Dire Media

Dire Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dire Media, Media/News Company, .

 |            ሰበር ዜና           "ከንቲባው ቃላቸውን ሰተዋል"============================የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን በህዝብ አመኔታ እንዲያጣ አድርገሀል" በ...
04/07/2022

| ሰበር ዜና
"ከንቲባው ቃላቸውን ሰተዋል"
============================
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን በህዝብ አመኔታ እንዲያጣ አድርገሀል" በሚል ምክንያት በእስር ላይ የሚገኘው አቶ በቃል ምስጋናው ለሶስትኛ ጊዜ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀረበ። በቃል ምስጋነው ከጠበቃው አቶ እንድሪያስ ተካልኝ ጋር ችሎት የቀረበ ሲሆን ችሎቱም ከአሁን ቀደሙ በተለየ በፖሊስ እና በጠበቃው መካከል ክርክር የተደረገ ሲሆን ክቡር ፍርድ ቤቱም የሁለቱንም ሀሳብ ተከታትሏል።

ፖሊስ ተለዋጭ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን ምክንያት ብሎ ያቀረበውም "የባለስልጣናትን ቃል መቀበል ፣ የባንኮች መልስ እንዲሁም የፎረንሲክ ምርመራ ሪፖርቶች ውጤት ስላልደረሰኝ ተጨማሪ ቀጠሮ ይሰጥልኝ" ሲል ለችሎቱ አቅርቧል። ፖሊስ ከዚህ ጋር አያይዞ ቃላቸውን የተቀበላቸው የተወሰኑ የመስተዳደሩ ባለስልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ ከእነሱም ውስጥ የመስተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አንዱ መሆናቸውን አሳውቋል።

ከንቲባ አቶ ከድር ከአሁን ቀደም በመስተዳደሩ የስብሰባ አዳራሽ በተካሄደው ስብሰባ ላይ የበቃል ምስጋናው እስር ከእሳቸው ውጪ እንደሆነ ቢናገሩም ከፍርድ ቤቱ ሂደት መረዳት እንደተቻለው ጉዳዩ በቀጥታ ከእሳቸው እና ከተለያዩ የከተማ አስተዳደሩ ባለስልጣናት ጋር እንደሚገናኝ ለመረዳት መቻላቸውን በስፍራው የተገኙ የአቶ በቃል ምስጋናው ቤተሰቦች እና ወዳጆች የገለፁ ሲሆን አክለውም ይህ ጉዳይ ግለሰባዊ እንዳይሆን ከፍተኛ ጥርጣሬና ስጋት እንዳደረባቸው ዘጋቢያችን ከስፍራው ያደረሰን ዘገባ ያመለክታል። ፍርድ ቤቱም ለሐምሌ7 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

------ DMN ------
Like our page ➣
DMN
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 |    ሦስተኛ ችሎትያለምንም ክስ በእስር ቤት 27ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አቶ በቃል ምስጋናው ለሦስተኛ ጊዜ ዛሬ ሰኔ27/2014አ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባል። በተጨማሪም ከአሁን ቀደም በነበሩት ...
04/07/2022

| ሦስተኛ ችሎት

ያለምንም ክስ በእስር ቤት 27ኛ ቀኑን ያስቆጠረው አቶ በቃል ምስጋናው ለሦስተኛ ጊዜ ዛሬ ሰኔ27/2014አ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባል። በተጨማሪም ከአሁን ቀደም በነበሩት ችሎቶች ምንም አይነት ክስ ያልተመሰረተበት ሲሆን የዛሬው ችሎት ከበፊቶቹ ሁለት ችሎቶች በተለየ አቃቤ ህግ ክስ ካልመሰረተ አቶ በቃልን በዋስ ወይም ፋይሉን ዘግቶ በነፃ ሊያሰናብተው ይገባል ሲሊ ለጉዳዩ እና ለአቶ በቃል ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች ገለፁ።

አቶ በቃል ሀሳቡን በነፃነት የመግለፅ መብቱን ተጠቅሞ ሀገርን ወገንን የሚጠቅም የተለያዩ ሀሳቦችን በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራት ይታወቃል። ሆኖም ግን የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር እና የሕግ የበላይነትን የሚገልፁ ሀሳቦች በአስተዳደሩ የተለያየ የስልጣን እርከን ላይ ያሉ ሹማምንቶችን በእጅጉ የሚያስከፉ ነበሩ። እስሩም ከዚህ ጋር በተገናኘ እንደሆነ በግለሰቡ ወዳጆች ይታመናል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 |አቶ በቃል ምስጋናውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በመታመማቸው ወደ ድልጮራ ሆስፒታል ተወሰዱ። አቶ በቃል ምስጋናውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በመታመማቸው ወደ ድልጮራ ሆስፒታል ተወሰዱ። በድልጮ...
30/06/2022

|አቶ በቃል ምስጋናውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በመታመማቸው ወደ ድልጮራ ሆስፒታል ተወሰዱ።

አቶ በቃል ምስጋናውን ጨምሮ በርካታ እስረኞች በመታመማቸው ወደ ድልጮራ ሆስፒታል ተወሰዱ። በድልጮራ ሆስፒታል ህክምናቸውን ለመከታተል የተወሰዱት አስረኞች በሽታውም ቀላል እንደሆነና ለከፋ አደጋ እንደማያጋልጥ የህክምና ባለሞያዎች ገልፀውላቸው ከዚራ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተወስደዋል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 |በሰላማዊ የትግል ገፅ ለሰው ልጆች ፍትህና ነፃነት የሚከፈል ዋጋ ከዚህም በላይ ውድ መሆኑ  ግልፅ ነው❗️❗️ በቃል ምስጋናው ( Bekal Ze Dire ) የሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት እ...
30/06/2022

|በሰላማዊ የትግል ገፅ ለሰው ልጆች ፍትህና ነፃነት የሚከፈል ዋጋ ከዚህም በላይ ውድ መሆኑ ግልፅ ነው❗️❗️

በቃል ምስጋናው ( Bekal Ze Dire ) የሰው ልጆች ነፃነትና እኩልነት እንዲከበር እንዲሁም ማህበራዊ ፍትህ የሰፈነባት ከተማ እንድትፈጠር በሰላማዊ መንገድ ከመታገል ያለፈ ትልም ሳይኖረው በአሳሪዎች የእጅ መዳፍ ስር ወድቋል❗️❗️

ፍትህ ለእውነት ከሚታገሉ ሰብዓውያን ጋር በዙፋኗ ትኖራለች❗️❗️

በቃል ለእስር ከተዳረገ ዛሬ #22ኛ ቀኑ ነው።

By Amanuel Tadesse

------ DMN ------
Like our page ➣
DMN
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwo

 | "ወጣቶችን በማፈን መልካም ስም መገንባት"*********************************የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ ልዑክ ወደ አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ፓሪስ ተጉዟል። ፓ...
29/06/2022

| "ወጣቶችን በማፈን መልካም ስም መገንባት"
*********************************
የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተመራ ልዑክ ወደ አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ፓሪስ ተጉዟል። ፓሪስ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ከድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ጋር ውይይት አድርገዋል። የከንቲባው ጉዞ በቅርቡ ሊዘጋጅ ላሰበው "ናፍቆት ድሬዳዋ" የገቢ ማሰባሰቢያ ቅስቀሳ ለማድረግ የታለመ ሲሆን በዚሁም የአስተዳደሩን መልካም ስም ለመገንባት ታቅዶ የተደረገ ጊዞ መሆንን ለዲ.ኤም.ኤን የደረሳት መረጃ ያመላክታል።

የአቶ ከድር ጁሀር የአስተዳደር መዋቅር በበርካታ ብልሹ አሰራር የሚታዩበት መሆኑን በበርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች የሚገለፅ ሲሆን አስተዳደሩም ይህን ለማረም ቁርጠኛነቱን በመዋቅሮቹ ውስጥ የተሰገሰጉትን ሙሰኛ አካላት በመታገል እና እርማት በመውሰድ ሊያረጋግጥ ይገባል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ይህንን ተከትሎ በርካታ የከተማዋ ወጣቶች "ፍትህ ይስፈን: መልካም አስተዳደር ይኑረን: ሙሰኝነት ይጥፋ" በማለት ተቃውሞአቸውን በተለያዩ መገናኝ ብዙሀን ሲገልፁ ይስተዋላል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ግን የከተማ አስተዳደሩ እየተከለያ ያለው አካሄድ ከመፍትሄው ጋር ፍፁም ተቃራኒ በሆነ መንገድ ለመልካም አስተዳደር መስፈን እና ለሁለንተናዊ የከተማዋ ብልፅግና ማህበረሰቡን በማንቃት የሚታወቁ ወጣቶችን ከያሉበት በማፈን ዝማ ለማሰኘት በአስተዳደሩ በዘመቻ እየተሰራ ነው ሲሉ ነዋሪዎቹ ያማርራሉ።

በአህመድ ናስር

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ተከፍቶ በከፊል ለስፖርት ወዳዱ የድሬዳዋ ሰው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሶ ዘብጥያ የወረደው ወጣት በቃል ምስጋናው በእ...
28/06/2022

| የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ተከፍቶ በከፊል ለስፖርት ወዳዱ የድሬዳዋ ሰው አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተከሶ ዘብጥያ የወረደው ወጣት በቃል ምስጋናው በእስር መቆየቱ ትልቅ ፍርደ ገምድልነት ነው በሚል በርካታ ወጣቶች ቅሬታቸውን እያሰሙ ይገኛሉ። አቶ በቃል ዛሬ 21ኛ ቀነኑን በእስር እያሳለፈ ይገኛል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | አቶ በቃል ምስጋናው ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ ማስረጃዎቼን ለማጠናቀር በማለት ለጠየቀው የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የአስር ቀናትን ለ 27/10/2014ዓ .ም ቀጠሮ ሰቶበታል። ፖሊስ...
24/06/2022

| አቶ በቃል ምስጋናው ዛሬ በዋለው ችሎት ፖሊስ ማስረጃዎቼን ለማጠናቀር በማለት ለጠየቀው የምርመራ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የአስር ቀናትን ለ 27/10/2014ዓ .ም ቀጠሮ ሰቶበታል። ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት በጠየቀበት ጊዜ ያቀረባቸው ምክንያቶች
1ኛ) የተጠርጣሪ በቃል ምስጋናውን የባንክ እንቅስቃሴ ለማጣራት
2ኛ) የአቶ በቃል ምስጋናው የላፕቶብ የሞባይል እና መሰል ንበረቶች የፎረንሲክ ምርመራ እንዲደረግባቸው
3ኛ) ከነማን ጋር ግንኙነት አለው የሚሉ እና በአራተኛነት የሰው የመለየት ማለትም የተለያዩ ሰዎችን በአካል ችሎት በማቅረብ አቶ በቃልን ምስጋናውን የመለየት ጥያቄ ማቅረብ የሚሉትን ምክንያቶች ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ የጠየቀባቸው ምክንያቶች መሆናቸውን Dmn አረጋግጣለች። በችሎቱ የአቶ በቃል የስነ ልቦና እና የሞራል ብሎም አካላዊ ሁኔታ በጣም ጥሩ በሚባልበት ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ለመመልከት ተችላል ሲል ዘጋቢያችን ገልፇል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | አቶ በቃል ምስጋናው በዛሬ እለት 17/10/2014 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባል። በዛሬው ችሎት የአቶ በቃል የክስ ሂደት የሚታይ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከችሎት በኋላ የምንዘ...
24/06/2022

| አቶ በቃል ምስጋናው በዛሬ እለት 17/10/2014 ዓ/ም ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባል። በዛሬው ችሎት የአቶ በቃል የክስ ሂደት የሚታይ ሲሆን ዝርዝር መረጃውን ከችሎት በኋላ የምንዘግብ ይሆናል። በድሬዳዋ ያላቹ ወጣቶች በችሎቱ በመታደም ከጎኑ እንድትሆኑ DMN ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 |የ82 ዓመቷ አዛውንት በሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝግበዋል።ባርባራ ሀምበርት የተባሉት አዛውንት 125 ኪሎ ሜትርን በ24 ሰዓት ውስጥ ሮጠው ጨርሰዋል።አዘውንቷ የፓሪስና የኒውዮርክ...
21/06/2022

|የ82 ዓመቷ አዛውንት በሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን አስመዝግበዋል።

ባርባራ ሀምበርት የተባሉት አዛውንት 125 ኪሎ ሜትርን በ24 ሰዓት ውስጥ ሮጠው ጨርሰዋል።

አዘውንቷ የፓሪስና የኒውዮርክ ማራቶንን ጨምሮ በ137 የሩጫ ውድድሮችና በ54 ማራቶኖች ላይ ተሳተፈዋል
የ82 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆኑት ፈረንሳዊቷ ባርባራ ሀምበርት በሩጫ አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገባቸው ተገለፀ።
ፈረንሳዊቷ አዘውንት ባርባራ ሀምበርት 125 ኪሎ ሜትርን ርቀትን በ24 ሰዓት ውስጥ ሮጠው በመጨረስ አዲስ ክብረወሰን በእጃቸው ማስገባታቸውን ኦዲቲ ሴንተራል ዘግቧል።
ባራ ሀምበርት ባሳለፍነው ግንቦት ወር መጨረሻ ላይበ ፈረንሳይ በሪቭ ላ ጋሊርዴ በተካሄደ ሻምፒየንስ ሺፕ ላይ ነው በእድሜያቸው ክልል የተዘጋጀውን ውድድር በ24 ሰዓታት ውስጥ ማጠናቀቅ የቻሉት።

ክብረወሰኑ ከዚህ በፊት በጀርመናዊት አዛውንት ተይዞ የነበረ ሲሆን፤ ጀርመናዊቷ አዛውንት በ24 ሰዓት ውስጥ 105 ኪሎ ሜትሮችን በመሮጥ ነበር ክብረወሰኑን ይዘው የቆዩት።
ፈረንሳዊቷ አዘውንት ባርባራ ሀምበርት በጀርመናዊቷ አዛውንት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በ20 ኪሎ ሜትር በማሻሻል ነው በእጃቸው ማስገባት የቻሉት።
ባርባራ ሀምበርት ሩጫ መሮጥ የጀመሩት በ43 ዓመታቸው እንደሆነ የተናገሩ ሲሆን፤ባለፉት 39 ዓመታት የፓሪስ እና የኒውዮርክ ማራቶንን ጨምሮ በ137 የሩጫ ውድድሮች እና በ54 ማራቶኖች ላይ ተሳተፈዋል።

“በጎዳናዎች ላይ ስሮጥ ነጻነት ይሰማኛል” የሚሉት ፈረንሳዊቷ አዘውንት ባርባራ ሀምበርት፤ “አእምሮዬ ነጻ ይሆናል” ሲሉም ተናግረዋል።

አዘውንቷ ባርባራ ሀምበርት የልጅ ልጅ ልጅ ማየት መቻላቸውን የሚናገሩት አዛውንቷ፤ እስካሁን ታመው መድሃኒት ወስደው እንደማያውቁ እና ጤንነትን ለመጠበቅ ስፖርት መስራት ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ።

ዘገባው የአል ዓይን ነው

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 |ለድሬዳዋ መቆርቆር ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ባለታሪኮች ውስጥ የኢትዮ-ምድር ባቡር ቀዳሚው ነው፡፡ የምድር ባቡር ታሪካዊ ገፅ የደም ያህል ከከተማው ማህበረሰብ ጋር የተዋሀደ፤...
21/06/2022

|ለድሬዳዋ መቆርቆር ትልቅ አስተዋፅኦ ካደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ባለታሪኮች ውስጥ የኢትዮ-ምድር ባቡር ቀዳሚው ነው፡፡ የምድር ባቡር ታሪካዊ ገፅ የደም ያህል ከከተማው ማህበረሰብ ጋር የተዋሀደ፤ በዘመን ቅብብሎሽ ታትሞ እልፍ አእላፍ ዓመታትን የሚኖር ቅርስ ነው፡፡

የዚህ ቅርስ ባለቤት የሆነው ህዝብ በምድር ባቡር ጉዳይ ከመጣህበት በነፍስ አይደራደርም! በባለሟሎች ሽንገላ አይደናገርም! በድርጎ ተቀባይ ምንዝሮች ጩኸት አይሸበርም! ከእልፍኝ አዳራሹ ድግስ በማይታጡ ምስለኔዎች ከመርህ ወርዶ የህልውናውን መሰረት አይንድም!!

የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች የከተማው ከንቲባን ጨምሮ የምድር ባቡርን ጉዳይ በተለይ የብዙ ወጣቶችን ባህሪ መግሪያ የሆነውን ታሪካዊ ሜዳ የህዝቡን ታሪካዊ ዳራ መነሻ አድርገው ከቆሙበት የስህተት መንገድ መለስ ብለው ባለቤትነቱን ለህዝብ ባረጋገጠ መልኩ ከግለሰብ እጅ ወደ ህዝባዊ ተቋም (ስፖርት ኮምሽን) መስጠታቸው ሚዛናዊ ውሳኔ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡፡

የ በቃል ምስጋናው Bekal Dire የትግል መነሻና መዳረሻም ይህ የማህበረሰቡ መርህ ነው! እስሩም ለዚህ መርህ መቆሙ ማወራረጃ ፖለቲካዊ ግብረ-መልስ ነው! መፍትሔውም ፖለቲካዊ ነው!

ፍትህ ከእውነት ጋር ለሚቆሙ ሰዎች ብቻ ጥብቅና ትቆማለች!

Amanuel tadesse

#11

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | "አንዱን ስህተት ለማረም ሌላ ስህተት መስራት"👉የድሬዳዋ ምድር ባቡር የስፖርት ማዘውተሪያ ማለትም ኳስ ሜዳ ፣ ቅርጫት ኳስ ሜዳ ፣የመዝናኛ አዳዳራሽ ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ዙሪያ ያሉ መ...
17/06/2022

| "አንዱን ስህተት ለማረም ሌላ ስህተት መስራት"

👉የድሬዳዋ ምድር ባቡር የስፖርት ማዘውተሪያ ማለትም ኳስ ሜዳ ፣ ቅርጫት ኳስ ሜዳ ፣የመዝናኛ አዳዳራሽ ፣ በስፖርት ማዘውተሪያ ዙሪያ ያሉ መኖሪያ ቤቶችን ያጠቃለለ ባጠቃላይ 17565.7 ካሬ በ20,358646 .30ብር በሆነ የሊዝ ዋጋ ለአቶ ፉአድ አባስ ለተባሉ ግለሰብ በቀን 05/02/2014 ዓ.ም ተሽጦ የካርታ እና የግንባታ ፍቃድ መሰጠቱ የሚታወስ ነው። ይህን ተከትሎ ጥቂት የማይባሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ለግለሰብ መተላለፉን እና የተላለፈበት መንገድ ግልፅ አለመሆን ብሎም የዋጋው መውረድን በመቃወም "ንብረትነቱ ወደ መንግስት ይመለስና፤ መንግስት ያልማው" የሚሉ ድምፆችን ማህበራዊ ሚዲያና የዩቱብ መገናኛ ብዙሀንን በመጠቀም ከፍተኛ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ቆይተዋል። የዚህ ኢ-ፍትሀዊ(ህገ-ወጥ) መሬት ንግድ በመቃወም ከሚታወቁት አቶ በቃል ምስጋናው ድሬዳዋ ካፈራቻቸው ወጣቶች ውስጥ በመጀመሪያ ደረጀ የሚቀመጥ ነው።

👉የአቶ በቃል ምስጋናው ልፋትና ጥረት እንዲሁን የሀገር ወዳዱ የድሬዳዋ ወጣቶች ከፍተኛ ንቅናቄ ፍሬ አፍርቶ የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ሜዳ እና በዙሪያው ያሉ መኖሪያ ቤቶች ለግለሰብ ከመዘዋር ተርፈዋል። ይህንን ያረጋገጡት የመስተዳድሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ሲሆኑ የስፖርት ማዘውተሪያውንም በመስተዳደሩ ጥረት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እንደሚያለሙት ቃል መግባታቸው ነው የታወቀው። ይህ ለድሬዳዋ ወጣት ታዲዎች እና ለመላው ስፖርት ወዳድ ማህበረሰብ እጅግ በጣም አስደሳች ዜና ነው።
👉ይሁንና ይህ እንዲሆን ያለውን አቅም ሁሉ አሟጦ በመጠቀም ኢፍትሀዊነትን የታገለው ወጣት በቃል ምስጋናው ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወደ ዘብጥያ መውረዱ ይታወቃል። ምንም እንኳን አቶ በቃል የታገለለት አላማ ከግብ የደረሰ ቢሆንም ከአላማው መሳካት ማዶ ዘብጥያ ተወርውሮ ይገኛል። የከተማ አስተዳደሩም ከህዝብ ጋር እልህ መጋባቱን ትቶ ነገሩን ከነዋሪው ፍላጎት አናፃር ለመፍታት የሄደበት እርቀት የሚያስመሰግነው ቢሆንም ለዚህ አላማ በመረጃና በማስረጃ የታገለውን አቶ በቃል ምስጋናውን ዘብጥያ ማውረዱ እጅግ በጣም የሚያሳዝንና በምንም መልኩ ተቀባይነት የሌለው ኢ ፍትሀዊነት ነው።

👉አንዱን ስህተት ለማረም ሌላ ስህተት መስራት ባሉበት እንደመራመድ ያለ ከንቱ ስራ ነው። ስለሆነም የከተማ መስተዳደሩ የህገ-ወጥ የመሬት ሽያጩን ካረመበት ትክክለኛነት በላይ አቶ በቃልን በእስር ቤት የሚያቆይበት ምክንያት በእጅጉ ነው። ስህተትን አርሞ ለመታረሙ ምክንያት የሆነን አካል ማሰር የለየለት አለማወቅም ጭምር ነው። የከተማ አስተዳደሩ አቶ በቃልን በእስር ቤት ማቆየቱ የሚጨምርለት አንዳች በጎ ነገር ባይኖረውም ያልታረመ ያልፀዳ አስተዳደር መሆኑን ግን በአደባባይ የሚያጋልጥ ነው። ስለዚህ ከእርማቱ ባሻገር አቶ በቃልን በነፃ እንዲያሰናብቱት ድምፄን አሰማለሁ።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 | " የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ሽያጭ ተቋረጠ"የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ "ለግለሰብ...
16/06/2022

| " የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ሽያጭ ተቋረጠ"

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍል አባላት ጋር በነበራቸው ቆይታ "ለግለሰብ ይተላለፍ የተባለው ውሳኔ" በህብረተሰቡ ስላልታመነበት እና ንብረትነቱ ከተማ አስተዳደሩ ስር ሆኖ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማደስ ለህብረተሰቡ ክፍት እንደሚሆን ገልፀዋል።

እንደሚታወሰው በዚህ ማህበራዊ ሚዲያ የስፖርት ማዘውተሪያው ለግለሰብ መዘዋወሩን በመቃወም የሚሰሞ ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፆች ነበሩ። ከዚህ ጋር በተያያዘ "መንግስት በህብረተሰቡ አመኔታ እንዳይኖረው አድግረሀል" በሚል የማህበረሰብ አንቂ የሆነው አቶ በቃል ምስጋና ዘብጥያ ወርዷል። አቶ በቃል የድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ለግለሰብ ኘሸጡን በመቃወም በማስረጃ የተደገፈ ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያሰማ እና ሲታገል የነበረ ወጣት መሆኑ ይታወቃል። DMN ያናገረቻቸው የከተማ ወጣቶች "ጉዳዩ እንደዚህ አይነት ውሳኔ ላይ ከደረሰ በዚህ ሰበብ የታሰረው አቶ በቃል ነፃ ሊወጣ ይገላ ብለዋል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 | አቶ በቃል ምስጋናው ከመኖሪያ ቤቱ ታስሮ ከተወሰደ ዛሬ አንድ ሳምንት አስቆጠረ። የአቶ በቃል ምስጋናን መታሰር "ፍትሀዊ" አይደለም ሲሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ...
15/06/2022

| አቶ በቃል ምስጋናው ከመኖሪያ ቤቱ ታስሮ ከተወሰደ ዛሬ አንድ ሳምንት አስቆጠረ። የአቶ በቃል ምስጋናን መታሰር "ፍትሀዊ" አይደለም ሲሉ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰሙ ሲሆን አሁንም በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

ሰኔ 3/10/2014ዓ.ም በዋለው ችሎት "መንግስት በድሬዳዋ ምድር ባቡር ምክንያት በህዝብ አመኔታ እንዲያጣ አድርገሀል" በሚል የክስ መዝገብ የተከፈተበት የማህበረሰብ አንቂ አቶ በቃል ምስጋና ፖሊስ በጠየቀው መሰረት ለፊታችን ሰኔ 17 ተለዋጭ ቀጠሮ እንደተሰጠበት ይታወሳል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 | ታዋቂው የትግረኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ   አረፈ። በድንገት ባጋጠመው ህመም ምክንያት ላለፉት አራት ቀናት በአዲስ ሕይወት ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም  ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። DMN...
12/06/2022

| ታዋቂው የትግረኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አረፈ። በድንገት ባጋጠመው ህመም ምክንያት ላለፉት አራት ቀናት በአዲስ ሕይወት ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ አልተቻለም። DMN በአርቲስቱ እረፍት የተሰማትን ሀዘን እየገለፀች ለወዳጅ ዘመደቹ መፅናናትን ትመኛለች።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 | ድሬዳዋ ያሉ ጠበቆች..."ለደህንነታችን ስለምንፈራ ጥብቅና አንቆምለትም!""መንግስትን በህዝብ አመኔታ እንዳይኖረው አድርገሀል" በሚል የክስ መዝገብ ለተከፈተበት ለአቶ በቃል ምስጋነው ቤተ...
11/06/2022

| ድሬዳዋ ያሉ ጠበቆች...

"ለደህንነታችን ስለምንፈራ ጥብቅና አንቆምለትም!"

"መንግስትን በህዝብ አመኔታ እንዳይኖረው አድርገሀል" በሚል የክስ መዝገብ ለተከፈተበት ለአቶ በቃል ምስጋነው ቤተሰቦቹ እና ወዳጅ ዘመዶቹ በድሬዳዋ ያሉ አንዳንድ ጠበቆች "ለደህንነታችን ስለምንፈራ ጥብቅና አንቆምለትም!" ማለታቸውን DMN ከውስጥ አዋቂዎች ለመረዳት የቻለች ሲሆን ይህ ሁኔታ ከተማዋ በምን አይነት አሳሳቢ የደህነነት ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ያየነበት ነው ሲሉም ሀዘናቸውን ገልፀዋል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 |    ለኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች  በድሬዳዋ ከተማ ለሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች ብሎም በከተማዋ የተንሰራፋውን አይን ያወጣ ሌብነት ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ሲሞግት የነበረው Bek...
11/06/2022

| ለኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች

በድሬዳዋ ከተማ ለሚፈፀሙ አስተዳደራዊ በደሎች ብሎም በከተማዋ የተንሰራፋውን አይን ያወጣ ሌብነት ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ሲሞግት የነበረው Bekal Dire (በቃሉ ምስጋናው) ባለፈው ዕረቡ ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ወደ ድሬዳዋ መወሰዱ ይታወቃል።

ከከተማዋ የመጡት የፖሊስ አባላት ከእርሱም አልፎ ወላጅ እናቱን ሲያንገላቷቸው እንደነበሩ እህቱ ገልፃልኛለች እኚሁ ፖሊሶች የመበርበሪያ ፈቃድ ሳይዙ ለረጅም ሰዓታት የእናቱን ቤት በማሸግ ሲበረብሩ ቆይተው ያሻቸውን ወስደው ወደ ድሬዳዋ ይዘውት ሄደዋል ።

በትላንትናው ዕለት በድድዳዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበው በቃሉ ምስጋናው ለ ሰኔ 17/2014 ዓም በድጋሚ ተቀጥሯል። እጅግ በጣም እሚያስገርመው ፍርድቤት ቀርቦ ክሱን እሚይዝለት ጠበቃ ሊያገኝ አለመቻሉ ነው በድሬዳዋ ከተማ እሚገኙ ጠበቆች "ለደህንነታችን ስለምንፈራ ጥብቅና ልንቆምለት አንችልም" ብለዋል። 😭

ጥያቄ አለኝ ❗❗❗

ለኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ማህበር ፣ ለሰብዓዊ መብት ተሟጋች ፣ለኢትዮጵያ ተከላካይ ጠበቆች ማህበር ፣ እንዲሁም ለሃገር ወዳድ የህግ ባለሞያዎች ይድረስልኝ።

*ጥያቄ 1

አንድ ህግን አስከብራለሁ እሚል አካል የፍርድቤት መጥሪያ ብቻ ይዞ የመበርበሪያ ፍቃድ ሳይዝ የሰው ቤት መበርበር እንዲሁም የተጠርጣሪውን ንብረቶችን መውሰድ ይችላል ወይ?

*ጥያቄ 2

ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ተይዞ ወደ ድሬዳዋ የሄደ ሲሆን እዛ እሚገኙ ጠበቆች ጥብቅና እንዲቆሙለት ሲጠየቁ "የከሰሰው የበላይ አካል ስለሆነ ጥብቅና አንቆምም" ብለዋል ።መንግስት ባለበት ሃገር እንዲህ አይነት ነገር ሲፈፀም ምንድነው እሚደረገው ?

ጥያቄ 3

እኔ ስከማውቀው ድረስ አንድ ሰው ጉዳዩ በዝግ ችሎት እሚታየው ለምሳሌ የተደፈረች ሴት ስትኖር እና ወንጀለኛው ድርጊቱን ለፍርድ ቤቱ በሚያስረዳበት ወቅት ለነገ የትዳር ወይም ማህበራዊ ሂወቷ ላይ እሚፈጥረው አሉታዊ ተፅእኖ ስለሚኖር ተብሎ የፍርድ ሂደቱ በዝግ እንዲታይ ይደረጋል አሊያም ዘግናኝ ወንጀል ወይ ደግሞ የሃገር ክህደት ወንጀል ተፈፅሟል ሲባል ችልቱ በዝግ ይታያል ።
ወደ ጥያቄዬ ስመለስ ተጠርጣሪው በቃሉ ምስጋናውን
የተከሰሰበት ወንጀል "ህዝብን ከመንግሥት ጋር ለማጋጨት" በሚል እና በምድር ባቡር ጉዳይ ነው(የምድር ባቡር ጉዳይ ማለት ተከሳሹን ጥርስ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው የመሬት ጉዳይ ነው አንጋፋው የኢትዮ ምድርባቡር ድርጅት ይዞታ የሆነው የድርጅቱ የሰራተኞቹ ብሎም የከተማዋ ነዋሪዎች የስፖርት ማዘውተሪያ የሆነውን ሰፊ ሜዳ ከህግ ውጪ ለባለሃብቶች ሊሸጥ መሆኑን የሰማው ተከሳሽ በማስረጃ ጭምር Deradawa Media Network ወይም DMN በተሰኘው ብሎጉ ላይ አጋልጧል ።ታዲያ እነዚህ ሁለት ክሶች ችሎቱ ዝግ እንዲሆን ያስገድዳሉ ወይ?

ጥያቄ 4

ተጠርጣሪው እንዴት የከሰሰውን አካል ማወቅ አይችልም? ከሳሹ ማን እንደሆነ ሲጠይቅ "ከሳሽህ የበላይ አካል ነው ተብሏል" በህግ ፊት የበላይ እና የበታች አለ ወይ?
በቃሉ ምስጋናው በተደጋጋሚ ለድሬዳዋ ህዝብ ድምፅ ሆኗል ፤ብልሹ አሰራርን እና ሌብነትን ታግሏል፤ ሁልጊዜ ያስገርመኝ የነበረበው ግን አሉቧልታን መሰረት አድርጎ አለማውራቱ ነው።
ለእያንዳንዱ መረጃዎቹ የተጠናከረ የሰነድ ማስረጃ መያዙና ይሄንንም ሲያገኝ በድፍረት ይፅፈዋል በዚህም በተደጋጋሚ ዛቻዎች ደርሰውበታል ።
"ህግ አስከብራለሁ እያሉ" ህግን መጣስ ወደለየለት አምባገነንነት መግባት ነው እና ቆም ብለን እናስብበት
(Bekal Dire )

በየኋላሸት ዘሪሁን

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 | ያለውን ችግር በእርቅ ቢፈቱት ይሻላል...ነዋሪነታቸው ከሀገር ውጭ ያደረጉ የድሬዳዋ ልጆች የ አቶ በቃል ምስጋናውን ጉዳይ ከተከበሩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር ጋ...
11/06/2022

| ያለውን ችግር በእርቅ ቢፈቱት ይሻላል...

ነዋሪነታቸው ከሀገር ውጭ ያደረጉ የድሬዳዋ ልጆች የ አቶ በቃል ምስጋናውን ጉዳይ ከተከበሩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከዲር ጁሀር ጋር በእርቅ ቢፈቱት ይሻልል ሲሉ ለDMN ገለፁ።

ዲያስፖራዎቹ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በግል መልካም ስብዕና ያላቸው በመሆኑ ጉዳዩን በሀገር ባህል መሰረት በእርቅ ሊፈቱት ይገባል ብለዋል። ጉዳዩ ከድሬዳዋዊነት ባህል ያፈነገጠ እንደሆነና በዚህ ደረጃ ብልሹ አሰራርን መቃወም ለእስር የሚዳርግ ጉዳይ መሆኑን እና በአቶ ከድር ጁሀር የስልጣን ዘመን ይህ መደረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው አክለው ገልፀዋል።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork።

 |       ሰበር ዜና ችሎት"ህዝብ በመስተዳደሩ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው አድርገሀል"===========================የማህበረሰብ አንቂ የሆኑት አቶ በቃል ምስጋናው ዛሬ እረፋዱ ...
10/06/2022

| ሰበር ዜና ችሎት

"ህዝብ በመስተዳደሩ ላይ አመኔታ እንዳይኖረው አድርገሀል"
===========================
የማህበረሰብ አንቂ የሆኑት አቶ በቃል ምስጋናው ዛሬ እረፋዱ ላይ ድሬዳዋ ምስራቅ ጀግኖች ትምህርት ቤት ፊትለፊት በሚገኘው ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን ችሎቱም ያለ ማንም ታዛቢ በዝግ ተደርጓል።

በችሎቱ አቶ በቃል ከሳሼ ማን ነው? ብለው በጠየቁበት ወቅት ከከተማ አስተዳደሩ የበላይ አካል እንደሆነ ብቻ በደፈናው የተነገረው ሲሆን ክሱም

" የምድር ባቡርን ሜዳ በተመለከተ ህብረተሰቡ ለከተማው አስተዳደር አመኔታ እንዳይኖረው አድርገሀል በዚህም ህዝብ ለህዝብ ልታጋጭ አነሳስተሀል"

የሚል ነው። ችሎቱም እጅግ አጭር የነበረ ሲሆን አሁን ከዚራ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ማረፊያ ቤት መልሰውታል።

DMN አቶ በቃል በተረጋጋና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ችላለች።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 ! በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊጀመር ነውየትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የብሄራዊ ሎጂስቲክስ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የፌደራል አመራሮች በድሬዳዋ ነፃ የን...
10/06/2022

! በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊጀመር ነው

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የብሄራዊ ሎጂስቲክስ ምክር ቤት አባላት እንዲሁም የፌደራል አመራሮች በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ለማስጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ከድሬዳዋ ካቢኔ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሯ ነፃ የንግድ ቀጠናው ድሬዳዋ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ ፓርክና ደረቅ ወደብን ከዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት፣ ከባቡርና ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር በማቀናጀት፣ አስፈላጊ የሆኑ የባንክና የጉምሩክ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ይህም እንደ ሀገር የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነትን ትርጉም ባለው መልኩ ሊለውጥ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው የሀገራችንን የገቢና ንግድ ስርዓት በማሳለጥ የተጀመረውን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡

የፌዴራል መንግስት ተቋማት የሥራ ሃላፊዎች በበኩላቸው መንግስት በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ለመመስረት መነሳቱ ለማሳካት ለታሰበው የኢኮኖሚ ሪፎርም አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል።

ለዚህም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሆኑ መናገራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የካቢኔ አመራሮች በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ለመመስረት መንግስት ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀው ለተግባራዊነቱ ከፌደራል አስፈጻሚ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | አቶ በቃል ምስጋናው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ መወሰዱ ለልጁ ደህንነት አስጊ ነው ሲሉ DMN ያነጋገረቻቸው ወዳጆቹ ገለፁ። አቶ በቃል ምስጋናው በድሬዳዋ በስፋት የተንሰራፋውን ዘረኝነትና...
10/06/2022

| አቶ በቃል ምስጋናው ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ መወሰዱ ለልጁ ደህንነት አስጊ ነው ሲሉ DMN ያነጋገረቻቸው ወዳጆቹ ገለፁ። አቶ በቃል ምስጋናው በድሬዳዋ በስፋት የተንሰራፋውን ዘረኝነትና አስተዳደራዊ ብልሽት በስፋት በማስረጃና በመረጃ ሲቃወም የነበረ የድሬዳዋ የማህበረሰብ አንቂ ነው። ይህ ስራው በአስተዳደሩ ባለስልጣናት እና ሙሰኛ ባለሀብቶች ጥርስ አስነክሶበታል። ከዚህ በመነሳት ጓደኞቹ ወዳጅ ዘመዶቹ ለደህንነቱ በእጅጉ እንደሚሰጉ ይገልፃሉ።

------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 |  ከ25 ዓመታት በኋላ                   💚💛❤️ኢትዮጵያ ግብፅን 2  - 0 አሸንፋለች ⚽️⚽️እንኳን ደስ አለን!!
09/06/2022

| ከ25 ዓመታት በኋላ
💚💛❤️
ኢትዮጵያ ግብፅን 2 - 0 አሸንፋለች ⚽️⚽️

እንኳን ደስ አለን!!

           ሰበር ዜናአቶ በቃሉ ምስጋናውን  #አራት ባለሀብቶች እንደከሰሱት DMN ምንጮች አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ክሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ መረጃው ያመላክታል። እንደሚታወቀው...
09/06/2022

ሰበር ዜና

አቶ በቃሉ ምስጋናውን #አራት ባለሀብቶች እንደከሰሱት DMN ምንጮች አረጋግጠዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ክሶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ መረጃው ያመላክታል። እንደሚታወቀው አቶ በቃሉ በድሬዳዋ ምድር ባቡር ስፖርት ማዘውተሪያ ሽያጭ ጉዳይ ላይ ህገ ወጥነቱን ሲሞግት እና ሌሎች የድሬዳዋን አስተዳደር አድሎአዊ አሰራር ሲቃወም የነበረ ልጅ መሆኑ ይታወቃል።

DMN|እናት የልጇን አስክሬን እስካሁን ማግኘት አልቻለችምትላንት ሰኔ1 በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ላዛሪስት ት/ቤት የሚማር የ4ዓመት ህፃን ልጅ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት ሲመለሱ ቱቦ ውስ...
09/06/2022

DMN|እናት የልጇን አስክሬን እስካሁን ማግኘት አልቻለችም

ትላንት ሰኔ1 በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ላዛሪስት ት/ቤት የሚማር የ4ዓመት ህፃን ልጅ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት ሲመለሱ ቱቦ ውስጥ አዳልጦት በመውደቁ በጎርፍ ተወስዷል።

እናትና የአካባቢው ህዝብ በሀዘን ተውጦ የህፃኑን አስክሬን ለማግኘት እስካሁን እየተረባረበ ነው!!

DMN ለወላጆቹ መፅናናትን እየተመኘች ወላጆች ልጆቻችሁን በትኩረት እንዲከታተሉ እና መጪውም ጊዜ ክረምት እንደመሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ ታሳስባለች።

Henok Fekadu

 |  ህግን ጥሶ ህግ ማስከበርየበቃሉ "እናት" መኖሪያ ቤት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ "ፖሊሶች ነን" ባሉ አካላት ተበረበረ። በብርበራውም የአቶ በቃሉ ምስጋናው የግን ንብረቶች ላፕቶፕ ፓድ ማስ...
09/06/2022

| ህግን ጥሶ ህግ ማስከበር

የበቃሉ "እናት" መኖሪያ ቤት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ "ፖሊሶች ነን" ባሉ አካላት ተበረበረ። በብርበራውም የአቶ በቃሉ ምስጋናው የግን ንብረቶች ላፕቶፕ ፓድ ማስታወሻ ደብተሮች በሙሉ ተወስደዋል። ንብረቱን የወሰዱት እና ፍተሻ ያደረጉት አካላት ምንም አይነት የፍርድ ቤት የመፈተሻ ማዘዣ ያልያዙ መሆናቸው ተውቋል።

-----------DMN------------
ebook page ➣
DMN
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

09/06/2022

በቃሉን በአስቸኳይ ፍቱት ‼

በቃሉ ምስጋናው ይባላል የፍቅር ያሸንፋል ማህበር የድሬዳዋና አካባቢዋ ፕሬዝዳንት ሲሆን በድሬዳዋና አካባቢዋ የሚስተዋሉ የህግ ጥሰቶችን እና ሙሰኛ ባለስልጣኖችን እግር ለእግር እየተከታተለ በማጋለጥ ይታወቃል።

በተለይ በቅርቡ የድሬደዋ ምድር ባቡር ጊቢን ሙሰኛ ባለ ስልጣናት ለባለሀብት ሊሸጡ ሲሉ በማህበራዊ ሚዲያ በማጋለጥ ከመሸጥ አድኗል። በዚህ ተግባሩም በተለያዩ ስልክ ቁጥሮች እየደወሉ ከፍተኛ ዛቻና ስድብ ይደርስበት እንደነበር ይነግረን ነበር።

በሙስና የተጨማለቁት እና እጀ ረጅሞቹ የድሬደዋ ባለስልጣናት ዛሬ በቃሉን ያለ ፍርድቤት መጥሪያ አፍነው ሲወስዱት የነበረውን ጭቅጭቅ በስልክ አሰምቶኛል። ነገ ወደ ድሬደዋ ሊያዘዋውሩት መሆኑንም አረጋግጫለሁ።

በቃሉ ሀገሩን እና ወገኖቹን የሚወድ፣ ያለ ምንም ጥቅማጥቅምና ክፍያ ወገኖቹን በነፃ እያገለገለ ያለ፣ ሀገሩ ከመውደድ ውጪ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ የሌለው የማህበራችን አመራር ነው።

የበቃሉ ወንጀል ሙሰኛ ባለስልጣኖችን ማጋለጡ ነው‼

ሚስባህ ከድር
------ DMN ------
Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

Media/news company

08/06/2022

| የማህበረሰብ አንቂ በመሆን የሚታወቀው አቶ በቃል ምስጋናው ልዩ ስሙ #የረር ሰፈር #አለማየሁ ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩ DMN ከቤተሰቦቹ ማረጋገጥ ተችሏል።

 | የDMN የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ የሔዱ ፖሊሶች የወጣት በቃል ምስጋናው መኖሪያ ቤትን ከበው እንደሚገኙና ቤተሰቦቹም ስልካቸውን ተቀምተው ወደቤት እንዳይገቡ...
08/06/2022

| የDMN የመረጃ ምንጮች እንዳረጋገጡት ከድሬዳዋ ወደ አዲስ አበባ የሔዱ ፖሊሶች የወጣት በቃል ምስጋናው መኖሪያ ቤትን ከበው እንደሚገኙና ቤተሰቦቹም ስልካቸውን ተቀምተው ወደቤት እንዳይገቡ ተደርገዋል።

መረጃውን እየተከታተለች የምትዘግብ መሆኑን እንገልፃለን።

======ፍትህን በማዋለድ ስም ፍትህን ማምከን=====የድሬዳዋ የፍቅር ሰባኪው የሌቦች መድሃኒት የሆነው   በመንግስት የፀጥታ አካላት ነን ባሉ ሰዎች አዲስ አበባ ካለው ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዷ...
08/06/2022

======ፍትህን በማዋለድ ስም ፍትህን ማምከን=====

የድሬዳዋ የፍቅር ሰባኪው የሌቦች መድሃኒት የሆነው
በመንግስት የፀጥታ አካላት ነን ባሉ ሰዎች አዲስ አበባ ካለው ከመኖሪያ ቤቱ ተወስዷል። እስካሁን የት ጣቢያ እንደታሰረ የታወቀ ነገር የለም።

 | በድሬዳዋ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው እዮብ ተስፋዬ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ በተካሄዱ ሁለት የፈጠራ ስራ ውድድሮች ላይ ራሱንና ት/ቤቱን በመወከል አንደኛ ደረጃን በመያዝ ...
07/06/2022

| በድሬዳዋ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆነው እዮብ ተስፋዬ በዚህ ወር ውስጥ ብቻ በተካሄዱ ሁለት የፈጠራ ስራ ውድድሮች ላይ ራሱንና ት/ቤቱን በመወከል አንደኛ ደረጃን በመያዝ ማሸነፍ የቻለ ታዳጊ ነው። በዛሬ እለት ድሬዳዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት በጋራ ባዘጋጁት አጠቃላይ የፈጠራ ስራ ውድድር ላይ አንደኛ በመውጣት የገንዘብና የእውቅና ሰርተፊኬት ማግኘትም ችሏል ።

ታዳጊው ከትምህርቱ ባሻገር በርካታ የቴክኖሎጂ ስራዎችን ይሰራል። ለአብነት:- የትምህርት ቤት መቆጣጠሪያ ሲስተም ፣ የሌባ መቆጣጠሪያ ፣ የዲጂታል አቴንዳንስ መያዣ ፣ በስልክ ብቻ HTML መጻፍ የሚያስችል መተግበሪያ እንዲሁም ሌሎች ከ 24 በላይ መተግበሪያዎችን እና ዌብሳይቶችን አበልጽጓል።


በቃል ድሬ

--------- DMN ---------

Like our page ➣
DMN
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

 | እኔን ግርም የሚለኝ የድሬደዋ ታክሲ ታሪፍ ነው። በአዲስ አበባ እስከ 2.5 ኪሎ ሜትር ታሪፉ በድሮው 2.50 በዛሬው ጭማሪ 3.00 ብር ተደርጓል። እዚህ ድሬ ደግም ከማደያ መስቀለኛ 1....
07/06/2022

| እኔን ግርም የሚለኝ የድሬደዋ ታክሲ ታሪፍ ነው። በአዲስ አበባ እስከ 2.5 ኪሎ ሜትር ታሪፉ በድሮው 2.50 በዛሬው ጭማሪ 3.00 ብር ተደርጓል። እዚህ ድሬ ደግም ከማደያ መስቀለኛ 1.5 ኪሎ ሜትር 5.00 ብር ነው። ህዝቡን በግራ በቀኝ ነጋዴውም አሽከርካሪውም ሁሉም ለመበዝበዝ ነው የሚራወጠው።

እንድሪያስ ተካልኝ ሽፈራው

--------- DMN ---------

Like our page ➣
www.facebook.com/diremedianetwork/
Subscribe to our YouTube Channel ➣
https://youtube.com/channel/UC346TY8iLQi5vjjDnqu5ryg
Join our Telegram Channel ➣
https://t.me/diremedianetwork

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share