Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ

  • Home
  • Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ

Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ News updates

ወጣት ኢንጂነር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዘማሪ ታዲዮስ ይባላል። ትጉህ ልጅ ነው ያለማጋነን በቤተክርስቲያን ጉዳይ የማይሰለች ጎበዝ እና ታታሪም ነው ይህ ወንድማችን "ራህማ ሚዲያ " የሚል ...
09/07/2024

ወጣት ኢንጂነር የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ዘማሪ ታዲዮስ ይባላል።

ትጉህ ልጅ ነው ያለማጋነን በቤተክርስቲያን ጉዳይ የማይሰለች ጎበዝ እና ታታሪም ነው ይህ ወንድማችን "ራህማ ሚዲያ " የሚል በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዙሪያ የሚዳስስ የዩቲዩብ ሚዲያ ቻናል ባለቤት ነው።

እስኪ ወዳጆቼ ኦርቶዶክሳዊያን የኛን ልጆች ማበረታታት እንለማመድ ??? ሼር እናድረግ እና መዝሙሩንም እናዳምጠው 🙏🙏🙏 በርታ ወንድም 🙏🙏🙏
https://youtu.be/nJI7Geot9QI?si=rTLNzwrmrC-LbMsT
ዝማሬ መላእክት ያሰማህ ወንድማችን

🆂🆄🅱🆂🅲🆁🅸🅱🅴0:00-እዳ አለብኝ6:15-የሰው እጅ አታሳየኝ12:25-ሰው ሰውን በንግግሩ ያደማል 22:15-በአንዳች አትጨነቅ26:45-እርሷ እንድትናገር31:29-ለመስቀልህ 38:52...

በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳና የማይጠብሪ ከተማ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ እንዲሆን በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ...
18/06/2023

በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳና የማይጠብሪ ከተማ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ እንዲሆን በሰላማዊ ሰልፍ ጠየቁ።

በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን የምዕራብ ጠለምት ወረዳና የማይጠብሪ ከተማ ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ "የጠለምት አማራ ማንነት ጥያቄ የፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው" ብለዋል።

ነዋሪዎቹ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የተለያዩ መፈክሮችንም አሰምተዋል።

ሕወሓት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በኀይል አካባቢውን ወደ ትግራይ አካሎት የቆየ መኾኑን ያነሱት ነዋሪዎቹ በአሁኑ ጊዜ አካባቢው ግፍ ሲፈጽምበት ከነበረው አገዛዝ ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በዱር በገደሉ በመታገል ነጻ መውጣቱን አስገንዝበዋል።

የማንነት ጥያቄያቸው ሕጋዊ ኾኖ የአካባቢያቸውን ሰላምና ልማት እንዲያስቀጥሉም መንግሥት ምላሽ እንዲሠጣቸው ጠይቀዋል።

አሚኮ

ሰበር ዜና!የኢዜማ የስራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑትአቶ የሽዋስ አሰፋ ፣ ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ፣አቶ ሀብታሙ ኪታባ  አቶ የጁአልጋው ጀመረ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ኑሪ ሙደሲር እና አቶ ዳንኤል ...
25/05/2023

ሰበር ዜና!

የኢዜማ የስራ አስፈፃሚ አባላት የሆኑት
አቶ የሽዋስ አሰፋ ፣ ወ/ሮ ናንሲ ውድነህ
፣አቶ ሀብታሙ ኪታባ አቶ የጁአልጋው ጀመረ፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ኑሪ ሙደሲር እና አቶ ዳንኤል ሺበሺ ከኢዜማ መልቀቃቸውን አሳወቁ::

Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ

ለሁሉም ሚዲያዎች በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከደረሰው ጉዳት ለመውጣት ለተጎጂዎች የሚደረግ ድጋፍ፤ መሰረታዊ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና የመልሶ ግንባታ ያለበትን ሂደት አስመልክቶ በ...
24/05/2023

ለሁሉም ሚዲያዎች
በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከደረሰው ጉዳት ለመውጣት ለተጎጂዎች የሚደረግ ድጋፍ፤ መሰረታዊ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥና የመልሶ ግንባታ ያለበትን ሂደት አስመልክቶ በተደረገ የቁጥጥር ግኝቶች ላይ በ17/09/2015ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል

አብዛኛዋ የትግራይ እናት ዛሬ በዚህ ፎቶ ትመሰላለች !! " ለህግ አንመራም ህግ አይከበርም አንታሰርም በህዝባችን ሞትና መቁሰል ህያው እንሆናለን"  ባሉ እብሪተኞች ምክንያት፤" ተው ልጆቻችሁ...
17/05/2023

አብዛኛዋ የትግራይ እናት ዛሬ በዚህ ፎቶ ትመሰላለች !!

" ለህግ አንመራም ህግ አይከበርም አንታሰርም በህዝባችን ሞትና መቁሰል ህያው እንሆናለን" ባሉ እብሪተኞች ምክንያት፤

" ተው ልጆቻችሁ ይሞታሉ ፣ ሴቶች ይደፈራሉ ፣ ስደት እና ረሀብ ይንሰራፋል እና ውግያ አይጠቅምም አስቡበት " ሲባል

በምላሹ " ሞክረና ስላላወከን ነው ለእኛኮ ጦርነት ባህ*ላዊ ጨዋታችን ነው መሽረፈት" አሉ አገርን ናቁ የሰው ክልል አጥር ነቀነቁ የአገር ኢኮኖሚ አናጉ

ከዛስ ከዓመታት ዘኋላ እንደተባለው ምን ሆነ በእብሪተኞች እና ማስተዋል በተሳናቸው ወጣቶቻቸው ድንፋታ ለውጊያ ሄደው ባልተመለሱ ሚሊዮን ልጆቻቸው እና በሺዎች አካል መጉደል ምክንያት ይኸው በየታዛቸው ቁጭ ብለው የደጃፋቸውን ማዶ በመቃኘት እንባ ያቀረሩ እናቶች ይታያሉ " ልጄስ?" እያሉ😭

ይህ የሆነው በተጋሩ ዲያስፖራ ፣ ምሁራን ፣ ፖለቲከኞች ፣ አክቲቪስት ፣ ጋዜጠኞች እና በክልሉ መሪ ፓርቲ አመራርና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎች ነው ዛሬ ሎሌ ሊሆኑ ....... ኤዲያ !🙏🙏🙏

አሁንም የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም በጎሪጥ ተመልክታችሁ የተሰየመውን ግዚያዊ አስተዳደር በማንጓጠጥና " እኛ ከሌለንበት " የምትሉ ሀይሎች አስቡበት ። አትንፈራገጡ የቀረው ጭራችሁ ነው ይ.ቆረጣል!😂

መረጃ  #ትግራይ  #ህወሓት  #መቀሌ ህወሃት እናድን በሚል ዶክተር ደብረፂዎን ፣ አለም ገበረዋሃድ እና ሞንጀሪኖ በትግራይ ያሉ ከተሞችን ተከፋፍለው ሰሞኑን ስብሰባ እያካሄዱ ነው።ዶ/ር ደብረ...
16/05/2023

መረጃ #ትግራይ
#ህወሓት #መቀሌ

ህወሃት እናድን በሚል ዶክተር ደብረፂዎን ፣ አለም ገበረዋሃድ እና ሞንጀሪኖ በትግራይ ያሉ ከተሞችን ተከፋፍለው ሰሞኑን ስብሰባ እያካሄዱ ነው።

ዶ/ር ደብረፅዮን የሽሬ አካባቢ ከተሞችን፣ሞንጀሪኖ የማይጨው አካባቢ ከተሞችን እና አለም ገ/ዋሀድ አድዋ ያሉ ከተሞችን ይዘው ስብሰባ እያደረጉ ነው። የስብሰባው አላማ ህወሃትን ህጋዊ ፓርቲ ለማድረግ እና ፓርቲውን ለመታደግ ነው ተብሏል። ጌታቸው ረዳ ብልፅግና ነው፣ እኛን ማማከር ትቷል .....የሚል ዘመቻ እንደጀመሩበት ታውቋል።

ህወሃት በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን የገበሩበት ድርጅት ነው ወደ ህጋዊ ሰውነት መመለስ አለበት፣ህወሃት ከፈረሰ ታላቋ ትግራይ የለችም... በማለት ወጣቶችን እየሰበሰቡ ማወያየት ጀምረዋል።

በትግራይ ረሃብ ጸንቷልዕርዳታው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል" ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " -  ወ/ሮ ት...
14/05/2023

በትግራይ ረሃብ ጸንቷል

ዕርዳታው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል

" ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " - ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ (የኢሮብ ወረዳ ነዋሪ) #እናት

በትግራይ በነበረው ጦርነት ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው የሚገኙ የኢሮብ ወረዳ ነዋሪዎች እርዳታ መቋረጡን ተከትሎ የከፋ ችግር ላይ መሆናቸው ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ በጦርነቱ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው ህፃናት ልጆቻቸውን ይዘው በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ይገኛሉ።

" የሰብዓዊ እርዳታ ካቆመ ብዙ ጊዜ ተቆጥሯል " ያሉት ወ/ሮ ትብለፅ ልጆቻውን ለመመገብ መቸገራቸውን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ትብለፅ ፤ " በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅዬ በመጠለያ ውስጥ ነው ያለሁት፤ እርዳታ ብዙም አላገኝም ነበር ፤ አሁን ደግሞ ካቆመ ብዙ ጊዜ አልፎታል። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብ ለማስተዳደር በጣም ከባድ ነው በፈጣሪ ኃይል ነው ያለነው። " ሲሉ ተደምጠዋል።

" እርዳታ ቆሟል ፤ ይህ ከፍተኛ ስጋት ነው ያሳደረብን " የሚሉት ወ/ሮ ትብለፅ " ልጆቼ ርቧቸው ሲያለቅሱብኝ አእምሮዬ በጣም ይጨናነቃል ፤ የማበላቸው የለኝም ሲጨንቀኝ ጥያቸው ወጣና ዛፍ ስር እቀመጣለሁ " ሲሉ ምን ያህል አስከፊ ሁኔታ ላይ እንዳሉ አስረድተዋል።

ቀድሞውኑም ችግር ላይ የነበሩት እነዚህ ዜጎች አሁን ላይ እርዳታ ማቆሙ የከፋ ችግር ላይ ጥሏቸዋል።

አንዲት የኢሮብ ነዋሪ በሰጠችው ቃል " በአሁን ሰዓት ለህፃናት #ወተት ለመስጠት ቀርቶ አንድ ዳቦም ቢሆን አይናቅም ለእኛ ትልቅ እርዳታ ነው ፤ እርዳታ ወደዚህ መምጣት ካቆመ ብዙ ወራት አልፏል ረሃብ ላይ ነው ያለነው " ስትል ሁኔታውን ገልጻለች።

ወ/ሮ ትብለፅ ሃዱሽ፤ አሁን ላይ የተገኘው ሰላም በጣም እንደሚያስደስት ገልፀው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

" ህዝባችን ወደቦታው ተመልሶ ሰርቶ እንዲበላና ከእርዳታ ጠባቂነት እንዲላቀቅ የሚመለከታቸው አካላት በጋር መስራት አለባቸው " ሲሉ መልዕልት አስተላልፈዋል።

የኢሮብ ነዋሪዎቹ በአካባቢያቸው የኤርትራ ኃይሎች እንደሚንቀሳቀሱ በመጠቆም ይኸው ኃይል ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ እንዲደረግ የሚመለከታቸው አከላት እንዲሰሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ...
13/05/2023

ቦርዱ የህወሓትን ጥያቄ ውድቅ አደረገ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ሲል በሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕ.ወ.ሓ.ት) ላይ ያስተላለፈውን የፓርቲውን ሕጋዊ ሰውነት ሥረዛ ፓርቲው " ይነሣልኝ " ሲል ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

ለቦርዱ ውሳኔ ምክንያት የሆነው ኃይልን መሰረት ያደረገ የአመፅ ተግባር አሁን ላይ ባይኖርም እንደገና ህጋዊ ሰውነቱን ለፓርቲው ለመመለስ የሚያስችሉ ድንጋጌዎች በአዋጅ 1162/2011 ተደንግጎ አይገኝም ሲል ምርጫ ቦርድ ገልጿል።

በዚህም የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ የማስመለስ ጉዳይ በህግ የተደገፈ ሆኖ እንዳላገኘው ቦርዱ አመልክቷል።

ፓርቲው ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ ለመንቀሳቀስ የሚችለው በአዋጅ 1162/2011 አንቀፅ 66 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት በድጋሚ የምዝገባ ጥያቄ ሲያቀርብ እና ቦርዱ ህጉን መሰረት አደርጎ ሲፈቅድ መሆኑን ቦርዱ ወስኗል።

የፓርቲው አመራሮች እና ንብረትን በተመለከተ የቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ ፓርቲው ላይ የሰጠው የስረዛ ውሳኔ ውጤቶች በመሆናቸው እንደአዲስ ሊጠየቁ የሚችሉ አይደሉም ያለው ምርጫ ቦርድ በዚህ በኩልም የተጠየቀውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።

(ደብዳቤው ከታቸወ ተያይዟል)

30/08/2022

በአማራ ክልል የተለያዩ ከተማዎች፣ ወረዳዎች እና ዞኖች በተንቀሳቃሾችና በአገልግሎት ሰጪዎች ላይ የሰዓት ገደብ ወስነዋል። በዚህም መሠረት መንቀሳቀስና አገልግሎት መስጠት የተከለከለው፦

ወልዲያ ከተማ

ሰው- ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 1፡00 ድረስ
ተሽከርካሪ- እስከ ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ

ሰቆጣ ከተማ

ሰው- ከምሽቱ 1፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ድረስ
ተሽከርካሪ - ከምሽቱ 12፡00 እስከ ንጋቱ 12፡00 ድረስ
ተፈናቃይ - ከካምፕ ውጭ መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ ክልክል ነው።

ሐይቅ ከተማ

ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ
መጠጥ ቤቶች - ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

ኩታበር

ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ
መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

ደሴ

ምግብና መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
ማንኛውም እንግዳ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
የከተማው ነዋሪ- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ታክሲ- ከምሽቱ 2፡ዐዐ በኋላ
ባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ

ኮምቦልቻ

ሰውም፣ታክሲዎችም- ከቀኑ 11፡00 በኋላ

መቅደላ

ተሽከርካሪ- ከምሽቱ 12፡ዐዐ እስከ ጧቱ 12፡ዐዐ ድረስ
ሰው- ከምሽቱ 2፡00 እስከ ጧቱ 12፡00 ድረስ
ምግብና መጠጥ ቤቶች -ከምሽቱ 2፡00 በኋላ

ደብረ ብርሃን

ተሽከርካሪ - ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ምግብና መጠጥ ቤቶች- ከምሽቱ 2፡00 በኋላ
ተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ ወደ ከተማዋም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

ደባርቅ ከተማ

ባጃጅ- ከምሽቱ 1፡00 በኋላ
ተፈናቃይ- ከምሽቱ 12፡00 በኋላ ወደ ከተማውም ወደ ጣቢያም መግባት ክልክል ነው።

ሌላ ሰበር መረጃዛሬ ማለዳ በተኩለሽ በኩል ገብቶ የነበረ የህውሃት ወራሪ ኃይል ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሙት እና ቁስለኛ መሆኑ ታውቋል።በጣት የሚቆጠሩት በጮቢ በር አድርገው ወደ ዋጃ ማምለጣ...
28/08/2022

ሌላ ሰበር መረጃ

ዛሬ ማለዳ በተኩለሽ በኩል ገብቶ የነበረ የህውሃት ወራሪ ኃይል ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ሙት እና ቁስለኛ መሆኑ ታውቋል።በጣት የሚቆጠሩት በጮቢ በር አድርገው ወደ ዋጃ ማምለጣቸውን የመረጃ ምንጨ ነግሮኛል።ከ600 በላይ ምርኮኛ የተያዘ ሲሆን በዚያ ያለው ባለድል ሠራዊት ወደ ቆቦ ለተቃረበው ጥምር ጦር ከምዕራብ ወደ ምስራቅ እያገዘ እንዳለ ታውቋል።የህውሃት ኃይል ቆቦን ለቆ ወደ ዋጃ አላማጣ በመሸሽ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
ባለንበት ተረጋግተን የሚዋደቁልንን ጀግኖች እናግዝ።ክብር ለኢትዮጵያ ጀግኖች።

ከሌላ አቅጣጫ አንድ ወሳኝ መረጃ አለ እመለሳለሁ ጠብቁኝ‼
ዋሱ መሀመድ

ትናንት በህውሃት ወረራ የተፈፀመባቸው የደቡብ ቆቦ አካባቢዎች ሮቢትን ጨምሮ ዛሬ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል። ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ እየመጣ የነበረው ወራሪ ሃይል በመከላከያ፣ል...
28/08/2022

ትናንት በህውሃት ወረራ የተፈፀመባቸው የደቡብ ቆቦ አካባቢዎች ሮቢትን ጨምሮ ዛሬ በጥምር ጦሩ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ታውቋል።

ወደ ወልዲያ አሰፍስፎ እየመጣ የነበረው ወራሪ ሃይል በመከላከያ፣ልዩ ሃይሉ እና ፋኖ በተወሰደበት ፈጣን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ፊቱ አዞሮ ቆቦን ለቆ ወደ አላማጣ በመውጣት ላይ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

በግዳን በኩል ጠዋት 4:30 ሙከራ ቢያደርግም ተመቶ መመለሱን ከስፍራው የደረሰኝ መረጃ ያመለክታል።

መፍትሔ የሚሰጠን አካል እየጠበቅን ነው ቤተሰቦቻችን ተጨፍጭፈውብን እኛም ጭፍጨፋውን ሸሽተን ህይወታችንን ብናተርፍ ወደ ነበራችሁበት ወለጋ ትመለሳላችሁ እየተባልን ነው።እየገደለን ያለው የክልሉ...
05/07/2022

መፍትሔ የሚሰጠን አካል እየጠበቅን ነው ቤተሰቦቻችን ተጨፍጭፈውብን እኛም ጭፍጨፋውን ሸሽተን ህይወታችንን ብናተርፍ ወደ ነበራችሁበት ወለጋ ትመለሳላችሁ እየተባልን ነው።

እየገደለን ያለው የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ነው። ከወለጋ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ኩታበር መጠለያ የሚገኙት ተጎጂዎች የተናገሩት ነው!!

👉👉👉 https://youtu.be/EscXGNJ1a_E

04/07/2022

ዝናብ‼

ከሀምሌ ወር አጋማሽ በኋላ ለተከታታይ ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊዘንብ ይችላል ተባለ!

በመደበኛ ሁኔታ በሀምሌ ወር የክረምት ዝናብ በሁለም የሀገሪቱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ላይ እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ እንደሚሄድ እና በአንዳንድ ቦታዎች ሊይ ነጎድጋዳማ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ሜትሮዎሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

በመጪው የሀምሌ ወር ከደቡብ ንፍቀ ክበብ ወደ ኢትዮጵያ እየገባ ያለዉ እርጥበት አዘል አየር እየተጠናከረ ሊሄድ እንደሚችልና ከዚህም ጋር ተያይዝ ቀደም ሲል ወቅታዊውን ዝናብ በመደበኛ ሁኔታ ማግኘት የጀመሩትን የምዕራብ አጋማሽና የመካከለኛዉ የኢትዮጵያ ክፍሎችን ጨምሮ የሰሜን ምሥራቅ እና የምሥራቅ ኢትዮጵያ አካባቢዎችን የሸፈነ ዝናብ በተጠናከረ ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረዉ ይጠበቃል ብላል፡፡

በተለይም ከወሩ አጋማሽ በኋላ ለተከታታይ ሰዓታት ያለማቋረጥ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል እንዲሁም በዉስን ሰዓት ከባድ መጠን ያለዉ ዝናብ ሊኖር ይችላል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዝ በአንዳንድ ተዳፋትና በወንዞች አካባቢ ለጎርፍ መከሰት መንስኤ ሊሆን ስለሚችል ማህበረሰባችንና የሚመለከተዉ ሁለ ከወዲሁ አስፈላጊዉን ክትትልና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን፡፡

በአጠቃላይ በሚቀጥለው ወር በኦሮሚያ ጅማ ኢለአባቦራ፣ ሁለም የሸዋ ዞኖች፣ በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል ምዕራብና ምሥራቅ ጎጃም፣ የሰሜን፣ የደቡብ፣ መካከለኛዉና ምዕራብ ጎንደር፣ የባህርዳር ዘሪያ፣ አዊ ዞን፣ የዋግህምራ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ በተጨማሪም የሰሜንና የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ የትግራይ፣ የአፋር፣ የጋምቤላና ከቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የከፊ፣ የቤንች ማጂ፣ ሸካና ምዕራብ ኦሞ የዲውሮ ልዩ ወረዳን ጨምሮ፣ ከደቡብ ብሄር ብሄረ ሰቦችና ህዜቦች ክልል የጉራጌ፣ የስልጤ፣ የሀዲያ፣ የሀላባ ጠምባሮ፣ ከምባታ፣ የወላይታ፣ የጋሞና ጎፊ በአብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ፡፡

በተጨማር ከኦሮሚያ ክልል በቄለምና ምዕራብ ወለጋ፣ ምዕራብ እና ምሥራቅ ሐረርጌ፣ የአርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ ዞኖች የሲዲማ ሁለም ዞኖች እና ከሱማሌ ክልል ደግሞ የሲቲና ፊፈን ዞኖች በአብዛኛው ከመደበኛ ጋር የተቀራረበ ዝናብ ያገኛል።በሌላ በኩል ቀሪዎቹ የሀገሪቱ አካባቢዎች መጠነኛ የደመና ሽፋንና ደረቅ ሆነዉ ይቆያለ ተብላል፡፡

ምንጭ:—ብስራት ሬዲዮ

ሰብአዊ እገዛ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙ ሶስት ሺ 297 መኪኖች ውስጥ  አንድ ሺ 128ቱ  መኪኖች አለመመለሳቸውን የአደጋና ስጋት ኮሚሽን አስታወቀ ሲል ኢፕድ ዘግቧል።የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነ...
24/06/2022

ሰብአዊ እገዛ ጭነው ወደ ትግራይ ከተጓዙ ሶስት ሺ 297 መኪኖች ውስጥ አንድ ሺ 128ቱ መኪኖች አለመመለሳቸውን የአደጋና ስጋት ኮሚሽን አስታወቀ ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

የኮሚሽኑ ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘዉዴ በክልሉ ለ5.2 ሚሊየን ህዝብ ድጋፍ እየተደረገለት መሆኑንም ተናግረዋል።

ባልተመለሱ መኪኖች ዙሪያ ከሚመለከተው አካል ጋር ክትትል የሚደረግበት መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

***************************************

የዛሬ ዓመትም ከሐምሌ ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ መቐለ የእርዳታ እህል ጭነው ከገቡት 466 የጭነት መኪኖች የተመለሱት 38 ብቻ መሆናቸውን የተባበሩትመንግሥታት ድርጅት ገልፆ እንደነበር ይታወሳል።

ከዛም የነዛ መኪኖች እጣ ፈንታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ኃይሎቹን ከቦታ ቦታ የሚያጓጉዝበት የግል ንብረቱ አድርጎት እንደነበር የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ አሁንም ተመሳሳይ ችግር እየተነገረ እኛም እያስተጋባን ነው!!! 😪

24/06/2022

ም/ ዕ ወለጋ በስልክ ያወራኋቸው የተጎጂ ቤተሰቦች ቤት ንብረታቸው ወድሞባቸው ፣ የሚላስ የሚቀመስ የሌላቸው ብዙዎች ናቸው ፣ በአካባቢው ዝናብ እየዘነበ በመሆኑ እና ያሉትም በየጥጋጥጉ ስለሆነ አግዙን እያሉ ይገኛሉ።

ሙሉውን ከታች ባለው ሊንክ ተጭነው ያድምጡ? 🙏

👉 https://youtu.be/kxMfgKNowtI

ሁላችንም የበኩላችንን ለማድረግ እንዘጋጅ Yared Shumete +251911473071 ያጋራውን መልዕክት በመቀበል እንተባበር!

https://youtu.be/kxMfgKNowtI

Hermela Aregawi

 #ይኣኽለና  #ይበቃል !
23/06/2022

#ይኣኽለና

#ይበቃል
!

♦ " ጊዜው እየረፈደ፣ ሞትም ዜና እየሆነ፣ ዜጋም ክብሩን እያጣ ስጋትም ገዥ እየሆነ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዲያበቃም ታላቅ ጥሪያችንን በሕያው እግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!"---ብፁዕ ወ...
23/06/2022

♦ " ጊዜው እየረፈደ፣ ሞትም ዜና እየሆነ፣ ዜጋም ክብሩን እያጣ ስጋትም ገዥ እየሆነ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዲያበቃም ታላቅ ጥሪያችንን በሕያው እግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!"
---
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ የወገኖቻችን ግድያ አስመልክቶ ያስተላለፉት የኀዘን መልዕክት ፦

---
በስመ አብ ወወልድ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
"ወተዘርወ ዕንቊ ቅዱስ ውስተ ኩሉ ፍኖት
“የመቅደሱ ድንጋዮች በጐዳና ሁሉ ራስ ተበተኑ። ሰቆቃ.ኤር. 4፡1
🔴 አባታዊ የኀዘን መልእክት

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በአገር ውስጥ እና በውጭ ያላችሁ የአገርን ክብር ለመጠበቅ በዳር ድንበር ያላችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤ ዘመናትን ፈጥሮ በሚገዛ፣ ዓለማትን በቃሉ በሚያስተዳድር፣ ለህላዌው መታጣት፣ ለጌትነቱ ዳርቻ በሌለው በሕያው እግዚአብሔር ስም አባታዊ ሰላምታችንን እናስተላልፋለን።

ስሜትን በሚወርር፣ ልብን በሚያሳዝን፣ ጉልበትን በሚሰብር ኀዘን ውስጥ ላሉት ወገኖቻችን፤ ትናንት ባለ ብዙ ቤተሰብ ዛሬ ሌጣ ለሆኑት፣ የክብር ሞትና መቃብር ለተነፈጉት፣ ሰው ሆነው በሰው ለተገፉት፣ ኢትዮጵያዊ ሁነው በኢትዮጵያውያን ለተሠዉት፣ አገር : ሳላቸው እንደ ባዕድ ለተቆጠሩት ለደከሙበት ምድር : በወርቅ ፈንታ ሰይፍ ለተከፈሉት ልጆቻችን እግዚአብሔር ያጽናችሁ በማለት፣ የሞቱትንም ደመ አቤልን ያከበረ አምላክ ደማቸውን እንዲመራመር በመለመን መልእክታችንን እንጀምራለን!

ብዙ መልካም ቃላት በሚነገሩበት፣ የጥበብ ድምፆች በሚያስተጋቡበት፣ መሠረት ፈርሶ ለጉልላት ጌጥ በምንጨነቅበት በዚህ ዘመን፣ “እንዴት ካለው ጊዜ ደረስን ማለት መመጻደቅ ባይሆን ኖሮ የሚባልበት ወቅት ሁኖ አግኝተነዋል። ትናንት ገንዘብን የሚቀሙ “እንዴት የሰውን ልፋት ይወስዳሉም ተብለው በተወገዙበት ምድር ሕይወትን የሚቀሙ፡ የሰው ዘር ቅነሳ የሚያደርጉ ግፈኞች ሲንጎማለሉ ማየት ያሳዝናል። ንጹሐን ወገኖቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ማንነት ብቻ ሲሞቱ ስናይ የዝቅታችንና የመውደቃችን ልክ ማጣት ጎልቶ ይታያል። በርግጥ የሞቱት ወገኖቻችን ሰማዕታት ናቸውና ቤተ ክርስቲያን ትዘክራቸዋለች። ሰማዕት ስለ እግዚአብሔር ብሎ የሚሞት ነው። እነዚህም ወገኖቻችን እግዚአብሔር በሰጣቸው ማንነት፣ ለምን እንዲህ ተፈጠራችሁ ተብለው የሞቱ ናቸውና ሰማዕታት እንላቸዋለን። ገዳዮችም ቀጥተኛ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎች ናቸው።

በወለጋና በጋምቤላ የአገራችን ክፍል የደረሰውን አሰቃቂ የወገኖቻችን ግድያ ስሰማ እንደ ወትሮው ልቤ በታላቅ ኀዘን ተመትቷል። በመላው የሀገራችን ክፍልም ክረምቱ ዓመት ከዓመት፣ ጠሉም የንጹሐን እንባ ሁኖ፣ “ሽሽታችሁ በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ" ያለው የጌታችን ቃል ደርሶ እያየን ነው። ጆሮ ከአቅሙ በላይ በሚሰማበት በዚህ ዘመን ያላችሁ ልጆቻችን አሁንም ልባችሁን እንደ ነቢዩ ዳዊት በእግዚአብሔር አበርቱ። ጠብና ክርክሩ እግዚኣብሔር ከፈጠረው ሰውነት ጋር ነውና እግዚአብሔር ፍርድ እንደሚሰጥ እናምናለን። የሃይማኖት አባቶችም የምናስተምረው ሕዝብ አልቆ ማንን ልናስተምር መሆኑን ደግመን ማሰብ ያስፈልገናል። አገራችን ኢትዮጵያ የሚያስከብሯትን መሪዎች አሁንም እየተጣራች ነውና መንግሥትና ሕዝብ ግፍን በተግባር ማውገዝ ያስፈልጋቸዋል። ነቢዩ ኤርምያስ በኀዘን ልቅሶው - የመቅደሱ ድንጋዮች በጐዳና ሁሉ ራስ ተበተኑ። ብሏል ሰቆቃ ኤር 4፡1። የሰው ልጅ ሕያው የእግዚአብሔር መቅደስ ነውና በየስፍራው ሲገደልና ቀባሪ ሲያጣ ስናይ ከነቢዩ ጋር ለማልቀስ እንገደዳለን።

ጊዜው እየረፈደ፣ ሞትም ዜና እየሆነ፣ ዜጋም ክብሩን እያጣ ስጋትም ገዥ እየሆነ የምንቀጥልበት ጊዜ እንዲያበቃም ታላቅ ጥሪያችንን በሕያው እግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ ! ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን! ሰኔ 16 ቀን 2014 ዓ.ም.
(EOTC)

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Fre-Neger Media ፍሬ‑ነገር ሚዲያ:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share