Ethio-World News

  • Home
  • Ethio-World News

Ethio-World News Speak the truth!!!

https://cryptotabbrowser.com/landing/79/14344259
05/12/2023

https://cryptotabbrowser.com/landing/79/14344259

Earn bitcoins while watching videos, chatting, or playing online. It has never been so easy to increase your income! Tell your friends about CryptoTab Browser, invite them to join, and earn more together. Grow your network—get more profit!

ማስታወቂያበ22/02/2016 ዓ.ም ፓስፓርት የምትወስዱ ደንበኞቻችን በ 7876 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የላክን ሲሆን  ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30-10፡00 ሰዓት ፒያሳ እናት ...
01/11/2023

ማስታወቂያ
በ22/02/2016 ዓ.ም ፓስፓርት የምትወስዱ ደንበኞቻችን በ 7876 አጭር የፅሁፍ መልዕክት የላክን ሲሆን ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30-10፡00 ሰዓት ፒያሳ እናት ህንፃ አጠገብ በሚገኘው ኢሚግሬሽን ቢሮ በመገኘት ፓስፖርታችሁን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ወደ ተቋማችን ስትመጡ ኦንላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
*የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት*
**
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.ics.gov.et
ቲክ ቶክ:- http://tiktok.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/IcsEthiopiaOfficial
Youtube፡- https://www.youtube.com/
ፌስቡክ:- FDRE Immigration and Citizenship Service
በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

Final Notice The Federal Democratic Republic of Ethiopia, Immigration and Citizenship Service is mandated to register and administer legal permits for foreign nationals living in Ethiopia by the authority vested on proclamation No. 354/2003. As a result, there was registration between July 18 to Aug...

ማስታወቂያበ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት ውል ሳትዋዋሉ ለቀራችሁ በሙሉ :-ውል መወያያ ለመጨረሻ ጊዜ ከጥቅምት 0...
19/10/2023

ማስታወቂያ

በ14ኛው ዙር የ20/80 እና በ3ኛው ዙር የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕድለኞች ሆናችሁ በተለያየ ምክንያት ውል ሳትዋዋሉ ለቀራችሁ በሙሉ :-

ውል መወያያ ለመጨረሻ ጊዜ ከጥቅምት 01/02/2016 ዓ.ም እስከ 30/02/2016 ዓ.ም ድረስ ውል የተራዘመ ስለሆነ በጠቀሰው ወቅት አስፈላጊውን መረጃ በማሟላት በኮርፖሬሽኑ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሚሰጥበት ቦሌ ክ/ከተማ በመቅረብ እንድትዋዋሉ ኮርፖሬሽኑ ያሳውቃል።

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ሳይዋዋል የቀረ ባለዕድለኛ በራሱ ጊዜ ቤቱን እንደተወው በመቁጠር ቤቱ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ የሚደረግ መሆኑን እናሳውቃለን።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን

ቢያንስ በአጸያፊ ስሙ እንጥራው! (በድሉ ዋቅጅራ)የመስዋእትነቱና የሰማእትነቱ ውጤት ምንድነው?  የትግራይ፣ የአማራ . . . የኢትዮጵያ እናቶች እንባ!?ስሙን አታሳምሩት! መስዋእትነትም፣ ሰማ...
15/10/2023

ቢያንስ በአጸያፊ ስሙ እንጥራው! (በድሉ ዋቅጅራ)
የመስዋእትነቱና የሰማእትነቱ ውጤት ምንድነው? የትግራይ፣ የአማራ . . . የኢትዮጵያ እናቶች እንባ!?

ስሙን አታሳምሩት! መስዋእትነትም፣ ሰማእትነትም አይደለም፡፡ በዚያ ጦርነት የተከበረ ድንበር፣ የተነሳ ሰንደቅ፣ የተመለሰ ነጻነት፣ የተረጋገጠ መብት፣ የተቀረፈ ድህነት፣ የለም፡፡ . . . . ልጆቿን ለተነጠቀች እናት ጠብ ያለ ነገር የለም፡፡ ከጦርነቱ ፍጻሜ በኋላ፣ እንደሀገርና እንደህዝብ ከጦርነቱ በፊት ከነበርንበት ጎድለን እንጂ ሞልተን፣ ደህይተን እንጂ በልጽገን አልተገኘንም፡፡ ያ ጦርነት የዘር ፖለቲካ የወለደው የእርስ በርስ መጨፋጨፍ እንጂ ሰማእትነትም፣ መስዋእትነትም አይደለም፡፡
ቢያንስ በአጸያፊ ስሙ እንጥራው፡፡ አጸያፊነቱን መቀበል ዳግም ላለመፈጸም የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡ መጨፋጨፍን መስዋእትነትና ሰማእትነት እያሉ ማንቆለጳጰስ ከብሄር ተኮር የእርስ በርስ መጨፋጨፍ እንዳንወጣ ያደርገናል፡፡ አዲስ አይን ለማውጣት፣ አዲስ ሰላማዊ መንገድ ለመከተል ቢዘገይም ዛሬ እጃችን ላይ እድል አለ፤ መንግስት ከክልሎችና ከተለያዩ ቡድኖች ጋር የሚገጥመውን አለመግባባት ለመፍታት ሰላማዊ ድርድርን ብቸኛ አማራጭ ማድረግ አለበት፡፡ ጦርነት ይብቃን፤ የወጣቶች ሞት ይብቃን፤ የእናቶች ሙሾና እንባ ይብቃን፡፡

15/10/2023
ዓለም እኮ ሰፊ ነች!ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡ ቀና በሉ! • ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ! • ከቡድናችሁ ውጪ...
03/10/2023

ዓለም እኮ ሰፊ ነች!

ዓለም እናንተ ስታጠቧት ትጠባለች፣ ሰፊነቷን ስትቀበሉና ስታዩላት ደግሞ በስፋቷ ልክ ታስተናግዳችኋለች፡፡

ቀና በሉ!

• ከሰፈራችሁ ውጪ ሌላ ሰፈር አለ!
• ከቡድናችሁ ውጪ ሌላ ቡድን አለ!
• ከመስሪያ ቤታችሁ ውጪ ሌላ መስሪያ ቤት አለ!
• በአካባቢች ካሉት ሰዎች ውጪም ሌሎች ሰዎች አሉ!
• አሁን ካላችሁ የገቢ ምንጭ ውጪ ሌላ የገቢ ምንጭ አለ!

ከፈጣሪ የተሰጣችሁን ሰፊ ዓለማችሁን አታጥብቧት፡፡ ምርጫችሁ አንድና አንድ ብቻ እንደሆነ ስታስቡና በዚያ ዙሪያ ብቻ ስትሽከረከሩ ዓለማችሁ እሱ ብቻ እስከሚመስል ድረስ ትጠባላችሁ፡፡

“ከዚህ ሁኔታ ውጪ መኖር በፍጹም አልችልም” ብላችሁ ያሰባችሁትን ሁኔታ በብዙ የሚያስንቁ ሁኔታዎች አሉ፡፡

“ከእነዚህ ሰዎች ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ብላችሁ ካሰባችኋቸው ሰዎች በብዙ የላቁ ሰዎች አሉ፡፡

“ከዚህ ስራ ውጪ በፍጹም መኖር አልችልም” ካላችሁት የስራ መስክ በብዙ የተሸሉ የስራ እድሎች አሉ፡፡

አትወጣጠሩ! አትጨናነቁ! ለክክለኛው ነገር ታማኝ መሆናችሁን ሳትለቁ በዙሪያች ብዙ እድሎች እንዳሉ አትዘንጉ፡፡

Via Dr Eyob

The splits from Tgist Assefa's world record run of 2:11:53 at the Berlin Marathon 🤯5km: 15:5910km: 31:4515km: 47:2620km:...
25/09/2023

The splits from Tgist Assefa's world record run of 2:11:53 at the Berlin Marathon 🤯

5km: 15:59
10km: 31:45
15km: 47:26
20km: 62:52
Half: 66:20
25km: 1:18:40
30km: 1:34:12
35km: 1:49:41
40km: 2:05:13
Finish: 2:11:53

 #ቴክኖሎጂ  ፈረንሳይ " አይፎን 12 " ን ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ ማዘዟን ተከትሎት የአውሮፓ ሀገራት ጉዳዩን እየተከታተሉ ነው ተብሏል።ፈረንሳይ አይፎን...
14/09/2023

#ቴክኖሎጂ

ፈረንሳይ " አይፎን 12 " ን ከልክ በላይ ጨረራ ያመነጫል በሚል የስልኩ ሽያጭ እንዲታገድ ማዘዟን ተከትሎት የአውሮፓ ሀገራት ጉዳዩን እየተከታተሉ ነው ተብሏል።

ፈረንሳይ አይፎን 12ን ያገደችው ከሚፈቀደው የኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲዬሽን በላይ እያመነጨ ነው በማለት ሲሆን ይህን እገዳ ተከትሎ ፦
- ቤልጂየም፣
- ኔዘርላንድስ
- ጀርመን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ እየተከታተሉት ነው ተብሏል።

የጀርመን ባለሥልጣናት ሁኔታው ወደ አውሮፓ አቀፍ እርምጃዎች ሊመራ ይችላል ብለዋል።

የቤልጂየም መንግስት እ.ኤ.አ. በ2020 ለመጀመሪያ ጊዜ የተለቀቀው አይፎን 12 መሆኑን እንዲገመግም ለተቆጣጣሪ አካል መመሪያ መስጠቱ ተነግሯል።

የቤልጂየም የዲጂታላይዜሽን ሚኒስትር ማቲዩ ሚሼል ፤ " ዜጎቻችን በሙሉ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ከማንኛውም አደጋ የተጠበቁ እንዲሆኑ ማድረግ የእኔ ኃላፊነት ነው። ጤና መቼም ቢሆን ችላ ሊባል የማይገባ ጉዳይ ነው። " ብለዋል።

ሁሉም የአፕል ሞዴሎችን እንዲመረምር ተቆጣጣሪውን አካል እንደተጠየቀ አመልክተዋል። ሌሎችም ብራንዶች ላይ ተመሳሳይ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የኔዘርላንድ ዲጂታል መሠረተ ልማት ኤጀንሲ ፤ በፈረንሣይ ምርመራ ላይ በመመርኮዝ ከልክ በላይ የጨረር መጠን እንደሚያመነጭ ጥርጥር የለውም ያለ ሲሆን አፕልን እንደሚያነጋግር አሳውቋል።

ነገር ግን “ ምንም አጣዳፊ የደህንነት ስጋት የለም ” ብሏል።

የጀርመኑ BNetzA ኔትወርክ ኤጀንሲ ፤ የፈረንሣይ ምርመራ በሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ላይ የሚተገበሩ እርምጃዎችን ሊያስወስድ የሚችል ነው ብሏል።

አፕል የፈረንሳዩን እገዳ ከሰማ በኃላ ለቢቢሲ በሰጠው ቃል ፤ አይፎን 12 የጨረራ መጠኑ በሰዎች ላይ ጉዳት እንደማያስከትል በመላው ዓለም ባሉ ተቆጣጣሪዎች እውቅና ያለው ምርት ነው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

በሌላ መረጃ ፤ አፕል አዲሱን " አይፎን 15 " ከነገ ጀምሮ ማዘዝ እንደሚቻል አሳውቋል።

አዲሱ ምርት እንደየአይነቱ በተለያየ የገንዘብ መጠን ለገበያ ቀርቧል።

አይፎን 15 በስንት ዶላር ነው ለገበያ የቀረበው ?

👉 አይፎን 15 ከ$799 እስከ $1,099 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ44,952 ብር እስከ 61,830 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕላስ ከ$899 እስከ $1,199 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ50,578 ብር እስከ 67,456 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ከ$999 እስከ $1499 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ56,204 ብር እስከ 84,335 ብር ይሆናል)

👉 አይፎን 15 ፕሮ ማክስ ከ$1,199 እስከ $1,599 (በኢትዮጵያ ብር በባንክ ቢሰላ ከ67,456 ብር እስከ 89,961 ብር ይሆናል)

ገንዘቡ #ዝቅተኛው እና #ከፍተኛውን ጣሪያ የሚያሳይ ሲሆን እንደ ስልኩ GB እና አይነት ይለያያል።

 " ዳንኤል " የተባለው አውሎ ንፋስ በፈጠረው ከባድ ጎርፍ በሊቢያየሞቱ ሰዎች 20 ሺህ ገደማ ሊደርሱ እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል።በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ እስካሁን ያሉበት አልታወቀም።...
14/09/2023



" ዳንኤል " የተባለው አውሎ ንፋስ በፈጠረው ከባድ ጎርፍ በሊቢያየሞቱ ሰዎች 20 ሺህ ገደማ ሊደርሱ እንደሚችሉ ቢቢሲ ዘግቧል።

በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ እስካሁን ያሉበት አልታወቀም።

ደርና የተባለችው ከተማ ትልቁ ጉዳት የደረሰባት ሲሆን አብዛኛው የከተማዋ ክፍል በውሃ ተወስዷል።

በሌላ በኩል ፤ አርብ በሞሮኮ በደረሰው ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ የሞቱ ሰዎች 3000 ገደማ መድረሳቸው የተነገረ ሲሆን አሁንም ድረስ በህይወት ያሉ ሰዎች ካሉ በሚል ፍለጋ እየተደረገ ነው። በአደጋው ሰዎችን በህይወት የማግኘቱ ነገር እጅግ የመነመነ ነው ተብሏል።

በአደጋው ከ5,530 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል።

 ትግራይ ድረስ ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።ከአንድ ሰዓት በፊት (እስካሁን ባለው መረጃ) በሬክተር ስኬል 5.0  የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከኤርትራ፣ አስመራ በ59 ኪሎሜትር ...
13/09/2023



ትግራይ ድረስ ንዝረቱ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

ከአንድ ሰዓት በፊት (እስካሁን ባለው መረጃ) በሬክተር ስኬል 5.0 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ከኤርትራ፣ አስመራ በ59 ኪሎሜትር ርቀት መከሰቱን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ሪፖርት አድርጓል።

የመሬት መንቀጥቀጡን የሚመለከት ዝርዝር መረጃዎች በሰዓታት ውስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የመሬት መንቀጥቀጡን በተመለከተ አንድ ኤርትራዊ ፤ " ከደቂቃዎች በፊት እናቴን በስልክ እያነጋገርኳት ነበር (አዲ ቀይኺ) በድንገት ግን የነበሩት ህፃናት ሲጯጯሁ ሰማሁ ፤ በሁኔታው ተደናግጬ እናቴን ምን እንደተፈጠረ ጠየኳት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደሆነ ነገረችኝ " ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በትግራይ ክልል መቐለ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ምሽት 2:52 ደቂቃ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተሰማቸው ጠቁመዋል። በሽረ፣ ዓዲግራት፣ ኣክሱም እንዲሁም ዓድዋና ሌሎች አካባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት የተሰማቸው እንዳሉ ቤተሰቦቻችን ገልጻዋል።

ሃምሌ 25 /2015 ዓ.ም ከምሽቱ 2:15 ገደማ ዋና መነሻው (Epicenter) ከምፅዋ ወደብ በ43 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሆነ ከባድና 5.6 ሬክተር ስኬል የሚለካ የመሬት መቀጥቀጥ ተከስቶ ፤ በእንዳስላሰ ሽረ ፣ ሰለኽለኻ ፣ አክሱም ፣ ዓድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ውቕሮ ፣ ሓውዜንና አከባቢው ፣ ኣፅቢ ፣ መቐለና ሌሎች አከባቢዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ እንደተሰማ አይዘነጋም።

13/09/2023

ለግብፅ መግለጫ ምን ምላሽ ተሰጠ ?

" ግብፆቹ ስለ4ኛው ሙሌት በደንብ ያውቃሉ ፤ ምንም የተጣሰ መርህ የለም " - ኢ/ር ጌዲዮን አስፋው

ከሰሞኑን ኢትዮጵያ 4ኛውን ዙር የአባይ ግድብ የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ ካሳወቀች በኃላ ግብፅ ሙሌቱ ህገወጥ እንደሆነና እ.ኤ.አ. በ2015 በሱዳን፣ በግብፅና በኢትዮጵያ የተፈረመውን የመርህ ስምምነት የጣሰ ነው በሚል ቁጣ አዘል መግለጫ አውጥታ ነበር።

ለዚህ ግብፅ መግለጫ ምላሽ የሰጡት የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎችና ባለስልጣናት " ምንም የተጣሰ ነገር የለም ፤ መግለጫዋ ለሀገር ውስጥ የሚዲያ ፍጆታ የሚውል ነው " ብለውታል።

የኢትዮጵያ የግድቡ ተደራዳሪ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋው ምን አሉ ?

" ምንም የተጣሰ ነገር የለም፡፡ ግብፆች ያወጡት ነገር ትክክል አይደለም፡፡ የመርህ ስምምነቱ አልተጣሰም፡፡

በመርህ ስምምነቱ መሠረት የወጣ የሙሌት ሠንጠረዥ አለ፣ በእሱ መሠረት ነው አሁን የሞላነው፡፡

አሁን በቅርቡ የተጀመረው ድርድር የአገሮቹ መሪዎች በሰጡት መመርያ መሠረት የተጀመረና የተካሄደ ነው።

የሦስትዮሽ ድርድር ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረው ከቆመበት መቀጠል እንጂ፣ አዲስ ድርድር አይደለም።

አራተኛው ሙሌት በቅርቡ ከተጀመረው ድርድር ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም፡፡

ግብፆቹ ስለአራተኛው ሙሌት በደንብ ያውቃሉ፡፡ በተስማማነው መሠረት ነው የተሞላው። "

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ምን አሉ ?

" ሙሌቱ በሌሎች የተፋሰሱ አገሮች ላይ ትርጉም ያለው ተፅዕኖ የለውም።

የእነሱ የሚዲያ እንካ ሰላንቲያ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የቀጠለ ነው፡፡

አሁን ያወጡት መግለጫም የተለመደ የሕዝብ ግንኙነትና የሚዲያ ፍጆታ ነው፣ ለውስጥ ፍጆታ የሚጠቀሙበት ነው፡፡

እኛ የእነሱ የሚዲያ እንካ ሰላንቲያ ውስጥ መግባት አንፈልግም፡፡

ይኼ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያከብረው ፕሮጀክት ነው፡፡ ግድቡ የትብብር እንጂ የፉክክር ምንጭ መሆን የለበትም። "

Credit - #ሪፖርተር

13/09/2023

ሰበር
ከባድ የመሬት ምንቀጥቀጥ ኤርትራ እና ትግራይ አከባቢ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ጀምሮ ደርሶአል። የደረሰው የጉዳት መጠን አልታወቀም።
ቀጣይ ዜናዎችን እናጋራለን

10/09/2023

ሰበር!!!!!!!
አራተኛው ዙር የውሃ ሙሊት ተጠናቋል!!!
ኢትዮጵያውያን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!!

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጡ።****የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋ...
08/09/2023

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ዛሬ በስካይ ላይት ሆቴል መግለጫ ሰጡ።
****
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ " የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር " መሆኑን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።
ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 - 6፡3ዐ ሰአት ድረስ በመምጣት መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን አሳውቀዋል።
ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀው ከተቋሙ ውጭ የሆኑ ደላሎች የሀሰት ማስረጃዎችን፣ ፓስፖርቶችን የተቋሙ በማስመሰል እና ሀሰተኛ ዌብሳይቶችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ለህገወጥ ድርጊት እየዳረጉ በመሆኑ ህ/ሠቡ ይህንን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ትክክለኛ የተቋሙን ዌብሳይት በመለየት መጠቀም እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡
ሙሉ መርጃ ለማግኝት ሊንኩን ይጫኑ
t.me/ethiopia_passportservice

ነገ ቅዳሜ ወይም እሁድ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል!!
08/09/2023

ነገ ቅዳሜ ወይም እሁድ ውሃው በግድቡ አናት ላይ ይፈሳል ተብሎ ይጠበቃል!!

የህዳሴ ግድቡ 4ኛ ዙር ሙሌት ከሰሞኑ እንደሚጠናቀቅ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ውሃው ሞልቶ ለመፍሰስ የሚጠይቀው የቀናት እድሜን ብቻ እንደሚቀረውም መረጃው ይጠቁማል።የህዳቤ ግድቡ አጠቃላይ ግ...
03/09/2023

የህዳሴ ግድቡ 4ኛ ዙር ሙሌት ከሰሞኑ እንደሚጠናቀቅ የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።ውሃው ሞልቶ ለመፍሰስ የሚጠይቀው የቀናት እድሜን ብቻ እንደሚቀረውም መረጃው ይጠቁማል።የህዳቤ ግድቡ አጠቃላይ ግንባታም ከ87% በላይ መጠናቀቁ ታውቋል።ተቋርጦ የነበረው የግድቡ የሶስትዮሽ ውይይት ሰሞኑን ካይሮ መጀመሩ ይታወሳል።

“ግጭት ውስጥ የገቡት ኤርትራውያኑ ሥደተኞች ከእስራዔል በአስቸኳይ እንዲወጡ እፈልጋለሁ” - ቤኒያሚን ኔታንያሁአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴል አቪቭ ከተማ በተከሰተው ግ...
03/09/2023

“ግጭት ውስጥ የገቡት ኤርትራውያኑ ሥደተኞች ከእስራዔል በአስቸኳይ እንዲወጡ እፈልጋለሁ” - ቤኒያሚን ኔታንያሁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቴል አቪቭ ከተማ በተከሰተው ግጭት የተሳተፉ ኤርትራውያኑ ሥደተኞች በአስቸኳይ እስራዔልን ለቀው እንዲወጡ እንደሚፈልጉ የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ገለጹ፡፡

ኔታንያሁ ጉዳዩን አስመልክተው በሠጡት አስተያየት÷ በጥገኝነት እስራዔል የሚገኙ አፍሪካውያን ሥደተኞች በሙሉ በአስቸኳይ ሀገሪቷን ለቀው እንዲወጡም እንዲታሰብበት ማሳሰባቸውን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው ዕለት ይኅን ያሉት ÷ በትናንትናው ዕለት የኤርትራ ተቀናቃኞች ከእስራዔል ፖሊስ ጋር ደም አፋሳሽ ግጭት ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

በደቡብ ቴል አቪቭ በተቀሰቀሰው ግጭት ከደርዘን በላይ ሰዎች መቁሰላቸው በዘገባው ተመላክቷል፡፡

በእስራዔል የሚገኙት የኤርትራ ሥደተኞች በቀሰቀሱት ግጭት የግንባታ እንጨቶችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን እና ድንጋዮችን ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡

የሱቅ መስኮቶችን እና የፖሊስ መኪናዎችን መሰባበራቸውም ነው ተነገረው፡፡

የእስራዔል ፖሊሶች የተለያየ ዓይነት አድማ በታኝ ጭስ እና አስደንጋጭ የእጅ ቦምቦችን በመጠቀም ሁኔታውን በቁጥጥር ሥር ለማዋል መሞከራቸው ተገልጿል፡፡

የመረጃው ምንጭ FBC

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

03/09/2023

በአዲስ አበባ ከተማ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በአማራ ክልል እየተፈጸሙ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል!

የኢሰመጉ ጋዜጣዊ መግለጫ-ነሀሴ 26/2015 ዓ.ም

ሙሉውን የኢሰመጉ ጋዜጣዊ መግለጫ ከቴሌግራም ቻናላችንን ላይ ማግኝት ይችላሉ።

https://t.me/ehrco/1848

ጸሐይ ሪልስቴት ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው!ብዙ ወርቅ ብዙ የባንክ ካዝናዎች . . . እየተገኙ ነው!!
01/09/2023

ጸሐይ ሪልስቴት ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው!
ብዙ ወርቅ ብዙ የባንክ ካዝናዎች . . .
እየተገኙ ነው!!

 #ብሪክስ ከሰሞኑ ሀገራችን የብሪክስ ሀገራት ጥምረትን እንደምትቀላቀል ይፋ ተደርጓል። ብሪክስ የጠንካራ ኢኮኖሚ ሀገራት ጥምረት ብቻ ሳይሆን G7 ተብለው የሚጠሩት ያደጉ ሀገራትን የሚቀናቀን ...
01/09/2023

#ብሪክስ ከሰሞኑ ሀገራችን የብሪክስ ሀገራት ጥምረትን እንደምትቀላቀል ይፋ ተደርጓል።

ብሪክስ የጠንካራ ኢኮኖሚ ሀገራት ጥምረት ብቻ ሳይሆን G7 ተብለው የሚጠሩት ያደጉ ሀገራትን የሚቀናቀን ስብስብ ሆኗል። ታድያ በዚህ ሁሉ መሀል በርካታ እድሎች፣ ስጋቶች እና ውዝግቦች አሉ፣ ከትልልቆቹ ሚድያዎቻችን እንደምንሰማው ሁሉም "ሳር በሳር" ሳይሆን የራሱ ችግሮችን እና እድሎችን ይዞ ሊመጣ ስለሚችል ይህን ሀሳብ ላስፍር።

ስብስቡን ቻይና እና ሩስያ ወደ ፖለቲካ፣ ህንድ፣ ብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ ወደ ኢኮኖሚ አቅጣጫ ሲስቡት ይታያል። ይህም ማለት ቻይና እና ሩስያ ብሪክስን ከምእራባውያን ሀገራት ጋር ባላቸው ተቀናቃኝነት ፖለቲካውን ማስኬጃ አንድ መንገድ ማድረግ ይፈልጋሉ፣ እነ ህንድ እና ብራዚል ደግሞ በመሀከላቸው ንግድን በማሳለጥ ህዝባቸውን ከድህነት ማውጫ መንገድ እንዲሆን ይፈልጋሉ።

እንደ ኢራን ያሉ አዲስ ተጋባዥ ሀገራት ደግሞ ዶላርን ከአለም ግብይት ለማስወጣት (de-dollarization) የሚደረገውን ጥረት በብሪክስ አሳክተው የራሳቸውን ነዳጅ በሌላ ከረንሲ ለመቸብቸብ ተልመዋል (የኢራን ሚድያዎች እና ባለስልጣናት ይህን በግልፅ ባለፈው ሳምንት ሲሉ ነበር)።

በአርጀንቲና ቀኝ ዘመሞች ከሁለት ወር በሗላ በሚደረግ ምርጫ ካሸነፉ ሀገራቸው ብሪክስን እንዳትቀላቀል እንደሚያደርጉ እየዛቱ ነው፣ ምክንያታቸው ደግሞ የሁለት ሀያላን ቡድኖች ግብግብ አያገባንም በማለት እንዲሁም ሩስያን በመቃወም ነው።

ሳውዲ አረቢያ፣ ግብፅ፣ ኤምሬትስ የመካከለኛው ምስራቅ ፖለቲካን (እና የዶላር ረብጣን) በስሩ ለማድረግ የተሄደበት ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ባላት የህዝብ ብዛት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ ተመራጭ እንዳረጋት ተንታኖች ይጠቅሳሉ።

ወደ ሀገራችን ስናተኩር፣

በአዋጅ ቁጥር 790 አንቀፅ ቁጥር 4 መሰረት የሀገሪቱ ጠ/ሚር ሀገሪቱ የሀገራት ስብስብን እንድትቀላቀል እንዲያደርጉ ስልጣን ሰጥቷቸዋል። ኃላ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሪክስ አባልነት መመስረቻን ያፀድቃል።

ይህ እንዳለ ሆኖ፣ በርካቶች አሁን ላይ ቻይና እና ሩስያ ስብስቡ ላይ ያላቸውን የበላይነት በመጥቀስ ወደ ፖለቲካ ያዘመመ ተቋም እንደሆነ ይጠቅሳሉ። ወደፊት ይህ ተቀልብሶ ወደ ኢኮኖሚ የሚያጋድል ከሆነ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገራት እድል ሊሆን እንደሚችልም ያነሳሉ።

በግሌ እንደማስበው ግን ማንንም ለማስደሰት ወይም ለማስቀየም ሳይሆን የኢኮኖሚ እና ጂኦፖለቲካ ጥቅማችንን ለማሳካት ከተሄደ መልካም ነው።

አለበለዛ አሁን ሀገር ውስጥ ከሚታዩት ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ጋር ተደምሮ ከሌሎች ሀገሮች ጋር መላተም የሚያመጣው መላተም (fall-out) እጅግ የከፋ ሊሆን ይችላል።

መልካም ቀን።

31/08/2023

ፀሐይ ሪልስቴት አሁንም እንደተከበበ ነው

ቻይናዊው የፀሐይ ሪልስቴት ባለቤት እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ማተም ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ከተሰማ በኋላ ግቢው በፌደራል ፓሊስ እና በፀጥታ ኃይሎች እንደተከበበ ነው።

ሲኤምሲ የሚገኘው ፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ከቀን ጀምሮ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ ይገኛል። ብርበራው ምሽቱም ላይ ቀጥሏል። እስካሁን በተደረገ ፍተሻ እስካሁን የተረጋገጠ 80 ሻንጣ ሙሉ ዶላር መገኘቱን በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። የሻንጣው ቁጥር ይጨምራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ ይሰሩበት የነበረ የዶላር ማተሚያ እና ማቀናበሪያ ማሽን በግቢው ውስጥ ተገኝቶ በኢግዚቢትነት ተይዟል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ የቻይና ዜጎች ወርቅ እና የከበሩ ድንጋዮች ከኢትዮጵያ በገፍ እያወጡ በህገወጥ ሲሸጡ መያዛቸው የሚታወስ ነው።

በፀሀይ ሪልሰቴት የዶላር ማተም ተግባር ላይም ሆነ በማእድን ዘረፋው ከተጠርጣሪዎቹ ጀርባ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሉበት።

እንዲህ አይነቱ ወንጀል በሀገር ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት ከማወጅ የሚተናነስ አይደለም።
ዘሀበሻ

ሰበርበሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩበት የፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ባለቤት (ቻይናዊ) እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአሁኑ ሰዓት ሲኤምሲ የሚገኘው ፀ...
31/08/2023

ሰበር
በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የሚኖሩበት የፀሐይ ሪልስቴት አፓርትመንት ባለቤት (ቻይናዊ) እና ግብረአበሮቹ በ"ዶላር ወንጀል" ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ዋሉ። በአሁኑ ሰዓት ሲኤምሲ የሚገኘው ፀሐይ ሪልስቴት በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ ተከቦ ከፍተኛ ፍተሻ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል። ቁጥሩ ያልታወቀ የዶላር ክምችት በቁጥጥር ስር መዋሉንም ዘ-ሐበሻ ከፖሊስ ምንጮች ሰምቷል። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን ይዘን እንቀርባለን።
የ ZeHabesha ዘገባ ነው

ከነዳጅ ዋጋ 📈ቤንዚን ላይ ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ።የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀ...
29/08/2023

ከነዳጅ ዋጋ 📈

ቤንዚን ላይ ከ5 ብር በላይ ጭማሪ ተደረገ።

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።

ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ይፋ መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሚያዝያ ወር 2015 ጀምሮ እስከሰኔ ወር መጨረሻ ድረስ አንጻራዊ መረጋጋት እንደታየበት ገልጿል፡፡

በዚህም ፥ ላለፉት አራት ወራት በችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ለውጥ ሳይደረግ መቆየቱን አስታውሷል፡፡

ሆኖም ግን የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከሐምሌ ጀምሮ የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሳየ በመምጣቱ ዋጋውን ማሻሻያ ማድረግ ማስፈለጉ ተገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት ፦

1. ቤንዚን ----------ብር 74.85 በሊትር
2. ነጭ ናፍጣ -----------ብር 76.34 በሊትር
3. ኬሮሲን ብር ------------76.34 በሊትር
4. የአውሮፕላን ነዳጅ ---------ብር 68.58 በሊትር
5. ቀላል ጥቁር ናፍጣ -----------62.22 በሊትር
6. ከባድ ጥቁር ናፍጣ -----------61.07 በሊትር መሆኑም ተመላክቷል፡፡

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

27/08/2023

ኢትዮጵያ 4ኛ ፣ 12ኛ እና 13ኛ

27/08/2023

ኢትዮጵያ
5ኛ ፣ 6ኛ እና 8ኛ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio-World News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share