ሐዲድ ሚዲያ-Hadid Media

  • Home
  • ሐዲድ ሚዲያ-Hadid Media

ሐዲድ ሚዲያ-Hadid Media ዜናዎች
እዉነተኛ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ዉግንና የሌለው የ?

07/08/2022

በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ የአሸባሪው ሸኔ የደቡብ ዞን ምክትል ሀላፊ ወደ መሀል አገር ሲጓዝ ተያዘ

በአሸባሪው ሸኔ የደቡብ ዞን ምክትል ሀላፊ የሚል ሀላፊነት የተሰጠው ተጠርጣሪ በቤት መኪና ወደ መሀል አገር ሲጓዝ በቦረና ዞን ሞያሌ ወረዳ መያዙን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው ኮሚኒኬሽን ረዳት ዲቪዥን ሀላፊ ኢንስፔክተር ግርማ ሹሚ ተጠርጣሪው መኪና ተኮናትሮ ወደመሀል አገር ለመግባት
ከአዳማ ከተማ በተላከለት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 B-37253 አአ በሆነ መኪና በመጓዝ ላይ እንዳለ በፖሊስ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰአት አከባቢ ተይዟል ብለዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ተጠርጣሪ ቀድሞ የሚታወቅበትን ‘መሀመድ አሜ’ የሚለውን የመጠሪያ ስሙን አብዱ ኡመር ሁሴን በሚል ቀይሮ መታወቂያ በማሰራት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡

ግለሰቡ ከአሸባሪው የሸኔ ቡድን ጋር ብቻ ሳይሆን አልሻባብን ከመሳሰሉ ከአለም አቀፍ አሸባሪዎች ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚጠረጠር እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡
የቦረና ዞን ፖሊስ ተጠርጣሪውን ጭኖ የነበረውን መኪና ከነአሽከርካሪው በቁጥጥር ስር አውሎ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እንደሆነ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ እየሠራ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ገለጹ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በታላቁ ህዳሴ ግድብ የግዳጅ ቀጣና ሰላም ለማረጋገጥ ቀን ከሌት ግዳጁን እየተወጣ እንደሚገኝ የሜካናይዝድ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ተናግረዋል።

ምክትል አዛዡ እንደገለጹት ሜካናይዝዱ ሰፋፊ ግዳጆችን በመፈጸም ከመተከል እስከ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በዘለቀ ሽፋን ስምሪቱን በማጠናከር ፀረ ሽምቅ እና ደፈጣ ውጊያዎችን በማካሄድ ጭምር የቀጣናውን ሰላም በጀግንነት አረጋግጧል ነው ያሉት።

ሜካናይዝዱ በመተከል ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በስፍራው ተሰማርተው ከሚገኙ የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ተልዕኮውን በስኬት እየፈፀመ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

ምክትል አዛዡ "በፀረ ሰላም ኃይሎች መሠረተ ቢስ ሐሳብ ሳንገታ ሕብረ ብሔራዊነታችንን አጠናክረን በቀጣናው አስተማማኝ ሰላምን ለማረጋገጥ ምን ጊዜም ዝግጁ ነን" ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

"የራያ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ የመላው አማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው"
የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ በራያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በደሴ ከተማ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። በምክክር መድረኩ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የራያ ተወላጆች እና የምሥራቅ አማራ ፋኖ አባላት ተገኝተዋል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ከድር ሙስጠፋ የውይይቱ ዓላማ የራያ የማንነት እና የወሰን ጉዳይ የመላው አማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ መሆኑን ማስገንዘብ ነው ብለዋል።

የወልድያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አበበ ግርማ የራያ ሕዝብ ለበርካታ ዓመታት በማንነቱ ጫና ሲደርስበት እንደነበር ተናግረዋል። አሁንም በከፋ ችግር ውስጥ መሆኑን ጠቅሰው ነፃነቱ ሊረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የራያ ሕዝብን አንድነት በማጠናከር የሕዝቡን ነጻነት ለመመለስ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ እየሠራ መሆኑን የተናገሩት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር እና የአብን ሊቀመንበር ዶክተር በለጠ ሞላ ኮሚቴውን በማገዝ የራያ ሕዝብ ነፃነቱን እንዲያገኝ በአንድነት መሥራት አለብን ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የወሎ ራያ አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ባለፈው አንድ ዓመት ባከናወናቸው ተግባራት እና የወደፊት የትግል አቅጣጫዎች ላይ እየመከረ ነው።

ዘጋባዉ የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነዉ::

10/07/2022

#ሐዲድ #ፈጣን #አዲስ መረጃ #ኢትዮጵያ

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሐዲድ ሚዲያ-Hadid Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share