22/12/2024
ከፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት በነበረን የሁለትዮሽ ውይይት ሰፋ ያለ መጠነርዕይ ባላቸው የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። ጠሚ አቢይ አህመድ
ክቡር ፕሬዚዳንት እና የፈረንሳይ መንግሥት በብሔራዊ ቤተመንግስት እና በመካሄድ ላይ ባለው የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት እድሳት ሥራዎች ላደረጉት አስተዋፅዖ ምስጋናዬን አቅርቤያለሁ። በውይይታችን በተለያዩ ዘርፎች የሚኖሩ ትብብሮችን የፈተሽን ሲሆን የፈረንሳይን ኢንቨስትመንት መጨመርን አስመልክቶ ብሎም በትምህርት እና ባሕል ዘርፎች ያለንን ግንኙነት በማጠናከር ጉዳዮች ላይ ተነጋግረናል። ታሪካዊ ትስስራችንን ይበልጥ የመገንባትን አስፈላጊነትንም በውይይታችን አፅንዖት ሰጥቼ አንስቻለሁ።