Badhaadhina Media Network

Badhaadhina Media Network Peace, Justice and freedom

Permanently closed.
12/22/2024

Jawween mana ofii diigee, OMN diigee, KFO diigee ammammoo biyya diiguu yaala. Hin milkooftu!

Aanaa galu Araara keessa deebii hin qabnee nuuf haa godhu nagaa nuuf haa buusu. Baga nagaan galtan
12/03/2024

Aanaa galu Araara keessa deebii hin qabnee nuuf haa godhu nagaa nuuf haa buusu. Baga nagaan galtan

12/03/2024

መጽሐፍት ለትውልድ!

በዚህ ርዕስ በሳምንት አንድ ቀን ሰኞ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ ጠቃሚ ናቸው ያልናቸውን መጽሐፍት ለአንባቢ የምንጋብዝበት ነው።

የመጽሐፍቱ ምርጫ የእናንተ የውድ ተከታዮቻችንም ጭምር ነው፤ አንብባችሁ የወደዳችሁትን መጽሐፍ ብትጠቁሙን እኛም አንብበን ያላነበቡ እንዲያነብቡት መልሰን እንጋብዛለን።

ለዛሬ "25 የስኬት ቁልፎች"ን በጨረፍታ ዳስሰን ሙሉውን እንዲያነቡት ግብዣችን ነው። እነሆ!! 25 የስኬት ቁልፎች

ርዕስ-25 የስኬት ቁልፎች
ደራሲ-ኢየብ ማሞ (ዶ/ር)
የገጽ ብዛት-160

ስኬትን የማይመኝ ሰው የለም፡፡ የስኬት ትርጉም ግን አወዛጋቢ የሆነበት ወቅት ላይ ነን ያለነው፡፡ ስኬት ለሚለው ቃል ሰዎች እንደ መነሻ ሃሳባቸውና እንደምኞታቸው ትርጉሙን ይለዋውጡታል፡፡ የስኬትን ትክክለኛ ትርጉምና 25 መሰረታዊ የስኬት ጎዳናዎችን ለመገንዘብ ይህ መጽሐፍ የግድ ነው፡፡

ደራሲው በ“25 የስኬት ቁልፎች” ሲሉ በሰየሙት መጽሐፋቸው ለስኬት ወሳኝ ናቸው ያሉዋቸውን ነጥቦች በሀያ አምስት ምዕራፎች ከፍሎ አቅርቧል ፡፡

“የነፋሱ ግፊያ ወደ ከፍታዬ ያወጣልኛል” በሚለው ምዕራፍ ለስኬት የተግዳሮት አስፈላጊነት ምን ያህል እንደሆነ ጽፈዋል ፡፡ ተግዳሮትና ስኬትን በንስርና ንፋስ ንፅፅር አቅርቦልናል ፡፡

ንስር የሚጋፋው አንድ ብቸኛ ተግዳሮት ነፋስ ነው ፡፡ የሚያስገርመው ነገር ግን ንስር ወደ ከፍታው እንዲወጣ የሚደግፈውም ያው የሚጋፋው ነፋስ ነው ፡፡ የንስር አቋም “የሚጋፋኝን ይህንን ነፋስ ተጠቅሜ ወደ ከፍታዬ እበራለሁ ፤ የነፋሱ ግፊያ ወደ ከፍታዬ ያወጣኛል ፡፡” የሚል ነው፡፡ ንስር ከሚጋፋው ብቸኛ ጠላቱ ከነፋስ ተግዳሮት ውጪ ለመኖር ቢወሰንና ያንን ጥያቄውን ተግባራዊ የሚያደርግለት ኃይል ተገኝቶ ነፋስ ከፍጥረት ክስተት ውስጥ ቢወጣለት የሚጋፋው ብቸኛ ነገር ስለተወገደለት “እፎይ” ይላል ፡፡ ታሪኩ ግን እዚያ ላይ ብቻ አያበቃም ፡፡ የከፍታ ህይወቱንም እዚያው ያስረክባል ፡፡ ከሚጋፋው ከብቸኛ ጠላቱ ከነፋስ ውጪ ንስር ከዶሮ ተለይቶ አይታይም ፡፡” ይለናል መጽሐፉ፡፡

ተግዳሮት በሌለበት ስኬት አይኖርም ነው አዝማሚያው ፡፡ ስኬታማ ሰዎች ከፈተና ርቀው የኖሩ ሳይሆኑ ወርቅ በእሳት እንደሚፈተው ፤ በፈተና ተፈትነው ነጥረው የወጡ ወርቆች ናቸው ፡፡ ወርቅ እነሱ ዘንድ የሚገኘውና ብርቅና ድንቅ የሚሆኑብንም ለዚህ ነው ፡፡

ስኬታማ ሰዎች ችግሮችን እንደ ዕድሎች እንጂ እንደ ችግሮች አያዩዋቸውም ፡፡ የተከፈተ በር የተከፈተ ስለሆነ ሌላ እምቅ ዕድል በውስጡ አላዘለ ይሆናል ፡፡ የተዘጋ በር ግን የመከፈት ዕድልን የያዘ በረከት ነው ። በተከፈተው በር መግባት ስኬት ሊሆን አይችልም ፡፡ የተዘጋውን በር በብልሀት ከፍቶ መግባት ግን ስኬት ነው ፡፡ ስለዚህ ስኬት ያለው ተግዳሮት ባለበት ነው ፡፡ የንስሩ ከፍታ በሚፈታተነው ነፋስ መኖር እንደተሳካ ስኬታማነት ከችግሮት ማህፀን ይወለዳል ፡፡

“የሰውን ዘር የአምፑልን ብርሃን እንዲፈለስፍ ያነሳሳው የጨለማው ተግዳሮት መሆኑን አትዘንጋ ። የበሽታው ግፊያና የስቃያችን ጥልቀት በህክምና ዛሬ የደረስንበት ደረጃ እንድንደርስ አበረታን ፡፡ መራራቃችንና ለመገናኘት ያለን ናፍቆት የጫነብን የመገለል ጫና የበረራን ፈጠራና የስልክን መስመር የመሳሰሉትን ብልሃቶች ከውስጣችን ፈልቅቆ አወጣው ፡፡” ይላል መጽሐፉ ፡፡

“በ30 ዓመቱ ሞተ ፣ በ60 ዓመቱ ተቀበረ” በሚል ርዕስ ስር በቀረበው ክፍል ባለ ራዕይ የመሆንና በዓላማ የመፅናት አስፈላጊነት ቀርቧል ፡፡ ከዓላማ ውጪ የሚኖር ህይወት ከህይወት አይቆጠርም ፡፡ ዓላማ ቢስ ወይም ከባለራዕይነት ወደ ዓላማ የለሽነት የመጣ ሰው ኖሯል ለማለት ከባድ እንደሆነ ያትታል - ይህ የመጽሐፉ ክፍል ፡፡

“አንድ ሰው በትርፍ ጊዜው ብዙ ሙታን ወደተቀበሩበት የመቃብር ስፍራ ሄዶ በሰዎች መቃብር ላይ የተጻፉትን ጽሑፎች በማንበብ ሳይ ሳለ ፣ በአንድ ሰው መቃብር ላይ አንድ ግር የሚል ጽሑፍ አነበበ ። ጽሑፉ በ”30 ዓመቱ ሞተ ፣ በ60 ዓመቱ ተቀበረ” ይላል፡ ጽሑፉ ግር ብሎት ቆሞ ማሰላሰል ጀመረ ፡፡ “አንድ ሰው በ30 ዓመቱ ሞቶ እንዴት ለ30 ዓመታት ሳይቀበር ሊቆይ ቻለ ?” ይህንን እያሰበ የጽሑፉን ትርጉም የሚያውቅ አንድ ሰው ደረሰ ፡፡ “ምን እንደምታስብ ገብቶኛል” አለው ሃሳቡን አንብቦ ፡፡
ጥያቄውን በግምት ደርሶበት ኖሮ በቀጥታ መልሱን ነገረው ፡፡ “ይህ ሰው እጅግ በጣም የሚያስገርም ራእይና ዓላማ የነበረው ሰው ነበር ፡፡ ብዙ ነገሮችን የመስራት እቅድ የነበረውና በዚህም ትጋቱ በሕብረተሰቡ ዘንድ እጅግ የታወቀና ለትልቅ ነገር የሚጠበቅ ሰው ነበር ፡፡ ልክ 30 ዓመት ሲሞላው በተለያዩ ውጣ ውረዶች በማለፉ ምክንያት ተስፋ በመቁረጥ ዓላማውን ሁሉ ትቶ ከርታታ ሰው ለመሆን በቃ ፡፡ የሚቀጥሉትን 30 ዓመታት እንዲሁ በየቦታው ሲንቀዋለል ነው ያሳለፈው ፤ ካለምንም ዓላማ ፡፡ የጽሑፉ ትርጉም ይህ ነው ፡፡ ሰውዬው ሞተ ብለው የሚያምኑት ራእዩን በጣለበትና ጊዜውን በተራ ነገር ማሳለፍ በጀመረበት በ30 ዓመቱ ነው - በአካል ቢኖርም ሞቷል ነው አባባላቸው ፡፡ ልክ በ60 ዓመቱ ታምሞ አካላዊ ሞትን ሲሞት ያን ጊዜ ተቀበረ ማለታቸው ነው”

በአካል መኖር ብቻውን ኖሯል አያስብልም ነው ነገሩ ፡፡ ህያው የሚያደርገን ራእይና የመኖር ዓላማ እንጂ ቆሞ መሄድ አይደለም ፡፡ ቆሞ ለመሄድ በአራት እግር ሆነ እንጂ እንስሳም ይሄዳል ፡፡ እንስሳ ግን የሰውን ስራ ከማቅለሉ ውጪ የራሱ ራዕይ የለውም ፡፡ ስለሌለውም የሌሎች ባሪያ ሆኖ ይኖራል ፡፡ በሰው ራእይና ዓላማ የለሽ ህይወት ህይወት ሳይሆን ሞት ነው ፡፡ ዓላማ አልባው ሰውም ለመቀበር ነፍሱ ከስጋው እስክትነጠል ይጠበቃል እንጂ ሙትማ ሙት ነው ፡፡ ሰውን ህያው የሚያደርገው ህልሙ ነው የሚል ይመስላል ፀሐፊው፡፡

ልክ ነው ዓላማ ያለው ሰው መሆንና በዓላማው የሚፀና ሰው መሆን ሁለት የስኬት ቁልፎች ናቸው ፡፡
ስኬታማ ሰዎች ባለራዕይ ናቸው ፡፡ ለራዕያቸውም ታማኝና ፅኑ ናቸው ፡፡ ለፈተናም ሆነ ለየትኛውም ነገር በቀላሉ እጅ አይሰጡም ፡፡ እጅ አለመስጠታቸው የህያውነታቸው ምልክት ፣ የስኬታቸው ጠቋሚ ነው ፡፡
በሌላው ስለ ትኩረት ወሳኝነት በሚያወራው “እንዲያይ ሳይሆን እንዲያተኩር” በሚለው ምዕራፍ ለስኬት የትኩረትን አስፈላጊነት ያትታል ደራሲው፡፡

“25 የስኬት ቁልፎች” የተሰኘው መጽሐፍ በዚህ መልኩ የተለያዩ 25 ለስኬት አስፈላጊ ያላቸውን ነጥቦች እየዳሰሰ በ160ኛው ገፅ ላይ ያበቃል ፡፡ መጽሐፉ በየጽሑፉ መሀል የሀሳቡ መደገፊያና ማጠናከሪያ የሆኑ አባባሎችን በወሽመጥነት እያስገባ ለአንባቢያን ቀርቧል ፡፡

በሰለሞን በቀለ

12/03/2024

በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ ናቸው

AMN ህዳር 23/2017 ዓ.ም

በለውጡ ዓመታት የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የአካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚነት ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ገለጸ።

በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት በሁሉም ዘርፎች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ የልማት ሥራዎች በስፋት ተከናውነዋል።

የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ምቹ አካባቢን በመፍጠር፣ በትምህርት ተደራሽነትና በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ ተጨባጭ ሥራዎች ተከናውነዋል።

በለውጡ ዓመታት በመሠረተ-ልማት ግንባታዎች ጭምር መንግሥት ለአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት መሥራቱን የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አባይነህ ጉጆ አንስተዋል።

የአካል ድጋፍ አግኝተው ወደ ቀደመ ሥራቸውና ኑሯቸው እንዲመለሱ የአካል ድጋፍ ማምረቻ ማዕከልን በማጠናከር ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚና የላቀ እንደነበር አንስተዋል።

በተለይም ለአይነስውራን ምቹና ዘመናዊ አዳሪ ትምህርት ቤት እንዲገነባ በማድረግ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ዘመን ተሻጋሪ ሥራ መሥራታቸውን ያነሱት ፕሬዝዳንቱ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል።

የአይነስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤትም ለአይነስውራን የመማር ተስፋቸውን ያለመለመ ትልቅ ሥራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በለውጡ ዓመታት ለአካል ጉዳተኞች የሚጠቅሙ የሕግና አሠራር ማሻሻያዎችን ለማድረግ የተጀመረው ጥረትም ወደ መጨረሻው ምዕራፍ እየተሸጋገረ በመሆኑ በቀጣይ ትልቅ ዕድል ይዞ የሚመጣ መሆኑን አንስተዋል።

በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየውን የሕንፃ አዋጅ ለማሻሻልም አዲስ ረቂቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረቡን ጠቅሰዋል።

እንደ አጠቃላይ በአዲስ አበባና ሌሎችም አካባቢዎች የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ ያሉ መሠረተ-ልማቶች አካል ጉዳተኞችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸው ለአካል ጉዳተኞች ትልቅ ተስፋ ሆኗል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

12/03/2024
12/03/2024
12/03/2024

ሀሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የተጠረጠረ ግለሰብ ተያዘ

AMN - ህዳር 23/2017 ዓ.ም

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አካባቢ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው ሰዎችን ወደ ውጭ ሀገር የመላክ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ ሳይኖረው አንድን ግለሰብ "ሁሉንም ነገር አስጨርሼ ወደ ዱባይ እልክሃለሁ" በማለት ከ297 ሺህ ብር በላይ እንደተቀበለ የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል፡፡

ከተጠርጣሪው የጉዞ ሰነድ የተሰጠው የግል ተበዳይም ወደ ዱባይ ለመሄድ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተገኘበት ወቅት ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑ እንደተገለፀለት ተጠቅሷል።

የግል ተበዳይን አቤቱታ የተቀበለው የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር አውሎ የፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዕዛዝ በማውጣት በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ብርበራ ሀሰተኛ ሰነዶችና ሰነዶቹን ለማዘጋጀት የሚጠቀምበትን ኮምፒውተር በማስረጃነት ተይዞ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሃሰተኛ ሰነዶች ከግለሰብ አልፈው በሃገር ላይ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት ተመሳሳይ ወንጀሎችን ለመከላከል ህብረተሰቡ ጥቆማና በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አድርጓል።

10/31/2024

በ2017 በጀት ዓመት በአገልግሎት ዘርፍ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት ይመዘገባል፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

AMN - ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም

በ2017 በጀት ዓመት በአገልግሎት ዘርፉ 7 ነጥብ 1 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ እየተካሄደ ባለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው፡፡

የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች በእጅጉ ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ እየሰጠ ያለውን አገልገሎት ለማሻሻልና ለማዘመን የሚያስችሉ ራዎችን በመስራት በበጀት ዓመቱ 124 አውሮፕላኖች እንደሚገዙ ተናግረዋል፡፡

አየር መንገዱ አሁን ላይ በዓመት ከ20 እስከ 25 ሚሊየን የሚደርሱ መንገደኞችን የሚያስተናግድ ሲሆን በቀጣይ ከ100 እስከ 130 የሚደርሱ መንገደኞችን በዓመት ለማስተናገድ የሚያስችል ኤርፖርት ለማስገንባት ጥናት መጠናቀቁንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

አዲስ የሚገነባው ኤርፖርት ከነባሩ ኤርፖርት 40 ኪሎ ሜትር የሚርቅ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሁለቱን ኤርፖርቶች በባቡር ትራንስፖርት በማገናኘት መጠቀም እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡

ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሰጠው አገልግሎት ክብርና ዝናውን አስጠብቆ ከመሄዱ በተጨማሪ፣ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ትልቅ ውጤት እያስመዘገበ የሚቀጥል ተቋም ሆኖ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስረዱት፡፡

እንደነዚህ አይነት ተቋማት በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ወደብ ለሌላቸው ሀገራት ወሳኝ መሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒትሩ ይህም ለኢትዮጵያ ማንሰራራት ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በአስማረ መኮንን



ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

10/29/2024
10/29/2024

Tajaajila kennamu hundaaf waraqaan eenyummaa biyyaleessa dhiyeessun dirqama- Tajaajila ragaalee mirkaneessuu fi galmeessu

AMN- Onkololeessa 19/2017

Tajaajila kennamu hundaaf waraqaan eenyummaa biyyaleessa dhiyeessun dirqama ta’uu isaa Tajaajila ragaalee mirkaneessuu fi galmeessu beeksissera.

Tajaajilli kun dameewwan 16 keessatti tajaajila mirkaneesuu sanadootaa fi galmee magaala Finfinnetti argaman argachuuf waraqaa eenyummaa dijiitaalaa ykn waraqaa raga Faayidaa raga ittiin galmaa’an dhiyeessun barbaachisaa ta’uun isaa ibseera.

Haaluma kanaan, Saadasa 1/2017 irraa eegalee tajaajila dhaabbatichi kennuuf waraqaa eenyummaa faayidaa (digital ID) ykn ragaa ittiin galmaa’an dhiyeessuun dirqama ta’uu hubachisuu isaa odeffannon Tajajilicharra arganne ni ibsa.

Address

Saint Paul, MN

Telephone

+251913141163

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Badhaadhina Media Network posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Badhaadhina Media Network:

Videos

Share