Meznagnia

Meznagnia Celebrating 10 Years.
(9)

Meznagnia(መዝናኛ) Magazine is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.

09/04/2024

ጳግሜን ለህብረት ለበጎ

Mark your calendars! On September 15th, 2024 the Business and Industry Show is where innovation meets opportunity. Wheth...
09/03/2024

Mark your calendars! On September 15th, 2024 the Business and Industry Show is where innovation meets opportunity. Whether you’re a startup or an established business, this is your chance to connect with industry leaders and grow your network. See you there!”

ሸዊት  ወልደ ገብርኤል ትባላለች  ገና በልጅነት እድሜዋ ነበር ወላጅ እናቷን በወሊድ ምክንያት  በሞት ያጣቺው የእናቷን ማጣት የከበዳት ሸዊት ገና የእናቷ ሀዘን ሳይወጣላት በ አምስት አመቷ ...
08/28/2024

ሸዊት ወልደ ገብርኤል ትባላለች ገና በልጅነት እድሜዋ ነበር ወላጅ እናቷን በወሊድ ምክንያት በሞት ያጣቺው የእናቷን ማጣት የከበዳት ሸዊት ገና የእናቷ ሀዘን ሳይወጣላት በ አምስት አመቷ ታናናሽ ወንድሟን እና እህቷን ከ አባቷ ጋር ሆና ወደ ህፃናት ማሳደጊያ ድርጅት አስገብተው ከአባቷ ጋር ሆና ወደ ቤታቸው ተመለሱ ሆኖም የእናቷን የሙት ዓመት ተስካር ለማውጣት ዝግጅት እያደረጉ ድንገት ወድቆ ባለቤቱ ባረፈች በዓመቱ አባቷም በሞት ተለያት።

በዚህ ሸዊት ከነበረችበት የገጠር ከተማ ከ አባቷ የበፊት ባለቤቱ የመኖር ግዴታ ተጣለባት የእንጀራ እናቷም መልካም ሴት ስለነበረች እንደ ልጆቿ ማሳደግ ጀመረች ሆኖም የሸዊት ታላቅ እህት ከዩንቨርስቲ ተምራ ስለተመረቀች እና ስራ አዲስ አበባ ስላገኘች የታላቅ እህቷ ባለቤት ጋር መቀሌ ሆና ትማር ነበር ከጊዜ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመኖር መጡ ሸዊትም አዲስ አበባ እደመጣች የጠፉ ወንድም እና እህቷን ማፈላለግ ጀመረች ።

በዚህ በልጅነቷ አርቲስት የመሆን ፍላጎቷ ታዋቂ ሆና ወንድም እና እህቷን ማግኘት ነበር በዚህም አዲስ አበባ እደመጣች አርቲስት ፍለጋ መንገድ ላይ ወታ ጠፍታለች ወደቤቷ ምትመለስበትን መንገድ ይጠፋባታል በዚህ ሁሉ የህይወት ውጣ ውረድ ወንድሟን የሚያፋልጋት ልጅ ትተዋወቅ እና ወደ ፍቅር ትገባለች በዚህም በትዳር ሆነው ቆንጆ የሚያምር ወንድ ልጅ ወልደዋል።

ከብዙ ፍለጋ በኋላ በአጋጣሚ ዶንኪ ቲዩብ ተቀጥራ መስራት በጀመረችበት ሰዓት የመቄዶንያ የቀጥታ ስርጭት ላይ በህይወቷ የምትጠብቅበትን ቀን የደስታ ዜና ሰማች! ፈረንሳይ ሀገር ወንድም እና እህቷ እደሚኖሩ ተነገራት በዚህም የመገናኘት ተስፋዋ ጨመረ እውነት ከተለያዩ 18ዓመት አመት በኋላ ወንድሟ በፈረንሳይ ሀገር ከሚያሳድነው የማደጎ አባቱ ጋር ወደ ኢትዮጵ ያመጥተው ከሸዊት ጋርሊገናች ችለዋል ።

Source:Donkey Tube

 ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመረጡየአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገቢሳ ኤጀታን (ፕ/ር) በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመ...
08/28/2024

ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመረጡ

የአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገቢሳ ኤጀታን (ፕ/ር) በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ምሁር ሲሆኑ÷ በዚህ ለወገን ጠቃሚ ተግባራቸውም በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተችሯቸዋል፡፡

በተለያየ ጊዜ 17 ከፍተኛ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት ፕሮፌሰሩ÷ በቅርቡ “ኦርደር ኦፍ ግሪፊን እና ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ተሸልመዋል፡፡

አሁን ደግሞ በፑርዱ ዩኒቨርሲቲ የዓመቱ ምርጥ ሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመርጠዋል፡፡

ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ ከ70 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማማከር ከ200 በላይ የምርምር ውጤቶችን ለኅትመት አብቅተዋል፡፡

የሮክፌለር ፋውንዴሽን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዲሁም የአሊያንስ ግሪን ሪቮሉሽን የክብር አባል ለመሆንም በቅተዋል፡፡

ከሮክፌለር፣ ከሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በትብብር የሚሠሩት ተመራማሪው፥ የሣይንስ ካውንስል፣ የሣሣካዎ ግሎባል የቦርድ አባልም ናቸው፡፡

ቀደም ሲልም የ “ወርልድ ፉድ ፕራይዝ” ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ጥገኛ አረምን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ለማዳቀል ለሚሠሩት ምርምርም ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች 5 ሚሊየን ዶላር ያገኙት ምሁሩ÷ በአሳለፍነው ጥቅምት የ “አሜሪካን ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ሽልማትን ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል።
የአሜሪካው ስመጥር ፑርዱ ዩኒቨርሲቲ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ገቢሳ ኤጀታን (ፕ/ር) በአከናወኑት የግብርና ምርምር ሥራ የዓመቱ የሰብል ልማት ተመራማሪ አድርጎ መርጧል፡፡

ገቢሳ ኤጀታ (ፕ/ር) በተለያየ ጊዜ በአካሄዱት ምርምር “ሃይብሪድ” የሆኑ የማሽላ ዘሮችን መፍጠር የቻሉ አንጋፋ ምሁር ሲሆኑ÷ በዚህ ለወገን ጠቃሚ ተግባራቸውም በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ተችሯቸዋል፡፡

በተለያየ ጊዜ 17 ከፍተኛ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት ፕሮፌሰሩ÷ በቅርቡ “ኦርደር ኦፍ ግሪፊን እና ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ተሸልመዋል፡፡

አሁን ደግሞ በፑርዱ ዩኒቨርሲቲ የዓመቱ ምርጥ ሰብል ልማት ተመራማሪ ተብለው ተመርጠዋል፡፡

ከምርምር ሥራቸው በተጨማሪ ከ70 በላይ ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በማማከር ከ200 በላይ የምርምር ውጤቶችን ለኅትመት አብቅተዋል፡፡

የሮክፌለር ፋውንዴሽን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) እንዲሁም የአሊያንስ ግሪን ሪቮሉሽን የክብር አባል ለመሆንም በቅተዋል፡፡

ከሮክፌለር፣ ከሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በትብብር የሚሠሩት ተመራማሪው፥ የሣይንስ ካውንስል፣ የሣሣካዎ ግሎባል የቦርድ አባልም ናቸው፡፡

ቀደም ሲልም የ “ወርልድ ፉድ ፕራይዝ” ሽልማትን ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ጥገኛ አረምን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን ለማዳቀል ለሚሠሩት ምርምርም ከቢል እና ሚሊንዳ ጌትስ ግብረ-ሠናይ ድርጅቶች 5 ሚሊየን ዶላር ያገኙት ምሁሩ÷ በአሳለፍነው ጥቅምት የ “አሜሪካን ብሔራዊ የሣይንስ ሜዳሊያ” ሽልማትን ከፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ተቀብለዋል።

 ቴዲ አፍሮ በካናዳ  ሊሸለም ነው፡፡ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ)  በሙዚቃ ዘርፍ ላበረከተው አሰተዋፅዖ  የዕውቅና ሽልማት ሊበረከትለት ነው።መቀመጫዉን በካናዳ ሀገር፣ በኦንታሪዮ...
08/28/2024

ቴዲ አፍሮ በካናዳ ሊሸለም ነው፡፡

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሙዚቃ ዘርፍ ላበረከተው አሰተዋፅዖ የዕውቅና ሽልማት ሊበረከትለት ነው።

መቀመጫዉን በካናዳ ሀገር፣ በኦንታሪዮ ግዛት፣ በቶሮንቶ ከተማ ያደረገው እና በየአመቱ በተሰማሩባቸው የተለያዮ የስራ እና የሞያ ዘርፎች ስኬታማ የሆነ ተግባር እና ለወገን የሚተርፍ ስራ የሰሩ ኢትዬጵያውያንን አወዳድሮ የሚሸልመው ቢቂላ አዋርድ፣ ዘንድሮ ለ10ኛ ጊዜ የተለያዩ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ያንን እንደሸልም አስታወቀ ።

ቢቂላ አዋርድ በመጭው ሴፕቴምበር 21 ቀን 2024 ዓ.ም በቶሮንቶ ከተማ በሚያካሂደው አመታዊው የሽልማት ስነ ስርዓት ላይ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ለወጣት ኢትዮጵያውያን ታላቅ አርአያ በመሆን በሙዚቃ ዘርፍ ላበረከተው አሰተዋፅዖ የእውቅና ሽልማት ሊበረከትለት መሆኑን ዛሬ ተገለፀ።

በቶሮንቶ የቢቂላ አዋርድ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ተሰማ ሙሉጌታ ሽልማቱን አስመልክተዉ እንደተናገሩት፣ አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሙዚቃ አልፎ ለኢትዮጵያ ወጣቶች በአርዓያነትና ተግቶ በመስራት ዙሪያ ያበረከተዉ ሚና የጎላ እና እዉቅናዉም ትርጉም ያለዉ ነዉ ብለዋል። አክለዉም፣ አርቲስቱ የመድረክ ላይ ስራዎቹ እና የበጎ አድራጎት ክንዉኖቹ፣ ለትውልዱ አርዓያ እንዲሆን አድርጎታል ብለዋል።

በዘንድሮው የቢቂላ አዋርድ ላይ ቴዎድሮስ ካሳሁንን ጨምሮ 15 ግለሰቦች ሲሸለሙ፣ ከእነርሱም መካከል በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ግዙፍ የመኪና ማቆሚያ ንግድ ስራ ላይ የተሰማሩት፣ የ U Street Parking ባለቤቱ አቶ ሔኖክ ተስፋዬ፣ ኢትዮጵያዊ ካናዳዊቷ የሴቶች መብት ተከራካሪ የሆነችው መሰረት ኃይለየሱስ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም እና ሌሎች በትምህርት፣ በጤና፣ በሳይንስ፣ በኪነ ጥበብና በተለያዩ የሙያ መስኮች ለሀገራቸውና ለወገናቸው አስተዋፅዖ ያበረከቱ ግለሰቦች ይሸለማሉ፡ ፡

Source: Daniel Gebremariam
Meznagnia

08/27/2024

ጦቢያ በካልጋሪ!!
እንዳትቀሩ!!

በጦቢያ ጃዝ ዝግጅቱ እያዝናና ጥልቅ ጉዳዬችን የሚዳሰው ፍራሽ አዳሽ (ተስፋሁን ከበደ)/ከ አመቱ ምርጥ ተዋናይት ተሸላሚ አርቲስት መስከረም አበራ እንዲሁም ከጥበብ ባለሙያ ምስራቅ ተረፈ ጋር በካልጋሪ ከተማ ዝግጅታቸውን Sunday, September 15, 2024 ያቀርባሉ::

Location @: White Diamond Conference Centre Calgary Chinatown.

Door open @1:00pm
Show start at 2:30pm

Hosted by: EC Fusion & Lounge
For More Info: +1 (403) 402-5913

Meznagnia(መዝናኛ) Magazine is a digital and print publication that focuses on lifestyle, news, arts, and entertainment in the Ethiopian, Eritrean, and African communities in the United States.
Celebrating 10 Years.

Daniel Gebremariam የካማላ ሀሪስን የፕሬዚዳንት የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዲመራ የተሾመው ትውልደ ከኢትዮጵያዊ  አሜሪካዊው ዮሐንስ አብርሃም።ዮሐንስ አብርሃም የ...
08/26/2024

Daniel Gebremariam የካማላ ሀሪስን የፕሬዚዳንት የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንዲመራ የተሾመው ትውልደ ከኢትዮጵያዊ አሜሪካዊው ዮሐንስ አብርሃም።

ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስን የፕሬዚዳንት የሽግግር ቡድን የዕለት ተዕለት ስራ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጠው ሲሆን የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ሁሴን ኦባማ የቅርብ ሰው መሆኑም ይነገራል።

ዮሐንስ በባራክ ሁሴን ኦባማ አስተዳደር ለስምንት ዓመታት በነጩ ቤተ መንግስት ሰርቷል።

ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቹ በአሜሪካን ሀገር፣ በቨርጂንያ ግዛት፣ ስፕሪንግፊልድ ከተማ ውስጥ ተወልዶ ያደገው የ42 ዓመቱ ጐልማሳ ዮሐንስ፣ ከየል ዩንቨርስቲ በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘ ሲሆን፣ ከሀርቫርድ ዩንቨርስቲ ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪውን በከፍተኛ ማዕረግ ተመርቆ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝቷል፣ በሃርቫርድ ኬኔዲ ትምህርት ቤትም በፖለቲካል ሳይንስ መምህርነትም አገልግሏል።

ይህ ትውልደ ኢትዮጵያዊ በጆ ባይደን አስተዳደር ውስጥም በነጩ ቤተ መንግስት ውስጥ Chief of Staff and Executive Secretary ሆኖ ከፍ ያለ ቦታ ይዞ አገልግሏል።

ዮሐንስ አብርሃም የካማላ ሀሪስን የሽግግር ፕሬዝዳንታዊ ቡድንን የዕለት ተዕለት ስራ የማስተዳደር ሃላፊነት የተሰጠው ሲሆን፣ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዉስጥ ይሰራበት ከነበረዉ የደቡብ ኤስያ ሀገራት የአሜሪካ አንባሳደርነት ኃላፊነቱን ለቆ፣ አዲስ ወደ ተሰጠውና ወደ ተሾመበት የስራ ኃላፊነት በሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚቀላቀል ታውቋል።

ምንጭ፦ ዳንኤል ገብረማርያም
Meznagnia Daniel Gebremariam

ኢትዮጵያዊው ቤዛ ኃይሉ ለማ በድርሰትና በዳይሬክተርነት የተሳተፈበት እና ኢትዮጵያዊ-ካናዳዊቷ የፊልም ፕሮዲዩሰርና  ዳይሬክተር ታማራ ዳዊት ፕሮዲዩስ ያደረገቸው “አልአዛር” የተባለው አዲስ ፊ...
08/26/2024

ኢትዮጵያዊው ቤዛ ኃይሉ ለማ በድርሰትና በዳይሬክተርነት የተሳተፈበት እና ኢትዮጵያዊ-ካናዳዊቷ የፊልም ፕሮዲዩሰርና ዳይሬክተር ታማራ ዳዊት ፕሮዲዩስ ያደረገቸው “አልአዛር” የተባለው አዲስ ፊልም በቶሮንቶ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለዕይታ ሊቀርብ ነው፡፡

ቤዛ ሀይሉ ለማ ድርሰትና ዝግጅት የሆነው ይህ ፊልም በቅርቡ በተከናወነው የካንስ ፊልም ፌስቲቫል ታይቶ በተመልካቾች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት እና አድናቆት አግኝቶ ነበር። ቤዛ ኃይሉ ከዚህ በፊት የሰራችው “ሃገረ ካታንጋ” የተባለው ፊልሙ ከ20 በሚበልጡ አለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተካፍሎ በርከት ያሉ ሽልማቶችን በማግኘት ተቀባይነትን አግንኝቶለት ነበር።

የ“አልአዛር” ፊልም ፕሮዲዩሰር ታማራ ዳዊት ለብዙ ከፍተኛ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች እና ኔትወርኮች ዶኩመንታሪና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ታዘጋጃለች:: በ2020 የሳሊን ማግኘት (Finding Sally)፥ በ2018 ዋሽንግተን ዲሲ Docs in Progress እና በ2015 Talents Durban documentary lab ተሳትፋለች:: የBrown Girls Doc Mafia እና Film Fatales አባል ነች::

የዘንድሮው የቶሮንቶ ፊልም ፌስቲቫል እንዲታዩ ከመረጣቸው ፊልሞች መካከል አንዱ “አልዛር” ሆኗል፡፡ የፌስቲቫሉ አዘጋጆች ፊልሙ የኢትዮጵያን አርሶ አደር ህይወት የሚዳስስ ከመሆኑም በላይ ጠንካራ እምነትን፣ ባህልንና የሰብአዊነትን ስሜት የሚያንፀባርቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ፊልሙን ፕሮዲውስ ያደረገው መቀመጫውን በካናዳ ያደረገው የታምራ ዳዊት “ጎበዝ ሚዲያ” ነው፡፡

“አልአዛር” ፊልም የፊታችን ሀሙስ ፣ ሴፕቴምበር 5 ከጠዋቱ 8:30AM ላይ በቶሮንቶ በሚገኘው የስኮሽያ ባንክ ቴያትር አዳራሽ ለተመልካች ለዕይታ እንዲቀርብ ፕሮግራም ተይዞለታል ። አልአዛር ፊልም በቶሮንቶ ፊልም ፌስቲቫል ከተሳተፈ በኋላ፣ በቶሮንቶ ከተማና በአካባቢዋ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የፊልም ተመልካቾች ለሶስት ተከታታይ ቀናት ለዕይታ እንደሚቀርብም ተገልጿል፡፡

የቶሮንቶ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (TIFF) በዓለም ላይ ካሉ ቀዳሚና ተወዳጅ የፊልም ፌስቲቫሎች ውስጥ የሚጠቀስ ነው። በዚህ ዓመታዊ ልዩ የፊልም ድግስ ላይ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በቀጥታ እስከ 480 ሺህ ሰዎች ይታደሙበታል። በአጠቃላይ በቴሌቪዥን “በላይት ቦክስ” ስርጭትና በሌሎች መንገዶች በርካታ ሚሊዮን ሰዎች ተሳታፊ የሚሆኑበት ነው።

ይህ ተወዳጅና አንጋፋ የፊልም ፌስቲቫል (ድግስ) እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር ከ1776 ጀምሮ ሲዘጋጅ ቆይቷል። ፌስቲቫሉ በቋሚነት ዓለም አቀፍ የፊልም ባህልን በመወከል ተወዳጅና ተናፋቂ ስፍራ መሆን ችሏል። ዋነኛ ራዕይውንም የሰው ልጅ ለዓለማችን ያለውን እይታ በፊልም ማስተካከል የሚለውን ውክልና መውሰድ ምርጫው አድርጓል።

በቶሮንቶ ከተማ፣ በኦንታሪዮ ግዛት በሚገኘው ‹‹ቤል ላይት ቦክስ›› የፌስቲቫሉ መዘጋጃ ማዕከል ፊልምን የተመለከቱ ውይይቶች፣ ትምህርታዊ ዝግጅቶች፣ ጥናቶች እና መሰል አውደ ርእዮች ይካሄዳሉ። በተለይ ኢንዱስትሪውን የሚደግፉ ፕሮጀክቶች በስፍራው ይፋ ከመደረጋቸው ባሻገር አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ይፋ የሚደረጉበት ወርክ ሾፖችም የሚዘጋጁበት ነው።

ይህ ታላቅ ፌስቲቫል ዓለም አቀፍ እውቅናው ጉልህ መሆኑን ለመገንዘብ አንድ ምሳሌ ማንሳት ብቻ በቂ ነው። የአውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2016 ሲሆን በዓመታዊ ድግሱ ላይ 397 ፊልም ከ83 አገራት ተወክለው ለእይታ ቀርበዋል። በወቅቱም ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ የፊልም አፍቃሪያን፣ ባለሙያዎችና እውቅ ሰዎች ታድመውበታል።

የቶሮንቶ ፊልም ፌስቲቫል ድረ ገጽ እየጎበኛችሁ ስለ ሚታዩ ፊልሞች እና ሰዓቱን ማግኘት ትችላላችሁ።

ዳንኤል ገብረማርያም እና ሔኖክ አለማየሁ
Source: Daniel Gebremariam & Henok Alemayehu


Daniel Gebremariam  :በአሜሪካን ሀገር፣ ኦሃዮ ግዛት፣ በኮሎምበስ ከተማ አቅራቢያ ሁለት የ19 አመት ወጣት መንታ ወንድማማቾች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።   እንደ ኦሃዮ ፖሊ...
08/24/2024

Daniel Gebremariam :በአሜሪካን ሀገር፣ ኦሃዮ ግዛት፣ በኮሎምበስ ከተማ አቅራቢያ ሁለት የ19 አመት ወጣት መንታ ወንድማማቾች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ።

እንደ ኦሃዮ ፖሊስ ዘገባ ፣ እሑድ፣ ነሐሴ 17 ቀን 2024፣ ከሌሊቱ 3፡30 PM ሰዓት ላይ፣ የ19 ዓመቱ ሳሙኤል በየነ እያሽከረከረ፣ መንታ ወንድሙን ጆይል በየነን በተሳፋሪነት ከፊት አስቀምጦ፣ መብራት ሳያበሩ፣ በሰዓት 35 ማይል፣ የፍጥነት ገደብ ማሸከርከር በሚገባቸው ጎዳና ላይ፣ ከተፈቀደው ፍጥነት እጥፍ በላይ በሰዓት 75 ማይል፣ በተሳሳተ ተቃራኒ አቅጣጫ፣ ዶጅ፣ ቻርጀር መኪናቸውን እያሸከረከሩ ከፊት ለፊታቸው አቅጣጫውን ጠብቆ ሲመጣ ከነበረ ኒሳን፣ አልቲማ መኪና ጋር ፊት ለፊት ተላትመው በመጋጨታቸው፣ መንታ ወንድማማቾቹ ፣ እንዲሁም ኒሳን መኪናውን ታሽከረክር የነበረችው የ32 ዓመት ወጣት ሴት፣ ከባድ አደጋ ደርሶባቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል ቢወስዱም፣ ህይወታቸው ሊያልፍ መቻሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑን አመልክቷል።

የጎ ፈንድ ሚ ሊንኩን ከዚህ በታች ያገኙታል።
https://www.gofundme.com/f/support-family-after-tragic-loss-of-twins

ሼር አድርጉት።
Daniel Gebremariam
Meznagnia

“ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው ሮናልዶ በዩትዩብ የሰበራቸው አዳደስ ክብረ ወሰኖች?ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ የተከፈተው የዩቱብ ቻናሉ 8 አዳዲስ ክብረ ወሰኖችን ሰ...
08/24/2024

“ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው ሮናልዶ በዩትዩብ የሰበራቸው አዳደስ ክብረ ወሰኖች?

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ የተከፈተው የዩቱብ ቻናሉ 8 አዳዲስ ክብረ ወሰኖችን ሰብሯል ክብረወሰኖች ራሳቸው ያሳድዱኛል” ያለው ፖርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዩትዩብ የሰበራቸው አዳደስ ክብረ ወሰኖች መስበሩን ቀጥሏል።

የ39 አመቱ የእግር ኳስ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የዩትዩብ ገጽ በከፈተ በሰአታት ውስጥ ከፍተኛ ገቢ ማግኝት መጀመሩ ተነገረ፡፡ በሳኡዲ ሊግ ለአል ናስር እየተጫወተ የሚገኝው ሮናልዶ በስፖንሰር ሺፕ እና በፊርማ ክፍያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ገቢ ከሚያገኙ ስፖርተኞች መካከል ቀዳሚው ነው፡፡

በኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገጽ 636 ሚሊየን ተከታዮችን በማግኝት ከአለም ቀዳሚው የሆነው ሮናልዶ ከትላንት በስቲያ በከፈተው የዩትዩብ ገጽም ክብረ ወሰኖችን እየሰባበረ ይገኛል፡፡

“ዩአር” ክርስቲያኖ በሚል ስያሜ የከፈተው ዩትዩብ 90 ደቂቃ ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚሊየን በላይ ተከታዮችን የሰበሰበ ሲሆን በአሁኑ ወቀት 30 ሚሊየን ሰብስክራይበሮችን አግኝቷል፡፡

ከ 4 ደቂቃ ያልበለጡ 19 አጫጭር ቪድዮዎችን የለቀቀው ክርስቲያኖ እስካሁን ከ3.1 እሰከ 24 ሚሊየን ድረስ እያንዳንዱ ቪድዮዎቹ ታይተውለታል፡፡ የዩትዩብ ገጽ ባለቤቶች አንድ ቪድዮ ለሚያገኝው አንድ ሺህ እይታ ከ2 –12 ዶላር ያገኛሉ ዩትዩብ ከማስታወቂያ ክፍያ የሚያገኝውን ገቢ 45 በመቶውን በመውሰድ 55 በመቶውን ለገጹ ባለቤቶች ይሰጣል፡፡

የሮናልዶ ገጽ አጠቃላይ የቪድዮ እይታ በአሁኑ ወቅት ከ120 ሚሊየን በላይ ተሻግሯል፡፡ በሰአታት ውስጥ በከፈተው ገጽ ከፍተኛ ሚሊየን ተከታዮችን ማግኝት የቻለው ሮናልዶ አሁን ላይ በዩትዩብ ከፍተኛ ተከታዮችን በመያዝ ቀዳሚ ከሆነው “ሚስተር ቢስት” ጋር ሊፎካከር እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

የተለያዩ የመዝናኛ እና የውድድር ይዘቶችን በመስራት የሚታወቀው ሚስተር ቢስት 400 ሚሊየን እይታን በማግኝት በወር 5 ሚሊየን ዶላር ከዩትዩብ ይከፈለዋል፡፡
ክርስቲያኖ የዩትዩብ ገጹን ከአለም አቀፍ አድናቂዮቹ ጋር ይበልጥ ለመቀራረብ እንደሚጠቀምበት አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም እስከዛሬ ሰዎች ያላዩትን የግል ህይወቱን ክፍል በገጹ እንደሚያጋራ እና የተለያዩ እንግዶችን በማቅረብ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ማቀዱን ነው የገለጸው፡፡

Nahom Atakilti is an Ethiopian British  bodybuilder, based in London and  running his own body transformation center.He ...
08/21/2024

Nahom Atakilti is an Ethiopian British bodybuilder, based in London and running his own body transformation center.

He wears a traditional Ethiopian cross around his neck most of the time.
nas_

በ10ሺ ለጣልያን  የሚሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የማነብርሃን (የማነ) ክሪፓ::👉🏾የማነብርሃን (የማነ) ክሪፓ (Yeman Crippa) የተወለደው ወሎ ደሴ ነው:: በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወላጆ...
08/21/2024

በ10ሺ ለጣልያን የሚሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊ የማነብርሃን (የማነ) ክሪፓ::

👉🏾የማነብርሃን (የማነ) ክሪፓ (Yeman Crippa) የተወለደው ወሎ ደሴ ነው:: በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወላጆቹን በማጣቱ ምክንያት ከሌሎች ሁለት ወንድሞቹ ጋር ወደ ጣልያን ትሬንቶ በጉዲፈቻነት ያመጡት ጣልያናውያኖቹ ጥንዶች (Roberto and Luisa Crippa) ነበሩ::

👉🏾 Yeman Crippa ዘንድሮ በቶክዮ ኦሎምፒክ ጣልያንን ወክሎ በ10ሺ ሜትር እንደሚወዳደር ይጠበቃል::

👉🏾የማነ በአውሮፓ በርቀቱ አለ የተባለ ተወዳዳሪ ነው:: አውሮፓ የተለያዩ ውድድሮች ወርቅ ተሸልሟል::

👉🏾የማነ በ10 ሺ ምርጥ ሰአት ያስመዘገበው
በዶሀ 27:10.76 (Doha 2019) ነበር::

በ10 ሺ ርቀት ሲፈን ሴት አትሌቶቻችንን እየተፈታተነች እንዳለችው የማነ የመፈታተን እድል ይኖረው ይሆን ? አብረን የምናየው ይሆናል::
....*****.....

Daniel Gebremariam

 Yodit Tewolde, 39, is a criminal defense attorney at her very own firm: The Law Office of Yodit Tewolde PLLC. She has w...
08/21/2024

Yodit Tewolde, 39, is a criminal defense attorney at her very own firm: The Law Office of Yodit Tewolde PLLC. She has worked as a prosecutor in both the adult and juvenile systems at the Dallas County District Attorney’s Office.

She was born in Sudan where her parents were refugees from the Eritrean/Ethiopian war. Her family then moved to the U.S. where she subsequently attended Texas A&M for undergrad and Southern University, an HBCU, for law school.

Yodit Tewolde has appeared on major news networks such as CNN, News One Now and Fox as a legal analyst and commentator. She enjoys serving her community through mentoring. In 2016, she was on the National Bar Association’s list for “40 Under 40 Nation’s Best Advocates.”





የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይቭ ያድርጉ።
👇👇👇👇👇👇
YouTube 👉Meznagnia

Nuhamin Petros obtained her PhD at Karolinska Institute, from National Centre for Su***de Research and Prevention of Men...
08/20/2024

Nuhamin Petros obtained her PhD at Karolinska Institute, from National Centre for Su***de Research and Prevention of Mental Health.

She earned degrees in psychology and biochemistry from the University of Rochester in New York. She finished her master’s degree in epidemiology in Sweden.

Her long-term goals include conducting research on cervical cancer and establishing a national registry and surveillance system for HPV vaccination and cervical cancer in Ethiopia. She wants to investigate the illness further. She is adamant that we have all

She graduated from University of Rochester in New York with degrees in biochemistry and psychology. In Sweden, she completed her epidemiology master’s degree.

Nuhamin has experience managing projects at Karolinska Institutet and the World Psychiatric Association and currently she is a Project Manager at Spinverse.

She works in the health industry, mostly in the field of digital health technologies.

Nuhamin is interested in pursuing research in cervical cancer and in the long run set up a surveillance/central register system for HPV vaccination and cervical cancer in Ethiopia. She is interested in conducting research on the disease.

She firmly think that we all have a responsibility to support our country in any manner we can. She adore her nation and want to contribute to the betterment of the health system in Ethiopia.

 Nardos Temesgen ,MD,  was born in Ethiopia, when she was 17 years old, she immigrated to the United States with her fam...
08/19/2024

Nardos Temesgen ,MD, was born in Ethiopia, when she was 17 years old, she immigrated to the United States with her family, and went on to attend Virginia Commonwealth University for her undergraduate studies. She received her Doctor of Medicine from Wright State University Boonshoft School of Medicine in Ohio and returned to the Washington, DC region to complete her internal medicine residency and cardiology and interventional cardiology fellowships at The George Washington University School of Medicine before joining the interventional cardiology team at MedStar Southern Maryland Hospital in November 2022.

As an interventional cardiologist, Dr. Temesgen specializes in the treatment of heart conditions such as blocked arteries and the repair of structural abnormalities such as heart valve defects and damaged blood vessels using minimally invasive, nonsurgical procedures including transradial catheterization. Dr. Temesgen and her team perform these procedures in the hospital’s dedicated cardiac catheterization lab utilizing advanced imaging technology.

“In interventional cardiology, we’re able to not only open up arterial blockages but also repair defects and even replace leaking or damaged heart valves without the need for an open, invasive surgery,” said Dr. Temesgen. “The benefits to the patients in this community are many.”

To schedule an appointment with Dr. Temesgen, please call 301-877-5677

Source: MediStar

Dr. Misker Kassahun Teka completed her master’s program in public health at the Bloomberg School of Public Health at Joh...
08/19/2024

Dr. Misker Kassahun Teka completed her master’s program in public health at the Bloomberg School of Public Health at Johns Hopkins University with success this year.

She is a general practitioner by profession who is a 2020 graduate of St. Paul’s Hospital Millennium Medical College.
She is also a professional Model who has represented Ethiopia in multiple international beauty contests.

Her notable titles include Miss Supranational Ethiopia 2016, Miss Universe Ethiopia 2017 1st Runner Up, and Miss Africa Beauty Queen 2018. She uses these platforms to educate youth to pursue both academic and extracurricular activities (such as art) and step out of their comfort zone.

She is passionate about health equity, mental health, and Health policy & management. She outshines leadership and management skills with guaranteed communication and advocacy skills. She is also experienced in event planning, digital marketing, and brand representation.

Dr. Misker is the co-founder of GIV Society Ethiopia (served as an Executive director for 2 and half years), a local not-for-profit organization that aims to tackle social challenges via volunteerism. Under her leadership, the organization has provided free healthcare for 3000 underprivileged individuals in 2 years by engaging more than 800 volunteer health professionals.

Her ultimate goal is to help the Ethiopian and African communities with better health services via improved
Healthcare Leadership and Health Policy. She also aspires to share her professional journey with youth all over the world in hopes of enhancing their career development.

Dr. Misker has appeared on multiple media platforms such as national Television, radio, international magazine covers, and international events as a panelist to advocate for mental health, public health, and youth professional development.
For more information and to book her services visit her website www.miskerkassahun.com

ቢንያም ሀሰን የስቴቱ የዓመቱ ምርጥ ተማሪ በሚል ተሸለመ 🥇ቢንያም ከኢትዮጵያዊያን እናትና አባቱ የተወለደው በስደተኛ ካምፕ ውስጥ ነበር፡፡ በሳውዝ ዳኮታ ግዛት በሚገኘው ጄፈርሰን ትምህርት ቤ...
08/18/2024

ቢንያም ሀሰን የስቴቱ የዓመቱ ምርጥ ተማሪ በሚል ተሸለመ 🥇
ቢንያም ከኢትዮጵያዊያን እናትና አባቱ የተወለደው በስደተኛ ካምፕ ውስጥ ነበር፡፡ በሳውዝ ዳኮታ ግዛት በሚገኘው ጄፈርሰን ትምህርት ቤት ዘንድሮ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ የዓመቱ ምርጥ ተማሪ ተብሎ ሽልማት ተቀብሏል፡፡

በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ ያደረገው ንግግር በአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ወላጆችንና የትምህርት ቤቱን ቦርድ አባላት ጭምር ደጋግሞ አስጨብጭቧል፡፡

ቢንያም ወደአሜሪካ ከቤተሰቦቹ ጋር ገብቶ በሳውዝ ዳኮታ ግዛት መኖር የጀመረው እ.ኤ.አ በ2012 የስድስት ዓመት እድሜ ላይ እንዳለ ነበር፡፡ ስድስቱን አመታት ከእናትና አባቱ ጋር በጅቡቲ ስደተኞች ካምፕ አሳልፏል፡፡ ወላጆቹ ከዩኒሴፍ ባገኙት ድጋፍ በመጀመሪያ ስፕሪንግ ፊልድ የገቡ ሲሆን በመቀጠል ወደቴክሳስ ከሄዱ በኋላ በመጨረሻ መቀመጫቸውን በሳውዝ ዳኮታ ለማድረግ ችለዋል፡፡

እናትና አባቱ እንግሊዘኛ መናገር የማይችሉ በመሆናቸው ከልጅነቱ አንስቶ አንዳንድ የወረቀት ስራዎችን ለቤተሰቦቹ የመተርጎም ሀላፊነትም ሊጫንበት ችሏል፡፡ ይህ ደግሞ ‹‹ኖው ዩር ራይትስ›› የተሰኘ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅቱን ከጓደኞቹ ጋር እንዲከፍት ምክንያት ሆኖታል፡፡ ይህ ድርጅት እንደቤተሰቦቹ እንግሊዘኛን መናገርና መስማት የማይችሉ ሰዎች በአሜሪካ ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን የወረቀት ስራዎች በነፃ የሚያከናውን ከመሆኑም በላይ ስለመብቶቻቸው ግንዛቤ የሚያስጨብጥ ነው፡፡

ቢንያም ከልጅነቱ አንስቶ ለወላጆቹ የማስተርጎም ስራ በማከናወኑ አሁን እናትና አባቱ ባለስራ ለመሆን ችለዋል፡፡ እራሱንም በአዳሪ ትምህርት ቤት ለማስገባት የቻለው በዚህ ጥረቱ ነበር፡፡ ዘንድሮ በትምህርት ቤቱ ውስጥ በተከናወነው የክርክር ውድድር ላይ ካሸነፈ በኋላ በግዛት ደረጃ በተከናወነው ውድድር አንደኛ ለመውጣት ችሏል፡፡ እንዲሁም ከክፍሉ ተማሪዎች አንደኛ በመወጣት ሌላ ድል አግኝቷል፡፡ ይህንን መሰል የስኬት ታሪኩን በስፋት ባቀረበበት ንግግር ላይ በአዳራሹ ውስጥ ጭብጨባዎች ተደጋግመው ተሰምተው አድናቆት እንደተቸረው ሚቸል ሪፐብሊክ ዘግቧል፡፡
ቢኒያምንም፣ ቤተሰቡንም እንኳን ደስ ያላችሁ በሏቸው!

Source: Alemayehu

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን በሽታ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን ዓለም አቀፍ የ...
08/16/2024

የዓለም ጤና ድርጅት የዝንጀሮ ፈንጣጣን በሽታ ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀ

የዓለም ጤና ድርጅት በተለያዩ አፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋ ያለውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ሲል አውጇል፡፡

ቫይረሱ በኮንጎ እና በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት እየተስፋፋና ህጻናትና ጎልማሶች በበሽታው እየተያዙ መሆኑም ተሰምቷል፡፡

በአህጉሪቱ ያለው የክትባት መጠን ጥቂት እንደሆነ የዘገበው አፍሪካ ኒውስ ነው።

በዚህ ሣምንት የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከላት (ሲዲሲ አፍሪካ) የዝንጀሮ ፈንጣጣ የህዝብ ጤና ድንገተኛ አደጋ መሆኑንና ከ14 ሺህ በላይ ሰዎች ሲያዙ፤ 524 ሰዎች በዚሁ ምክንያት መሞታቸውን በመግለጽ ዓለም አቀፍ ድጋፍ መጠየቁ ይታወሳል።

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም፥ በሽታው ሁሉንም ሊያሳስብ እንደሚገባ ጠቅሰው፤ ከአፍሪካ አልፎም የበለጠ የመስፋፋት እድሉ በጣም አሳሳቢ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

ሲዲሲ አፍሪካ በፈረንጆቹ 2024 በ13 ሀገራት ውስጥ በሽታው መከሰቱን ገልጾ፥ ቀደም ካለው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በበሽታው የተያዙ ሰዎች 160 በመቶ መጨመሩን አስታውቋል።

በበሽታው ምክንያት የሚከሰተው ሞት ደግሞ በ19 በመቶ ከፍ ማለቱም ነው የተገለጸው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ የአደጋ ጊዜ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲሚ ኦርጋና እንዳሉት፥ ቀደም ሲል በሽታው ባልነበረባቸው ሀገራት እንደ ዩጋንዳ፣ ርዋንዳ፣ ብሩንዲ እና ኬንያ ባሉ ሀገራት መከሰቱ ተገልጿል።

በፈረንጆቹ 2022 በሽታው ሲከሰት ከ70 በላይ ሀገራትን ሲያጠቃ ከ1 በመቶ ያነሱ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘገባው አስታውሷል።

Olympic medallist Yared Nuguse thanks Taylor Swift after podium finish at the Paris OlympicsYared Nuguse, who secured a ...
08/15/2024

Olympic medallist Yared Nuguse thanks Taylor Swift after podium finish at the Paris Olympics

Yared Nuguse, who secured a podium finish at the Paris Olympics, surprised fans by thanking pop superstar Taylor Swift during his post-race interview. The American middle-distance runner, known for his speed and determination, credited Swift’s music for helping him stay focused and motivated throughout his training and competition. Nuguse revealed that listening to Swift’s songs had become a pre-race ritual, boosting his morale before crucial events. The unexpected shoutout quickly gained attention on social media, with fans of both the athlete and the singer celebrating the unique connection between music and athletic achievement.


ሄቨንሊ ሪል ስቴት ከኒው ኤራ ኢቲ ትሬዲንግ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ታዋቂ ከሆኑት ከ FASTPAY LLC እና ኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኃ.የተ.ሽ.ማ ጋር የ...
08/14/2024

ሄቨንሊ ሪል ስቴት ከኒው ኤራ ኢቲ ትሬዲንግ ባለአንድ አባል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጋር በመተባበር ታዋቂ ከሆኑት ከ FASTPAY LLC እና ኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኃ.የተ.ሽ.ማ ጋር የመግባቢያ ስምምነት አድርገዋል።

እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2024 በቤተሳይዳ፣ ሜሪላንድ፣ ኒው ኤራ ኢቲ ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ ከሆኑት ከወይዘሪት ዮዲት ጥበቡ ከFASTPAY LLC ማኔጂንግ ፓርትነር አቶ ፍፁም መርዳሳ እና በኢትዮ ሌጋል ሺልድ ማኔጂንግ ፓርትነር አቶ ቴዎድሮስ ፍቃዱ ይህንን የስምምነት ፊርማ አድርገዋል። ስምምነቱ በጫካ ሃውሲንግ ፕሮጀክት ቤት ገዥዎች ሁሉን አቀፍ የህግ አገልግሎት በቅናሽ ዋጋ ይሰጣል።

በኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኃ.የተ.ሽ.ማ የኢትዮጵያን ዲያስፖራ ማህበረሰብ ለማገልገል ጠንካራ ቁርጠኝነት ያለው ሲሆን በሪል ስቴት ግብይት ወቅት የህግ ተግዳሮቶችን የሚያጋጥሙትን የቤት ገዢዎች ችግር ይቀርፋል። በኢትዮ ሌጋል ሺልድ ኃ.የተ.ሽ.ማ የኮንትራት ግምገማ፣ የባለቤትነት መብት ፍለጋ፣ የፋይናንስ ድጋፍ እና አለመግባባቶችን መፍታትን ጨምሮ ጠቃሚ አገልግሎቶችን ይሰጣል። ይህ ትብብር በሪል እስቴት ግብይቶች ውስጥ የጋራ እምነት ጉዳዮችን እና የህግ ተግዳሮቶችን ይፈታል፣ ይህም ለቤት ገዢዎች ቀላል ሂደትን ያረጋግጣል።

በሲልቨር ስፕሪንግ፣ አሜሪካ የሚገኘው FASTPAY LLC፣ ለክፍያ ሥርዓቶች የቴክኖሎጂ መፍትሄዎች ግንባር ቀደም አቅራቢ ነው። ኩባንያው ለአለም አቀፍ የገንዘብ ልውውጥ አገልግሎት የተሰራ ልዩ የገንዘብ ማስተላለፊያ ሶፍትዌር ፍቃድ ይዟል. በዚህ አጋርነት፣ FASTPAY የሐዋላ አገልግሎትን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን ይህም ለተጠቃሚዎች የበለጠ ወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ በማድረግ ቤት ገዥዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ተጠቃሚ ያደርጋል።

"Strategic Collaboration Enhances Legal and Financial Services for Home Buyers"
Heavenly Real Estate, in partnership with New Era Et Trading, is delighted to announce the signing of a Memorandum of Understanding with FASTPAY LLC and Ethio Legal Shield LLP, a distinguished Ethiopian law firm.

On August 9, 2024, in Bethesda, Maryland, Ms. Yodit Tibebu, CEO of New Era Et Trading, Mr. Tewodros Fikadu, Managing Partner of Ethio Legal Shield LLP, and Mr. Fitsum Merdassa, Managing Partner of FASTPAY LLC, formalized this strategic collaboration. The agreement is set to provide home buyers at the Chaka Project with access to comprehensive legal services at discounted rates.

FASTPAY LLC, based in Silver Spring, MD, USA, is a leader in payment system technologies, specializing in international remittance services through its licensed software. This partnership aims to enhance the efficiency and affordability of remittances for users worldwide, including homebuyers, who will benefit from more streamlined and cost-effective transactions.

Ethio Legal Shield, known for its strong dedication to serving the Ethiopian diaspora, is committed to addressing the legal challenges often encountered by home buyers in real estate transactions. Their services, including contract review, title search, financing assistance, and dispute resolution, will play a crucial role in overcoming trust issues and ensuring a smoother, more secure process for home buyers.
Heavenly Real Estate, in partnership with New Era Et Trading, is delighted to announce the signing of a Memorandum of Understanding with FASTPAY LLC and Ethio Legal Shield LLP, a distinguished Ethiopian law firm.

On August 9, 2024, in Bethesda, Maryland, Ms. Yodit Tibebu, CEO of New Era Et Trading, Mr. Tewodros Fikadu, Managing Partner of Ethio Legal Shield LLP, and Mr. Fitsum Merdassa, Managing Partner of FASTPAY LLC, formalized this strategic collaboration. The agreement is set to provide home buyers at the Chaka Project with access to comprehensive legal services at discounted rates.

FASTPAY LLC, based in Silver Spring, MD, USA, is a leader in payment system technologies, specializing in international remittance services through its licensed software. This partnership aims to enhance the efficiency and affordability of remittances for users worldwide, including homebuyers, who will benefit from more streamlined and cost-effective transactions.

Ethio Legal Shield, known for its strong dedication to serving the Ethiopian diaspora, is committed to addressing the legal challenges often encountered by home buyers in real estate transactions. Their services, including contract review, title search, financing assistance, and dispute resolution, will play a crucial role in overcoming trust issues and ensuring a smoother, more secure process for home buyers.
Heavenly Real Estate, in partnership with New Era Et Trading, is delighted to announce the signing of a Memorandum of Understanding with FASTPAY LLC and Ethio Legal Shield LLP, a distinguished Ethiopian law firm.

Ashenda, also known as “Maria”, “Aini Wari”, and “Shadiye” is a cultural festival and cerebration that takes place in Ti...
08/14/2024

Ashenda, also known as “Maria”, “Aini Wari”, and “Shadiye” is a cultural festival and cerebration that takes place in Tigray, Amhara and Agew, Ethiopia. It is primarily celebrated by young girls and women. Ashenda is held annually in the month of August, lasting for approximately one week.

The festival is a joyful occasion filled with music, dancing and traditional attire. Every year young girls eagerly await the great day that dawns Ashenda, the colorful festival. Young girls, especially teenagers go euphoric on this day because it is their freedom day, that they are given a green light to go out to the streets to sing and dance with friends and peers for a week or so.

During Ashenda women come together in their communities, wearing colorful traditional dresses, jewelry, and hairstyles. They sing and dance in groups, forming circles and moving in a coordinated and rhythmic manner. Ashenda is not only
a celebratory event but also a time for socializing, reuniting with friends and family, and showcasing the cultural heritage. It is a significant occasion that promotes unity, pride and cultural preservation.

Happy Ashenda.
Photo:: Working on her magazine that prints her culture and customs alongside Ashenda Ambasadoor . Please message her directly to obtain a copy of the magazine.

መረጃ አዘል ጥያቄአሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ትላንት በቤተመንግሥት በተካኼደ ሥነሥርዓት የተሰጠውን የ2 ሚልየን ብር ሽልማት አነሰኝ ብቻ ሳይሆን “ይህ ለእኔ ስድብ ነው” በማለት መመለሱ ተሰምቷል።...
08/14/2024

መረጃ አዘል ጥያቄ

አሰልጣኝ ገመዶ ደደፎ ትላንት በቤተመንግሥት በተካኼደ ሥነሥርዓት የተሰጠውን የ2 ሚልየን ብር ሽልማት አነሰኝ ብቻ ሳይሆን “ይህ ለእኔ ስድብ ነው” በማለት መመለሱ ተሰምቷል።

#ጥያቄ
የአሰልጣኙ ውሳኔ ላይ አስተያየትዎ ምንድነው?

(ጨዋነት የጎደላቸው አስተያየቶች አይስተናገዱም)

የዛሬ 12 ዓመት በ2012 በተካሄደው በLondon Olompics የ1500ሜ. የሴቶች ፍፃሜ ውድድር 5ኛ በመውጣት የጨረሰችው አበባ አረጋዊ 3ተኛ እና 4ተኛ ወጥተው የነበሩ ሁለት አትሌቶች ው...
08/13/2024

የዛሬ 12 ዓመት በ2012 በተካሄደው በLondon Olompics የ1500ሜ. የሴቶች ፍፃሜ ውድድር 5ኛ በመውጣት የጨረሰችው አበባ አረጋዊ 3ተኛ እና 4ተኛ ወጥተው የነበሩ ሁለት አትሌቶች ውጤቶቻቸው በተለያዩ ምክንያቶች ስለተሰረዘ ከ12 ዓመት በኋላ ውጤቷ ተከልሶ ወደ 3ኛ አድጎ የነሐስ ሜዳልያ በትላንትናው ዕለት በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ከተማ(፣ የፓሪስ ኦሎምፒክ 2024 የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ፣ በስታድ ዲፍራንስ አቅራቢያ በሚገኘው እና ከኤፌል ታወር ትይዩ በሆነው ፣ቻምፒዮንስ ፓርክ) ላይ ተበርክቶላታል 💪 🇪🇹 !!!

የ2012ቱን ሩጫ ውድድር ከዚህ በታች የYoutube ሊንኩን አያይዤላቿለሁ😊!



“PARIS, FRANCE - AUGUST 09, 2024:
Abeba Aregawi (አበባ አረጋዊ)of Ethiopia is awarded the bronze medal for 1500 meter dash from the 2012 London Olympics during a medal reallocation ceremony on day fourteen of the Olympic Games Paris 2024 at Champions Park on August 09, 2024 in Paris, France.”

Champions Park - Olympic Games Paris 9/8/2024: Day 14

(Photo by Pascal Le Segretain/Getty Images)

https://youtu.be/lWzqfiWRE9Q?si=P5TkYXaAARtRipIV

የዚህ የሜዳል reallocation official ዘገባ ምንጭ:-
https://olympics.com/athlete365/news/gamestime/ten-olympians-to-receive-reallocated-olympic-medals-at-champions-park-during-olympic-games-paris-2024-x4005

በእነዛ ሽርፍራፊ ሰከንዶች ሰቴፈን ከሪ የአሜሪካ ዝነኛ የቅርጫት ኳስ ቡድንን ከፓሪስ ኦሎምፒያድ መድረክ ታደገ ። ጠንካራው የሰርቢያ ባስኬት ቦል ቡድን የNBA ኮኮቦቹን በላቀ ብቃት ተፋጠጠ ...
08/09/2024

በእነዛ ሽርፍራፊ ሰከንዶች ሰቴፈን ከሪ የአሜሪካ ዝነኛ የቅርጫት ኳስ ቡድንን ከፓሪስ ኦሎምፒያድ መድረክ ታደገ ። ጠንካራው የሰርቢያ ባስኬት ቦል ቡድን የNBA ኮኮቦቹን በላቀ ብቃት ተፋጠጠ ። የኖቫክ ጆኮቪች የድል መንፈስ የተጠናወታቸው የሰርብያ ኮኮቦች ለወርቅ ሜዳሊያ ፍፃሜ ለመድረስም በታላቅ ብቃት ከጫፍ ደረሱ ።

በእነዛ ሽርፍራፊ ሰከንዶች አሜሪካ ልትወድቅ ? የብዙዎች ጥያቄ ...??? 16 ግዜ የኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያውን በኦሎምፒክ ታሪክ ያሸነፈው የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ጋላክቲኮ ስብስብ ግን በ4ኛው ዙር ሞቶ ተነሳ ። በአጠቃላይ 95 ለ91 በሆነ ውጤት ድልም ነሳ ።

መልከኛው ተወዳጅ የንስር ዐይን ያለው በራሪው ኮኮብ ስቴፈን ከሪ ብቻውን 36 ቅርጫቶችን ማስቆጠር ተዓምር አሳየ ። አሜሪካ በ3ኛው ዙር በሰርቢያ 76 ለ61 ከመመራት ተነስታ በፍፃሜው ራውንድ 95 ለ91 ድምር ውጤት ስትረታ ለብረን ጀምስን ጨምሮ ኬቨን ዱራንት የመሣሰሉ ኮኮቦች የባስኬት ኮርቱ ተጋድሎ አስደናቂ ነበር ። በምርጡ የsemi final የኦሎምፒክ ጨዋታ የጎልደን ስቴት ዋሪየርሱ ንጉስ ስቴፈን ከሪ ደግሞ የጨዋታው top of the match !!! THE CHEF | Stephen Curry ሀገሩ አሜሪካንን ታደገ ። ቤጂንግ ለንደን ሪዬ ቶኪዬ ባለፉት 4 ተከታታይ ኦሎምፒኮች የወርቅ ሜዳሊያውን በተከታታይ ያሸነፉት የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ኮኮቦች ለአምስተኛ ተከታታይ ድላቸው በፍፃሜው ጀርመንን ረታ ፍፃሜ ከደረሰችው የፈረንሳይ ባስኬት ቦል ቡድን ነገ ቅዳሜ ምሽት 5:30 ላይ ይፋጠጣሉ ። የማይክል ጆርዳን ሀገር አሜሪካ በኦሎምፒክ ታሪክ በቅርጫት ኳስ ዘመን ተሻጋሪ ድንቅ ቡድኖቿ ለ17ኛ ግዜ የወርቅ ሜዳሊያውን ለማሸነፍ ከzizu የለብሉ የቅርጫት ኳስ ዌንባኒያማ የመሳሰሉ ሎጋዎች ከያዘው የፈረንሣይ ባስኬት ቦል ጠንካራ ቡድን በቤሪሲ አሬና ትፋለማለች ።

ፈረንሳይ በእግር ኳስም በመድፉ ንጉስ ቲየሪ ዳንኤል ኦንሪ እየተመራች ዛሬ ምሽት 2: 00 ከስፔን ለኦሎምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ትጫወታለች ። ትናንት የሃኪሚ ሀገር ሞሮኮ ግብፅን 6ለ0 ረምርማ የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆናለች ።

Daniel Gebremariam Meznagnia

ለስዊዘርላንድ የምትሮጠው የ27 ዓመቷ ወጣት ተወልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄለን በቀለ ናት።በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የሴቶች 10,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በነገው እለት ይካሄዳል ። ውድድሩን ያሸ...
08/08/2024

ለስዊዘርላንድ የምትሮጠው የ27 ዓመቷ ወጣት ተወልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄለን በቀለ ናት።

በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ የሴቶች 10,000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር በነገው እለት ይካሄዳል ።

ውድድሩን ያሸንፋሉ ተብለው ቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አትሌቶች መካከል አንዷ ለስዊዘርላንድ የምትሮጠው የ27 ዓመቷ ወጣት ተወልደ ኢትዮጵያዊቷ ሄለን በቀለ ናት።

ሄለን በቀለ በዘንድሮው የፓሪስ ኦሎምፒክ ከሚወዳደሩ የማራቶን አትሌቶች መካከል አንዷ ናት። ይሁንና ኢትዮጵያን አትወክልም፤ ስዊዘርላንድን እንጂ።

ሄለን ጥሩ ሰዓት ካላቸው አትሌቶች መካከል አንዷ ናት። እንደ IAAF መረጃ ከሆነ ለሲውዘር ላንድ ለመሮጥ ፍቃድ ያገኘችው ከ4 ወር በፊት መጋቢት ላይ ነው። ወደ ሲውዘርላንድ ያመራችው ደግሞ በ2008 ዓ.ም ላይ ነበር።

በአውሮፓ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይም ጥሩ ውጤት እያመጣች ያለችው ሄለን ፥ ዘንድሮ በርሊን ማራቶን 2:19:44 የገባችበት ሰዓት የግል ምርጧ ነው።
ለሲዊዘርላንድ ለመሮጥ የተስማማችው ዘንድሮ ከ4 ወር በፊት መጋቢት ላይ መሆኑን አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌደሬሽን ከድረገፅ ያመለክታል።

#.meznagnia

Thank you!! 80,000 Followers.
08/08/2024

Thank you!! 80,000 Followers.

“ያ ሌላ :ይሄ ሌላ” የሚሉት የቼክ ሪፐብሊክ የቴኒስ ተወዳዳሪዎች በፓሪስ ኦሎምፒክካትሪና ሲንኮቫ እና ቶማስ ማችክ ለአራት አመታቶች በፍቅር የተጣመሩ ጥንዶች ነበሩ: ሆኖም ግን ጥምረታቸው አ...
08/08/2024

“ያ ሌላ :ይሄ ሌላ” የሚሉት የቼክ ሪፐብሊክ የቴኒስ ተወዳዳሪዎች በፓሪስ ኦሎምፒክ

ካትሪና ሲንኮቫ እና ቶማስ ማችክ ለአራት አመታቶች በፍቅር የተጣመሩ ጥንዶች ነበሩ: ሆኖም ግን ጥምረታቸው አልተሳካምና ተለያይተው የራሳቸውን መንገድ ሄዱ

ሆኖም ግን የፓሪሲ ኦሎምፒክ እነዚህን ጥንዶች በጥምር የሜዳ ቴኒስ ውድድር ላይ በጋራ ተወዳድረው ተጋጣሚዎቻቸውን በመርታት ለራሳቸው እና ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳሊያ አምጥተዋል

“እንዴት ይህንን ማሳካት ቻላችሁ: በፍቅር ተለያይታችሁ አንድ ላይ እንዲህ አይነት ስኬት ማስመዝገብ እንዴት ቻላችሁ?”

ጥንዶቹ ሲመልሱ

👇🏾

“ያ ሌላ : ይሄ ሌላ” ይላሉ

❤️🙌🏼


#2024

ዶ/ር ናዳ ሃፌዝ ፡ ትባላለች ።  የህክምና ትምህርቷን በካይሮ በሚገኝ የህክምና ዩኒቨርስቲ ጨርሳ በሙያዋ ታገለግላለች ።የ26 አመቷ  ናዳ ሀፌዝ ይህ ብቻ አይደለችም ። ስፖርተኛም ናት ፡ ገ...
08/08/2024

ዶ/ር ናዳ ሃፌዝ ፡ ትባላለች ። የህክምና ትምህርቷን በካይሮ በሚገኝ የህክምና ዩኒቨርስቲ ጨርሳ በሙያዋ ታገለግላለች ።

የ26 አመቷ ናዳ ሀፌዝ ይህ ብቻ አይደለችም ። ስፖርተኛም ናት ፡ ገና የ11 አመት ልጅ እያለች ጀምሮ በምትጫወተው የሰይፍ ፍልሚያ ፕሮፌሽናል ሆና ፡ ሀገሯን ግብፅን ወክላ በሶስት ኦሎምፒክ ተካፍላለች ።......
እየተካሄደ በሚገኘው የፓሪሱ ኦሎምፒክ ላይም እንደተለመደው ሀገሯን ወክላ ለ16 ዙሮች ከተለያዩ ሀገራት ተወዳዳሪዎች ጋር በሰይፍ ስትፋለም ቆይታለች ።.....
ታዲያ ይህችን ጎበዝ ሴት ከሌሎች ተወዳዳሪዎች ምን ይለያታል ከተባለ ። ይህች ስለት የማይቆርጠው ሙሉ ልብስ እና ፊቷን የሚሸፍን የብረት ማስክ ለብሳ ሰይፏን በፍጥነት እየሰነዘረችና እየመከተች ትወዳደር የነበረው ፡ ስፖርተኛ የሰባት ወር እርጉዝ ሆና መሆኑ ነው ። በዚህ ሁኔታ እያለች ተወዳድራም እውቋን አሜሪካዊት የሰይፍ ተፋላሚ Elizabeth Tartakovsky ንም ጭምር በማሸነፍ እስከ 16 ኛ ዙር መድረስ ችላ ነበር ። ....
ዶ/ር ናዳ ሀፌዝ ፡ ከኦሎምፒክ መንደር ሆና ባስተላለፈችው መልእክትም. .. “ እኔና በሆዴ ያለው ልጃችን ፡ በኦሎምፒክ መድረክ ለሀገራችን የቻልነው ለመስራት ሞክረናል ። እናም የመጀመሪያ ልጃችንን እርጉዝ ሆኜ በዚህ ውድድር እንድሳተፍ ለፈቀደልኝ ባለቤቴ ምስጋና አቀርባለሁ ስትል ተናግራለች ።....

#2024

Address

50 Pickitt
Alexandria, VA
22312

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Meznagnia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Meznagnia:

Videos

Share


Other Media/News Companies in Alexandria

Show All