![](https://img3.medioq.com/291/197/132224532911970.jpg)
11/10/2022
በትምህርት ስርዓታችን ላይ ለአመታት ተንሰራፍተው የነበሩ የትምህርት ጥራት እና አግባብነት መዛነፍ ፤ እንዲሁም የስብዕና ግንባታ ጉድለት እና የስርዓቱ ስብራቶችን በተለያዩ አማራጮች ማረም ከአንድ ኃላፊነት ካለበት መንግሥት የሚጠበቅ ግዴታ ነው።
በዚህ ረገድ በአሁኑ ወቅት በመንግስት እየተወሰዱ ያሉትን የስርዓተ ትምህርት ለውጥና የመፈተንና - የአፈታተን ባህልን የመቀየር ጅምር ጥረት እንዲሁም ለዘለቄታው እየተሰሩ ያሉ ለውጦችን መደገፍና ለተፈፃሚነቱ መተባበር ለመንግሥት እና ለተቋማት ብቻ የሚተው ተግባር ሳይሆን በእኩሌታ ችግር ፈቺ (problem solver ) የሆነ እና ትውልድ የመፍጠር ኃላፊነት የሚሰማው ፤ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተግባር ነው።
ግርማ የሽጥላ የአማራ ብልፅግና ፓ/ፅ/ቤት ኃላፊ