Fetehe

Fetehe የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዲሁም የአስተዳደር በደሎችን ?

ሰበር መረጃ!!አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከሃላፊነታቸው ተነሱ     *********************አቶ ዮሃንስ ቧያለው ከኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ...
29/04/2022

ሰበር መረጃ!!
አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከሃላፊነታቸው ተነሱ
*********************
አቶ ዮሃንስ ቧያለው ከኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኃላፊነታቸው ተነስተዋል።አሁን ላለው ስርዓት ከማጎብደድ እና ከመንበርከክ ይልቅ የስርዓቱን ዝርክርክነት እና ብልሽት በደንብ አድርገው ያጋለጡት አቶ ዮሃንስ ከሃላፊነት የመነሳት ጉዳይ ተጠባቂ ነበር፡፡

አሳዛኝ ሰበር ዜና የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለፀ !!!የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለፀየሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶ አመሻሹ ላይ ባወ...
29/04/2022

አሳዛኝ ሰበር ዜና
የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለፀ !!!

የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉ ተገለፀ

የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶ አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ ከሶላት በተመለሱ ሙስሊሞች የወራቤ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መቃጠሉን ገልጾ በተመሳሳይም የሳንኩራ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በአክራሪ ኃይሎች መቃጠሉ ገልጿል።

ሀገረ ስብከቱ የፌዴራል እና የክልሉ መንግስታት እየተፈጠረ ያለውን ችግር በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

በዞኑ ኦርቶዶክሳውያንና አብያተ ክርስቲያናት በጫና ውስጥ መሆናቸውን የገለፀው ሀገረ ስብከቱ ከፍተኛ ጥበቃ እንዲደረግ ጠይቋል።

ይህንን እኩይ ተግባር የፈፀሙ ወንጀለኞች ለሕግ እንዲቀርቡና ፍትሕ እንዲሰፍን እንዲደረግ ጭምር ነው የሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የጠየቀው።

በጎንደር ከተማ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫየአማራ ሕዝብ በተለያዩ ቦታዎችና ዘርፈ ብዙ በሆኑ ውጫዊ እና ውስጣዊ የማጥቂያ ስልቶች የተወነጨፉበትን ቀስቶች መክቶ ሳይጨርስ በታ...
29/04/2022

በጎንደር ከተማ የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ሕዝብ በተለያዩ ቦታዎችና ዘርፈ ብዙ በሆኑ ውጫዊ እና ውስጣዊ የማጥቂያ ስልቶች የተወነጨፉበትን ቀስቶች መክቶ ሳይጨርስ በታሪካዊቷና ተቻችሎና ተከባብሮ የመኖር ተምሳሌት በሆነችው ጎንደር ከተማ ውስጥ ሀይማኖትን ሽፋን ያደረገ ግጭት በመቀስቀስ የሕዝቡን አንድነት ለመስበር ጥረት ተደርጓል።

በዛሬው እለት የጎንደር ከተማ ነዋሪ እና የጎንደር ሕዝበ ሙስሊምና ሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲሁም የሁሉም አባት የነበሩት ታላቁ ሸኽ ከማል ለጋስ ሥርዓተ ቀብር እየተፈጸመ በነበረበት ሰዓት ከቀብር ቦታው ጋር ድንበርተኛ የሆነው ቤተ ክርስቲያን ላይ ለቀብር የሚሆን ድንጋይ "እናነሳለን የመስጊዱ ክልል ነው፤ አታነሱም የቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ነው" በሚል በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተጀመረ ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል። የተለያዩ ንብረቶችና ተቋማትን የማጥፋት እንቅስቃሴዎችም ተስተውለዋል።

በተፈጠረው ግጭት በንጹሃን ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የክልሉ መንግሥት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን እየገለጽን ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናትን እንመኛለን፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት በማንኛውንም አይነት የጽንፈኝነት አስተሳሰብ የሚፈጠር የሰላም መደፍረስንም ሆነ በንጹሃን ሕይወት፣ አካልና ሀብት ንብረት ላይ የሚደርስ ጥፋትን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም፡፡ ስለሆነም በጥፋተኞች ላይ አስፈላጊውን ሁሉ ህጋዊ እና ተመጣጣኝ እርምጃም ይወስዳል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የክልሉ መንግሥት የተከሰተውን ግጭት ለማብረድ፤ በድርጊቱ የተሳተፉትንና ግጭቱን እያባባሱ ያሉ አካላትንም በቁጥጥር ሥር ለማዋል የክልላችን የጸጥታ ኃይል፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ሰላም ወዳድ የሆኑት የጎንደር ከተማ ወጣቶች ጋር ተቀናጅቶ ውጤታማ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል።

በመሆኑም አካባቢውን በማረጋጋት እና ህግና ሥርዓትን በማስከበር ግጭቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ተችሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠንና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን በማሳባሰብ ለሕዝቡ ትክክለኛ መረጃዎችን የመግለጽ፣ የወንጀሉ ተጠርጣሪዎችን በህግ ጥላ ሥር የማዋል፣ ተጎጅዎች ድጋፍ እንዲደረግላቸው የማጣራት ሥራዎችን በማከናወን ለሕዝብ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡

መላው የጎንደር ከተማ ሕዝብ ራሱን፣ አካባቢውን እና ከተማውን በማረጋጋት፣ በመጠበቅና የበኩሉን ሁሉ አስተዋጽኦ በመወጣት መንግሥት አጥፊዎችን በህግ ፊት ለማቅረብ እያከናወነ የሚገኘውን እንቅስቃሴ ከጸጥታ ኃይላችን ጎን በመሆን በተለመደው መንገድ ትብብሩን እንዲያስቀጥል እንጠይቃለን፡፡

ሚያዚያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም.
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ባሕር ዳር

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fetehe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share