በጎ ራዕይ ሚዲያ Bego Raey media

  • Home
  • በጎ ራዕይ ሚዲያ Bego Raey media

በጎ ራዕይ ሚዲያ Bego Raey media We would love to hear Some Good News and share it with the world. Hosted by Miky Ab

የነገ ሀገር ተስፋ የሆኑ ታዳጊ ሕፃናት በካንሰር ሕመም ታመው ከተለያዮ ክፍለ ሀገራት ለሕክምና በሚመጡበት ወቅት ማረፊያቸውን ምግባቸውን እና የሕክምና ወጫቸውን በመቻል ለበርካቶች መልካም ነገ...
17/03/2024

የነገ ሀገር ተስፋ የሆኑ ታዳጊ ሕፃናት በካንሰር ሕመም ታመው ከተለያዮ ክፍለ ሀገራት ለሕክምና በሚመጡበት ወቅት ማረፊያቸውን ምግባቸውን እና የሕክምና ወጫቸውን በመቻል ለበርካቶች መልካም ነገር እያደረገ ለሚገኘው 70 ደረጃ ጋር ለተስፋ አዲስ የካንስር ህሙማን መርጃ ድርጅት
5 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና በስጦታ በአሜሪካ ከሚገኙት ሲስተርስ ሁድ ግብረሰናይ ማህበር በSisterhood ግብረሰናይ ድርጅት ተበረከተለት
ሁላችንም በአገራችን ለሚገኙ መልካም እየሰሩ ለሚገኙ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅቶች የበኩላችንን ብናደርግ የበርካቶችን ሕይወት መታደግ እንችላለን
ይህንን መልካም ነገር ያደረጉት እናመሠግናለን
❤️❤️❤️🙏🙏🙏
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
በጎ ራዕይ በጎ አድራጎት

 😭😭የሚያውቀው ሰው ከቤቱ ጠርቶ አስበላው‼️ #ሼር በማድረግ ተጠርጣሪውን አፋልጉን🙏በሁሉ የሚወደደው ትሁቱ ወንድማችን  #ሚኪያስ ታህሳስ7 በቢሾፍቱ ከተማ በተደረገው የ2ተኛ ዓመት   አንደኛ...
04/03/2024

😭😭
የሚያውቀው ሰው ከቤቱ ጠርቶ አስበላው‼️
#ሼር በማድረግ ተጠርጣሪውን አፋልጉን🙏

በሁሉ የሚወደደው ትሁቱ ወንድማችን #ሚኪያስ ታህሳስ7 በቢሾፍቱ ከተማ በተደረገው የ2ተኛ ዓመት አንደኛ በመውጣቱ ተሸልሞ "የከተማችን ተስፋ ነህ፣ለተሻለ መልካም ስራ ያብቃህ " እያሉ መርቀውትና አሞግሰውት ነገውን ለማየት የሚናፍቁ ብዙ ነበሩ!! 😭

ሀሙስ የካቲት21 105ተብሎ በሚጠራው ሰፈራቸው ለብዙ ዓመታት ተከራይቶ የሚኖር አንድ ሰላምተኛው ወጣት #እዩኤል(ኪያ) "አሪፍ ገንዘብ የሚያስገኝ ወደ አዲስ አበባ ቦሌ የምትወስዳቸው ሰዎች አሉ፣6000 ይከፍሉሀል"ብሎ አናግሮት አርብ የካቲት22 በተቀጣጠሩበት ሰዓት ተገናኝተው መንገድ ጀመሩ!!

በሚያውቀው ሰው በጎረቤቱ አማካኝነት ያገኛቸው ሰዎች ስለሆኑ ምንም ስጋት ያልገባቸው ቤተሰብ ከሰዓታት በኋላ "የት ደርሶ ይሆን?" ለማለት ስልክ ሲደውሉለት ዝግ ሆነ፣ደጋግመው ሲሞክሩ ምንም መልስ አጡ!!
ሚኪ ከሌላው ጊዜ በተለየ ሲያመሽባቸው ቤት መጥቶ ያናገረውን ልጅ ፍለጋ የተከራየበት ቤት ሄዱ!!እሱም የለም!!ስልኩም ዝግ ነው!!ወደ ቤቱ ሲገቡ ዋና ዋና የሚባሉ እቃዎቹን አውጥቶ ተሰውሯል!!

ጓደኛው እንደነገረኝ ከሆነ "ተባባሪ ወንጀለኞች አንድ ሴትና አንድ ወንድ ገላን አካባቢ ከተደበቁበት ቤት ውስጥ በጭካኔ ገድለውት ከሰረቁት መኪና ጋር በፖሊስ ብርቱ ጥረት ትላንት ተይዘዋል"

ዋነኛው ወንጀሉ እንዲፈፀም "ና" ብሎ ጠርቶ አመቻችቶ ያስበላው ተጠርጣሪ #እዩኤል እስካሁን አልተያዘም!! እባካችሁን #ሼር በማድረግ እንፈልገው🙏
የወንድማችንም ስርዓተ ቀብር ነገ ሰኞ ጠዋት4ሰዓት
ቢሾፍቱ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ይፈፀማል!!
0966459183-ጌትነት
0911092299-ተስፋዬ

 🙏  አንጀት ይበላል😭😭😭ይህ የ1ዓመት ህፃን   ይባላል!ከተወለደ ጀምሮ በልብ ህመም እየተሰቃየ የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ "ቀዶ ጥገናው ውስብስብ በመሆኑ  #በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሄዶ መ...
16/02/2024

🙏 አንጀት ይበላል😭😭😭

ይህ የ1ዓመት ህፃን ይባላል!ከተወለደ ጀምሮ በልብ ህመም እየተሰቃየ የጥቁር አንበሳ የህክምና ቦርድ "ቀዶ ጥገናው ውስብስብ በመሆኑ #በአስቸኳይ ወደ ውጪ ሄዶ መታከም አለበት"ብለው እናትና አባቱ ጭንቅ ላይ ናቸው!! የቻልነውን በማገዝ በፀሎትና #በሼር እንተባበር🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000397123964-ዮናስ አበራ(አባት)
አቢሲኒያ:22535927
#ስልክ
0910858219
0913720015
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
"

ሁላችንም የዚህች እንቦቀቅላ ሕፃን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር እንታደግ     | ብሌን ጋዲሳ ትባላለች ። የ6አመት አመት ልጅ ናት። በከፍተኛ የልብ ህመም ትሰቃያለች። ውጪ ሄዳ እንድትታከም ...
16/02/2024

ሁላችንም የዚህች እንቦቀቅላ ሕፃን ሕይወት ከእግዚአብሔር ጋር እንታደግ

| ብሌን ጋዲሳ ትባላለች ። የ6አመት አመት ልጅ ናት። በከፍተኛ የልብ ህመም ትሰቃያለች። ውጪ ሄዳ እንድትታከም ተፅፎላታል። ነገር ግን ቤተሰቦቿ የተጠየቀውን ገንዘብ መክፈል ፈፅሞ አይችሉም ።

ቀዶ ጥገናው ብቻ ወደ #8ሺ ዶላር ይፈጃል ።
ከዛ ትራንስፖርት አለ።

እባካችሁ የአቅማችሁን ለግሱና ታክማ ድና እሷም ቤተሰቧም እፎይ እንዲሉ ምክንያት ሁኗቸው። የኔ ልጅ ብትሆን ብላችሁ ድረሱላት። በዚህ እድሜዋ ስትሰቃይ ማየት በጣም ከባድ ነው።

እግዚአብሔርም እንድንደርስላት ይጠብቃል።

መረጃ ከፈለጋችሁ ለናትና አባቷ ደውሉላቸው።
እባካችሁ እግዚአብሔር ያሳሰባችሁን አነሰ ሳትሉ እርዷቸው።

የወላጆቿ ስልክ:
091040810 / 0901468835

የአባቷ አካውንት : ጋዲሳ በየነ ጂማ
CBE 1000536012587
Dashen 5058102198011
Abyssinia 33314949

እግዚአብሔር ከክፋ ሁሉ ይጠብቃችሁ 🙏
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
በጎ ራዕይ በጎ አድራጎት
ለሌላ እንዲደርስ ሼር

እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉላት እባካችሁ 🙏🙏🙏 ሼር ማድረግ በጎነት ነው የነፍስ አድን ጥሪ🙏በምስሉ ላይ የምታይዋት ልጃችን ወጣት ትዕግስት አስቻለው በከፍተኛ የልብ ህመም የጤና ...
03/02/2024

እናንተ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሼር አድርጉላት እባካችሁ 🙏🙏🙏 ሼር ማድረግ በጎነት ነው

የነፍስ አድን ጥሪ🙏

በምስሉ ላይ የምታይዋት ልጃችን ወጣት ትዕግስት አስቻለው በከፍተኛ የልብ ህመም የጤና እክል ተይዛ ገና በ16 ዓመት በለጋ እድሜዋ የአልጋ ቁራኛ ፣ የደዌ እስረኛ ሆናብናለች፡፡

ከመቂ ዱግዳ ሆስፒታል ወደ ጥቁር አንበሳ ሄዳ የልብ ቀዶ ጥገና ህክምና በቶሎ ማግኘት እንዳለባት ቢነገረንም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለመታከም በትንሹ አራት ወር እና ከዚያ በላይ የወረፋ ጊዜያትን መጠበቅ እንዳለባት ከወዲሁ አውቀናል።

ይሁን እንጂ ልጃችን ህክምናዉን በአስቸኳይ ማግኘት ካልቻለች በህይወት መቀየት የምትችልባቸው ጊዜያት እጅግ አጭር በመሆናቸው ሌሎች አማራጮችን ለማየትና የቀዶ ጥገና ህክምናዉን በአፋጣኝ እንድታገኝ የእናንተን እጅ ለመጠበቅ ተገደናል።

ሁለት ዓመታትን ባስቆጠረው የልብ ጤናዋ መታወክ ምክንያት በህክምና ወጪ ጥሪታችንን የጨረስን በመሆኑና በዚኛው ዙር የቀዶ ጥገና ህክምናዋም ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ የሚያስወጣን በመሆኑ የእናንተ የልበ ቀና ወገኖቻችንን እርዳታ ያስፈልገናል

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር

* 1000271891637 ላይ ለአስቻለው አየለ ፣

ወይንም ደግሞ

በአንበሳ ኢንተ. ባንክ ሂሳብ ቁጥር :- 00310683665-43 ላይ ለትዕግስት አስቻለው አየለ ብላችሁ የአቅማችሁን መዋጮ እንድታዋጡልን እና የልጃችንን ህይወት እንድትታደጉልን በፈጣሪ ስም እንማፀናቹሃለን::

* 0910734680
ወርቁ ተገኝ (ወንድም)

* 0925282673
አስቻለው አየለ (አባት)

* 0901706158
ትዕግስት አሰቻለው (ታማሚዋ)

🙏🙏🙏

መልካም ዜናእግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን  እንኳን ደስ አለን ረዱ  ጌታቸው በሰላም ተገኝታለች እግዚአብሔር መልካም ነው በፀሎት ሼር በማድረግ ለማፈላለግ ከጎናቸው የነበራችሁን በሙሉ ቤተሰቧ ...
05/12/2023

መልካም ዜና
እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን እንኳን ደስ አለን ረዱ ጌታቸው በሰላም ተገኝታለች እግዚአብሔር መልካም ነው በፀሎት ሼር በማድረግ ለማፈላለግ ከጎናቸው የነበራችሁን በሙሉ ቤተሰቧ አመሠግነዋል

መልካም ዜና እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን እህታችን ተገኝታለች ቤተሰቦቿ አብራችሁን ለነበራችሁ ለተጨነቃችሁ በአጠቃላይ በሶሻል ሚዲያ ሼር አድርጋችሁ ለሌሎች እንዲደርስ ላደረጋችሁ በሙሉ በእግ...
05/12/2023

መልካም ዜና እግዚአብሔር የተመሠገነ ይሁን እህታችን ተገኝታለች ቤተሰቦቿ አብራችሁን ለነበራችሁ ለተጨነቃችሁ በአጠቃላይ በሶሻል ሚዲያ ሼር አድርጋችሁ ለሌሎች እንዲደርስ ላደረጋችሁ በሙሉ በእግዚአብሔር ስም አመሥግነዋል

የአፋልጉኝ ተማጽኖ  | ተፈላጊ፦   ትባላለች። በአዲስ አበባ ከተማ በወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የዘጠነኛ (9ኛ) ክፍል ተማሪ ናት። በ12/03/2016 ዓ.ም ረቡዕ ዕለት ትምህርት ...
02/12/2023

የአፋልጉኝ ተማጽኖ

| ተፈላጊ፦ ትባላለች። በአዲስ አበባ ከተማ በወ/ሮ ቀለመወርቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የዘጠነኛ (9ኛ) ክፍል ተማሪ ናት።

በ12/03/2016 ዓ.ም ረቡዕ ዕለት ትምህርት ቤት ሄዳ ወደ ቤት አልተመለሰችም። ዛሬ ዘጠነኛ (9) ቀናት ይዛለች።

ልጃችን - የምታወቀው ዘመድ ወይም የቅርብ ጓደኛ የላትም።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምርያ ለራስ ደስታ ፖሊስ ጣቢያ የዕለት ሁኔታ በ13/3/2016 ዓ.ም አስመዝግበናል። እስካሁን ምንም ዓይነት ፍንጭ አላገኘንም።

ቤተሰብ በጣም በጭንቀት ነው ያለው።

እባካችሁን ያለችበትን ቦታና ሁኔታ የሚያውቅ ሰው እንዲያፋልገን ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ተባበሩን!!!

ፈላጊ፦ መክብብ ግርማ 0913837314
እመቤት ድንበሩ 0922283505
ትእግስት ሸዋፈራ 0969141540

ሼርርር ለብዙዎች በመድረስ ለምትታወቀዋ እህታችን!!!!"ካመናችሁኝ እንድታከም ካገዛችሁኝ፡ ነገን በህይወት ድኜ ተርፌ ስመጣ ውለታችሁን እከፍላለሁ"ከፊቷ  ፈገግታ  የማይጠፋው  ለብዙዎች በመድ...
01/12/2023

ሼርርር ለብዙዎች በመድረስ ለምትታወቀዋ እህታችን!!!!
"ካመናችሁኝ እንድታከም ካገዛችሁኝ፡ ነገን በህይወት ድኜ ተርፌ ስመጣ ውለታችሁን እከፍላለሁ"

ከፊቷ ፈገግታ የማይጠፋው ለብዙዎች በመድረስ ለብዙዎች መታከም፣ መዳን፣ መሳቅና መጥገብ ምክንያት እና ሰበብ በመሆን የምናውቃት ህይወት መስፍን፡ ዛሬ አመመኝ አሳክሙኝ እያለች ነው ።ታዲያ ትላንት ለብዙዎች ደጋፊና አጋር የሆነችሁ ይችህ ሳቂታ ወጣት ዛሬ ላይ የእኛን እገዛና እርዳታ ትሻለች ሁላችንም ከተባበርንና ከተጋገዝን የእህታችንን ጤና ከእግዚአብሔር ጋር እንመልሳለን ስለዚህ አነሰ በዛ ሳንል የምንችለውን እናግዝ መስጠት መታደል ነው

ለረጅም ጊዜ የቆየ vein fistula የሚባል የእጅ ህመም ታማለች ህይወት በአንድ ወር ዉስጥ፡ ወደ ዉጭ ሄዳ የተሻለ ህክምና ማግኘት እንደለባት ከሕክምና ባለሞያዎች የተነገራት ሲሆን ለዚህም ሕክምና ወጭ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ያስፈልጋታል

በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
በጎ_ራዕይ_በጎ_አድራጎት

ህይወት መስፍን ሰለሞን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000181181129

ረዱ አልመጣችም!   | ስሟ ረድኤት ጌታቸው ትባላለች። እድሜዋ 17 ነዉ።ረዱ - ለመጨረሻ ጊዜ የነበረችው ስራ ቦታዋ ቦሌ ሞርኒንግ እስታር ህንፃ ነበር።" መጣሁ" ብላ 10:00 ስአት ላይ ከ...
21/11/2023

ረዱ አልመጣችም!

| ስሟ ረድኤት ጌታቸው ትባላለች። እድሜዋ 17 ነዉ።

ረዱ - ለመጨረሻ ጊዜ የነበረችው ስራ ቦታዋ ቦሌ ሞርኒንግ እስታር ህንፃ ነበር።

" መጣሁ" ብላ 10:00 ስአት ላይ ከሥራ እንደወጣች አልተመለሰችም።

ረዱ - ቤት ብትጠበቅም፤ አልመጣችም።

በሰአቱ የለበሠችዉ ፥ ጥቁር ጃኬት፣ አረንጓዴ ቲሽርት፣ ጅንስ ሱሪ፣ ነጭ ጫማ እና ጥቁር ቦርሣ ነበር።

ያለችበትን የምታውቁ ወይንም ያያችኋት ካላችሁ በእነዚህ ስልክ ቁጥሮች እንድታሳውቁን በፈጣሪ ስም እንጠይቃቹኋለን።
"መልካም ማድረግ ለራስ ነው "

ቤተሰቦቿ
0974112409 ቃልኪዳን እህት
0911422994 ጌታቸው አባት
0922667765

 #እግዚአብሔርሁሌም ስሙ የተመሠገነ ይሁንይ🙏ህዳር1 ከቃሊቲ የጠፋችው የ13ዓመቷ ህፃን  #ማህሌት  በህይወት ተገኝታለች!!አንዲት ልበመልካም ሴት ከዱከም የእናንተ ደጋጎችን  #ሼር አይታ ከቀ...
21/11/2023

#እግዚአብሔርሁሌም ስሙ የተመሠገነ ይሁንይ🙏

ህዳር1 ከቃሊቲ የጠፋችው የ13ዓመቷ ህፃን #ማህሌት በህይወት ተገኝታለች!!

አንዲት ልበመልካም ሴት ከዱከም የእናንተ ደጋጎችን #ሼር አይታ ከቀመጡት ስልክ መርጣ አባት አለሁበል ጋር ትደውላለች!!

"ልጃችሁ እኔ ጋር 3ቀን አድራለች!ኑና ውሰዷት" ብላ የቤቷን አቅጣጫ ትነግራቸዋለች!!

ተስፋ የቆረጡት ቀንና ለሊት የሚያነቡት እናትና አባት ዛሬ በለሊት ተሳፍረው ዱከም ደረሱ!10ቀናት የተንከራተቱባት ልጃቸውን ባልጠበቁት ሁኔታ ሰው ቤት በህይወት አግኝተዋት አቀፏት💖

እኛም ህፃን ማህሌትን "ምንድነው የተፈጠረው?" ብለን ጠየቅናት!
"ጭንቀት ነገር እንደሚሰማትና ለቀናት ሰው ቤት ተጠግታ እንዳደረች"ነገረችን!
ዝርዝር ነገሩን ቤት ሲደርሱና እሷም ስትረጋጋ እንሰማለን!! !!
"መልካም ማድረግ መታደል ነው "
_በጎ_አድራጎት

 ??   #እንድረስላት😭 ይህች የ13ዓመት ህፃን የ6ተኛ ክፍል የሳለሁአዲስ ሰፈር ት/ቤት ተማሪ   ትባላለች!ቅዳሜ ህዳር1 ቤት የነበረው አባቷን ቻው ብላ ቀድማት ከወጣችው እናቷ ጋርም 6ሰዓ...
20/11/2023

?? #እንድረስላት😭

ይህች የ13ዓመት ህፃን የ6ተኛ ክፍል የሳለሁአዲስ ሰፈር ት/ቤት ተማሪ ትባላለች!

ቅዳሜ ህዳር1 ቤት የነበረው አባቷን ቻው ብላ ቀድማት ከወጣችው እናቷ ጋርም 6ሰዓት ላይ አብራ ለመመለስ ተቀጣጥራ ደብተሯን በትንሽዬ ቦርሳ ይዛ ቃሊቲ ከሚገኘው ቤታቸው እንደተለመደው በጠዋት ትወጣለች!

ት/ቤት በር ላይ እንደደረሰች የክፍል ጓደኞቿም "ማሂ ማሂ መጣች "እያሉ እየጠሯት አንዲት ሌላ ቦታ 10ኛ ክፍል የምትማር የምታውቃት ሴት በድንገት መጥታ "ነይ ጓደኛሽ ጋር እንሂድ እሷ አልመጣችም"በማለት ቤቷ ይሄዳሉ!!

ጓደኛዋም "ህፃን ልጅ ጠብቂ ስለተባልኩ ዛሬ ት/ቤት አልገባም"ብላ ትሸኛቸዋለች!!

ከደቂቃዎች በኋላ ሁለቱ ሴቶች መንገድ ላይ አንድ ባለባጃጅ ያገኙና ትንሽ ካወሩ በኋላ የ10ኛ ክፍል ተማሪዋ ስትመለስ ህፃን ማህሌት ግን የት እንደገባች ምን እንደሆነች ሳይታወቅ ትሰወራለች!!

በፍለጋ የተንከራተቱት እናትና አባት የተፈጠረውን በማግስቱ የነገረቻቸው አንደኛዋ ሴት "ልጃችንን የት አደረግሻት?እባክሽን ንገሪን"ቢሏት ቢለምኗት "እኔ አላውቅም እሱ ነው የወሳዳት!ይዟት ከሄደ በኋላ ብቻውን ተመለሰ የታለች ብዬ ስጠይቀውም ዝም አለኝ"ብላ ባለባጃጁ ቤት ይዛቸው ትሄዳለች!!

የ21ዓመቱ ወጣት ደግሞ ትንሽ ካንገራገረ በኋላ "ከባጃጁ ላይ እኮ ወርዳለች እኔ ወዴትም ይዣት አልሄድኩም!ምንም የማውቀው ነገር የለም"ብሎ ክዷል!!

እሺ ?? ማን ወሰዳት?

ያለፉትን 8ቀናት ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ሲሆን ባለባጃጁ እስር ቤት ይገኛል!የ17ዓመቷ ሴት ደግሞ በዋስ ወጥታ ህፃን ማህሌትን እንድትፈልጋት ትዕዛዝ ተሰጥቷታል! ?

እናንተ ደጋጎች ህፃን ማሂ በደህና እንድትገኝ እየፀለይንላት #ሼር በማድረግ እንፈልጋት🙏
"መልካም ማድረግ ለራስ ነው "

0906195480-አለሁበል
0920302319-ወደርየለሽ
0925178462-አለኸኝ

የፕሮግራም ማስተካከያ  እባካችሁ ሼር ሼር አድርጉት ከይቅርታ ጋር እሁድ ጠዋት ለካንሰር ሕሙማን ሕፃናት የደም ልገሳ በደም ባንክ የፕሮግራም መጣበብ  ምክንያት ለቅዳሜ ጠዋት 3ሰዓት በተስፋ ...
26/10/2023

የፕሮግራም ማስተካከያ እባካችሁ ሼር ሼር አድርጉት
ከይቅርታ ጋር እሁድ ጠዋት ለካንሰር ሕሙማን ሕፃናት የደም ልገሳ በደም ባንክ የፕሮግራም መጣበብ ምክንያት ለቅዳሜ ጠዋት 3ሰዓት በተስፋ አዲስ የካንሰር ሕሙማን
ማዕከል 4ኪሎ 70ደረጃ ሆኗል ቅዳሜ ለማይመቻችሁ ደግሞ እሁድ ከጠዋት ጀምሮ በደም ባንክ ስታዲየም ፊት ለፊት በሚገኘው እንድትለግሱ እንለምናለን ለነገ ሀገር ተስፋ ለሆኑ ሕፃናት ደርሶ ክብር የሆነውን ደሞን ለግሰው የሕፃናት ሕይወት መታደግ ምንኛ መታደል ነው ሁላችሁም እግዚአብሔር ይባርካችሁ በፕሮግራሙ መቀየር ይቅርታ በድጋሚ እንጠይቃለን

ሁላችንም በመልካም ነገር ላይ ተገኝቶ መልካም እንደ ማድረግ መታደል ወይም መመረጥ የለም መልካምነት ከምንም በላይ ያስደስታል ዛሬ ላይ በርካቶች የነገ ሀገር ተስፋ የሆኑ ሕፃናት በአሁኑ ወቅት...
25/10/2023

ሁላችንም በመልካም ነገር ላይ ተገኝቶ መልካም እንደ ማድረግ መታደል ወይም መመረጥ የለም መልካምነት ከምንም በላይ ያስደስታል ዛሬ ላይ በርካቶች የነገ ሀገር ተስፋ የሆኑ ሕፃናት በአሁኑ ወቅት በአለማችን እጅግ አስፈሪ እና አስቸጋሪ በሆነው የካንሰር ሕመም እየተሰቃዮ ይገኛሉ እናም እነዚህ ሕፃናት በደም እጦት ምክያት እያጣናቸው ነው ሁላችንም ከተባበርን ግን ትልቁን የሕይወት ስጦታ ደማችንን ከለገስን የነዚህን ሕፃናት ሕይወት መታደግ እንችላለን ሁላችንም ቤተሰባችንን ጓደኞቻችንን ዘመዶቻችንን ይዘን ለዚህ መልካም ዓላማ የፊታችን እሁድ ከጠዋቱ 3ሰአት ጀምሮ ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል እንገናኝ የእናንተ ደም የህፃናቱን ህይወት ያተርፋል እሁድ ጠዋት 3ሰአት ቀጠሯችሁን ህፃናቱ ጋር እናድርግ አድራሻ 4ኪሎ 70ደረጃ 🙏

መልካምና አስደሳች ዜናለሁሉም በቅድሜ እግዚአብሔር ስሙ የተመሠገነ ይሁን መቼም ሰው ልጅ ብቻውን ቢደክም ቢለፋ ፈጣሪ ካልፈቀደ ምንም የሚሳካ ነገር አይኖርም ፈጣሪ ታዲያ ዛሬ ወንድማችን ሐብታ...
24/10/2023

መልካምና አስደሳች ዜና
ለሁሉም በቅድሜ እግዚአብሔር ስሙ የተመሠገነ ይሁን መቼም ሰው ልጅ ብቻውን ቢደክም ቢለፋ ፈጣሪ ካልፈቀደ ምንም የሚሳካ ነገር አይኖርም ፈጣሪ ታዲያ ዛሬ ወንድማችን ሐብታሙ ኩላሊቱ ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ እንደዚያ ሲሰቃይና የሁለት ዓመቱ ልጁ እንደዚያ እያለቀሰ አባቱን እንድናድንለት የሁላችንም እርዳታ ሲሻ እግዚአብሔር ሁሉንም ከዚህ መልካም አላማ ጋር በማስተባበርና አንድ በማድረግ ፍፃሜውን አሳምሮት ዛሬ ወንድማችን ሕክምናውን አጠናቆ ወደ ውድ አገሩ ተመልሷል ሁሉንም ያደረገውን እግዚአብሔር አመሥግኑልኝ ብሏል እኛ ከተባበርንና አንድ ከሆንን ለበርካታ ወገኖቻችን መሆን እንችላለን በመስጠት ደሀ የሆነ የለም ሁላችንም እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀን ውሌም ሰጭ ያድርገን የምንሰጠው አንጣ በሉ እግዚአብሔር እናመሥግን ላደረገልን መልካም ነገር ሐብትሽ እንኳን ደስ አለህ
በጎ ራዕይ በጎ አድራጎት
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም

የልጅ_ነገር 😥 እባካችሁ ሼር አድርጉት ለመጀመሪያ ህክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል አመራን። የካቲት 12 ሆስፒታል ደግሞ ወደ  ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተላክን። ልጄ ሄመን ክትትል ጀመረች ...
12/10/2023

የልጅ_ነገር 😥 እባካችሁ ሼር አድርጉት

ለመጀመሪያ ህክምና ወደ የካቲት 12 ሆስፒታል አመራን። የካቲት 12 ሆስፒታል ደግሞ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተላክን።

ልጄ ሄመን ክትትል ጀመረች ሄመን የልብ ሕክምና እንዳለባት ተነገረን። ይሁንና ለ3 ወራት ተቀጠርን።
ቀጠሮዋ ደርሶ ዳግም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አመራን።
ዶክተሩ ጋር ቀረበች።ሄመን ከፍተኛ የልብ ሕመም ላይ እንደምትገኝ አሳወቁን። ወረፋ ስላለ ኦፕራሲዮን ለመስራት 8 ወራት ድረስ ጠብቁን አሉን። 8ወራት ትጠብቃላችሁ - ተባልን።
ልጄ ሄመን የሳንባ ምቷ ከጨመረ ኦፕራሲዮን መደረግ አትችልም። ... ልጄ ስምንት ወራት መጠበቅ አትችልም ። ... የልብ ምቷ በጣም ቀንሷል። እንዲሁም ምግብም አትበላም።
በግል ሕክምና ለማሳከም እንቅስቃሴ ጀምረናል።

ወላጅ እናቷ ውብአለም ተስፋዬ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
1000536211989

ስልክ ቁጥር
+251-969-92-05-18

እንዲሁም

ወላጅ አባቷ በሀይሉ ከፍያለው ተገኝ
ዳሽን ባንክ
የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር
5174001171001
ስልክ ቁጥር 0913-24-47-32

11/10/2023

መቼ አንድም ቀን ይከብዳል እንኳንስ 6 አመት ሙሉ መሠቃየት ሁላችንም ከተባበርንና ከተጋገዝን ከእግዚአብሔር ጋር ይህች እህታችን የሕክምና አገልግሎት እንድታገኝ ማድረግ እንችላለን መቼም ሰው ለመርዳት ሀብታም መሆን አይሻም መልካም ልብ እንጂ ዛሬ ነገ ሳንል በመላው ዓለም ላላችሁ ወገኖች እህታችን እንድረስላት 🙏
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
በጎ ራዕይ በጎ አድራጎት

ለመርዳት የበለጠ መረጃ ለማገኘት ከዚህ በታች ባለው መረጃ ያግኙዋት

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር :-
1000089976115 ሸዋጌጥ ጥላሁን ዘለቀ

ስልክ ቁጥር 👇
0915017773
0975048204

እንኳን እግዚአብሔር በሰላም ወደ አዲሱ ዓመት አደረሰን አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የደስታ ዓመት ፈጣሪ ያድርግልን ሁላችንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ወገኖቻችን መልካም ...
11/09/2023

እንኳን እግዚአብሔር በሰላም ወደ አዲሱ ዓመት አደረሰን አዲሱ አመት የሰላም የፍቅር የደስታ ዓመት ፈጣሪ ያድርግልን ሁላችንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከራሳችን አልፈን ለሌሎች ወገኖቻችን መልካም እንሁን መልካም እናድርግ ካለን ላይ እናካፍል ዓመቱን በመልካም ስራ እንጀምር በመስጠት ደሀ የሆነ የለም ሁላችንም ሰጭ እንሁን ከመቀበል በበለጠ በመስጠት ውስጥ የሚገኙ ደስታ ይበልጣል እግዚአብሔር ሁላችንም መልካም እንድናደርግ ይርዳን መልካም አዲስ ዓመት እንቁጣጣሽ እንኳን በደህና መጣሽ 2016

ሁላችንም ከተባበርን ለበርካታ ወገኖቻችን መድረስ እና የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት መታደግ ከእግዚአብሔር ጋር እንችላለን ወገን ዛሬ ጀምሮ የአቅማችንን እናድርግ በመስጠት ደሀ የሆነ የለም በ...
31/08/2023

ሁላችንም ከተባበርን ለበርካታ ወገኖቻችን መድረስ እና የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት መታደግ ከእግዚአብሔር ጋር እንችላለን ወገን ዛሬ ጀምሮ የአቅማችንን እናድርግ
በመስጠት ደሀ የሆነ የለም
በጎ ራዕይ በጎ አድራጎት
እባካችሁ ሼር አድርጉት

Check out MikyAb's video.

ሁላችንም የተቻለንን እንርዳ ለመርዳት ሀብታም መሆን አይሻም መልካም ልብ እንጂ
28/08/2023

ሁላችንም የተቻለንን እንርዳ ለመርዳት ሀብታም መሆን አይሻም መልካም ልብ እንጂ

Dear friends and supporters, we are reaching out to you today to ask for your he… Genet Tekele needs your support for Urgent Medical Funds for Yeteneyat Mamo

ወጣት ዳንኤል ስንታየሁ ይባላል ድንገት ባጋጠመው የደም ካንሠር በሽታ ከአገር ውጭ ሄዶ መታከም እንዳለበት ከዶክተሮች ተነግሮታል ሁላችንም የአንድ ወር ጊዜ ነው ያለ ተብሏል ሁላችንም ይህንን ...
19/08/2023

ወጣት ዳንኤል ስንታየሁ ይባላል ድንገት ባጋጠመው የደም ካንሠር በሽታ ከአገር ውጭ ሄዶ መታከም እንዳለበት ከዶክተሮች ተነግሮታል ሁላችንም የአንድ ወር ጊዜ ነው ያለ ተብሏል ሁላችንም ይህንን የ23ዓመት ወጣት ሕይወት ተረባርበን የአቅማችንን በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር እንታደገው ለመርዳት ሀብታም መሆን አይሻም ቀና ልብ እንጂ ከዚህ በታች የሕክምና ማስረጃውንና የሱንና የአባቱን ስልክ እና የባንክ አካውንት ቁጥር አስቀምጠናል መርዳት አቅሙ የሌላችሁ ደግሞ በፀሎት አስብት ደውሉለት
1000474037855 Daniel sentayehu
1000285349153 sentayehu tesfaye
ቀርበዉ በሰልክ ማዉራት ለሚፈልጉ
0911070121 sentayehu
0942702762 daniel

ሁላችንም የአቅማችንን ካደረግን የበርካታ ወገኖቻችንን ሕይወት መታደግ እንችላለን
በጎ _ራዕይ _በጎ አድራጎት

22/07/2023

እህታችን ሕይወት ታደጓት ለአንድ ዓመት ልጄ ልኑርለት እባካችሁ ትለናለች

ያልፋል እባላለሁ 4ኛአመት የድግሪ ተማሪ ነኝ በከፍተኛ የልብ ህመም እየተሰቃየሁ ነው ከዚህ በፊት ለቀዶ ጥገኛ 220,000 ብር ተጠይቄ ያንን ለመክፈል ሳልችል በጥቁር አንበሳ ህክምናዬን ስከታተል ብቆይም የተሰጠኝ ወረፋ ከህመሜ አንጻር ያንን ያህል ጊዜ መጠበቅ እንደማልችል እና ቀዶ ጥገናውን በግል እንዳደርግ በሀኪሞች ተነግሮኛል የቀድሞ ጤናዬን ለመመለስ አረቲፍሻል የልብ ቱቦ መቀየር እንዳለበት እና አሁን ግን የህክምናውም ወጪ ከ3እጥፍ በላይ ማለትም ከ ከ600,000 ብር በላይ እደሆነ ተነግሮኛል። የ1 አመት ልጅ አለኝ እኔም ሳልጠግበው እሱም የእናትን ፍቅር ሳያውቀው እንዳላልፍ ከፈጣሪ ቀጥሎ ያላችሁኝ እናንተ ናችሁ እና በአለም ያላችሁ ሰውን መርዳት የምትችሉ ሁሉ የቻላችሁትን በማድረግ ህይወቴን እንድታተርፉልኝ ስል በፈጣሪ ስም እለምናችኋለሁ ።
ልቤን ጠግኑልኝ
ስም ያልፋል ምኒሊክ ታደሰ
ንግድ ባንክ 1000372126691
ዳሸን 5194436368011
ስልክ 0996 991511
መስጠት ከምንም በላይ መታደል ነው
በጎ-ራዕይ -በጎ አድራጎት
ሁላችንም ሼር በማድረግ የእህታችንን ሕይወት እንታደግ

ወንድሜ ሙለታ ጫላ ይባላል በአሁኑ ወቅት በልብ ህመም እየተሰቃየ ይገኛል ታዲያ ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ አሁን የቀዶ ሕክምና ለማድረግ እና ወደ ጤናው ለመመለስ 850,000(ስምንት መቶ አምሣ ...
19/07/2023

ወንድሜ ሙለታ ጫላ ይባላል በአሁኑ ወቅት በልብ ህመም እየተሰቃየ ይገኛል ታዲያ ሕክምና ሲከታተል ቆይቶ አሁን የቀዶ ሕክምና ለማድረግ እና ወደ ጤናው ለመመለስ 850,000(ስምንት መቶ አምሣ ሺህ )ብር ተጠይቋል እባካችሁ የወንድሜን ሕይወት ታደጉልኝ ስል በእግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ ከዚህ ክፉ በሽታ ይጠብቃችሁ ለምታደርጉልን ድጋፍ እግዚአብሔር ይባርካችሁ

https://gofund.me/5a706c96አስቸኳይ!ውድ ወዳጆችና ቤተሰቦች። በእስከዛሬው ትብብራችሁና ምላሻችሁ  ደጋፋችሁ  በጣም እናመሰግናለን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ ሁሌም ለወገን ደራሽ ...
06/07/2023

https://gofund.me/5a706c96

አስቸኳይ!
ውድ ወዳጆችና ቤተሰቦች። በእስከዛሬው ትብብራችሁና ምላሻችሁ ደጋፋችሁ በጣም እናመሰግናለን። እግዚአብሔር ይባርካችሁ ሁሌም ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን አሳይታችሁናል ከእግዚአብሔር ጋር
በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ያለንበትን አስቸኳይ ሁኔታ ልንገልፅላችሁ ግድ ሆኖብናል። እህታችን ብሌን ላለፉት 5 ወራት ስድስቱን የኪሞ ህክምናዎች ካደረገች በኋላ በተደረገው የባዮፕሲ ምርመራ ያልጠበቅነውን ምላሽ ከሐኪምዋ አግኝተናል። የተለየ የመድሐኒት ቅንብርና ተጨማሪ 14 ኪሞዎች መውሰድ እንዳለባት። ለዚህም ከሌሎች ወጪዎች ጋር ወደ 30ሺህ ዶላር ይጠይቃል።
ብሌንና አብራት በህንድ አገር ሆና የምታስታምማት መንታ እህቷ በአስቸኳይ የኛን እርዳታ ይሻሉ።
እባካችሁን በምንችለው አቅም ሁሉ እስከ መጨረሻው የዚህች እህታችንን ሕይወት ለመታደግ አሁንም ከጎኑዋ እንድትሆኑ እንጠይቃለን ሁላችንም ከዚህ መጥፎ ህመም ፈጣሪ ይጠብቃችሁ እግዚአብሔር በምታደርጉት ሁሉ እርሱ ይባርካችሁ ።

Blen Merid, our 32 years old sister who is full of life, was diagnosed with a breast canc… Tsegereda Gashawbeza needs your support for Please let’s help Blen

 😭😭😭 ‼️ ይህች የ7ዓመቷ ቆንጅዬ ህፃን   ትባላለች! ከዘጠኝ ወራት በፊት ሀምሌ10 የኬጂ3 ትምህርቷን ጨርሳ በጥሩ ውጤት ተመርቃ ወደ ቤቷ ስትገባ የምትሳሳላት እናቷ ያዘጋጀችላትን ኬክ በ...
24/05/2023

😭😭😭
‼️

ይህች የ7ዓመቷ ቆንጅዬ ህፃን ትባላለች! ከዘጠኝ ወራት በፊት ሀምሌ10 የኬጂ3 ትምህርቷን ጨርሳ በጥሩ ውጤት ተመርቃ ወደ ቤቷ ስትገባ የምትሳሳላት እናቷ ያዘጋጀችላትን ኬክ በደስታ እየቆረሰች በወዳጅ ጎረቤቷም ተከባ "ልጃችን እንኳን ደስ አለሽ ለትልቁ ምርቃትም ያብቃሽ"ተብላለች!

በማግስቱ ተኝታ ስትነሳ ግን ህፃን ዳያን ራስምታት ጀመራት!የመጀመሪያ ቀን"ፀጉሯን ስለተሰራች ይሆናል" ብለው ችላ ቢሏትም ህመሙ እየባሰባት በተደጋጋሚ "እማዬ እየደከመኝ ነው"ማለት ሰትጀምር አቅራቢያ የሚገኝ ጤና ጣቢያ ወሰዷት!!
"ቀላል ነው ራስ ምታት ነው"ብለው ሽሮፕ ሰጧት!!

ወደ ቤት በተስፋ የተመለሰችው ፑፒ ህመሟ እየባሰባት፣ምግብ እምቢ እያላት ድካሙም ሲበረታባት እናት ተጨንቃ ወደ ግል ሆስፒታል አናንያ ወሰደቻት!!
እዛም "ምንም የለባትም ደህና ናት"ብለው ለትኩሳቷ የሚሆን ሽሮፕ ሰጥተው መለሷት!!

ከ3ቀናት በኋላ እራቷን በልታ ሚሪንዳ ጠጥታ የተኛችው ህፃን ዳያን ሊሊት ላይ ድምፅ ማውጣት መተንፈስ አቃታት፣ ሰውነቷ እምቢ አልታዘዝ አላት😭ከተኛችበት ፍራሽ መነሳት አልቻለችም😭 እግርና እጇን ድንገት ያዛት😭መራመድና መቆም ተሳናት!

እናት ተደናግጣ መልሳ ወደ አናንያ ሆስፒታል ስትወስዳት"እንዴ ኮማ ውስጥ ናት እኮ ወደ ራስደስታ ሆስፒታል በአስቸኳይ ውሰዷት"ብለው ሪፈር ፃፉላት!!

ራስደስታም ከአቅሜ በላይ ነው ብሎ ወደ ጥቁር አንበሳ ልኳቸው ለ41ቀናት ፅኑ ህሙማን ክፍል Icu ውስጥ ቆየች!!4ወር ከ15ቀናት በማሽን እየተነፈሰች ሆስፒታል አደረች!!

እናት ኢትዮጲያ ለ7ዓመታት ስደት ላይ ቆይታ እናትና አባቷን በተከታታይ በሞት አጥታ መፅናኛዬ ያለቻት ልጇም የጭንቅላት ቲቢ ነው ብለዋት ባልጠነከረ ሰውነቷ አንገቷ ተቀዶ የመተንፈሻ ማሽን ተገጠመላት! ልጇን ለማዳን አለኝ የምትላቸውን በደህና ጊዜ የነበራትን ንብረት ቀስ በቀስ አውጥታ ሸጠች!ግን ተስፋ አጣች!
ህፃኗ ፓፒ ለመተንፈስ፣ምራቋን ለመትፋትና ለመዋጥ ያለማሽን እንቢ አላት😭

እናት የሰው ፊት ላለማየት እንደምንም እየታገለች በብዙ ብትንከራተትም አሁን ግን ልጇ ፓፒ የተሻለ ህክምና የረጅም ጊዜ ፊዚዮቴራፒ ያስፈልጋታል ስለተባለች ተጨንቃለች!!

እናንተ ደጋጎች ሆይ የምትችሉትን አድርጉ🙏 #በፀሎት በሙያና በምትፈልጉት አግዙ🙏 #ሼር በማድረግም ለልበመልካሞች አድርሱ🙏
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም መልካም ማድረግ መታደል ነው "
#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000296881523-ኢትዮጵያ ተፈሪ(እናት)
#ስልክ
0911859057-ኢትዮጵያ

መኖር እየፈለኩኝ በብር እጦት እንዳልሞት ድረሱልኝ 💔     ቤተልሄም ማናዬ ትባላለች የድሬዳዋ ልጅ ስትሆን የ 21 አመት ወጣት ናት ። በድንገት ባጋጠማት ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም እየተሰቃ...
23/05/2023

መኖር እየፈለኩኝ በብር እጦት እንዳልሞት ድረሱልኝ 💔

ቤተልሄም ማናዬ ትባላለች የድሬዳዋ ልጅ ስትሆን የ 21 አመት ወጣት ናት ። በድንገት ባጋጠማት ከፍተኛ የሆነ የልብ ህመም እየተሰቃየች ትገኛለች 💔

በአጭር ጊዜ ውስጥም የልብ ቀዶ ጥገና ማድረግ እንዳለባት የህክምና ዶክተሮች የወሰኑ ሲሆን ለህክምናውም ከአንድ ሚሊዮን ( 1,000,000 ) ብር በላይ እንደሚያስፈልጋት ተነግሯታል

ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ወጣት ቤቴልሄምን መርዳትም ሆነ ማገዝ የምትፈልጉ 👇

👉 የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000286844751 ቤተልሄም ማናዬ

👉 አዋሽ ባንክ 01336719848400 ቤተልሄም ማናዬ

📞 ስልክ 0946024735 ቤተልሄም

🛑 ሼር አድርጉት 🙏

 #አስቸኳይ ነው  #እባካችሁ መልዕክቱን  #ሼር አድርጉት     #ልጄን አድኑልኝ 😭😭 #ከራሱ አንደበት... #የልጆቼ እናት በጭንቅላት ነርቭ በሽታ ለተከታታይ 3 አመታት ያክል ተሰቃይታ በሚ...
21/05/2023

#አስቸኳይ ነው #እባካችሁ መልዕክቱን #ሼር አድርጉት

#ልጄን አድኑልኝ 😭😭

#ከራሱ አንደበት...

#የልጆቼ እናት በጭንቅላት ነርቭ በሽታ ለተከታታይ 3 አመታት ያክል ተሰቃይታ በሚያሳዝን ሁኔታ ልጆቼን ጥላብኝ ላትመለስ ለእስከወዲያኛው አሸለበች 😭

#ይህ ክፉ ሀዘን ከልቤ ላይ ሳይጠፋ እንደገና ሴት ልጄ በነርቭ በሽታ ይኸው በፎቶ እንደምትመለከቷት ታማብኝ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እያደረገች ትገኛለች

#ከአጠገቤ አይዞህ የሚለኝ እንኳን ምንም ዘመድ የለኝም ልጄን እንደባለቤቴ በሞት ከማጣቴ በፊት #በፈጣሪ ስም ድረሱልኝ

#ንግድ ባንክ
1000073732054.........ወልዴ በሬ ( አባት )

#ስልክ ቁጥር

09 43 40 31 74..............ወልዴ ( አባት )

ሰውን ለመርዳት ሀብታም መሆን አይሻም መልካም ልብ እንጂ

18/05/2023
የሦስት ልጆቹን  አባት እንታደገው!   በማድረግ ለብዙዎች ታደርሱ ዘንድ እንማፀናለንብርሃኑ አለሙ  በኮንስትራክሽን ስራ ላይ ተሠማርቶ  ሦስት ልጆቹንና ቤተሰቡን ያስተዳድር ነበር። አሁን ባጋ...
18/05/2023

የሦስት ልጆቹን አባት እንታደገው!

በማድረግ ለብዙዎች ታደርሱ ዘንድ እንማፀናለን

ብርሃኑ አለሙ በኮንስትራክሽን ስራ ላይ ተሠማርቶ ሦስት ልጆቹንና ቤተሰቡን ያስተዳድር ነበር። አሁን ባጋጠመው ድንገተኛ የስኳር ህመም ምክንያት ሁለቱም ኩላሊቶቹ መስራት ስላቆሙ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዲያደርግ የሆስፒታሉ የሃኪሞች ቦርድ ወስኗል።

ይህንን የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ከ 2,500,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) ያስፈልገዋል።

ብርሃኑ ይህንን ገንዘብ አግኝቶ እስከሚታከም ድረስ ነብሱን ለማቆየት በሳምንት ሦስት ጊዜ የኩላሊት እጥበት ማድረግ ስላለበት ለአንድ ግዜ ብቻ እጥበት 3,500 ብር በወር ሌላ ወጪዎችን ሳይጨምር 42,000 ብር በላይ ወጪ በማድረግ ዛሬ ላይ የራሱን አቅም አሟጦ ጨርሷል።

እናንት ደጋግ ኢትዮጵያውያን ሆይ ይህንን የሶስት ልጆች አባት በቻልነው አቅም በመደገፍ ለሱ የመኖር ተስፋና ለህፃናት ልጆቹም አባታቸውን ለማትረፍ የአቅማችሁን ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንለምናለን!

Please

ስልክ ቁጥር
0911 718936 / 0911461412 / 0913116011

የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000328391407

የአቢሲንያ ባንክ
97239789

ሕብረት ባንክ
1010416457467016

አዋሽ ባንክ
01320134208901

ዳሸን ባንክ
5090179193011

ንብ ባንክ
069 SAV9068

የኦሮሚያ ሕብረት ስራ ባንክ
1047500032006

በቅድሚያም ለምታደርጉት ድጋፍ በሙሉ ፈጣሪ ይስጥልን
ከድንገተኛ አደጋ ፈጣሪ ይጠብቃችሁ

ብዙ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ስላሉ እባካችሁ ሼር ይደረግ 🙏

"ፍቅራችንን እና ድጋፋችንን ለነገ ተስፋዎች" በተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች የተመሰረተው "ወደ ፍቅር. . . ማህበር" ተከታዩን መልዕክት አድርሶናል። በ"ስለ እ...
25/11/2022

"ፍቅራችንን እና ድጋፋችንን ለነገ ተስፋዎች"

በተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አድናቂዎች የተመሰረተው "ወደ ፍቅር. . . ማህበር" ተከታዩን መልዕክት አድርሶናል።

በ"ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት" ክብካቤ ለሚደረግላቸው የነገ ተስፋዎች ፍቅራችንን የምንገልፅበት አብሮነታችንን በድጋፋችን የምናሳይበት ልዩ የአብሮነት(መዝናኛ) እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም አዘጋጅቶል። ለመላው የንጉሱ አድናቂዎች እና የበጎ ስራችን ደጋፊዎች በዚህ የተቀደሰ በጎ ተግባር ላይ በመሳተፍ የአቅማችሁን ጠጠር በመወርወር ተካፋይ እንድትሆኑ ማህበራችን ጥሪ ያቀርባል።

#እሁድ
#ሰዓት ከጠዋቱ 2:30-11:30 ግቢ ውስጥ

🔰በእለቱ በአካል ተገኝተው ድጋፋቸውን ማድረግ ለማይችሉ በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም ለሚገኙ የበጎ ስራችን ደጋፊዎች እንዲሁም ለክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን አድናቂዎች ከታች በምስሉ ላይ በሚገኘው የስለ እናት በጎ አድራጎት የባንክ ሒሳብ ቁጥር ላይ በገንዘብ ድጋፋቸውን ማድረግ ይችላሉ።

✅️የምግብ ልገሳ አይነቶች
ወተት ኒዶ
የምግብ ዘይት
ጤፍ
ስኳር
የለውዝ ቅቤ
እንቁላል
ማርማራታ
ፓስቲኒ
ብስኩት
ቅንጬ ( የገብስ/የአጃ)
የምግብ ቅቤ (ሸኖ ለጋ)
ክኖር መረቅ
ሴሪፋም
በርበሬ
ምስር ክክ
ሽሮ

✅️የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ አይነቶች
የአዋቂ ዳይፐር ትልቁ
ቫዝሊን
ሶፍት
በረኪና ዲቶል
የገላ ሳሙና
የልብስ ሳሙና
ኤር ፍሬሽነር
ፈሳሽ ሳሙና (ላርጎ)
ዲቶል
በረኪና
ዱቄት ሳሙና (ኦሞ)

#ወደፍቅር. . .
#ድጋፋችንን

#ስለእናት
#ኢትዮጵያ

Address


Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+17207565716

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በጎ ራዕይ ሚዲያ Bego Raey media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to በጎ ራዕይ ሚዲያ Bego Raey media:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Opening Hours
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share