Amhara Daily News

  • Home
  • Amhara Daily News

Amhara Daily News Amhara Daily News የእናንተው ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ ናት Like Share Invite

11/12/2022
09/12/2022

ሰበር ዜና
ከ20 በላይ ቁልፍ የሸኔ አመራሮች እርምጃ ተወስዶባቸዋል

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ሆሮጉድሩ ወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋና ሰሜን ሸዋ ዞኖች ይንቀሳቀሱ በነበሩ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት ላይ በተከናወነው ተከታታይ ኦፕሬሽን ከ20 በላይ ቁልፍ አመራሮች መገደላቸው ታውቋል፡፡

የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሰሞኑን በተከታታይ ያከናወኑትን ኦፕሬሽን በተመለከተ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት፤ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ የሸኔ አባላት ላይ በተጠና መንገድ በተወሰዱ እርምጃዎች የሽብር ቡድን ዋና አዛዥ ኩምሳ ድሪባ ወይንም መሮ በመባል ከሚታወቀው ግለሰብ ጋር በቅርበት የሚንቀሳቀሱ አምስት ቁልፍ የሽብር ቡድኑ መሪዎችን ጨምሮ በተለያዩ ዞኖች ታጣቂ ቡድኑን የሚያስተባብሩ ከ20 በላይ አመራሮች ተገድለዋል፡፡

የመሮ የቅርብ ሰዎች የነበሩት መንጫስ፣ ሚካኤል ተርፋ ወይም ገዳ፣ ወንዴ፣ ጉቱና ገሜ የተባሉ አመራሮች በተወሰደው እርምጃ መገደላቸውን የሚያመለክቱት የመረጃ ምንጮች፤ ይህንን ተከትሎ በቅርቡ በተቃጣበት ጥቃት የመቁሰል አደጋ ደርሶበት የነበረው ዋና አዛዡ መሮ ከሕመሙ ሳያገግም በቄለም ወለጋ ዞን ወደ አሳቻ ስፍራ በመሸሽ ለመደበቅ ሙከራ ማድረጉን ጠቁመዋል፡፡

በሸኔ ቁልፍ አመራሮች ላይ የተወሰደው እርምጃ በቡድኑ የኃይል አዛዦችና ታጣቂዎች ዘንድ ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥና የስነልቦና ቀውስ እንዳሳደረም እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ የተለያዩ መረጃዎች ተገኝተዋል፡፡

ቡድኑ እየደረሰበት ባለው ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራዎች በእውር ድንብር ንፁሐንን ለማጥቃት መሞከሩ አንዱ ማሳያ ነው፤ ይሁንና የመንግሥት የጸጥታ አካላት እግር በእግር እየተከተሉ በወሰዱት የተቀናጀ እርምጃ ሸኔ መፈናፈኛ ማጣቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡ ወደ ሽሽት የገቡት ታጣቂዎች በኅብረተሰቡ ላይ ዘረፋና ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለመፈጸም ያደረጉት ጥረትም የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በጋራ ባከናወኑት ስምሪት ከሽፏል፡፡

የሸኔ አመራሮችን መገደል ተከትሎ የቡድኑ አንዳንድ አዋጊዎች ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመሸሽ ቢያስቡም በጎረቤት ሀገራት ተሸሽገው የሚገኙ የሸኔ ሴል አባላት ታድነው እንዲያዙና ለመንግሥት ተላልፈው እንዲሰጡ ከስምምነት በመደረሱና በከበባ ውስጥ በመግባታቸው ሥጋት ውስጥ መውደቃቸው ታውቋል፡፡

አመራሮቹና ታጣቂዎቹ በቀጣይ የትግል ስልታችን ዙሪያ ምክክር ማድረግ ያስፈልጋል ውጊያውን እናቁም ወይም እጅ እንስጥ የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን፤ ይህን ተከትሎም መጠራጠር፣ ክፍፍል፣ አለመተማመንም በከፍተኛ ደረጃ መፈጠሩንና አለመግባባቱም መሣሪያ እስከ መማዘዝ ወዳደረስ ግጭት ማምራቱ እየተገለጸ ይገኛል፡፡

በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማት ላይ ዝርፊያና ውድመት እያደረሰ የሚገኘው እንዲሁም ንፁሐንን በማገት ዘረፋና ግድያ እየፈፀመ ያለው የሸኔ የሽብር ቡድን እንዲከሰም በፌደራል እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ አካላት ተከታታይና የተቀናጀ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡ መላው የኦሮሚያ ሕዝብም የቡድኑን አረመኔያዊና ኢሰብአዊ ድርጊቶች በማጋለጥና ጥቆማ በመስጠት ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጎን መቆሙ ታውቋል፡፡

31/10/2022

‹‹ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው›› - ዕብሪት ሲወጥራቸው
‹‹ሽምግልናߴኮ ባህላዊ እሴታችን ነው፤ ኧረ አስታርቁን›› - መከላከያ ሲደቁሳቸው

የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አመራሮች ጉዳይ ግራ አጋቢ ሆኗል፡፡ ለቀቅ ሲያደርጓቸው ፉከራና ቀረርቷቸው አይጣል ነው፡፡ ኒውክሌር የታጠቁ፣ ከምሥራቅ አፍሪካ አልፈው በመላው ዓለም የኃይል ሚዛን አስጠባቂ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ የመንደር ሽፍታ ቡድንነታቸውን ዘንግተው የዓለም ልዕለ ኃያል ሀገር እንደሆኑ ይሰማቸዋል፡፡ ለያዝ ለገናዥ በማስቸገር ልክ በሌለው ዕብሪት ተወጥረው እንደ ሰፈር ጎረምሳ . . . በበረት ውስጥ እንደገባ በጥባጭ ኮርማ ያደርጋቸዋል ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሀይል ‹‹ትዕግስትም ልክ አለው!›› በማለት ወደ ህወሓት መንደር የገሰገሰ እንደሁ እነርሱን አያድርጋችሁ፡፡ ከፍርጠጣቸው እኩል ምንዳ የሚሰፈርላቸው የውጭ ዜጎችና የቡድኑ ደጋፊዎችን ያካተተው የፕሮፓጋንዳ ክንፋቸው ለቅሶና የለየለት ቅጥፈት የማኅበራዊ ሚድያውን ሜዳ ይቆጣጠረዋል፡፡ በዕብሪት ተነሳስተው ወረራ ሲፈጽሙ እራሳቸውን እንደ ጀግና ሲያወድሱ የነበሩት በሙሉ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያለጥርጣሬ የሚገዛውንና አንጀቱን የሚበላውን የጄኖሳይድ ተፈጸመብን አጀንዳ ይከፍታሉ፡፡ ንፁሐን ተገደሉ ከተሞች ወደሙ ይላሉ፡፡ ሰሞኑን‹‹የመከላከያ ኃይሎች ከተማውን በእሳት አቃጥሉ ብለዋል›› በሚል የሠሯት ግን ብዙም ያልተሸጠች ድራማ ለህወሓት የፕሮፓጋን ክንፍ ቅጥፈት ጥሩ ማሳያ ትሆናለች፡፡

ጭምቡሉን ያለ ሀፍረት አውልቆ የህወሓትን የበሬ ወለደ ቅጠፈት ማስተጋባት የጀመረው አብርሃ ደስታም ‹‹አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ እንደሚባለው›› ሰሞኑን አዲስ ፈራሚ በመሆን የሚረጨው የሐሰት መርዝ አስገራሚ ሆኗል፡፡ አብርሃ መከላከያ በራያ አካባቢ ንፁሐንን ገድሏል በሚል ያሰራጨው የበሬ ወለደ ወሬ ህወሓት የራያን ሕዝብ በብረት መዳፍ ቀጥቅጬ ካልገዛሁ በማለት ያደረሰውን ግፍ ለማስረሳት የተሰነዘረች የፈጠራ ክስ መሆና ነው ።

አሁን አሁን ነገሮች እየተቋጩ መሆናቸውን የሚያመላክቱ ፍንጮች ይታያሉ፡፡ የአሸባሪ ቡድኑ መታደራዊ አመራር ታደሰ ወረደ ጥይት የሳተው ታጣቂ መስሎ በድንጋጤ ገርጥቶ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ሽሬ፣ አድዋ፣ አክሱምና ሌሎችም በርካታ ስፍራዎች በጥምር ጦሩ መያዛቸውን አምኗል፡፡ ከወደ ደቡብ አፍሪካ የሚመጡ መረጃች እንደሚጠቁሙት በዕብሪት ተወጥረው ‹‹ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው ፤ ጦርነቱ አልቋል ከማን ጋር ነው የምንደራደረው›› በማለት ሲፎክሩ የነበሩትም፤ ‹‹ሽምግልናߴኮ ባህላዊ እሴታችን ነው፤ ኧረ አስታርቁን›› በማለት የሰላም ውይይቱ ቀን ተራዝሞላቸዋል፡፡ ሆኖም የሰላም ውይይቱ ጊዜ ቢራዘምም የዕብሪተኞች ቀን ግን ማጠሩ አይቀርም።

የመጨረሻውን ጊዜ መደረሱን የሽብር ቡድኑ አመነሰሞኑን የጥምር ጦሩ በሁሉም አቅጣጫ በከፍተኛ ወኔ ወደ መቐለ መገስገሱን ተከትሎ ትግራይ ነጻ እንደሚሆነ በማመናቸው ምክኒያት የህዝቡን ከየፌደራል...
28/10/2022

የመጨረሻውን ጊዜ መደረሱን የሽብር ቡድኑ አመነ

ሰሞኑን የጥምር ጦሩ በሁሉም አቅጣጫ በከፍተኛ ወኔ ወደ መቐለ መገስገሱን ተከትሎ ትግራይ ነጻ እንደሚሆነ በማመናቸው ምክኒያት የህዝቡን ከየፌደራል መንግስቱን የሚቃቅሩ የሃሰት መረጃዎች ባላቸው እዝ ሰንሰለት ተጠቀመው ቤት ለቤትና በየሃይማት ተቋማቱ እያሰራጩ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በማህበራዊ ሚዲያም ለማሰራጨት ካሰቧቸው አጀንዳዎች መካከል የትግራይ አሰተዳደር በምሰልኔ ሰለሚመራ እንዳተቀበሉት በማለት አይቀሬ ሽንፈቱን ህዝቡ እንዲከላከልለት በማሰተጋባት ላይይገኛል፡፡
የትግራይ ህዝብ ሆይ የዚህ ሴራ ሰለባ እንዳትሆን!

ኢትዮጵም ትግራይም ታሸንፋለች

የመጨረሻው ሰዓት ሲደርስ ስንዴው ከእንክርዳዱ እየለየ ነው።
17/10/2022

የመጨረሻው ሰዓት ሲደርስ ስንዴው ከእንክርዳዱ እየለየ ነው።

ጀርመን ጨምሮ ከ14 በላይ የአውሮፓ ሀገራት ከሚሳኤል ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ህብረት ፈጠሩሀገራቱ ገንዘብ በጋራ በማዋጣት የአየር ጥቃትን የሚከላከል የጦር መሳሪያ ለመግዛትም ተስማምተዋልጀ...
14/10/2022

ጀርመን ጨምሮ ከ14 በላይ የአውሮፓ ሀገራት ከሚሳኤል ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ህብረት ፈጠሩ
ሀገራቱ ገንዘብ በጋራ በማዋጣት የአየር ጥቃትን የሚከላከል የጦር መሳሪያ ለመግዛትም ተስማምተዋል
ጀርመን ጨምሮ ከ14 በላይ የአውሮፓ ሀገራት ከሚሳኤል ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ህብረት ፈጠሩ።
ስምንት ወራት ሊሞላው ጥቂት ቀናት የቀሩት የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት በየጊዜው አዳዲስ ክስተቶች ማስተናገዱን ቀጥሏል።
ሩሲያ የዩክሬንን ጦርነት ካሸነፈች አውሮፓ ስጋት ውስጥ እንደሚወድቅ ኔቶ ገለጸ
የዓለም ምግብ እና ነዳጅ ዋጋ መናር፣ አራት የዩክሬን ግዛቶች በህዝበ ውሳኔ ወደ ሩሲያ መጠቃለል፣ አዲስ የዲፕሎማሲ ህብረት እና ሌሎችም ክስተቶች ከጦርነቱ ውጤቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ባሳለፍነው ቅዳሜ ክሪሚያን ከሌሎች የሩሲያ ግዛቶች ጋር የሚያስተሳስረው ድልድይ በዩክሬን አደጋ ደርሶበታል ያለችው ሩሲያ በዩክሬን ከተሞችን ላይ የሚሳኤል ጥቃት በመሰንዘር ላይ ትገኛለች።
የሩሲያን አዲስ ጥቃት ተከትሎም ከ14 በላይ ሀገራት ከተሞቻቸውን በጋራ ከሚሳኤል ጥቃት ለሙከላከል አዲስ ህብረት መፍጠራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ጀርመን፣ ቤልጂየም፣ ብሪታንያ፣ ቡልጋሪያ፣ ኖርዌይ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ኢስቶኒያ፣ ሆላንድ፣ ስሎቫኪያ፣ ሮማንያ፣ እና ፊንላንድ ህብረቱን ከፈጠሩ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።
ይሄንን ህብረት ጀርመን እንደምትመራው የተገለጸ ሲሆን፤ ወጪን በቀነሰ መንገድ ባጋራ የአየር ላይ ጥቃቶችን ሊያስቆም የሚችሉ የጦር መሳሪያዎችን በሙግዛት በአውሮፓ ከተሞች ላይ ሊፈጠር የሚችልን ጥቃት ለመመከት ያለመ ነው ተብሏል።
ዩክሬን ኔቶን የምትቀላቀል ከሆነ 3ኛው የዓለም ጦርነት ይነሳል ሲሉ የሩሲያ ባለስልጣን አስጠነቀቁ
ሀገራቱ ከተሞቻቸውን ከሚሳኤል ጥቃት ለመጠበቅም ጀርመን እና እስራኤል ሰራሽ የአየር ጥቃት ማምከኛ የጦር መሳሪያዎችን ጥቅም ላይ እንደሚያውሉም ተገልጿል።
አዲስ ህብረት የፈጠሩት እነዚህ ሀገራት አብዛኞቹ የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶ አባል ሀገራት ሲሆኑ አዲሱ ጥምረት ከዚህ በተጨማሪ እና በተናበበ መንገድ ይሆናልም ተብሏል።

14/10/2022

በመጨረሻም እውነት ተገለጠች፤ ሕወሐትም ወደ ጥንት ግብሯ ተመለሰች!

የወያኔ ጀሌ ላይ የሚሰነዘርበት ምት ከምንጊዜውም በላይ አሁን በርትቷል። ከውጭ ላኪዎቻቸው የሚሰማው ለቅሶ የመጨመሩ ምክንያትም ይሄው ነው። ታዲያ በህወሃት መንጋ ላይ የሚሰነዘረው ምት ሲበረታ አንድ ለየት ያለ አካሄድ እየታየ ነው።

በውጊያ ግንባሮች የጀግናው መከላከያ ሰራዊታችንን ምት መቋቋም ያቃታቸው የህወሃት ታጣቂዎች ከግንባር ሸሽተው ወደ ከተሞች እየሸሸ ነው። ለትግራይ ህዝብ እዋጋለሁ የሚለው ይህ ቡድን ታዲያ ሽንፈቱ አይቀሬ መሆኑን ሲረዳ “ንፁሃን ተጎዱ” የሚለውን የቀደመ የሃሰት ትርክቱን ለማጠናከርና የአለምአቀፍ ትኩረትን ለመሳብ አቅዷል። ህፃናትንና አዛውንቶችን ሳይቀር ያሰለፈበት የህዝብ ማእበል ሲከሽፍ፤ በብዙ ዙሮች መሬት ፈልፍሎ የሰራቸው ምሽጎች እንደማያድኑት ሲረዳ አሁን የትግራይን ከተሞች ምሽጉ እያደረገ ነው። ይህ ደግሞ የአለምአቀፍ ትኩረትን ስቦ ላኪዎቹ እንዲያድኑት ከመፈለግ የመነጨ ውሳኔ ነው። ታዲያ ከተሞች ውስጥ ውጊያ ቢደረግ፣ የትግራይ ህዝብ በዚህ ምክንያት ቢጎዳ ለህወሃት ምኑ ነው?

በተግባር ከሃውዜን የጀመረው ልማዳቸው አሁን በቅርቡም በአማራና አፋር ክልል ከተሞች ውስጥ ገብቶ የፈፀመውን ጥፋት ለተመለከተ ይህ የህወሃት የአሁኑ የሽንፈት ውሳኔ ላያስገርመው ይችላል። መከላከያ ጦርነቱን ከከተማ ለማራቅ ሲሞክር በተቃራኒው የህወሃት ጀሌ ንፁሃንን ኢላማ አድርጎ ጦርነቱን ወደ ከተሞች በመሳብ የፈፀመውን በታሪክ የተመዘገበ ጥፋት ማንም ኢትዮጵያዊ አይረሳውም። በሌላ በኩል መንግስት የትግራይ ህዝብ ከጦርነት አካባቢዎች እንዲርቅ በተደጋጋሚ በይፋ ማሳሰቡና ሲቪሎች እንዳይጎዱ ሲወስድ የቆየው እርምጃ ሁሉ በግልፅ ይታወቃል።ታዲያ እውነት ለትግራይ ህዝብ የቆመው ማን ነው?
የትግራይ ህዝብ ልብ ብለህ ስማኝ!

የህወሃት ጀሌ ቀዬህን፣ መኖሪያ መንደርህን የጦርነት አውድማ ለማድረግ ከውጊያ እየሸሸ ወደ ከተሞች እየገባ ነው። ይህ ከራሱ የስልጣን ጥማትና ፍፁም ራስ ወዳድ ፍላጎት አሻግሮ ማየት የማይችለው ቡድን ምክንያት ምን እስኪደርስብህ ነው የምትጠብቀው? ጭራሽ ወደ ቀዬህና ወደ ቤትህ ሲመጣስ ለምን ትታገሰዋለህ?

እምቢ በል!
የትግራይ ህዝብ የህወሃት ሽንፈት መወጫ አይሆንም በል! ብትችል ቀዬህን፣ ከተማህን በዚህ መንጋ አታስደፍር። እሱንም ካልቻልክ ራስህን ወደምታድንበት አካባቢ ከህወሃት የጭካኔ ስራ የተረፉ ልጆችህን ሰብስበህ ውጣ!

ኢትዮጵያ እና አየርላንድ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደሚመጥን ተግባር አየርላንድ እንድትመለስ ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች።አየርላንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያላትን የተ...
13/10/2022

ኢትዮጵያ እና አየርላንድ ያላቸውን ታሪካዊ ግንኙነት ወደሚመጥን ተግባር አየርላንድ እንድትመለስ ኢትዮጵያ አስጠነቀቀች።

አየርላንድ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ያላትን የተለዋጭ አባልነት በመጠቀም በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ አጀንዳ እንድትሆን ለማድረግ እየሰራች እንደሆነ የተለያዩ ምንጮች ጠቁመዋል።

ከዚህም ባለፈ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ቀውስ የህወሃት የሽብር ቡድንን ተጠያቂ የሚያደርጉ ማስረጃዎችን ጭምር ችላ በማለት አየርላንድ ለሽብር ቡድኑ የዲፕሎማሲ ድጋፍ ማድረጓን እንድታቆም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ይፋዊ ደብዳቤ ተጽፏል።

13/10/2022
የቴድሮስ አድሃኖም የግብፅ ጉዞ ገመና ሲገለጥየቴድሮስ አድሃኖም ድንገተኛ የግብፅ ጉዞ ከአለም የጤና ድርጅት መደበኛ ስራ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ቀደም ብሎ ሲነገር ቢቆይም ዛሬ በወጡ ሚስጥራ...
13/10/2022

የቴድሮስ አድሃኖም የግብፅ ጉዞ ገመና ሲገለጥ

የቴድሮስ አድሃኖም ድንገተኛ የግብፅ ጉዞ ከአለም የጤና ድርጅት መደበኛ ስራ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ቀደም ብሎ ሲነገር ቢቆይም ዛሬ በወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች ሰውዬው ወደ ግብፅ ያመራበት ምክንያት በሞት አፋፍ ላይ ላሉ የወንጀል አጋሮቹ (እነ ደብረፅዮን) እርዳታ ለማሰባሰብ እንደሆነ ተረጋግጧል። ከቀናት በፊት በደህንነት ዶክመንቶች ሾልኮ የወጣ መረጃ እንዳመለከተው ግብፅ GIS ተብሎ በሚጠራው የስለላ ድርጅቷ አማካኝነት 2 ሚሊየን ዶላር በቅርቡ ለህወሃት መክፈሏ ተገልጾ ነበር። ይህ ክፍያ ህወሃት ሶስተኛውን የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉልና በጦርነቱ እንዲቀጥል እንደሆነ ታውቋል። በተጨማሪም ግብፅ በየ45 ቀኑ 500 ሺ የአሜሪካ ዶላር በዚሁ የስላላ ድርጅቷ አማካኝነት ለህወሃት እየለገሰች እንደቆየች ተገልጿል።

የሰሞኑ የቴድሮስ አድሃኖም ጉዞም በጤና ሽፋን ይሁን እንጂ ከዚሁ ለህወሃት ከሚደረግ ድጋፍ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ዛሬ እየወጡ ያሉ መረጃዎች ጠቁመዋል። የቴድሮስ አድሃኖም ዋነኛ የጉዞ አላማ የግብፅ ድጋፍ እንዲጨምር ለማግባባትና ድጋፉ በቴድሮስ አድሃኖም በኩል አድርጎ አውሮፓና አሜሪካ ለሚገኙ የህወሃት የዲያስፖራ ሴሎች እንዲደርስ ከዛም በጥቁር ገበያ አማካኝነት በትግራይ ለሚገኘው የህወሃት አመራር እንዲደርስ ለማድረግ ነው። እንግዲህ ሚስጥሩ ይሄው ነው። ልብ ያለው ልብ ይበል። ሰወዬውን ማጋለጥ የኛ የኢትዮጵያውያን ድርሻ ነው!

11/10/2022

ሰሞኑን የሽብር ቡድኑ በጥምር ጡሩ በተወሰደበት እርምጃ ከራያ ቆቦ ለቆ ሲወጣ ከአካባቢው በርካታ ወጣቶችን አፍኖ መወስዱን ተክትሎ በአካባው ያለው ወጣት በእልህና በቁጭት ለመታገል የሃገር ደጀን የሆነውን መከላከያንና የክልሉን የፀጥታ ሃይል በመቀላቀልና በመደግፍ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኖን በራያ አላማጣ፣ በራያ ኦፍላ/ኮረም ዙሪያ፣ራያ ጨርጨር፣ራያ አዘቦና እንድርታ ዙሪያ በጦርነቱ አልተሳተፈም በሚል የትህነግ አመራሮች ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ቤት ለቤት አፋሳ እያደረጉ መሆኑን ወደ ራያ ቆቦ የሽሹና ወደ አዲስ አበባበ ቤተሰቦቻቸው እየደወሉ እያሳወቁ ይገኛሉ፡፡ይህንንም በመቀዋወም ቤት የሚያድር የራያና የእንድርት ወታጣት አለመኖሩን የውስጥ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ኦሮማይ! የመጨረሻው መጀመሪያ የደረሰ ይመስላል፡፡

11/10/2022

ሁመራ ህልም የሆነበት በሜ/ጀነራል ሙዘይ የሚመራው የአሸባሪው ህወሓት ጦር ከ 10 ሺ በላይ የሚሆኑትን ታጣቂዎቹን አጥቷል

የሁመራን ኮሪደር ለማስከፈት ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገው በሜ/ጀነራል ሙዘይ የሚመራው የህወሓት የሽብር ቡድን ተደጋጋሚ ሽንፈትና ውርደት ተከናንቧል።

ከተለያዩ የሱዳን ከተሞችና የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የትግራይ ተወላጆችን በመመልመልና በማሰልጠን የሁመራን ኮሪደር ለማስከፈት ተደጋጋሚ ትንኮሳ ሲያደርግ የነበረው በሜ/ጀነራል ሙዘይ የሚመራው የህወሓት ኃይል፤ በቅርቡም ያልተሳካለትን ሙከራ አድርጓል። መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሜ/ጀነራል ሙዘይ እስካሁን 12,000 ታጣቂዎች በሱዳን በኩል አሰማርቶ ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑት ተደምስሰዋል።

በአሸባሪ ቡድኑ ላይ በተደጋጋሚ የደረሰው ያልተጠበቀ ሽንፈት እየተሰማ መሆኑን ተከትሎ በጠላት ዘንድ በተለይ በምዕራብ ግንባር በሚገኙት ታጣቂዎች ላይ ከፍተኛ የሞራል ውድቀት እና ሥጋት ተፈጥሯል። በዚህም ምክንያት ቀሪዎቹ ታጣቂዎች ሁኔታዎች ከተመቻቸላቸው ለወገን ኃይል እጅ ለመስጠት የሚፈልጉ መሆናቸው ታውቋል። ከምርኮኞችና ከኢንተለጀስ ምንጮች ይህ መረጃ የደረሰው የወገን ኃይል እጅ ለመስጠት የሚፈልጉ ታጣቂዎችን ለመቀበል ዝግጁነቱ ያለው መሆኑ ታውቋል።

11/10/2022

የትግራይ ህዝብ ዝምታውን ይስበር!
ህወሓት እየደጋገመ ክተት ቢያወጅም የትራይ ህዝብ በዝመታ አልፎታል! የትግራይ ህዝብ ከወንድም ህዝቡ ጋር እንዲጫረስ የሚቀርብለትን የክተት ጥሪ ካሁን በኋላ በዝምታ ማለፍ የለበትም! ህወሓትን በቃቀኝ ብሎ እስከመጨረሻው ሊታገለው ይገባል፡፡
¬¬¬¬----
ትህነግ በድርድር ሰበቡ የዝግጅት ጊዜ ለመግዛት እንደፈለገ አለም አውቆበታል፡፡ ይህን የጦርነት ስልቱን ያረጀ ያፈጀ እንደሆነ ያልተረዳው የትህነግ አመራር ለዳግም እልቂት የትግራይን ህዝብ ለማስጨረስ የክተት አዋጅ አውጇል፡፡
----
የመንግሰትን ትግስትና ሆደሰፊነትን እንደፍርሃት የቆጠረው ወያኔ ከዕለት ወደ ዕለት የእውር-ድንብር መንገዱን እንደቀጠለበት ነው፡፡ የግብጽና ሱዳንን ተልዕኮ ለማስፈጽም ቆርጦ የተነሳው የሽብር ቡድኑ ዛሬም ሽንፈቱን በህዝባዊ መአበል ለመቀልበስ የጦርነት ነጋሪቱን ጎሱማል፡፡
-----
የተከበርከው የትግራይ ህዝብ!
ስለምን ብለክ ልጆችክን ትገብራለክ? የትግራይ ወጣትስ ላረጀና ላፈጀ የፖለቲካ ቁማር 1ነፍስህን ለመስዋት ታቀርባለክ? እንቢ በል! ከቻልክ ወያኔን ታገልና ደምስስ ካልቻልክ ደግሞ ሰምተህ እንዳልሰማ ሁንና ከመንግስት ጎን ተሰለፍ!
¬¬¬¬-----
የትግራይ ህዝብ የነጻነት ጥማት መቼ ይሆን የሚያበቃው?

እህቴ የምስራቅ አማራ ፋኖ ናት። እኔ ደግሞ ከእሷ ተለይቸ እቤት መቀመጥ አልችልም። እኔም ወደ ፋኖ ሄድኩ። ነገር ግን የምስራቅ አማራ ፋኖ አንተ ህፃን ነህ ብለው ከለከሉኝ። ያም ሆኖ ከእህቴ...
11/10/2022

እህቴ የምስራቅ አማራ ፋኖ ናት። እኔ ደግሞ ከእሷ ተለይቸ እቤት መቀመጥ አልችልም። እኔም ወደ ፋኖ ሄድኩ። ነገር ግን የምስራቅ አማራ ፋኖ አንተ ህፃን ነህ ብለው ከለከሉኝ። ያም ሆኖ ከእህቴ ጋር አልተለየሁም። በዚህ መሐል በአሸባሪው እጅ ወደቅኩ።
ወዲያው የመከላከያ ሰራዊት ልብስ አለበሱኝ። የመከላከያ ሰራዊት ተመረከ፣ መከላከያ ሰራዊት ህፃናትን ወደ ጦር ግንባር እያስገባ ነው በማለትም ቪዲዮ ሰሩብኝ። ወደ መቀሌ ሊወስዱኝ ሲሉም በማሽላ ማሳ ውስጥ ገብቸ አመለጥኳቸው። የአካባቢውን ገበሬ የመከላከያ ሰራዊት ልብስ እያለበሱ መከላከያ ተማረከ፣ ፋኖ ተማረከ ይላሉ። ውሸታቸውን ነው። አንድ የራያ ቆቦ ታዳጊ የተናገረው

የግብፅ የመረጃ ተቋም ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና ሦስተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል 2 ሚልዮን ዶላር እንዳበረከተለትና በየ 45 ቀኑም 500 ሺ ዶላር ድጋፍ ሲያደ...
11/10/2022

የግብፅ የመረጃ ተቋም ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና ሦስተኛውን ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል 2 ሚልዮን ዶላር እንዳበረከተለትና በየ 45 ቀኑም 500 ሺ ዶላር ድጋፍ ሲያደርግለት እንደቆየ ምስጢራዊ ሰነዶች አጋለጡ

የግብፅ ጠቅላላ የመረጃ አገልግልት (General Intelligence Service- GIS) ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበት እንዲሁም የህዳሴ ግድቡ 3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመጀመሩ በፊት የተለያዩ የሀገር ውስጥ ታጣቂ ኃይሎችን ስምሪት በመስጠት ሂደቱ እንዲስተጓጎል ከሀገሪቱ መንግሥት ተልዕኮ ተሰጥቶት ሲንቀሳቀስ እንደነበር ምስጢራዊ ሰነዶች አጋልጠዋል፡፡

የግብፅ ጠቅላላ የመረጃ አገልግልት (General Intelligence Service- GIS) ቦርድ ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙታዝ ሙስጠፋ እና የአፍሪካ ላይዘን ኃላፊ ብ/ጀነራል ሙስጠፋ ማርዋን 2 ሚልዮን የአሜሪካ ዶላር በዲፕሎማሲያዊ ሂደት ወደ ሱዳን ካስገቡ በኋላ በካርቱም ለሚገኙ የሽብር ቡድኑ ተወካዮች ማስረከባቸውን የሚያጋልጡ የሰነድ ማስረጃዎች የተገኙ ሲሆን፤ ህወሓት ጦርነቱን እንዲገፋበትና በኢትዮጵያ አለመረጋጋቱ እንዲቀጥል በየ45 ቀኑ 500 ሺ የአሜሪካ ድላር ድጋፍ ሲደረግለት እንደነበረም ተረጋግጧል፡፡

ሱዳን እና ግብፅ ህወሓትን በመጠቀም የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥትና አጠቃላይ ፖለቲካዊ ሁኔታውን ለመቀየር ያላቸውን ፍላጎት ለማሳካት ለአሸባሪ ቡድኑ የፋይናንስ፣ የሎጀስቲክ፣ የስልጠናና ሌሎችም የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ በተለይም ግብፅ የሽብር ቡድኑ የመንግሥት ለውጥ ማምጣት ባይቻል እንኳን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂ ኃይሎችን በማቀናጀት የህዳሴ ድግቡን የ3ኛው ዙር የውሃ ሙሌት እንዲያስተጓጉል ከፍተኛ ተስፋ አድርጋ የነበረ ሲሆን፤ የትግራይ ክልል ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮችም የገንዘብ ድጋፍ ከተደረገላቸው የተሰጣቸውን ተልዕኮ እንደሚያከናውኑ ተስማምተው እንደነበር ታውቋል፡፡

መረጃ‼️ህወሀት አለ የሚለውን የሰዉ ሀይል ይዞ ወደ ወልቃይት ግንባር ለመዝመት በማሰባሰብ ላይ ነው። ይህ የሽብር ቡድኑ የመጨረሻ አማራጩ ስለሆነ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት መረጃዎች ይጠቁማሉ...
08/10/2022

መረጃ‼️
ህወሀት አለ የሚለውን የሰዉ ሀይል ይዞ ወደ ወልቃይት ግንባር ለመዝመት በማሰባሰብ ላይ ነው። ይህ የሽብር ቡድኑ የመጨረሻ አማራጩ ስለሆነ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ይሄን ግንባር አሉ የተባሉ የቡድኑ የጦር መሪዎችም የሚመሩት ሲሆን፤ ትላንት ከሰዓት ጀምሮ አዲዐርቃይ የነበረውን ሀይሉን በዋልድባ በኩል ወደ ወልቃይት አቅጣጫ እያስጠጋ እንደሆነ ታውቋል።

በደቡብ አፍሪካ በ29/01/2015 ዓ/ም ይጀመራል ተብሎ በነበረው የሰላም ንግግር መድረክ መገኘት አልችልም ያሉት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ድርድሩ ላይ ላለመገኘታቸው በምክንያ...
08/10/2022

በደቡብ አፍሪካ በ29/01/2015 ዓ/ም ይጀመራል ተብሎ በነበረው የሰላም ንግግር መድረክ መገኘት አልችልም ያሉት የቀድሞ የኬንያ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ ድርድሩ ላይ ላለመገኘታቸው በምክንያትነት ያቀረቡት በተመሳሳይ ቀን የያዙት ስራ ስለነበር መሆኑን የገለጹ ሲሆን ኬንያታ ሌላ የንግግር ቀን እስኪወሰን ድረስ፣ ኅብረቱ ስለ ሰላም ንግግሩ ቅርጽ፣ አካሄድና አወያዮች መከተል ስላለባቸው ደንቦች ዝርዝር ማብራሪያ እንዲሰጣቸውም ጠይቀዋል።
በተጨማሪም በደብዳቤው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ማድረግ ከንግግሩ ከአጀንዳዎች ሁሉ ቀዳሚው እንደሚሆን ተስፋቸውን ገልጸው፤ ይህም የሰዎችን ስቃይ በማስቆም ሰብአዊ እርዳታ እንዲቀርብ ከማስቻሉ ባሻገር ለንግግሩ ትክክለኛውን ሁኔታ እንደሚፈጥር አስረድተዋል።
ኡሁሩ ኬንያታ ከጻፉት ደብዳቤ እንደምንረዳው ተደራዳሪዎች ያለቅድመ ሁኔታ ለመደራደር ከተስማሙ በኋላ እሱ ለማደራደር የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታ መጠየቁ ለአሸባሪው የህወሃት ታጣቂ ቡድን የእፎይታ ጊዜ ለመስጠት ከማሰብ የመነጨ ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል።

08/10/2022

አሳዛኙ የህወሃት የእርዳታ ፖለቲካ፣ የእርዳታ ሰራተኞች ስቃይና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዝምታ!

ህወሃት ከሰማይ በታች ያልፈፀመው ምንም አይነት ግፍና አሰቃቂ ተግባር እንደሌለ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያውቃል። ከሰሞኑ ደግሞ የዚህ ፀረ-ሰው ቡድን ዋነኛ ስትራቴጂ ከእርዳታና ከእርዳታ ድርጅቶች ጋር የተገናኘ ነው። ለነገሩ ቡድኑ እርዳታን ለሽብርና ለፖለቲካ አላማው ሲጠቀም ዘንድሮ የመጀመሪያ አለመሆኑን ሁላችንም እናውቃለን። እነዚህ ጉግ ማንጉጎች በትግል ወቅት በርሃብ ከሚሰቃየው የትግራይ ህፃን አፍ እየቀሙ ታጣቂዎቻቸውን ሲመግቡ እንደነበረ ታሪክ ያሰፈረው ሃቅ ነው። መቼም አመል አይለቅም እንዲሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ የእርዳታ ድርጅቶችና እርዳታን ለሽብር ተግባር የማዋል ልምዱን አጠናክሮ መቀጠሉ ከመቀሌና ከትግራይ ነዋሪዎች አንድ አንድ መረጃዎች እየደረሱኝ ነው።

ይህ ፀረ-ሰው የሆነ ቡድን አሸባሪው ቡድን ከዚህ በፊት ወደ ትግራይ የገቡ መኪኖችን አስገድዶ በመውሰድ የታጣቂ ማመላለሻ አድርጎ እየተጠቀመ እንደሚገኝ፤ ለእርዳታ ማመላሻ ተሽከርካሪዎች የተመደበ ነዳጅ መዝረፉ፤ አመራሮቹ ሆን ብለው በመቀሌ የሚገኙ የጦር መሳሪያ መጋዘኖችን የተመድ አርማ እየቀቡ የጥቃት ዒላማ እንዲሆኑ ሲጥሩ እንደነበር፤ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ሰራተኞችን አስገድደው የኮሚኒኬሽን መሳሪያቸውን እንደሚጠቀሙ የሚታወቅ ሲሆን፤ ሰሞኑን ደግሞ የቡድኑ ታጣቂዎችና ደጋፊዎች በተለይ እንደ ራያ ባሉ አካባቢዎች ከእርዳታ ጋር በተገናኘ እየፈፀሙ የሚገኙት አሻጥርና ሴራ በጣም አሳዛኝ ነው።

በራያ የህወሃት ሴሎችና ደጋፊዎች ለእርዳታ ድርጅቶች የተሳሳተና ትክክል ያልሆነ መረጃ በመስጠት ሰብዓዊ እርዳታ ለተጎጂው ህዝብ እንዳይደረሰ ከሰውነት ተራ ዝቅ ያለ ሴራ እየሰሩ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ተችሏል። እነዚህ አካላት ለእርዳታ ድርጅቶች በሚሰጧቸው የተሳሳተ መረጃ የህወሃት ደጋፊዎችና ሴሎች ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እያደረጉ እንደሚገኝ፣ በሚያሳዝን መልኩ ንፁህ ህዝብ እርዳታ እንዳይደርሰው የእርዳታ ፖለቲካውን አጠናክሮ መቀጠሉን ለማወቅ ተችላል። በህወሃት አሰራር መሰረት ሰብዓዊ እርዳታን ለማግኘት የግድ የህወሃት ደጋፊና ታጣቂ መሆን ይገባል ተብሏል። በጣም የሚገርመው ጉዳይ እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ እርዳታን በተመለከተ ቅድሚያ የሚሰጠው ለህወሃት ደጋፊዎችና አባላት ብቻ መሆኑ ታውቋል።

በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የእርዳታ ሰራተኞች ካለምንም ጣልቃ ገብነትና ጫና ስራቸውን በገለልተኝኘት መስራት አለባቸው የሚለውን አለም አቀፍ መርህ በመጣስ ቡድኑ እያደረገባቸው በሚገኘው ጫና በተለይም በራያ፣ አላማጣና ኮረም አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ የሚገኙ የእርዳታ ሰራተኞች ስራቸውን መስራት በማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸውን እየገለፁ ነው። ጫናው በተለይ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የእርዳታ ሰራተኞች ላይ የበረታ ሲሆን እነዚህ ሰራተኞች በግድ በጦርነት ላይ እንዲሳተፉ እየተደረጉ እንደሚገኝም ታውቋል። ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ በአዲስ አበባ የሚገኙ የእርዳታ ድርጅቶች የተወሰኑ አመራሮች ጉዳዩን በተመለከተ ስብሰባ ማድረጋቸውን እንዲሁም በክስተቱ ዙሪያ የተቀናጀና የተደራጀ ሪፖርት ለማውጣት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ።

ይህ ሁሉ አሳዛኝ ክስተት በእርዳታ ስም እየተፈፀመ ቢገኝም የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶችን ጨምሮ አለም አቀፉ ማሀበረሰብ በጉዳዩ ዙሪያ ዝምታን መርጧል። የህወሃትን ጥፋት ባለየ የማለፍ ልምድ ያዳበረው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ይህንን አሳዛኝ ጉዳይ እንዲያወግዘው ግፊት ማድረጉ ከሁላችንም የሚዲያ ባለሞያዎችና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚጠበቅ ነው።

08/10/2022

የህወሓትን ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች አርስ በርስ እያባሉ ያሉ ወቅታዊ አጀንዳዎች ምንድን ናቸው ?

ሕወሓት ከፍጥረቷ ጀምሮ እርስ በርስ መበላላትና መጠፋፋት የታሪኳ አካል ያደረገች ድርጅት ናት፡፡ ሰሞኑን ይህን ታሪኳን የሚያድስ አዙሪት ውስጥ ገብታለች፡፡
ከህወሓት ጓዳ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የፌዴራል መንግሥት በአፍሪካ ሕብረት አማካኝነት የሚካሄደውን ድርድር እንደሚቀበል መግለጹን ተከትሎ የቡድኑ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ጎራ ለይተው ድርድር እናድርግ ወይስ አናድርግ በሚል ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በቡድኑ ውስጥ መከፋፈሉ በግልጽ ከመታወቁ አልፎ እርስ በእርስ የመጠፋፋት አዝማሚያ እየታየ መሆኑ ታውቋል፡፡

በህወሓት መካከል ቁርሾ የፈጠረው ሌላው ጉዳይ ውጊያው ትግራይን ወጣት አልባ እያደረጋት ስለሆነ መቆም አለበት የሚለውን ከሕዝብ እየመጣ የሚገኘውን ጫና የተወሰኑ አመራሮች መደገፋቸው ነው፡፡ በተለይ ቡድኑ በሦስተኛው ዙር በከፈተው ጥቃት ያልጠበቀው ሰብዓዊ ጉዳት ማስተናገዱ ከፍተኛ ሽኩቻ አስከትሏል፡፡ በዚህም የተነሳ ውጊያው ቆሞ የትግራይ ሕዝብ ከእኛ ውጪ ያለውን አማራጭ እንዲሞክር እድል እንስጠው የሚሉ አመራሮች ብቅ ብቅ በማለታቸው እንደ ከሃዲ ተቆጥረው እርምጃ እንዲወሰድባቸው በድብቅ ስብሰባ መካሄዱ ታውቋል፡፡

08/10/2022

ሰበር መረጃ

ሦስት የአሸባሪው ቡድን ማሠልጠኛዎች በኢትዮጵያ አየር ኃይል ዶግ አመድ መሆናቸውን ተከትሎ ጌታቸው ረዳ በሲቪሎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ ብሎ ትዊት እንደሚያደርግ ይጠበቃል

አሸባሪው ህወሓት በሁሉም አቅጣጫ ከፍተኛ ምት እያረፈበት ሲሆን፤ ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የቡድኑ ሦስት ወሳኝ ማሠልጠኛዎችን ዶግ አመድ አድርጓቸዋል፡፡

ህወሓት በአንድ በኩል ድርድር እያለ በሌላ በኩል በርካቶችን በአፈሳ ጭምር እየሰበሰበ ማሠልጠን መቀጠሉን የሚያሳዩ ማስረጃዎች በመገኘታቸው የዛና፣ ደንጎላት እና አግበ የታጣቂ ማሠልጠኛዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

አሸባሪው ህወሓት ያልጠበቀው ኪሳራ በማስተናገዱ ከፍተኛ ድንጋጤ የተፈጠረበት ሲሆን፤ የቡድኑ የፕሮፖጋንዳ ክንፍ እርምጃው በሲቪሎች ላይ እንደተወሰደ አስመስሎ የሀሰት መረጃ እንዲያሰራጭ አቅጣጫ ተሰጥቶታል፡፡ የቡድኑ አፈቀላጤ ጌታቸው ረዳም ይህንኑ የሚያስተጋባ የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ለማሰራጨት ቀዳሚው እንደሚሆን ይጠበቃል።

08/10/2022

ጀግናው የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዛሬ ለውጥ አምጪ ርምጃ ወስዷል። በዚህ ርምጃ አሸባሪው ሕወሐት ታጣቂዎቹን ሲያሠለጥንባቸው በነበሩ የወታደራዊ ማዕከላት ላይ ኢላማውን የጠበቀ አኩሪ ርምጃ ወስዷል።
• ደርቤ ከርቤ (ዛና)
• ደንጎላት
• አግበ
የተባሉት የጁንታው የማሠልጠኛ ማዕከላት በአየር ኃይላችን ርምጃ ተወስዶባቸዋል።

ህወሓት ድርድሩን እንደሚቀበል ገለጸ!!አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ቡድን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲደራደር ያቀረበለትን ጥሪ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ ቡድኑ ለ...
06/10/2022

ህወሓት ድርድሩን እንደሚቀበል ገለጸ!!

አሸባሪው የህወሓት ታጣቂ ቡድን የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር እንዲደራደር ያቀረበለትን ጥሪ መቀበሉን አስታውቋል፡፡ ቡድኑ ለአፍሪካ ህብረት በላከው ደብዳቤ በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ለቀረበላቸው የድርድር ጥሪ ምስጋና በማቅረብ ህወሓት የተደራዳሪ ቡድን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመላክ ዝግጁ መሆኑንና በደቡብ አፍሪካ በታቀደው ድርድር የሚሳተፍ መሆኑን ገለጸዋል፡፡
የቡድኑ ፕሬዚደንት ዶ/ር ደ/ጺዮን ገ/ሚካኤል ድርድሩን አስመልክተው ለአፍሪካ ህብረት በላኩት ደብዳቤ ግጭት ማቆም የድርድሩ አጀንዳ መሆኑ ቢታወቅ ጠቃሚ እንደነበር በመጠቆም፤ ግልጽ እንዲሆኑልን የምንፈልጋቸው ካሉዋቸው ነጥቦች መካከል በድርድሩ እንደ ታዛቢ፣ ተሳታፊ እና ዋስትና ሰጭ፣ የሚጋበዙ ተጨማሪ አካላት ስለመኖራቸው፤ የአለምአቀፉ ማህበረሰብ ስለሚኖረው ሚና፣ የተደራዳሪዎች የጉዞ ወጪና እና ቁሳቁሶች እንዲሁም የደህንነት ጉዳይ ዙሪያ ማብራሪያ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

የመቀለ ከተማ ህዝብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በየበሩ ሰቅሎ መከላከያ ሰራዊትን እየጠበቀ ነው ተባለታዋቂው የትግራይ ፓለቲከኛ አቶ ሊላይ ሀይለማርያም  እንደገለፁት የመቀለ ከተማ ህዝብ የኢት...
05/10/2022

የመቀለ ከተማ ህዝብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በየበሩ ሰቅሎ መከላከያ ሰራዊትን እየጠበቀ ነው ተባለ

ታዋቂው የትግራይ ፓለቲከኛ አቶ ሊላይ ሀይለማርያም እንደገለፁት የመቀለ ከተማ ህዝብ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በየበሩ ሰቅሎ መከላከያ ሰራዊትን እየጠበቀ ነው።

በመቀለ ከተማ በአሁኑ ወቅት ከሁለት የማይበልጡ ፓትሮል ተሽከርካሪዎች ህዝቡ አመፅ እንዳያነሳ እየተዟዟሩ ይጠብቃሉ እንጂ የህወሓት ታጣቂ በከተማው አይታይም ብለዋል።

ህዝቡም ከዛሬ ነገ መከላከያ ይገባል በሚል የሀገሩን ሰንደቅ ዓላማ በየበሩ ሰቅሎ በጉጉት እየጠበቀ መሆኑን ገልፀዋል።

በራያ ቆቦ ግንባር ሽንፈት የገጠመው የህወሓት ሰራዊት ከእዝ ሰንሰለት ወጥቶ እየጠፋ መሆኑንም አቶ ሊላይ አረጋግጠዋል።

ፓርቲያቸው ራዕይ ፓርቲም በአፋር ክልል ጉባኤውን በስኬት አካሂዶ ህወሓትን ከትግራይ ህዝብ ትከሻ ማውረድ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ ማስቀመጡንም ለኢሳት ገልፀዋል።

01/10/2022
19/09/2022

ያልተነገረው የህወሃት ገመና

የህወሃት ታጣቂ ለሶስተኛ ዙር ውጊያ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ከ150 ሺ በላይ ታጣቂ እንደተገደለበት በውጭ ሀገር የሚገኙ የቡድኑ አመራሮች እየገለጹ ነው።
ቡድኑ ዳገም ጦርነት ከቀሰቀሰ ከነሀሴ 18/2014 ጀምሮ ባሉት ሀያ ስድስት ቀናት ውስጥ ቡድኑ 150ሺ ታጣቂዎች እንደተገደሉበት የቡድኑ አመራሮች ሪፖርት ሲደርሳቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተዋል። ከዚህም በላይ እውነታው ለትግራይ ህዝብ የደረሰ ጊዜ ቡድኑን ችግር ውስጥ የሚከት በመሆኑ መረጃው የደረሳቸው አካላት መረጃውን ለማንም ከመግለጽ እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ከዚህም በላይ የመከላከያ ሰራዊት በጥቂት ቀናት ውስጥ ከሁሉም አቅጣጫ ውጊያ በመክፈት መቀሌን ለመቆጣጠር አቅዶ እየተዘጋጀ በመሆኑ ከአሁን በኋላ ለአንድ ሳምንት ጠንከር ያለ ወጊያ ከተካሄደ ምናልባት ከአንድ መቶ ሺ በላይ ታጣቂ ሊያልቅ የሚችል በመሆኑ ቡድኑ ምን ያክል ቀናት ውጊያ ተቋቁሞ ሊያካሄድ ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ከቷቸዋል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው የመንግስት ሃይል ለ24 ሰኣታት በማያቋርጥ ሁኔታ የአየር እርምጃዎችን ለማስቀጠል ማቀዱን የሚገልጹ መረጃዎችን መውጣታቸው እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ 400ሺ የሚሆን ልዩ ወደ ግንባር እየገቡ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ መውጣቱ የቡድኑ የወደፊት ህልውና አደጋ ውስጥ መግባቱን እያመላከተ መሆኑ እየተገለጸ ነው።

በተጨማሪም በዚህም በሰቆጣ ግንባር ውጊያ ሲያካሄድ የነበረው የጠላት አርሚ 26፣ አርሚ 22 እና አርሚ 33 ሙሉ በሙሉ የተደመሰሰ መሆኑን የታወቀ ሲሆን በአፋር ግንባር በተለይ በቢሶበር እና ወርቄ አካባቢ ሲዋጋ የነበረው በወዲ አባተ የሚመራው የጠላት አርሚ 44 75% የሚሆነው ሃይሉ ተደምስሷል። በተጨማሪም የጠላት ሃይል ከዞብል አካባቢ ወደ ደደቢት ድጋፍ ለማድረግ የሄደው የጠላት አርሚ 42 ሃይል አብዛኛው ተደምስሶ ቀሪው ወደ ኋላ ወጥቶ ራሱን እንዲያደራጅ መመሪያ እንደተሰጠው ታውቋል። በዚህም ምክንያት ጠላት የተበታተነውን ሃይሉን ለማሰባሰብ እና አሉሁኝ ለማለት ጥቂት ሃይል በማይጸብሪ በኩል ውጊያ እንዲያካሄድ አቅጠጫ ተሰጥቶት እድሉን እየሞከረ እነደሚገኝ ታውቋል።

ህወሃት  በትላንትናው ዕለት በ3 /1/2015 ዓ/ም በደረሰበት የአየር ላይ ጥቃት የቡድኑ ልሳን የሆነው ድምፂ ወያነ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ድምጽ ወያኔን ወደ ሳተላይት...
14/09/2022

ህወሃት በትላንትናው ዕለት በ3 /1/2015 ዓ/ም በደረሰበት የአየር ላይ ጥቃት የቡድኑ ልሳን የሆነው ድምፂ ወያነ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት መሆኑን ተከትሎ ድምጽ ወያኔን ወደ ሳተላይት ለመመለስ ከሀገር ውጭ የሚገኘውን የብሄሩ ተወላጅ የዲያስፖራ ማህበረሰብ በመማጸን ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የሽብር ቡድኑ በትግርኛ ቋንቋ በጻፈው ደብዳቤ "ድምፂ ወያነ ወደ ሳተላይት እንዲመለስ የትግራይ ዳያስፖራ የቻልከውን እርዳን፣ ወደ ሳተላይት እንድንመለስ ሁሉም በውጭ የሚኖር ትግራዋይ የድርሻው ይወጣ"። በማለት የተማጽኖ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ባንዳው አሰማኽኝ አስረስ ዛሬም በፓርላማው ፊት በአማራ ክልል የሚደረጋውን አፈና የሚደግፍ ሀሳብ አንስቷል፡፡
14/06/2022

ባንዳው አሰማኽኝ አስረስ ዛሬም በፓርላማው ፊት በአማራ ክልል የሚደረጋውን አፈና የሚደግፍ ሀሳብ አንስቷል፡፡

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share