CORE What makes CORE different!? We are a social media platform thats is free from everything. join us and share, communicate, and have fun!

09/10/2022

አዲሱ ዓመት የሰላም የፍቅር የመተሳሰብ የማስተዋል ያድርግልን
🌼🌼🌼2015🌼🌼🌼

70 የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ   | ፍቃድ ሳይኖራቸው የውጭ ሀገር ገንዘብ በመመንዘር የሀዋላ ስራ ሲሰሩ ነበር  ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ...
08/06/2022

70 የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ

| ፍቃድ ሳይኖራቸው የውጭ ሀገር ገንዘብ በመመንዘር የሀዋላ ስራ ሲሰሩ ነበር ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ 70 የኤርትራ ዜግነት ያላቸው ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

በተመሳሳይ ወንጀል የተጠረጠሩ ሌሎች ሁለት ግለሰቦች ደግም የኢትዮጲያ ዜግነት እንዳላቸው ለፍርድ ቤት አስመዝግበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ረፋድ ላይ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል።

በሀዋላ ስራ ላይ ተሰማርቶ እንደሚሰራ ለፍርድ ቤቱ አምኖ የገለጸው ኤርሞን ሳሀለ : የማነ ገ/ሚካኤል : አማንኤል ረዘነ :መንግስቱ ወልደ ገሪማን ጨምሮ ባጠቃላይ 72 ተጠርጣሪዎች ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ አስሩ ሴቶች ናቸው።

ተጠርጣሪዎቹ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከ :በለሚ ኩራ እና በኮልፌ ክ/ከ በተለያዩ ወረዳዎች ኗሪ መሆናቸውን ለፍርድ ቤቱ አስመዝግበዋል።

ተጠርጣሪዎችን ፍርድ ቤት ያቀረቡት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አራት መርማሪዎች የጥርጣሬ መነሻ ምክንያታቸውን በጥምረት አቅርበዋል።

በዚህም ከደህንነት ተቋም እና ከኢንሳ ጋር በመተባባበር በተካሄደ የኦፕሬሽን ስራ በከተማዋ በተለያዩ አካባቢዎች በህገወጥ መንገድ የተለያዩ ውጭ ሀገር እና የኢትዮጲያ ገንዘብ ሲያዘዋውሩ መያዛቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

ሲዘዋወር ነበረ ከተባለ የገንዘብ መጠን ውስጥ 27 ሺህ 491 የአሜሪካን ዶላር፣ 15 ሺህ 325 ዩሮ፣ 680 ፓውንድ፣ 6 ሺህ 689 የኤርትራ ናቅፋ፣ 5 ሺህ 200 የሲውዝ ፍራንክ፣ 500 የአንጎላ ክዋንዛ፣ 1 ሺህ 680 የኳታር ሪያል፣ 1 ሺህ የኖርዌይ ክሮን እና 49 ሺህ 735 የኢትዮጵያ ብር እና የተለያዩ የባንክ ደብተሮች መያዙን ለፍርድ ቤቱ አብራርተዋል።

በሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዲከሰት ለማድረግ ከብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ሳይኖራቸው የውጭ ገንዘብ የመመንዘር ስራ ሲሰሩ ነበር ሲሉ መርማሪዎቹ በየተራ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል።

የተጠርጣሪዎችን ቃል ለመቀበል: አሻራ እና ፎቶ ለማስነሳትና ተጨማሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ የ14 ቀን ጊዜ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ቢኒያም ሰመረ የተባለ ተጠርጣሪ በበኩሉ በመኖሪያ ቤቴ የተገኘው 900 ዶላር ከቤተሰቡ በስጦታ በየጊዜው የላከለት ገንዘብ መሆኑን አብራርቷል።

ኤርሞን ሳሀረ የተባለ ተጠርጣሪ ደግሞ በፍተሻ ደረሰኝ ብቻ የተገኘበት ቢሆንም የሀዋላ አገልግሎት በግሉ እንደሚሰራ ግን አምኖ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ኢትዮጲያዊ ዜግነት ያላቸው ዳንኤል መረሃ ወልደ ሰንበት የተባሉ ተጠርጣሪ ደግሞ በመምህር ሙያ ለ20 አመት መስራታቸውን ጠቅሰው ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት እንደሌለው ገልጸዋል።

በመምህር ሙያ መሰማራታቸው ሌላ ወንጀል አይሰሩም ማለት አደለም ሲል ፖሊስ ምላሽ ሰቷል።

ሰመረ ተስፋ ማርያም የተባለ የኤርትራ ዜግነት ያለው ተጠርጣሪ ጠበቃ የሆነው ተስፋሁን አግደው በበኩሉ

መርማሪ ፖሊስ ለጊዜ ቀጠሮ መጠየቂያ የሚያስችል የጥርጣሬ መነሻ አለማቅረቡን ገልጾ ተከራክሯል።

ደንበኛዬ በስር የሚቆዩበትን ምክንያት በዝርዝር ባልገለጸበት ሁኔታ ታስሮ ሊቆይ አይገባም በማለት ዋስትና እንዲፈቀድለት ጠይቋል።

በወንጀል ህግ አንቀጽ 41 መሰረት ወንጀል ግላዊ መሆኑን የጠቀሰው ጠበቃው የተናጠል ተሳትፏቸው ባልተገለጸበት ሁኔታ ገንዘብ ተገኝቶበታል ተብሎ ማሰር ተገቢ አደለም በማለት ተከራክሯል።

በመርማሪ ፖሊስ በኩሉ ከ100 ሺህ በላይ ገንዘብ ግለሰብ ይዞ መገኘቱ በራሱ በህግ የሚያስጠይቅ ነው ሲል ምላሽ ተሰቷል።

የተለያዩ የውጭ ሀገር ገንዘቦች በመኖሪያ ቤታቸው የተገኘባቸው ከ15 በላይ ተጠርጣሪዎች ኢንባሲ በዶላር እንድንከፍል ስለሚጠይቀን ለክፍያ በቤታችን ያስቀመጥነው ገንዘብ ነው እንጂ ወንጀል አልፈጸምንም ሲሉ አብራርተዋል ።

በቤታቸው በተደረገ ብርበራ ከባንክ የሂሳብ ደብተር እና ከደረሰኝ ውጪ ጥሬ ገንዘብ እንዳልተገኘባቸው ገልጸው ከወንጀል ጋር የሚያገናኛቸው ጉዳይ እንደሌለ ያብራሩ ተጠርጣሪዎችም ነበሩ።

የጊዜ ቀጠሮ መዝገባቸውን የተመለከተው ፍርድ ቤቱ የሁሉም ተጠርጣሪዎች ተሳትፎ በቀጣይ ቀጠሮ በዝርዝር እንዲቀርብ አዟል።

ሁሉም የተጠረጠሩበት ጉዳይ ተመሳሳይ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ግን የተለያዩ የምርመራ ቀናቶችን ለፖሊስ ፈቅዷል።

በዚህም ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ጊዜ ውስጥ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ እንዲቀርብና የተጀመረው ምርመራን እንዲያከናውን አርባ ተጠርጣሪዎች ላይ የ7 ቀን የምርመራ ጊዜ የፈቀደ ሲሆን

ሌሎች አስር ተጠርጣሪዎች ላይ የ9 ቀን ተጨማሪ ምርመራ ቀናትን ለፖሊስ የፈቀደው ፍርድ ቤቱ ቀሪ ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ ደግሞ የ10 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።

የጊዜ ቀጠሮውን የተመለከቱት ዳኛ ቀጠሮ ከመድረሱ በፊት ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች ካሉ ተጣርቶ እንዲለቀቁ የሚል ሀሳብ ለፖሊስ ሰተዋል።

Via Tarik Adugna

Nancy Pelosi's visit to Taiwan is a clear provocation, and China has the right to take measures to save its country: Rus...
08/02/2022

Nancy Pelosi's visit to Taiwan is a clear provocation, and China has the right to take measures to save its country: Russia’s Foreign Ministry

21 Chinese warplanes entered Taiwan's Air Defence Identification Zone, on day of Pelosi visit: Taiwanese Defence Ministr...
08/02/2022

21 Chinese warplanes entered Taiwan's Air Defence Identification Zone, on day of Pelosi visit: Taiwanese Defence Ministry

Chinese Army says will conduct military exercises including live-fire drills in Taiwan strait. This come amid rising ten...
08/02/2022

Chinese Army says will conduct military exercises including live-fire drills in Taiwan strait. This come amid rising tensions due to US House speaker Nancy Pelosi visit to Taipei.

US House speaker Nancy Pelosi expected lands in Taipei. Chinese fighter jets crossing Taiwan Strait, according to Chines...
08/02/2022

US House speaker Nancy Pelosi expected lands in Taipei. Chinese fighter jets crossing Taiwan Strait, according to Chinese state media.

አገር እና ጥበብ መውደድ ድንበር አልባ ነው። ሮፍናንን በዚም መንገድ ሳይታክት ሲመላለስ አየኹት። ደግሜ ደጋግሜ ተደንቄያለሁ።ሮፍናን ጠቢብነቱን ዳግም አስመስክሯል ብዬ ከልቤ አምናለሁ። ዘመኑ...
07/10/2022

አገር እና ጥበብ መውደድ ድንበር አልባ ነው።

ሮፍናንን በዚም መንገድ ሳይታክት ሲመላለስ አየኹት። ደግሜ ደጋግሜ ተደንቄያለሁ።

ሮፍናን ጠቢብነቱን ዳግም አስመስክሯል ብዬ ከልቤ አምናለሁ። ዘመኑን በዋጀ ምት ዘመን አይሽሬ ቅኔዎች ተቀኝቷል።

እኔ ያንተ ትውልድ አባል በመኾኔ ብቻ እኮራለሁ!!

የኔን ምርጥ አንደኛ ለማውጣት ቸገረኝ። ለጊዜው በምስሉ ላይ ያለውን "የአማኙ ቅኔ" በቀዳሚነት መርጬዋለሁ።
እናንተስ?

ሙሉ አልበሙን በተከታዩ ሊንክ (ብቻ -አደራ) ያገኙታል።
https://youtube.com/playlist?list=PL0cLi6iI80Vh0Yj5ySh9Yj5Evoc1thzpN

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገአዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ...
07/05/2022

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሬ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሚኒስቴሩ ለፋና ብሮድካስንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ መሰረት÷
ቤንዚን----47 ነጥብ 83 በሊትር
ነጭ ናፍጣ ….49 ነጥብ 02 በሊትር
ኬሮሲን…49 ነጥብ 02 በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ…53 ነጥብ 10 በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ…52 ነጥብ 37 በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ…98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን አስታውቋል፡፡

At least 150 people killed in new round of attacks in Hawa Gellan district in Ethiopia's Oromia region. The villages whe...
07/04/2022

At least 150 people killed in new round of attacks in Hawa Gellan district in Ethiopia's Oromia region. The villages where the attacks took place are populated by ethnic Amharas.

Wow! That's awesome! Love it. What a tree
05/25/2022

Wow! That's awesome! Love it. What a tree

Tree was saved by a tree😀
05/21/2022

Tree was saved by a tree😀

The tree that does not give up. 🌳 ♥ ️
05/21/2022

The tree that does not give up. 🌳 ♥ ️

05/18/2022

"በአንድ ሳምንት ዉስጥ ሦስት ሴቶች አዲስ አበባ ዉስጥ ራሳቸዉን ከፎቅ ወርዉረዉ ገለዋል።" 😔

ራስ መግደል ያስደነግጣል። ከፎቅ መውደቅ ያስደነግጣል። በአንድ ሳምንት ውስጥ ሶስት (ያልተቆጠረ እና ለዜና ያልበቃ አይጠፋም) ሰው አንድ አይነት አሟሟት መሞቱን መስማት ያስደነግጣል።

የአሟሟትም ወረት አለው? ፋሽን አለው? በተለያዩ ጊዜያት የሰማናቸው አይነት አሟሟቶች አሉ። ፎቅ ስለበዛ የሚል ነሆለልም አይጠፋም።

ያም ሆነ ይህ የአእምሮ ጤንነት በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ያመላክታል።

ወጉን፣ ባህሉን፣ ማንነቱን፣ ቀስ እያልን እየናድነው መተከዣ ጎረቤት ለማጣት እንለፋለን።

ልባዊ ጓደኝነት ጥንታዊ ሆኗል። ለአስር ብር የሚሸጠን ብዙ ነው።

ከቁስ ውጭ ሌላ ምንም እንዳናስብ ወላጆች (የጠቀሙን መስሏቸው ሁሉን በማሟላት) እና ባለስልጣናት እየታገሉ ነው።

እምነታችንን እንድንተው፣ በመንፈስ እንዳንጽናና በስልጣኔ ስም ሊያስጥለን ደጅ የሚጠናው ብዙ ነው።

ድራግ እንደማስቲካ ነው አሉ።

ማኅበራዊ ሚዲያም አለ። መለስ ቀለስ ብሎ ለማሰብ በምን ፋታ?

ወድቆ ለመሞት ሲታሰብ፣ ድንገት ብተርፍስ? ብሎ ማሰብ ቢቻል ጥሩ ነበር። ነበር። ነበር።

ራስ ወዳድ ሆነን ራሳችንን ለማጥፋት ስንቆርጥ፣ ለመሞት ወድቀን እምቢ ቢለን፣ ከነስብርብራችን ተቀብለው የሚያስታምሙን ቤተሰቦች አሉን እና አንጨክን። እንጠቅማለን። ጨክነን የምንተዋቸው የሚወዱን ብዙ አሉ።

ኑር ባታምንም!!

05/15/2022
        Last Prayer - Last Walk - Last Memories 😢Funeral of Sheikh Khalifa bin Zayed😥 Rest in eternal peace oh beloved k...
05/13/2022

Last Prayer - Last Walk - Last Memories 😢
Funeral of Sheikh Khalifa bin Zayed😥
Rest in eternal peace oh beloved king.

 : Gov't adjusts fuel priceJust four months after making a decision to gradually lift oil subsidy, the federal governmen...
05/07/2022

: Gov't adjusts fuel price

Just four months after making a decision to gradually lift oil subsidy, the federal government adjusts the price of fuel.

Effective as of tomorrow, the price of benzene sees a five birr increase, costing 36.8 birr a litre. The price of diesel fuel adjusted by 22.4 percent, reaching 35.4 birr.

The government has been facing an increase in import bill due to a surge in price of oil in the global market. Coupled with the fast depreciation of birr, this has escalated fuel subsidy provided to the public over inflation fears.

Lately, there has been a shortage fuel across gas stations in Ethiopia, which officials attribute to hoarding practices and growing contraband market.

https://youtu.be/BUCxaB4QiN0
05/02/2022

https://youtu.be/BUCxaB4QiN0

ፕሮግራሜ ሲለቀቅ ወዲያዉ እንዲደርስዎ ይህንን ሊንክ ይጫኑ https://bit.ly/3mGI4J6 ማሳሰቢያ:- በዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁ ቪድዮዎች በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ስለሆነ መልሶ በዩቱብም ሆነ በሌሎች...

Address

New York, NY

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when CORE posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share