06/09/2024
ይሄ ፖስት የቁርጥ ቀን ወዳጆችን እንደሚያስከፋ አልጠራጠርም😅
🥩 🥩🥩🥩🥩
ይሄ ፎቶው ላይ ግስጥ ብሎ የሚታየው ሸበላ የኮሶ ትል ነው። ጥሬ ስጋ መብላት ከሚያስከትላቸው መዘዞች ሁላችንም በስፋት የሰማነው ስለኮሶ ነው። ነገር ግን ያልበሰለ ስጋ መብላት ከኮሶ ባሻገር ሌሎች መዘዞች አሉት::
🥩🥩🥩🥩
በቅድሚያ ግን ለመሆኑ አንዳንድ የቲክታክ ወትዋቾች እንደሚደሰኩሩት ጥሬ ስጋ መብላት ለጤና ጥቅም አለው ወይ? ጥሬ ሙዳ ስጋ ጋር በሚደረገው ትንቅንቅ ከሚፈረጥመው የመንጋጋ ጡንቻ ባሻገር ጥሬ ስጋ ከበሰለ ስጋ የተሻለ አንዳችም ጠቀሜታ የለውም🤪 እንዲያውም በተቃራኒው የበሰለ ምግብ በቀላሉ ስለሚፈጭ አንጀታችን ንጥረነገሮችን በቀላሉ ለማግኘት ይመቸዋል።
🥩🥩🥩🥩
ጥሬ ስጋ ከኮሶ ባሻገር ሌሎች በርካታ ኢንፌክሽኖችን ሊያስከትል ይችላል። በተለይ ለተለመዱት አንቲባዮቲክ የማይበገሩ አደገኛ ባክቴሪያዎች የሚያመጡት የምግብ መመረዝ ከኮሶ የበለጠ አሳሳቢ ሆኗል።
ህፃናት፣ ነፍሰጡሮችና የመከላከል ሀይላቸው የተዳከመ ህሙማን ጥሬ ስጋ ቀርቶ የተነካካ ምግብ እንዳይበሉ ይመከራል። የእነዚህ ባክቴሪያዎች የብከላ አቅም በጣም ሀይለኛ ከመሆኑ የተነሳ እንኳን ጥሬ ስጋውን ራሱን እሱ የነካውን ምግብ መብላት በራሱ መመረዝ ሊያስከትል ይችላል።
👉እንደመፍትሄ - ጥሬ ስጋ ባለበት ምግቦችን ስንገዛ ስናዘጋጅና ስናቀርብ ሌላኛው ተመጋቢ “ፆመኛ” እንደሆነ ማሰብ ነው። የ”ፆመኛው" ምግብ እንዳይነካ የምናደርገውን ጥንቃቄ እዚህ ላይ መተግበር። ለምሳሌ ጥሬ ስጋ ስንገዛ ለብቻው በፌስታል ማሸግ፤ ጥሬ ስጋ የከተፍንበት ቢላና መክተፊያ ማጠብ፣ ጥሬ ስጋና ሌሎች ጥሬያቸውን የሚበሉ ነገሮችን(ለምሳሌ ሰላጣ) አለማነካካት፣ ለይቶ ማቅረብ…you get the point
🥩🥩🥩🥩🥩
በነገራችን ላይ የምግብ መመረዝን እንደቀልድ ባናየው መልካም ነው። በአለም ዙሪያ በየአመቱ ግማሽ ሚሊየን የሚጠጉ ሞቶችን የሚያስከትል ከባድ የጤና ችግር ነው። ከዚህ ቁጥር ውስጥ ከጥሬ ስጋ ጋር የተያያዘው ምን ያክሉ እንደሆነ መረጃ የለኝም። you get the point…
🥩🥩🥩🥩🥩
“ጥንታዊው ሰው ጥሬ ስጋ ስለሚበላ ጤናማ ነበር” ይልሃል የቲክታክ ኃሳዊ ተመራማሪ (pseudopaleontologist)። ጥንታዊው ሰው አማካይ እድሜው ከሰላሳ ሳይዘል እንደሚሞት ልብ ሳይል። እውነተኞቹ ተመራማሪዎች እንደሚሉት ጥንታዊው ሰው እሳትን አግኝቶ ምግቡን ማብሰል ሲጀምር ነው አንጎሉ መጎልበት ሲጀምር ነው ከዋሻ ወጥቶ አለምን በቁጥጥሩ ስር ያዋለው።
Abiy Meaza