Inside Afar

Inside Afar Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Inside Afar, Media/News Company, .

Afar Land Of Origin 🔴
22/12/2023

Afar Land Of Origin 🔴

የአፋር ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ትልቅ ዋጋ የከፈሉት መሪ፡- ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ*******************በአፋር ሱልጣኔት ታሪክ ከታላቁ መሪ ከሱልጣን አሊሚራህ አብራክ ከ...
14/09/2023

የአፋር ህዝብ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ትልቅ ዋጋ የከፈሉት መሪ፡- ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ
*******************
በአፋር ሱልጣኔት ታሪክ ከታላቁ መሪ ከሱልጣን አሊሚራህ አብራክ ከተገኙ ልጆች መካከል ስድስተኛው ልጅ ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ ናቸው፡፡ የቀድሞ የአፋር ሱልጣኔት መሪ ሱልጣን ሃንፍሬ አሊሚራህ ከዓመታት በፊት ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ ወንድማቸው ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ የሱልጣንነት ሹመታቸውን መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ.ም ተቀብለዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በ1944 ዓ.ም በሱልጣኔቶች መናገሻ በአሳይታ ወረዳ ልዩ ስሙ ሂናሌ በተባለ ቀበሌ ነበር የተወለዱት። እድሜያቸው ለቁርዓን ሲደርስ ሱልጣን አሊሚራህ ወዳስገነቧቸው መድረሳ ገቡ። ከመድረሳው ከ1ኛ እሰከ 4ኛ ክፍል የቀለም ትምህርት ቀስመዋል። ከአምስተኛ ክፍል እስከ ስምንተኛ ክፍል በአስመራ ከተማ ተከታተሉ፤ ቀሪውን ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ እና በግብፅ "ኢስማኤል ቃቢሲያ" በተባለ ትምህርት ቤት አጠናቀቁ።

በ1962 ዓ.ም ወደእንግሊዝ በማምራት ለአንድ ዓመት ተኩል የቋንቋ ትምህርት የተማሩት ሱልጣን አህመድ፤ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በመጓዝ ከ1963 እስከ 1967 ዓ.ም ከፍተኛ ትምህታቸውን ተከታትለዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ የደርግ መንግሥት በአፋር በገባበት ወቅት እና አባታቸው ሱልጣን አሊሚራህ በስደት ወደሳዑዲ አረቢያ ሲያቀኑ ከወንድማቸው ከሱልጣን ሐንፋሬ ጋር በመሆን ደርግን በመዋጋት ለ17 አመታት ህይወታቸውን ለአፋር ህዝብ ነፃነት ሲታገሉ ኖረዋል።

በተለይም ከ1967 እስከ 1973 ድረስ የአፋር ነፃ አውጪ ፓርቲን በማቋቋም በዞን አንድ፣ በዞን ሶስት፣ በዞን አራት በመንቀሳቀስ ከአፋምቦ ወረዳ ኦጋግና_ዓዳይቶ ላይ በትግል ምሽግ ውስጥ ለአምስት አመታት የፓርቲው የጦር ግንባር ዋና መሪ በመሆን ከደርግ ጋር እልህ አስጨራሽ ጦርነት አድርገዋል።

ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በርካታ የጦርነት ውሎዎችን ያካሄዱ ሲሆን አዳይቱ፣ ኡሙሌይታ፣ ኦጋግ፣ ኢድግሎ፣ ሃሪሳ፣ አሳይታ፣ አልገና፣ አፋምቦ፣ ዳትባህሪ፣ ክፊሉ፣ ጉርጉራ፣ ዓስማራ፣ ዳሊይ፣ ሃዶላ እና የመሳሰሉት ደርግን ላይ ድል በማድረግ በፓርቲው ቁጥጥር ሥር ለማድረግ የቻሉባቸው አካባቢዎች ነበሩ።

ሱልጣኑ የደርግ ሥርዓትን ለመገርሰስ እስከተቻለበት ድረስ በሳዑዲ የአፋር ነፃ አውጭ የውጭ ግኑኝነት አመራር በመሆን ለትግሉ ድጋፍ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በመገናኘት ስኬታማ የወዳጅነት ድጋፍ የሚገኝበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሰርተዋል።

ሱልጣን አሕመድ ከተለያዩ ሀገራት ጋር መልካም ግንኙት እንዲፈጠር የሰሩ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲ፣ ፈረንሣይ፣ ጣለያን፣ ባህሬን፣ ኢራቅ፣ አሜሪካ፣ ቤልጅየም፣ ሆላንድ፣ ሊቢያ፣ ኬኒያ፣ ኢንግሊዝ፣ ሞሮኮ፣ ታንዛኒያ እና ኩዌት ተጠቃሽ ሀገራት መሆናቸውን በ2008 ዓ.ም ለ"አፋር ህዝብ ትግል" መፅሐፍ ደራሲ በሰጡት ሃሳብ ተናግረዋል።

ሱልጣን አህመድ አሁን ያለው የፌዴራሊዝም ሥርዓት እንዲመጣና የአፋር ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ እንዲመለስለት ዱር ቤቴ ብለው የወጡት ገና በ23 ዓመታቸው ሲሆን፣ ጦር መርተው የትግሉን ፍሬ ለማየት ከቻሉ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው።

በ1983 በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ሲቋቋም የአፋር ነፃ አውጪን በመወከል የምክር ቤቱ ተሳታፊ የነበሩት ሱልጣን አህመድ፤ ድሉ ከተገኘ በኋላ ፊታቸው ወደግል ሥራ በማዞር በንባብና ጥናት ላይ አተኩረዋል። ሱልጣን አሕመድ አሊሚራህ በሃይማኖትም በሳይንሱም ትልቅ ዕውቀት አሏቸው ከሚባሉ የአፋር ምሁራን መካከል አንዱ ናቸው።

ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ ከአርባ ዓመት በላይ የትዳር አጋራቸው ከሆኑት አሜሪካዊት እንስት 9 ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፤ በአውሳ ሱልጣኔቶች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ ዜጋ ጋር ትዳር የመሰረቱም ብቸኛው መሪ ናቸው፡፡

Ebc

''አፋር የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን የቆላ ስንዴ ዘር መገኛም ጭምር ነው'''የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ሃጂ አወል አርባ
25/02/2023

''አፋር የሰው ዘር ብቻ ሳይሆን የቆላ ስንዴ ዘር መገኛም ጭምር ነው'''

የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ሃጂ አወል አርባ

በሰራሀው ስራ ሽልማቱ ይገበሃል..!!!የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በግጭቱ ምክንያት የወደሙ የጤና ተቋማት በአጭር ጊዜና በፍጥነት ወደ ስራ እንዲመለስ በ...
31/12/2022

በሰራሀው ስራ ሽልማቱ ይገበሃል..!!!

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ በግጭቱ ምክንያት የወደሙ የጤና ተቋማት በአጭር ጊዜና በፍጥነት ወደ ስራ እንዲመለስ በማድረ በክልሉ መሰረታዊ የሆኑ የጤና ስራዎችን ላይ እንዲሁ የጤና መድንን ተደራሽ በማድረግ ባሳዩት አኩሪ ስራ ከምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ደመቀ መኮነን እጅ ሽልማት ተበርክቶለታል።

Natnael Mekonnen

18/09/2022

ምርጥ መረጃ

From The Land of Origins Ethiopia 🇪🇹Afars The Proud Peoples of East Africa. Afar warrior in Danakil desert.The Afar, als...
08/09/2022

From The Land of Origins Ethiopia 🇪🇹
Afars The Proud Peoples of East Africa. Afar warrior in Danakil desert.

The Afar, also known as the Danakil, Adali and Odali, are a Cush*tic-speaking ethnic group inhabiting the Horn of Africa. They primarily live in the Afar Region of Ethiopia 🇪🇹 and in northern Djibouti 🇩🇯 as well as the entire southern coast of Eritrea 🇪🇷

Inside Afar

አንጋፋው የታሪክ ጸሀፊ ዶክተር ሀሺም ጀማሉዲን ሻሚ ወደ አኼራ ሄዱ።አንጋፋው የታሪክ ፀሃፊና በአፋር ፀሃፊያን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 700 ገፅ በላይ የያዘ የአፋር ታሪክን የሚያትት መፅሃፍ ...
01/08/2022

አንጋፋው የታሪክ ጸሀፊ ዶክተር ሀሺም ጀማሉዲን ሻሚ ወደ አኼራ ሄዱ።

አንጋፋው የታሪክ ፀሃፊና በአፋር ፀሃፊያን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 700 ገፅ በላይ የያዘ የአፋር ታሪክን የሚያትት መፅሃፍ ከወላጅ አባቱ ጋር በመሆን ለንባብ ያበቃው የታሪክ ሰው ዶ/ር ሀሺም ጀማሉዲን ዛሬ በሀገረ ቱርክ ወደ አኼራ ተሸጋግሯል። .
ዶክተር ሀሺም ለአፋር ታሪክ መሠረቱን የጣለ፣ የአሁኑ ትውልድ ለቀጣይ ለሚያደርጋቸው ለታሪካዊ ጥናቶች ግብዓትና መነሻ ሊሆን የሚችል 11 ምዕራፍ ያቀፈ መፅሃፍን ለአፋር አበርክቷል። መፅሃፉ በአማረኛና እንግሊዝኛም ተተርጉሟል። ዶክተር ሀሺም በፃፈው ታሪክ ሁለት የተለያዩ ትውልድን በመስተሳሰሩና ታሪክ ለትውልድ እንዲተላለፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ በማበርከቱ በአፋር ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው አንጋፋ የታሪክ ሊቅ ነበሩ። አሏህ ማረፊያው ጀነተል ፍርደውስ ያድርግለት።

ይህ በአሜሪካ የሚገኝ The mother mosque of America{እናት መስጂድ} የሚል ስያሜ የተሰጠው በአሜሪካ ውስጥ  ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባ መስጂድ ነው!በU.S አሜሪካ cedar አይ...
28/07/2022

ይህ በአሜሪካ የሚገኝ The mother mosque of America
{እናት መስጂድ} የሚል ስያሜ የተሰጠው በአሜሪካ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባ መስጂድ ነው!

በU.S አሜሪካ cedar አይዋ ውስጥ በ1934 ተገንብቶ እስከ ዛሬ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ❤
ስለ ኢስላም

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ሀጂ አወል አርባ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጀግኖቻችን አትሌቶች ድል የምስጋና ፕሮግራም አካሄዷል!
28/07/2022

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት ሀጂ አወል አርባ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በጀግኖቻችን አትሌቶች ድል የምስጋና ፕሮግራም አካሄዷል!

ሰበር ዜና✊💪በአፋርና በተባበሩት ሶማሌ ሃይሎች መካከል ለ2 ቀናት በተደረገው ውጊያ ወራሪዎች ፈርጥጠው ወደ ሶማሌ ክልል ገብተዋል።የአፋር ጀግኖች ጀግንነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።💪💪✊✊In...
28/07/2022

ሰበር ዜና✊💪

በአፋርና በተባበሩት ሶማሌ ሃይሎች መካከል ለ2 ቀናት በተደረገው ውጊያ ወራሪዎች ፈርጥጠው ወደ ሶማሌ ክልል ገብተዋል።የአፋር ጀግኖች ጀግንነታቸውን በተግባር አሳይተዋል።💪💪✊✊

Inside Afar

❤❤❤❤
20/06/2022

❤❤❤❤

Afar Cultural Hair Style (Ayri/Rasta)❤❤❤❤
20/06/2022

Afar Cultural Hair Style (Ayri/Rasta)❤❤❤❤

ቅድምያ ለሀገርና ለህዝብ ነው..!!!ይህ በቀይ የተሰመረበት ሰው ሃጂ ኢብራሂም ኡስማን ይባላል የአፋር ክልል አርብቶአደር ቢሮ ሃላፊ ሲሆኑ በወራሪው ሃይል ላይ የእግር እሳት የሆነ አመራርም ...
13/04/2022

ቅድምያ ለሀገርና ለህዝብ ነው..!!!

ይህ በቀይ የተሰመረበት ሰው ሃጂ ኢብራሂም ኡስማን ይባላል የአፋር ክልል አርብቶአደር ቢሮ ሃላፊ ሲሆኑ በወራሪው ሃይል ላይ የእግር እሳት የሆነ አመራርም አዋጊም ጭምር ነው። የአፋር ህዝብ ያፈናቀለ ጠላት እያለ በፓራዶ መኪና እና የቅንጦት ንሮ አልፈልግም በማለት ለወራት ደረቅ ብስኩትና ሙቅ ውሃ እየጠጣ ጠላትን እንቅልፍ ያሳጣ ጀግና ነው። በርግጥ እስካሁን የአፋር ክልል አመራሮች 75% የህዝባቸውን ደህንነት ለመጠበቅ በሁሉም ግባር ውጊያውን አስተባብረዋል አሁንም እያስተባበሩ ይገኛሉ።

Afar
11/04/2022

Afar

መልካም ዜና!!!ባለፉት ወራት ወራሪው ጁንታ በአፋር ጭፍራ ግምባር በመግባት የሚሌን ጥቁር መስመር ዘግተን ኢትዮጵያን እናንበረክካለን ባሉበት ጊዜ በጭፍራ ግምባር ኮማንድ ፖስት አዛዥ በመሆን ...
05/04/2022

መልካም ዜና!!!

ባለፉት ወራት ወራሪው ጁንታ በአፋር ጭፍራ ግምባር በመግባት የሚሌን ጥቁር መስመር ዘግተን ኢትዮጵያን እናንበረክካለን ባሉበት ጊዜ በጭፍራ ግምባር ኮማንድ ፖስት አዛዥ በመሆን የጠላትን ህልም ያከሸፈው ጀግናው አብዱ ሙሳ የአፋር ክልል ሰመራ ሎግያ ከተማ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል። በተሰጠው ሃላፊነት አሁን የጠላትን ኔትዎርክ በመቆራረጥ በጠላት ላይ ያሳዩትን ድል አሁን በልማቱ እንደሚያስቀጥል ተስፋ አለን።መልካም የስራ ዘመን ይሁንሎት።

ሰበር የድል ዜና!!!የአርሚ-5 ምሽጎች ተሰብረዋል ሃይሉም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተበታትኗል!!!!በበራህሌ ግምባር ወራሪው ሃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል በዚህ ግምባር የተቆጣው የአፋ...
25/01/2022

ሰበር የድል ዜና!!!

የአርሚ-5 ምሽጎች ተሰብረዋል ሃይሉም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተበታትኗል!!!!

በበራህሌ ግምባር ወራሪው ሃይል ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበታል በዚህ ግምባር የተቆጣው የአፋር ህዝባዊ ሰራዊት በቁጭትና በንዴት ጠላት መሽጎባቸው የነበረውን አከባቢዎች በጨበጣ ሳይቀር እልህ አስጨራሽ ውጊያ በማድረግ የግልና የቡድን መሳሪያዎችን ማርኳል።

በአሸባሪው ምግበይ የሚመራው ይህ ሃይል የጁንታው መሪዎች የሚተማመንበት አርሚ-5 ሲሆን ይህ ሃይል ግን በደረሰበት መብረቃዊ ጥቃት ግማሹ እንዲበተን ግማሹ እጅ እንዲሰጥ ተደርጓል። የአፋር ሰራዊት የበራህሌ ሰንሰለታማ ተራሮችን በደምብ በማወቁና በተቃራኒው የጠላት ሃይል አከባቢውን በደምብ አለመወቁ የአፋር አናብስቶች ወሳኝ ቦታዎችን ከጠላት እንዲረከብ ረድቶታል።

በአብኣላ እና በመጋሌ ግምባር እስካሁን ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል በነዚህ ግምባሮች ጠላት አከባቢውን ባለማወቁ የአፋር ህዝባዊ ሃይል እየቆራረጠ እየመታው ይገኛል። ኢንሻአላህ በቅርቡ ወራሪውን ሙሉ ለሙሉ አፅድተን የአፋርን ህዝብ ሰላም እናስጠብቃለን። Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ድል ለኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹
🇪🇹🇪🇹 ድል ለአፋር ህዝባዊ ሃይል🇪🇹🇪🇹

Afar People Force 24hrs Redy
13/01/2022

Afar People Force 24hrs Redy

አፋር ለኢትዮጵያ ሀገሩ!!!
07/12/2021

አፋር ለኢትዮጵያ ሀገሩ!!!

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪቃዊ መሪን በዋሽንግተን ነጩ ቤተመንግሥት ተቀብለው ሊነጋገሩ ነው!!የአፍሪካ ፖሊካና ዲፕሎማሲ ከእጁ በመውጣቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ...
13/10/2021

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለመጀመሪያ ጊዜ አፍሪቃዊ መሪን በዋሽንግተን ነጩ ቤተመንግሥት ተቀብለው ሊነጋገሩ ነው!!

የአፍሪካ ፖሊካና ዲፕሎማሲ ከእጁ በመውጣቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ባይደን በነገው ዕለት ከኬንያው ፕሬዝደንት ዑሁሩ ኬንያታ ጋር በነጩ ቤተመንግሥት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

ባይደን ከኬንያው መሪ ጋር የሚነጋገሩት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ጦርነት የሚሳተፉ ወገኖች ላይ ሀገራቸው የምትጥለውን ማዕቀብ እየመዘኑ እንደሆነም ተገልጿል። ኬንያ በያዝነው የጥቅምት ወር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤትን የፕሬዝደንትነት መንበር ይዛለች።

ኢትዮጵያን በፍቅር እንጂ በፉከራ በማስፈራራት ማንበርከክ እንደማይቻል አስረግጠናል

🇪🇹🇪🇹 እናመሰግናለን 🇪🇹🇪🇹ወጣቱና በቅርቡ የሰመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በሆኑት በዶ/ር መሐመድ ኡስማን አስተባባሪነት ጁንታው በአፋር ክልል በደረገው ወረራና ጦርነት ምክነያት ከቤት ንብረታ...
03/09/2021

🇪🇹🇪🇹 እናመሰግናለን 🇪🇹🇪🇹

ወጣቱና በቅርቡ የሰመራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት በሆኑት በዶ/ር መሐመድ ኡስማን አስተባባሪነት ጁንታው በአፋር ክልል በደረገው ወረራና ጦርነት ምክነያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል። ዩኒቨርስቲዎቹ ለአፋር ህዝብና መንግስት ያላቸውን ድጋፍና አብሮነትን አሳይተዋል የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተማረ ሃይል ከማምረት በተጨማሪ መደጋገፍን መተባበርን እንዲሁም ኢትዮጽያዊነት ለመጪው ትውልድ የሚያስተምር አኩሪ ስራ እየሰሩ ነው በአፋር ህዝብ ስም እናመሰግናለን🙏🙏

ዩኒቨርሲቲዎቹ ያደረጉት የገንዘብ ድጋፍ ዝርዝር
1. Bonga University :- 750,000
2. Wachamo University:- 2,000,000
3. Haramaya University:- 1,600,000
4. Bule Hora University:- 1,750,200
5. Wolega University:- 2,000,000
Total:- 8,100,200 birr

🇪🇹🇪🇹 ስንተባበር እናሸንፋለን 🇪🇹🇪🇹

በአፋር ጀግኖች የተማረከው የሶማሌ ክልል ልዩሃይል ኮማንደር!!
26/08/2021

በአፋር ጀግኖች የተማረከው የሶማሌ ክልል ልዩሃይል ኮማንደር!!

Afar Beauty ❤❤❤
24/08/2021

Afar Beauty ❤❤❤

😭😭የጋሊኮማ ጁንታው ያደረሰብን ጥቁር ታሪክ ከትውልድ ትውልድ እናስተላልፋለን።እናት ልጆቿን ለማዳን ለጥይት ጀርባ ሰጥታለች።እናታቸው በጥይት ተደብድባ የሞተችውን እናቱን ጡት ሲጠባ ታላቅ እህ...
11/08/2021

😭😭

የጋሊኮማ ጁንታው ያደረሰብን ጥቁር ታሪክ ከትውልድ ትውልድ እናስተላልፋለን።

እናት ልጆቿን ለማዳን ለጥይት ጀርባ ሰጥታለች።

እናታቸው በጥይት ተደብድባ የሞተችውን እናቱን ጡት ሲጠባ ታላቅ እህት ስታለቅስ ስትሯሯጥ ከማየት በላይ ምን አሰቃቂ ክስተት አለ።

ሙሉ ቤተሰባቸው ተረሽነው ወደ ጫካ የገቡት ህፃናት በጅብ ተበልተዋል የሚል ዜና ከመስማት በላይ ልብ የሚሰብር ዜና የት አለ።

በጋሊኮማ ጁንታው በአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው ግፍ ለታሪክ ይፅፋል።

06/08/2021

የአፋር እና የአማራ ህዝብ ኢትዮጵያን ለመታደግ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል🇪🇹🇪🇹

  💚💛❤️
27/07/2021

💚💛❤️

ሰበር ዜና!!!የጠረፍ ተከላካዮች የበርሃ አናብስቶች አፋሮች ከላይ እስከ ታች ተነቃንቋል።በቅርቡ የክልላችን ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል ባቀረቡት የሀገር አድን ጥሪ ተከትሎ ከሁሉም የክልሉ አከባቢዎ...
24/07/2021

ሰበር ዜና!!!

የጠረፍ ተከላካዮች የበርሃ አናብስቶች አፋሮች ከላይ እስከ ታች ተነቃንቋል።

በቅርቡ የክልላችን ፕሬዚዳንት ሃጂ አወል ባቀረቡት የሀገር አድን ጥሪ ተከትሎ ከሁሉም የክልሉ አከባቢዎች ብዛታቸው ከ70,000 በላይ የሆነ መዋጋት የሚችሉ የአፋር ወጣቶች ጥሪውን ተቀብለው በእልህ በንዴት እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትደፈርም የአፋር ህዝብ ክብር አይደፈርም እያለ እንደጎርፍ ትግሉን እየተቀላቀለ ነው።

በመቀጠልም ከጥሪው ማግስት ለመከላከያ ሰራዊት እንዲሁም ለሚኒሻ ስልጠና ከ50,000 በላይ ወጣቶች ተመዝግቧል።

የትግራይ ህዝብ ፤ ኣካላችን ኣሸባሪው ጁንታ ፤ ጠላታችንCredit: Geez Media- የፌደራል መንግስት ከትግራይ ለሚፈናቀሉ ሰዎች በዓፋር፣ቆቦ እና ጎንደር መጠልዎች ሰራ (pictured)።...
23/07/2021

የትግራይ ህዝብ ፤ ኣካላችን
ኣሸባሪው ጁንታ ፤ ጠላታችን

Credit: Geez Media

- የፌደራል መንግስት ከትግራይ ለሚፈናቀሉ ሰዎች በዓፋር፣ቆቦ እና ጎንደር መጠልዎች ሰራ (pictured)።

- የትግራይ ህዝብ ወደ አጎራባች ክልሎች እየተፈናቀለ ነው።

- ከተሰደዱት ውስጥ እናቶች እና ህፃናት ይበዛሉ።

- ጁንታው የስልጣን ኮረቻው ለማመቻቸት ብሎ የትግራይ ህዝብ ወደ መከራ አስገብቶታል።

- ህዝቡ እንዳይራብ ተብሎ እየሄደ ያለው እርዳታም ለተቸገረው ህዝብ እየደረሰ አይደለም።

- እርዳታው ጁንታው በቀጥታ ወደ ራሱ ታጣቂዎች እንደሚወስደው ምንጮች አረጋግጠዋል።

ሱዳን የምዕራብ አፍሪካን ሙሉ ድጋፍ አገኘሁ አለች!!!የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር-የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ድጋፍ አገኝቻለሁ አለች!! ሚኒስትሯ ማሪያም ሳዲቅ አል-...
02/06/2021

ሱዳን የምዕራብ አፍሪካን ሙሉ ድጋፍ አገኘሁ አለች!!!

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር-የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከምዕራብ አፍሪካ አገራት ድጋፍ አገኝቻለሁ አለች!!

ሚኒስትሯ ማሪያም ሳዲቅ አል-መህዲ ናይጄሪያ ፣ ጋና ፣ ሴኔጋል እና ኒጀርን ያከተተ የምዕራብ አፍሪካ አገራት ጉብኝታቸውን ጨርሰው ዛሬ ማምሻውን ከተመለሰች በኋላ ለሱዳን የዜና አገልግሎት (Suna) በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልፀዋል።

ግብፅ ታማኝ ተልዕኮ አስፈፃሚ ያገኘች ይመስላል።

የኛ ዲፕሎማት አሁንም እንደተኙ ነው ይገርማል።

Ahmed Habib Alzarkawi

ሚስጥራዊ መረጃዎች!!!!ከወር በፊት የግብፅና የሱዳን ጀነራሎች ከጂቡቲ መንግስት ጋር ያደረጉት ሚስጥራዊ ውይይት እና ሌሎች ያልተሰሙ ነጥቦች በቀደም ተከተል አስቀምጫለሁ!!!April 28-ጀነ...
28/05/2021

ሚስጥራዊ መረጃዎች!!!!

ከወር በፊት የግብፅና የሱዳን ጀነራሎች ከጂቡቲ መንግስት ጋር ያደረጉት ሚስጥራዊ ውይይት እና ሌሎች ያልተሰሙ ነጥቦች በቀደም ተከተል አስቀምጫለሁ!!!

April 28-ጀነራል መሐመድ ዛኪ የግብፅ መከላከያ ሚኒስትር እና ሁለት የሱዳን ጀነራሎች እና አንድ ኮሌኔል) በጂቡቲ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ከሌሊቱ 10:00 ሰአት በጅቡቲ ፕሬዝደንት አቀባበል ተደርጎላቸው በቤተመንግስት ከፕሬዝደንቱ ጋር የሶስትዮሽ ውይይት አካሄደዋል።

April 29-ጀነራሎቹ ከጂቡቲ የጦር ሃይሎች ጠ/ኢታማጆር ዘከሪያ ሼክ ኢብራሂም እንዲሁም ከኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ሚስጥራዊ ስብሰባ አድርገዋል።

May 13 ከ3,000 በላይ ግብፃውያን ማለት 2,000 የግብፅ ሰራዊትና 1000 ሲቪል ማለት ለግምባታ የሚያስፈልጉ ሰዎችን እንዲሁም የግምባታ ቁሳቁስ የጫነች የግብፅ መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደርሳለች።

May 26 ከዚህ በኋላ ነበር አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በትናንትናው እለት ወደ ጂቡቲ በመምራት ከኢስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር ከዚህ ቀደም በሚስጥር የግብፅ ሱዳንና የጂቡቲ ጀነራሎች የተወያዩበትን ሰነድ ስምምነት ይፋዊ ውይይት ያደረጉት።

የግብፅ መንግስት በጂቡቲ ባህር ሃይል ከመጠናከር በተጨማሪ ግዙፍ የአየርሃይል ማረፍያ ለመስራትም ጭምር ተስማምተዋል።

ግብፅ በቀጠናው ከአባይ ግድብ በተጨማሪ በባህረስላጤው ተፅዕኖ ለማሰደር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገች ነው።
ምንጭ፦Ahmed Habib Alzarkawi

Afar cultural dance ❤❤
19/05/2021

Afar cultural dance ❤❤

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Inside Afar posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share