01/06/2024
በዓሉን አቅመ ደካሞችን በመጠየቅና አብሮነታችንን በሚያጠናክሩ ዕሴቶች ማክበር ይገባል - አቶ ደስታ ሌዳሞ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የገናን በዓል ስናከብር አቅመ ደካሞችን በመጠየቅና አብሮነታችንን በሚያጠናክሩ ዕሴቶች ማክበር እንደሚገባ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስገነዘቡ።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የዘንድሮን የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል በሚከተለው ቀርቧል።
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የመወለዱ ምስጥር የሰዉ ልጆችን ከጨለማው ዓለም የባርነት ህይወት ነጻ ለማውጣትና የዘለዓለምን ህይወት ለመስጠት የታለመ ቢሆንም በሌላ መልኩ ኢየሱስ ክርስቶስ ከተወለደ በኋላ ለሰው ልጅ ሰላምን ፣ፍቅርን፣አንድነትን፣ህብረትን ፣መተሳሰብን፣መዋደድንና መከባበርን አስተምሮናል።
ኢየሱስ የሰላም ፣የፍቅርና የአንድነት ምሳሌያችን እንደሆነ ሁሉ እኛም ከጥላቻ ይልቅ ሰላምንና አንድነትን ብንናፍቅ ለሀገራችን የሚበጅ ሲሆን ለሰማያዊ መንግስትም ቢሆን ደስ የሚያሰኝ በረከታችን ይሆናል።
ልማትንና ብልጽግናን ሁላችንም የምንናፍቀው ጉዳይ ሲሆን ይህም በሀገራችን ሊሳካ የሚችለው በህዝቦች መሀከል ሰላም፣ፍቅርና አንድነት ሲረጋገጥ ነው፤ቁጭታችን የነበረዉን የልማት ተግዳሮታችንን የሚቀርፍልንና የብልጽግና ጉዟችን ሥራ አመላካች የሆነ በሰጥቶ መቀበል በርህና በጋራ ጥቅም ላይ በተመሠረተ ከሱማሌ ላንድ ጋር ኢትዮጵያ የባህር በር እንድታገኝ የጋሪ መግባቢያ ሰነድ መፈራረማችን ይታወቃል ፤ይህም ኢትዮጵያ አንድ እርምጃ በኢኮሚም ይሁን ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚጠናክር በመሆኑ መላው ኢትዮጵያዊ ደስ ሊሰኝ ይገባል።
ስለዚህም አብሮነታችንንና መቻቻላችንን፤ወንድማዊ መዋደዳችንንና መከባበራችንን ፤ሀገራዊ መተሳሰባችንንና የዘወትር አብሮነታችንንሉዓላዊ አርማችን ልናደርጋቸው ይገባል።
በመጨረሻም በዓሉን የተቸገሩትን በማሰብ ፣በመርዳት ፣አቅመ ደከሠሞችን በመደገፍ እና የአብሮነት እሴቶቻችንን በሚያጎላና የኢትዮጵያዊ ጨዋነትን በሚያሳይ መልኩ ማክበር ይገባል።
በደሰጋሚ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ !
ምንጭ:-
ሲዳማ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ