ``Emperor Menilik 2nd – The military strategist and diplomat who changed the course of history`` የተባለው መጽሐፍ ለገበያ ቀርቧል። ደራሲው ከዚህ በፊት ስድስት መጻህፍት የነበሯቸው ሲሆን፤ አምስቱ በአማርኛ የተጻፉ፤ አንዱ ደግሞ በእንግሊዘኛ የተጻፈ ነው። ደራሲው ያሁኑን መጽሐፋቸውን የጻፉት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ነው። በኢትዮጵያ ለገበያ የበቃው ይህ መጽሐፍ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ በአማዞን የመጽሐፍ መሸጫ ድረ ገጽ በኩል የሚከፋፈል ይሆናል።

የአሳዬ ደርቤ አዲስ መፅሀፍአሳዬ ደርቤን ወግ እያዋዛ ሲፅፍ እናውቀዋለን:: ብዕሩን ማሸሞንሞን ይችልበታል፣ በዛው ልክ "ሲጠላህ ይራገጣል" ይሉታል ተቀናቃኝ ብዕረኞቹ ፣  ከንፈር ለነከሰባቸው...
10/10/2020

የአሳዬ ደርቤ አዲስ መፅሀፍ

አሳዬ ደርቤን ወግ እያዋዛ ሲፅፍ እናውቀዋለን:: ብዕሩን ማሸሞንሞን ይችልበታል፣ በዛው ልክ "ሲጠላህ ይራገጣል" ይሉታል ተቀናቃኝ ብዕረኞቹ ፣ ከንፈር ለነከሰባቸው አፈር ድሜ ሲያስግጥም ትጉህ ነው:: የሚያስጠሉትን ነፍሳት በሽሙጥ ቁም ስቅል ያሳያል:: ሆኖም ግሩም ደራሲ ነው። ከዚህ በፊት "እስኪነጋ ድረስ" እና "ጎዳናው እስኪቋጭ" የተባሉ መፅሀፍትን አሳትሟል። አዲሱ ``የሐሳብ ቀን- ዘሎች`` የተሰኘ ስራውን በዚህ ሣምንት አሣትሟል። ዘጠኝ ጥያቄዎችን አቅርቤለት እንደሚከተለው መልሶልኛል።

1ኛ መፃፍ የምታዘወትርበት ጊዜ

ከቡና በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ሠ0ት
2ኛ ደጋግመህ ብታነበው የማትሰለቸው ደራሲ

አዳም ረታ ከሀገር ዉስጥ
ሶስትዮቭስኪ ከሀገር ውስጥ

3ኛ በስነ ጽሁፍ ዛር ታምናለህ? ካመንክ መቼ ይከሠትልሀል ?
አምናለሁ ማህበራዊ ጉድለት ስሰማና ሳይ

4ኛ አሁን ምን መጽሐፍ እጅህ ላይ አለ? ማለትም ከሠሞኑ ምን እያነበብክ ነው ?
Homo Deus

5ኛ የሚመስጥህ ሀሳብ
ግለ ታሪክ

6ኛ የምትወደው አምባገነን መሪ
ፕሬዚዳንት መንግስቱ ሀይለማርያም

7ኛ ዘረኝነት ስነ ፅሁፍን ይጎዳል? ፅሀፊ ዘረኛ ቢሆንስ ?
አለማቀፍ ሀሳብ ማራገብ ነው ያለበት ደራሲ ፣ ጥበት ስነ ፅሁፍን ያቀጭጫታል።

8ኛ አሳዬ አንተ ዘረኛ ነህ? ሰዎች ሲሉህ ስለምሰማ ነው፡፡
እኔም እሠማለሁ፡፡ ስለ ራስ ብሄር መገፋት እና መበደል መጮህ ዘረኝነት አያስብልም፡፡ ብሄርህ ሲበድልና ሲጨቁን ነው መጥፎነቱ ስለዚህ አይደለሁም፡፡

9ኛ መጻፍ ገንዘብ ያስገኛል?
በጭራሽ ! እኔ የምፅፈው ለገንዘብ አይደለም :: እርካታ ስላለ ነው ፅሁፍ ውስጥ ፣ እንደውም አክሳሪ ነው። በአዟሪ ቁጥጥርና እያስገደደህ ትፅፋለህ። ዋጋ ላይ ከብሩ ቀጥሎ ነጥብ ከነጥብ ቀጥሎ ሣንቲም ካልፃፍክ ይታደምበሀል።
እንዳውም ይሄ የመጨረሻ የማሣትመው መፅሀፌ ሳይሆን አይቀርም።

የ2020 የኤምቲቪ ኤሚ አዋርድ እጩዎች ይፋ ሆነዋልየዘንድሮው የአምቲቪ ኤሚ አዋርድ እጩ ሙዚቀኞች ይፋ ሆነዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊው  አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ)፣ ሌዲ ጋጋ፣ ሮዲ ሪች፣ ጀስ...
07/10/2020

የ2020 የኤምቲቪ ኤሚ አዋርድ እጩዎች ይፋ ሆነዋል

የዘንድሮው የአምቲቪ ኤሚ አዋርድ እጩ ሙዚቀኞች ይፋ ሆነዋል። ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ)፣ ሌዲ ጋጋ፣ ሮዲ ሪች፣ ጀስቲን ቢበር፣ ካርዲ ቢ፣ ማይሊ ሳይረስ… በእጩዎቹ ዝርዝር ውስጥ ከተካተቱት ይገኙበታል።
በህዝብ ምርጫ አሸናፊው የሚወሰንለት ይህ የሽልማት ስነስርዓት፤ ማንኛውም ሰው ደምጹን ወደ mtvema.com በመግባት ለመረጠው ድምጻዊ መስጠት ይችላል።
የዘንድሮ እጩዎች ከታች የተዘረዘሩትን ይመስላሉ፡-

ምርጥ ቪዲዮ

Billie Eilish – "everything i wanted"
Cardi B ft. Megan Thee Stallion – "WAP"
DJ Khaled ft. Drake – "POPSTAR"
Karol G ft. Nicki Minaj – "Tusa"
Lady Gaga, Ariana Grande – "Rain On Me"
Taylor Swift – "The Man"
The Weeknd – "Blinding Lights"

ምርጥ አርቲስት

Dua Lipa
Harry Styles
Justin Bieber
Lady Gaga
Miley Cyrus
The Weeknd

ምርጥ ሙዚቃ

BTS – "Dynamite"
DaBaby ft. Roddy Ricch – "Rockstar"
Dua Lipa – "Don’t Start Now"
Lady Gaga, Ariana Grande – "Rain On Me"
Roddy Ricch – "The Box"
The Weeknd – "Blinding Lights"

ምርጥ ጥምረት
BLACKPINK, Selena Gomez – "Ice Cream"
Cardi B ft. Megan Thee Stallion – "WAP"
DaBaby ft.. Roddy Ricch – "Rockstar"
Justin Bieber ft. Quavo – "Intentions"
Karol G ft. Nicki Minaj – "Tusa"
Lady Gaga, Ariana Grande – "Rain On Me"
Sam Smith, Demi Lovato – "I’m Ready"

ምርጥ ፖፕ

BTS
Dua Lipa
Harry Styles
Justin Bieber
Katy Perry
Lady Gaga
Little Mix

ምርጥ ቡድን

5 Seconds of Summer
BLACKPINK
BTS
Chloe x Halle
CNCO
Little Mix

ምርጥ አዲስ ድምጻዊ

BENEE
DaBaby
Doja Cat
Jack Harlow
Roddy Ricch
YUNGBLUD

ምርጥ አድናቂዎች ያሏቸው

Ariana Grande
BLACKPINK
BTS
Justin Bieber
Lady Gaga
Taylor Swift

ምርጥ የላቲን ድምጻዊ

Anuel AA
Bad Bunny
J Balvin
Karol G
Maluma
Ozuna

ምርጥ የሮክ ድምጻዊ

Coldplay
Green Day
Liam Gallagher
Pearl Jam
Tame Impala
The Killers

ምርጥ የሂፕሃፕ ድምጻዊ

Cardi B
DaBaby
Drake
Eminem
Megan Thee Stallion
Roddy Ricch
Travis Scott

ምርጥ ኤሌክትሮኒክ ድምጻዊ

Calvin Harris
David Guetta
Kygo Marshmello
Martin Garrix
The Chainsmokers

ምርጥ አማራጭ/ ድብልቅ ድምጻዊ

blackbear
FKA twigs
Hayley Williams
Machine Gun Kelly
The 1975
twenty one pilots

ቪዲዮ ለበጎ ምግባር

Anderson .Paak – "Lockdown"
David Guetta & Sia – "Let’s love"
Demi Lovato - "I Love Me"
H.E.R. – "I Can’t Breathe"
Jorja Smith – "By Any Means"
Lil Baby – "The Bigger Picture"

ምርጥ ተጽእኖ

AJ Mitchell
Ashnikko
BENEE
Brockhampton
Conan Gray
Doja Cat
Georgia
Jack Harlow
Lil Tecca
Tate McRae
Wallows
YUNGBLUD

ምርጥ የመድረክ ቨርቹዋል

BTS – Map Of The Soul Concert Live Stream
J Balvin – Behind The Colores Live Experience
Katy Perry @ Tomorrow Land – Around The World
Little Mix – UNCancelled
Maluma – Papi Juancho Live
Post Malone - Nirvana Tribute

የ2020 ኤምቲቪ ኤማ ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ Nov 8, 2020 የሚተላለፍ ይሆናል።

ታዛ መጽሔት በቅጽ 4 - ቁጥር 38 እትሟ ዋና ትኩረቷን በሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ላይ አድርጋ ቅዳሜ ለገበያ ትበቃለች፡፡ ከውስጥ ገጾች ትንሽዋን ቅምሻ እነሆ፡-‹‹ታማኝ በየነ››"...አንድ ጊ...
02/10/2020

ታዛ መጽሔት በቅጽ 4 - ቁጥር 38 እትሟ ዋና ትኩረቷን በሙዚቃው ንጉስ ጥላሁን ላይ አድርጋ ቅዳሜ ለገበያ ትበቃለች፡፡ ከውስጥ ገጾች ትንሽዋን ቅምሻ እነሆ፡-
‹‹ታማኝ በየነ››
"...አንድ ጊዜ ለህዝብ ለህዝብ ስንወጣ፤ “ጉብል” የሚለው አልበሙ ለገበያ ከወጣ በኋላ ነው። በወጣ በሳምንቱ ነው መሰለኝ እኛም የወጣነው። ከወጣን ሶስት ወር ከሆነን በኋላ በአጋጣሚ ሞንትሪያል የሚባል ከተማ ካናዳ ውስጥ ሆነን፤ ነዋይ ደበበ ወደሀገር ቤት ይደውላል። ደውሎ ሲያወራ ስለካሴት ስራ አንስቶ ሲጠይቅ፤ ኬኔዲ መንገሻ አዲስ አልበም ማውጣቱን ይሰማል። እኛ ከወጣንና የጥላሁን አልበም ከወጣ ከሶስት ወር በኋላ የኬኔዲ አልበም ይወጣል። የኬኔዲ አልበም በጣም ይገንናል፤ በጣም ይወደዳል። እናም ነዋይ ደበበ ስልኩን ጨርሶ ሲመጣ፤ ወደ ጥላሁን ቀርቦ “ጋሼ ጋሼ፤ እህ… ኬኔዲ የሚባል ዘፋኝ መጥቶ ካሴትህን አጠፋው አሉ። በጣም ጥሩ ሆኖለታል የእሱ፤ እየተሰማ ነው። ያንተን እየሸፈነው ነው” አለው። “ታዲያ ዘመኑ ሆኖ ይሆናላ፤ የእሱ ዘመን ሊሆን ይችላል። እኔ እኮ ብዙ ዘፈንኩ፤ ይሄ እኮ ያለ ነገር ነው” አለው። እንደቀላል ነገር ነው ያየው። ለነገሩ ነዋይም ሳያስበው ነው ያለው። ነገር ግን ጥላሁንን ምንም አልተሰማውም። ይሄ ዘመኑ የፈጠረው እና ዘመኑ የተቀበለው ሰው ነው፤ እኔም መቀበል አለብኝ ብሎ ነው የሚያስበው። እንዲህ መጣብኝ… እንዲህ ልሆን ነው… የሚል ስሜት የለውም..."

ሰአሊ ሰሎሜ ሙለታ ትባላለች። በAddis fine Art ጋለሪ ስዕሎቿ ይታዩላታል። "እንስትነትና ተፈጥሮ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው" የምትለው ሠሎሜ፤ የፈርኒቸር ቤት ሽያጭ ባለሙያ...
21/09/2020

ሰአሊ ሰሎሜ ሙለታ ትባላለች። በAddis fine Art ጋለሪ ስዕሎቿ ይታዩላታል። "እንስትነትና ተፈጥሮ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው" የምትለው ሠሎሜ፤ የፈርኒቸር ቤት ሽያጭ ባለሙያ ነበረች። ወደ ስዕል የሙሉ ጊዜ ስራ ከመግባቷ በፊት ከፈርኒቸር የሽያጭ ስራ ያጠራቀመቸውን ገንዘብ ቀለም ትገዛበት ነበር። ''ከልብስና ጫማ ይልቅ ገንዘቤ ቀለም ላይ ይውል ነበር" የምትለው ሠሎሜ ስዕልን የሙሉ ጊዜ ስራ ካደረገች በኋላ 4 ጊዜ የብቻ ኤግዝቢሽን ላይ አቅርባለች። "ስትስይ ምን ያነሳሳሻል?" ብዬ ጠይቄያት
"ጉንጬን እስኪደክመኝ የማኝከው ቆሎና 7 ሲኒ ቡና ብላኛለች። ከመፅሐፍት በተለይም ራዕይ ዮሀንስን ለምናቧ የምታነብ ሲሆን አንድን ስዕል እስከ 150,000 ብር ትሸጣለች። አርአያዎቿ ወንድ ባለብሩሾች ሲሆኑ ከውጭ ሀገር ሠዐሊ ጉስታቭ ክሊምትን ከሀገር ውስጥ ሠዐሊ ተስፋዬ ኡርጌሳ ነው። "ስለ ሴቶች ወንዶች ይስላሉ፣ እሱ ከውጭ ወደ ውስጥ ነው ፤ እኔ ግን ስለ ሴቶች ብሩሹ ሸራ ላይ ሲያርፍ ውበቱ የሚፈልቀው ከውስጥ ነው" ብላኛለች። ስራዋን ማየት የምትሹ እና በእናትነት መመሰጥ የምትፈልጉ ቦሌ ወደ ፋይን አርት አቅኑና ተደሰቱ። ዘወትር ከሠኞ እስከ ቅዳሜ ከጧቱ 4:00 እስከ 12:00 ሰዓት

19/09/2020
ባራክ ሁሴን ኦባማ " የቃልኪዳን ምድር" (A PROMISED LAND) ብሎ የተሰየመ አዲስ መፅሀፍ አሳትሟል፡፡Yes we can በሚለው የምርጫ ቅስቀሳ መፈክሩ በመላው ዓለም ንቅናቄ መፍጠር ች...
18/09/2020

ባራክ ሁሴን ኦባማ " የቃልኪዳን ምድር" (A PROMISED LAND) ብሎ የተሰየመ አዲስ መፅሀፍ አሳትሟል፡፡

Yes we can በሚለው የምርጫ ቅስቀሳ መፈክሩ በመላው ዓለም ንቅናቄ መፍጠር ችሏል። ኦባማ አሜሪካንን ለመጀመሪያ ጊዜ ከበላይ ሆኖ የመራ ጥቁር ፕሬዝደንት ነው። ባራክ ሁሴን ኦባማ h8 ተከታታይ ዓመታት ሀገሪቱን ሲመራት ከጉድለቴም ከብርታቴም ጨልፌ፤ ሀገሪቱ ከክፍፍል ተርፋ ለሁሉም የሚሰራ ዲሞክራሲ ማስፈን እንደሚቻል ፅፌያለሁ ብሎ በፌስ ቡክና በትዊተር ገፁ ነግሮናል። አምስተኛው እንደሆነ የተነገረው ይህ መፅሀፍ እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ የኦሳማ ቢንላደንን ግድያ ጨምሮ የመጀመሪያ የስልጣን ዘመኑን ይዳስሳል። የቀድሞው ፕሬዚደንት ትዊተር ገፁ ላይ " ለወጣቶች ዓለምን ለማሻሻል የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ያነሳሳል " ያሉት መፅሀፋቸው የሠሞኑ ሶሻል ሚድያ መነጋገሪያ ነው።

መክሊት፡የደራሲ እንዳለጌታ የፈጠራ ትሩፋት የሆነው “መክሊት” የተሰኘ የአጭር ተረኮች መጽሐፍ ህትመቱን አጠናቅቆ ለገበያ ቀርቧል። ደራሲው በ1996 ዓ.ም. ከታተመው “ከጥቁር ሰማይ ስር” ከተ...
16/09/2020

መክሊት


የደራሲ እንዳለጌታ የፈጠራ ትሩፋት የሆነው “መክሊት” የተሰኘ የአጭር ተረኮች መጽሐፍ ህትመቱን አጠናቅቆ ለገበያ ቀርቧል። ደራሲው በ1996 ዓ.ም. ከታተመው “ከጥቁር ሰማይ ስር” ከተሰኘው የመጀመሪያው የአጭር ልቦለድ ስብስብ መጽሐፉ አንስቶ አሁን እስከታተመው “መክሊት” የተሰኘ የአጫጭር ትረካዎች ስብስብ ድረስ በድምሩ አስራ ሶስት መጻህፍትን ለአንባቢያን አቅርቧል። በአስራ ስድስት ዓመታት ውስጥ አስራ ሶስት መጽሐፍ ለማሳተም መቻሉ፤ የደራሲ እንዳለጌታ ከበደን ታታሪነት ያሳያል።

በእታፍዘር አታሚዎች ለህትመት የበቃው ይህ መጽሐፍ በ260 ገጾች የቀረበ ሲሆን፤ የገበያ ዋጋውም አንድ መቶ ሃያ ብር ብቻ ነው። በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ታሪኮች ባለ ብዙ ዘውጎች ናቸው። ከምንኖርበት ዓለም ጋር የሚቀራረቡ እውናዊ ተረኮች፣ ልዩ የፈጠራ ችሎታ የተስተዋለባቸው ምናባዊ ተረኮች፣ ሃገርኛ መልክ የያዙ የተውሶ (Adaption) ተረኮች፣ እንዲሁም በኑሯችን ውስጥ ባሉ መስተጋብሮች ላይ ልዩ ምልከታ ያከላቸው ሞጋች እና ተሳላቂ ተረኮች ተካትተውበታል።

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ከዚህ ቀደም “ዛጎል” ፣ “ደርሶመልስ” ፣ “እምቢታ” ፣ “ምሳሌ” ፣ “ከጥቁር ሰማይ ስር” ፣ “የመኝታ ቤት ምስጢሮች” ፣ “ጽላሎት” ፣ “ልብ ሲበርደው” ፣ “ኬር ሻዶ” ፣ “ማዕቀብ” ፣ “በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ሥራዎቹ” ፣ “ያልተቀበልናቸው”… የሚባሉ አንቱታ ያስገኙለትን መጻህፍት በግሉ ያሳተመ ሲሆን፤ ከተለያዩ ደራሲያን ጋር በመሆንም ተጨማሪ መጻህፍትን አሳትሟል። አሁን ደግሞ “መክሊት” የተሰኘውን የአጭር ተረኮች ስብስብ መጽሐፍ እንካችሁ ብሎናል። መልካም ንባብ!!

ታዛ መጽሔትን ቅዳሜ ነሐሴ 30 ላይ ይጠብቋት። እንደተለመደው በውብ ጥንቅሮቿ ተሰናድታ፣ ጥንቅቅ ተደርገው የተከሸኑ ፅሁፎች፣ ዜናዎች፣ ግጥሞች፣ ልቦለዶች፣ ምስሎች… ይዛ ወደ እናንተው ወደክቡ...
03/09/2020

ታዛ መጽሔትን ቅዳሜ ነሐሴ 30 ላይ ይጠብቋት። እንደተለመደው በውብ ጥንቅሮቿ ተሰናድታ፣ ጥንቅቅ ተደርገው የተከሸኑ ፅሁፎች፣ ዜናዎች፣ ግጥሞች፣ ልቦለዶች፣ ምስሎች… ይዛ ወደ እናንተው ወደክቡራን አንባቢዎቻችን ትቀርባለች።

19/08/2020

ዜና እረፍት...
የ Ethiopian Idol መሥራች ከእዚህ ዓለም በሞት ተለየ ፦
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የነበረውን Ethiopian Idol በማዘጋጀት እና በመላው አውሮፓ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎችን ፕሮሞት በማድረግ የሚታወቀው ይስሃቅ ጌቱ በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
አቶ ይስሃቅ የሦስት ልጆች አባት ነበር
ምንጭ፦ ጌጡ ተመስገን
:=>> የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል ለአቶ ይስሃቅ ጌቱ ቤተሰብ ወዳጅ እና አድናቂዎች መጽናናትን ይመኛል።

የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል በአንጋፋው አርቲስት፤ ድምጻዊ ሐጎስ ገብረህይወት ህልፈት የተሰማውን ሐዘን ለመግለጽ ይወዳል። ከዘጠኝ በላይ የሙዚቃ አልበሞችን በመስራት አንቱታ ያተረፉት አርቲስት...
17/08/2020

የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል በአንጋፋው አርቲስት፤ ድምጻዊ ሐጎስ ገብረህይወት ህልፈት የተሰማውን ሐዘን ለመግለጽ ይወዳል። ከዘጠኝ በላይ የሙዚቃ አልበሞችን በመስራት አንቱታ ያተረፉት አርቲስት ሐጎስ ገብረህይወት፤ ህልፈታቸው የተሰማው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። ለወዳጅ አድናቂዎቻቸው እና ለቤተሰባቸው መጽናናቱን እንመኛለን፤ አርቲስ ሐጎስ ገብረህይወት ነብስ ይማር!!

Taza 3 - 35Editors Note:ቀዳሚ-ቃልባሳለፍነው ወር ትልቅ የሚዲያ አጀንዳዎች ሆነው ካለፉ ርዕሰ-ጉዳዮች ውስጥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ ውሃ ሙሌት ዜና ነው...
11/08/2020

Taza 3 - 35
Editors Note
:
ቀዳሚ-ቃል

ባሳለፍነው ወር ትልቅ የሚዲያ አጀንዳዎች ሆነው ካለፉ ርዕሰ-ጉዳዮች ውስጥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ደረጃ ውሃ ሙሌት ዜና ነው። ይህ ዜና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የምስራች ሆኖ አልፏል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በግድቡ ዙሪያ በፖለቲካ ኃይሎች መካከል ልዩነቶች ታይተዋል። ይህ ልዩነት ግን እስካሁን በተጓዘበት መንገድ ሊቀጥል አይገባም። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያንን አንድ ሊያደርጉና በአንድ ሐሳብ ዙሪያ ሊያሰባስቡ ከሚችሉ ጥቂት ነገሮች አባይ አንዱ ነውና። ሌላው በግድቡ ላይ ትንሽም ቢሆን ገንቢ አስተዋጽኦ የነበራቸውን ሰዎች ተገቢውን ከበሬታ ልንሰጥ ይገባል። ግድቡን አቅዶ ካስጀመረው፤ ገንብቶ እስካጠናቀቀው ድረስ ያሉት ሁሉም ተሳታፊ አካላት ለፕሮጀክቱ ከፍፃሜ መድረስ የራሳቸውን የሆነ ገንቢ ሚና ስለተወጡ ምስጋናው ለሁሉም ቢሆን መልካም ነው።

የሚዲያዎች ገንቢ ሚና በሃገራችን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይም የበለጠ እየጎለበተ ሊሄድ ይገባል። ዳር እና ዳር ሆኖ ከመጯጯህ ባለፈ ሚዲያዎች ራሳቸውን በሃገራችን ለሚፈጠሩ መልካም ነገሮች እንደመነሻ እና ማነሳሻ አስበው፤ ጠንክረው ቀና የሆነ ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል። ይህ ተግባር እንደባህል ከተወሰደ ለአጠቃላይ የሃገሪቱ መፃኢ ዕድል ሰናይ የሆነ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ለመጪው ትውልድም ጥላቻን፣ መናናቅን እና ስድብን ከማስተማር ይልቅ፤ የጨዋ ባህላችንን አርአያ በመከተል መልካም መልካሙን እና ለሃገርም ለራስም ጠቃሚ የሆነውን ባህል ወልማድ ማስተማሩ እና ማሳወቁ በጎ ነው። ያልተዘራ አይበቅልም እንዲሉ አበው፤ ዛሬ የተሰራው ነውና ለነገ ፍሬ አፍርቶ ውጤቱ የሚታየው፤ ከስር ከስሩ በተገቢው መንገድ ዛሬን የታነጸ ትውልድ ነው ነገ ለሃገርም ለወገንም ስም አስጠሪ እና አኩሪ የሚሆነው።

ኢትዮጵያ ከብዙ ዘመናት አንስቶ ለአካባቢ እና ለአየር ንብረት ጤናማነት በመቆርቆር የምትታወቅ ሀገር ናት። ይህ መቆርቆሯ ታዲያ በሃገር ውስጥ ብቻ የሚታይ ሳይሆን፤ በመሪዎች ደረጃም የአፍሪካን አህጉር ወክላ በዓለም መድረክ ስለከባቢ አየር ጥበቃ የሰበከች የተሟገተች ነች። ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ “አረንጓዴ አሻራ” የተሰኘ መርሃግብር ተቀርጾ፤ ከፍተኛ የሆነ የችግኝ ተከላ እንቅስቃሴ በመላው ሃገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ ተግባር በሃገራችን የከባቢ አየር ለውጥ ላይ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን ከባቢ አየር ለውጥ ላይ ጥሩ ሚና ስለሚጫወት፤ ይበል ይቀጥል የሚያስብል ስራ ነው። አሁን የምንተክላቸው ችግኞች ለመጪው ዘመን ትውልዶቻችን ንጹህ አየርን የምናቀብልባቸው ደኖቻችን ናቸው።

እርግጥ ነው በሃገራችን ውስጥ ቁጥራቸው አያሌ የሆነ መሻሻል እና በበጎ መልኩ መለወጥ ያለባቸው ነገሮች አሉ። ይህ እንዲሆን ግን ከፍተኛ ልፋት እና ጥረት ይጠይቃል። ታዲያ ሁሉንም ነገር ለማሳካት እያንዳንዱን አጋጣሚ ለበጎ ነገር ለማዋል ፍላጎት ሊኖር የተገባ ነው። አዲስ እና ያልተጠበቀ አጋጣሚ በተከሰተ ቁጥር ተሯሩጦ የራስን ፍላጎት ብቻ ለማሳካት መሞከር ሌላውን እስካልጎዳ ድረስ ክፋት የለውም። አጋጣሚዎችን በሌሎች ላይ ለማትረፍ እና ብዙ ሰዎችን ጎድቶ ራስን ለመጥቀም መሯሯጥ ግን ለትዝብት የሚዳርግና የሚያስገምት ተግባር ነው። እናም አጉል ራስ-ወዳድነትን ለማናችንም ስለማይጠቅም ወደኋላ አቆይተን፤ ስለጋራ ፍላጎታችን፣ ስለጋራ ጥቅማችን፣ አብረን ከፍ ከፍ ስለምንልበት ጉዳይ… እያሰብን እየሰራን ቀጣዩን ዘመናችንን ብሩህ እናድርገው።

ወርሃዊዋ ታዛ መጽሔት እንደተለመደው አጓጊ የሆኑ ጽሁፎቿን ይዛ ቀጠሮዋን ሳታዛንፍ ከተፍ ብላለች። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ
07/08/2020

ወርሃዊዋ ታዛ መጽሔት እንደተለመደው አጓጊ የሆኑ ጽሁፎቿን ይዛ ቀጠሮዋን ሳታዛንፍ ከተፍ ብላለች። መልካም ንባብ ይሁንላችሁ

23/06/2020

የፍጻሜው መጀመሪያ ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግዙፍ የግድብ ፕሮጀክት ለመገንባት አስባ በይፋ ሥራ ከጀመረች ዘጠኝ ዓመት ሞላት። “የታላቁ ህዳሴ ግድብ” የተሰኘው ግንባታዋ ከብዙ ውጣ ...

ታዛ መጽሔት እንደተለመደው አምራ ደምቃና አሸብርቃ፤ ጊዜዋን ጠብቃ ቅዳሜ ለገበያ ልትበቃ መሰናዶዋን አጠናቅቃ እነሆ በ34ኛ አእተትመም መጥታለች። በውስጥ ገጾቻችን የክዋኔ ጥበብ ባለሞያዎች በ...
19/06/2020

ታዛ መጽሔት እንደተለመደው አምራ ደምቃና አሸብርቃ፤ ጊዜዋን ጠብቃ ቅዳሜ ለገበያ ልትበቃ መሰናዶዋን አጠናቅቃ እነሆ በ34ኛ አእተትመም መጥታለች። በውስጥ ገጾቻችን የክዋኔ ጥበብ ባለሞያዎች በዘመነ-ኮሮና እያጋጠማቸው ስላለው ችግር እና፤ ስለሃገራችን ማህበረዊ ወኪነጥበባዊ እንዲሁም ስፖርታዊ ጉዳዮች ዳሰሳ አድርገናል። ያንብቧት ይወዷታል ይዝናኑባታል ይማሩባታል።

መንዙማ እና ኪነ-ጥበብByዳዊት አርአያ:የምትከተላቸውን ሃይማኖቶች በቀደምቶቹ ነቢያት የተሰበከች ሀገር ናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ አጥምቆ ክርስትናን ሰብኮ የላከው ከመጀመሪያዎቹ ...
17/06/2020

መንዙማ እና ኪነ-ጥበብ

Byዳዊት አርአያ

:

የምትከተላቸውን ሃይማኖቶች በቀደምቶቹ ነቢያት የተሰበከች ሀገር ናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ አጥምቆ ክርስትናን ሰብኮ የላከው ከመጀመሪያዎቹ ነቢያት አንዱ ነው። ነቢዩ መሐመድ እስልምናን ከማስፋፋታቸው በፊት የምእመናኑን ህይወት ከሞት ጠብቀው፤ የአማኞችን ቁጥር ያበዙት ወደ ሀበሻ ንጉሥ አስሐባዎችን ልከው ነበር። ከዓለም ቀድመው እስልምናን ከተቀበሉት ዋነኞች ተርታ የምትነኝ ሀገር ህዝቦች ነን። ቀድማ እስልምናን የተቀበለችው እሙ አይመን ኢትዮጵያዊት ናት። የአዛን ጥሪን ለዓለም ያስተማረው ቢላል የሐበሻ ደም ያለው ቆራጥ አማኝ ነው።

ኢትዮጵያ የሁሉም ሃይማኖቶች ቀደምት መኖሪያ ትሁን እንጂ፣ ተቀባይ ብቻም አልነበረችም። የተቀበለችውን ከማንነቷ ጋር ቀይጣ የራሷን ቀለም ትሰጠዋለች። የሐበሻ ሙስሊም የራሱ ቀለም አለው። የራሱ ብቻ የሆነ፣ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ብቻ ከቀረው ሙስሊም ወንድሙ የሚለይበት ማንነት አለው። የራስ ብቻ ባህርይ ባለቤት ነው።

መንዙማ የዚህ ነባራዊ እውነት ማሳያ እንደሆነ የሚያምኑ ጥቂቶች አይደሉም። እንደ ሁሉም የራሳችን እሴቶች ሁሉ በቅጡ ካልተጠኑት፣ በትኩረት ካልተመረመሩት መካከል የሚመደበው መንዙማ ‘ኢትዮጵያዊ ብቻ ነው’ ብለው የሚከራከሩ እንዳሉ ሁሉ፤ የለም ሁሉም ሙስሊም የሚጋራው ሀይማኖታዊ ተግባር ነው የሚሉም አሉ። ምሁራዊ ክርክሩን ለመስኩ ባለሙያዎች እና ለእምነቱ ልሂቃን ትተን በመንዙማ እና የመንዙማ ባህርይ ባላቸው የኪነ-ጥበብ ሥራዎች ዙሪያ ጥቂት ለማለት እንሞክር።

ትርጓሜ

መንዙማ ቃሉ አረብኛ ነው። ‘ነዘመ’ ከሚለው የአረብኛ ሥርወ-ቃል የመጣ ነው። ነዘመ ማለት ገጠመ ማለት ነው። መንዙማ ዝርው ያልሆነ፣ (ግጥም) ማለት ነው። በአረቦች መንዙማ ትምህርታዊ ጉዳዮችን ለማስተላለፍ የሚያገለግል ግጥም ማለት ነው። በእንግሊዝኛ ‹Deductive Poetry› የሚለው ነው። ለምሳሌ ሰዋሰውን ለማወቅ በግጥም ቢጠቀሙ መንዙማ ይባላል።

በሃገራችንም ለነብዩ ሙሐመድ ፍቅር፣ ክብር፣… ማሳያ የሚገጠሙ ግጥሞች ናቸው። አላህን ለማወደስ የሚደረገውም ይካተታል። ደጋግ ሰዎችን ለማወደስ የሚደረገውም በዚሁ የሚካተት ነው።

በአብዛኛው ወንዶች ሲከውኑት ይስተዋል እንጂ ሴቶችም ተሳትፈውበታል። ከከበሮ ወይም ድቤ በስተቀር የሙዚቃ መሳሪያ እንደማያጅበው ደጋግመን ብንሰማም በበገና ሳይቀር የታጀቡ መንዙማዎች መኖራቸውን አጥኚዎች ይገልጻሉ። ባህሩ ሰፊ ነው። ለማወቅ የሻተ ከቆፈረ ብዙ የሚያፍስበት…

ለስለስ ያለ ዜማ ያለው መንዙማ በርካታ መልእክቶች ይተላለፉበታል። ሐይማኖታዊ ትምህርቶች፣ አፈንጋጭን ከስሁት ተግባሩ እንዲታቀብ የሚገስጹ ኃይለ-ቃሎች፣ የማጽናኛ-የማበረታቻ ሐሳቦች ይካተቱበታል። ከበድ ያሉ ሐይማኖታዊ ፍልስፍናዎች እና ነቢዩን፣ ፈጣሪን እና በእምነቱ ትልቅ ቦታ ያላቸውን ለማወደስ ጥቅም ላይ ይውላል።

ስንኞቹ ሙሉ በሙሉ በአረብኛ ቋንቋ የተሰናኙ ሊሆኑ ይችላሉ። የአማርኛ እና የአረብኛ ቅይጥ የሆኑት ግን እጅግ የተለመዱት ናቸው። በተለይ ትንሽ ቀደም ያሉት መንዙማዎች በሀይማኖቱ ላቅ ያለ ደረጃ ለደረሱት የሚተዉ ነበሩ። በቅብብል ይዜማል። ከመሃል ስንኙን የሚደረድረውን ሰው የሚያደምጡት በመቀበል ያግዙታል። መልእክት ካዘሉት ስንኞች የሚከተለውን አዝማች በጭብጨባ እያጀቡ በህብረት ያዜሙታል። አጠር ያሉ ስንኞች አንድን መልእክት የሚያስተላልፉ ከሁለት እስከ አራት የግጥም መስመሮች በመንዙማ ይዘረዘራሉ።

መቼ ተጀመረ?

መንዙማ መች ጀመረ ከማለት ግጥም የሚባለው ጥበብ መች ጀመረ የሚለውን ማየቱ መቅደም አለበት። ግጥም መች ጀመረ ሲባል ደግሞ የሰው ልጅ በምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ወደማለት እየደረሰ ነው። ግጥም ከሰው ልጅ ጋ አብሮ ረጅም ዘመን ይኖራል።

እስልምና በመካ ከመነሳቱ በፊት አረቦች በግጥም ችሎታቸው በጣም የተደነቁ ነበሩ። በሃገራችን ደግሞ ከእስልምና ወደሀገራችን መግባት ጋር የሚያያዝ ነው። (በጥናት የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም)

በአረቡ ዓለም ጽሑፋቸው ከሃገር ሀገር የሚሸጋገር ‘ማዲሆች’ አሉ። ‘አልወራቂ’፣ ‘’ቡሰይሪ ‘ጦራኢፊ’… የታወቁ ገጣሚያን ናቸው።

ቡሰይሪ ግብጻዊ ሲሆን 13ኛው ክፍለዘመን የኖረ እስከዛሬም ግጥሙ ዘመን ተሻግሮ የመጣ ገጣሚ ነው። የግጥም ስልቱ ‹ቡርዳ› ይባላል።

በነብዩ ዘመን ነብዩን በማወደስ የታወቁ ገጣሚያን ነበሩ እነ ካእብ ኢብኑ ዙበይር፣ ሀሳን ኢብኑ ሳቢት ተጠቃሾች ናቸው።

ስንኞች

መንዙማ አልፎ አልፎ መዝናኛ ነው፤ አንዳንዴ የጸሎት ማዳረሻ ነው፤ ብዙዉን ጊዜ የማኅበረሰብን ሰንኮፍ ማሳያም ነው፤ አንዳንዴ የሃገር ፍቅር መግለጫም ነው።

ብዙዎቹ የመንዙማ ሥንኞች የሥነ-ምግባር ተምሳሌት ተደርገው የሚታሰቡትን ነብዩ ሙሐመድን ያወድሳሉ። አፈንጋጮችን ይገስጻሉ፣ ባሕል ከላሾችን ይኮረኩማሉ።

አቶ ተመስገን ፈንታው መቀለ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሥነ-ጽሑፍና ፎክሎርን ለ12 ዓመታት አስተምረዋል። በመንዙማ ዙርያ የተሠሩ በርከት ያሉ ጥናታዊ ወረቀቶችን አማክረዋል። በአንድ ቃለ-መጠይቃቸው ላይ “ሴት አያቴ በመንዙማ ነው ያሳደገችኝ” ይላሉ።

የክርስትና ሀይማኖት ተከታይ መሆናቸው መንዙማን ከማጣጣም እንዳላቦዘናቸው ሲያስረዱ።

“ወሎ ውስጥ መንዙማ ባሕል ነው። የየትኛውንም እምነት ተከታይ ሁን መንዙማን ትሰማለህ፤ በአንድም ሆነ በሌላ… አያቴ መንዙማን “የእስልምና” ብላ አይደለም የምትረዳው። እሷ የምታውቀው የወሎዬ መሆኑን ነው። መንዙማ ለእሷ ከአምላክ ጋር መገናኛ፣ መታረቂያ፣ መለማመኛ፣ ስሜቷን መተንፈሻ ነው።” ብለዋል።

አንዳንድ የመንዙማ ተንታኞች የመንዙማን ዋጋ ከፍ ሲያደርጉ የእስልምና ምሶሶ ከሆነው ተውሂድ ጋር ያያይዙታል። ‹ላ ኢላ ሃኢለላህ ፣ ሙሐመዱ ነብይ ረሱሉላህ› ነው። አላህ አንድ ሙሐመድ መልእክተኛው ነው ማለት ነው። መንዙማ የሚጀምረው ከዚህ ነው ይላሉ።

ሌላ ገጣሚ በበኩሉ “የአርሹ ባለቤት ማሕሙድ ነው ይህም ሙሐመድ ነው። አላህ ለሙሐመድ ያለውን ፍቅር ለመግለጽ ከራሱ ስም ቆርሶ ስም ሰጠው እሱ ማሕሙድ ሲሆን ወዳጁን ሙሐመድ አለው።” ብሏል። (ማሕሙድ ማለት ተመስጋኝ ማለት ሲሆን ሙሐመድ ደግሞ ምስጉን ማለት ነው)

መንዙማ በኢትዮጵያ

መንዙማ በኢትዮጵያ በዚህ ጊዜ ጀመረ የሚል መረጃ አልተገኘም። ሆኖም የተስፋፋበት ዘመን ይታወቃል። ከ896 እስከ 1280ዎቹ በሸዋና ዙርያዋ የሙስሊም ሱልጣኔቶች ባበቡበት ዘመን መንዙማ አልፎ አልፎ መታየቱ የጽሑፍ ማስረጃዎች ይገልጻሉ። በይበልጥ ግን ኢትዮጵያውያን ለትምህርት በእግራቸው ወጥተው ሲመለሱ የመንዙማን ባሕል እንዳስፋፉ ተጽፏል።

አቶ ሐሰን ካዎ ግን “ከእስልምና መነሳት ጊዜ ጀምሮ በመካ፣ ከእስልምና ወደ አክሱም መግባት ጀምሮ ነው በኢትዮጵያ መንዙማ የነበረው” ይላል። አቶ አደም ካሚልም በዚህ ይስማማሉ። ወሎ ውስጥ ንጉስ የሚባል ቦታ ከ300 ዓመታት በፊት በሰፊው ተጀመረ ይላሉ። የሃበሻ ቡሰይሪዎች በዚህ ዘመን በዝተው ታይተዋል።፡ ለምሳሌ አንይ ራያ፣ ሸኅ አሊ ጎንደር ተጠቃሽ ናቸው። በወሎ የትምህርት ማእከል የነበረች በመሆኗ ከየአካባቢው በመምጣት ለዓመታት እውቀት ሲቀስሙ የነበሩ ሰዎች በመጨረሻ ሸኽ እየሆኑ ወደየአካባቢው ሲሄዱ መንዙማውን ያሰራጩት ነበር።

እንደ አቶ አደም ካሚል ገለጻ የሃገራችን መንዙማ የትም ሃገር ካለው በቋንቋና በሃሳብ ምጥቀቱ ይለያል። ብዙ ጊዜ አረቦቹን የሚያስገርማቸውም ይኸው ነው። እኛ ቅኝ ባለመገዛታችን ከአረብኛው የተደበላለቀ ቋንቋ ያለው መንዙማ የለንም።

እንደ አቶ ሀሰን ማብራሪያ የሐረር መንዙማ አገባቡ ወሎ ካለው ይለያል ይላል። በሐረር የሚታወቀው ዚክሪ ነው መንዙማ አይደለም። ዚክሪ እራሱን የቻለ ባህል አለው፤ አረብኛና የአካባቢው ቋንቋ ጋር ተቀላቅለው ተጣጥመው የሚባል ነው።

ነባሩ ትውፊት እና ዓለማዊው ኪነ-ጥበብ

ነባሩን ትውፊት ወደ ዓለማዊው ኪነ-ጥበብ ይዘውት የዘለቁም አሉ። ከነዚህ መካከል ኑረዲን ኢሳ አንዱ ነው። በግጥሞቹ ላይ አብዝቶ ተጠቅሞባቸዋል። “ዒሻራ፣ መደድ” በተባሉት የግጥም እና የአጫጭር ልብ ወለድ መድብሎቹ አማርኛን ከአረብኛ ጋር እየቀላቀለ የመንዙማውን ዘዬ በግሩም ሁኔታ ተጠቅሞበታል። አብዲ ሚፍታህም “ኧረ!” በተሰኘው የግጥም መድብሉ ላይ በተመሳሳይ የአረብኛውን ቅልቅል ግጥሞች አስነብቦናል። ላነሳነው ጉዳይ ምሳሌ የሚሆነንን አንድ አጠር ያለ ግጥም ከአብዲ ሚፍታህ ስብስቦች እንመልከት።

ኢክቱብ

ተቀኘሁኝ ብሎ ከፍ ከፍ ብሎ

በጠረፍ ጠባቂ ማማ ላይ ተሰቅሎ

ለካስ ህላዌውን ከልሶ ቢያሰላው

ባለ ቅኔ ሳይሆን ቅኔ ኖሯል እርሱ

በ’ኻሊቁ’ ብእር ‘ምትዘርፍ ነፍሱ!

በግጥሙ ላይ ኢክቱብ እና ኻሊቁ የተሰኙ እንግዳ ቃላት ይገኛሉ። ኢክቱብ፡- ጻፍ ማለት ሲሆን ኻሊቁ፡- አምላክ የሚል ትርጓሜ አላቸው። ከአረብ የተወሰዱ ናቸው። ግጥሙን በምልአት ለመረዳት ተርጓሚ ያስፈልጋቸዋል። በመንዙማው ላይ ግን ተመሳሳይ ጥያቄ አናነሳም የዚህም ምክንያት አብዛኛው ታዳሚ ቢያንስ ቁርአንን የቀራ ስለሚሆን ነው። ይህንን ነባር መንዙማዊ ልማድ ነው እንግዲህ ገጣሚ አብዲ ወደ ዓለማዊ ግጥሞች ያሰረገው።

ተመሳሳይ የአገጣጠም ስልትን የተከተሉ ዘፈኖችም አሉ።

እናቱ ዱበርቲ አባቱ ሼህ ናቸው

አድርገው ያሉትን የሚያደርግላቸው

ነጃ በለኝ ወሎ በል እስቲ ፈርጀኝ

እያሽሞነሞነ ይዋል ሲያበጃጀኝ

ሃና ሸንቁጤ ያቀነቀነችው ይሕ ዜማ የአካባቢውን የንግግር ዘዬ ብቻ ሳሆን ሀይማኖታዊ ስርአቱንም በሚያውቅ ሰው መሰናዳቱ ያስታውቃል። በመንዙማ ዘዬ ይገጠም እንጂ ምቱ የወሎ ነው። እርስዋም ጥሩ አድርጋ ተጫውታዋለች። መዝሙርም አልነው መንዙማ ዋነኛው ተወዳሽ ፍቅር ነው የሚል ይዘት ያለውን ተከታዩን ግጥም ስናደምጥ ደግሞ የፍቅር ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ ሊያስረዳን ሲጥር እናገኘዋለን።

አንዴ በመዝሙሩ አንዴ በመንዙማ

ሲያወድስ ይውላል የፍቅርን ከራማ

የዜማ መነሻቸውን ከመንዙማ ካደረጉት መካከል የቴዎድሮስ ካሳሁንን ማንሳት ይቻላል። ሼመንደፈር

አዛን አለ መስጊድ ልትነጋ ምድር

ልሂድ ሸመንደፈር ልሳፈር ባቡር

በእንግድነት መጥታ ከሸገር ሀረር

ልቤን ይዛው ሄደች ወደ ሩቅ ሐገር

እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂም) መንዙማን መነሻ አድርጋ የሰራቻቸው ዘፈኖች አሏት። የጃን ስዩም ሔኖክ ቢላል ደግሞ አረብኛን ከአማርኛ በመቀላቀል የተሰራ ግሩም ዘፈን ነው። የግጥሙ ደራሲ ሙሉጌታ ተስፋዬ ነው።

ሙሃባ ነው እንጂ ያቀናው ሃገሩን

ጃሂል ገድሎን ነበር አሳክሮት ነገሩን

ኢትዩጵያዊውን ቢላል የሚያነሳሳው የግጥሞቹ ሐሳብ የቢላልን አስተምህሮት ይሰብካል። ሐይማኖታዊውን መልእክት ከሀይማኖት ክልል ውስጥ ያወጣውና ለሰው ልጆች ሁሉ ይሰጠዋል። እንደ መንዙማው ሁሉ በተሰናሰለ ውህደት የማይጎረብጥ የአማርኛ እና የአረብኛ ድቅል ግጥም ነው። ከቁርዓን ያልተጠጋ ወይም ሁለቱንም ቋንቋዎች የማያውቅ አድማጭ በቅጡ አይረዳውም። ይህ ነው እንግዲህ ልዩ ነገር ማለት። የራስን ቀለም በነበረው ሀይማኖታዊ አካሄድ ውስጥ መጨመር እንዲህ ይገለጻል። አረብኛም አማርኛም ያልሆነ ግጥም፤ ነገር ግን የሚጥም

ይላችኋል ቢላል ይላችኋል

ሁሉንም በዙብል ሁሉንም በሃላል

https://taza.debreyaredpublisher.com/2020/05/27/%e1%88%98%e1%8a%95%e1%8b%99%e1%88%9b-%e1%8a%a5%e1%8a%93-%e1%8a%aa%e1%8a%90-%e1%8c%a5%e1%89%a0%e1%89%a5/

የምትከተላቸውን ሃይማኖቶች በቀደምቶቹ ነቢያት የተሰበከች ሀገር ናት ኢትዮጵያ። ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ አጥምቆ ክርስትናን ሰብኮ የላከው ከመጀመሪያዎቹ ነቢያት አንዱ ነው። ነቢዩ .....

https://taza.debreyaredpublisher.com/2020/05/27/%e1%88%88%e1%89%a3%e1%88%ad%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b...
16/06/2020

https://taza.debreyaredpublisher.com/2020/05/27/%e1%88%88%e1%89%a3%e1%88%ad%e1%8a%90%e1%89%b5-%e1%8b%a8%e1%89%b0%e1%88%b8%e1%8c%a1%e1%89%b5-%e1%8a%a2%e1%89%b5%e1%8b%ae%e1%8c%b5%e1%8b%ab%e1%8b%8a-%e1%8b%a8%e1%8c%80%e1%8a%94%e1%88%ab%e1%88%8d/

ለባርነት የተሸጡት ኢትዮጵያዊ የጀኔራል አብርሃም ፔትሮቪች ጋኒባል (1696-1781) አጭር ታሪክ፡- ክፍል ሁለት ባይለየኝ ጣሰው (ዶ/ር) የአብርሃም ፔትሮቪች ጋኒባል የትምህርት ዓለም፣ ሙያና የሥ...

04/06/2020
የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 29፣ 2012 ዓ.ም በእጅዎ ትገባለች ቅጽ 3 ቁጥር 33 ታዛ መጽሔት፤
04/06/2020

የፊታችን ቅዳሜ ግንቦት 29፣ 2012 ዓ.ም በእጅዎ ትገባለች ቅጽ 3 ቁጥር 33 ታዛ መጽሔት፤

02/06/2020

ዓለማችን በርካታ አምባገነን መሪዎችን አፍርታለች። በአስገራሚ ተግባራቸው ጎልተው ከሚጠቀሱ መሪዎች አንደኛው የቱርክሜኒስታኑ ፕሬዝዳንት ሳፖርሙራት ንያዞቭ እንደሚሆን አይጠረጠር.....

02/06/2020

ቪድዮ ሶፎክለስ By ጆኒ በሪሁ Posted on May 27, 2020 Share Tweet Share Share Email Comments Related Items: Share Tweet Share Share Email Click to comment Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Required fields are marked *Comment Name * Email * Website Sav...

22/05/2020

“ዓለም የተበላሸችው ክፉ ሰዎች በመኖራቸው ብቻ ሳይሆን፤ መልካም ሰዎች እውነቱን ባለ መመስከራቸው ጭምር ነው” ይላሉ የሀሳብ ሰዎች። እውነትም ነው። ሰዎች የሚያውቁትን ባለመመስከራቸ...

ቅጽ 3 ቁጥር 32 ታዛ መጽሔት፤˝ የፖለቲካ ባህላችን ጉዞ በዞረ ድምር ወይስ…?” የሚል የሽፋን ገጽ በመያዝ እና ሌሎች ጥበባዊ ርዕሰ-ጉዳዮችን በማንሳት ለአንባቢዎቿ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ...
16/05/2020

ቅጽ 3 ቁጥር 32 ታዛ መጽሔት፤
˝ የፖለቲካ ባህላችን ጉዞ በዞረ ድምር ወይስ…?”
የሚል የሽፋን ገጽ በመያዝ እና ሌሎች ጥበባዊ ርዕሰ-ጉዳዮችን በማንሳት ለአንባቢዎቿ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ትውላለች፡፡

ቅጽ 3 ቁጥር 32 ታዛ መጽሔት፤˝ የፖለቲካ ባህላችን በዞረ ድምር ወይስ…?” የሚል የሽፋን ገጽ በመያዝ እና ሌሎች ጥበባዊ ርዕሰ-ጉዳዮችን በማንሳት ለአንባቢዎቿ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ትውላ...
16/05/2020

ቅጽ 3 ቁጥር 32 ታዛ መጽሔት፤
˝ የፖለቲካ ባህላችን በዞረ ድምር ወይስ…?”
የሚል የሽፋን ገጽ በመያዝ እና ሌሎች ጥበባዊ ርዕሰ-ጉዳዮችን በማንሳት ለአንባቢዎቿ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ትውላለች፡፡

15/05/2020

ግጥም ግሼ አባይ ግዮን By ጆኒ በሪሁ Posted on May 15, 2020 Share Tweet Share Share Email Comments Related Items: Share Tweet Share Share Email Click to comment Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Required fields are marked *Comment Name * Email * ...

06/05/2020
06/05/2020

የታዛ ድምፆች ከጣሊያን የተላከ ደብዳቤ By ዕቑባይ በርሀ Posted on May 6, 2020 Share Tweet Share Share Email Comments Related Items: Share Tweet Share Share Email Click to comment Leave a Reply Cancel replyYour email address will not be published. Required fields ar...

05/05/2020

የሚፈነጥቀው – የገደል ዳር ጢሱ ሳቅ ነው ስል ከርሜ ለቅሶ ነበር ለሱ በዘመናት ብሶት ስሜቱ ሲነካ እምባ እያፈሰሰ ወንዝ ያለቅሳል ለካ ዶፍ ጭሆት አሰማ ድንገት ደፈረሰ ምን መርዶ ሰምቶ ነ....

29/04/2020

ዓለም አንድ ቋንቋ እየተናገረች ነው፡፡ ድሃ ሀብታም፣ ሶሻሊስት ኮሚኒስት፣ ሰሃራ ሳይቤሪያ ሳይል ስለ አንድ ነገር ብቻ እያሰበ፣ እየተጨነቀ፣ የመፍትሔ ጫፍ እያሰሰ ነው፡፡ እጃችሁን ታ....

ከጣሊያናዊቷ ደራሲ የተላከ ደብዳቤ!
25/04/2020

ከጣሊያናዊቷ ደራሲ የተላከ ደብዳቤ!

ፍራንሲስካ ሜላንደሪ ትባላለች። እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ1964 ዓ.ም. ሮም ከተማ ተወለደች። የልቦለድ ደራሲ፣ የፊልም ጸሐፊ እና የዶክመንተሪ አዘጋጅ ናት። pzon PR apallu carige prize የተሰኘውን ...

25/04/2020

ጋዜጠኛ ላዕከማሪያም ደምሴ በ1950 እና 60ዎቹ፣ አለፍ ሲልም 70ዎቹ የነበሩ አብዛኞቹ የአገራችን ጋዜጠኞች በልምድ፣ በተሰጥኦ እና በፍላጎት ነበር የሚሰሩት። ሳይንሳዊው የጋዜጠኝነት ትምህ....

የመፅሐፍ ዳሰሳርዕስ - የሴቶች ሁለንተናዊ አበርክቶhttps://taza.debreyaredpublisher.com/2020/04/14/%e1%89%81%e1%88%9d%e1%8a%90%e1%8c%88%e1%...
16/04/2020

የመፅሐፍ ዳሰሳ
ርዕስ - የሴቶች ሁለንተናዊ አበርክቶ
https://taza.debreyaredpublisher.com/2020/04/14/%e1%89%81%e1%88%9d%e1%8a%90%e1%8c%88%e1%88%ab%e1%88%9d-%e1%8c%88%e1%8c%be%e1%89%bd/

ርዕስ፡- የሴቶች ሁለንተናዊ አበርክቶ      የገፅ ብዛት፡- 220 + 20 አርታኢ፡- አብዱራህማን አህመዲን ዘውግ፡- የጥናት ጽሑፎች ስብስብ የሕትመት ዘመን፡- ጥቅምት 2012 ዓ.ም. አሳታሚ፡- የሴቶች ...

13/04/2020

ውድ ተከታታዮቻችን የቴሌግራም ቻነል የከፈትን ስለሆነ፤ ተጨማሪ ዜናዎቻችንን ከስር ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
https://t.me/tazamagazine

ውድ አንባቢዎቻችን፤ እናንተ የምትወዷት ታዛ መጽሔት እንደተለመደው በሰፊ ይዘትና ልዩ አቀራረብ ተከሽና በዛሬው ዕለት ገበያ ላይ ውላለች። አንብቧት፤ ትወዷታላችሁ፣ ትዝናኑባታላችሁ፣ ትማሩባታላ...
11/04/2020

ውድ አንባቢዎቻችን፤ እናንተ የምትወዷት ታዛ መጽሔት እንደተለመደው በሰፊ ይዘትና ልዩ አቀራረብ ተከሽና በዛሬው ዕለት ገበያ ላይ ውላለች። አንብቧት፤ ትወዷታላችሁ፣ ትዝናኑባታላችሁ፣ ትማሩባታላችሁ!!!

08/04/2020

ቀዳሚ ቃል
=> ታዛ መፅሔት ቅፅ 3 እትም 31ን ቅዳሜ ይጠብቋት...............
በአጭር ጊዜ ውስጥ የዓለምን ተለምዷዊ አካሄድ ባልተጠበቀ መንገድ
ያስጓዘው ኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) የሐገራችንም ስጋት መሆን ከጀመረ
ሳምንታት ተቆጥረዋል። ትላንት በሩቁ ስንመለከተው የነበረው ጥፋት ዛሬ
ደጃችን ላይ ነው። የጤና እና የማኅበራዊ ደህንነት ፖሊሲያቸው የጠነከረውን
አገራት ያብረከረከው ተህዋስ የምንተነፍሰው አየር ላይ ናኝቷል። የኢኮኖሚ፣
የፖለቲካ፣ የቴክኖሎጂ፣ የስፖርት፣ የባህል፣ የኪነጥበብ፣… ዜናዎች በኮሮና
እና ኮሮና ነክ ወሬዎች ተተክተዋል። እንቅስቃሴአችን ብቻ ሳይሆን ሀሳባችን
እና አስተሳሰባችንም ጭምር ተህዋሱን በመከላከል ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በፍጥነት መላቀቅ የማንችለው የቀደመ ልማዳችን ለተህዋሱ
መዛመት ምቹ ሁኔታን እያመቻቸ ነው፡፡ የሐኪሞችን ምክር እያደመጥን
አይደለም፡፡ ምላሻችን አዝጋሚ ነው፡፡ የዘገየው ምላሽ ዋጋ ካስከፈላቸው ሀገሮች
የተማርን አይመስልም፡፡ የተጠናከረ ቁጥጥር እና ስርአት ማክበር ሞትን
ካስቀረላቸው ሐገሮች ተሞኩሮ የቀሰምን አይመስልም፡፡
ራሳችንን በቁጥር እያጽናናን ነው፡፡ የታማሚዎቻችን ብዛት ሁለት ዲጅት
አልሞላም እንላለን፡፡ ከጠቅላላ ቁጥራችን ጋር እያካፈልን ፐርሰንት እንሰራለን፡፡
አንድ ተገቢውን ጥንቃቄ ያላደረገ ህንዳዊ የሐይማኖት ሰባኪ አርባ ሺሕ ሰዎችን
ማስያዙን እንዘነጋለን፡፡ አንድ ቀድማ የመመርመር እድሏን ያዘገየች ኮርያዊት
ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎችን በቫይረሱ እንዳስያዘች ለማሰብ ጊዜ አጥተናል፡፡
ራሳችንን እያሞኘን ነው፡፡ ቫይረሱ ለጥቁር ሰው፣ ለነጭ ሽንኩርት፣ ለአየር
ንብረት እንደሚበገር እናወራለን፡፡ የዓለም ጤና ድርጅትን የጥንቃቄ መመሪያ
ጥለን ምንጩ ባልታወቀ ሕግ እንዳኛለን፡፡ ሰፊ ምርምር እና ረጅም የፍተሻ
ሂደት ባለው የመድሃኒቱ ግኝት ዜና የተጋነነ ተስፋ እናደርጋለን፡፡…
አሁንም አልረፈደም፡፡ ጥቂት የጥንቃቄ ድርጊቶች የበዛውን ኃላፊነት
እንድንወጣ እድል ይሰጡናል፡፡ ጥቂት የቤት ውስጥ ትእግስት የብዙኃንን
ሞት ያስቀራል፡፡ ጥቂት የመረዳዳት ድርጊት የበዛ ማኅበራዊ ኪሳራ ውስጥ
እንዳንወድቅ ያደርጋል፡፡ ማንም ብቻውን ሊተርፍ ወይም ብቻውን ሊሞት
አይችልም፡፡ ሁላችንም ለሁላችንም እያንዳንዳችን ለሁላችንም ስንል ተገቢውን
ጥንቃቄ እንውሰድ!

05/04/2020

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ላይ ጥናት ለማካሄድ
10 ሚሊየን ብር መደበ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኮቪድ-19 ላይ ጥናት ለማካሄድ 10 ሚሊየን ብር መደበ፡፡ በዛሬው እለት በኮቪድ-19 ላይ ጥናት የሚያኪያሂድ የጥናት ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ቡድኑ ጥናቱን ለመጀመር ይችል ዘንድ ከተመደበው አጠቃላይ ፈንድ ውስጥ አንድ ሚሊየን ብር ወጪ ሆኖ ተሰጥቶታል፡፡ የጥናት ቡድኑ አባላት ከተለያዩ ኮሌጆችና ተቋማት ከልዩ ልዩ መስክ የተውጣጡ ምሁራንን ያካተተ ሲሆን የመጀመሪያ ስብሰባውንም በዛሬው እለት መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም አድርጓል፡፡ የጥናት ቡድኑ ይህን ገዳይ የኮሮና ቫይረስ ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት አስተዋፅኦ ለማድረግ ጠቃሚ ግብአት ሊሆን የሚችል የጥናት ግኝቱን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡፡ ለጥናቱ የተመደበው ቀሪው ገንዘብ በውድድር ላይ ተመስርቶ በመሰል ጥናት ለመሳተፍ ለሚሹ የአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ስታፍ አባላት የሚቀርብ ይሆናል፡፡
ጣሰው ወልደሐና (ፕሮፍሰር)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም

Addis Ababa University has earmarked ETB 10 million
to undertake a study on COVID-19.

Addis Ababa University has earmarked ETB 10 million to undertake a study on COVID-19. The first Thematic Working Group on VOVID-19 is established today and awarded Birr one million to conduct action research on COVID-19 and related issues. The team is an inter-disciplinary team composed of different colleges and institutes, and kicked-off its first meeting today on the 26th of March, 2020. The team is expected to present its research findings that would contribute to the fight against the deadly virus. The rest of the fund will be provided on competition basis for interested AAU staff who would like to undertake a similar study.

Tassew Woldehanna (Prof)
President of Addis Ababa University
26 March 2020

የካንትሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነው ዝነኛው ኬኒ ሮጀርስ፤ ትላንት መጋቢት 11 ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በ81 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል፡፡ ☞ የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል የተሰማውን ጥልቅ...
21/03/2020

የካንትሪ ሙዚቃ አቀንቃኝ የሆነው ዝነኛው ኬኒ ሮጀርስ፤ ትላንት መጋቢት 11 ከምሽቱ 4 ሰዓት ከ25 ደቂቃ ላይ በ81 ዓመቱ ህይወቱ አልፏል፡፡
☞ የታዛ መጽሔት ዝግጅት ክፍል የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ለአድናቂዎቹና ወዳጆቹ ይገልፃል፡፡

The Rogers family is sad to announce that Kenny Rogers passed away last night at 10:25 p.m. at the age of 81. Rogers passed away peacefully at home from natural causes under the care of hospice and surrounded by his family. https://ymlp.com/zbjSX9

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when TAZA ታዛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to TAZA ታዛ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share