09/10/2022
ሕወሓት ለትግራይ ህዝብ በዕርዳታ የመጣ መድሃኒትን ዘርፏል
አሸባሪው ሕወሓት በመቀሌ የሚገኘውን የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ የመድሃት መጋዘን በመዝረፉ እና መድሃቱን ለተዋጊዎቹ እንዲውል በማድርጉ የመቀሌ ሕዝብ በከፍተኛ የመድሃት ችግር ውስጥ መግባቱን መረጃዎች አለመከቱ፡፡
ከመቀሌ እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ህወሓት መቀሌ የሚገኘውን የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ መጋዘን ሙሉ ለሙሉ ዘረፋ መፈፀሙንና ይህም ድርጊቱ የWHO ሃላፊ ቴድሮስ አድሃኖም ይሁንታ ሳያገኝ እንዳልቀረ ነው የተጠቆመው፡፡
ህወሃት ዘረፋ የፈጸመው በተለየያዩ ግንባሮች ባደረጋቸው ውጊያዎች የቆሰሉ የአሸባሪው ቡድን አባላት ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ እና የቡድኑ አባላት ህክምና ማግኘት ባለመቻላቸው ከተዋጊዎቹ ቅሬታ እንዳይነሳ መልስ ለመስጠት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
ህወሓት ለቁስለኞች ብቻ ሳይሆን ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች በዓለም ጤና ድርጅት የመጠባበቂያነት የተቀመጠውን የደም ግፊት፣የስኳርና ሌሎች መድሃኒቶች መውሰዱ የተገለፀ ሲሆን በመቀሌ በአሁኑ ወቅት በተለይም አዛውንቶችና ሽማግሌዎች የስኳርና የደም ግፊት መድሃኒት በማጣታቸው ለከፍተኛ አደጋ መጋለጣቸውን እየወጡ ያሉ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡
የትግራይን ህዝብ አፍኖ ለፖለቲካ ጥቅሙ ማዋልን የለመደው ህወሓት ከአሁን ቀደም የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለዕርዳታ ማሰራጫ ያሰቀመጠውን 570 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ በመዝረፉ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ የሰብአዊ እርዳታ ማከፋፈል እንዳልቻለ መናገሩ የሚታወስ ነው፡፡
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በርግጥ ተቆርቋሪነቱ ለትግራይ ህዝብ ከሆነ ሕወሓት በትግራይ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ እንዲያስቆምና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ንብረት የሆኑ መጋዘኖችን እየዘረፈ ለጦርነት ማዋሉንም በግልጽ ሊያወግዝ ይገባል።