Hawassa tabour times

  • Home
  • Hawassa tabour times

Hawassa tabour times Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hawassa tabour times, Media/News Company, .

26/04/2022
26/04/2022

የ'መደመር' እሳቤ_ ልዩነቶችን ያከበረ የሀገር ግንባታ መንገድ፣

የሀገር ግንባታ ሂደት የሁሉንም ተዋኒያን ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው ። ሀገር ግንባታ ሂደት በመሆኑ በትውልዶች ቅብብሎሽ እየቀጠለ የመጣ እና ወደፊትም የሚቀጥል ሂደት ስለመሆኑም የሚታወቅ ነው።

የሀገር ግንባታው ሂደት የተሳለጠና ውጤታማ እንዲሆን የሀገር ግንባታው ሂደት ተዋናዮችን ተሳትፎና ተነሳሽነት የሚያጠናክሩ እርምጃዎችን ማሳደግ ተገቢ ይሆናል።

የ'መደመር' እሳቤ በሀገር ግንባታው ሂደት ቀደም ሲል ለተደረጉ ጥረቶችና ለተገኙ ስኬቶች አክብሮት ኣለዉ፣ ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉም ይሠራል። ስህተቶች እንዳይደገሙ ይጥራል። ለመጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማውረስም አበክሮ ይሠራል።

የ'መደመር' እሳቤ በሀገር ግንባታ ሂደት ሁሉም ተዋናዮች የማይተካ ሚና እንዳላቸው ይገነዘባል። በመሆኑም ሰብዓዊ፣ ቁሳዊ፣ መንፈሳዊና ሌሎችም አቅሞችና እሴቶች ተሰባስበውና ተደምረዉ በሀገር ግንባታዉ ሂደት ጉልህ ሚና እንዲጫወቱ በመሥራት አስፈላጊነት ላይ ያተኩራል። ኃይልን ከመበተን ይልቅ የመሰብሰብ ፣ የማከማቸትና የማደርጀት አቅጣጫን ይከተላል 'መደመር'።

በመደመር እይታ በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ብሔራዊ መግባባት መፍጠር እጅግ አስፈላጊ ነዉ።

ብሔራዊ መግባባት በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአብዛኛው ህዝብ ጋር (ከሊህቃን እስከ ህዝብ የሚዘልቅ ) መግባባት መፍጠር ማለት ነው ።

ልዩነቶችን ያከበረ፣ ነገር ግን ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎችን መሠረት ያደረገ ብሔራዊ መግባባት የተሻለ ሀገር ለመገንባት ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሀይሎች ሀገርን ያስቀደመ ተነሳሽነት መዉሰድ ይጠበቅባቸዋል።

የፖለቲካ አመለካከት፣ የብሔር፣ የሃይማኖት፣ ,,,ወዘተ ልዩነቶች እንደተጠበቁ ሆነዉ ከሀገር ህልው ፣ ከብሔራዊ ጥቅምና ክብር ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የጋራ መግባባት ለማሳደግ የፖለቲካና የሙያዉ ዘርፍ ሊሂቃን የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙ በመሆናቸው ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል።

በኢትዮጵያ የስርዓቶች መፈራረቅ ሂደት ዉስጥ በሀገረ መንግስቱ ቅቡልነት ላይ ጥያቄ የሚያስነሱ የልዩነት መነሻ ሆነዉ የዘለቁ ጉዳዮቾን መፍታት ወሳኝ ነዉ።

የመደመር እሳቤ ብሔራዊ የምክክር ሂደቱ ፍሬ እንዲያፈራ መሠረት የሚሆን ነዉ። ከልዩነቶቻችን ይልቅ የሚያቀራርቡን እዉነታዎች ሚዛን ይደፋሉና በምክክር እንዳኝ።

ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል!ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማስከበር የህግ ጥሰቶች እንዳይኖር የሌሎች ሰዎች መብት ማክበር አለብን። መብትና ግደታው ከኃላፊ...
20/04/2022

ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል!

ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማስከበር የህግ ጥሰቶች እንዳይኖር የሌሎች ሰዎች መብት ማክበር አለብን። መብትና ግደታው ከኃላፊነት ጋር የሚመጣ ጉዳይ ነው። ስንታሰር በግፍ ታስራያለሁ ከማለታችንን ይልቅ ነገሮችን በሴከነ መንግድ የህዝባችንና ሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ ከሚጥሉ ጉዳዮች መቆጠብ አለብን።

መንግስት ከመሬት ተንስቶ ማንንም ዝም ብሎ አላሰረም። ነገሮቹን ሁሉ ከክልል ጥያቄ ጋር አገናኝቶ ማውራት ተገቢነት የለውም። ወላይታ ክልል እንዲሆን የሚቃወም ወላይታ የለም። ከዚህ ውጪ የሚደረግ ጨኸት ተቀባይነት አይኖርም።

ከጭፍን ጥላቻ ወጥተን ለህዝባችን የሚጠቀሙና ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ፍጹም ሰላማዊና ህዝባዊ በሆኑ መንገድ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

በሀሰተኛ አካውንት ተደብቀህ ስለጻፍክ ከህግ ጥላ ስር ማምለጥ አትችልም።

ማህበራዊ ሚዲያ የራሱ የሆኑ ህጎች አሉ፡፡ የጥላቻ ንግግር በአዋጁ ቁጥር 11/85 መሠረት በህግ ተጠያቂ ያስደርጋል፡፡

በየአከባቢው ህብረተሰቡን የሚሸብሩ ግለሰቦችን ህዝቡ ለይተው ያዉቃል፡፡ ስለዚህ ነጻነታችንን በአግባቡ እንጠቀም፤ አለበለዚያ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላልና፡፡ መብትና ግደታችንን ለየትን መጠቅም አለብን፡፡

20/04/2022


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለብልፅግና ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ከተናገሩት

20/04/2022

👉 መደመር አዲስ የፖለቲካ paradigm ነው፡፡

👉 ብልፅግና ያን paradigm ተሸክሞ የሚያስፈፅም ስብስብ ነው፡፡ ሃይል ነው ፓርቲ ነው፡፡

👉 መደመር ማእቀፍ ነው፡፡ ብልፅግና ይዘት ነው፡፡

👉 መደመር container ነው፡፡ ብልፅግና content ነው፡፡

👉 ኮንቴይነር ከኮንቴንቱ ወይም እኩል ወይም የላቀ መሆን አለበት፡፡

👉 መደመር አቅጣጫን ይወስናል፡፡ ብልፅግና ግን መዳረሻን ይወስናል፡፡

👉 መደመር direction ብልፅግና destination ይወስናል፡፡

👉 ለዚህ ነው መደመር መንገዳችን ብልፅግና መዳረሻችን የምንለው፡፡

👉 መደመር ፍልስፍና ነው፡፡ ፓርቲ ግን ክዋኔ ነው፡፡

👉 ይሄኛው theory ይህኛው practice ነው፡፡

👉 መደመር ቴዎሪውን ያወራዋል፡፡ ብልፅግና ይኖረዋል ይሰራዋል፡፡

20/04/2022

የአብሮነትና የትብብር እሴቶችን እናፅና!

ኢትዮጽያ ታላቅ የለዉጥ ጉዞ ጀምራለች ። የለዉጡ ሂደት በታላላቅ ተስፋዎች ታጅቦ፣ በተገዳዳሪ ስጋቶች እየተፈተነ ቀጥሏል።

የለዉጡ ጉዞ የዉስጥና የዉጪ ኃይሎች በደቀኑት ፈተና እንዲሁም ጊዜያዊ በሆኑ የኑሮ ዉድነትና ሌሎች ችግሮች ተከብቦ እየተራመደ ነዉ።

በሰበብ አስባቡ የእርስ በርስ ጥርጣሬን በማንገስ፣ ግጭትን በመደገስ፣ የማህበራዊ ሚዲያ 'አንቂዎችን' ለእኩይ ተልእኮ በማሰለፍ አብሮነታችንንና ህብረታችንን በመናድ ለዉጡን የመቀልበሱ ሙከራም ቀጥሏል።

አብሮነታችንና ህብረታችን ሲፀና ለዉጡም እየፀና የመሄዱ አይቀሬነት ያስከፋቸዉ ኃይሎች አንድነታችንና ህብረታችንን ለማናጋት እየሠሩ ናቸዉ።

ይህንን የጠላትን ፍላጎት ታሳቢ በማድረግ ለዉጡን ለማፅናት አንድነታችንን ማፅናት፣ ሀገርን ማስቀደምና መደማመጥ አስፈላጊ ነዉ።

'ትልቁን ምስ'_ ሀገርን በማስቀደም በጥቃቅን ጉዳዮች ተጠምደን ኃይላችንን ከማባከን እንቆጠብ። በመረጃ ላይ ተመስርተን የ #ዲጂታል ሚዲያዉን ጦርነት እንመክት። አብዛኛዉ ሚዲያ የዲጅታል ሚዲያዉን ጨሞሮ ዓላማዉና ግቡ ከሚዲያዉ በስተጀርባ ባለዉ የሚዲያዉ ባለቤት ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል።

ሚዲያዉ የሚያስተጋባው በዋናነት የሚዲያዉን ባለቤት ፍላጎት መሆኑን ለመረዳት በተለይም በህልውና ጦርነቱ ወቅት የአሜሪካና የምዕራቡ ትላልቅ የተባሉ ሚዲያዎች የማንን ፍላጎት አጀንዳ አድርገዉ ሲሞግቱ እንደነበሩ ማስታወስ በቂ ነዉ። እነዚህ የኃያላን ሚዲያዎች እዉነቱን በመካድ፣ ሐሰቱን እዉነት ለማስመሠል ሞክረዋል።

በስነ ልቦና ጦርነትና በሴራ ትርክት የሚያደናግሩን ኃይሎች 'አንድነታችንን' እና ህብረታችንን በመሰነጣጠቅ ተልዕኳቸዉን ለማሳካት እየተጉ ናቸዉ።

አንድነታችንና ህብረታችን በፀና ጊዜ ሴራቸዉ ይከሽፋል፣ ስንከፋፋል ደግሞ ምቹ ሁኔታ ያገኛሉ።

ታላቅ የለዉጥ ጉዞ የጀመረ ሀገርና ህዝብ በጥቃቅን አተካራዎች ኃይሉን ከማባከን ይልቅ ለትልቁ ዓላማ ቅድሚያ ሰጥቶ በራዕይዉ መንገድ መራመድ ይጠበቅበታል ።
የሴራ ትርክትን በመፈብረክ የስነ ልቦና ጦርነት የሚሰነዝሩብንን ኃይሎች መመከቻዉ ዋናዉ ኃይል አንድነታችንንና ህብረታችንን ከማፅናት ይመነጫልና የአንድነትና የህብረት እሴቶችን እናጎልብት ።

ጥቃቅን ጉዳዮች ትልቁን ተልዕኮ እንዳያደናቅፉት በዋናዉ የጉዞ መሥመራችን ላይ እናተኩር። ጠላቶቻችን በከፈቱልን ቦይ እንዳንመራ ነገሮችን እንመርምር። ከጅምላ ጥላቻም ይሁን ከቁንፁል አድናቂነት ይልቅ የጉዳዮችን ሙሉ ገፅታ እናስተውል።
የአብሮነትና የትብብር እሴቶችን እናፅና!

19/04/2022

የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ስልጠና መስጠታቸውን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በማህበራዊ ድህረ ገጹ ገልጸዋል፡፡

የፓርቲያችን ፕረዚዳንት እና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር የሰጡትን ስልጠና በተመለከተ የተዘጋጀውን ፕሮግራም ዛሬ ምሽት ከ3፡00 ጀምሮ በዋልታ ቴሌቪዥን እና በፌስቡክ ገጻቸው በቀጥታ የምናሰራጭ መሆኑን የገለጹ ስለሆነ እንድትከታተሉን በአክብሮት ጋብዘዋል።

ምንጭ ዋልታ

19/04/2022

ከ'መገፋፋት' ፖለቲካ ወደ መደማመጥና መደራደር ከፍታ... !

በሀገር ግንባታ ሂደት የመላው ዜጎች አስተዋጽኦ እጅግ መሠረታዊ ጉዳይ ነዉ።

ሀገር የሚገነባበት የሀሳብ ማዕቀፍ ወይም ፍልስፍና ይዘቱና ቅርጹ ቢለያይም፣ የሀሳብ ማዕቀፉ በአብዛኛው ዜጋ ቅቡልነት ካገኘ በሀሳብ ማዕቀፉ ላይ አንፃራዊ መግባባት መፍጠር ይቻላል።

በዚህ ሂደት የፓለቲካ አመለካከትና መሠል ልዩነቶችን አክብሮ ከመገፋፋት ይልቅ የመደማመጥ፣ የመደራደርና የመተባበር እሴቶችን ከፍ ማድረግ ትልቁን ምስል ሎማስቀደም የሀገር ግንባታዉን ሂደት ለማሳለጥ ወሳኝ ነዉ።

የፖለቲካ አመለካከት ልዪነት፣ የብሔር ልዩነት ፣ የእምነት፣ የጾታና መሰል ልዩነቶች ተፈጥሯዊ ናቸዉ። ሰለሆነም እነዚህ ልዩነቶች ተከባብረዉና ተደማምጠዉ ሀገርን የማሳደግ ሚናቸዉን እንዲወጡ መስራት ደግሞ የሁሉም ዜጋ የቤት ስራ ሊሆን ይገባል።

የምንገኝበት ምዕራፍ እነዚህን ልዩነቶች አክብረን ፤ ለብሔራዊ ጥቅሞቻችን መረጋገጥ በጋራ መቆም አስፈላጊነቱ የጎላበት ወቅት ነዉ።

የኢትዮጵያን ጥቅሞች የሚጋፉ ሀይሎች ጥምረት ፈጥረዉ ለጥፋት ባሳፈሰፉበት በአሁኑ ወቅት በ'ዉኃ ቀጠና' ንትርክ መገፋፋት ሀገርን ይጎዳል። ብሔራዊ ጥቅማችንን እና ሉዓላዊ ክብራችንን ለጠላት ጥቃት አሳልፎ ይሰጣል።

ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ሉዓላዊ ክብራችንን የሚፈታተኑ የዉስጥና የዉጭ ሀይሎችን ጫና መቋቋም የሚችል ከመቶ ሚሊየን በላይ ህዝቦች ድምጽና ኃይል ባለፀጋዎች ነን።

ይህንን ፀጋና አቅም በአግባቡ መጠቀም፣ ጠላትን ለመመከትና ለሀገር ግንባታ ማዋል ያስፈልጋል።

አንድነታችንና ህብረታችን ሲሳሳ ጠላታችን ይፋፋል። ይበረታል።

ጊዜያዊ ፈተና የሆኑትን የኑሮ ዉድነትና ሌሎችንም የህዝብ ብሶቶችን እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው አንድነታችንን ለመሸርሸር፣ መንግስትን ለማዳካምና እርስ በርስ መጠራጠርና ግጭት እንዲነግስ ለማድረግ እየሠሩ ያሉ የዉስጥና የዉጪ ኃይሎች በርካታ ናቸዉ።

የእነዚህን ኃይሎች ፍላጎት መቀልበስ የሚቻለው አንድነታችንን በማጠናከር ነዉ።
አንድነት ማለት ደግሞ አንድ አይነትነት ማለት አይደለም።ይልቁንም በሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነትና እህትማማችነት የደመቀ የአንተ ትብስ አንቺ ትብሽ መንፈስን ማፅናት መሆኑ በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲነሳ ቆይቷል።

ሰለሆነም ልዩነታችንን አክብረን፤ ለብሔራዊ ጥቅሞቻችን በጋራ ዘብ እንቁም።

ከ' መገፋፋት' ፖለቲካ ወደ መደማመጥና መደራደር መንፈስ ከፍ እንበል! ኢትዮጵያን ለሁላችንም የምትመች እናድርግ።

19/04/2022

ሴናተር ኪም ጃክሰን በሕወሓት የሀሰት መረጃ በመታለል ኢትዮጵያ ላይ ስለነበራቸው አቋም ይቅርታ ጠየቁ

ወላይታ ሶዶ፡ ሚያዝያ 10/2014 በአሜሪካ የጆርጂያ ሴናተር ኪም ጃክሰን በሕወሓትና ደጋፊዎቹ ፕሮፖጋንዳና የሀሰት መረጃ በመታለል አለአግባብ ኢትዮጵያ ላይ ለወሰዱት የተሳሳተ አቋም ይቅርታ ጠየቁ፡፡

ሴናተሯ ይቅርታ የጠየቁት በአሜሪካ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ሲሆን ሴናተር ኪም ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒቲ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያዊያን ስለጦርነቱ እውነታና መሬት ላይ ስላለው ሃቅ እንዳስረዷቸው ገልጸዋል።

በአሜሪካ የጆርጂያ ሴናተር ኪም ጃክሰን በተለያዩ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች እና በኢሜል በሚደርሱኝ መልዕክቶች ኢትዮጵያዊያን ከትግራይ ሕዝብ ጋር ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለባቸው አሳውቀውኛል፤ ወንድሞቻችን፣ እህቶቻችን እና ጓደኞቻችን ናቸው ሲሉም በተደጋጋሚ በኢሜል ገልጸውልኛል ብለዋል፡፡

እኔም አሁን የደረስኩበትን እውነታ ከግምት ሳላስገባ ቀድሞ በደረሰኝ የሕወሓት ደጋፊዎች ሀሰት መረጃ ብቻ የተሳሳተ አቋም ይዤ ነበር ሲሉም አክለዋል፡፡

እውነታውን እንዳይ ስላደረጋችሁ አመሰግናለሁ ያሉት ሴናተሯ ለፈጠርኩት ስህተትም ሙሉ ኃላፊነት ወስጄ ለማረም እሠራለሁ፤ የኢትዮጵያ መንግሥትንና ሕዝቡን ይቅርታ እጠይቃለሁ ነው ያሉት ባደረጉት ንግግራቸው፡፡
ዘገባው የዋልታ ነው

18/04/2022

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን የተዛባ ፖሊሲ እንዲያቆሙ ሩስያ ጠየቀች

ወላይታ ሶዶ፤ ሚያዚያ 10/2014 ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉትን የተዛባ ፖሊሲ እንዲያቆሙ ሩስያ ጠየቀች።

ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ በተናጠል ፖለቲካዊ ጫና በማሳደር እና ኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ በመጣል የሚከተሉትን የተዛባ ፖሊሲ እንዲያቆሙ ሩስያ ጠየቀች።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ስለኢትዮጵያ በተደረገ ውይይት ላይ አስተያየት የሰጡት የሩስያ ምክትል ቋሚ ተወካይ አና ኤስቲግኒቫ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በኢትዮጵያ እና በቀጣናው ሰላም ለማምጣት የሚያደርጉትን የጋራ ጥረት እናበረታታለን ብለዋል።

18/04/2022

"ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ እንዲሰጡ ተወሰነ" - ትምህርት ሚኒስቴር

መኮራረጅ፣ የፈተና ስርቆትና ሌሎች ችግሮችን ለማስቀረት ከዚህ በኋላ ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በትምህርር ቤቶች ሳይሆን በፌደራል ተቋማት ውስጥ ብቻ የሚሰጡ ይሆናል ሲሉ ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ተናገሩ።

ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት የትምህርት ጥራት ላይ እንሰራለን ያሉት ሚኒስትሩ አንዱ ችግር ከሀገር አቀፍ ፈተና ጋር ተያይዞ የሚነሳ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል።

ሚኒስቴሩ የ2014 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተናን ለመስጠት የሚያስችሉ 1 ሚሊዮን ታብሌቶችን በማስመጣት ላይ መሆኑንም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ገልጸዋል።

18/04/2022

ኢትዮጵያ እንደው እንደዋዛ የተፈጠረች አገር አይደለችም፡፡ ኢትዮጵያ የዘመናት ውጣ ውረድን ድል አድርገው በመጡ ህዘቦች የተገነባች አገር ናት፡፡

የኢትዮጵያዊነት እሴት መሰረቱ ጽኑ ነው፡፡ አባቶቻችን ደማቸውን እንደ ጅረት አፍሰው ነገን አስበው በደማቸው ያጸኗት አገር ናት ኢትዮጵያ፡፡

ዛሬ አገር ህመም ላይ ነች፡፡ በአገራችን ዘመናትን የተሻገረው የሃሰት ትርክት እርስ በእርስ መቋሰልን ፈጥሯል፡፡

ኢትዮጵያዊነት እሴትን ማጠልሽት፤ ኢትዮጵያንም ማፈራረስ ግባቸው በሆኑና ጭካኔ መለያቸው በሆነ እንደ እፉኝት ልጆቻቸውን በሚሰለቅጡና የሰው ሽታ በሌላቸው ቡድኖች ዜጎች ሰሰዉ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡

እነዚህ ኃይሎች መነሻቸውም መዳረሻቸውም አገር መበታተን ነው፡፡ አዎ አገር ከፈረሰች፤ እርስ በእርስ መስማማታችን፣ መተሳሳባችን፣ መደጋገፋችን ከእኛ እርቆ አገራችን አንድነቷ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ከሆነ በእርግጥም ድሉ የእፉኝቶች ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ትርክት፣ አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈሉ አገርና ህዝብ እንዳይረጋጉ ማድረግ መጨረሻው በህዝብ ዘንድ ቁጣን መጫር እና በአገሩና በመሪዎቹ ላይ ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ነው፡፡

የማንወጣው የሚመስለውን ተራራ በጽናት መሻገር የሚቻለው ወደፊት የሚጠብቀንን የብርሃን ወጋገን በተስፋ ማየት ስንችል ብቻ ነው፡፡

አገራችን አሁን የሚያስፈልጋት ከትናንት ተምሮ ዛሬን አስተካክሎ የተሻለች ነገን መፍጠር የሚችል ቁመና ያለው ዜጋ መሆን ስንችል ብቻ ነው፡፡

አገር እኛ ነው የምትሻው፡፡ አገራችን የተጋረጠባትን አደጋ ዙሪያ መለሱን ቃኝቶ በተረጋጋ መንፈስ የመፍትሄ አካል በመሆን መወጣት እንድትችል አቅም መሆን ያስፈልጋል፡፡

ኢትዮጵያ ጸንታ የኖረችው በዜጎቿ ነው፡፡ ዛሬም የምትጸናው እና ችግሮቿን የምትሻገር በዜጎቿ ነው፡፡ በመሆኑም የተረጋጋ ህዝብና መንግስት እንዲፈጠር ካስፈለገ ሁሉም ከተከለለበት ቅርፊት ራሱን ገልጦ በማውጣት ለኢትዮጵያዊነት መኖር እና መስራት ይገባዋል፡፡

16/04/2022

ወጣቶች -በምክንያትና በስሌት የሚመሩ ኃይሎች ፣

ወጣቶች በሀገራችን የፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ ልዩ ሥፍራ አላቸዉ። ከ19 60ዎቹ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች እስከ አዲሱ የሀገራችን የለዉጥ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ወጣቶች አሻራ ጉልህ ነዉ።

ብልጽግና ደግሞ በትዉልድ ቅብብሎሽ እየተረጋገጠ የሚሄድ ብሩህ የጉዞ ሂደት ነዉ። ብልጽግና በዜጎች የነቃ ተሳትፎ እዉን እየሆነ የሚቀጥል የትዉልዶች የቤት ስራ ነዉ።

ለዚህም ነዉ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ ብቻ ሳይሆኑ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ባለቤትም ናቸዉ የሚለዉ ብልጽግና ፓርቲ።

ወጣቱ የዛሬዋም የነገዋም ኢትዮጵያ የለዉጥ ተዋናይና ተስፋ ነዉ።

ብልጽግና ፓርቲ የወጣቱን ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎችና ችግሮች መፍታት የሀገራችንን ችግሮች በወሳኝ መልኩ መፍታት ነዉ ብሎ ያምናል። ኢትዮጵያ የወጣቶች ሀገር ናትና ለወጣቱ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት የሚሠራ ሥራ ፋይዳዉ ከፍተኛ ነዉ።

የበለፀገች ሀገር መፍጠር የወጣቱን ትጋት ይጠይቃል። ወጣቱ ከማህበራዊ ሚዲያዎች ጫና፣ ከፅንፈኛ አስተሳሰብና ተግባር ራሱን በመከላከል ለዘላቂ ጥቅሙ ዘብ መቆም አለበት።

አሁናዊ ሀገራዊ ኢኮኖሚያዊ ፣ የፖለቲካዊና ማህበራዊ ችግሮችን በመፍታቱ ሂደትም ወጣቱ የመፍትሄ ቁልፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ከሴራ ፖለታካዉ ዉዥንብርና የመጠፋፋት ፖለቲካ ሰለባ ላለመሆንም በምክንያታዊነት መርህና በአስታዋይነት መመራት ይኖርበታል ።

ወጣቶች _ለኢትዮጵያ ለዉጥና መፃኢ ተስፋ የሚተጉ ኃይሎች ናቸዉና ብዙ ይጠበቅባቸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ ዉዥንብሮችን ቆም ብሎ ማጥራት፣ በስሜት ሳይሆን በሰሌት መመራት የወቅቱን ፈተና ለመሻገር ጠቃሚ ነዉ።

ወጣቶች _ በምክንያትና በሰሌት የሚመሩ ኃይሎች መሆን ይጠበቅባቸዋል ። ምክንያታዊነትና ስሌት ለኢትዮጵያ ግንባታ መሠረታዊ ነዉ።

16/04/2022

ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

ወላይታ ሶዶ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ጽ/ቤት ምርጫውን ተከትሎ ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም የግዙፉ ሰብአዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅት ኢትዮጵያ የቦርድ አባል ሆና መመረጧ በመላው ዓለም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት ኢትዮጵያን ጨምሮ የተሻለ ሥራ እንዲከውን ኃላፊነቷን ትወጣለች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የድርጅቱ አስፈፃሚ ቦርድ የተቋሙ የበላይ አስተዳዳሪ ሲሆን፥ 36 የተመድ ወይም የተባበሩት መንግስታት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) አባል ሀገራትን የያዘ ነው።

ቦርዱ ለድርጅቱ ድጋፍንና የፖሊሲ አቅጣጫ የሚያደርግ ሲሆን፥ ስራውንም ይከታተላል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hawassa tabour times posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share