Daily Informer

  • Home
  • Daily Informer

Daily Informer Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Daily Informer, Media/News Company, .

07/07/2023

የአማራ ልጆችን ከተቋማት የመመንጠር ፋሽስታዊው አደገኛ ዘመቻ‼
( "Genocide by other means")

ፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግስት፥ የአማራ ቴክኖክራቶችን ከሀገሪቱ ተቋማት በስፋት ለማጥራት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። ለዚህ ethnic cleansing እንደመንደርደሪያ እየተጠቀመበት ያለው ደግሞ፥ "በዚህ ተቋም የአመራር ቦታዎች ላይ የአማራ ተወላጆች ቁጥር ይህን ያህል ነው፤ የሌሎች ደግሞ በጣም ትንሽ ነው" የሚል የፈጠራ ሰነድ በማዘጋጀትና በማህበራዊ ሚዲያ በማዘዋወር ነው።

በነገራችን ላይ በሀገሪቱ ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ አመራር የሚገኙ ቴክኖክራት አማራዎች እዚያ ደረጃ የደረሱት በችሎታቸው እንጂ በፖለቲካ ሹመት እንዳልሆነ ግልፅ ነው‼‼‼

እዚህ ጋር ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር እኔ እያልሁ ያለሁትም ይሁን ፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግስት ዒላማ ያደረጋቸው፥ ከጠላት-ብ.አ.ዴ.ን. ጋር ንክኪ የሌላቸውን ነገር ግን በትምህርት ዝግጅትና በአመራር ጥበብ ልቀው በመገኘት የነበረባቸውንና ያለባቸውን ማንነት-ተኮር ጫና ተቋቁመው በቴክኖክራትነትና በቢሮክራትነት የሚያገለግሉትን ሲሆን፥ ይህ በፋሽስታዊው የኦሮሙማ መንግሥት የተጠነሰሰው አማራን ከተቋም አመራርነት የማጥራት ዘመቻ ፥ "Genocide by other means" መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል ‼‼‼

ዴቭ ዳዊት።

ግዑዙ ፓርላማ*************አንድ የፓርላማ አባል የገዥ ፓርቲው አቅም ማጣት አገር አደጋ ላይ ስትወድቅ መሪን ከስልጣን ውረድ ወይ መፍትሄ ፈልግ ማለት ትልቁ ሀሳብ ነው። እንኳን አሁን ...
06/07/2023

ግዑዙ ፓርላማ
*************
አንድ የፓርላማ አባል የገዥ ፓርቲው አቅም ማጣት አገር አደጋ ላይ ስትወድቅ መሪን ከስልጣን ውረድ ወይ መፍትሄ ፈልግ ማለት ትልቁ ሀሳብ ነው። እንኳን አሁን ሰው ወቶ መግባት አልችል ያለበት ዜጎች የሚታገቱበት ሚሊየኖች በተፈናቀሉበት ባጠቃላይ የመሪውም የፓርቲውም አመራር የከሸፈበት ዘመን ላይ ይቅርና በአንፃራዊ ዜጎች የትኛውም የአገሪቱ ስፍራቸው በሰላም በሚንቀሳቀሱበት በመለስ ዜናዊ ዘመን ስልጣነወን ይልቀቁ የሚሉ የፓርላማ አባላት ብዙ ነበሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብቻ ሳይሆን ሙሉ ፓርላማው ሸምለስ ስለሆነ እንጅ የሰለጠነ ቢሆን ኖሮ ወይ ስልጣን ይለቃል ወይ የተጠየቁ ጥያቄወችን ለመመለስ ይሞክራል።
ቆይ ስልጣን ልቀቁ አይባሉ ጠቅላዩ የሚሉ ግዑዝ የፓርላማ ሰወችን ሳቅም ማየት ጀመርን። ታምር እኮ ነው አገር መምራት ስላልቻሉ ወይ በአግባቡ ይምሩ ወይ ስልጣን ይልቀቁ ተብለው ከመጠየቅም አልፈዋል ጠቅላዩ። ጨርሶ ዜጎች በጠቅላዩ ተስፋ ከመቀረጥ አልፈው ዛሬ ላይ እየታገቱ በገንዘብ የሚለቀቁበት ሰው ሆነው እንድ ባሪያዘመን ንግድ ሽያጭ የተጀመረበት ጊዜ ነው።

ጠቅላዩ በሳቸው ዘመን ከሞቱት ሚሊየኖች መስዋዕትነት አንፃር ተሰምቶዋቸው ባስተካከሉ ነበረ። በሰውየው የአመራር ብቃት ማነስ ህግ ከመናቁ የተነሳ ወንጀል ተበራክቶዋል። ዜጎች በረሀብ እያለቁ ነው በሰላም ከክልል ወደ ክልል መሄድ ለዜጎች የጦርነት ያህል ከብዶዋል ምንም ሰላም የለም ታዲያ ወይ ስልጣን ይልቀቁ ወይ ያስተካክሉ ተብለው መጠየቃቸው እንዲያውም ትህትና ስላለ ነው።

ሲጀመር ፓርላማው ሰው የለውም ጨርሶ ሞጋች ጥያቄን የሚጠይቁ እንኳን የሉም ከአብን ተወካዮች በቀር ሌሎቹ ዳርዳር ሲሉ ሲልመጠመጡ የመረጣቸውን ህዝብ ችግር እና ጥያቄ እንኳን ይዘው ሲገቡ አላየንም። የመረጣቸው ህዝብ ተፈናቅሎ ተሰዶ በአገሩ መኖር ተስኖት እያዩ ፓርላማ ገብተው ተጎልተው ይወጣሉ።

🔥 ‼️ #በደምበጫ በነበረው ውጊያ ከኦነግ የተማረከን መሳሪየ አስመልሳለሁ በማለት ሲንቀሳቀስ የነበረው የሚሊሻ ቡድን በደምበጫ ወረዳ በዎዳን ቀበሌ የኦነግን ትጥቅ ሊያስመልስ ሲቀሳቀስ ከነበረ...
05/07/2023

🔥 ‼️

#በደምበጫ በነበረው ውጊያ ከኦነግ የተማረከን መሳሪየ አስመልሳለሁ በማለት ሲንቀሳቀስ የነበረው የሚሊሻ ቡድን በደምበጫ ወረዳ በዎዳን ቀበሌ የኦነግን ትጥቅ ሊያስመልስ ሲቀሳቀስ ከነበረው ታጣቂ ቡድን አስከሬናቸውን ይዘው መመለሳቸው ተረጋግጧል‼️

#ብራቦ💪
💪
💪

28/10/2015

https://t.me/NISIREamhra

05/07/2023

አብዛኛዉ ከአማራ ማሕበረሰብ ውጭ ያለ ብሔር አማራ ወደ ሥልጣን መንበሩ እንዲመጣ ይፈልጋል ሃምሳ አመት በጣም ተናፍቋል።
አማራ ተራራው የነፃነት አባት

https://gofund.me/3719b997
02/07/2023

https://gofund.me/3719b997

ወድ የ Tolosa Ethiopia Media አድማጮች የህዝብ ድምፅ መሆን በጣም ከባድ በነበረበት ዘመን የዛሬ 10 ዓመት ነበር ግፍ የ… Tolosa Ibsa needs your support for Tolosa Ethiopia Media. Kind Regards.

ቶሎሳ ኢብሳ እንኳን ተወለድክልን🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂በእውነተኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ወያኔን እርቃኗን ያስቀራት፣አሁንም የአብይ አህመድን መንግስት ዘቅዝቆ እያራገፈው የሚገኘው ሃቀኛው ወንድማችን...
30/06/2023

ቶሎሳ ኢብሳ እንኳን ተወለድክልን
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂
በእውነተኛ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ወያኔን እርቃኗን ያስቀራት፣አሁንም የአብይ አህመድን መንግስት ዘቅዝቆ እያራገፈው የሚገኘው ሃቀኛው ወንድማችን Tolosa Ibsa Ibsa እንኳን ተወለድክ። በአንተ መወለድ ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን አትርፈናል። በተለይ በአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ግፍ በመረጃና በማስረጃ ለምታጋልጠው ስራህ ትልቅ አክብሮት አለን። አንተን ከፍ አድርገን የምናከብርበት ጊዜ ይመጣል። ቀሪ ዘመንህ የተሳካ ይሁንልህ።

የህዝቡ ቁጣና ውሳኔዎቹደጋዳሞት ፈረስ ቤት    ደጋ ዳሞት በጠዋቱ ህዝቡ ቀፎው እንደተነካ ንብ ገንፍሎ እንደወጣ ይታወቃል።የህዝባዊ አመጹ ውሳኔዎች:1. ከየቀበሌው የተሰባሰበው ሚሊሻ(ጉጅሌ) ...
27/06/2023

የህዝቡ ቁጣና ውሳኔዎቹ
ደጋዳሞት ፈረስ ቤት

ደጋ ዳሞት በጠዋቱ ህዝቡ ቀፎው እንደተነካ ንብ ገንፍሎ እንደወጣ ይታወቃል።

የህዝባዊ አመጹ ውሳኔዎች:
1. ከየቀበሌው የተሰባሰበው ሚሊሻ(ጉጅሌ) በአፋጣኝ ወደ ቤቱ ሄዶ ልጆቹን ያሳድግ፤

2. በአዲስ ፋኖ ማሰልጠን ከነገ ጀምሮ እንዲጀመር፣

3. ጥያቄውን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለማስመሰል ለሞከሩ ተላላኪ አመራሮች ደግሞ፦ "ፈረስ ቤት ከአዲስ አበባ ቀድማ ነው የተቆረቆረችው፤ ግን ይህን ያክል ዘመን ምንም ሳትሰራ ኖረህ፤ ዛሬ መሰረተ ልማት ምናምን ብትል ለኛ እሱ ቅንጦት ነው፤ ብርቃችን አይደለም፤ ጉዳዩ የመኖርና ያለመኖር ነው" በሚል ተደምድሟል፣

4. ሱቆችና ሌሎች የቢሮና የንግድ ተቋማትን የመክፈት ውሳኔን በተመለከተ: ግንባር (ውጊያ) ላይ የነበሩ ፋኖ ጓዶቻችን ሲመጡ ያኔ እነሱ እንዳሉን እናደርጋለን።

5. የመንገዱን መከፈትና አደረጃጀትን በተመለከተም፥ አሁንም ፋኖዎቻችን ሲመጡ በጋራ ይወሰናል፥ እነሱ ከኛ የተሻለ መረጃ አላቸውና!!!

6. ሰላማችንን ራሳችን እንጠብቃለን: ሚሊሻ፣ካድሬና ፖሊስ ከዚህ አያስፈልገንም።

7. የቢቡኝ ወረዳ የድጎ ጽዮንን አመራር እንፋረዳቸዋለን! ምክንያቱም
"ሂዱ ደጋ ዳሞት ፋኖ አለ" ብለው ያሴሩ ከኛዎቹ በተጨማሪ እነሱ ናቸው፥ምግብ እያበሉ: መንገድም አስከፍተው: አምቡላንስም ያመቻቹላቸው የድጎ ባንዳዎች ናቸው እና ይሄ ይታሰብበት።

8. በመጨረሻም ከየአቅጣጫው በአይን ጥቅሻ ተሰባስቦ አረፋ ፍልቅልቅ ላይ የኦነጉን ኃይል ከአፈር የደባለቀው ግስላው የአማራ ፋኖ በድል አድራጊነት እየተገማሸረ ወደ ከተማችን በመምጣት ላይ ነውና ፋኖን ተቀብለን ያኔ ብዙ ተጨማሪ ውሳኔዎችን በጋራ እናስቀምጣለን።

ፈረስቤት ደጋ ዳሞት!!!

27/06/2023

የአቶ ሽመልስ አብዲሳ የአንድ ወቅት አነጋጋሪ ንግግር ዛሬ የት ደርሷል⁉️ ምን ያሕል ተፈፅሟል!? አዴፓ/ብልፅግና እና አብንስ የት ደረሱ⁉️

"ኢህአዴግ የተሰራው ለህውሓት ነውና የተሰራበት ምክንያት ደግሞ ስልጣን ላይ ለመቆየት ነው። እኛም ብልፅግናን የሰራነው ከስልጣን ለመውረድ አይደለም። ብልፅግና ደግሞ ወደዳችሁም ጠላችሁም የኛ ነው። እኛ ነን የሰራነው። ለእኛ እንደሚሆነን አድርገን።" ሽመልስ አብዲሳ

በተመሳሳይ መንገድ ህወሃት ኢህአዴግ እንዲመቸው አድርጎ ነበር የሰራው። ኢህአዴግ ገና ሲፈጠር የቀድሞዎቹ የኦህዴድ መስራች ሰዎች ለመታገል ሞክረዋል። ግን አልቻሉም። ያልቻሉበት ምክንያት ደግሞ ጠብመንጃ ስለሌላቸው፣ ኃይል ስለሌላቸው ነበር። ኢህአዴግ ሳይመሰረት በፊት አሁን የምናወራውን ነገር አንስተው ነበር።

አሁን ዶ/ር ቢቂላ ያነሳውን ነገር ሁሉ አንስተው ነበር። እነ ኢብራሂም መልካ ተገምግመው የተባረሩት በዚህ ነው። ስለ ውክልና እና ስለ ፍትሃዊነት ስለ ጠየቁ። ግን majorityን minority የሚያደርጉበት instrument ስለሆነ፤ minorityን majority አድርገው እዚህ ሀገር ላይ የማዕከላዊ መንግስት ስልጣንን ለመቆጣጠር ሲባል ነው አሳምረው የሰሩት። ከተሰራበት መንገድ ውጭ እንዳያድግ ደግሞ ሲንከባከቡት ኖሩ። በመጀመርያ ዙር የተንከባከቡት በሞግዚት ነበር። እነ ሰለሞን ጢሞ፣ እነ ቢተው በላይና በመሳሰሉት ሲንከባከቡት ነበር። ሞግዚትን እንደምንም በትግል ማሸነፍ ሲቻል ደግሞ internally click ገነቡ ማለት ነው። በclick ደግሞ ሲንከባከቡት ቆዩ። ይሄ እውነት ነው። ስለዚህ በ2008 ክረምት ውስጥ ሊቀመንበር መቀየር ሲቻል ነው ትግሉ አንድ አቅጣጫ የያዘው። እንደ ህውሃትም እንደ ኢህአዴግም ብለው ያበዱ ጊዜ ማለት ነው። ማበዳቸውም ልክ ነበር። ስለዚህ ቁጭ ተብሎ አማራጭ ሲሰላ በሶስት መንገድ ለውጥ ማምጣት እንችላለን ተባለ።

አንደኛው አብዮት እናካሂድ ተባለ። አንዱ አማራጭ እሱ ነበር። አብዮት አይሆንም ሌላ ችግር ያመጣል። እንደዚያ ዓይነት ዝግጅት አልነበረንም። plus ሁልጊዜ ከዜሮ መጀመር ነው የሚሆነው ተብሎ አብዮት ለፍጥነት ጥሩ ነው ጣጣ የለውም፣ ጭቅጭቅ የለውም፣ የጨረስከውን ጨርሰህ ወደ አንድ አቅጣጫ ታወጣለህ፣ ማሰር ያለብህን አስረህ እንደማለት ነበር። ያ መንገዱን ቢያቃልልንም ብለን ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ አብዮት አይበጀንም፣ አያዋጣንም ተብሎ ነው ተጠንቶ የተተወው። ይህ አማራጭ እንዲቀር የተደረገው።

ሁለተኛው በevolutionary መንገድ ለውጥ ማምጣት ነው። ቀስ በቀስ። ያም ብለን በevolutionary መንገድ መለወጥ አይቻልም ተባለ።

ሶስተኛው ለውጥ ማምጫ መንገድ reform ነው reform ትንሽ ፍጥነትም አለው። structurally ነገሩን ለመቀየርም የተመቻች መንገድ አለው። in between ስለሆነ። ሌላውንም ህዝብ ሳያስደነብሩ፣ ዘመድ እያበዙ፣ እያፈሩ፣ የኦሮሞን ጥያቄና ፍላጎት በreform መንገድ መመለስ እንችላለን ተብሎ ነው reform የተመረጠው። ይህ ነው በ 2009 በድርጅት conference ወስነን የገባንበት ይሄን ሪፎርም። basically ብዙ ሪፎርም አለ ነገር ግን ሪፎርሙን በሙሉ መንገድ ለማካሄድ ኦሮሚያ ውስጥ መጀመርያ ላይ ሰዎቹን ለማስደንገጥ፣ እረፍት ለመንሳት አጀንዳ ለእነሱ ለማቀበል፣ እነሱን corner ለማድረግ፣ ብዙ ነገር አድርገናል። የመሬቱን ታስታውሳላችሁ፣ የማዕድኑን ታስታውሳላችሁ፣ የህገ ወጥ ንግድን ታሳታውሳላችሁ፣ ስለ ኮንትራባንድ ታስታውሳላችሁ፣ ስለ አዲስ አበባ ታስታውሳላችሁ፣ ስለ አፋን ኦሮሞ ብዙ አጀንዳዎችን ፈጥርን እረፍት ለመንሳት።

እእእእ ቄሮ ስለምትሉትም፣ ትንሽ ያው እነ ፍቃዱን እና እሱን አያካትትም እንጅ እኔ ቄሮ ነኝ። ይህን ቄሮን ወደድክም ጠላህም ኦህዴድ ነው የፈጠረው። እዚህ ውስጥ ያላችሁ young የሆናችሁትን ያሳየን ኦህዴድ ነው። ትምህርት ቤት በሙሉ ኦሮሚያ እንዲከፈት ተደርጎ እንዲማር የተደረገው በኦህዴድ ነው። የዚህ ዘመን ቄሮ conscious ስለሆነ fearless ሆኖ እንዲሄድ ያደረገው ስለ ተማረና conscious ስለሆነ ነው።

So, አብዮቱ በሚካሄድበት ግዜ በነበሩት አመታት፣ ብዙ ነገሮች አሉ ማለት ነው ወደፊት በታሪክ የምንፅፈው። ሰልፍ እየበተንም እያወጣንም ነበር ማለት ነው። አሁን ሁሉም ሰው እንዲህ አድርገን፣ እንዲያ አድርገን እያለ የሚያወራው አይደለም ማለት ነው። ከውጭም ከውስጥም ሁሉንም coordinate አድርገን ቁማሩን በደንብ ነው የተጫወትነው። ቁማሩን ስለተጫወትን ነው ነው የበላነው መጨረሻ ላይ፣ እንጂ በስጥታ የሰጠን ሰው፣ እባካችሁ እንጅ ምነው ብሎ የሰጠን የለም። ይህ clearly መታወቅ አለበት።

ፖለቲካ ደግሞ እናንተ ሰዎች ተንኮል ነው ሌላ ነገር አይደለም፣ ምን ያክል ተንኮል ትችላለህ ነው፣ ምን ያክል በ intrigue መጫወት ትችላለህ ነው፣ ምን ያክል power calculusሷን properly calculate አድርገህ መጫወት ትችላለህ ነው። ልክ ፍቄ እንዳለው በስሜት አይቻልም በስሜት እማ ተሞክሯል hundred years, ማሸነፍ የሌለው ትግል ብዙ አድርገናል፣ ማሸነፍ የሚችል ትግል ያመጣነው calculate ተደርጎ ስለተሰራ ነው ማለት ነው። ዘመድ ለማብዛት calculate ተደርጎ ብዙ ነገር ተሰርቷል፣ ደቡብ ብዙ ተሱርቷል፣ ባህርዳር አባይ ተኪዶ ብዙ ሰርተናል፣ ብዙ ነው ማለት ነው፣ የምንችለው convince አድርገን፣ ያልቻልነውን confuse አድርገን።

አሁን የሚያስቸግረው ምንድነው ሌላው ሰው ለምን confused ሆነ ብላችሁ ትጨነቃላችሁ ፣ ምን አገባችሁ? በእንደዚህ አይነት ጨዋታ ነው መጨረሻ ላይ ህወሃት ወደሚሄድበት ግራ ገብቶት ያሰለፈውን ሃይል ሁሉ ከእጁ አውጥተን፣ ደቡብንም ከእጁ አውጥተን፣ የአማራን ፓርቲንም ከእጁ እውጠተን፣ እኛ ውስጥም የሚላላኩትን መርምረን አባርረን፣ አባርረን ነው ራሳችንን አፅድተን ተሰልፈን አማራጭ አሳጥተነው ወደ ምርጫ እንዲገባ የተደረገው። ህዝቡ ተደራጅቷል፣ አብዮት ነው ያለው፣ እሳት ነው እየነደደ ያለው፣ internally ደግሞ እሱ የሚንጠለጠልባቸውን ሁሉ በትነንበት አንድ ሰው እንዳይኖረው አድርገን የኛ ሰው ሲወጣ እና ሲገባ የሚያወራውን ሁላ እእእእ የምንችለውን በምንችለው።

አሁን የቤት እመቤት ነን ማለት ነው፣ seriously ማለት ነው፣ እንዲህ በዋዛ አልመጣም፣ ምክንያቱም የሚላላክ ብዙ ስላለ ነው ዛሬም ለመላላክ ሰልፍ የገባው፣ መላላክ ደግሞ ከኛ በላይ የሚችል የለም። so wisely ነው ማለት ነው የተቀበልነው፣ በጨዋታ ነው የተነጠቅነው (×2)። ፓርቲ ሰራን ይሄው፣ የሰራነው ፓርቲ እንደ ምሁር እንድትረዱ የምንፈልገው፣ ጅማሬውም ፍፃሜውም የኦሮሞን ህዝብ ጥቅም እና ፋይዳ እና የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን ጥቅም እና ፋይዳ ማስከበር ነው። ከዚህ ውጭ ምንም አላማ የለውም።

ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ፕሮግራሙ ፍቃዱ እንዳብራራው የመተዳደርያ ደንቡ የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም እንዲመልስ ነው የተሰራው፣ እንዳትሳሳቱ የመጀመርያው እና ዋናው በዚህ ፓርቲ ውስጥ ያለን ተሳትፎ በህዝብ ብዛት እና በብሄር ብዛት እንዲሆን ተብሎ ነው የተቀመጠው። በፊት በዛ መላላክም ተሳትፎአችን ትንሽ ነው፣ አሁን ተሳትፎአችን በህዝባችን ልክ ዴሞክራቲክ በሆነ መንገድ እንዲሆን አደረግን ማለት ነው፣ አንደኛው ይህ ነው። ሁለተኛው የፓርቲው ፕሬዝዳንትና ምክትሉ በምርጫ ጉባኤ ይካሄድ ብለን ነው የወሰንነው። So, አርባ ፐርሰንት ቢሆን እኛ ያለን ተሳትፎ በህዝብ ቁጥራችን ልክ ፓርቲው ውስጥ ያለን፣ ያ አርባ ፐርሰንት ካልመረጠህ ፕሬዝዳንት (ሊቀመንበር) አይደለም ምክትልም ለመሆን አትችልም ማለት ነው።

ስለዚህ የሃገር ባለቤትነትን ጉዳይ ከስልጣን ጋርም ያለውን በአሰራር ዘግተነዋል ማለት ነው። ብልፅግናን minimum ካሁን በኋላ የሚመራው ኦሮሞ መሆን አለበት ካልሆነ ደግሞ ኦሮሞ ሊፈቅድለት ይገባል። እንደዚያ አይነት ፓርቲ ነው የገነባነው።

ሁለተኛ ያነሳችሁት አፋን ኦሮሞን የተመለከተ አንድ ዳታ ልስጣችሁ። በ87 አፋን ኦሮሞ በ12 በ13 % ከአማርኛ በታች ነበር። አሁን አፋን ኦሮሞ ኢትዮጵያ ውስጥ አማርኛን ከ 10% በላይ ይበልጠዋል። የአማራን ብሄር አላልኩኝም እኔ አፋን ኦሮሞ በተናጋሪ አማርኛ ቋንቋ ይበልጣል ነው ያልኩት። አማርኛ ነው አፋን ኦሮሞን በተናጋሪ ብዛት የሚበልጠው ብላችሁ ካሰባችሁ ትልቅ ስህተት ውስጥ ናችሁ። ቤንሻንጉል 37% አፋን ኦሮሞ ይናገራል፣ ጋምቤላ፣ ሃረሪ፣ ሶማሌ ውስጥ፣ ነው ያልኩት። አማርኛ እየሞተ ነው የመጣው፣ ወደታች ነው እየሄደ ያለው። So, አፋን ኦሮሞ ይዋጣል ይሞታል ምናምን የምትሉ፣ ኦሮሞ ይዋጣል የምትሉ ስነስርዓት ያዙ። ኦሮሞ እኮ የሆነ handicapped ነገር አይደለም ኦሮሞ፣ ወይም ክኒን አይደለም ኦሮሞ። ድሮም አልተዋጠ፣ በአፋኝ ስርዓት ውስጥም አልተዋጠም፣ forget it። ኦሮሞን ልክ እንደ wheelchair እነሱ በ AC ውስጥ oxygen ሰጥተውት፣ መርፌ ወግተው እያኖሩት እንዳሉ አስመስለው የሚያወሩልን እነሱ እየዋሹ ነው፣ እየዋሹ ነው ያሉት። ኦሮሞን እኔ አላኖረውም አንተም አታኖረውም ፣ እኛ ላይ depend አያደርግም የሱ ኑሮ፣ ይህን እወቁ። So, እዚህ state building ውስጥ የሚወጡ ህግጋት፣ የሚወጡ ስትራቴጂዎች፣ የሚወጡ ስርዓቶች፣ የሚወጡ ሲስተሞች ነው ኦሮሙማችንን በውስጡ treat የምናደርገው፣ ሁሉንም ብሄር ብሄረሰብ ወደ center የምናመጣው።

አምስት ቋንቋ ስንል ለሌላው ክልል ተጨንቀን አይደለም፣ ትግርኛና አማርኛ already አሉ። ፌዴራል ውስጥ በቂ ነው ያለው። ሶስት አምጥተንበት ለማውረድ ነው። ገባችሁ ለማመጣጠን። ሁለቱ almost 90% አላቸው፣ አሁን ሁሉም institution ውስጥ፣ አሁን እኛ የፌዴራል ቋንቋ እናድርግ ስንል ሶማሌኛ፣ ኣፋርኛ፣ እና አፋን ኦሮሞ ስንል በኋላ ፕሮፖርሽናል ይሆናል ማለት ነው። የፌዴራል public service፣ ፕሮፖርሽናል ሲሆን ሶስቱ ይገባል ማለት ነው። ሁለቱ የሚጨመር ነገር የለውም ማለት ነው ይወርዳል እንጂ! ሶስቱ ናቸው የሚገቡት ማለት ነው። So, እኛም እንደኛ፣ ሁሉም እንደ ራሱ፣ ይኖረዋል ማለት ነው። ስለዚህ የሚወጡ ሲስተሞችን እና ህግጋትንም በዛ መንገድ ነው። ሃጂ የአፋን ኦሮሞ ጉዳይ የእኛን መሞት አይፈልግም። አፋን ኦሮሞ ተመልሷል ሰዎች።

የቋንቋ ፖሊሲ ከሁለት ወይም ከሶስት ሳምንት በኋላ ለካቢኔ ይቀርባል። ተጠናቅቋል። ለፌዴራል ካቢኔ ማለት ነው። ፓርቲዎች ወስነዋል። ስድስት ክልሎች ነው እንዲወስኑ የምንፈልገው። እነዚያ ስድስቱ ክልሎች ደግሞ አሁን እንደ ድሮው አይደለም ፓርቲው ስር ነው የሚተዳደሩት። ብልፅግና ስር፣ ስለዚህ ህግንም ሆነ ምንንም ለማስተካከል ምርጫ ድረስ መድረስ ያለብን አይመስለኝም። ስለዚህ ብልፅግና የአፋን ኦሮሞን ጉዳይ መልሶታል።

ስለዚህ ለstate building ዕድል አለን፣ ያለንን ስልጣን ተጠቅመን፣ እኛን የምትመስል state መገንባት እንችላለን ነው አንደኛው፣ ብልፅግናን ለዚህ ነው እየገነባነው ያለነው። ሁለተኛው ብልፅግናን እየገነባን ያለነው ለnation building ነው፣ የቀድሞው (የሰዎቹ) nation building aborted ሆኗል። መቶ አመት ተሞክሮ፣ አንድ ብሄር፣ አንድ ሃይማኖት ፣ አንድ ባህል፣ አንድ ሃይማኖት የሚባለው ወድቋል። አሁን እኛ እንደ ኦሮሞ እኛን የምትመስል ኢትዮጵያ መልሰን reconstruct ለማድረግ ፣ superstructure ውስጥ ኦሮሞነትን ለመትከል እድል አለን ማለት ነው። እሱ ላይ መስራት እንችላለን። እንደምታውቁት ድንበሩም አልቋል አዋጁም ተጠናቋል፣ አዋጁ ግን ምንም አይጠቅመንም እውነቱን ነው የምነግራችሁ፣ ብናፀድቀውም ለስም ነው እንጅ long lasting solution አያመጣም።

አዲስ አበባ ላይ መፍትሄ የሚያመጣው ሶስት ነገር ነው፣ አንደኛው ሰውን ማስፈር ነው፣ በስራ፣ ከማውራት በስራ፣ አትጠይቁን የምንችለውን እያደረግን ነው። ሁለተኛው አዲስ አዲስ አበባን irrelevant ማድረግ ነው። አዲስ አበባን irrelevant ለማድረግ እየሰራን ነው። ከተሳካልን ከምርጫ በኋላ የፌዴራል መንግስቱን መቀመጫ፣ አራት አምስት ቦታ ለመክፈል እንፈልጋለን።

ዝም ብሎ አዲስ አበባን በስራችን እናስገባለን ብሎ መለፍለፍ አይደለም። እንዴት ታደርገዋለህ ፣ ፈንጂውን እንዴት ታፈነዳዋለህ? አሁን እኛ ኦሮሚያ ከልክ በላይ እየለማች ነው፣ ሌላው ክልል ከልክ በላይ እየተጎዳ ነው። ይህ ደግሞ እየሆነ ያለው የፌዴራሉን መንግሥት ኦሮሚያ ስለተቆጣጠረው ነው። የፌዴራሉ መንግስት መከፈል አለበት ብለን ከሌላው ህዝብ ጋር ተጨንቀንበት እየሰራን ነው።

ስለዚህ ይሄንን ስናደርግ irrelevant ትሆናለች አዲስ አበባ። ሶስተኛ አዲስ አበባ ላይ ያለው ሌላ economic option መፍጠር ነው። ለዚህ በቂ ዝግጅት አድርገናል። አሁን በቅርቡ ለጨፌ እናቀርባለን እድሉ ስላለን። ይሄንን አድርገን ነው እንጅ የምንፈታው ሰውም ማባረር አንችልም። ሰው መግደልም አንችልም። ማጫረስም አንችልም። እንዲህ አድርገን ነው ነገሩን የምንፈታው ብለን ነው እየሄድን ያለነው። ስለዚህ ከፈጣሪ ጋር፣ ከእውነት ጋር፣ እየሰራን ካለነው ስራ ጋር፣ ከእናንተ ጋር ከሁሉም የኦሮሞ ህዝብ ጋር ብልፅግና ይቀጥላል። የኦሮሚያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!

ምስራቅ አፍሪካን እንመራለን!
ኢትዮጵያን እንደምትመቸን አድርገን እንገነባታለን! እየገነባናትም ነው። ስለዚህ መክዳት፣ መከዳት የሚባለው ነገር የለም፣ ሊኖርም አይችልም፣ እንዲህ አይነትም ቦታ የለም፣ እንዲህ አይነት አመለካከትም የለም ይህንኑ ለማለት ነው በርቱ! በግልፅ ስለተናገራችሁን አመሰግናለሁ ልላችሁ እፈልጋለሁ።"

27/06/2023

"አባይ ሸለቆ ዘብ" ስሙ በጣም ልብ ያሞቃል። አባይ ወንዝ በዚህ ሰዓት እኔ ነኝ ያለ ወንድ አይሻገረውም። የአባይ ሸለቆ ዘቦችም ወንድ ነኝ ያለ አያንበረክካቸውም።

14/06/2023

በወቅታዊ የክልላችን ሁኔታ ከአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ

"መላው የአማራ ህዝብ ወንድ ሴት : ጨርቄን ማቄን ሳትል በደምህ ባለው የአባቶችህና በውስጥህም በነገሰው ጀግንነትህ ላይ በድፍረት የዘመተብህን ጠላት ድባቅ ለመምታት ዛሬ ታጥቀህ ውጣ"

ችግርህ ሥርዓት ወለድና ተቋማዊ ሆኖ የችግሩ ህልውናም ለጠላትህ ተላላኪ በሆኑ አማራ ነን ባይ መሪዎች እስከዛሬ ድረስ እንደቀጠለ ይገኛል::

በሌላ መልኩ የአማራ ሕዝብ ችግሩን በልኩ ተረድቶ በችግሩ አጽናፍ ልክ ለመመከት ከመታተር ይልቅ ከሥርዓቱ እየተቀዳ በመሪዎቹ የሚወርድበትን የመከራ ዶፍ " ሀገር እንድትቀጥል በሚል ምናባዊ ተስፋና ለመሪም ካለው ጥንታዊና ክብር የመስጠት ማህበረሰባዊ እሴት ዛሬ ለደረሰበት የህልውና አደጋ ለመድረስ በቅቷል።ላለፉት 30 ዓመታት የወረደበትን የመፈናቀል፣ስደት፣፣ርሀብ፣ሞት፣ቁሳዊና መንፈሳዊ ፀጋዎቹ ጥፋትና ውድመት ፣ከቤተ እምነቶቹ ጥፋት...አሁን እስካለበት የመውጣትና መግባት አለመቻል ሰቆቃ የተዳረገው ለመሪና ለሀገረ መንግስት ካለው የዳበረ አክብሮቱ ነው።

አሁን ላይ ግን ይህን እሴቱን ቆም ብሎ እንደገና ሊፈትሸውና ሁሉን ሆኖ የመሰረታትና ከነ ክብርና ልዕልነዋ ተጠበቃ እንድትቆይ የደም ዋጋ የከፈለላት እንደፈራረሰችና ምናባዊ እንደሆነች፣መሪዎቹም የሞቱና የርሀቡ ምንጭና አስፈጻሚ እንደሆኑ አምኖ ህልውናውን በክንዱ ለማረጋገጥ መነሳት ይኖርበታል።

አሁን ያሉት መሪዎች፣በርሀብ አለንጋ ከመግረፍ በተጨማሪ በየ ደጁ ሞት ደቅነው ቀንና ሌሊት የጥይት በረዶ እያዘነቡ ይገኛሉ።እነዚህን ቡድኖች እንደመሪ ተቀብሎ መቀመጥ የመጥፋት እድሜን ከማሳጠር የዘለለ ትርጉምም የለውም!!!እነዚ መሪዎች የአማራ ችግር መዋቅራዊ መሆኑን በመገንዘብ በመዋቅር ለመቀልበስ የሚቋቋሙትን ተቋማት ሲያፈርሱና የተቋሙን መሪዎችም ደም ሲያፈሱ ኖረዋል አሁንም እያፈሰሱ ነው።

ወደፊትም ቀሪ መሪዎችህን ደም አፍስሶ የደም ወንበሩን ለማጽናትና አንተን ምልክቴ አልባ ተቅበዝባዥ ለማድረግ ያለ እረፍት እየሰሩ ነው።ለዚህም ማሳያው ከውድ ልጆችህ ውስጥ የአማራ ፋኖ በጎንደር መሪና የአማራ ፋኖ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂ ሺ አለቃ መሳፍንት ተስፉን ፣ በክስ የሚፈለገውን የአማራ ፋኖ የጋራ ምክር ቤት ዋና አዛዥ ሻለቃ ሰፈር መልስን: የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ዋና አዛዥና የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪ ዋርካው ምሬ ወዳጆን፣ የሸዋ ጀግና የፋኖ መሪዎችና ሰራዊትን እንዲሁም ታላቁ እስክንደር ነጋን ለማጥፋት እያሳደደ ሲሆን : በዚህ ሰዓት ደግሞ የአማራ ሕዝባዊ ሀይል መሪ የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴን ለማጥፋት የሚኖርበትን ቤት በመክበብ የጥይት ዶፍ እያወረደበት ይገኛል።

ይህ ሁሉ የሚያሳየው ትላንትና በቃን ወግዱልን መሪ የለኝም ብሎ አምኖ በህወሃትና : በብልፅግና ተወካዮች ላይ ፍጥኖ ካለመነሳት የመነጨ ነው። ከዚህ በኋላ ሀገርም ብልፅግና የሚባል መሪም የለኝም ብለህ ተነስ: ውጣ: ዝመት::
የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ የተሰራብንን መዋቅር ሰራሽ ችግር በመዋቅር ለመመለስ ላለፉት ሁለት ዓመታት ዳግም ተፈትነው የማይወድቁ ተቋማትን ሲተክል የቆየ ሲሆን አሁናዊ የህልውና ፈተናውን ለመቀልበስ ደግሞ ከወቅታዊ ችግሩ ባሕሪና መልክ ጋር ቀጥታ ከሚያስፈልገው የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት ጋር እንደ መአከልና በስሩ ካቀፋቸው አባላቶቹ ጋር በትጋት በመስራት ላይ ይገኛል::

በዞን ደረጃ ለችግሩ ተመሳሳይ አረዳድ እንዲኖር ከመስራት ጀመሮ ሲወጣ ሲወርድ ቆይቷል አሁንም እየሰራ ይገኛል:: በመሆኑም አንተን ሊያጠፋ የመጣውን የብልፅግናን እሳቤ አሸቀንጥሮ በመጣል አሁን ከበባ ውስጥ ያለውን ውድ ልጅህ አርበኛ ዘመነ ካሴን እንድታድን: በመሳደድ ላይ ላሉት ልጆችህ ደጀን እንድትሆን፣የእስር ትዕዛዝ ለወጣባቸው የፋኖ መሪ አይተኬ ልጆችህ ልዩ ጥበቃ እንድታደርግ እንዲሁም በቃኝ ብለህ ለሥርዓት ለውጥ እንድትነሳ እያሳሰብን በተጨማሪነትም ሕዝባዊ ኮሚቴው ለሚያስተላልፈው ማንኛውም መልክትም በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ለመፈጸም ተዘጋጅተህ እንድትጠብቅ እናሳስባለን።

ህልውናችን በክንዳችን !!!!

የአማራ ሕዝባዊ ኮሚቴ
ሰኔ 7/2015 ዓ.ም

መረጃጭራቁ ብልፅግና በዘመነ ካሴ ላይ ተኩስ ከፍቷል በዙሪያዉ  በአካባቢዉ ያላችሁ ፋኖም ሆነ ሚኒሻ ወደ  ቦታዉ ባስቼኳይ እንድትሄዱ እና ትግሉን እንድትቀላቀሉ ስል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ...
14/06/2023

መረጃ

ጭራቁ ብልፅግና በዘመነ ካሴ ላይ ተኩስ ከፍቷል በዙሪያዉ በአካባቢዉ ያላችሁ ፋኖም ሆነ ሚኒሻ ወደ ቦታዉ ባስቼኳይ እንድትሄዱ እና ትግሉን እንድትቀላቀሉ ስል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ሼር ሼር

ድምፃዊ ዳኜ ዋለ(የጨነቀለት)

የአዲስ አበባ ወጣትን እና የአማራ ተወላጆችን በመደራጀት እያፈኑ እና እያሳደዱ ያሉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ደርሶኛል።1ኛ. ዳንኤል አብዲሳ፤ የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሰላምና ፀጥታ ባለሙያ ነ...
13/06/2023

የአዲስ አበባ ወጣትን እና የአማራ ተወላጆችን በመደራጀት እያፈኑ እና እያሳደዱ ያሉ ግለሰቦች ስም ዝርዝር ደርሶኛል።

1ኛ. ዳንኤል አብዲሳ፤ የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሰላምና ፀጥታ ባለሙያ ነው። ከሁለት ሳምንት በፊት ከቡራዮ ፍቃድ አግኝቶ ሽጉጥ የያዘ ሲሆን ሽጉጡን ኦነግ ሸኔ ነው የሰጠው።

2ኛ. ታሪኩ መንግስቱ፤ የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ ነው።

3ኛ. ጉዴሳ ትሬሳ፤ የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 የብልፅግና አደረጃጀት ፅ/ቤት ኃላፊ ነው።

4ኛ. ታምራት ተረፈ፥ የኦሮሚያ አዲስ አበባ ወጣት አደረጃጀት ሰብሳቢ እና የወጣት ሊግ ስራ አስፈፃሚ ነው።

5ኛ. ብስራት ሙላቱ፤ የወረዳ 6 የወጣት ሊግ ስራ አስፈፃሚ ነው።
ሰሞኑን በኦሮምኛ ቋንቋ ስለአዲስ አበባ ወጣት የጥላቻ ቅስቀሳ በሚዲያ አድርጓል። (መረጃው እንደደረሰኝ አጋራለሁ)

6ኛ. ለሊሳ ፊጤ ያደታ፤ የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ ነው። (ይኸ ሰው በከፍተኛ ሁኔታ አሁንም አማራ እያሳፈሰ ነው )

ፎቶቸውን ከላይ ስማቸው እንደተጠቀሰው በቅደም ተከተል ነው። ያስቀመጥሁት!

ሌሎች ክፍለ ከተማዎችም በቀጣይ ይዤ እመለሳለሁ።

12/06/2023

. ሰበር መረጃ‼️

የአብይ የፀጥታ ግብረሀይል ከክልሉ የፀጥታ ቡድን ጋር አሁን (በዚህ ሰአት) በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 16 በሚገኘው ሆም-ላንድ ሆቴል አማራን ለማጥፋት እየመከረ ይገኛል።

የመረጃ ምንጫችን ስብሰባውን እየተከታተለ የሚገኝ ሲሆን እንደደረሰን የምናጋራችሁ ይሆናል።
ማስጠንቀቂያ‼️
ለከሀዲ አማራዎች በሙሉ፦ አማራን ለማጥፋት ከኦነግ ግብረ-ሀይል ጋር እየዶለታችሁ የምትገኙ ስነ-ልቦናችሁ አማራ ያልሆነ አማራዎች እንድታውቁት የምንፈልገው የቅጣት እርምጃችን ከሁሉም በፊት እናተ ላይ የከፋ እንደሚሆን ነው።

ድል ለአማራ ህዝብ‼️
አንድ ህዝብ አንድ አማራ‼️
ፕሮፌሰር ዘ-አምሀራ

 #በፋኖ ስም በእድሜ ትንሹ ታሳሪ የዓመቱ የራያ ቆቦ አማራ ሆኗል። ፋኖ ብሩክ በየነ በራያ ቆቦ በብልጽግና ካድሬዎች  የፋኖ ተላላኪ ነህ በማለት አስረዉ እያሠቃዩት ይገኛሉ የዋርካዉ ምሬ ወዳ...
12/06/2023

#በፋኖ ስም በእድሜ ትንሹ ታሳሪ የዓመቱ የራያ ቆቦ አማራ ሆኗል።

ፋኖ ብሩክ በየነ በራያ ቆቦ በብልጽግና ካድሬዎች የፋኖ ተላላኪ ነህ በማለት አስረዉ እያሠቃዩት ይገኛሉ የዋርካዉ ምሬ ወዳጆን ስልክ አግንተንበታል ካለበት ተናገር እያሉ እያሠቃዩት ነዉ ለብቻዉ ነዉ የተዘጋበት እና በጣም እየተሠቃየ ነዉ ቆቦ ከከተማዉ ፖሊስ ጣቢያ

ይህ ሰው ኮማንደር መኮነን አየለ  ይባላል።  በአማራ ክልል በመረጃ ሙያነት ቁንጮ ሁኖ ያገለግላል።  ብዙዎቻችንን ያለ ምክንያት እንድንታሰር እንድንሳደድ ያደረገ እና በጎን በኩል  ሌላ ሰዎች...
08/06/2023

ይህ ሰው ኮማንደር መኮነን አየለ ይባላል። በአማራ ክልል በመረጃ ሙያነት ቁንጮ ሁኖ ያገለግላል። ብዙዎቻችንን ያለ ምክንያት እንድንታሰር እንድንሳደድ ያደረገ እና በጎን በኩል ሌላ ሰዎች እንደሚያሳስሩን እንደሚያሳድዱን በአፈ ጮሌዎች አማካኝነት ይነግረናል።

ውስጠ ሚስጥሩን ጠለቅ ብለን ስንመረምር ያገኘነው ግን በተቃራኒው ነው። እሱ የሚፈጽመውን በተቃራኒው ነው መረጃ የሚሰጠው። በማሰርና በማሳደድ አንድም ቀን በየትኛውም ማህበራዊ ሚዲያ ስሙ ተነስቶ አያውቅም።

ዛሬ ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ባልሰጥም አንድ አንድ ከህዝብ ወገን የሆኑትን ወንድሞች በህዝብ ለማስመታት በተደጋጋሚ በተለይም በጸጥታ ሀይል አመራሮች ላይ ስሁት የሆነ መረጃን እያቀበለ የሚገኘው በፎቶ የምታዩት ግለሰብ ነው።
Mereja TV የሚደርሷችሁን መረጃዎች ከቂም በቀል ነጻ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ብትሞክሩ መልካም ነው። የህዝብን ትግል እየደገፈ የሚገኙትን በሁሉም ተቋም ያሉትን ወገኖች ማበረታታት ሲገባ እንዲሸማቀቁ ማድረግ ስህተት ነው።

07/06/2023

በአማራ ህዝብ መደራጀት የደነገጠው አብይ አህመድ!

06/06/2023

ከአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት
የምስራቅ አማራ ፋኖ የአቋም መግለጫ

በአምባገነኑ አብይ አህመድ አሊ የሚመራው አማራ ጠሉ የብልጽግና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት አውጆ ዘርፈ ብዙ ውድመት እያደርሰ ይገኛል። የአማራን ህዝብ በእምነቱና በብሄሩ በዋለበት ባደረበት ሁሉ እያሳደደ አገርም እምነትም እንዳይኖረው ለማድረግ የብልጽግና መንግስት ያለ እረፍት እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ማሳያም የሰሞኑን የአዲስ አበባው የአንዋር መስጅዱ የህዝበ ሙስሊሙ ጭፍጨፋ እና የደብረ ኤልያሱ የቅድስተ ስላሴ አንድነት ገዳም የኦርቶዶክሳውያኑ ጅምላ ጭፍጨፋ ዋነኛ ማሳያ ነው።

ህዝብን በጅምላ መግደሉ፥ ማሳደዱ፥ ማዋከቡ እና ማፈናቀሉ በአማራው ህዝብ ላይ ይበርታ እንጅ በሁሉም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ላይ እንደሆነ የአደባባይ ሀቅ ነው። በኦሮሙማ የሚመራው የብልጽግና መንግስት በአጠቃላይ ሰላም ፈላጊ መንግስት አይደለም። የብልጽግና መንግስት ሀገራን ኢትዮጵያን ብሎም የአማራ ን ወደ ዘላቂ የሰላም እጦትና ቀውስ ውስጥ በማስገባት የሚፈልገውን ሀገረ መንግስት ማዋለድ መዳረሻው እንደሆነ ይታወቃል።

ስለሆነም ባለፈው ሁለት ወራቶች ለሀገርና ለህዝብ ስንል እንደ ትህነግና ኦነግ ደቡብ አፍሪካ ኬንያ ወይም ታንዛኒያ ሳይሆን በሀገር በቀል እሴታችን በሆነው የሽምግልና ስርአት ከመንግስት ጋር ለሰላም ብለን ተደራድረን የነበረ መሆኑ ይታወቃል።ነገር ግን የብልጽግና መንግስት የአማራ ክልልን ሰላምና መረጋጋት ስለማይፈልገው "አታንደፋርሽብኝ" ብሎ አሁን ያለንበትን ጦርነት ከፍቶብናል።

ስለሆነም መላው የአማራ ህዝብ ሆይ የተጀመረው ትግል የፍትህ፥ የእኩልነትና የዲሞክራሲ ብቻ ሳይሆን የመኖር ያለመኖር የህልውና ትግል መሆኑን በመገንዘብ የሞት የሽረት ትግል ማደረግ እንደ ህዝብ ብቸኛ መዳኛችን መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።

በመጨረሻም የተጀመረው የአማራ ህዝብ ትግል የህልውና ብሎም የተቀማናትን ሀገራችን ኢትዮጵያን የማስመለስና የሀገራችን ባለቤት የመሆን ነውና የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ለህዝባችን የሚከተሉትን ጥሪ ያቀርባል።

1ኛ. የአማራ ፋኖ አንድነት ም/ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ ከነጻነት ታጋዩ እስክንድር ነጋ ጋር በአንድነት እየሰራን የነበረ ሲሆን አሁን ከተመሰረተውና በእርሱ ከሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር ጋር በጋራ የምንታገል መሆኑን ለህዝባችን ለመግለጽ እንወዳለን።

2ኛ. የአምባገነኑን ስርአት ነውር በአደባባይ በመቃወማቸው እና ከህዝብ ጎን በመቆማቸው ያለወንጀላቸው የታሰሩት የአማራ ተወላጅና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች፥ አትጊዎች፥ ሙህራኖችና ፋኖዎቻችን እንዲፈቱ ህዝባችን የጋራ ትግል እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን።

3ኛ. መላው ህዝባችን በሀይማኖት ተቋማት በተፈጸመው ጭፍጨፋ ለጠፋው ነፍስና ለወደመው ንብረት የአብይ አህመድ የብልጽግና መንግስትን ተጠያቂ እንዲያደርግና በድርጊቱ የተሳተፉ ሁሉ ለህግ እንዲቀርቡ ህዝባችን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ስንል ጥሪ እናቀርባለን።

4ኛ. በሀይማኖት ተቋማቶቹ እና ጦርነት በተከፈተበት ቦታ ሁሉ ለጠፋው ነፍስና ለወደመው ንብረት መንግስት ካሳ እንዲከፍል እንጠይቃለን።

5ኛ. ከአማራ ህዝብ አብራክ የወጣችሁ ከቀበሌ እስከ ፌደራል ያላችሁ አመራሮች፥ፖሊሶች፥ሚሊሾችና አድማ ብተናዎች ከቻላችሁ ከህዝባችሁ ጎን ተሰልፋችሁ ይህንን ውስጡ የተፈረካከሰና የበሰበሰ ስርዐት እንድትታገሉ ጥሪ እያቀረብን ይህንን ሳታደርጉ ብትቀሩ ግን በእናንተም ሆነ በቤተሰቦቻችሁ ላይ ለሚደርስ ማንኛውም አይነት ጥቃት ሀላፊነት የማንወስድ መሆኑን ለማረጋገጥ እንወዳለን።

6ኛ. በባህር ማዶ በአሜሪካ፥በአውሮፓ፥በአረብ ሀገራቶች በአጠቃላይ በመላው ውጪው አለም የምትኖሩ የአማራ ተወላጅ ዲያስፖራዎች በጸረ-ወያኔ ትግሉ የነበራችሁ ጉልህ ሚና አሁን ላለንበት የህልውና ትግልም ይኼው የነበረው ፋኖን በትጥቅና ስንቅ ብሎም በሀሳብ የማደራጀትና ለድል የማብቃት ጉልህ ሚናችሁ እስከ ዘላቂ ነጻነት ድረስ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአማራ ህዝብና በሀገራችን ኢትዮጵያ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በመጨረሻም ወንድማችን አርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን እንኳን ከጠባቡ እስር ቤት ወደ ሰፊው እስርቤት እግዚአብሄር በደህና አመጣህ እያልን በቀጣይም የተጀመረው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ለድል ይበቃ ዘንድ ያለህን የመሪነት ሚና አጠናክረህ እንድትቀጥል እንፈልጋለን።

አማራ በልጆቹ ትግል ህልውናውን አረጋግጦ የተቀማውን ሀገሩን ኢትዮጵያን ያስመልሳል። የሀገሩ ባለቤትም ይሆናል።

ምስራቅ አማራ ፋኖ
ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም

06/06/2023

በኮረኔል ፈንታው ሙሃባ እና ኮረኔል ሞገስ ዘገየ ከሚመራው የፋኖ ኃይል በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ‼️

መንግሥት የእምነት ተቋማትን ለማውደም ንፁሃንን በግልፅ ለመጨፍጨፍ እንዲመቸው ህግ ማስከበር በሚል ተልካሻ ልብ ወለድ በመድረስ ሆን ብሎ በህዝባችንና በእምነት ተቋሞቻችን ላይ ግልፅ የሆነ ጦርነት በመክፈት ከፍተኛ ውድሙት በአማኞችና በእምነት ተቋሞች ላይ እያደረሰ ይገኛል።

በመሆኑም መንግሥት የራሱን ፍላጎት ፍፁም ጥላቻና እብሪት በህግ ማስከበር ስም እየተወጣና ህዝባችን ላይ ባለው ወደር የሌለው ጥላቻ በግልፅ እየገደለንና ጥላቻውንም ፊት ለፊት እያሳየን ይገኛል። ህገ ወጡና ሽብርተኛው የአብይ አህመድ መንግሥት የዘር ጨፍጫፊነቱን ህጋዊ ለማድረግ የሄደበት ርቀት ህዝብን እያታለለ የሚኖርበት ያደገበት ቀጣፊ ባህሪው እንደሆነ እኛም እንገነዘባለን ህዝባችንም ጠንቅቆ ያውቃል።

በመሆኑም አንባገነኑ የአብይ አህመድ መንግሥትና ሰራዊቱ በንፁሃን ህዝባችን ላይ እየደረሰ ባለው ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ በእጅጉ ያዘንንና ልባችን የደማ እንደሆነ ለመግለፅ እየወደድን ጉዳትና ሞት ለደረሰባቸው ንፁሃን ጠበልተኞች የገዳም አባቶች እና በመስጊድ ውስጥ ጉዳትና ሞት እንዲሁም በንፁሃን ህዝባችን ላይ የተፈፀመባችሁን ድርጊት እያወገዝን ለቁስላችሁ ምህረትን ለሞታችሁ እረፍትን ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ ከልብ መፅናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን።

እንደሚታወቀው መንግሥት እንደ ህዝብ አማራን! እንደ እምነት ተቋም የኢትዮጵያን ህዝብ ነባር እምነት የሆኑትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስና እስልምንና ጠል መሆኑና እነርሱን ለማጥፋትም 7/24 ያለ እረፍት የሚሰራ ነውረኛ ኢትዮጵያ ጠል መንግሥታዊ ስርዓት መሆኑ ይታወቃል። ይህ የከረፋ መንግሥታዊ ስርዓት የጀመረውን ከታች የዘረዘርናቸውን አፀያፊ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆም ስንል በጥብቅ እናሳስባለን።

1ኛ. በታላቁ እስክንድር ነጋና በሚመራው የአማራ ህዝባዊ ግንባር /APF ላይ የሚደረግን ስም ማጥፋትና የማሳደድ ተግባር እንዲሁም በግንባሩ መሪ እስክንድር ነጋ ላይ የታወጀውን የግድያ ትዕዛዝ የማንቀበለውና እስከ መጨረሻውም ከፅኑ ታጋያችን ጎን እንደምንቆም እየገለፅን ከግንባሩ የሚወርዱ ማናቸውንም ትእዛዝና ግዳጅ ለመፈፀም ሙሉ ፍቃደኞችና ዝግጁ መሆናችንን ጭምር ከወዲሁ እንገልጻለን።

2ኛ. በመዲናችን አዲስ አበባ በሙስሊሙ እምነት ተከታዮች የሚደረግን ጭፍጨፋና አዲስ ከተማ ለማዋለድ በሚል ፌዝ ወይም ህዝባዊ ንቀት የመስጂድ/የእምነት ተቋማት ውድመትና ማንነት ተኮር መፈናቀሎችን የምናወግዝና ከእንግዲህ የማንታገስ እንደሆነ ለማሳወቅና የትግል ቀይ መስመራችንም እንደሆነ በማወቅ ከልጅ እስከ አዋቂ ከጎናችን እንድትቆሙ ሕዝባዊ የትግል ጥሪያችንን እናቀርባለን።

3ኛ. በምስ/ጎጃም ደብር ኤሊያስ ገዳም ላይ የደረሰውን አስነዋሪ መንግሥታዊ ሽብር እያወገዝን ህዝባችን ራሱን ለማይቀርለት የሞት ሽረት ትግል ራሱን ከወዲሁ እንዲያዘጋጅ እና የተጀመረውን ሕዝባዊ ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና እንዲሁም ያልተቀላቀለ ለቅድስናው ትግል ራሱን እንዲያዘጋጅና በየደረጃው ለሚደረጉ ጥሪዎች ነቅቶና ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

4ኛ. የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች መንግሥት እያደረገ ባለው አፀያፊ ተግባር ባለመሳተፍ ህዝባዊነቱችሁን ከህዝብ ጎን በመቆም እንድታሳዩ ጥሪ እያቀረብን ይህን ማድረግ ያልቻለ ሰራዊት ከህዝብ የተነጠለ የፓርቲ ዘበኛ እንደሆነ አውቆ ከቻለ ከመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ከማናቸውም የመንግሥት ፀጥታ ተቋማት ራሱን እንዲያገልና ከህዝብ ጎን እንዲሰለፍ በህዝብ ስም ጥሪ እናቀርባለን።

በመጨረሻም አማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በግለሰቦች ፍላጎት በሃሰተኛ ከሳሾች ያለምንም ፍርድ በእስር ላይ ሲንገላታ የከረመው ጓዳችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ከእስር ተፈቶ ቤተሰቡንና የሚወደውን ህዝቡን በመቀላቀሉ የተሰማንን ልባዊ ደስታ እየገለፅን ወደ ተጀመረውም ፈታኝ የትግል ጉዞ በማይናወጠው ፅኑ አቋሙ በአጭር ጊዜ በተሻለ ስነልቦናና በተሻለ የትግል መንገድ እንደሚቀላቀልና ለትግላችን ትልቅ አቅም እንዲሚሆን ኃይላችን በፅኑ ያምናል።

ኃይላችን ያለው "ፋኖ" ከሚለው ታላቁ ስማችን ላይ ነው።
ድል ለሰፊው ለአማራ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ግንቦት 28 ቀን 2015 ዓም

ሰበር መረጃበዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በደብረ ኤሊያስ እና አካባቢው  መንግስት አካሄድሁት ባልው ኦፕሬሽን  ብዙ ወታደሮቹ ከጥቅም ውጭ የተደረጉበት መሆኑና በዚህ የተበሳጨው ይህ ታጣቂ የገዳሙን ...
05/06/2023

ሰበር መረጃ

በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በደብረ ኤሊያስ እና አካባቢው መንግስት አካሄድሁት ባልው ኦፕሬሽን ብዙ ወታደሮቹ ከጥቅም ውጭ የተደረጉበት መሆኑና በዚህ የተበሳጨው ይህ ታጣቂ የገዳሙን ፀበልተኞችን እስከ የገዳሙ መነኩሴዎች ድረስ መረሸኑ የሚታወቅ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ለስልጣነ መንበሬ ስጋት ነው ያለውን የጎጃምን በተለየም የደብረ ኤሊያስን አካባቢ በልዩ ሁኔታ ለመጨፍጨፍ አዲስ የኦፕሬሽን እቅድ ማውጣቱን ከውስጥ ምንጫችን በኩል ለማወቅ ችለናል።

በዚህም መሰረት ፋሽስቱ አብይ አህመድ በወታደራዊ ማዕበል መውረርና በአየር ሀይል የታገዘ ጭፍጨፋ ማድረግን የአዲሱ እቅዱ አካል አድርጎ ማምጣቱን ለማውቅ ችለናል። በዚህም "ሰባሪ" የሚል ስያሜ በተሰጠው ኦፕሬሽንም አማራ የሆኑ ወታደራዊ አመራሮች የተገለሉበትና ሙሉ በሙሉ በኦሮሞ አመራሮች ብቻ የሚመራ የጭፍጨፋ እቅድ መሆኑን መረጃውን አድርሰውናል።

ይህ ወራሪ ሀይል የአማራን ህዝብ ለማጥፋትና ለመውረር በሚያደርገው እንቅስቃሴም በአአካባቢው የአማራ ህዝብ ከኋላ ጥቃት ይደርስብኛል የሚል ስጋት ስላደረበት የሀይሉን እንቅስቃሴ በሌሊት እና በኤሊኮፍተር የታገዘ ጉዞ ማድርግን የእቅዱ አካል ማድረጉን ለማወቅ ችለናል።

እያንዳንዷን የአብይን አካሄድና ትዕዛዝ ከአፉ እንደወጣች ለኛ ስለምትደርስ የመከላከል ዘዴአችን ቀይረን እንጠብቀዋለን።

በነገራችን ላይ የዚህ ጉጀሌ ቡድን ድንቁርና የሚታየው አየር ሀይል የት ቦታ መጠቀም እንዳለበት እንኳን አያውቅም። ሆኖም ግን የአየር ሀይል ብሎ የሚደሰኩርበትን የጉዳት መጠኑን ስለምናውቀው ስጋታችን ሊሆን አይችልም። እንዳመጣጡ ቀምሶ ይመለሳል።

ድል ለአማራ ህዝብ !!

05/06/2023

ሰበር ዜና
በአምባሰል ወረዳ ፋኖን ደምስሱ ተብለው የተላኩ የብአዴን አመራሮችና አገልጋዮች ተማረኩ።

የአብይ አገዛዝ የጭካኔ ጥግ በደብረኤሊያስ ገዳማዊያን ላይ!የአብይ አህመድ/ኦህዴድ ሰራዊት በደብረኤሊያስ ገዳም የሚገኙ ፀበልተኞችን ለቀረፃ አንተባበርም ያሏቸውን ፀበልተኞች በዚህ መልኩ አሰል...
05/06/2023

የአብይ አገዛዝ የጭካኔ ጥግ በደብረኤሊያስ ገዳማዊያን ላይ!

የአብይ አህመድ/ኦህዴድ ሰራዊት በደብረኤሊያስ ገዳም የሚገኙ ፀበልተኞችን ለቀረፃ አንተባበርም ያሏቸውን ፀበልተኞች በዚህ መልኩ አሰልፈው ረሽነዋቸዋል። ከተረሸኑት መካከል ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን ወጣት እጁን ወደኋላ አስረው በዚህ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ረሽነውታል።

ሰበር_መረጃየወልድያ ብልፅግና አመራሮች እርስ በርስ ተታኮሱወልደያ የብልፅግና አመራር ተከፋፍሎ  እየተጠፋፋ ነው። አዳሩን የዞኑ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ ቤት በድሸቃና በብሬን የተደበደበ ሲሆን...
01/06/2023

ሰበር_መረጃ

የወልድያ ብልፅግና አመራሮች እርስ በርስ ተታኮሱ

ወልደያ የብልፅግና አመራር ተከፋፍሎ እየተጠፋፋ ነው። አዳሩን የዞኑ ሰላምና ደህንነት ሃላፊ ቤት በድሸቃና በብሬን የተደበደበ ሲሆን፣ በተመሳሳይ እዛው ወልዲያ ፒያሳ አካባቢ ምሽት ላይ ለፀጥታ ስራ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ሚሊሻዎች ላየ በተፈፀመ የቦንብ ጥቃት 7 የሚሆኑ መቁሰላቸው ተነግሯል።

የአማራ ህዝብ ከእንግዲህ ለፖለቲካ ትንተና በሚደርግ ስብሰባ በመሳተፍ ጊዜውን ማጥፋት የለበትም። በውጭም፣ በሀገር ቤትም ቁጭ ብሎ ስለ ፖለቲካ የሚተነትን ሞልቷል። የጎደለን በተግባር የሚታገል...
31/05/2023

የአማራ ህዝብ ከእንግዲህ ለፖለቲካ ትንተና በሚደርግ ስብሰባ በመሳተፍ ጊዜውን ማጥፋት የለበትም። በውጭም፣ በሀገር ቤትም ቁጭ ብሎ ስለ ፖለቲካ የሚተነትን ሞልቷል። የጎደለን በተግባር የሚታገል ቆራጥ ነው። ስለ አብይ አህመድ ኦሮሙማ ኘሮጀክት የአርሶ አደር እናቶች ሳይቀሩ በሚገባ ይተነትኑታል። ስለዚህ ሙሉ ሀይላችንን በተግባረሰ የትጥቅ ትግል ላይ ማድረግ ይጠበቅብናል። በትጥቅ የሚደገፍ የከተማ ላይ ሰልፍም አማራጫችን ነው።

(ሻለቃ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ - የአማራ ህዝባዊ ግንባር የውጭ ሀገር አስተባባሪ)

ቁርጥ መንግስት ... ‼➙ ለብልፅግና አመራሮች ቢሮ እድሳትና ፈርኒቸር ግዢ  ዶላር አለ፤➙ ለፓርክ ግንባታ ግብዓቶች ግዢ ዶላር አለ፤➙ ለድሮን መግዣ ዶላር አለ፤➙ ለችግኝ፣ ለአትክልት ፣ ለ...
30/05/2023

ቁርጥ መንግስት ... ‼

➙ ለብልፅግና አመራሮች ቢሮ እድሳትና ፈርኒቸር ግዢ ዶላር አለ፤
➙ ለፓርክ ግንባታ ግብዓቶች ግዢ ዶላር አለ፤
➙ ለድሮን መግዣ ዶላር አለ፤
➙ ለችግኝ፣ ለአትክልት ፣ ለአበባ ፣ ወዘተ መግዣ ዶላር አለ፤
➙ የበረሃ አሸዋ መቅዘፊያ ተሽከርካሪ መግዣ ዶላር አለ፤
➙ ለብልፅግና ጌቶች መጠበቂያ የሚሆን ዘመን አፈራሽ ጠበንጃ እና ተተኳሽ መግዣ ዶላር አለ፤
➙ የአፈና ቴክኖሎጂ ለመግዣ ዶላር አለ፤

ግንሳ ፤

▪️ለእርሻ የሚሆን ማዳበሪያ መግዣ ዶላር የለም
▪️ የምርጥ ዘር መግዣ የሚሆን ዶላር የለም
▪️ለፍትሐዊ የግብርና ሽግግር የሚሆን ግብዓት መግዣ ዶላር የለም
▪️የማዳበሪያ ፋብሪካ መገንቢያ ዶላር የለም
▪️ ለስኳር ፋብሪካ ግንባታ የሚሆን ዶላር የለም

አየኸው!?

ምን ሆነ መሰለህ! ያኔ በዘውዳዊው አገዛዝ ዘመን፣ በመሳፍንትና መኳንንት ቤት የሆነ ነው።
የቤቱ እመቤት ፡ ታዛዥ ፈልገው ሠራተኞች ተጣሩ።

"አሽከር!?" አሉ።

" እመት እመቤቴ?" ብላ፡ አንዲት ቆንጆ መልከኛ ልጅ፣ እጅ ነሳች።

እመቤትቷ ተመለከቷት!! በጣም ቆንጆ ናት።
"አንችው ነሽ አሽከሯ !?" ጠየቋት።
"አዎ እመይቴ!" አለች!!።

"ቁርጥ ሰው!!" አሏት።

እናሳ!

ያለንበት አገዛዝ ቁርጥ መንግስት አይመስልም ⁉

ድል ለአማራ !!



አመፅና ጦርነትን የዓላማ ማስፈፀሚያ ያደረገ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ልማድ እየፈተነን ነው ‼ይሔ አርሶአደር፤➙ ገዢዎች በፈጠሩለት፣ እሱ ምክንያት ባልሆነበት የሁለት ዓመት ጦርነት በአንድ በኩል...
30/05/2023

አመፅና ጦርነትን የዓላማ ማስፈፀሚያ ያደረገ የ19ኛው ክፍለ ዘመን ልማድ እየፈተነን ነው ‼

ይሔ አርሶአደር፤

➙ ገዢዎች በፈጠሩለት፣ እሱ ምክንያት ባልሆነበት የሁለት ዓመት ጦርነት በአንድ በኩል ዝመት ተብሎ፤ በሌላ በኩል የዘመቻ ስንቅ አዋጣ ተብሎ ሲሰቃይ የከረመ ነው!!

➙ ያለውን ብቻ ሳንሆን የሌለውን አዋጥቷል። ልጆቹን፣ ወንድሞቹን፣ በሬዎቹን፣ ሀብቱን እና ጊዜውን ለአገዛዙ ጦርነት ሰውቷል!!

➙ ይሔንን "የለውጥ ዘመን" ተብዬ ዓመታት ሁሉ፣ የሚያማክረው፣ የሚያወያየው፣ የሚያዳምጠው ፣ የሚያከብረው መሪ እና አመራር አላገኘም።

➙ ሁለንተናዊ የግብርና ምርት ለውጥ ትልም በሌለበት፣ የምርጥ ዘር አቅርቦት በሌለበት፣ የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት በታጣበት፣ "የፎቶ ግብርና ሽግግር" ግብዓት ይሆን ዘንድ፣ ለፓርኮችና መዝናኛዎች ቅድሚያ በሰጠ አገዛዝ ጫና ውስጥ የከረመ ነው።

➙ በነዚህ ዘመናት ሁሉ የወገኖቹን ግድያ ሲስማ፣ የወገኖቹን መፈናቀል ሲመለከትና ሲያስተናግድ ነው የከረመው፤

➙ ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እየጠየቀ፤ ፋኖና ልዩ ኃይልን አምጣ የሚባል ገበሬ ነው።

ይሔ ሁሉ ግን የገዢው ቡድንን የጥቅለላ እና መስፋፋት ዓላማ ለማስፈፀም አመፅና ጦርነትን ተገቢ መሣሪያዎች አድርጎ በቆረጠ አገዛዝ ስር በመሆናችን ነው።

አመፁም፣ ቀውሱም፣ ስቃዩም፣ ... አስፈላጊና አይቀሬ አድርጎ በሚያስብ አገዛዝ ስር እንገኛለን !!

ሆኖም ከገበሬው ጋር ተጣልቶ የሚፀና ስርዓት የለምና የአብይ አገዛዝ ከጥቅለላ ፋሽስታዊ ቅዠቱ ይገረሰሳል!

ፋሽዝምና ፋሽስቶች ይሸነፋሉ !

ድል ለሰፊው ሕዝብ !
ድል ለአማራ !



29/05/2023

የደብረኤልያስ ሕዝብ ጥሪ አቀረበ‼️

አንገት ለአንገት ከፋሽቱ አገዛዝ ጋር እየተናናቀ ያለው የደብረኤልያስ እና አካባቢው ሕዝብ እንዲሁም ሕዝባዊ ኃይሉ ከደጀን እስከ ባህርዳር ያሉ መንገዶች እንዲዘጉ እና በቅርብ የሚገኘው የአማራ ሕዝባዊ ኃይል የተቃጠብንን ጥቃት በመመከቱ በኩል እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

በማንነቱ እና በሐይማኖቱ ጥቃት የተከፈተበት የደብረኤልያስ እና አካባቢው ሕዝብ፤ ሴት፣ ወንድ ሳይል ከህጻን እስከ አዋቂ ራሱን የመከላከል ክተት አውጆ ሊያጠፋው ከመጣው የፋሽስት አገዛዝ ጋር አንገት ለአንገት መተናነቁን ከቦታው በደረሰን መረጃ መሠረት ማረጋገጥ ችለናል።

29/05/2023

መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሞክራችኋል በሚል ለ28 ቀናት በኦሮሚያ ክልል ገላን ከተማ በሚገኘው የልዩ ሀይሉ ካምፕ ውስጥ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሲፈፀምባቸው መቆየቱን ለአማራ ድምፅ ተናግረዋል።

ከታፈኑት መካከል የምኒልክ ሆስፒታል፣ የአለርት ሆስፒታል፣ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ከፍተኛ ሀኪሞች ይገኙበታል።

ከታሣሪዎቹ መካከል የእግር እና የእጃቸው ጥፍር በፒንሳ የተነቀለ፣ ጀርባቸውን በኤሌክትሪክ የተገረፉ በዱላ እና በክላሽ ሰደፍ የተደበደቡ መኖራቸውም ተገልጿል።

ከ28ቱ ሰዎች ውስጥ አንዷ ሴት ስትሆን በተደጋጋሚ በቡድን ሲደበድቧት መሰንበታቸውንም እስረኞቹ ተናግረዋል።

በተፈፀመባት ድብደባ በአፍና እና በአፍንጫዋ ደም ሲፈሣት መቆየቱንና እስከአሁንም ህክምና ማገኘት እንዳልቻለች የአማራ ድምፅ ለማረጋገጥ ችሏል።

እስረኞቹ ለ28 ቀናት በጨለማ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን እና በቀን አንድ ግዜ ብቻ ደረቅ ዳቦ ሲቀርብላቸው እንደነበርም ተናግረዋል።

28ቱም ከአድስ አበባ ከተማ የተወሰዱ ሲሆን በምርመራ ላይ ሲጠየቁ የነበሩት የአማራን ህዝብ አደራጅታችሁ መንግስትን ለመገልበጥ እየሰራችሁ ነው፣ ይህ ደግሞ አይሳካላችሁም፣ ከፈለጋችሁ አዲስ አበባን ለቃችሁ ውጡ የሚል እንደነበር ነው የገለፁት።

በህቡዕ ተደራጅታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እየተንቀሳቀሳችሁ ነው፣ አማራ ክልል ድረስ አደረጃጀት ዘርግታችሁ ሁከት እና ብጥብጥ ቀስቅሳችኋል፣ ማነው መሪያቹህ? በሚል በጦር መሣሪያ እና ስለታማ መሣሪያ በተለይ አንገታቸው ላይ በማድረግ ሲያስፈራሯቸው እና ምርመራ ሲካሄዱባቸው መሰንበቱን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እናንተ ኦሮሞ ጠል ናችሁ፣ ይህ ስርአት ወደዳችሁም ጠላችሁም የኦሮሞ ስርአት ነው፣ በአዲስ አበባ መኖር ከፈለጋችሁ ለጥቀጥ ብላችሁ የኦሮሞን ህዝብ እግር ማጠብ አለባችሁ፣ ካልፈለጋችሁ ግን ከተማዋን ለቃችሁ ውጡ በሚልና ሌሎች ፅያፍ ስድቦችን መርማሪ ፖሊሶች ሲሰድቧቸው እንደነበር ነው የተናገሩት።

ከታሳሪዎቹ መካከል 28ቱ ከ28ቀን ቦኋላ ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን አሁንም እዛው ገላን በሚገኘው የልዩ ሀይሉ ካምፕ ድብደባ እየተፈፀመባቸው ያሉ የአማራ ተወላጆች መኖራቸው ተጠቁሟል።

ከእስረኞቹ መካከል በተለይ አንደኛው በምርመራ ላይ በተፈፀመበት ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በተኛበት እንደሚፀዳዳ እና ራሱን መቆጣጠር እንደተሳነው እንዲሁም ለአዕምሮ ህመም መዳረጉን ነው የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የአማራ ድምፅ ሚድያ ማረጋገጥ የቻለው።

28ቱ እስረኞች ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ/ም ሜክሲኮ ወደሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው እንደሚከተለው ይቀርባል፦

1ኛ፦ቢኒያም አለማየሁ(ሲቪል ኢንጂነር)
2ኛ፦መላክ ምሳሌ (መሐንዲስ)
3ኛ፦ዳዊት ይፍሩ(ዋና ኢንስፔክተር)
4ኛ፦ጌጤ አመኑ(ሳጅን)
5ኛ፦ጌታወይ ታደሰ(ኮማንደር)
6ኛ፦አወቀ ስንሻው(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰራተኛ)
7ኛ፦ ይመር ምንተስኖት(ሲቪል ኢንጂነር)
8ኛ፦ጌታነህ ብርሀኔ(ጤና መኮነን/ምኒልክ ሆስፒታል)
9ኛ፦አብርሃም መልካሙ(ሳይካትሪስት/የአለርት ሆስፒታል)
10ኛ፦ምኒበል ጀግኔ(ሳይካትሪስት/የጦር ሃይሎች ሆስፒታል)
11ኛ፦ኤርሚያስ መኩሪያ(phd)
12ኛ፦ደበበ ባሻህውረድ(ባለሃብት)
13ኛ፦ንብረት አበጀ(የግሮሰሪ ባለቤት)
14ኛ፦ይልማ በዛብህ(በቦሌ ክ/ከተማ የደንብ ማስከበር ፅ/ቤት ኃላፊ)
15ኛ፦ቅድስት ከበደ(የቤት እመቤት)
16ኛ፦ፍቃዱ መንግስቴ(ፋርማሲስት/ዘውዲቱ ሆስፒታል)
17ኛ፦አንዷለም አሻግሬ(እንስፔክተር)
18ኛ፦ማናየ አየለ(MBA/የግል ስራ)
19ኛ፦አለም ሁሉምጤና(መምህር)
20ኛ፦ይስሃቅ አይቼው(መርጌታ)
21ኛ፦ጌታነህ ታከለ(የአየር መንገድ ሰራተኛ)
22ኛ፦እንዳልካቸው እሸቱ(የሸገር ብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት ሰራተኛ)
23ኛ፦ክበር አለማየሁ(መሐንዲስ)
24ኛ፦ባሳዝን እርገጤ(የአንበሣ ባስ አሽከርካሪ)
25ኛ፦መብራቱ አበራ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)
26ኛ፦ውበት አካል(ጥበቃ)
27ኛ፦ዜና ሀይሉ(የኮንስትራክሽን ሰራተኛ)
28ኛ፦ሰለሞን ደሴ(ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 11 አካውንታንት)

እነዚህ የአማራ ተወላጅ የሆኑ 28 ሰዎች ለ28 ቀናት ገላን በሚገኘው የልዩ ሃይሉ ካምፕ ውስጥ በጨለማ ክፍል ታስረው የግፍ አይነት ሲፈፀምባቸው የነበሩና ከግንቦት 18/2015 ዓ/ም ጀምሮ ሜክሲኮ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተዛወሩ ናቸው።

👉 እነዚህ የአማራ ተወላጆች በ28 ቀናት ውስጥ የተፈፀመባቸው የግፍ አይነት፦

1ኛ የተፈፀመባቸው አካላዊ በደል፦
፦ግርፋት
፦በኤሌክትሪክ (shok)
፦ስብዕና የሚነኩ ስድቦችን እየተሰደቡ ግድግዳ መግፋት
፦በክላሽ ሰደፍ ድብደባ
፦ጥፍራቸውን በፒንሳ መነቀል
፦ምግብ መከልከል
፦አድራሻቸው መሰወር(ቤተሰብ ያሉበትን እንዳያውቅ)

2ኛ የተፈፀመባቸው ስነልቦናዊ በደል፦
፦የምኒልክ ቆማጣዎች
፦የታሪክ ሌቦች
፦መጤዎች
፦ተስፋፊዎች
፦ቁምጣ ለባሾች
፦የምትጠይቁትን የማታውቁ
፦ወራሪዎች
፦ለእናንተ ስልጣን ከምናጋራ ኢትዮጵያ ትፍረስ
፦አዲስ አበባ የኛ ናት ስሟም ፊንፊኔ ነው
፦ወያኔ ቤታችሁ ድረስ መጥቶ ሚስትህን፣ልጅህን፣እህትህን እና እናትህን ሲደፍር የት ነበራችሁ?...እኛነን ያዳናችሁ
፦እንዴት ከኦሮሞ ጋር ትፎካከራላችሁ?እናንተ የኦሮሞን ያክል መብት ሊሰጣችሁ አይገባም
፦ገና ጨፍጭፈን ከምድረገፅ እናጠፋችኋለን የሚሉ ስድቦች እና ማስፈራራቶች ናቸው።

👉በአሁን ሰአት በአማራ ተወላጆች ላይ የሚካሄደውን አፈና በበላይነት የሚመሩ እና የሚያስተባብሩ ተቋማት፦
፦የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ
፦የብሔራዊ ደህንነት ቢሮ
፦ቴሌ ኮሙዩኒኬሽን
፦የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
፦የኦሮሚያ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ
፦የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን
፦የገላን ፖሊስ መምሪያ
፦በኦሮሞ ህዝብ ስም የተቋቋሙ የቢዝነስ ተቋማት እና የኦሮሞ ባለ ሀብቶች
፦እራሱን "የኦሮሚያ ሲኖዶስ" በሚል የሚጠራው ተቋም

👉የአማራ ተወላጆችን በማሳፈን፣ ምርመራውን በመምራት እና አሰቃቂ ድብደባ እንዲሁም ግፍ እንዲፈፀምባቸው ትዕዛዝ በመስጠት የሚሳተፉ፦
፦ደመላሽ ገ/ሚካኤል(የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር)
፦ተመስገን ጥሩነህ(ከብሔራዊ ደህንነት)
፦መላኩ ፈንታ(ከወንጀል መከላከል ቢሮ)
፦ዘላለም መንግስቴ(የወንጀል ምርመራ ኃላፊ)
፦አበራ ወንዴ(የኦፕሬሽን መምሪያ ኃላፊ)
፦አህመድ አብደል(የኦፕሬሽን መምሪያ ም/ኃላፊ)
፦ኮ/ር ኢብራሂም(የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ኃላፊ)
፦ኮ/ር ኢቻራ(የኮማንዶ ልዩ ኦፕሬሽን ም/ኃላፊ)
፦ምክትል ኢንርፔክተር ኢፋ(የስለላ ኃላፊ) እና ሌሎች የደህንነት አባላት

Daily Informer

የአብይ ቡድን ነጣጥሎ ሊበላን ካሰበ እኛም ምርኩዞቹን እየነጣጠልን እንበላቸዋለን። በጧቱ ልጥፌ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ከፍተኛው የአማራ ብልፅግና የአብይን ትዕዛዝ ለመፈፀም ተስማምተዋል። ኦፕ...
29/05/2023

የአብይ ቡድን ነጣጥሎ ሊበላን ካሰበ እኛም ምርኩዞቹን እየነጣጠልን እንበላቸዋለን። በጧቱ ልጥፌ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ከፍተኛው የአማራ ብልፅግና የአብይን ትዕዛዝ ለመፈፀም ተስማምተዋል። ኦፕሬሽኑን ደግሞ ለስሙ በአቶ ተመስገን ጥሩነህ የሚመራው የኦህዴድ ደህንነት እና መከላከያ ሲሆን ክልሉ ላይ ደግሞ በዋናነት እያስተባበሩ ያሉት የምናምን የምናምን አስተባባሪ ክላስተር ሀላፊ የተባለው ሰማ ጥሩነህ እና የክልሉ ሠላምና ደህንነት አቶ ደሳለኝ ጣሰው የተባለ ምዕራብ ጎንደርን የኮንትሮባንዲስት እና በመንደር የተደራጁ ሌቦች መጫዎች አድርጎት የመጣው የማይረባ ሰው ነው። በነገራችን ላይ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ እንዲገደል የተስማማ ሰው ነው።

አቶ ሰማ ጥሩነህ የቅማንት ኮሚቴን በማገዝ በጎንደር ከፍተኛ ደም አፍሳሽ ግጭት ሲያደርግ የነበረ እና አሁንም ስራ ወዳዱን የአገው ህዝብ እና የጎጃም አማራ ህዝብን ወደ ግጭት በማስገባት አካባቢውን የቀውስ ቀጠና አድርጎታል። ከጃዊ ትልቁ ተራራ በስተጀርባ የአገው ሸንጎ የሚባሉ ታጣቂዎች በመሠልጠን ላይ ይገኛሉ። ይህ ቡድን ዋና ተልዕኮው በዛ አካባቢ ያለን ገበሬ እንዲገድል: እንዲያፈናቅል : እንዲማረር በማድረግ አካባቢውን ለቆ እንዲወጣ በእነ ሰማ ጥሩነህ በስውር እየተሰራበት ይገኛል። ሰማ ጥሩነህ በዚህ አያበቃም ቁርጠኛ የአማራ ጀነራሎችንም እንዲመቱ በመሠለል ለእነ አብይ እና ለእነ ብርሃኑ ጁላ ሪፖርት ያቀርባል።

ስለሆነም እነሱ ተከፍፍለው በአማራ ህዝብ ላይ ጦርነት ሲያውጁ: ሲገድሉ: ሲያፈናቅሉ እኛም ተነጥለው ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረጋችን ከትክክልም በላይ ነው። የያዝነው ትግል ነው። እነሱ አምርረው ሊያጠፉን እንደተነሱት እኛም አምርረን እንታገላቸዋለን።አንዳንዶቻችሁ እናንተ የምትፈልጉትን ብቻ እንድንዘምት አትቋምጡ። እንደ አኪለስ ተረከዝ የስርዓቱን ቁርጭምጭሚት በመምታት ትግላችንን እንቀጥላለን።

22/05/2023

"ሰሚ ያጣው ትንቢት" ሁላችሁም አድምጡት

"ሴትዮዋ የሰጡኝ ኮንዶሚኒየም ሽንት ቤት የሌለው ነው፤  እናም ቀይረን ባለ 40/60 እንሰጥኻለን ቢሉኝም እስካሁን ድረስ የተገባልኝ ቃል ተፈጻሚ ባለመሆኑ የሐብታሙ አያሌውንና የብሩክ ይባስን...
22/05/2023

"ሴትዮዋ የሰጡኝ ኮንዶሚኒየም ሽንት ቤት የሌለው ነው፤ እናም ቀይረን ባለ 40/60 እንሰጥኻለን ቢሉኝም እስካሁን ድረስ የተገባልኝ ቃል ተፈጻሚ ባለመሆኑ የሐብታሙ አያሌውንና የብሩክ ይባስን ስድብ በነጻ እየጠጣሁ ነው። 😂😂

ሻምበል በላይነህ የተባለ ቅ ሌ*ታ ም ትናንት ኢሳት ቲቪ ላይ የተናገረው።
😂😂🤣🤣

ይህ ሀቅ ተቀበል!!!ወዳጆቼ ታስታውሳላችሁ? ''ሙስሊም በመሆኔ የደረሰብኝ አንዳችም ጭቆና የለም'' በማለቴ (which was the fact) አንድ ሶስት ቀን በመደዳ ዋና ዋናዎቹም፤ ግልገሎቻ...
21/05/2023

ይህ ሀቅ ተቀበል!!!

ወዳጆቼ ታስታውሳላችሁ? ''ሙስሊም በመሆኔ የደረሰብኝ አንዳችም ጭቆና የለም'' በማለቴ (which was the fact) አንድ ሶስት ቀን በመደዳ ዋና ዋናዎቹም፤ ግልገሎቻቸውም የስድብ ውርጂብኝ ያዘነቡብኝን? ውርጂብኙ ሌላ ሳይሆን አማራ ሙስሊም በመሆኔ እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

''አማራን አንፈልግም'' ከሚል መነሻነት የሙስሊሞች መሪዎችን እና ዑለማዎችን ለ'ነርሱ በማይመጥን መንገድ ካስወገዱ በኋላ በአሳፋሪ ሁኔታ ደንበኛ የመንግሥት ፓራሳይትነታቸውን ሲያረጋግጡ ከርመዋል። ይቅርና 30 መስጊድ ፈርሶ ባሕር ዳር የሚገኘው የመጅሊስ ቢሮ አጥር ''ተነክቷል'' በሚል የተነሳውን አቧራ የምትዘነጉት አይደለም። የአማራ ጥላቻ አንድ ያደረጋችሁ የድ* *ማን ስብስብ ሁላ እናንተንም የማይምር ''የበላይ'' መጥቶባችሁ ማጣፊያው ሲያጥራችሁ ያሳየን ፈጣሪያችን ይመስገን።

ሞት፣ መፈናቀል፣ የእናቶች እንባ፣ የድሃ ቤት ፈረሳ፣ መሳጂዶችና አብያተ-ክርስቲያናት ፈረሳ ወዘተ. እያየ የሚቀመጥ የሕዝብ ተወካይ ማፈር አለበት። በበኩሌ በራሴ አፍራለሁ። ሰውን ቀና ብሎ ለማየትም ሆነ በማኅበራዊ ሚዲያ ብቅ ለማለትም አፍሬያለሁ። ምንም ለማድረግ ባለመቻሌም አፍራለሁ።

ለማንኛውም ኢትዮጵያዊነቴን ማንም አይወስድብኝም።
አማራ ነኝ!
ሙስሊም ነኝ!

ማአሰላማ!
Hawlet Ahmed

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Daily Informer posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share