06/05/2023
የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በእያንዳንዳችን እጅ ነው!
ሥርዐት ጠብቀን የምንማጸናቸው አባቶች ድምጻችንን ለመስማት የተዘጋጁ አይመስሉም። ከሚሞቱላቸው ልጆቻቸው ይልቅ ማዕበል የሚያናውጠውን የፖለቲካ ትርፍ ለማዳመጥ ጆሯቸውን አዘንብለዋል። ከገዳማውያን ይልቅ ብሔርተኞችን ተቀብለዋል። ከዋልድባ እስከ ማኅበረ ሥላሴ፣ ከጣና ቂርቆስ እስከ ደብረ ሊባኖስ የተማጸኑ ድምጾች ቦታ አጥተዋል። አባቶች የጀመሩት ኢቀኖናዊ አካሄድ ቤተ ክርስቲያንን የሚደፋፈር ቅጽሯን የሚያፈርስ ነው። ከነዮዲት፣ ከነግራኝ እና ከውጭ ጠላቶች ጥፋት ቀጥሎ የሚመጣው ቀኖናዊ ጥሰት በታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ የታሪካችን ጠባሳ ሆኗል።
ምንም እንኳን መፍትሔው እየከረረ እና እየጠነከረ ቢሄድም እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ ይህንን ሕገ ወጥ ሹመት መከላከላችንን እንቀጥላለን። ተቃውሟችንን እና ድምፃችንን ንቀው ፖለቲካዊ ሲመተ ኤጲስ ቆጶሳትን በሚያካሂዱ አካላት ግን እጃችን መጠንከሩ ልባችንም መጨከኑ የግድ ነው። ቤተ ክርስቲያን በውጭ ኃይሎች ስትደፈር ከሞትን በውስጥ ፖለቲከኞች መሠረቷ ሲናጋ ዝም እንል ዘንድ አይገባንምና። ቤተ ክርስቲያን በሁላችን እጅ ናት እና አጥብቀን እንያዛት።
ድምፀ ተዋሕዶ
https://t.me/onesinod