ስለ ጋዜጠኝነት -All about Journalism

  • Home
  • ስለ ጋዜጠኝነት -All about Journalism

ስለ ጋዜጠኝነት -All about Journalism This page is for students , journalists , those professional related to Media.

11/03/2022

World Radio Day

10/03/2022
10/03/2022

JUST OUT! UNESCO's global report on finds the business model of the news media is broken and our fundamental right to information at risk. It's time to stand up for and protect journalism! Read more: https://on.unesco.org/3CvNm3z

10/03/2022

Journalism is the strong voice against the
Injustice.

How social media helped women's rights?✓ Tackling violence against women through social media tools: Social media tools ...
08/03/2022

How social media helped women's rights?
✓ Tackling violence against women through social media tools: Social media tools have helped female victims to share their experiences of violence with other victims, creating a space to exchange knowledge and information on their rights, legal processes and welfare services.

ማህበራዊ ሚዲያ የሴቶችን መብት በማስጠበቅ እንዴት ረዳ?✓ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማህበራዊ ሚዲያ መሳሪያዎች በመታገዝ መከላከል ይቻላል፡- የማህበራዊ ሚዲያ መሳሪያዎች ሴት ተጎጂዎች...
08/03/2022

ማህበራዊ ሚዲያ የሴቶችን መብት በማስጠበቅ እንዴት ረዳ?
✓ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማህበራዊ ሚዲያ መሳሪያዎች በመታገዝ መከላከል ይቻላል፡- የማህበራዊ ሚዲያ መሳሪያዎች ሴት ተጎጂዎች የጥቃት ልምዳቸውን ለሌሎች ተጎጂዎች እንዲያካፍሉ ረድቷቸዋል፣በመብቶቻቸው፣ህጋዊ ሂደቶች እና የበጎ አድራጎት አገልግሎቶች ላይ እውቀትና መረጃ ለመለዋወጥ የሚያስችል ቦታ ፈጥሯል።

06/03/2022

አንዳንዴ ጥልቀት ያለው ዘገባ ወይም የፕሮጀክት ዘገባ እየተባለ የሚጠቀሰው የምርመራ ጋዜጠኝነት ከ‹ሊክ ጆርናሊዝም› ወይም በተለይ የፖለቲካ ሥልጣን ላይ ካሉ ሰዎች የሚገኙ ሰነዶችና ሐሳቦች በመጠቀም ከሚሠራው ሥራ ጋር መቀላቀል ተገቢ አይደለም። በእርግጥ ዴሞክራሲ ብቅ እያለ ባለባቸው አካባቢዎች፣ ትርጉሙ አሻሚ ሊሆን ይችላል። በዚህም መሠረት በድብቅ የወጡ ሰነዶችን ያካተተ ወይም ወሳኝ የሆነ ዘገባ ሁሉ የምርመራ ዘገባ ተብሎ ሊጠራ ይችላል። በተመሳሳይ ወንጀል ወይም ሙስና ላይ ያተኮረ ዘገባ፣ ትንታኔ ወይም ወጣ ያሉ ዕይታዊ ጽሑፎች ጭምር በስህተት የምርመራ ዘገባ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ።

በሙያው አንጋፋ የሆኑ አሠልጣኞች እንደሚሉት፣ ምርጥ የሚባል የምርመራ ጋዜጠኝነት በጥንቃቄ የተመላ ዘዴ፣ ከመጀመሪያ ደረጃ ምንጭ የተገኙ መረጃዎች ላይ መሠረቱን የጣለ፣ መላምት ያለውና ያንንም የሚፈትሽ እንዲሁም ማስረጃዎችን በተደጋጋሚ ማጣራትን የሚያካትት ነው። መዝገበ ቃላቱም ‹ምርመራ› የሚለውን ቃል ‹ሥልታዊ ምርምር› ሲል ይተረጉመዋል። ይህም በአንድ ቀን ወይም በኹለት ቀን ተሠርቶ የሚጠናቀቅ አይደለም፤ ሰፊ ምርመራ ጊዜን ይፈልጋል።

በዘርፉ ለአዳዲስ ዘዴዎች ጥርጊያ የሚሆኑ ነጥቦች አሉ። ለምሳሌ በ1990 ኮምፕዩተሮችን መጠቀም ለመረጃ ትንተና እና ምልከታ ረድቷል። ‹‹የምርመራ ዘገባ አዳዲስ ዘዴዎችንና ነገሮች በአዲስ መንገድ እንዴት ማድረግ እንደሚቻል ያስተምራልና ጠቃሚ ነው።›› ይላሉ፣ ለምርመራ ዘጋቢዎችና ባለሞያዎች ዋና አዘጋጅ ሆነው ለዓመታት ያገለገሉትና በኢሊኖይስ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት ክፍል መሪ ብራንት ሆስተን። አክለውም አሉ፤ ‹‹እነዛ ዘዴዎች ሲሰርጹ በእለታዊ አዘጋገብ ላይም ይካተታሉ። እናም በምርመራ ጋዜጠኝነት መነሻነት በጠቅላላ የሙያውን አጥር እያሰፋን እንሄዳለን›› ብለዋል።

06/03/2022

አንዳንድ ጋዜጠኞች ሁሉም ዘገባ የምርመራ ዘገባ ነው ብለው ይሞግታሉ። ይህ በእርግጥ እውነትነት አለው። አንዳንድ የምርመራ ዘዴዎችን በሥራቸው የመጨረሻ ሰዓታት ላይ የሚገኙና በአንድ ጉዳይ ላይ አተኩረው የሚሠሩ ጋዜጠኞች ይጠቀሙታል። እንዲሁም የምርመራ ዘገባ ቡድን አባላት አንድን ዘገባ ለመሥራት ባላቸው አጭር ጊዜ ሊጠቀሙት ይችላሉ። ግን የምርመራ ጋዜጠኝነት ከዚህ በእጅጉ ይሰፋል። የጥበባዊ አሠራሮች አንድነት ሲሆን፣ በዘርፉ ብቁ ለመሆንም ዓመታትን የሚጠይቅ ነው።

በምርመራ ጋዜጠኝነት ከፍተኛ ሽልማቶችን ያገኙ ዘገባዎች፣ ሙያው ምን ያህል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ያለ ጥናታዊ ምርምርና አዘጋገብ እንደሚፈልግ ማሳያ ናቸው። እነዚህም የተዘረፈ የሕዝብ ገንዘብ፣ ሥልጣንን ያለአግባብ መጠቀም፣ የአካባቢ ብክለት፣ የጤና ዘርፍ ላይ ያሉ አሳፋሪ ጥፋቶችንና መሰል ሌሎች ጉዳዮችን የሚከተሉና ጥልቅና በጥንቃቄ የተመሉ ምርመራዎች ናቸው።

የምርመራ አዘጋገብን በሚመለከት የተለያዩ ትርጓሜዎች ይሰጡ እንጂ፣ አዘጋገቡ በሚያካትታቸው ነጥቦች ዙሪያ ግን የጋዜጠኝነት ባለሞያዎች ልዩነት የላቸውም። ይልቁንም ሥልታዊ፣ ጥልቀት ያለው፣ ያል...
06/03/2022

የምርመራ አዘጋገብን በሚመለከት የተለያዩ ትርጓሜዎች ይሰጡ እንጂ፣ አዘጋገቡ በሚያካትታቸው ነጥቦች ዙሪያ ግን የጋዜጠኝነት ባለሞያዎች ልዩነት የላቸውም። ይልቁንም ሥልታዊ፣ ጥልቀት ያለው፣ ያልተቀዳ ጥናትና ዘገባ፣ ብዙ ጊዜ በምስጢር የተያዙ ጉዳዮችን የሚያጋልጥ ነው በሚለው ላይ ይስማማሉ። ሌሎች ደግሞ ተግባራዊነቱ ላይ የሕዝብ የሆኑ መዝገቦችንና መረጃዎችን በከፍተኛ ደረጃ አካትቶ አትኩሮቱ ማኅበራዊ ፍትህና ተጠያቂነት እንደሆነ አጽንዖት ይሰጣሉ።

በዩኔስኮ የታተመ ‹ስቶሪ ቤዝንድ- ኢንኳየሪ› የተሰኘ የምርመራ ጋዜጠኝነት መመሪያ መጽሐፍ፣ የምርመራ ዘገባን እንደሚከተለው ይተረጉመዋል፤ ‹‹የምርመራ ጋዜጠኝነት ኃይል ባለው ሥልጣን ሆነ ተብሎ አልያም በድንገት በእውነታዎች መደበላለቅና ለመረዳት ግልጽ ባልሆኑ ሁኔታዎች የተደበቁ ጉዳዮችን ለሕዝብ መግለጥን ያካትታል። በምስጢር የተያዙ እንዲሁም በግልጽ የሚገኙ ምንጮችንና ሰነዶችን መጠቀምንም ይጠይቃል።››

በተጓዳኝ የ‹ደች- ፍሌሚሽ› የምርመራ ጋዜጠኝነት ማኅበር (VVOJ) የምርመራ ዘገባን በቀላሉ ‹ወሳኝ እና ጥልቀት ያለው ጋዜጠኝነት› ሲል ይተረጉመዋል

Calling all English-speaking journalists globally! Tsinghua University is offering a master of arts degree in global bus...
05/03/2022

Calling all English-speaking journalists globally! Tsinghua University is offering a master of arts degree in global business journalism. Scholarships are available.
🗓️ Deadline: April 1
https://buff.ly/3IBVlP5

English-speaking journalists worldwide can apply for a global journalism program in China. The School of Journalism and Communication at Tsinghua University offers a master of arts degree in global business journalism, which seeks to train future journalists who can help the public understand the co...

Quick tips for being a smarter reporterBy Greg HardestyBe a human being first, and a reporter second. This especially ap...
05/03/2022

Quick tips for being a smarter reporter

By Greg Hardesty

Be a human being first, and a reporter second. This especially applies when covering tragedies. Show empathy. Keep your notebook and pen out of sight until after you look a person in the eye and introduce yourself, and chat briefly. Make a connection, then get to work.

Listen, listen, listen. You will get your best material by shutting up and not interjecting often when a source is talking. You can interact, of course, but keep it to a minimum.

Clearly explain the angle of your story before you interview someone, including when the story will run (if you know). People feel more comfortable when you spell things out to them however briefly.

Always get a phone number/email to confirm facts. This is crucial. Never get out of the habit of fact-checking (from a printout of your story; never from the computer screen). Also, you never know when you will need an extra quote or more information from your source. So you better know how to reach them.

On especially tight deadlines, use e-mail. When sources aren't being exactly helpful, urge them to collect their thoughts and send you them in an e-mail that you later can use for quotes. This works wonders,

Never be afraid to ask someone to repeat what they have said. Your source wants you to get things right. So get things right. Don't feel shy about re-confirming even the most basic stuff (i.e., name spelling).

Reconfirm facts via research. For example, go on the Internet to confirm the full, official name of an organization to which a source belongs. People often speak in shorthand. It's your job as a journalist to confirm all factual stuff in your story. Get things right.

Urge your source to let you know what they thought of your story. Doing so makes a source feel as if he or she is part of a team (in a sense) and sometimes leads to great follow-up story ideas. Don't act like some snobbish reporter on high who is immune from criticism (and praise, too, for that matter).

Think visually when writing. Visualize a story like a movie in your head. Try to place the reader at a scene. You can still do this, to a degree, when writing straight news — even briefs. Don't get lazy just because your story may be short,.

When writing, pay attention to the rhythm of the words. Read your story out loud if you must, but good writing should be inviting to read — it should be effortless and pleasing, like listening to a favorite song. Good stories should have zest, bounce and energy.

Remember: If you are bored with your story, your reader will be doubly bored. Attack each story by challenging yourself: How can I make this the most interesting story possible? How can I grab the throat of my reader?

Always cultivate story ideas. Urge sources to call you if they ever think they may have a good story for you — even if it has nothing to do with the story you are working on when you talk to them. And when going about your daily lives outside of work, do the same if the subject of what you do comes up. Use the eyes and ears of the community to your advantage.

________________________________________

Greg Hardesty has been a journalist for nearly 20 years, Hardesty also teaches journalism at Cal State Long Beach. Prior to joining the Register, Hardesty was a copy editor and page designer for the Glendale News Press and Daily Pilot. He also has worked as a copy editor for the Japan Times in Tokyo and has reported for business lifestyle magazines in Orange County.

ከግራ ወደ ቀኝ ተስፋዬ ገሠሠ-ከፍተኛ የትያትር ጥበብ መምህርና ባለሙያ በዓሉ ግርማ የላቀ ደራሲና ጋዜጠኛ አሳምነው ገብረወልድ እጅግ ታዋቂ የሬዲዮ ጋዜጠኛ
05/03/2022

ከግራ ወደ ቀኝ ተስፋዬ ገሠሠ-ከፍተኛ የትያትር ጥበብ መምህርና ባለሙያ በዓሉ ግርማ የላቀ ደራሲና ጋዜጠኛ አሳምነው ገብረወልድ እጅግ ታዋቂ የሬዲዮ ጋዜጠኛ

አንጋፋ ጋዜጠኛ፤ ሙዚቀኛ፤ ፤ ታላቅ ምሁር፤ የፓን አፍሪካኒዝም ታጋይ፤ ዲፕሎማት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ሲታወሱ  ===============================ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ትውልዳ...
05/03/2022

አንጋፋ ጋዜጠኛ፤ ሙዚቀኛ፤ ፤ ታላቅ ምሁር፤ የፓን አፍሪካኒዝም ታጋይ፤ ዲፕሎማት ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ሲታወሱ
===============================

ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ ትውልዳቸው በአዲስ አበባ ነው፡፡ ምርጥ እና አንጋፋ ጋዜጠኛ፤ ሙዚቀኛ፤ ፤ ታላቅ ምሁር፤ የፓን አፍሪካኒዝም ታጋይ፤ ዲፕሎማት…ናቸው፡፡

እኝህ ታላቅ የኢትዮጵያ ምሁር የመጀመርያው አንጋፋ ጋዜጠኛ ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ፕሮፌሰሩ ሙዚቃ ይወዳሉ፡፡ መውደድ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ሙዚቃ መሳርያዎችንም ይጫወታሉ፡፡ ጊታር ፣ሳክስፎን እና ፒያኖ የሚጫወቱት ፕሮፌሰሩ በተለይ ከበሮ በእጆቻቸው ሲጫወቱ ልዮ ናቸው፡፡
ከበሮ የሙዚቃ መቀደሻ መሳርያ ነው፡፡ ከበሮ የሰው ልጅ የመጀመርያው መልዕክተኛ ነው፡፡ ቆየት ያሉ ሙዚቃዎችን ይወዳሉ።

አማርኛ፣እንግሊዘኛ፣ፈረንሳይኛ እና ጣሊያንኛን በደንብ አቀላጥፈው የሚናገሩት ፕሮፌሰሩ አረብኛ እና ራሺያንኛ ይሞክራሉ ። ከ26 የሚበልጡ ዶክመንታሪ ፊልሞችንም ሰርተዋል፡፡

ቤተሰባቸው

አባታቸው የሙዚቃ ሊቅ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ የአባታቸው የጊታር እና የቫዮሊን ተማሪ ነበሩ፡፡ አሜሪካዊ የሆኑት እኝህ ወላጆቻቸው

በ1923 የንጉሱ የዘውድ በዓልን ለማክበር እና ኢትዮጵያን ለመርዳት ከመጣው የካሪቢያን ቡድን ጋር አብረው ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡ ትዳር መስርተውም ዮሴፍ ኃይለስላሴ ፎርድ እና አብይ ፎርድን ወልደው ኑሮአቸውን በኢትዮጵያ ቀጥለዋል፡፡

ትምህርታቸውና የሙያ አገልግሎታቸው

ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን እናታቸው ባሰሩት ቤተ-ኡራኤል በኃላ ላይ ልዕልት ዘነበወርቅ በተባለው የአፀደ ህፃናት እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፤2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሊሴይ ገ/ማሪያም ከተማሩ በኃላ ስኮላርሽፕ አግኝተው ወደ አሜሪካ ሚሲሲፒ አቀኑ፡፡

በዚያም በፓኔ ውድስ ጁኒየር ኮሌጅ በኢለመንታሪ ኢዱኬሽን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

በማስከተልም ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሰቲ ስኩል ኦፍ ጀኔራል ስተዲስ በፊልም ጥናቶች /Directing track and scholarship or criticism track/ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ወይም ማስተሬት ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል፡፡

በሃዋርድ ዩኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርንትን ማዕረግ እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ለ33 አመታት ያህል ሰርተዋል፡፡በቆይታቸውም በዩኒቨርሰቲው በኮምኒኬሽን ዲፓርትመንት የሬዲዮ፣ቴሌቪዥን እና ፊልም ትምህርት እንዲሰጥ አድርገዋል፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥም እንደ እነ ሀይሌ ገሪማ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንዲያስተምሩ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡

ፕሮፌሰር አብይ ፎርድ የቀድሞው የአ.አ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምኒኬሽን የድህረ ምረቃ ት/ቤት ዲን፤ የዩኒቨርስቲው ፐሬዚዳንት ፅ/ቤት ከፍተኛ የአለም አቀፍ ሚዲያዎች አማካሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በተጨማሪም በዩኒቨርስቲው የስነ ጥበባት እና ፊልም ት/ቤት ልዩ አማካሪ እና በዩኒቨርስቲው የፊልም ጥናት ክፍል ለመጀመር የተደራጀው ግብረ ሀይል አማካሪ ነበሩ፡፡

ፕሮፌሰሩ በአሜሪካ አየር ሀይል ኤሮ አክቲቪቲ በፓይለትነት አገልግለዋል ከዚህም ባሻገር የኢትዮ- አሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

ነብይ መኮንንን ስለፕሮፌሰሩ

… ይህን ያህል ተምሮ ምን ሰርትዋል ? ምንስ ሆኖ አገልግልዋል ? ማለት መቼም ያባት ነው :: የሰራው ስራ ሲደረደር ያስደነግጣል :: አንዳንዶቻችን በእድሜያችን እዚህ ትግባ የማትባል ትንሽ ስራ ያስመዘገብን እንደሆነ የአለምን ሪኮርድ የሰበርን ይመስል ዘራፍ ማለትን እንደባህል ሰልጥነንበታልና እንደው የጨዋ ቢሆነን ፕሮፌሰር የሰራበትን ቦታና ሙያ ብደረድረው መልካም መሰለኝ ::

*የማስ ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂና የአፍሪካና የ 3ተኛው አለም የልማት ጽንሰ ሀሳብ ስፔሻሊስት ::

*በአሜሪካን አየር ሀይል ዲሲ ስኳድሮን ዋና ፓይለትና የኤሮኖቲክስ ኢንስትራክተር :: የሞሽን ፓክስቸርስና የቴለቪዥን መሀንዲሶች ማህበር የቀድሞው አባል :: የአፍሪካውያን የመላው አለም የፊልም ስራዎች የቪድዮግራፊክስ ፌዴሬሽን መስራችና የአደራጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ::

*የፓን አፍሪካን ሲኒስጽ ፌዴሬሽን አባል ::

*የዋሽንግተን ዲሲ የት /ርት ቦርድ የመገናኛ ብዙሀን አማካሪ ::

*የቀድሞ የፖዘቲቭ ኢንኮርፖሬሽን ፕሬዚዳንት ::

*የሰምና ወርቅ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር ::

*በቡርኪና ፋሶ ኡጋዱጉ በሚገኘው የጥቁር ኢንስቲትዩት በሚባለው ተቋም ውስጥ የአለም አቀፍ የስራ አመራር አባል ::

*የፋና ፕሮዳክሽንስ ፕሬዚዳንት ::

*የወርልድ ስፔስ አማካሪ ::

*የሚግኖ ሎራን ኢኒስ ፎርድ ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት :: ሌላም ሳይጽፍ የተዋቸው መአት አሉ .....

ምስጋና እና ምንጭ
ጌጡ ተመስገን
ግሩም ሰይፉ
Habeshawi
mekilit.blogspot.com
Tofik Hussen
ገጣሚ፤ ጋዜጠኛ እና ተርጓሚ ነብይ መኮንን በአሜሪካ የተሳካላቸው አበሾች አሉ በሚል ከፃፈው ማስታወሻ

ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ጥቅምት 12 ቀን 1923 ዓ.ም. በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ውድነህ ተፈሪና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ የተወለዱት ማሞ ውድነህ፣ ...
05/03/2022

ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ

ጥቅምት 12 ቀን 1923 ዓ.ም. በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ውድነህ ተፈሪና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ የተወለዱት ማሞ ውድነህ፣ ወደ ስነ ጽሁፉ ዓለም በመዝለቅ (በተለይ በስለላ ሥራ ላይ ያተኮሩ) 53 መጻህፍትን ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ወደ አማርኛ በመተርጎም ለአንባቢያን አድርሰዋል።

📖✍️📘

በፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ወቅት ገና በልጅነታቸው ወላጆቻቸውን ያጡት ማሞ፣ የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት በ15 ዓመት እድሜያቸው እንደነበር ታሪካቸው ያስረዳል፡፡

📖✍️📘

በ1948 ዓ.ም. ልብወለድ ጽሁፎች መጻፍ የጀመሩት ደራሲ እና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ፣ የመጀመርያ ጽሑፋቸው ባለ 160 ገጽ የሆነውና በትያትር መልክ የተተወነው ‹‹የሴትዋ ፈተና - አለፈ በደህና›› የሚል ነበር፡፡ በ1960 ዓ.ም. ‹‹ብዕር እንደዋዛ›› በሚል ርእስ ባሳተሙት የግጥም መጽሐፋቸው ታሪክንና መንፈሳዊነትን ለወጣቶች አስተምረውበታል፡፡

📖✍️📘

ደራሲ ማሞ ውድነህ ቀደምት ከሆኑት ጋዜጠኞች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ‹‹ፖሊስና እርምጃው›› የተባለው ጋዜጣ መሥራችና ዋና አዘጋጅም ነበሩ። ከቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ለረጅም ዓመታት ሰርተዋል።

📖✍️📘

ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ፣ ወደ ሥነ ጽሑፉ ዓለም በጥልቀት እንዲገቡ ምክንያት የሆናቸው አጋጣሚ የተፈጠረው በ1952 ዓ.ም. ነበር፡፡ በወቅቱም እርሳቸው ‹‹የኢትዮጵያ ድምፅ›› ጋዜጣ ላይ ‹‹የት ትገኛለች?›› በሚል ርዕስ ለጻፉት መጣጥፍ ዕውቁ ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ‹‹እሱስ የት ይገኛል?›› በማለት የሰጠው የሚል ምላሽ ለረጅም ጊዜ አከራክሯቸዋል፡፡

የጽሑፍ እሰጥ አገባው በወንዶችና ሴቶች መካከል ያለውን የወግ ልዩነት አስመልክቶ የተደረገ ሙግት ነበር፡፡ በወቅቱ በስፋት ተነባቢ በነበረው በዚሁ ጋዜጣ የቀጠለው ክርክር እስከ መንግሥት ባለሥልጣናት ድረስ አነጋጋሪ ለመሆን እንደበቃ ይነገራል፡፡

ክርክሩ የበርካቶችን ቀልብ በመሳቡ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አቶ መኰንን ሀብተ ወልድ ‹‹ጉዳዩ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው›› በማለት መጠናት አለበት ብለው አምባሳደር ዘውዴ ረታ ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞና ኮሚቴው ሁለቱንም ተከራካሪዎች ጠርቶ ባነጋገራቸው ወቅት ‹‹ፊት ለፊት ቢገናኙ ይገዳደላሉ›› ተብሎ በሕዝቡ ይናፈስ በነበረው ወሬ ምክንያት ፖሊስ በመካከላቸው ቢገኝም ባለጉዳዮቹ ማሞ ውድነህና ጳውሎስ ኞኞ ተሳስቀው መሳሳማቸው የኮሚቴውን አባላት ያስደነቀ አጋጣሚ እንደነበር ደራሲ ማሞ በህይወት በነበሩበት ጊዜ ተናግረዋል።

📖✍️📘

ደራሲ እና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ በ‹‹የካቲት›› መጽሔት ላይ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ‹‹የአገራችንን የባህል ልብስ ለብሰው ቢታዩስ?›› በሚል ርዕስ ያቀረቡት አስተያየት የመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ የነበሩት አንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ማዕረጉ በዛብህ 150 ብር እንዲቀጡ ምክንያት ሆኗል፡፡

📖✍️📘

ከባለቤታቸው ከወ/ሮ አልማዝ ገብሩ ጋር ከ50 አመት በላይ በትዳር ያሳለፉት ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ አሁን ላለው ትውልድ ትልቅ ተምሳሌት ስለመሆናቸው በሚያውቋቸው ሰዎች የሚመሰከርላቸው ሰው ናቸው።

‹‹በትዳር ለረዥም ጊዜ ለመኖርዎ ምስጢሩ ምንድነው?›› ተብለው ተጠይቀው ሲመልሱም፣ ‹‹መተማመንና መቻቻል›› በሚል በአጭሩ የገለጹት ደራሲ እና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ፣ ልጆቻቸው አንድም ቀን ጭቅጭቅ ሰምተው እንደማያውቁ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡ ‹‹ችግር ሲኖር ቤት ቆልፈን እንነጋርበታለን›› በማለት ልጆቻቸው ክፉ ቃል ሳይሰሙ ማደጋቸውን ተናግረዋል፡፡

ስድስት ልጆችና 10 የልጅ ልጆችን ለማየት የበቁት ደራሲ እና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ‹‹ሀብታችን ልጆቻችን ናቸው›› በማለት በኩራት የመናገር ልምድ ነበራቸው፡፡ በመጨረሻም ባደረባቸዉ ሕመም ምክንያት የካቲት 23 ቀን 2004 ዓ.ም በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

📖✍️📘

በስለላና በወንጀል ምርመራ ላይ በሚያጠነጥኑ በርካታ የትርጉም ሥራዎቻቸውና ድርሰቶቻቸው የሚታወቁት ደራሲ ማሞ ውድነህ፣ ሥራዎቻቸው ሕዝባዊነትንና ባሕል አክባሪነትን የተላበሱ በመሆናቸው ዘመን ተሻጋሪ ያደርጋቸዋል፡፡

📖✍️📘
የ ዘመኑ ጋዜጠኞች ከደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ምን ይማሩ? ሀሳባችሁን ግለፁልን

አንጋፋው ጋዜጠኛ  እና ደራሲ  አጥናፍ ሰገድ ይልማ ================================አጥናፍ ሰገድ ይልማ ከ 1952 -1972 ድረስ ባሉት ዓመታት  በማስታወቂያ ሚኒስቴር  ...
05/03/2022

አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ
================================
አጥናፍ ሰገድ ይልማ ከ 1952 -1972 ድረስ ባሉት ዓመታት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ከ ጀማሪ ዘጋቢነት እስከ ዋና አዘጋጅነትየሠሩ ሲሆን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅም ነበሩ።

ከ 1972 ዓ.ም በሁዋላም በተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት በሐላፊነት አገልግለዋል።
- ጋሽ አጥናፍሰገድ ከአንጋፋ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ባቋቋሙት ልሣነ ሕዝብ ጋዜጣ እና መፅሔት ከፀሐፊነት እስከ አዘጋጅነት ሠርተዋል።

በጦብያ መፅሔት ላይም አባ ገምባው በተሰኘ የብዕር ሥም በርካታ ፅሁፎችን አስነብበዋል።
ጋሽ አጥናፍ መፅሐፍ ፅፈው አሣትመው ለንባብ ያበቁት ከ 70ኛ ዓመታቸው በሁዋላ ነበር።

በጋዜጦች እና መፅሔቶች ላይ በብዕር ሥም የሚፅፉትን የሚያነቡ ወዳጆቻቸው መፅሐፍ እንዲፅፉ ቢመክሯቸውም ጋሽ አጥናፍሰገድ ግን አልተቀበሏቸውም። ምክንያታቸውም ከታላላቅ የሐገራችን ደራሲዎች እኩል እንዴት ደራሲ ተብዬ እጠራለሁ የሚል ከአክብሮት የመነጨ ፍርሐት ነበር።

በ 1989 ዓመተ ምህረት ያለ ክስ ያለ ፍርድ ታስረው በመጨረሻም በስህተት ነው ተብለው ነፃ ተለቀዋል ። "የበደል ካሳ" የተሰኘ ልብ ወለድ መፅሐፍም ፅፈዋል።

ጋሽ አጥናፍ ሰገድ የጋዜጠኝነት እና የፅሁፍ ሥራን መሥራት ከጀመሩ ከ 50ዓመታት በሁዋላ ፣ ዕድሜያቸው 70 ካለፈ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ "የበደል ካሳ " የተሰኘ መፅሐፋቸውን ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ ብለው ለሕትመት አበቁ።
ከዚህ መፅሐፍ በሁዋላ
-የአቤቶ ኢያሱ አነሳስ እና አወዳደቅ
-የእንስሳት ዓመፅ እና ድርድር
- የሕይወቴ ሚስጥር (ግለ ታሪክ)
-ሐገር የፈታ ሽፍታ
-የፖለቲካ አሽሙር
የተሰኙ መፅሐፍትን እና ሌሎችንም ለንባብ አብቅተዋል።
/ከአዜብ ወርቁ የተወሰደ/

የዘመኑ ጋዜጠኞች ትጋትን: የሙያ ፍቅርን : ማንበብ መመራመርን ተማሩ !!

8 ቱ የምርጥ ጋዜጠኛ መለያ ባሕርያት- # 1 የማወቅ ጉጉትምርጥ ጋዜጠኛ ሁሉንም ነገር ለማወቅ ይጥራል፡፡   # 2 ሐቀኝነትምርጥ ጋዜጠኛ በተፈጥሮ  ሐቀኛ ነው፡፡ # 3 ደፋርምርጥ ጋዜጠኛ ደ...
05/03/2022

8 ቱ የምርጥ ጋዜጠኛ መለያ ባሕርያት-
# 1 የማወቅ ጉጉት
ምርጥ ጋዜጠኛ ሁሉንም ነገር ለማወቅ ይጥራል፡፡
# 2 ሐቀኝነት
ምርጥ ጋዜጠኛ በተፈጥሮ ሐቀኛ ነው፡፡
# 3 ደፋር
ምርጥ ጋዜጠኛ ደፋር ነው፡፡
# 4 ታማኝነት
ምርጥ ጋዜጠኛ ታማኝ ነው፡፡ታማኝነቱ ለህዝብ ነው፡፡ የህዝብ ጠባቂ ነው፡፡
# 5 ትህትና
ምርጥ ጋዜጠኛ ትሁት ነው፡፡ የተለያዩ ምንጮች :የስራ ባልደረቦች እና ሌሎች ሰዎችን በትህትና ይቀርባል፡፡
# 6 እምነት የሚጣልበት
ምርጥ ጋዜጠኛ እምነት የሚጣልበት ሰው ነው፡፡
# 7 ሙያ ወዳጅ
ምርጥ ጋዜጠኛ ሙያውን የሚወድ ነው፡፡
# 8 በራስ መተማመን
ምርጥ ጋዜጠኛ በራስ የመተማመን ስሜት አለው፡፡ በቀላሉ ተስፋ ሊቆርጥ አይችልም፡፡ፈታኝ ሁኔታን ይቋቋማል፡፡

‹‹ጋዜጠኝነት ያለአስተማሪ››‹‹ጋዜጠኝነት ያለአስተማሪ›› መጽሐፍን ያላነበበ እና እውነትም ያለአስተማሪ አንብቦ ያልተረዳ፤ ሥልጠናም ያልሰጠበት በተለይ ጋዜጠኛ ይኖራል አልልም፡፡ የዚህች መጽ...
05/03/2022

‹‹ጋዜጠኝነት ያለአስተማሪ››

‹‹ጋዜጠኝነት ያለአስተማሪ›› መጽሐፍን ያላነበበ እና እውነትም ያለአስተማሪ አንብቦ ያልተረዳ፤ ሥልጠናም ያልሰጠበት በተለይ ጋዜጠኛ ይኖራል አልልም፡፡ የዚህች መጽሐፍ ደራሲ፤ ጋዜጠኛ ላዕከማሪያም ደምሴ ናቸው

የሙያ አጋሮቼ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ስለ ጋዜጠኝነት ሙያ ይህን መጽሐፍ ፈልጋችሁ አንብቡ።Tibebu Belete
05/03/2022

የሙያ አጋሮቼ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ስለ ጋዜጠኝነት ሙያ ይህን መጽሐፍ ፈልጋችሁ አንብቡ።
Tibebu Belete

05/03/2022

Journalism is not a crime it is a profession!
ጋዜጠኝነት ወንጀል አይደለም!

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ሲታወስ‹‹ዳኙ ሊመታ ነው፤ ዳኙ ገላግለን . . . ወይኔ ዳኙ አ – ገ – ባ -፤ ደንሶ አገባ ዳኙ፣ ቀኝ አሳይቶ ግራ፣ ግራ አሳይቶ ቀኝ በጣም አስደናቂ ግብ ነው . . ...
05/03/2022

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ሲታወስ

‹‹ዳኙ ሊመታ ነው፤ ዳኙ ገላግለን . . . ወይኔ ዳኙ አ – ገ – ባ -፤ ደንሶ አገባ ዳኙ፣ ቀኝ አሳይቶ ግራ፣ ግራ አሳይቶ ቀኝ በጣም አስደናቂ ግብ ነው . . . ›› ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ደስታና ሲቃ፣ ስሜትም በተቀላቀለበት ድምፀት ታኅሣሥ 17 ቀን 1980 ዓ.ም. ያስተጋባው ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ነበረ፡፡

በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ሁነኛ ሥፍራ ያለው ደምሴ፣ የስፖርት ዜናዊነቱን የጀመረው ምሥራቃዊቷ ድሬዳዋ ከተማ በአማተርነት እየዘገበ ወደ አዲስ አበባ መላክ በጀመረበት ጊዜ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያና ብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ጋዜጠኛና ‹‹የስፖርት ፋና›› ጋዜጣ መሥራች ከነበረው ታላቁ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ተሰማ ጋር ቅርበት ስለነበረው ከድሬዳዋ የሐረርጌን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየዘገበ ይልክ ነበር፡፡

ኢትዮጵያ 10ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ካስተናገደችባቸው ከተሞች አንዷ ደምሴ ዳምጤ የነበረባት የኖረባት ድሬዳዋ የእግር ኳስ ዘገባ ትሩፋት ያቀረበባትም ነች፡፡ ለአገሪቱ ስፖርት ዕድገት በተለይም እግር ኳሱ እንዲያብብ በሙያው ያደረገው ጥረት ኢትዮጵያውያን ተጫዋቾች ክሂላቸው ከማንም እንደማያንስ በማንፀባረቅ ነበር፡፡ በ1970ዎቹ መጨረሻና በ80ዎቹ መጀመርያ ጎልተው ወጥተው የነበሩት እነሙሉጌታ ከበደ፣ ሙሉጌታ ወልደየስ፣ ገብረመድኅን ኃይሌን ሲያወድስ ገጣሚ ሆኖ በመገኘት ነበር፡፡

‹‹የምን ማራዶና የምን ፔሌ ፔሌ
እኛም አገር አለ ገብረመድኅን ኃይሌ›› ጎልታ የምትጠቀስለት መንቶ ግጥሙ ነበረች፡፡

በዘመኑ እየበረከቱ የመጡት ወጣት ጋዜጠኞች አርአያቸው እንደሆነ የሚናገሩለት ደምሴ፣ ሦስት ኦሊምፒኮች የዓለም ሻምፒዮናዎች፣ የአገር አቋራጭ ውድድሮችን እየተመለከተ ዜናውን አድርሷል፡፡

ጋዜጠኛ ደምሴ ተወልዶ ያደገው ድሬደዋ በኢትዮጵያ ሬድዮ ከመቀጠሩ በፊት የስፖርት ፊሪላንስ ጋዜጠኛ ሆኖ ከትውልድ ስፍራው ይሰራ ነበር፡፡

ጋዜጠኛ ደምሴ ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ደከመኝ ሳይል የሰራና በዚህም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ባለሙያ ነበር፡፡

በሙያውም አትላንታ፣አቴንስና ቤጅንግ ኦሎምፒኮችን በስፍራው በመገኘት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፏል፡፡

ደምሴ ኢትዮጵያ በ1980 ለምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች ሻምፒዮና(ሴካፋ) ከዚምባብዌ ጋር አዲስ አበባ ላይ ለፍጻሜ በፍጹም ቅጣት በደረሰችበት ወቅት ዳኛቸው ደምሴ በመጨረሻ ለሚመታት ምት ”ዳኙ ገላግለን”ብሎ በሬዲዮ ባስተላለፈው የቀጥታ ስርጭት ሳቢያ ብዙዎች ይህንኑ እንደ ቅጽል ስም አድርገውለት መቅረቱም ይታወቃል።

ከአንጋፋዎቹ ዝነኛና ታዋቂ የአገራችን የስፖርትጋዜጠኞች ሰለሞን ተሰማ ነጋ ወልደስላሴና ፍቅሩ ኪዳኔ ቀጥሎ በ1962 ዓ.ም. ከድሬ ደዋ በአማተር የስፖርት ዜና ዘጋቢነት ለ ሰባት አመታት በመቀጠልም በኢትዮጵያ ሬድዮ ድርጅት እስካሁን ለ33 ዓመታት ባጠቃላይ ከ40 ዓመት በላይ የስፖርት ጋዜጠኛ በመሆን ያገለገለ ታዋቂና ዝነኛው ጋዜጠኞ ደምሴ ዳምጤ –
– በሞስኮ ፤ በሎሳጀለስ ፤ በሴኦል ፤ በባርሴሎና ፤ በአትላንታ ፤ በሲድኒ ፤ በአቴንስና በቤጂንግ የኦሎምፕክ ጨዋታዎች ባቀረባቸው የስፖርት ዘገባዎች፤
– በዓለምና የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የእግር ኳስ ጨዋታዎች ባስተላለፈው የእግር ኳስ ቀጥታ ስርጭት፤
– በዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮንና በመላ አፍሪካ ጨዋታዎች፤
በ መልካም ስራዎቹ ሲታወስ ይኖራል ።

05/03/2022

ከ አየለ አዲስ

የኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት የሚነሳው በነጋሪት ከሚጎሰም አዋጅ ነገራ ነው፡፡ ማለዳ ጥሩንባቸውን ነፍተው የሞት ዜና የነገሩን ፣መለከት፣ እምቢልታ አጭህው የጦር ወሬ ያደረሱን፣ መሰንቆቻቸውን ይዘው እንደ ኢትዮጵያዊ ወግ እና ባህል በቅኔ ፣ በግጥም መረጃን ና መደሰተን ለህብረተሰቡ አድረሰዋል፡፡ ትላንት ዜና የነበሩት ዛሬ ታሪክ ሁነዋል፡፡
ዘመናዊ መገናኛ ዘዴዎች ከመፈልሰፋቸው በፊት ዜና ነበረ፡፡ ጭምጭምታዎች ወንዝ አቋርጠው የቤተመንግስቱን ሰሞነኛ ወግ በገበያ ፣ በቤተ ከርስቲያን ፣ በማህበር ምን አዲስ ተሰማ ብለው ያሰማሉ፡፡ አፋሮች ዳጉ ብለው የየቀኑን ውሎ እንደሚያለወውጡት ሁሉ ፤ ሁሉም የራሱ መለያ ወግ እና ባህል አለው፡፡ ነበረው፡፡

ኢትዮጵያ የማተሚያ ማሽን ደጇ የረገጠው እንደዘመነኞቹ የታሪክ መፃህፍት በአንድ መቶ ሃምሳ አመታት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከ500 መቶ አመታት በፊት ነው፡፡ ከዚህ ቀድሞ በድንጋይ ላይ ፅሁፎች ንጉስ ኢዛና የቀን ውሎውን ፣ የጦር ድሉን መዝግቦ በዜና መልክ አስተላልፏል፡፡

ከሰባት መቶ ዓመታት በፊት ቀድማ ፅሐፈ ትዕዛዝ ያሁኖቹን የኮንምንኬሽን ጉዳዩቸ ሚኒስቴር ሹማ የየዕለት መረጃዎች ለህዝብ ጀሮ ታደረስ የነበረች ሀገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ ከዚህ በፊት እንደዝመና ታሪካችን ብራና ዳምጠው ፣ ቀለም በጥብጠው ‹‹ዜና መዋዕል›› ብለው ለህትመታቸው ስያሜ የውሎ ዜና በእጅ ፅሁፍ እየተባዛ ይሸጥ ነበር፡፡ ስንክሳሩ ፣ ገድሉ እና ድርሳኑ በዜና ዘገባችን ውስጥ የራሱ የታሪክ ድርሻ አለው፡፡

ቀዳሚዋ የአዕምሮ ጋዜጣ እንኳን በአፃፃፍ ስርዓቷ የኢትዮጵያ ውልድ ናት፡፡

በዚህ መፅሀፍም ያልተሰሙ ፣ ያልታዩ እና የልተዳሰሱ ከጥንት ፅህፈት ታሪካችን እስከ ዘመናዊው ኢንተርኔት ድረስ ተቃኝቷል፡፡ በታሪክ ፅህፈት ውስጥ በመረጃ ክፍተት ያልተሟሉትን የማረም እና ለቀጣይ ለምሰራው ምርምር መሰረት እንዲሆን የተደጎሰ እና በማስረጃዎች የበለፀገ ነው፡፡ ለአሰተያየታችሁ ልባዊ መስጋናየ ከፍ ያለ ነው፡፡ [email protected]

የጋዜጠኞችን ከለላና የሚዲያ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ነጥቦች✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍በአለማችን ዲሞክራሲ ባልበለፀገባቸው ሀገራት መንግስታት እና የተለያዩ ቡድኖች ትኩረት ከሚያደርጉባቸው...
05/03/2022

የጋዜጠኞችን ከለላና የሚዲያ ብልፅግና ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ነጥቦች
✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍✍
በአለማችን ዲሞክራሲ ባልበለፀገባቸው ሀገራት መንግስታት እና የተለያዩ ቡድኖች ትኩረት ከሚያደርጉባቸው እና ተፅኖ ከሚያሳድሩባቸው የሙያ ዘርፎች መካከል ጋዜጠኝነት ዋንኛው ነው፡፡እነዚህ አካላት በዝምታ ውስጥ ያሉ፡የታፈኑ ድምፆች አደባባይ እንዳይወጡ በማድረግ ጥቅማቸውን ለማረጋገጥ ይጥራሉ፡፡ስለሆነም ያልተሰሙ ድምፆችን ለማውጣት የሚሰሩ ጋዜጠኞች የተጠናከረ ሀገራዊ ህጋዊ ከለላ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ዲሞክራሲ ለማስፈን የሚሠራ ታዳጊ ሀገር ከመገናኛ ብዙኃን አንፃር ያሉ አሮጌ የህግ ማእቀፎችን ማሻሻል ይጠበቅበታል፡፡የሚዲያ እንዲስቱሪውን በተስፋ ብርሀን ሊሞሉ የሚችሉ አዳዲስ ማእቀፎችን ማዘጋጀትም አለበት፡፡የሀሳብ ነፃነትንና ብዝሀነትን የሚያፍኑትን ማስወገድን ይጠይቀዋል፡፡በተጨመሪም በሚዲያው ላይ የሚኖር መረጃ የማግኘት ገደብ፡የተጓተተ ና ያልተገባ ፍቃድ አሠጣጥ ና ተፅኖ ፈጣሪ ቁጥጥር እና እርምጃ ማስተካከልን ይጠበቅበታል፡፡ በመሆኑም እነዚሀን ና ሌሎች የህግ ማእቀፍ ማሻሻያዎችን ማድረግ ነፃ ሚዲያ ለመገንባት ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለሆነም ከሚዲያ ጋር የተያያዙ የህግ ማዕቀፎችን ማሻሻል እንዲሁም የፍትህ አካላት ለጋዜጠኞች መብት ዘብ መቆም ሙያው የላቀ ሚና እንዲጫወት ያስችለዋል፡፡
በተጨማሪም በብዙ ሀገራት የጋዜጠኞች የሙያ ማህበራት በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ጥሰቶችን በመከላከል በኩል ጠቃሚ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው፡፡ ማህበራቱ በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ አካላዊ ና ስነልቦነዊ ጥቃትን ከመከላከል ባሻገር ስለሙያው እና እድገቱ ለሀገር መሪዎች፡ለፓለቲከኞች እና ለተፅኖ ፈጣሪ ሰዎች ግንዛቤ ለመፍጠር የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃሉ፡፡ለአብነትም በላቲን አሜሪካ ከ1990ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ጋዜጠኞች ባቋቋሙት ሀገራዊ የፕሬስ ማህበር መብቶቻቸውን ለማረጋገጥ ሰርተዋል፡፡“ጋዜጠኞች በሙያቸው መደራጀታቸው በሙያቸው ላይ የሚደርሱ ጥሰቶችን ለመከላከል ያስቻለ፡ባለደረቦቻቸውን ከጥቃት ለመሸፈን ያገዘ" ሲሉ አባላቱ ይገልፁታል፡፡
በሀገራችንም ሙያዊ መርሆችን ያከበረ፡ለህዝብ የወገነ፡ነፃ፡ሀላፊነት የሚሰማው ሚዲያ ለመገንባት ከላይ የተጠቀሱትን ማሻሻያዎችን እና አሠራሮችን ተግባራዊ ማድረግ በእጅጉ ይጠቅማል፡፡

05/03/2022

Notes on Science journalism.

Sources of Science journalism, Tips, Rules & Tools .

1. Write about science which applies to people’s lives:

A particular scientific finding can help you sell the science in a story. You should think harder about how to incorporate science into stories that affect your readers directly, whether it’s their health, sports, outdoor activities and so on.

It’s the most obvious way of getting people interested in science.

For example:

What does this mean to my health? Is this going to cure cancer? Is this going to help create a car with much less energy?

2. Explain something trending:

From climate change to Zica (virus), science and health topics are almost always in the news in some form. Journalists must seek out the trending science-related topics in the public conversation and political debate — and to bring the science to the forefront of those discussions. “When there is a trend story”. It is great to find some research that backs up and provides evidence for that trend.

3. Combine fun and serious learning:

For successful science journalism you need to “put a fun spin on science.”

Two examples:

“The Brain Scoop” and “SciShow”. These YouTube-based science shows “have hundreds of thousands of views because they’re funny, but they’re serious at the same time. So the storytellers are funny, but the information they convey is serious. People get to smile as they watch the videos, but they also come away from them having learned something.

4. Look to popular culture for science stories:

There’s a part of science that is purely about discovery, adventure, and that’s the kind of science you’ll see in the movies — the ‘Indiana Jones’ kind of science and the ‘Jurassic Park’ kind of science.

Use those types of pop culture references as the foundation for related science stories, showing readers the real-world research or actual advancements that films, shows, songs and books fictionally depict.

5. Revamp you evergreen stories”

Take some of your classic go-to article topics — like midterm and final exam anxiety — and introduce new science angles into the mix, like discussing how the human body reacts to stress.

6. Embrace the embargo:

In science publications, there is traditionally an embargo system in which scientists agree to not say a word about their research until it is published. However, there are special embargoed early copies of many pubs which journalists can access to begin working on related stories in order to have them ready and fully vetted by the time the research is released. Journalists to contact their campus press office to be put on this embargo early copy list — enabling you to be right on the edge of breaking science news.

7. Search for the human connection:

Instead of reporting just the straight science, running periodic profiles of professors and science students — as a more reader-friendly filter through which to tell their research stories. Balancing the science in every article with quotes from everyday individuals — again as a method to make the pieces more relevant to a wider audience.

8. Start a science beat:

Reading scientific writing and doing science journalism gets easier with practice and hands-on experience. By allocating a specific person or team to work a focused science beat, you can help students gain that experience and also develop more interesting, informative and comprehensive science stories for your news outlet.

9. Don’t let the titles scare you:

Titles for scientific papers — such as “A Remotely-Sensed Global-Terrestrial Drought Severity Index” — can easily be intimidating. Once you work to grasp their related meaning or real-world connections, the research they are describing is often more accessible than the titles might indicate. The research paper with the drought title, for example, led to a fun show-and-tell news feature about predicting drought — explained by a scientist from atop a mountain.

10. Get out of the office:

Do not interview scientists in their offices. Instead, take them to their labs or places of research so you can observe them in their natural habitats and see some real action.

11. Strike out the student journalist stereotype:

While science journalism has a stigma, so do student journalists — which can make scientists wary about whether an undergrad newshound can report on their research accurately. Putting together a portfolio of your publication’s science articles to help show prospective scientist interviewees the depth, breadth and veracity they can expect in the story you’re hoping to write about them.

12. Air the scientist voice:

Many scientists avoid declaring any real-world applications for their research, while journalists always strive to explain why a particular finding should matter to the public. But sometimes it’s important to present both of these perspectives — to ensure your science stories are more well-rounded and honest and to keep everyone (readers, your editors and your scientist sources) happy.

13. Ask scientists for analogies:

Asking scientists for their own analogies or metaphors to describe their research in layman’s terms or to run your own analogy attempts by them to make sure they are correct.

14. Don’t fear fact checking:

Pre-publication review of a story by a source is obviously a rare practice in journalism. But it can be very helpful at times on the science beat considering the complexity of the subject matter. To get around sharing your actual story draft with a scientist, Explaining the overall concept to them and then spot-checking
specific facts. The ultimate goal must always be accuracy.

15. Take a science field trip from time to time:

You may not restricting yourself to only the scientists, scientific research or science labs on your own campus. If you can find a scientist, scientific community, science conference or research lab off campus that is connected to a subject you’re currently reporting, don’t be afraid to reach out and set up a field trip.

16. Being a non-scientist writing about science is A-OK:

As a nonscientist yourself and reporting about majors fall outside the sciences have the advantage of knowing what an average reader most wants to know or might not be able to grasp from a science story. Sometimes it’s even better if you have somebody who is not a scientist because they don’t tend to use jargon and don’t tend to assume people already know how science works.

17. Have a science major on staff:

While non-science majors can bring an every-person angle to science stories, science majors are still invaluable editorial assets for a number of reasons. Chief among them: They are able to use their departmental connections to help build a bridge between your newsroom and campus research labs.

18. Passion is mandatory:

Whether or not you work in the labs, if you aren’t passionate about scientific discovery, you won’t succeed as a science journalist. More carefulness and endeavor than usual are needed to succeed at finding and breaking interesting science stories — in part because very few of them exist in obvious news circles.

19. Immerse yourself in the research:

It can be challenging to grasp the finer details of a research project through just one or two interviews. Embedding yourself or one of your reporters into a particular research lab for a few weeks or even a full semester — attending meetings, experiments and group activities.

This type of full immersion can reveal the day-to-day, little-known aspects of research work and shine a spotlight on the traditionally unsung members of a lab, including the undergraduate and graduate student research assistants.

20. Ditch words:

Using photography, photo essays, videography and other multimedia tools and platforms as much as possible — at times in place of words — to breathe new life into an already-overdone story such as climate change. A fresh multimedia take “has this wow effect [as in] ‘Oh wow, this is crazy, weird, interesting, different!'”

Send your valuable feedback/Comments/queries & messages for doubts.

05/03/2022

CNN will stop broadcasting in Russia, the news channel said after the introduction of a new law there that could jail anyone intentionally spreading "fake" news.

Lawmakers passed amendments to the criminal code making the spread of "fake" information an offense punishable with fines or jail terms. They also imposed fines for anyone calling for sanctions against Russia following the invasion of Ukraine.

News organizations including the BBC and Canadian Broadcasting Corp have also suspended reporting from Russia following the passing of the law.

Russia has called its actions in Ukraine a "special operation".

Here is one of our favorite quotes about journalism from our latest course 𝐓𝐡𝐞 𝐄𝐥𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐨𝐟 𝐉𝐨𝐮𝐫𝐧𝐚𝐥𝐢𝐬𝐦. Access the Broadc...
05/03/2022

Here is one of our favorite quotes about journalism from our latest course 𝐓𝐡𝐞 𝐄𝐥𝐞𝐦𝐞𝐧𝐭𝐬 𝐨𝐟 𝐉𝐨𝐮𝐫𝐧𝐚𝐥𝐢𝐬𝐦. Access the Broadcast Journalism course on editmentor.com and get introduced to the basic principles of producing news content. 🎞⁣



This page is for students , journalists , those professional related to Media.
05/03/2022

This page is for students , journalists , those professional related to Media.

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስለ ጋዜጠኝነት -All about Journalism posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share