Click Dessie

Click Dessie Make Wollo Great Again

ቢሊዬ❤ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዛሬ አየሁሽአሁን ምን ማለት እንዳለብኝ ባላውቅም በዚች ቅጽበት የሚሰማኝን ስሜት ግን መናገር እፈልጋለሁ። ገና በመጀመሪያ እንዳየሁሽ ልቤ ስንጥቅ ሲል የነበረኝን ስ...
08/21/2023

ቢሊዬ❤ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዛሬ አየሁሽ
አሁን ምን ማለት እንዳለብኝ ባላውቅም በዚች ቅጽበት የሚሰማኝን ስሜት ግን መናገር እፈልጋለሁ። ገና በመጀመሪያ እንዳየሁሽ ልቤ ስንጥቅ ሲል የነበረኝን ስሜት መቼም በሕይወት እያለሁ አልረሳውም። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የምታደርጊውንና የምትናገሪውን በሙሉ በስስት እከተላለሁ አዳምጣለሁ። ምንም እንኳን ለአንቺ ያለኝን ስሜት ለመግለፅ ትክክለኛ ቦታ ባላገኝም አንቺን ባሰብኩ ጊዜ የሚሰማኝ ስሜት ልዩ በመሆኑ በተደጋጋሚ አስብሻለሁ፤ በቃ ደስ ይለኛላ። ቢሊ 😍 በሁሉም ነገሮችሽ እንደማፈቅርሽ ግን እንደዚህ በአደባባይ ላሳውቅሺ እፈልጋለሁ።

07/22/2023

lmkkl

06/07/2023

በዘመነ ካሴ ላይ የተፈጸመውን ተደጋጋሚ “የአጋንንት ጥቃት” ማክሸፉን የጎጃም ፀረ-ድግምት ብርጌድ አስታወቀ 😂

Getnet Almaw Tiruneh - ጌትነት አልማው ጥሩነህ

የጠላት ወገን በዘመነ ካሴ ላይ በተደጋጋሚ የሰነዘረውን የአጋንንት ጥቃት በአስተማማኝ ሁኔታ ማክሸፉን የጎጃም ፀረ-ድግምት ብርጌድ (ጎፀድ) አስታውቋል !!

የብርጌዱ አዛዥና የአለም ፀረ-ድግምት የበላይ አዛዥ አቶ ደምለው ቅደድ ከጎጃም ጎረቤት ለተውጣጡና #ዋጃጋንት የሚገኘውን የጎጃም ፀረ-ድግምት (ጎፀድ) በመጎብኘት ላይ ለሚገኙ ከፍተኛ የድግምት ባለሙያዎች በዛሬው ቀን እንደገለጹት ብርጌዱ በዘመነ ካሴ ላይ በተደጋጋሚ የተቃጣውን የአጋንንት ጥቃት በአስተማማኝ ብቃት ማክሸፉን ገልጸው በአሁኑ ሰዓት ብርጌዱ “በአንደርብ መምታት፣ ጥላ ወጊ፣ በድግምት ማፍዘዝ፣ የጠላትን ልብ ማራራት” በሚል የተለዩ አራት የሚሆኑ ፕሮጀክቶችን ከፍተኛ ሃብትና ባለሙያ መድቦ እያበለጸገ መሆኑን ገልጸዋል... 😂

የጎጃም ፀረ-ድግምት ብርጌድ የበላይ አዛዥ የሆኑት አቶ ደምለው ቅደድ ከጎጃም ጎረቤት ለተውጣጡና ማዕከሉን በመጎብኘት ላይ ለሚገኙ ከፍተኛ የድግምት ባለሙያዎች “ጎረቤት ክፍለ ሃገራት መሰል ፀረ-ድግምት ማዕከላት ሲያደራጁ የማዕከሉ ድጋፍ እንደማይለያቸው” ገልጸው ማዕከሉ በአሁኑ ሰዓት ከኢራን፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ራሽያና ቱርክ ጋር በጋራ ለመስራት ውል ማሰሩን ገልጸውላቸዋል..



አሳፍራችሁን ያልሞትነውን ሰዎች እንዲህ በሳቅ ግደሉን እንጂ !... 😂...😂...😂

ደሴ ውስጥ ብቻ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የዘረፈው የወያኔ አርሚ 31  ገመና በአንድ አባሉ ሲጋለጥ ......👉-ዘረፋው ከከፍተኛ አመራሮች የተላለፈ ትዕዛዝ መሆኑን የአርሚው አዛዦች ሲያብራ...
05/15/2023

ደሴ ውስጥ ብቻ ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የዘረፈው የወያኔ አርሚ 31 ገመና በአንድ አባሉ ሲጋለጥ ......

👉-ዘረፋው ከከፍተኛ አመራሮች የተላለፈ ትዕዛዝ መሆኑን የአርሚው አዛዦች ሲያብራሩ
"አርሚ 31 ከባንኮች የተገኘውን ብር በሙሉ ሰብስቦ ለትግራይ መንግስት እንዲያስረክብ ተልዕኮ ተሰጥቶታል" አሉ።
👉- ከዛ በኋላ ዘረፋውን የሚያስፈፅሙ የሰራዊቱ አባላት ተመለመሉ
-በሌ/ኮ ገ/ስላሴ ገ/መድህን ከሚመራው የአርሚው የመሃንዲስ አባላት
እና ...
-በሌ/ኮ ጨርቆስ ከሚመራው የአርሚው የስለላ አባላት ሰዎች ተመለመሉ። ስራውን ከህዝብ ዕይታ ውጪ ሆኖና ምስጢራዊነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዲፈፀምም ትዕዛዝ ተሰጣቸው ።

👉- እነዚህ የጦሩ አባላት ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ጄኔሬተሮችንና ግራይንደሮችን ተሸክመው ይሰማራሉ።ካዝናዎችን ሲሰብሩ ያድራሉ ።
👉 -ካዝናዎችን እየሰበሩ የሰበሰቡትን ብር በመኪና እየጫኑ ኮ/ል ገ/ብረስላሴ ይዞት ወደነበረው ቤት ( መጠለያ ) ይወስዱታል።
👉የፋይናንስ ሃላፊው ገብረሃንስ ጧት ጧት ወደ ቤቱ እየመጣ ብሩን ይቆጥራል
👉 በመጨረሻም ስራው ሲጠናቀቅ በዘረፋው የተሳተፉት ለያንዳንዳቸው 7 ሺ ብር ተሰጥቷቸዋል።
👉- በዘረፋ የተሰበሰበው ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በኩንታሎች እየተሞላ ወደ መቀሌ ተወሰደ።
ኮ/ል ገ/ስላሴ ፣የፋይናንስ ሃላፊው ገብረዮሃንስ እና የኮ/ል ገ/ስላሴ መጋቢ የነበረችው ዳናይት አብረው ወደ መቀሌ የተጓዙት ሰዎች ናቸው።
👉 ብሩ መቀሌ ውስጥ ላጪ በተባለው ሰፈር ካለው የገብረዮሃንስ ቤት ውስጥ ተራገፈ።

በዚህ ዘረፋ ላይ የተሳተፉ ከፍተኛ የአርሚው አመራሮች
1-ብ/ጄነራል ዘነበ ክፍሉ- የአርሚ 31 አዛዥ
2-ገዛኸኝ - የአርሚው ኮሚሳር (አሁን የትግራይ ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ሆኗል )
3-ኮ/ል ፍሰሃ ፅዮን - የአርሚው ሎጂስቲክስ
4- ሌ/ኮ ገብረስላሴ ገብረመድህን - የአርሚው የመሃንዲስ ሃላፊ
5- ሌ/ኮ ጨርቆስ - የስለላ ሃላፊ
6-ገብረዮሃንስ - የፋይናንስ ሃላፊ
Asfaw Abreha

በነገራችን ላይ የኦሮሚያ ሙስሊሞች በኦሮሞ ፖለቲካ ላይ ካላቸው ውክልና ይልቅ የአማራ ክልል ሙስሊሞች በአማራ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ውክልና ይበልጣል ። ይሄ በማስረጃ ሊረጋገጥ የሚችል ሀቅ ነ...
05/05/2023

በነገራችን ላይ የኦሮሚያ ሙስሊሞች በኦሮሞ ፖለቲካ ላይ ካላቸው ውክልና ይልቅ የአማራ ክልል ሙስሊሞች በአማራ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ውክልና ይበልጣል ። ይሄ በማስረጃ ሊረጋገጥ የሚችል ሀቅ ነው ።

የኦሮሚያ ሙስሊሞች በአሁኑ ሰአት በኦሮሚያም ሆነ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ተሳትፎና ውክልና ከትግራይና ከጋምቤላ ቀጥሎ እጅግ ዝቅተኛው ነው ። በኦሮሚያ ብልፅግና ውስጥ ያላቸው ድርሻም ከሌላው ብልፅግና በጣም ያነሰ ነው ። በተቃዋሚው ፖለቲካ ዘርፍም ያላቸው እንቅስቃሴ ደካማ ነው ። ከጀዋር ሙሀመድ በሗላ በኦሮሚያ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር የሚያስችል ሙስሊም ፖለቲከኛና የፖለቲካ አመራር አለ ማለት ያስቸግራል ። ይህ ሁሉ የሚሆነው ከኦሮሚያ ክልል ህዝብ ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው ሙስሊሙ ሆኖ ሳለ ነው ።

የኦሮሚያ ሙስሊሞች በክልሉ ስራ አስፈፃሚ ውስጥ ያላቸው ድርሻ 20% እንኳ አይሆንም ።

በአንፃሩ የሙስሊሙ ቁጥር ከክርስቲያኑ አንፃር አናሳ የሆነበትን የአማራ ክልል ፖለቲካን ብናይ ሙስሊሞች በገዥውም ይሁን በተቃዋሚ ፓርቲ ውስጥ ጠንካራ ተሳትፎ አላቸው ። የአማራ ብልፅግና መሪው ሙስሊሙ ደመቀ መኮንን ጨምሮ በርካታ ፖለቲከኞች አሉ ።
አብንን እንኳ ብንመለከት በፓርቲው አመራር ደረጃ ጠንካራ ሙስሊሞች ያሉበት ፓርቲ ነው ።

የኦሮሚያ ክልል ግን ሙስሊሞችን እየሸነገለ ከፖለቲካ ተሳትፎ እያራቃቸው ይገኛል ። የሀረርጌ ፤ የባሌ ፤ የአርሲ ፤ የጅማ ፤ የቦረና ፤ የጉጂ ኦሮሞዎች ያላቸው የፖለቲካ ተሳትፎ እጅግ አናሳ ነው ። በተቃራኒው የኦሮሚያን ፖለቲካ በወለጋና በሸዋዎች ይዘወራል ። እነዚህ ደግሞ ሙስሊም ጠል ፖለቲከኞች የሚፈሩበት ቦታ ነው ።

ለኦሮሚያ ፕሮቴስታንት እና ዋቄፈታ የፖለቲካ መሪዎች ሙስሊሙ ኦሮሞ ከእምነቱ ይልቅ የብሔር ማንነቱ ላይ የበለጠ ትኩረት ማድረጉን እንደ ትልቅ አጋጣሚ በመውሰድ እየተጠቀሙት ይገኛሉ ።

ለሌሎች አናሳ ሙስሊሞች ጠበቃና ሚዛን መሆነ የነበረበት ሰፊው የኦሮሞ ሙስሊም ማህበረሰብ የክልሉን ፖለቲካ እንኳ መዘወር አቅቶት በኢስላም ጠል ፖለቲከኞች መገዛቱ የሚጎረብጥ ሀቅ ነው ።



ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial

የከተማችን ማህበረሰብ ለፀጥታ ሀይሉ የሚሰጡትን መረጃ እና ጥቆማ ከዚህ በበለጠ ማጠናከር ይኖርበናል ሲል የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ማህብረሰብ አቀፍ የፖሊሰ አገልግሎት ዋ /ክፍል ...
05/05/2023

የከተማችን ማህበረሰብ ለፀጥታ ሀይሉ የሚሰጡትን መረጃ እና ጥቆማ ከዚህ በበለጠ ማጠናከር ይኖርበናል ሲል የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ማህብረሰብ አቀፍ የፖሊሰ አገልግሎት ዋ /ክፍል ገለፀ።

የደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ ማህብረሰብ አቀፍ የፖሊሰ አገልግሎት ዋ/ክፍል ሃላፊ ኮማንደር አበባዉ አሻግሬ እንደተናገሩ የከተማዋንዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በተለየ ትኩረት በመያዝ በየደረጃው ያለውን ማህብረሰብ በማሳተፍ እንደ አካባቢያችን ተጨባጭ ሁኔታ ህገወጥ ተግባራት የሚፈፅሙትን ግለሰቦች በመለየትና ከህዝብ በመነጠል የማህብረሰቡን ሰላም ማረጋግጥ ይኖርበናል።
የከተማችን ሰላም ለማሰጠበቅ ማህበረሰብ ለፀጥታ ሀይሎ መረጃ በመሠጠት ሰላማችንን መጠበቅ ይኖርበናል።

በከተማች ወሰጥ በዚህ ሳምንት የተለያዩ የፀጥታ ሀይሎች ሚሊትሪ (አልባሳት) በመለበሰ ሰዎችን የሚያሰፈራሩ እና የሚያጭበረብሩ እንዳሉ በወሠጥ መሰመር ጥቆማ እየደረሰን ነዉ ።ሰልዚህም እንደዚህ አይነት ዉንጀልኞችን ለመያዝ እና ለመቆጣጠር የፀጥታ ሀይሉ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ የ24ሰአት እሰታደ ባይ በመሆን እየሰራ እና እየተከታትል ነዉ። ማህበረሰብም በአካባቢዎ ይህንን አይነት ተግባር የሚፈፀም ካጋጠምዎት ወዲያዉኑ ለፀጥታ ሀይሉ ጥቆማ ማደርግ አልብዎት።

አሁንም ሰላም ወዳዱ ማህበረሰብ የፀጥታ ሀይሉ ደጋፍ እና ደጀንነቱን እያረጋገጠና እየደገፈ የከተማችንሰላምን ሰላም ለማስጠበቅ እየሰራ ነው፣ ይሰራልም። ማህበረሰቡ ትክክለኛ መረጃዎችንም ለፀጥታ አካሎቻችን ማድረሱን እንዲቀጥል ሲል ጥሪ አቀርቧል።

👉የተለያዩ መረጃዎችን መሰጠት ካሰፈልገዎት!!!
በደሴ ከተማ አሰተዳደር ፖሊሰ መምሪያ እና በ5ቱ ዋና ፖሊሰ ጣቢያ የመረጃ ሰልክ ቁጥሮች
1ኛ ፖሊሰ ጣቢያ ፦033 111 1107
የጣቢያ ሃላፊ ፦ 0920132011
2ኛ ፖሊሰ ጣቢያ ፦ 033 111 1601
የጣቢያ ሃላፊ ፦ 0914071024
3ኛ ፖሊሰ ጣቢያ፦ 033 111 1011
የጣቢያ ሃላፊ፦ 0914713766
4ኛ ፖሊሰ ጣቢያ፦ 033 111 5119
የጣቢያ ሃላፊ፦ 0910441992
5ኛ ፖሊሰ ጣቢያ፦033 312 3669
የጣቢያ ሃላፊ ፦ 0914600053
የፖሊሰ መምሪያወ ፦ 033 111 77 48
የመምሪያ ሃላፊ ፦ 0902209702
የዞን ማህ/አቀ/የፖሊሰ አገልግሎት ዋ/ክፍል ሃላፊ፦0912955818 ደዉልዉ መረጃ መሰጠት ይችላሉ።
ወንጀልን በጋራ እንከላከል!!!!

The Most Beautiful View Of  27 መድኋኒዓለም | ደሴ መድሀኒዓለም እና አካባቢውመልካም ቀን🥰 AHS Production
05/05/2023

The Most Beautiful View Of
27 መድኋኒዓለም | ደሴ መድሀኒዓለም እና አካባቢው
መልካም ቀን🥰 AHS Production

ወንድሞቻቸውን እንጂ "ጠላቴ" የሚሉትን ዋና ሃይል  ሲገድሉ ቀርቶ ሲያቆስሉ አይተን አናውቅም።  እራስን ማጥፋትና ማዋረድ የአማራ ህዝብ ታሪክና ማንነት እስኪመስል ድረስ ከትናንት እስከ ዛሬ ...
04/27/2023

ወንድሞቻቸውን እንጂ "ጠላቴ" የሚሉትን ዋና ሃይል ሲገድሉ ቀርቶ ሲያቆስሉ አይተን አናውቅም። እራስን ማጥፋትና ማዋረድ የአማራ ህዝብ ታሪክና ማንነት እስኪመስል ድረስ ከትናንት እስከ ዛሬ ድረስ ቤታቸውን በደም በማግማት ላይ ናቸው።

አቶ ግርማ ነብስህ በሰላም ትረፍ።

ግንቦት(1) ልደታን በርዕሰ አድባራት ወገዳማት መንበረ ፓትርያርክ  ተድባበ ማርያም ያክብሩ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ተድባበ የቀደምት ስልጣኔ መነሻ፣ የጥበብ እጆች...
04/25/2023

ግንቦት(1) ልደታን በርዕሰ አድባራት ወገዳማት መንበረ ፓትርያርክ ተድባበ ማርያም ያክብሩ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ተድባበ የቀደምት ስልጣኔ መነሻ፣ የጥበብ እጆች ከፍታ፣ የአስተሳሰብ ልዕልና፣ ዘመን ተሻጋሪ እይታ የሚጎናፀፉበት፣ የታሪክና የቅርስ አምባሳደር፣ የእምነት አምባ ....

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በደቡብ ወሎ ዞን አማሃራ ሣይንት ወረዳ ከዞኑ ርዕሰ ከተማ ደሴ 228 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ከወረዳው ርዕሰ ከተማ አጅባር በስተሰሜን ምስራቅ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ታሪካዊና ጥንታዊ ገዳም ናት፡፡

ርዕሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በ982 ዓ.ዓ./ከክርስቶስ ልደት በፊት 982 ዓመት ላይ የተመሰረተች) ከአክሱም ጽዮን ቀጥላ በኢትዮጵያ 2ኛ የሆነች ጥንታዊት ገዳም ነች፡፡

የመሰረቷት የንግስት ሳባ የልጅ ልጆች፣ የቀዳማዊ ምኒሊክ ልጆች፣ ኢትዮጵያዊያን እና የብሉይ ኪዳን ሌዋዊያን ካህናት ናቸው፡፡

ገዳሟ የተለያዬ ስያሜ ሲኖራት በሊቀ ካህናቱ አዛርያስ አነጋገር ‹‹ተድባበ ጽዮን›› በሌሎች የእስራኤል ካህናት ‹‹ደብረ-ድባብ›› በአክሱም ነገስታት አነጋገር‹‹ተድባበ ማርያም›› በአጼ ገላውድዎስ አነጋገር ‹‹ተድባበ ማርያም ንግስት ሰይፈ ገላውድዎስ የግራኝ እመቤት›› በባህታዊ አባ-ኪዳነ ማርያም አነጋር ደግሞ ‹‹እምዬ ተድባበ ማርያም›› እየተባለች ትጠራለች። ተድባበ የሚለው ቃል ከግዕዝ የተወረሰ ሲሆን ትርጓሜውም ድባብ (ጫፍ)፣ ጉልላት፣ መደምደሚያ፣ ጃንጥላ ማለት ሲሆን የደብሯን ታላቅነትና መልከዓምድሩን ለመግለፅ የተሠጠ ስያሜ ነው።

የኢትዮጵያ የታሪክ እና የቅርስ ጎተራ የሆነችው ተድባበ ማሪያም የወሎ፣ የጎጃምና የጎንደር መገናኛ ልዩ ስፍራ ላይ ስትሆን ከምስራቅ ጎጃም ሁለት እጁነሴ፣ ከደቡብ ጎንደር ስማዳ፣ ከደቡብ ወሎ መቅደላ ወረዳ፣ ከአጅባር ከተማና ቦር ተራራ የሚዋሰን ሲሆን ዙሪያው በጥርብ አለት ታጥሮ 12 ተፈጥሯዊ መግቢያና መውጫ በሮች ያሉት ገዥ መሬት ላይ ነው፡፡ ማራኪ መልክዓ ምድራዊ ውበትን በታደለው አምባ የምትገኘው ተድባበ ማርያም በኢትዮጵያ ታሪክ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው በዋጋ የማይተመኑ እጅግ ውድና ዘመን ተሻጋሪ ቅርሶችም ባለቤት ናት፡፡

ቅድመ ልደተ ክርስቶስ መሥዋዕተ ኦሪት የተሰዋባቸው ሁለት ሀገራት ብቻ ሲሆኑ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ብቻ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ በ፭ ቦታዎች ሲሰዋ እንደነበር ይታወቃል። እነዚህም ብርብር ማርያም፣ ጣና ቂርቆስ፣ መርጡለ ማርያም፣ ተድባበ ማርያምና አክሱም ጽዮን ናቸው።

ዐምሐራ ሳይንት ውስጥ የምትገኘው ተድባበ ማርያም አለቃ በትረያርክ (ፓትርያርክ) ይባላል። የአክሱሙ ንቡረ ዕድ ሲባል የመርጡለ ማርያሙ ደግም ርእሰ ርኡሳን ይባላል። በመርጡለ ማርያም የአስተርእዮ ማርያም ከፍ ባለ ደረጃ ሲከበር በአክሱም ደግሞ ኅዳር ጽዮን። እንደነዚህም ሁሉ በተድባበ ማርያም ግንቦት ልደታ በልዩ ድምቀት ይከበራል። ይኽም በበዓሉ ላይ የቤተ ክህነቱም የቤተ መንግሥቱም ሊቃናት ሰብሰብ ብለው ይገኙም ነበረ።

ተድባበ ማርያም ሲደርሱ ኦሪትና ወንጌል፣ ብሉይና ሐዲስ ወደተረካከቡበት መድረክ መሔድዎን አይርሱ። ኹለቱ ኪዳናት ሰላማዊ ሽግግር ወይም ስምም ቅብብሎሽ ያደረጉባቸው መቃድስ ጥቂቶች ናቸው።

ርእሰ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም የሐዲስ ኪዳን የሥርዓት መነሻ የቅኔ ምንጭ የድጓ ምልክት ነቅ ድጓ ከጠፋ በኋላ በጎ ነገርን በሚያሳስብና በበጎ ሰዎች እያደረም መልካም የሆነውን ሁሉ እንደፈቃዱ የጠፋውን መልሶ የተሰወረውንም ገልጦ በሚያሰራ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ፈቃድና አነሳሺነት እንደገና የድጓን ምልክት በመድረስ ለትወልድ ያሰተላልፉ አዛዢ ጌራንና አዛዢ ዘራጉኤልን ያፈራች ዙሪያዋን በታላላቅ ገዳማት እና አድባራት የተከበበች የአማርኛ ቋንቋ መገኛ እንደሆነች የሚነገርላት የጎንደር የጎጃምና የሸዋ እንዲሁም የወሎ መገናኛ ማዕከል የሆነች ለስነ ልሳን ተመራማሪዎች ትልቅ የቅርስ ስፍራ የሆነችው ርእስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም የታቦር ተራራ የቅኔ መገኛ ሰማንያ ጋሻ መሬት የሸፈነው የቦረና ሳይንት ወረሂመኖ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኝባት ስትሆን ለኢትዮጵያ ታላቅ የታሪክ ማሕደርም ናት፡፡

የኦሪት እመቤቲቱን - ዘመነ ብሉይ ኪዳን
የያሬድ ዜማ ምልክት የተቀረፀባት
ንጉስ ምኒልክ-1ኛ
ንጉስ አብርሃ ወአፅበሃ
ኢዛና ሳይዛና
ዘመነ ብሉይ ኪዳን
ንጉስ ሚካኤል
ልደታ ማርያም
በእስራኤል ነገዶች የተሰየሙ ባለ-12 በሮች

የሀገር ውስጥ እና ውጭ ሀገር ቱሪስቶች እንዲሁም የተዋህዶ ልጆች ግንቦት ልደታን በጥንታዊቷና ታሪካዊቷ ተድባበ ማሪያም ተገኝታችሁ
የአካባቢውን ሀይማኖታዊ፣ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶች በመጎብኘት ትናንታችሁን በመመልከት ዛሬችሁን በመስራት ነጋችሁን ታሳምሩ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ጋብዘናችኋል፡፡

እንግዴ ሆናችሁ እዩብኝ በሞቴ እንጀራ ካረጉት ይበላል ሳይንቴ
እንግዳ ሆናችሁ እዩብኝ በሞቴ እሳት ካደረጉት ይፋጃል ሳይንቴ
12 ነው ተድባበ ማሪያም በሩ የቅኔና ድጓ የአቋቋም መምህሩ
የነገስታት አክሊል የጳጳሳት ክብሩ ሰው ብቻ አይደለም ተባርኳል አገሩ
የአጼ ዮሀንስ የገላውድዎስ የንግስት ዘውድቱ የልብሰ መንግርቱ
ያግዙፍ ቅርሳችን መንበረ ዳዊቱ ይምጡና ይጎብኙት ይዩት ይደሰቱ

ከተድባበ አይቀርም!!!
ደቡብ ወሎ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ

04/12/2023

ይድረስ ነገሩ ላልገባችሁ ‼️

ህወሓት የገመዳቸው የኢትዮጵያን እስራት ያፀኑት ሶስቱ የሰንሰቱ ቀለበቶች

1) የብሄር ክልሎች
2) የብሄር ፓርቲዎች
3) የብሄር ታጣቂዎች

እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ላይ ሁለቱ ቀለበቶች ስለተፈቱ ሶስተኛውም ኢትዮጵያን ብቻውን ጠፍንጎ ማሰር እንዳይችል ሆኗል።

Tesfaye Kebede

በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሱ ፋኖወች ይፋዊ ይቅርታ ጠየቁ—————///—————————-የአማራ ክልል መንግሥት ከዚህ በፊት በግላቸው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በማወያየት ወ...
04/12/2023

በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሱ ፋኖወች ይፋዊ ይቅርታ ጠየቁ
—————///—————————-
የአማራ ክልል መንግሥት ከዚህ በፊት በግላቸው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን በማወያየት ወደ መደበኛ የጸጥታ አደረጃጀት እንዲገቡ ወይም ደግሞ ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል።

በዚህ ጥረቱም በርካታዎች ጥሪውን ተቀብለው ተግባራዊ አድርገዋል። ነገር ግን በቅርቡ በሰሜን ወሎ ዞን አካባቢ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች የመንግሥትን ጥሪ ባለመቀበል ከመከላከያ ጋር ወደ ግጭት የገቡ መሆኑም ይታወሳል።

ሆኖም በቅርቡ የፋኖ አባላቱ ይፋዊ ይቅርታ በመጠየቅ የመንግሥትን የሰላም ጥሪ መቀበላቸውን በማሳወቅ ከክልሉ መንግሥት እና ከመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር ውይይት አድርገው ወደ መደበኛ ህይወት ለመመለስ መስማማታቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ዝርዝር ዜናው እንደደረሰን እናቀርባለን።

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ)

ደሴ ከተማ ‼️ የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 2/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦ 1 ....
04/10/2023

ደሴ ከተማ ‼️
የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 2/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦

1 . በከተማችን በዛሬው ዕለት የፀጥታ እና አለመረጋጋት ችግር ተፈጥሯል። ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘ ፀጥታው ወደነበረበት እስኪመለስ ድረስ ላልተወሰኑ ቀናቶች ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ፤
2 . በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:30 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፤ በተመሳሳይ የሰው እንቅስቃሴም ከምሺቱ 4 ሰዓት በኋላ የተከለከለ ነው።
3 . የፀጥታ ስምሪት ይዞ ከሚንቀሳቀሰው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4 . ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

5 . በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው ።

6 . በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

7 . ተፈቀደለት አካል ውጭ በከተማችን ውስጥ በማንኛውም ቦታ ቀንም ሆነ ሌሊት የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

8 . የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
-የልዩ ኋይል ፣
-የፓሊስ ፣
-የመከላከያ ሠራዊት ፣
-የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ የልዩ ኃይል አመራሮቻችሁ ባዘጋጁላችሁ ማረፊያ እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው

12 . ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

በመጨረሻም የተከበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በከተማችን እየተሰራ ያለው ልማት ለደቂቃም ሊስተጓጎል አይገባም። ህዝባችን ሰላም ፣ ልማት እንደሚፈልግ ጠንቅቀን እንረዳለን። የደሴ ህዝብ ከእንግዳህ በሴራ እየተጎዳ መቀጠል የለበትም። ወጣቶቻችን በሆደ ሰፊነት በትዕግስት በስክነት ነገሮች እንድፈቱ እንደሚፈልጉና ልማቱን ምንም እንቅፋት እንዲፈጠርበት እንደማይፈልጉ ጠንቅቀን እናውቃለን።

መንግስት ህግ ለማስከበር የተደራጀ ኃይል እና ዝግጅት ቢኖረውም ከተማችን ነገሮች በሰከነ መንገድ በውይይት እንደፈቱ ከመፈለግ ታግሰናል። ዋናው ችግር ከሌላ ቦታ በመጡ ኃይሎች አስተባባሪነት እንጅ የከተማችን ህዝብ እንዳልሆነ ህዝባችን ልብ ሊል ይገባል።
ስለሆነም ይህ የተላለፈ ውሳኔ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ህዝባችን ወጣቱ ከጎናችን እንድሆን ጥሪያችን እናስተላልፍ

የደሴ ከተማ አስተዳደር የጸጥታ ኮማንድ ፖስት

Address

California City, CA

Telephone

+12062587281

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Click Dessie posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share