Semera Daily News

  • Home
  • Semera Daily News
11/08/2022

Asaaki korrkorooy beeri Qunnxa Foqo👌✌️

ፖለቲካችንን እናሰልጥን! ፖለቲካና ሀይማኖት ይቀራረባል:: ሁለቱም  በግል እምነት ላይ ይመሰረታል:: ሀገር ደግሞ ለሁሉም እኩል ይሆን ዘንድ ይጠበቃል:: አባቶቻችን ከረጅም ዓመታት በፊት "ሀ...
03/07/2022

ፖለቲካችንን እናሰልጥን!

ፖለቲካና ሀይማኖት ይቀራረባል:: ሁለቱም በግል እምነት ላይ ይመሰረታል:: ሀገር ደግሞ ለሁሉም እኩል ይሆን ዘንድ ይጠበቃል:: አባቶቻችን ከረጅም ዓመታት በፊት "ሀገር የጋራ ሀይማኖት የግል " ያሉት ለዚሁ ይመስላል:: ትላንትና ዛሬ በሰመራ ዩንቨርሲቲ አስተባባሪነት በሰመራ ከተማ " ሀገር የጋራ ፖለቲካ የግል" ብለናል:: የአፋር ህዝብ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር ሙሳ አደምና እኔ ብልፅግና በአንድ መድረክ ምሁራንን አወያይተናል! ለብዙዎች ትንሽ ሊመስል ይችላል:: በተጨባጭ ግን ፖለቲካችን ሊሰለጥን መሆኑን ያሳያል:: በየደረጃዉ ፖለቲካችን የሚሰለጥን ከሆነ የኢትዮጵያችን ልዕልና እጅግ ይፈጥናል!

Taye Dendea Aredo

የኢንጂነር አኢሻ ሙሀመድ አባት ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ ወደአኼራ ሔደዋል።የኢፌዲሪ የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አዒሻ አባት ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ ኑሯቸው የነበረ በአፋር ሰመራ/...
03/07/2022

የኢንጂነር አኢሻ ሙሀመድ አባት ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ ወደአኼራ ሔደዋል።

የኢፌዲሪ የመስኖና ቆላማ አከባቢዎች ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አዒሻ አባት ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ ኑሯቸው የነበረ በአፋር ሰመራ/ሎጊያ ሲሆን ባለፉት ጊዜያት የጤና እክል ገጥሟችው በዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታል ክትትል ሲያደርጉ ከቆዩ ቡኃላ የተሻለ ሕክምና ለማደረግ ወደአዲስ አበበ አምርተዉ ነበር።

የአሏህ ውሳኔ ሆነና፣ በዛሬው እለት ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ ወደማይቀረው አኼራ ሔድዋል።

ሀጅ ሙሀመድ ሙሳ በአፋር ህዝብ ዘንድ እጅግ የተከበሩና የሚታገሩ፣ አስታራቂና የሀገር ሽማግሌ፣ ታላቅም አባት ነበሩ።

አሏህ(ሱ.ወ) መልካም ስራቸውን ይቀበላቸው፤
የጀነተል-ፊርደዉስ ሙሽሪነትም ይወፍቃቸው
አሚን🤲

ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቸው እንዲሁም ለመላው የአፋር ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን።🤲🤲

ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን

24/02/2022

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፤ከሰዓታት በፊት ዋና ከተማዋን ለ'ቀው አምልጠዋል።

(ዘለንስኪ የተሰወሩት፤ ቆላ ተምቤን ይሁን አለያም ሌላ ቦታ፤እስካሁን አልታወቀም)

በኢትዮጵያ ጉዳይ "ያዙኝ ልቀቁኝ!" እያለ ሲፎክር የነበረው ተመድም፤ ሩሲያ ላይ ሲሆን ነጠላውን አዘቅዝቆ መማጸን ይዟል።

እነ አሜሪካን ተማምና ያለ አቅሟ ሩሲያ ጋር ስትገላገል የቆዬችው ዩክሬንም፦"የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም" የሚለው ብሂል የደረሰባት ትመስላለች።

Dereje habteweld

ሰበር ዜና ❗️ ተጀመረ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ፑቲን ጦራቸው ሙሉ ዩክሬን ላይ እንዲሰማራ እና እንዲቆጣጠር አዘዙ። ከዩክሬን ጋር ውጊያው ተጀመረ። ዩክሬንን አለንልሽ ሲሉ የነበሩት አሜሪካ እና ...
24/02/2022

ሰበር ዜና ❗️

ተጀመረ የሩሲያው ፕሬዘዳንት ፑቲን ጦራቸው ሙሉ ዩክሬን ላይ እንዲሰማራ እና እንዲቆጣጠር አዘዙ። ከዩክሬን ጋር ውጊያው ተጀመረ። ዩክሬንን አለንልሽ ሲሉ የነበሩት አሜሪካ እና ምእራባውያን ጦር እንደማይልኩ ተናግረው ስትወረር ቆመው እያዩ ነው። የዩክሬን መሪ እስከቻልነው እንከላከላለን ብለዋል።
ያስገርማል 🤔

ትንሽ ብቻ ጠብቅ‼ መሀመድ አልአሩሲ ከግብፅና ሳውዲ ተንታኞች ጋር በአልጀዚራ ተናንቋል። አወያዩ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ያለግብፅ ፍቃድ ናይልን ለመገደብ፣ እየገነባች ነው ያለፍቃድ ግን ውሃ መያዝ ...
20/02/2022

ትንሽ ብቻ ጠብቅ‼

መሀመድ አልአሩሲ ከግብፅና ሳውዲ ተንታኞች ጋር በአልጀዚራ ተናንቋል።

አወያዩ ጋዜጠኛ ኢትዮጵያ ያለግብፅ ፍቃድ ናይልን ለመገደብ፣ እየገነባች ነው ያለፍቃድ ግን ውሃ መያዝ አትችልም በሚለው የግብፁና የሳውዲው ተንታኝ ሀሳብ ላይ የመሀመድ አልአሩሲን መልስ ይጠይቀዋል።

አልአሩሲ ሲመልስ

እንገድበዋለን፣ ውሃም እንይዛለን። ይገርመሃል ያለፍቃዳችሁ ሀይል እናመነጫለን። ምክንያቱም ይህ አላህ ለኢትዮጵያ የሰጣት የተፈጥሮ ፀጋ ነውና የማንንም ፍቃድ አትሻም።
አንተኛው የሳውዲ ዜጋ ልጠይቅህ፣

ነዳጅ ስታወጡ ኢትዮጵያን አስፈቅዳቹሃል

ብሎ ጠየቀ

የተጠየቀው በቁጣ

"ለምን እናንተን እናስፈቅዳለን። ነዳጁ መሬታችን ላይ የወጣ የኛ ሀብት አይደል? "

ብሎ መለሰ

አልአሩሲ እየሳቀ፣

"እኔም የምልህ በኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ፈቃጅና ከልካይ እናንተን ማን አደረጋችሁ? ከመሬታችን ላይ 86 በመቶ የሚመነጭ ሀብት ፍቃድ የምንጠይቀው አብደን ነው? አንጠይቅም" አለ።

ወደ ግብፃዊው እያመለከተ

"አንተ ግብፃዊውም ኢትዮጵያ አብረን እንመከር ማለቷ ፍቃድ ለመጠየቅ አይደለም። መልካም ጉርብትና ስለሆነ መተማመኛ ለመስጠት ነው። አስዋንንን ስትገነቡ አላስፈቀዳችሁንም። እኛም ፍቃድ አንጠይቅም። አለማቀፍ መርህ ይህ ነው። ቱርክ አላስፈቀደችም። አሜሪካ አላስፈቀደችም። ቻይና አላስፈቀደችም። ኢትዮጵያም አታስፈቅድም። ለምሳሌ ጉዳዩን እንገልብጠውና ግብፅ የናይል መነሻ ብትሆን እና ኢትዮጵያ የግብፅ ቦታ ላይ ብትሆን ግድብ ለመገንባት ታስፈቅዱን ነበረ? "

ብሎ ጠየቀው።

ግብፃዊው ዝም አለ። ፈገግ አለ። ፈገግ አባባሉ "ለምን እናስፈቅዳለን" የሚል ትዕቢት አለበት።

"የግብፅ ጦር ታላቅ ነው። ኢትዮጵያውያን ሆይ አትፈታተኑን" አለ ግብፃዊው።

"በጦርነት ኢትዮጵያን አያቶችህ ያውቋታል። ትምህርት ሰጥታ መልሳለች። በፍቅር እንጂ በፀብ ኢትዮጵያን ማንበርከክ አትችሉም። ሀገራችን በትዕቢተኞች መልካም ፍቃድ አልቆመችም። በልጆችዋ ጀግንነት ነው እዚህ የደረሰችው።"

አለ አልአሩሲ ጥርሱን በመግጠም

"እስቲ ውሃ ያዙና መልሳችንን ታያላችሁ" አለ ግብፃዊው

"ማብራት አመንጭተን እናሳይህ የለም? ትንሽ ብቻ ጠብቅ።"

የአልጀዚራው ጋዜጠኛ ወደ ሌላ ጥያቄ ዞረ።

አልአሩሲ በራስመተማመን ጥያቄውን ይጠብቅ ያዘ።

እነሆ ዛሬ ቀኑ ደረሰ።

ጀግናችን አልአሩሲ ሆይ እናት ሀገርህ ኢትዮጵያ ታመሰግንሃለች 🙏

20/02/2022

ስለ ታላቁ የሕዳሴው ግድባችን እንኳን ደስ አለን መሪ እና መንግሥት ያልፋሉ ሀገር ግን ትቀጥላለች።
musa adem omer

ተጀመረ...!አሸባሪው ቡድን በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የዘር ፍጅት ተቃውሞ በቤልጅየም ብራሰልስ በ6ኛው የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች የጋራ ጉባኤ መሰብሰብያ...
18/02/2022

ተጀመረ...!

አሸባሪው ቡድን በአፋርና በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው የዘር ፍጅት ተቃውሞ በቤልጅየም ብራሰልስ በ6ኛው የአፍሪካ ህብረትና የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች የጋራ ጉባኤ መሰብሰብያ አዳራሽ ፊትለፊት።
Ahmed habib

  : የወልቃይትን መንገድ ብቻ እናስከፍት ስል አልሰማ ብላችሁኝ ሸዋሮቢት ድረስ በመሄድ ልጆቻችንን አስፈጅተን ተመለስን:: ሌ/ጄ ሳድቃን ገ/ትንሳኤ ከህወሓት አመራሮች ጋር በተደረገው ስብሰባ...
16/02/2022

: የወልቃይትን መንገድ ብቻ እናስከፍት ስል አልሰማ ብላችሁኝ ሸዋሮቢት ድረስ በመሄድ ልጆቻችንን አስፈጅተን ተመለስን::

ሌ/ጄ ሳድቃን ገ/ትንሳኤ ከህወሓት አመራሮች ጋር በተደረገው ስብሰባ ላይ በልዩነት ከተናገሩት የተወሰደ::

በፖሊስ የሚፈለገው የሃይማኖት መምሕር ሸሽቶ እንግሊዝ መግባቱ ተሰማ         ማክሰኞ የካቲት 8፣ 2014 ― በፖሊስ የሚፈለገው የሃይማኖት መምህሩ ምሕረተአብ አሰፋ ሸሽቶ እንግሊዝ አገር ...
15/02/2022

በፖሊስ የሚፈለገው የሃይማኖት መምሕር ሸሽቶ እንግሊዝ መግባቱ ተሰማ

ማክሰኞ የካቲት 8፣ 2014 ― በፖሊስ የሚፈለገው የሃይማኖት መምህሩ ምሕረተአብ አሰፋ ሸሽቶ እንግሊዝ አገር መግባቱ ተሰምቷል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ  ሠመራ ገቡ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆና የተባ...
09/02/2022

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንትና የተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሠመራ ገቡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ ዛሬ ሠመራ ከተማ ገቡ።
ďťż
ሠመራ ሱልጣን አሊሚራህ ሃንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን በተለይ ከዞን ሁለት ተፈናቅለው ሀመድ ኤላ፣ አፍዴራና ሰመራ ያሉትን ተፈናቃዮች ያስጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጉዟችን እስከ መቀሌ ነው ኡቱካ✊✊💪💪❤
27/01/2022

ጉዟችን እስከ መቀሌ ነው

ኡቱካ✊✊💪💪❤

06/01/2022
የአእምሮ በረሃ እንጂ የመሬት በረሃ የለውም ! '' ":-  አምባሳደር  ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ                              **********  ታሀሳስ 23/2014...
02/01/2022

የአእምሮ በረሃ እንጂ የመሬት በረሃ የለውም ! '' ":- አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ
**********
ታሀሳስ 23/2014 ( አፋ.ብ.መ.ድ. )......
በእውነት ነው የምልክ እዚህ በረሃ ላይ እንደዚህ እያየህው ለማመን የሚከብድ ግን እውነት የሆነ ነገር ስመለከት ለካ ''የአእምሮ በረሃ እንጂ የመሬት በረሃ የለውም'' ካለሙት መልማት ይችላል ሲሉ ሰው ለሰው ድርጀት አምባሳደር ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ገልፀዋል ።

ይህን የገለፁት አምባሳደር ሀይሌ ዛሬ አፋር ሰመራ ተገኝተው የሰው ለሰው ድርጅት ለአፉር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ይዘው የመጡትን ካስረከቡ ቦሀላ የክልሉን የቆላማ ሰንዴ ልማት እና ሊሎች የመስኖ ልማት ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነበር ።

ባየሁት ነገር በጣም ተገርሚለሁ የዛሬ ሁለት አመት ወይም ሶስት አመት አፋር ''እዚህ ቦታላይ ወደ ውጭ የሚላክ ምርት ካልሰራሁ በእውነት ነው የምልክ የለሁም'' ማለት ነው በማለት አምባሳደር ሀይሌ ለራሳቸው ቃል መግባታቸውን ተናግሯል ።

በመጨረሻም አምባሳደር ሀይሌ ዲያስፎራዎች እና ባለሀብቶች አፋርን ይጎብኙ በሙሉ አቅማቸውም ኢንቨስት ቢያደር የውሀ፣ የመሬት እና የአየር ንብረት ችግር የለም በተጨባጭ ያየሁትን ነው የምመሰክረው ብሏል።

በም/ርዕሠ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት አቶ አሊ ሁሴን ዌኢሳ በበኩላቸው በአፋር ክልል 22ወንዞች አሉ ከነዚህ ወንዞች ውስጥ ትልቁ አዋሽ ነው ይሁን እና አዋሽን እንኳን በጣም በትንሹ ነው እየተጠቀምን ያለነው ገና ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ።

በክልላችን ውሀእና መሬት እያለን የጠፋው የሚሰራ ሰው ነው በአሁን ጊዜ የተወሰነ የተጀመሩ ነገሮች ቢኖርም ገና ቡዙ ይቀራል ሰፊ የመሬት እና የውሀ ሀብት ካለን አኳያ በማለት ዲያስፎራዎች እና ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉም መልዕክት አስተላልፈዋል አቶ አሊ ሁሴን ።

የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ላይ ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት  መድረክ ተጠናቀቀ።***...
02/01/2022

የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ላይ ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።
************************************************
ሰመራ 23/04/2014 የአፋር ክልል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች በሚል ስያካሄዱ የነበሩ ውይይት መድረክ ተጠናቀቀ።

የውይይት መድረኩን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አዋል አርባ እና የአፋር ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር ኢሴ አዳም በወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ በደህረ ጦርነት መዛነፎች እና እርምቶች ያሉትን ጉዳዮች ለአመራሩ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አዋል አርባ በህብረ ብሔራዊ ዘመቻ ከተመዘገቡ ድሎች መካከል ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን ለማዳን በውጭም ሆነ በሀገር ውስጥ የፈጠሩት አገራዊ አንድነትና ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በድህረ ጦርነቱ ተግባሮችም ተጠናክሮ እንድቀጥሉ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን የማፍረስ አጀንዳ ያላቸውን የውስጥና የውጭ ኃይሎችን ወረራ እየመከትን የተጀመሩ የብልጽግና ጉዞ ማስቀጠል የሚያስችሉ ዘላቂ ሠላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በትኩረት እንደሚሠራም ገልጸዋል።

አክለውም ተገደን በገባንበት ጦርነት የተገኙትን ሁለንተናዊ ድሎች ጠብቆ የማስፋትና ወደ ዘላቂ ሰላምና ልማት ማሸጋገር ላይ ትኩረት መሰጠት እንደአለበት ገልጿል።

የተገኘውን ድል ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ሰብአዊና የፀጥታ ፈተናዎችን በብቃት መፍታትና በአግባቡ መምራትም እኩል ትኩረት ያገኛሉ ብሏል፡፡

በተጨማሪም ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት የጋራ አቋም፣ ወጥ እሳቤ እና ተቀራራቢ አፈፃፀም አሁን ካለው አመራር የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የአፋር ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢሴ አዳም በበኩላቸው የምክክር መድረኩ ዓላማ የክልሉን አመራር ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት እና ማብቃት ነው ብለዋል፡፡

ጦርነቱ በህልውና ላይ የመጣ በመሆኑ ህልውናችንን ለመመከት የፈጠርነውን አንድነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና አቅም አድርገን መጠቀም አለብን ሲሉም ገልጸዋል።

አመራሩ በተለይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የተፈጠረውን ትብብርና አንድነት በቀጣይነት ለልማት መጠቀም እንዳለበት ነው የተናገሩት፡፡

አንድነትን ማጠናከር እና በድል ማግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ቀድሞ ለይቶ መፍታት ከውይይት መድረኩ የሚጠበቅ ውጤት እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ዛሬ ሶስተኛ ቀን በያዘው በዚሁ መድረክ የክልሉ ካቢኔ አባላት፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና የዞንና የወረዳ አስተባባሪ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን በዝርዝር ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይቱ በዞን ፣ በወረዳ ፣ በከተሞች ፣ በቀበሌ እና እሰከ ህዝብ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

እናመሰግናለን!!!የአሜሪካ ኮንግረስ አባል   ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአግዋ (AGOA) እንዳያግድና እንድትቆይ የሚቻለኝን ያህል እየሰራሁ ነው፣ ተስፋም አለኝ ሲሉ ለኢትዮጵያውያን ...
15/12/2021

እናመሰግናለን!!!

የአሜሪካ ኮንግረስ አባል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢትዮጵያን ከአግዋ (AGOA) እንዳያግድና እንድትቆይ የሚቻለኝን ያህል እየሰራሁ ነው፣ ተስፋም አለኝ ሲሉ ለኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሲቪክ ካውንስል ዛሬ አረጋገጡ።

እናመሰግናለን ክብርት ሚኒሰቴር ዳግማዊት ሞገስ!!!የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለአፋር የ10ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
09/12/2021

እናመሰግናለን ክብርት ሚኒሰቴር ዳግማዊት ሞገስ!!!

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ለአፋር የ10ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

የአፋር አናብስት ተዘጋጅቷል!!!የአፋር ክልል መንግስት የሜካናይዝድ ሃይል በትናንትናው እለት አስመርቋል ......ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ የሚያሰጋ ምድራዊ ሃይል አይኖርም። Ahmed Habib...
08/12/2021

የአፋር አናብስት ተዘጋጅቷል!!!

የአፋር ክልል መንግስት የሜካናይዝድ ሃይል በትናንትናው እለት አስመርቋል ......ከዚህ በኋላ ለኢትዮጵያ የሚያሰጋ ምድራዊ ሃይል አይኖርም።

Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጵያ አሸንፋለች🇪🇹🇪🇹

የአፋር ክልል ፖሊስ አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድኑን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየመከተ መሆኑ ተገለፀ********************************************************አዲስ...
04/12/2021

የአፋር ክልል ፖሊስ አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ቡድኑን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየመከተ መሆኑ ተገለፀ
********************************************************
አዲስ አበባ፣ ህዳር 25 ቀን 2014 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፡-
ዘመቻ ለህብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚመራውን ዘመቻ ተከትሎ የፀጥታ አካላት ጥምረት ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለትም በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት በተካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ለመታደም የተገኙት የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ዐሊ ዲኒ በክልሉ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ እና የስራ አፈጻፀም ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው ከህግ ማስከበር ዘመቻው በኋላ መንግስት የጥሞና ጊዜ መስጠቱን ተከትሎ የሀገራችን የፀጥታ ኃይል ከትግራይ ክልል ወረዳዎች ለቆ በመውጣቱ የጁንታው ኃይል ራሱን እንደ አሸናፊ በመቁጠር በክልላችን ወረራ አካሂዷል ብለዋል፡፡
የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይል ከሀገር መከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በአሁኑ ወቅት አሸባሪው የጁንታ ቡድኑን በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየመከተ መሆኑን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በደረሰበት ወረራ የተቆጣው የአፋር ህዝብም ከክልሉ የፀጥታ ሀይል ጎን በመሰለፍ ሰፊ የሆነ የመከላከል ስራ ሰርቷል ብለዋል፡፡ የክልሉን ልዩ ሀይል እና ሚሊሺያን በሰው ሀይል በማጠናከርና ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ አሸባሪ ጁንታው ወሮ የያዘባቸው የአፋር ክልል ወረዳዎችን ማስለቀቅ ተችሏል ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ሀራብ ወረዳ በኩል ወደ ጭፍራ በመግባት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ አውታር የሆነውን የሚሌ መንገድ ለመዝጋት ያለመው ጠላት በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልሉ ልዩ ሀይልና ሚሊሺያ እንዲሁም በሌሎች ክልል ልዩ ሀይል ቅንጅት ከአካባቢው ለቆ እንዲወጣ ተደርጓል ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የአፋር ክልል ፖሊስ ከህዝቡ ጋር በመሆን በጭፍራ ግምባር ላይ ቁጥር ስፍር የሌለው ሞርተር፣ ክላሽኢንኮቭ፣ ዲሽቃ እና ብሬን እንዲሁም ታንክ ከጠላት ሀይል በመማረክ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረክቧል ብለዋል፡፡
የክልሉ ልዩ ሀይል ካሳ ጊታን እና ቡርቃንም በማስለቀቅ በአሁኑ ወቅት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ ወደ ባቲ እየገሰገሰ ይገኛል ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ የክልሉ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታን በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪ ሲሰጡ ክልሉ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ መሆኑንና የውጊያ ግምባር በክልሉ እንደሌለ ጠቁመዋል፡፡
ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ሆነን ጠላትን ከጭፍራ፣ ከካሳ ጊታ እና ከቡርቃ አስወጥተናል ያሉት ኮሚሽነሩ ይህ ማለት ግን ትግሉ አብቅቷል ማለት አይደለም ብለዋል፡፡
ሀገርን ለማፈራረስ የተነሳው ሀይል እስኪጠፋ ድረስ ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጎን በመሆን ይህንን አሸባሪ ሀይል መዋጋቱን እንቀጥላለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡
የአሸባሪው ዓላማ አስፈፃሚዎችንም አድነን በመያዝ ህጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡

 #ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ተላለፈብልጽግና ፓርቲ(ህዳር 25/2014) ከአሸባሪው ህወኃት ጋር ፊት ለፊት በመፋለም ለኢ...
04/12/2021

#ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ተላለፈ

ብልጽግና ፓርቲ(ህዳር 25/2014) ከአሸባሪው ህወኃት ጋር ፊት ለፊት በመፋለም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት መስዋዕት እየከፈለ ለሚገኘው የአፋር ህዝብ የአጋርነትና የድጋፍ ጥሪ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ፡፡

በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤና የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ዛህራ ሁመድ አሸባሪው ህወኃት በአፋር ክልል በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶችን ማድረሱን ጠቅሰው በጥቅምት ወር በተካሄደ ዳሰሳዊ ጥናት መሰረት አፋጣኝ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውና ጥቃቱ በደረሰባቸው ወረዳዎች የተፈናቀሉ ከ360ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

ሰብሳቢዋ አያይዘውም የሽብር ቡድኑ ጥቃት ባደረሰባቸው አካባቢዎች የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን ከጥቅም ውጭ ማድረጉን አውስተው ጥቃት በደረሰባቸው 21 ወረዳዎች ከ1.3 ሚሊዬን በላይ የክልሉ ህዝብ የኢትዮጵያን ህዝብ አስቸኳይ ድጋፍ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን የአርብቶ አደሩ ሀብትና ንብረት በአሸባሪው ህወኃት ቡድን ከመዘረፉም በላይ እንስሳትን በመግደል የጭካኔ ተግባሩን አሳይቷል ብለዋል፡፡

በመጨረሻም ማንኛውንም አይነት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልግ አካል አዋሬ አካባቢ በሚገኘው ሱልጣን አሊ ሚራህ መስጂድ ቅጥር ግቢ በመገኘት መለገስ የሚቻል ሲሆን የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ አካላት ደግሞ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000444559512 ገቢ ማድረግ እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

Prosperity Party - ብልፅግና

የውጭ ሀገር መምህራን የተሳተፉበት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የክተት ጥሪ ዘማች አርሶአደሮች ሰብል ስብሰባ... ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎ...
04/12/2021

የውጭ ሀገር መምህራን የተሳተፉበት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሠራተኞች የክተት ጥሪ ዘማች አርሶአደሮች ሰብል ስብሰባ...

ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት በጎዛምን ወረዳ ቸርተከል ቀበሌ የክተት ጥሪ ዘማች አርሶአደሮችን ሰብል ስብሰባ አከናውነዋል፡፡ በሰብል ስብሰባው ላይ የኢንስትቲዩቱ የውጭ ሀገር መምህራን ተሳትፈውበታል፡፡

በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት የውጭ ሀገር ዜጋ እና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስትቲዩት የኤሌክትሪካል ምህንድስና መምህር ላክሽሜ በዚህ ተግባር መሳተፋቸው እንዳስደሰታቸው በመግለጽ የኢትዮጵያን ሰላምና አንድነት በመመኘት ለህልውና ዘመቻው አጋርነታቸውን መግለጻቸውን ከደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

 ‼️ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲሉ ኪም ጆንግ ዩን ገለፁ❗️*****************"ኢትዮጵያ ባለውለታችን ናት።አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም የማትቀይር ከሆ...
03/12/2021

‼️
ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲሉ ኪም ጆንግ ዩን ገለፁ❗️
*****************

"ኢትዮጵያ ባለውለታችን ናት።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም የማትቀይር ከሆነ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እንገደዳለን ሲሉ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ዩን ገልፀዋል"።

"የአፋር ህዝብ ድሬዳዋን መቼም ላይረሳት በነጭ መዝገብ ላይ አስፍሯታል" አቶ አወል አርባ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፤ በአፋር ክልል በአሸባሪው ትህነግ ለተፈናቀሉ ወገኖቻች...
03/12/2021

"የአፋር ህዝብ ድሬዳዋን መቼም ላይረሳት በነጭ መዝገብ ላይ አስፍሯታል" አቶ አወል አርባ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፤ በአፋር ክልል በአሸባሪው ትህነግ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን፤ ከአስተዳደሩ የተሰበሰበውን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ የቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ በአፋር ግንባር በመገኘት አስረከቡ።

የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ አወል አርባ፤ ከዚህ ቀደም በክልሉ በደረሰው የጎርፍ አደጋ ከድሬዳዋ የተደረገላቸውን ድጋፍ በማስታወስ፤ አስተዳደሩን እና ህዝቡን ለዚህኛውም ድጋፍ አመስግነው፤ "የአፋር ህዝብ ድሬዳዋን መቼም ላይረሳት በነጭ መዝገብ አስፍሯታል" ብለዋል። በጥቁር መዝገብ የሰፈረው አሸባሪው ጁንታና ተባባሪዎቹ በኢትዮጵያዊያን ብርቱ ክንድ ላይመለሱ እንደሚጠፉም አረጋግጠዋል።

ወደ አፋር ግንባር በተጓዘው የአስተዳደሩ ልዑክ ውስጥ፤ ከከንቲባ ከድር ጁሀር በተጨማሪ፤ በምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ፤ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ፤ እንዲሁም አባ ገዳዎች እና ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

  ግንባር!🇪🇹✅የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌትናል ጀነራል በጫ ደበሌ በጭፍራ ግምባር ተገኝተው ለሰራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።ባደረጉት ንግግርም የሰራ...
03/12/2021

ግንባር!🇪🇹✅
የመከላከያ ሚኒስቴር የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ሌትናል ጀነራል በጫ ደበሌ በጭፍራ ግምባር ተገኝተው ለሰራዊት አባላት ንግግር አድርገዋል።

ባደረጉት ንግግርም የሰራዊት አባላቱ ጀግኖች እንደሆኑ ገልፀውላቸዋል ።

አዚህ የምትዋጉት አሸባሪውን ብቻ ሳይሆን ጋላቢዎቻቸውን ጭምር ነው ብለዋል ።

የውስጥ ሀይሎች ለውጪ ወኪል ሆነው ኢትዮጵያን በሚወጉበት ወቅት በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን ሲሉ አስገንዝበዋል ።

ይህ ትውልድ በዚህ ታሪካዊ ወቅት አሸባሪውን የመቅበር እድል በማግኘቱ ሊደሰት ይገባል ብለዋል።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ አወል አርባ ፣ የአፋር ህዝብ መከላከያን እየደገፈ ጠላትን እየመከተ ይገኛል ብለዋል።

ወደ ፊትም የአፋር ህዘብ ሽብርተኛውን እስከመጨረሻው ለመቅበር ሁሉንም ነገር ያደረጋል ብለዋል።

ጀግናው አትሌት ሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በበኩላቸው ፣ እተዋጋችሁ ያላችሁት የአፍሪካንና የጥቁሮችን ውጊያ ነው።

እውነትን ይዛችሁ ስለሞትዋጉ ጠላትን ድል እንደምታደረጉ ጥርጥር የለኝም በማለት የሰራዊቱን ሞራል አነሳስተዋል።

 ❗️ወራሪው የጁንታው ሃይል በካሳጊታና በጭፍራ ግምባር የነበረው የአርሚ 4 እና አርሚ 2 ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ የተበተነው ተበትኖ በአፋር ህዝባዊ ሰራዊትና በጀግናው መከላከያ ሰራዊት የተማረኩ...
01/12/2021

❗️

ወራሪው የጁንታው ሃይል በካሳጊታና በጭፍራ ግምባር የነበረው የአርሚ 4 እና አርሚ 2 ሙሉ ለሙሉ ተደምስሶ የተበተነው ተበትኖ በአፋር ህዝባዊ ሰራዊትና በጀግናው መከላከያ ሰራዊት የተማረኩ ጁንታዎች ናቸው።
[Ahmed Habib Alzarkawi]

30/11/2021
ጁንታው በአፋር አዲስ ጥቃት ከፍቷል!!!ከሸዋሮቢት ተዶቅሶ የተባረረው የጁንታው ሃይል ተሰባስቦ ከሸዋሮቢት 14 ኪ/ሜ ርቀት በምትገኘው ሃዳሌ ኤላ ወረዳ በአፋር ህዝብ ላይ ጥቃት ከፍቷል ጁንታ...
29/11/2021

ጁንታው በአፋር አዲስ ጥቃት ከፍቷል!!!

ከሸዋሮቢት ተዶቅሶ የተባረረው የጁንታው ሃይል ተሰባስቦ ከሸዋሮቢት 14 ኪ/ሜ ርቀት በምትገኘው ሃዳሌ ኤላ ወረዳ በአፋር ህዝብ ላይ ጥቃት ከፍቷል ጁንታው ወደ ወረዳው ለመግባት ዛሬም ትናንትም ከፍተኛ ውጊያ እያካሄደ ይገኛል።

በጭፍራና ካሳጊታ ግምባሮች በመሸነፉ የተበሳጨው የጁንታው ሃይል ባልታሰበ አቅጣጫ ንፁሃን ላይ ጥቃት መክፈቱ ዛሬም ነገም ዋጋ ያስከፍለዋል። Ahmed Habib Alzarkawi

🇪🇹🇪🇹 ኢትዮጵያ አሸንፋለች🇪🇹🇪🇹
Ahmed habib alzekawi

ይናገራል ፎቶ
29/11/2021

ይናገራል ፎቶ

29/11/2021

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለድል ያበቃን የሀገር ፍቅር ነው ብሉዋል

-ከ 80 Million በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ባለቤትና የዓለማችን ታዋቂው አርትስት   የ   ዘመቻን በይፋ ተቀለቅሏል!Damala Badara Akon Thiam ወይም በአጭሩ Akon ይ...
29/11/2021

-ከ 80 Million በላይ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ባለቤትና የዓለማችን ታዋቂው አርትስት የ ዘመቻን በይፋ ተቀለቅሏል!

Damala Badara Akon Thiam ወይም በአጭሩ Akon ይባላል። የዘር ግንዱ ከምዕራባዊቷ ሴኔጋል የሚመዘዘው ትውልደ-ሴኔጋላዊ አሜሪካዊ ታዋቂ ዘፋኝና Song Writer ነው። Akon በዛሬው እለት በኢንስታግራም ፔጁ ላይ "DEFEND AFRICA nomore የሚል ቲ-ሸርትን በመልበስ ዘመቻውን በይፋ ተቀላቅሏል።

- አኮን በማህበራዊ ሚዲያ
~ በፌስቡክ ከ 53 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች፣
~ በቲዊተር ከ 6 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ፣
~ በ U-Tube 10 ሚሊዮን በላይ ተከታይ፣
~ በ ኢንስታግራም ከ 7 ሚሊዮን በላይ
~ በ Deezer ከ 4 ሚሊዮን ተከታዮች በአጠቃላይ ከ 80 million በላይ ተከታዮች ያሉት ታዋቂ አርትስት ነው።

- በአንድ ወቅት Akon በ መፅሄትም የዓለማችን 100 ተፅኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከልም አንዱ በመሆን ሲመረጥ፣ በሙዚቃ ስራው የዓለማችን ውዱ ሽልማት የግራሚ አዋርድ እጩም ነበር።

ይህ ታዋቂ ግለሰብ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ላይ የተጀመረው የውስጥ ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ዘመቻውን መቀላቀሉ የ Nomore እንቅስቃሴ የዓለም አቀፍነቱን ቅርፅ እየያዘ መምጣቱን ያሳያል።

ይቀጥላል!

ጭፍራ ከተማ በልጆቻ አሸብርቃ
28/11/2021

ጭፍራ ከተማ በልጆቻ አሸብርቃ

"በአገር ወዳድነታችን ብዙ ዋጋ እየከፈልን ነው። ያም ሆኖ ግን በባንዳዊነት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት የሚመጣ መከራ ጣፋጭ ነውና እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንን።"የአፋር ክልል ፕሬዝዳን...
28/11/2021

"በአገር ወዳድነታችን ብዙ ዋጋ እየከፈልን ነው። ያም ሆኖ ግን በባንዳዊነት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ በኢትዮጵያዊነት የሚመጣ መከራ ጣፋጭ ነውና እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንን።"

የአፋር ክልል ፕሬዝዳንት የተከበሩ አቶ አወል አርባ

ሰበር ዜና!በኤፌዴሪ ጠቅላይ የጦር አዛዥ ኮሎኔል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሚመራው የአፋር ግንባር የጠላትን ሀይል በመደምሰስ ጭፍራና ቡርቃን ተቆጣጥሯል ::Ⓒᶜᴸᴬˢˢʸ ᴱᴺᵀᴱᴿᵀᴬᴵᴺ...
26/11/2021

ሰበር ዜና!

በኤፌዴሪ ጠቅላይ የጦር አዛዥ ኮሎኔል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የሚመራው የአፋር ግንባር የጠላትን ሀይል በመደምሰስ ጭፍራና ቡርቃን ተቆጣጥሯል ::

Ⓒᶜᴸᴬˢˢʸ ᴱᴺᵀᴱᴿᵀᴬᴵᴺᴹᴱᴺᵀ

በመቀሌ ዛሬ ጧት የድሮን ጥቃት ደረሰየኢትዮጵያ መንግስት ጦር የትግራይ ክልል መስተዳድር ርእሰ-ከተማ መቀሌን ዛሬ ጧት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተነገረ። የዓይን ምስክሮች እ...
26/11/2021

በመቀሌ ዛሬ ጧት የድሮን ጥቃት ደረሰ

የኢትዮጵያ መንግስት ጦር የትግራይ ክልል መስተዳድር ርእሰ-ከተማ መቀሌን ዛሬ ጧት በሰዉ አልባ አዉሮፕላን (ድሮን) እንደመታ ተነገረ። የዓይን ምስክሮች እንዳስታወቁት በተለምዶ ዲያስፖራ ተብሎ የሚጠራዉ የሐድነት ክፍለ ከተማ የደረሰዉ ጥቃት ሁለት መኖሪያ ቤቶችን አፍርሷል ወይም አቃጥሏል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ሌሎች ቤቶችም መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በሰዎች ላይ ግን ፍርስራሽና የመስተዋት ስብርባሪና ካደረሰዉ አነስተኛ ጉዳት በስተቀር የደረሰ ነገር የለም። የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ቃል አቀባይ ጌታቸዉ ረዳ የዛሬዉን ጥቃት ተስፋ ከቆረጠ ሥርዓት የተሰነዘረ የተስፋ መቁረጥ ርምጃ በማለት ነቅፈዉታል። መቀሌ ባለፈዉ ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያም በድሮን ተመትታ ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ስለዛሬዉ ጥቃት እስከአሁን ምንም ያለዉ የለም።

ዘገባ ፎቶ፤ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ DW መቀሌ

 ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአፋር ግንባር ዳሳ ጊታን አስለቅቀናል፡፡ ጭፍራ እና ቡርቃ ዛሬ እንገባለን ብሏል ከግንባር።
26/11/2021


ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በአፋር ግንባር ዳሳ ጊታን አስለቅቀናል፡፡
ጭፍራ እና ቡርቃ ዛሬ እንገባለን ብሏል ከግንባር።

ቤታቸውን ሸጠው ለአገር መከላከያ ሰራዊት የለገሱት እናት ህዳር 17/2014 (ኢዜአ)በአዲስ አበባ አንዲት እናት መኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን ብር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ለገሱ።በአዲስ...
26/11/2021

ቤታቸውን ሸጠው ለአገር መከላከያ ሰራዊት የለገሱት እናት

ህዳር 17/2014 (ኢዜአ)በአዲስ አበባ አንዲት እናት መኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን ብር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ለገሱ።

በአዲስ አበባ የሚኖሩት ወይዘሮ ቦጋለች ከበደ፤ የመኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን በር ለአገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አድርገዋል።

አገር ከሌለ ሁሉም ነገር የማይቻል በመሆኑ በቤት ለመኖር ቅድሚያ አገርን በክብር ማኖር ይገባል በማለት ቤታቸውን ሸጠው ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው ሰራዊት ለግሰዋል።

የአገር ህልውናን ለማስጠበቅ እየተደረገ ባለው ዘመቻ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ በመዝመትም፤ በመደገፍም የጎላ እስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
መረጃዎቻችንን ለማግኘት

25/11/2021

ጉዞ ወደባቲ

ትግሉ የአፍሪካ ነው!!የአሰብ ቀይ ባህር አፋሮች የ   ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። 🇪🇹🇪🇷  🇪🇷🇪🇹 እስኪ ሞራል ስጧቸው።ጂቡቲም በቅርቡ ትቀላቀላለች ብለን እንጠብቃለን!Ahmed Habib Alza...
25/11/2021

ትግሉ የአፍሪካ ነው!!
የአሰብ ቀይ ባህር አፋሮች የ ዘመቻውን ተቀላቅለዋል። 🇪🇹🇪🇷 🇪🇷🇪🇹 እስኪ ሞራል ስጧቸው።
ጂቡቲም በቅርቡ ትቀላቀላለች ብለን እንጠብቃለን!

Ahmed Habib Alzarkawi

😅በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ለጁንታው ዳዲ ሻወር (ቀብር) ተደርጓል። 😆😆 👇
25/11/2021

😅በአዲስ አበባ አራዳ ክፍለ ከተማ ለጁንታው ዳዲ ሻወር (ቀብር) ተደርጓል።
😆😆 👇

Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Semera Daily News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Semera Daily News:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share