26/04/2022
የአገዎች ስልጣኔ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።........................////
የአገው ነግስታት በስልጣናቸው ዘመን በአክሱማውያን እግር ተተክተዉ ለኢትዮጵያ በሀውርታዊ መንግሥትና ሕብረተሰብ ዕድገት መስፋፋት ጠንካራ መሠረት አበጅ።
በዚህ ረገድና ታሪካዊ የሽግግር ዘመን የአገው ነግሥታት 1ኛ፤ በጎሳ ፣በቋንቋና በባህል በተለየዩ በኢትዮጵያ ኩሻዊ፣ሴማዊና ናይሎቲካዊ ማህበረሰቦች መካከል ለዘላቂ ብሔራዊ አንድነትና ዉህደት ታሪካዊ የሥርዓት አንድነት አጠነከሩ ። የሮማውያንና የፋርሳውያን የአፄ መንግሥታት በአረቦችና በቱርኮች እጅ ተንኮታኩተው እንደወደቁ የአክሱማዉያን መንግስታዊ ሥርዓት እንዳይጠፋ አደረጉ ።
2ኛ፤ የአገሪቱን የአዋማዝም ፣የጁዳይዝም፣የክርስትና የእስልምና የሃይማኖችን በሚከተሉ በጎሳና በቋንቋ በተለያዩ ብዙ ማህበረሰቦች መካከል የሕግና የሃይል ተፅዕኖ ሳይደርግ በአንድ ማዕከላዊ የአፄ መንግስት ሥልጣንና ሥርዓት ስር ለአንድ የኢትዮጵያ በሀውርታዊ ሕብረተሰብ ዕድገት ሰፊ ፖለቲካዊ መንገድና መሠረት አበጅ። በአገሪቱ ረጅም ታሪክ የአገው ስርወ መንግሥት በተለይ የሰላም ዘመን ነበር ።
3ኛ ፤በድህረ አክሱም በአገሪቱ የዉጭ ግንኝነት ጉዳይ በዘመኑ በአከባቢው አዲሱን የእስላም ሃይማኖትና ሥርዓት ከሚከትሉ ሃይለኛ የየመንና የግብፅ አጎራባች መንግሥታት ጋር በተላይም በንግድና በሃይማኖት መስኮችና ጉዳዮች እንደ ወቅቱ ተጨባጭ ዓለም አቀፍ ሁኔታና አሰራር የተሸለ መግባባት ለመፍጠር ብርቱ ብሔራዊ ጥረት አድርጎል ።
4ኛ ፤በዘመኑ ከ1095 እስከ 1365 በመካከለኛው ምስራቅና በግብፅ እስትራቴጂያዊ አገሮች በአውሮፓ ክርስቲያንና በአከባቢው እስላም መንግሥትና ህዝቦች መከካል ከተካሄደው ሁሉ አቀፍ "የመስቀል ጦርነት "አገሪቱን ገለልተኛ ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ሊደርስበት ከሚችለው ጉዳት በጥበብ አድኖዋል።በመሆኑም በዘመኑ በቅድስት ኢየሩሳሌም ከተማ ለአገሪቱ ቤተክርስቲያን ከእስላም ባላሥልጣኖች የአምልኮ ቦታ ለመገኘትም ችሎአል ።ይህም ለአገው መነግሥታት ዲፕሎማሲያዊ ጥበብና ችሎታ ታሪካዊ ምሳሌ ነው ።
5ኛ ፤የአገው ብልህ ነገሥታት በላስታ ከቋጥኝ ድንጋይ አስፈልፍለው ያሰሩት የላሊበላ የቤተክርስቲያን ህንፃዎች እንደ አክሱም ሾጣጣ የድንጋይ ሀውልቶች የአገሪቱ ብቻ ሳይሆኑ እንደ ታላቅ የዓለም ባህላዊ ቅርስ ናችው ።በመጨረሻም በኢትዮጵያ በሀውርታዊ መንግሥትና ሕብረተሰብ ከጥንቱ የግዕዝ ፊደልና ጽሐፈት ጋር ዛሬ ብሔራዊ የመገናኛ መሣሪያ ሊሆን የበቃው የአማረኛ ቋንቋ "ልሳነ አፄ / ልሳነ ቤተመንግሥት " ተብሎ በአገው ስርወ መንግሥት ዘመን በቤተ መንግሥት አከባቢ እንደ ተከስተ ብዙ የታሪክ ድርሳናት ይነግራሉ ።
ንብረት ተሠማ
ምንጩ ላጲሶ ጌ.ድሌቦ(ዶር)
April 26-2022
ቁጥር 2 ይቀጥላል
Also follow tele add https://t.me/muwa12
You can view and join right away.