Magna Addis

Magna Addis Magna Addis Radio Programme 📻📡

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ የቀላቲ ቢውቲ ብራንድ አምባሳደር ሆነች። ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለቀላቲ ቢዉቲ የሁለት ዓመት የክብር አምባሳደር በመሆን ስምምነት ፈፅመች። ስምምነቱ ለቴሌቪዥን ማስታወቂ...
18/12/2024

ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ የቀላቲ ቢውቲ ብራንድ አምባሳደር ሆነች።

ድምፃዊ ቬሮኒካ አዳነ ለቀላቲ ቢዉቲ የሁለት ዓመት የክብር አምባሳደር በመሆን ስምምነት ፈፅመች። ስምምነቱ ለቴሌቪዥን ማስታወቂያ፣ ቢል ቦርድ እና ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ለመስራት ተስማማታለች።

ቀላቲ ቢውቲ በ2008 በሮቤል ቀላቲ የተሰረተ ሲሆን በአዲስ አበባ ቦሌ መድኃኒአለም ሞል እና በዱባይ ሱቅ አለው። የሰው ጸጉር፣ የሰው ሰራሽ ጸጉር፣ ኮስሞቲክስ እና የውበት ምርቶችን መሸጫ ከስምና የውበት መጠበቂ ምርቶች በመሸጥ ላይ ነው፡፡

በብዙ አይነት የጸጉር ማስረዘሚያ፣ ዊግ እና የጸጉር መንከባከቢያ ጸጉሮች እንዳሉት ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም ሜካፕና የቆዳ መንከባከቢያ ምርቶች ሽቶዎችና ለሌሎች ለውበት አስፈላጊ ነገሮችን እንደሚሸጡ ተገልጿል።

ቀላቲ በትግርኛ ስጦታ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ በሰሜን አሜሪካ ቅርጫፍ ለመክፈት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ገልጿል።

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

ሁለቱ እውቅ አርቲስቶች በእግርኳስ አመራርነት ተመረጡ ።የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል ። በፕሬዝዳንትነት የቀድሞውን አልቢትር ኢንጂነር ሀይለየሱስ ፍሰ...
05/12/2024

ሁለቱ እውቅ አርቲስቶች በእግርኳስ አመራርነት ተመረጡ ።

የአዲስአበባ እግርኳስ ፌደሬሽን ዛሬ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጧል ።

በፕሬዝዳንትነት የቀድሞውን አልቢትር ኢንጂነር ሀይለየሱስ ፍሰሃን መርጧል ። ለፕሬዚዳንትነት ከድሞው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የባንኮች ፣ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና ተጨዋች ከነበረው አንተነህ ፈለቀ ብርቱ ፏክክር እንደገጠማቸው ተነግሯል ።

9 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያካተተው ምርጫው በምክትል ፕረዚዳንትነት ተዋናይነት ማስተዋል ወንደሰንን መርጧል ።

አርቲስት ሀረገወይን አሰፋ ደግሞ በአቃቤ ነዋይነት መመረጧን የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታውቋል ።

# #ማኛአዲስ 2017

እንኳን ለሊቀ መላኩ ቅዱስሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። #ማኛአዲስ 2017 Addis
21/11/2024

እንኳን ለሊቀ መላኩ ቅዱስሚካኤል አመታዊ የንግስ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ማኛአዲስ 2017
Addis

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካን መረቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል...
20/11/2024

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካን መረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል የተገነባውን ኢትኖ ማይኒንግ የወርቅ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ኢትኖ ማይኒንግ የአኮቦ ሚኒራልስ ኩባንያ መጋቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ኩባንያው በስካንዲኔቪያን ሀገራት መሠረቱን ያደረገ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በኩል ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ወርቅ ፍለጋ እና ማውጫ ላይ የተሰማራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አኮቦ ወረዳ በተከናወነው ትርጉም ባለው የኢንቨስትመንት ሥራም ለሁሉም አካላት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ባለፉት ሶስት አስርት ዓመታት በአኮቦ የምትገኘው ዲማ ከተማ በአነስተኛ ባሕላዊ የወርቅ ማዕድን ማውጣት ሒደት ለብዙ ጊዜ ብክነት የተሞላበት አሠራር መቆየቱን አስታውሰዋል።

ይህ አዲስ ኢንቨስትመንት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ እና ደረጃውን የጠበቀ የወርቅ ምርት ከማስገኘቱም በላይ በሕገ-ወጥ የማዕድን ሥራ ለተጋረጠው ፈተና ምላሽ ይሰጣል ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለጋምቤላ ክልል ዘላቂ ልማት በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት ለሕዝቡ እና ለክልሉ ጠቀሜታ ለማዋል ያለውን ተነሳሽነት እንደሚያሳይም ነው ያስረዱት፡፡

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

 ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።አየር መንገዱ ዝርዝር...
18/11/2024



ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

አየር መንገዱ ዝርዝር መስፈርቱንና የምዝገባ ቦታዎችን ያሳወቀ ሲሆን ለአዲስ አበባ ከተማ አመልካቾች ከታች ያለውን የኦንላይን የመመዝገቢያ ቅፅ ይፋ አድርጓል።

ለመመዝገብ (አዲስ አበባ)👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/eaa/applocation-for-local

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

በዛሬው እለት በመርካቶ የሚገኙ የተለያዩ የገበያ ማዕከላት ተዘግተው መዋላቸውን ባደረገው ቅኝት ማየት ችለናል። የመርካቶ ገበያም ከዚህ ቀደም ከነበረው የንግድ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መዋሉን ነጋ...
18/11/2024

በዛሬው እለት በመርካቶ የሚገኙ የተለያዩ የገበያ ማዕከላት ተዘግተው መዋላቸውን ባደረገው ቅኝት ማየት ችለናል።

የመርካቶ ገበያም ከዚህ ቀደም ከነበረው የንግድ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዞ መዋሉን ነጋዴዎች ተናግረዋል።

ተዘግተው ከዋሉት የገበያ ማዕከላት መካከል
ሚሊተሪ ተራ ፤ ዱባይ ተራ ፤ አድማስ እና አመዴ ገበያ አካባቢ የሚገኙ ሱቆች ይገኙበታል።

ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን የዘጉት ከደረሰኝ ጋር በተገናኘ ውዝግብ መሆኑ ታውቋል።

ነጋዴዎቹ ዛሬ ጠዋት በርካታ የንግድ ሱቆች ዝግ እንደነበሩ የተናገሩ ሲሆን በከሰአቱ የገበያ ሁኔታ አንዳንድ ሱቆች እንደተከፈቱ ገልፀዋል።

# #ማኛአዲስ 2017

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏልበከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክ...
15/11/2024

የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የወጣ ወጣት በተአምር ህይወቱ ተርፏል

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የወጣ ወጣት ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው ወጣቱ ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም በማለቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳድር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ በተአምር ህይወቱን ታድገዋል፡፡የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

ሙዚቀኛ መሰለ አስማማው አረፈለ20 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስመጥር የክራር ተጫዋች እና አቀናባሪ የነበረው መሰለ አስማማው ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። ሙዚቀኛ መሰለ...
12/11/2024

ሙዚቀኛ መሰለ አስማማው አረፈ

ለ20 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስመጥር የክራር ተጫዋች እና አቀናባሪ የነበረው መሰለ አስማማው ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። ሙዚቀኛ መሰለ ባደረበት ህመም ለወራት በህክምና ሲረዳ ቆይቶ አርፏል ።

# #ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

ሰዎች ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ   ሆስፒታል እንደሚመጡ ተገለጸ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ስር ያለው ብሔራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል በዓመት ለ100 ሰዎች የንቅለ ተከ...
10/11/2024

ሰዎች ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እንደሚመጡ ተገለጸ

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ስር ያለው ብሔራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል በዓመት ለ100 ሰዎች የንቅለ ተከላ ህክምና የመስጠት አቅም ቢኖረኝም የግብዓት እጥረት አለብኝ ብሏል

የአካል ልገሳ ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው የሚሉት ዶክተር ጸጋይ ኩላሊታችንን መሸጥ እንፈልጋለን፣ ኩላሊታችንን ግዙን የሚሉ ዜጎች ወደ ማዕከሉ እንደሚመጡም አክለዋል፡፡

# #ማኛአዲስ 2017

አንጋፋው ጋዜጠኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ ዴቼ ቬለን ለረዥም ዓመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ፤ ለረዥም ጊዜያት በህመም ተይዞ ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ...
10/11/2024

አንጋፋው ጋዜጠኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ዴቼ ቬለን ለረዥም ዓመታት ያገለገለው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን ፤ ለረዥም ጊዜያት በህመም ተይዞ ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት እስራኤል ቴል አቪቭ ዛሬ ጠዋት ማለፉን ከልጁ ቢታንያ ዜናነህ ተሰምቷል ።

የዜናነህ መኮንን የቀብር ሰነ ስረዓት ቴል አቪቭ ውስጥ በሚገኝ ያኮም መካነ መቃብር እንደሚፈጸም ልጁ ቢታንያ ዜናነህ መግለጿን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል ። ዜናነህ ባለትዳር እና የሶስት ሴቶች ልጆች አባት ነበር ።

# #ማኛአዲስ 2017

ልደቱ አያሌው ከቀዶ ህክምና በኋላ ወደ ቤቱ መግባቱን አስታወቀበጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ...
10/11/2024

ልደቱ አያሌው ከቀዶ ህክምና በኋላ ወደ ቤቱ መግባቱን አስታወቀ

በጭንቀት ላይ ለሰነበታችሁ ዘመድ ወዳጆቸ እና የትግል አጋሮቸ በሙሉ።ለገጠመኝ የጤና ችግር ከአንድ ቀን በፊት የተካሄደልኝ የቀዶ ጥገና ህክምና በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። የፈጣሪ ፈቃድ ሆኖ አሁን ላይ ጤናየ በጥሩ ሁኔታ ስለሚገኝም ከሆስፒታል ወጥቸ ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ።

ስለ ደህንነቴ ተጨንቃችሁ በፀሎትና በሀሳብ ስታግዙኝ ለሰነበታችሁ ወዳጅ ዘመዶቸ በሙሉ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። አሁን ረዥም ጊዜ የፈጀው የህክምናየ ሂደት በመጠናቀቅ ላይ ነው። ስለሆነም ወደ አገሬ ተመልሸ ለመሄድ የነበረኝ ከፍተኛ ፍላጐትና ጉጉት ዕውን ሊሆን በመቃረቡ ደስ ብሎኛል።

ከአክብሮት ጋር
ልደቱ አያሌው
ህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም

# #ማኛአዲስ

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው በአፍሪካ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል። 🇪🇹 # #ማኛአዲስ 2017
05/11/2024

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነው በአፍሪካ የመጀመሪያው ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ዛሬ ኢትዮጵያ ገብቷል።

🇪🇹

# #ማኛአዲስ 2017

 በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4....
02/11/2024



በዓለም አቀፍ ደረጃ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የ ' የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ / USGS ድረገጽ ' ከአዋሽ 29 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ዛሬ ሌሊት 6:04 በሬክተር ስኬል 4.7 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ገልጿል።

ትላንትና ለሊት ላይ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 4.6 ነበር የተመዘገበው ፤ የዛሬው 4.7 ነው የተመዘገበው።

# #ማኛአዲስ

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ!የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለው...
02/11/2024

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል በዚህም መሰረት መገናኛ ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ከመገናኛ - ቃሊቲ ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች ወደ መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በጊዜያዊነት ተዛውሯል፡፡

ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች ደግሞ አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ - ገርጂ ፣ ከመገናኛ-ጎሮ ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው በመረጃው አስታውቋል።

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

01/11/2024

ዛሬ ምሽት 3:55 ላይ በአፋር ክልል ፣ ' አዋሽ ' አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር ከነዋሪዎች የመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

አንድ የአዋሽ ነዋሪ ፤ " የዛሬውስ በጣም ያስፈራ ነበር " ሲል ሁኔታውን ገልጾታል።

ሌላ ነዋሪው ፥ " በጣም ነው ያስደነገጠን ከባለፉት አንጻር ዛሬ በጣም ነው የተሰማው አላህ ይጠብቀን " ብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ዘልቆ መሰማቱንም ከነዋሪዎች የሚመጡት መልዕክቶች ያስረዳሉ።

እንደ ' አሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ' መረጃ ከአዋሽ በምዕራብ በኩል 8 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር።

በሬክተር ስኬል 4.6 የተመዘገበ እንደሆነ ጠቁሟል።

ዝርዝር መረጃ ከባለሞያዎችን እንደሰማን የምናቀርብ ይሆናል።

# #ማኛአዲስ

ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ...
01/11/2024

ዛሬ በኮንታ በደረሰ የመሬት መሸራተት አደጋ 6 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

መረጃው በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ነው።

# #ማኛአዲስ 2017

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀጥቅምት 21 ቀን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር...
31/10/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሃሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

ጥቅምት 21 ቀን በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል እንዳይበር ተከልክሏል የሚል መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ተመልክተናል ብሏል አየር መንገዱ።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራን አየር ክልል እንዲጠቀም ከኤርትራ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የተሰጠው እና የኤርትራ አየር ክልልን ለመደበኛ በረራ እየተጠቀመ መሆኑን እረጋግጦ በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተገለፀው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል።

#ማኛአዲስ 2017
Magna Addis

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጡ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ተሸለመ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ...
30/10/2024

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምርጡ የአፍሪካ አየር መንገድ በሚል ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው APEX Passenger Choice Awards 2025፣ ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ “Best Overall in Africa award” በሚል ተሸልሟል፡፡

አየር መንገዱ በዚህ የሽልማት አሰጣጥ መርሓ ግብር ላይ በምርጥ የበረራ ላይ መስተንግዶ፣ በምርጥ የበረራ ላይ መዝናኛ አገልግሎት፣ በምርጥ የበረራ ላይ የምግብ እና መጠጥ አገልግሎት፣ በምርጥ የአውሮፕላን ውስጥ መቀመጫ ምቾት እንዲሁም በምርጥ የበረራ ላይ ገመድ አልባ ኢንተርኔት አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ምርጡ አየር መንገድ በመሆን ተሸልሟል።

# #ማኛአዲስ 2017

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Magna Addis posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share