Gerba mereja

Gerba mereja ልዩ የመረጃ ማዕከል የሆነውን ፔጃችንን ላይክ በማድረግ መረጃ ይቀበሉ ያቀብሉ ይሳተፉ

12/10/2021

ሰላም ውድ የገርባ ልጆች እንደምን አላችሁ?
የመተባበር መንፈስ የመረዳዳት ልምዳችን ደስና ይበል የሚያስብል ነው። ከህፃን እስከ አዛውንት በርብርብ መንግስትን የሚያስንቅ ትምህርትቤት ገንብተን አስረክበናል።ወደፊትም መሰልና የበለጡ ስራዎችን እንደምንሰራ እጂጉን አምናለሁ።ሆኖም የማህበረሰባችንን ለልማት የሚዘረጋውን እጁ እንዳይዝል ረፍት የለሽ የመዋጮ ስድር ባይኖርና መንግስት መሸፈን ያለበትን ነገር እንዲሸፍን ጫና የመደረግ ልምድ ቢኖር መልካም ነው።ምክኒያቱም የገርባ ህዝብ ሁሉንም ነገር በራሱ እንዲሸፍን ከመንግስት በኩል ምልከታ እየተፈጠረ በመሆኑ ለዚህም አንድ ወዳጄ እንደነገረኝ ከሆነ የትምህርት ቤታችን ዳይሬክተር ከወረዳም ሆነ ከበላይ አካል ለሚጠይቁት ማናቸውም የይሟላልኝ ጥያቄ ከህዝብ እንዲያገኙ የመመለስ ሁኔታ መፈጠሩና በዳይሬክተሩ የግል ጥረት እንጂ ምንም አይነት የማስተባበር እና የመደገፍ ፍላጎት አለመኖር ይታያል። ስለዚህ የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤትም ሆነ ሌሎች ሴክተሮች የገርባን ህዝብ ልማት የኛ ነው ብለው ለምርጫ ቅስቀሳ እንደተጠቀሙበት ሁሉ ዛሬም ቢያንስ የመንግስት በጀት ባይኖር እንኳ የኔነት ስሜት ኖሯቸው ትምህርት ቤቱ የጎደለውን ለማሟላት ሃላፊነት ወስደው የማስተባበር ስራ መስራት ይጠበቅባቸው ነበር። ለአልማ መዋጮ ወይም ለተለያዩ ሪፖርቶች ብቻ የሚፈልገንን የወረዳና ከዚያ በላይ ያለ የመንግስት አካል ከአሁን ብኋላ ሲጠቅመን ብቻ ነው የምንጠቅመው የሚል እምነት አለኝ። እናለማለን ይደግፈን !!! ለከተማችን ማንኛውም ልማት እናበረክታለን !!! ቃሉ ግን ....

ሰላም ያገሬ ልጆች

13/07/2021

ይሰማል!!!!!

13/07/2021

የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው ለሚለው ተረት የገርባን ልጅ ውሃ ጠማው ቢባል ይገባል ። ከከተማቺን አልፎ ለባቲ ማንቆርቆር የቻለ የቡርቂቄ ሜዳ ዛሬ ላይ ጠብታ ውሀ የነፈገን ምን ቢከፋው ነው።
ለመሆኑ ውሃ ልማት ነው ውሃ ጥፋት ተቋማችን ? በመብራት መቆራረጥ ምክኒያት ከሆነ በጀኔሬተር ለምን አያመርትም? ለመሆኑ ተቋሙ አትራፊ የንግድ ድርጅትነው ወይስ አገልግሎት ሰጪ? ከምንም በላይ የህዝብ አገልገሎት ና ጥቅም ይቀድማል ። እባካቹ የተቋሙ ባለሙያዎች ሃላፊዎችና የቦርድ አመራሮች አስቸኳይ መፍትሄ እንድታደርጉ አጥብቀን እንጠይቃለን ።
አትርሱ እየበላ ሲያንቀው ከቧንቧ መጠጣት የለመደ ህዝብ ነው የምታገለግሉት ። ካልሆነ ግን እንደ ህዝብ ሌላ የመፍትሄ አማራጭ ለመጠቀም ግድ ይለናል።

ይድረስ
04/06/2021

ይድረስ

“ይሄ ህዝብ ሃላፊነቱን ለመወጣት ራሱን ማዘጋጀት አለበት‼”

“በሽምግልና የተያዙ ጉዳዮች በዚህ ሳምንት ውጤት ላይ የማይደርሱ ከሆነ የጉባዔውን ውሳኔ ለማስፈፀም እንገደዳለን።..
ያሉትን አመራጮች ሁሉ ተሞክረዋል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ግልፅና የማያሻማ አቋም ላይ ሊደረስ ይገባል።
ይሄ ህዝብ ሃላፊነቱን ለመወጣት ራሱን ማዘጋጀት አለበት፤
አማራጭ የለውም።” ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ ከRN05 ጋር ባደረጉት ቆይታ ከተናገሩ ተቀንጭቦ የተወሰደ።

21/05/2021

ሚዲያዎችና እስልምና ከሰሞኑ..
የሀሩን ሚዲያ ዶክመንቴሽን ክፍል ከሰሞኑ የተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ምልከታ በማድረግ ሳምፕል ሚዲያዎችን በመምረጥ መረጃዎችን የሰበሰበ ሲሆን የተግባሩ ዋና ጭብጥም እነዚህ ሚዲያዎች እስልምናን በተመለከተ ያቀረቧቸውን ዘገባዎች ብዛት መመርመር ነው። ለጥናቱ ያለፉት ሁለት ሳምንታትን ብቻ መሠረት በማድረግ ምልከታ የደረገ ሲሆን ውጤቱ እንደሚከተለው ነው።
ካሉ ሚዲያዎች ውስጥ ለሳምፕል ሶስት ሚዲያዎችን የመረጥን ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ ሀይማኖታዊ (የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አማኞች) ሲሆን ሌሎቹ አለማዊ /Secular/ ሚዲያ ነን ብለው ራሳቸውን የሚገልፁ ናቸው። በነዚህ ሚዲያዎች በባለፈው ሁለት ሳምንት እስልምናንና ሙስሊሞችን አስመልክቶ የተሰሩ ዘገባዎችን ስንመለከት በድምሩ (የሁሉም) 25 ፕሮግራሞችን የሰሩ ሲሆን በዝርዝር ደግሞ ሀይማኖታዊው ሚዲያ በሁለት ሳምንት ውስጥ 7 ፕሮግራም ሰርቷል። በተመሳሳይ ራሳቸውን አለማዊ በሚል የጠሩ አካላት ደግሞ አንደኛው 11 ሌላኛው 7 በድምሩ 18 ፕሮግራም ሰርተዋል።
ከሰሞኑ ሚዳያዎቹ በተናበበ መልኩ ስለ እስልምና የሚሰሯቸውን እንደ አሸን የፈሉ ፕሮግራሞች የተመለከተ ሰው ከጀርባው ምን አይነት እቅዶች እንዳሉ ፍንትው አድርገው ይገልፁልናል። ሀሩን ሚዲያ በዚህ ዘገባ ዙሪያ ዝርዝር ውይይት በምሽቱ ፕሮግራማችን ወደናንተ የሚያቀርብ ይሆናል።
© ሀሩን ሚዲያ

21/05/2021
21/05/2021

በብሔራዊ የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳይ ላይ የሙስሊሙን መሳተፍ በስጋት የሚተነትኑ ኃይሎች ትውልዱን ቢገዳደሩት አሳ ጎርጓሪ ሲል ዶሴው ይገለጥ እያለ ነው።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ከዚህ ቀደም የእጩዎችን መዘርዝር ይፋ አድርጎ ነበር።በዚያ መረጃ ላይ ተጨማሪ ፓራሜትር አጣርተው ይህንን ደታ ይዘው መጥተዋል።

በነካካችሁት ቁጥር ቆፍሮ የሚያድር ትውልድ ተፈጥሮባችሁ ምን ታደርጉት እንግዲህ?

15/05/2021
13/05/2021

ብዙ ተከታይ በሚኖረው በዚ ህ ፔጅ መረጃ ማስተላለፍ ከፈለጉ በውስጥ መስመር ያድርሱን

13/05/2021

ሰላም የፔጃችን ቤተሰቦች በዚህ ፔጅ የፈለጋቹትን ገርባን የተመለከተ መረጃ በግልፅና በውስጥ መስመር እንደየመረጃው ሁኔታ እናደርሳለን ከእርሶ የሚጠበቀው ፔጃችንን ላይክ ማድረግና በውስጥ መስመር ወይም በኮሜንት የሚፈልጉትን መረጃ ይጠይቁን

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gerba mereja posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share