12/05/2024
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን በጎምቦራ ወረዳ የጤና ጽ/ቤት ሠራተኞች ደመወዝ እስካሁን ድረስ 295% አልተከፈለም ።👇
👉የመስከረም ወር 2016 ዓ.ም ➞ 100%
👉የየካቲት ወር 2016 ዓ.ም ➞ 100%
👉የሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ➞ 25 %
👉የሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ➞ 20%
👉የጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም ➞ 50%
➞ጠቅላላ ድምር 295% አልተከፈለም ።
✍️በእኛ ዞን ነባራዊ ሁኔታ የተለያዩ ምክንያቶችን እየደረደሩ የሠራተኛውን ደመወዝ ፈቃዱን ሳይጠይቁ በፐርሰንት ቀንሶ መክፈል የተለመደ አሰራር እየሆነ መምጣቱን ከተለያዩ መዋቅሮች ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
✍️የመንግሥት ሃላፊዎች የሚወስኗቸው እያንዳንዱ ውሳኔዎች ህግን መሰረት ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ ለሚመሩት ተቋምም ሆነ ለሚያስተዳድሩት ሠራተኛ ደህንነት መጠበቅ እጅግ ወሳኝ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል፡፡
➞የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ የሚቆረጠው በምን አግባብ ነው?
✍️የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 በፌደራል መንግሥቱ ሥር ተቀጥረው የሚሰሩ ሠራተኞች የሚተዳደሩበት ህግ ነው፡፡ በዚህ ህግ ላይ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በምን አኳኋን ሊቆረጥ እንደሚችል በግልፅ አስቀምጧል፡፡ የአዋጁ አንቀፅ 9 (2) የደመወዝ ክፍያ በሚለው ርዕስ እንዲህ ይነበባል፡፡
✍️የማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ ደመወዝ፣
ሀ) ሠራተኛው ስምምነቱን በጽሑፍ ሲገልጽ፣
ለ) በፍርድ ቤት ትዕዛዝ፣
ሐ) በሕግ በተደነገገው መሠረት ፣ ካልሆነ በስተቀር ሊያዝ፣ ሊቆረጥ ወይም በፐርሰንት ቀንሶ መክፈል አይችልም፡፡
➞ደሞዙ ከፍቃዱ ውጪ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ምን ማድረግ ይችላል ?
✍️የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀፅ 79 የመንግሥት ሠራተኞች መብቴ ተጣሰ ብለው የሚያቀርቧቸውን የስራ ክርክር ክሶችን የሚዳኝ የአስተዳደር ፍርድ ቤት ተቋቁሟል፡፡ ይህ ፍርድ ቤት ከሚያያቸው ጉዳዮች መካከል ከህግ ውጪ የደመወዝ መያዝ ወይም መቆረጥ አንዱ ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ በተገለፀው አኳሃን በጽሑፍ ስምምነቱን ሳይገልፅ ደሞዙ የተቆረጠበት የመንግሥት ሠራተኛ ቀጣሪውን መ/ቤት በአስተዳደር ፍ/ቤት ቀርቦ መክሰስ እና የተቆረጠበትን ደሞዙን ማስመለስ እንደሚችል ህጉ ያስቀምጣል፡፡
✍️በፐርሰንት ቀንሶ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ መክፈል ከህግ ውጪ ከመሆኑም ባሻገር በስራው እርካታ የራቀውን ሠራተኛ ከመፍጠር አልፎ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚያመጣው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል ሠራተኛውም በመሪዎች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ በጀርባ ሆኖ ከማጉረምረም ይልቅ መብቱን እና ግዴታውን ጠንቅቆ በማወቅ በህግ ለተሰጠው መብት መታገል እና ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል፡፡
👉ውድ ወገኖቻችን ለተጠቀሰው ሀሳብ በኮሜንት መስጫው ላይ ገንቢ አስተያየትዎን ያካፍሉን!!
ህዳር 26/2017 ዓ.ም