Ashruka አሽሩካ

Ashruka አሽሩካ Activism 💚💛❤️✊
(18)

አሸንድየ በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሰንበት ተማሪዎች🙏🏽❤️ለአሸንድየ ተጨዋቾች ተምሳሌትና የድንግልናቸው አርአያ የሚያደርጓት ድንግል ማርያም አካላዊ ሥጋዋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለሱ...
24/08/2024

አሸንድየ በዓል በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ሰንበት ተማሪዎች🙏🏽❤️

ለአሸንድየ ተጨዋቾች ተምሳሌትና የድንግልናቸው አርአያ የሚያደርጓት ድንግል ማርያም አካላዊ ሥጋዋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለሱን፤ እንደዚሁም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር ከነበረበት መነሣቱን ምክንያት በማ ድረግ‹‹የአሸንድየ በዓል በልጃገረዶች ዘንድ ተወዳጅ የኾነው በሔዋን ምክንያት የተዘጋው ገነት በእመቤታችን አማካኝነት በመከፈቱ ነው።”::

እመቤታችን መመኪያቸው ስለ ኾነች ልጃገረዶች በዓሉን በደስታ ያከብሩታል።

እመቤታችን በነሐሴ ፲፮ ቀን በቅዱሳን መላእክት ሽብሸባ፣ ዕልልታና ዝማሬ ታጅባ ከምድር ወደ ሰማይ ስታርግ ሐዋርያት በታላቅ ደስታ ይመለከቱ፣ ይደነቁም ነበር፡፡

ደናግልም ከቅዱሳን መላእክት ከተመለከቱት ሥርዓት በመነሣት ነጫጭ ልብሶችን ለብሰው፣ አምረውና አጊጠው፣ ረጃጅምና ለምለም ቅጠል በወገባቸው አሥረው እንደ መላእክቱ አክናፍ ወገባቸውን ከግራ ወደ ቀኝ እያመላለሱ፣እያዘዋወሩና እያሸበሸቡ፣ በአንደበታቸው እየዘመሩና በእጆቻቸው እያጨበጨቡ በአንድነት ተሰባሰባስበው በፍቅርና በሐሴት የወቅቱ መታሰቢያ የኾነውን የአሸንድየ በዓል ያከብራሉ ፡፡

እናቶችና እኅቶች በዐደባባይ ወጥተው የድንግል ማርያምን ትንሣኤና ዕርገት እንደ ነጻነታቸው ቀን በመቍጠር ከበሮ አዘጋጅተው ‹‹አሸንድዬ›› የተባለውን ቄጠማ በወገባቸው ታጥቀው ምስጋና በማቅረብ በዓሉን ይዘክራሉ፡፡

በአጠቃላይ የአሸንድየ ላስታ ላሊበላ ጨዋታ የፍልሰታ በዓል መከበር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በምእመኑ ዘንድ ለበርካታ ዓመታት እየተከበረ የኖረ ሃይማኖታዊ ትውፊት የያዘ በዓል ነው፡፡

Source: Lalibela

አየር መንገዱን አትጠቀሙ ❗️❗️❗️የራሱ ህዝብ ንጹሀን የሚገደሉበትን ጦር መሳርያ የሚያመላልስ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አትጠቀሙ:: የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቺካጎ ኮንቬንሽን እና ሌሎች ...
24/08/2024

አየር መንገዱን አትጠቀሙ ❗️❗️❗️

የራሱ ህዝብ ንጹሀን የሚገደሉበትን ጦር መሳርያ የሚያመላልስ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አትጠቀሙ::

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቺካጎ ኮንቬንሽን እና ሌሎች የአቭዬሽን ህጎችን በመጣስ በህዝብ ማመላለሻ አውሮፕላን ወታደሮችን እና የጦር መሳርያዎችን ቀድሞውን ወደ ትግራይ አሁን ደግሞ ወደ አማራ እንዳጏጏዘ መረጃዎች ያሳያሉ::

ይህን ግዙፍ ኢትዮጵያውያን የምንኮራበት የአፍሪካ ኩራት ጭምር የሆነውን አየር መንገድ የብልጽግናው አብይ አህመድ ገዳይ ስርአት ለስልጣን ማራዘምያ እየተጠቀመበት ይገኛል::

በደል የፈጸሙት በወንጀል እንኪጠየቁ እና አየር መንገዱም ይህን ጣልቃ ገብነት እስኪያቆም ሀገር ወዳድ ከሆኑ የኢትዮጵያ አየር መንገድን አይጠቀሙ::

Boycott Ethiopian airlines ❗️
Ethiopian Airlines

አሸንድዬ የአማራ ባህል በኢትዮጵያ💚💛❤️👌🏾እንደየአከቢው (ወሎ ሸዋ ጎጃም ጎንደር) ሻደይ ሶለል እንግጫ ነቀላ የሚሉ መጠሪያዎችም አሉት:: ከነሐሴ ፍልሰታ ጾም ጋር ተያይዞ ሀይማኖታዊ እና ባ...
24/08/2024

አሸንድዬ የአማራ ባህል በኢትዮጵያ💚💛❤️👌🏾

እንደየአከቢው (ወሎ ሸዋ ጎጃም ጎንደር) ሻደይ ሶለል እንግጫ ነቀላ የሚሉ መጠሪያዎችም አሉት:: ከነሐሴ ፍልሰታ ጾም ጋር ተያይዞ ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ ለዘመናት ሲከበር የኖረ ቱባ ባህል ነው:: በላሊበላም በታላቅ ድምቀት የሚከበር በአል ነው::

በአሉ በአዲስ አበባ እና ጦርነት ባላየለባቸው የአማራ ክልል ከተሞች እንዲሁም ከሀገር ውጪ በሚገኙ የአማራ ልጆች እና በሌሎችም ኢትዮጵያውያን እየተከበረ ይገኛል::

Ashendye Amhara culture know as also Shadey or Solel in different parts of the the Amhara community in Ethiopia.

Even if large parts of Amhara region under attack. Ethiopians in Addis Abeba and some parts of Amhara region celebrated Ashendye wishing peace to resume soon.

The Amhara people in Ethiopia is the second largest population in Ethiopia.
…..*****…..

24/08/2024

እግዚአብሔር ይመስገን

ልብ ይሰብራል እንቅልፍ ይነሳል 🥲 ፎቶው ተልኮልኝ አጋጣሚ ስልኬን ስከፍተው ያየውት መግለጽ አልችልም 😭እባካችሁ ይሄን ግፍ ማስተባበል አቁሙ ❗️ ሰውየውም የሌሎች ማስተማርያ ይሁን ❗️
23/08/2024

ልብ ይሰብራል እንቅልፍ ይነሳል 🥲

ፎቶው ተልኮልኝ አጋጣሚ ስልኬን ስከፍተው ያየውት መግለጽ አልችልም 😭

እባካችሁ ይሄን ግፍ ማስተባበል አቁሙ ❗️ ሰውየውም የሌሎች ማስተማርያ ይሁን ❗️

የተደፈሩ ሴቶችም ወንዶችም ብዙዎቹ ፍርድ የማያገኙት ለወንጀሉ ከለላ በሚሰጡ የደፋሪ ቤተሰቦች ምክንያት ነው ❗️❗️❗️ #ፍትህለሄቨን
23/08/2024

የተደፈሩ ሴቶችም ወንዶችም ብዙዎቹ ፍርድ የማያገኙት ለወንጀሉ ከለላ በሚሰጡ የደፋሪ ቤተሰቦች ምክንያት ነው ❗️❗️❗️

#ፍትህለሄቨን

"ባሌ አልደፈረም አልገደለም" ባይ ነች:: አይኗን በጨው አጥባ እየተከራከረች ነው:: ቪድዮውን ያያችሁ ምን ተሰማችሁ ?    #ፍትህለሄቨን
23/08/2024

"ባሌ አልደፈረም አልገደለም" ባይ ነች:: አይኗን በጨው አጥባ እየተከራከረች ነው:: ቪድዮውን ያያችሁ ምን ተሰማችሁ ?

#ፍትህለሄቨን

አሸንድዬ ሻደይ ሶለል 👌🏾 ❤️ውበት ሲለካ በባህላችን ነው ለካ
22/08/2024

አሸንድዬ ሻደይ ሶለል 👌🏾 ❤️
ውበት ሲለካ
በባህላችን ነው ለካ

እሰይ እሰይ ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንኳን ለዕርግተ ድንግል ማርያም በዓል አደረሰን 🙏🏽❤️
22/08/2024

እሰይ እሰይ ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንኳን ለዕርግተ ድንግል ማርያም በዓል አደረሰን 🙏🏽❤️

ጉርሻዎች የትኛው ድምጻችን ነው የተሰማው ? ጥያቄያችን ፍትሕ ነው ⁉️ ጥያቄያችን  #ፍትህለሄቨን እና እየተደፈሩ ያሉ ሴቶች ፍትህ ይሰጣቸው ነው ❗️ጥያቄያችን በጦርነት እየተደፈሩ ያሉትም ፍ...
21/08/2024

ጉርሻዎች የትኛው ድምጻችን ነው የተሰማው ? ጥያቄያችን ፍትሕ ነው ⁉️ ጥያቄያችን #ፍትህለሄቨን እና እየተደፈሩ ያሉ ሴቶች ፍትህ ይሰጣቸው ነው ❗️ጥያቄያችን በጦርነት እየተደፈሩ ያሉትም ፍትህ ያግኙ ነው ❗️❗️❗️ ስሜታዊነት ይቅር ❗️
ጉርሻ page 🙏🏽

ነገኮ እናታችን ኪዳነ ምሕረት ናት ❤️ በምልጃዋ ትጠብቀን 🙏🏽 እንኳን አደረሰን ⛪️
21/08/2024

ነገኮ እናታችን ኪዳነ ምሕረት ናት ❤️ በምልጃዋ ትጠብቀን 🙏🏽 እንኳን አደረሰን ⛪️

የፍትህ ጥያቄው ይመለስ ❗️❗️❗️ህግ ይሻሻል ❗️ በደለኞች አስተማሪ ቅጣት ይቀጡ ❗️
21/08/2024

የፍትህ ጥያቄው ይመለስ ❗️❗️❗️ህግ ይሻሻል ❗️ በደለኞች አስተማሪ ቅጣት ይቀጡ ❗️

21/08/2024

ሸዋ - አማራ

በርካታ ንጹሀን የፋኖ አባላት ናችሁ በሚል በመከላከያ ከሰሞኑን በግፍ ተግድለዋል::

ትናንት ስለ ሔቨን ክፉ ኮሜንት ያደረገውን ያቀመሳችሁት ቀጣይ 👇🏽🙏🏽📌ህጻናት እና ሴቶችን በግፍ በድሮን ጭምር ገድሏል❗️📌ሰራዊቱ በግፍ አሁን ድረስ በአማራ ሴቶችን እና ወንዶችን እየደፈሩ ይ...
21/08/2024

ትናንት ስለ ሔቨን ክፉ ኮሜንት ያደረገውን ያቀመሳችሁት ቀጣይ 👇🏽🙏🏽

📌ህጻናት እና ሴቶችን በግፍ በድሮን ጭምር ገድሏል❗️

📌ሰራዊቱ በግፍ አሁን ድረስ በአማራ ሴቶችን እና ወንዶችን እየደፈሩ ይገኛሉ ❗️

📌ባለፈው ጦርነት ደፋሪ ወታደሮች ፍርድ እንዳይሰጣቸው ፍርዱን አዘግይቷል ❗️

ፍትህ ስለሌለ ሠላም ጠፍቷል

ፍትህ በሌለበት ህዝብ ፍርድ ይሰጣል

ሠላም እንዲመጣ ፍትህ መስፈን ይገባዋል ❗️

20/08/2024

ለህጻን ሄቨን ፍትህ ሲጠይቅ በፖሊስ ታሰረ

ፍትህ ለሄቨን በማለት ሰልፍ የወጡ ጏደኛሞች  በአዲስ አበባ ፖሊስ ታስረዋል❗️
20/08/2024

ፍትህ ለሄቨን በማለት ሰልፍ የወጡ ጏደኛሞች በአዲስ አበባ ፖሊስ ታስረዋል❗️

“ልጆቻችን በቤታቸው ውስጥ ደኅንነታቸው ካልተጠበቀ ሌላ ወደየት መሄድ እንችላለን?” የፌቨን እናት። የቢቢሲ ዘገባ
20/08/2024

“ልጆቻችን በቤታቸው ውስጥ ደኅንነታቸው ካልተጠበቀ ሌላ ወደየት መሄድ እንችላለን?” የፌቨን እናት። የቢቢሲ ዘገባ

የሰባት ሄቨን አወት ተደፍራ በአረመኔያዊ ሁኔታ በቤት አከራይዋ ግለሰብ መገደሏ በርካቶችን አስደንግጧል እንዲሁም አስቆጥቷል። የሁለተኛ ክፍል ተማሪ የነበረችው ሄቨንን በመድፈር በዘ....

ግን ለምን ? ❗️❗️❗️አይበቃም ወይ ⁉️
20/08/2024

ግን ለምን ? ❗️❗️❗️አይበቃም ወይ ⁉️

19/08/2024

ቡሄ ደብረታቦር 👌🏾💚💛❤️

ዝናን ለህዝብ  ❗️🙏🏽ዝናቸውን የህዝብን ብሶት የማይጠቀሙትን "ቦይኮት" የማድረግ ዘመቻ ከወራት በፊት በአሜሪካ ሲካሄድ ነበር::"ቦይኮቱ" የራሳቸውን ገንዘብ ከመሰብሰብ ውጪ ህብረተሰብ ላይ ...
19/08/2024

ዝናን ለህዝብ ❗️🙏🏽

ዝናቸውን የህዝብን ብሶት የማይጠቀሙትን "ቦይኮት" የማድረግ ዘመቻ ከወራት በፊት በአሜሪካ ሲካሄድ ነበር::

"ቦይኮቱ" የራሳቸውን ገንዘብ ከመሰብሰብ ውጪ ህብረተሰብ ላይ ለውጥ እንዲመጣ የማያግዙትን ህብረተሰቡ ግፍ ሲፈጸም የማይቃወሙትን ማህበራዊ አገልግሎት የማይሰጡትን መስምያዬ "ጥጥ" ነው እንዲላቸው ነበር ቅስቅሳው::

እንደኔ አመለካከት በርግጥ ማህበረሰባዊነት ከግዳጅ ባይወለድም ቅሉ በራሳቸው ተነሳሽነት ለህዝብ ድምጽ የሚሆኑትን ልናከብራቸው ይገባል::

አርቲስት ቬሮኒካ እና በርካታ አርቲስቶች #ፍትህለሄቨን በማለት ድጻሽቸውን እያሰሙ ነው::

ለውጥ በጋራ ጥረት አንድ ቀን ይመጣ ይሆናልና ክፋትን አብረን እንቃወም ❗️....*****.....

ሰሚ ሳይኖር ግን ለምን እንጮሀለን ? ❗️❗️❗️…..******…..የሰሞኑ ጩኽታችን ይቀዘቅዝና እንለምደውና ደግሞ ለሌላ ጩኽት እንዳንገናኝ ትኩረታችን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 627 እንዲሻሻል...
19/08/2024

ሰሚ ሳይኖር ግን ለምን እንጮሀለን ? ❗️❗️❗️
…..******…..
የሰሞኑ ጩኽታችን ይቀዘቅዝና እንለምደውና ደግሞ ለሌላ ጩኽት እንዳንገናኝ ትኩረታችን የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 627 እንዲሻሻል ግፊት ማድረግ ላይ መሆን አለበት ❗️

ደፋሪው እንደፈለገ አሰቃይቶ ቢደፍር ቅጣቱ ከ 15 አመት እስከ 25 አመት ይላል::
....*****.....
የወንጀለኛ ህግ አንቀጽ 627 : በሕፃናት ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረ ሥጋ ድፍረት በደል

፩ ማንም ሰው ከእርሱ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካላት፣ ዕድሜዋ አስራ ሦስት ዓመት ካልሞላት ልጅ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የፈፀመ ወይም ይህችው ልጅ እንዲህ አይነቱን ድርጊት ከእርሱ ጋር እንድትፈጽም ያደረገ እንደሆነ፤ ከአስራ አምስት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡....*****.....
ድምጽ እያሰማችሁ ያላችሁ ሁላችሁ ወላጆች ተጽእኖ ፈጣሪ የሆናችሁ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታችሁ የህግ ሰዎች እንደሁልጊዜው ሰሞነኛ ሆኖ እንዳይቀር በባለሙያዎች ተደግፎ የህግ ለውጥ እንዲደረግ ጫና ማድረጉ ላይ ትኩረት መደረግ አለበት ባይ ነኝ::

ቋሚ መፍትሄ በሌለበት ቋሚ ጩኽት መቀጠሉ አይቀርምና መሰረታዊ ለውጥ ላይ እንስራ ❗️❗️❗️🙏🏽::
....*****.....
ፍትህ ለሄቨን
ፍትህ ለሴቶች
ፍትህ በጦርነት ሰበብ እየተደፈሩ ላሉ ወንዶች እና ሴቶች
#ፍትህለሄቨን
#ዝምአልልም
#ዝምአንልም

የአብይ አህመድ ጨካኝ  ሰራዊት በአማራ ንጹሀንን በግፍ መግደሉን ያቁም ❗️❗️❗️ፍትሕ ለኤልሳ በሪሁን Justice for Elsa
19/08/2024

የአብይ አህመድ ጨካኝ ሰራዊት በአማራ ንጹሀንን በግፍ መግደሉን ያቁም ❗️❗️❗️

ፍትሕ ለኤልሳ በሪሁን
Justice for Elsa

ጨፍጫፊው የአብይ አገዛዝ ከስልጣን መወገድ አለበት ❗️ ካኑማ 💪🏾💚💛❤️
18/08/2024

ጨፍጫፊው የአብይ አገዛዝ ከስልጣን መወገድ አለበት ❗️ ካኑማ 💪🏾💚💛❤️

በህጻን ሔቨን ላይ የተፈጸመው ግፍ ቁጣን ቀስቅሷል ፍትህ እየተጠየቀ ነው 🥲እንዲህ አይነት ጸያፍ እና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሁላችንም ማውገዝ አለብን እናትየዋን ለማጽናናት እና በፍርድ ሂደት ለማ...
18/08/2024

በህጻን ሔቨን ላይ የተፈጸመው ግፍ ቁጣን ቀስቅሷል ፍትህ እየተጠየቀ ነው 🥲

እንዲህ አይነት ጸያፍ እና ኢ-ሰብአዊ ድርጊት ሁላችንም ማውገዝ አለብን

እናትየዋን ለማጽናናት እና በፍርድ ሂደት ለማገዝ

📌የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር

1000177318934

አበቅየለሽ አደባ

ፍትሕ ❗️❗️❗️❗️

Adress

Stockholm

Telefon

+46764321468

Webbplats

Aviseringar

Var den första att veta och låt oss skicka ett mail när Ashruka አሽሩካ postar nyheter och kampanjer. Din e-postadress kommer inte att användas för något annat ändamål, och du kan när som helst avbryta prenumerationen.

Kontakta Affären

Skicka ett meddelande till Ashruka አሽሩካ:

Videor

Dela

እንኳን ደህና መጣችሁ!

ይህ ስለ ፍቅር የሚወራበት ፣ የመረጃ እና የመዝናኛ ፔጅ ነው።

Närliggande medieföretag


Övriga Medier/nyheter i Stockholm

Visa Alla

Du kanske också gillar