#እስኪ_በዚህ_እድሜ_ደረጃ_ወደታች_ወርዶ_በህፃናት_አእምሮ_ዉስጥ_ያለውን_ቃል_ማንሊበርዘው_ይችላል ?
ቱርጉሙን_ኢሀው ከዚህ በታች⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከኾነች እሳት ጠብቁ፡፡
በእርሷ ላይ ጨካኞች፣ ኀይለኞች የኾኑ መላእክት አልሉ፡፡
አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም፡፡
የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ፡፡
እላንተ የካዳችሁ ሆይ! ዛሬ አታመካኙ፡፡
የምትመነዱት ያንን ትሠሩት የነበራችሁትን ብቻ ነው (ይባላሉ)፡፡
[አት-ታሕሪም 6-7]
#እንዲህ_በህፃናት_አእምሮ_ተቀርፆ_እየተነበበ_እንዴት_ይበረዝ
ኑሕንም ከዚያ በፊት (ጌታውን) በጠራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ለእርሱም (ጥሪውን) ተቀበልነው፡፡
እርሱንም ቤተሰቦቹንም ከከባድ ጭንቅ አዳን፡፡
ከነዚያም በታምራቶቻችን ከአስተባበሉት ሕዝቦች (ተንኮል) ጠበቅነው፡፡ እነሱ ክፉ ሕዝቦች አመጸኞች ነበሩና፡፡
ሁሉንም አሰጠምናቸውም፡፡
ዳውድንና ሱለይማንንም በአዝመራው ነገር በሚፈርዱ ጊዜ የሕዝቦቹ ፍየሎች ሌሊት በርሱ ውስጥ በተሰማሩ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
ፍርዳቸውንም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡
ለሱለይማንም (ትክክለኛይቱን ፍርድ) አሳወቅናት፡፡
ለሁሉም ጥበብንና ዕውቀትን ሰጠን፡፡
ተራራዎችን ከዳውድ ጋር የሚያወድሱ ሲኾኑ ገራን፡፡
አእዋፍንም (እንደዚሁ ገራን)፡፡
ሠሪዎችም ነበርን፡፡
የብረት ልብስንም ሥራ ለእናንተ ከጦራችሁ ትጠብቃችሁ ዘንድ አስተማርነው፡፡
እናንተ አመስጋኞች ናችሁን
ለሱለይማንም ነፋስን በኀይል የምትነፍስ በትዕዛዙ ወደዚያች በእርሷ ውስጥ በረከትን ወደ አደረግንባት ምድር (ወደ ሻም) የምትፈስ ስትኾን (ገራንለት)፡፡
በነገሩ ሁሉም ዐዋቂዎች ነበርን፡፡
ከሰይጣናትም ለእርሱ (ሉልን ለማውጣት) የሚጠልሙንና ከዚያም ሌላ ያለን ሥራ የሚሠሩን (ገራንለት)፡፡
ለእነሱም ተጠባባቂዎች ነበርን፡፡
አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ
«(እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡
«ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡
«በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡
«ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡
{الشعراء ٧٨-٨١}
(ከሓዲዎች) አይመለከቱምን? ወደ ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
ወደ ሰማይም እንዴት ከፍ እንደ ተደረገች!
ወደ ተራራዎችም እንዴት እንደ ተቸከሉ!
ወደ ምድርም እንዴእንዴት እንደተዘረጋች (አይመለከቱምን?)
[لغاشية: ١٧-٢٠]
የደጋኑን ወጣት ሑሴን አሕመድ ድምፅ አዳምጡልኝ