የደጓ ልጅ/Yedeguwa Lij

የደጓ ልጅ/Yedeguwa Lij ኑ በአጭር ጊዜ ጥሩ ተከፋይ መሆን ይፈልጋሉ በዚህ ቁጥር ያናግሩኝ 0963186920

Archaeology
27/06/2024

Archaeology

18/01/2023
ከፖለቲከኛው እስከ አዋቂ ሙህራን ትግል ደከመን ብለው ቁጭ ባሉበት ሀገርየተማሪ ትግል የት ያደርሳል?
17/12/2022

ከፖለቲከኛው እስከ አዋቂ ሙህራን ትግል ደከመን ብለው ቁጭ ባሉበት ሀገር
የተማሪ ትግል የት ያደርሳል?

❗️  አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ❗️ከዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም          -------------------------------የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ...
10/12/2022

❗️ አስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ❗️
ከዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም
-------------------------------

የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም "በታጠቁ ኃይሎች" እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ማምሻው የታጠቁ ኃይሎት በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባት መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል ፡፡ ሚዲያችን የሚመለከታቸውን አካላት ቦታው ድረስ በመደወል እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት እንዲህ በማለት ገልጸዋል" ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀዋል ፡ ገዳሙን በሁሉም አቅጣጫ በመግባት እያስጨነቁ ይገኛሉ ሦስት አገልጋዮችን አግተዋቸዋል ድረሱልን ድረሱልን " የሚል ድምፅን አሰምተዋል፡፡ የወረዳ ቤተክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመሆን ለመታደግ እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የሚመለከተው የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር በአስቸኳይ የመነኮሳትን እንግልትና የድረሱልን ድምጽ በመስማት አስፈላጊው የፀጥታ ኃይል ወደ ቦታው እንዲልክና ለሀገር የሚጸልዩ መነኮሳትንና ደቀመዛሙርት እንዲታደግ እንጠይቃለን ፡፡

ሼር በማድረግ የመነኮሳትን ሕይወት እንታደግ

እውነተኛ የቤተክርስቲያን ድምፅ

ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ

በቤት ሰራተኛ ተሰርቆ የጠፋው የሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ህጻን ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ። ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓም በ...
27/10/2022

በቤት ሰራተኛ ተሰርቆ የጠፋው የሁለት ዓመት ከዘጠኝ ወር ህጻን ከአዲስ አበባ ክልል ውጪ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል መገኘቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ጥቅምት 6 ቀን 2015 ዓም በለሚ ኩራ ክ ከተማ ልዩ ቦታው አያት ከሚባል አካባቢ ከቀኑ 10:30 ሰዓት በቤት ሰራተኛዋ ተሠርቆ የጠፋው ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ ከ11 ቀናት ብርቱ ክትትል በኋላ የተገኘ ሲሆን ከተጠርጣሪዋ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ጨምሮ ሶስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ ህጻን ሳሙኤል ዮሀንስ መጥፋት ሪፖርት ከደረሰው ጀምሮ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ባደረገው የሌት ተቀን አድካሚ ክትትል በደብረ ማርቆስ በአዲስ አለም ገጠራማና አስቸጋሪ ቦታዎች ፍለጋውን በማጠናከር እንዲሁም ከሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በአዲስ አበባ በተደረጉ አድካሚ ፖሊሳዊ ስራዎች ከፍተኛ ገንዘብ ካላመጣችሁ ህፃኑን አታገኙም እያለ ሲደራደር የነበረውም ግለሰብ ጭምር ሊያዝ ችሏል።

ከተጠርጣሪዎቹ ጋር በተገናኘ ቀሪ የምርመራ ውጤቶች በቀጣይ ይፋ የሚደረጉ ሲሆን ህብረተሰቡም የቤት ሰራተኞች ሲቀጥር ማንነትና ህጋዊነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው  ወደ ግቢ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበየሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በደቡብ ቴሌቪዥን ዜና 24 ላይ ቀርበው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረ...
10/10/2022

ተፈታኝ ተማሪዎች ተረጋግተው ወደ ግቢ እንዲመለሱ ጥሪ ቀረበ

የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ በደቡብ ቴሌቪዥን ዜና 24 ላይ ቀርበው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረውን ድንገተኛ አደጋ አሁናዊ ሁኔታ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል

እንደ አቶ አለማየሁ ገለጻ አደጋው የደረሰው በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ እና በቴክኖ ግቢ መካከል ያለው የተማሪዎች መሸጋገሪያ ድልድልይ በመደርመሱ ነው፡፡

415 ተማሪዎች በድልድዩ ላይ ሆነው ድልድዩ መደርመሱን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ 310 ተማሪዎች ቀላልና 110 ተማሪዎች ላይ መካከለኛና ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል፡፡

20 ተማሪዎች የአጥንት ስብራተ ያጋጠማቸው ሲሆን 85 በሚሆኑት ላይ ቀላል አካላዊ ጉዳት መድረሱንም አብራርተዋል፡፡

የአንድ ተማሪ ህይወት በአደጋው ማለፉንም ነው የተናገሩት፡፡
ተጎጂዎች በከተማው በሚገኙ የሪፌራል፣ ያኔት፣ አዳሬ እና ሞቲቴ ፉራ ሆስፒታሎች ህክምና እየተሰጣቸው ይገኛል፡፡

ተማሪዎች ሳይደናገጡ ተረጋግተው ወደ ግቢው እንዲመለሱ ጥሪ ያቀረቡት አቶ አለማየሁ ፈተናውን አስመልክቶ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መመሪያ እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡ በተመሳሳይ የተማሪ ወላጆችም ሳይረበሹ ተማሪዎችን በማረጋጋት ሂደት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የክልል መንግስት በጸጥታው ረገድ የሚጠበቅበትን እየተወጣ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ ደቡብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት

 ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድ...
27/09/2022



ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ባደረበት ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የቅርብ ወዳጆቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

25/09/2022

እኔም ዘመነ ካሴ ነኝ! ፋሲል ደሞዝ

"ዘመነ ካሴ ሰው ዘቅዝቆ አልገደለም፣ አላስገደለም። ባንክ አልዘረፈም፣ አላዘረፈም። መንገድ አልዘጋም፣ አላስዘጋም። ዘመነ የሰራው ወንጀል ለአማራ መቆሙ ብቻ ነው። ዘመነን ፍቱት።" ፋሲል ደመወዝ

 #ሰበር ዜና!!ዛሬ ከለሊቱ 10፡30 ላይ በግርማ የሺጥላ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርገበት።አማራ ክልል  ዳንግላ ከተማ 05 ቀበሌ እርሻ ሰብል አካባቢ ባለቤቱ እና ልጆቹ በሚኖሩበት መኖሪያ ቤ...
25/09/2022

#ሰበር ዜና!!

ዛሬ ከለሊቱ 10፡30 ላይ በግርማ የሺጥላ ላይ የመግደል ሙከራ ተደርገበት።

አማራ ክልል ዳንግላ ከተማ 05 ቀበሌ እርሻ ሰብል አካባቢ ባለቤቱ እና ልጆቹ በሚኖሩበት መኖሪያ ቤት ላይ ባልታወቁ ኃይሎች በተጣለ ሁለት ቦንብ በመኖሪያ ቤቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። በቤተሰቡም ላይ የመቁሰል ጉዳት ደርሷል።

ከቦንብ ፍንዳታው በኋላም በዳንግላ ከተማ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር ። ዛሬ ጧት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት እንዳለና ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ ኃይልም መሰማራቱን ያገኘነው መርጃ ያመላክታል።

25/09/2022

“እኔም ዘመነ ካሴ ነኝ” -አርቲስት ፋሲል ደመወዝ

"ዘመነ ካሴ ሰው ዘቅዝቆ አልገደለም፣ አላስገደለም። ባንክ አልዘረፈም፣ አላዘረፈም። መንገድ አልዘጋም፣ አላስዘጋም። ዘመነ የሰራው ወንጀል ለአማራ መቆሙ ብቻ ነው። ዘመነን ፍቱት።"

24/09/2022

ሻለቃ አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የጠቅላላ ጉባኤ ዋና ሰብሳቢ ዘመነ ካሴ ባስቸኳይ እንዲፈታ ዛሬ ጠየቁ።

በተጨማሪም ከወሎ፣ከጎጃም፣ከጎንደር እና ከሸዋ የታሰሩ ፋኖዎች እንዲሁም በአዲስ አበባ የታገቱ ጋዜጠኞች፣ማህበረሰብ አንቂዎች እና ሌሎችም እንዲፈቱ ጠይቀዋል።
https://t.me/kidstethiopia

የኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ስርዓተ ቀብር በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ተፈጽመ ******* ዛሬ ለከተማችን መራር ኀዘን ሆነ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊ...
22/09/2022

የኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ስርዓተ ቀብር በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት ተፈጽመ
*******
ዛሬ ለከተማችን መራር ኀዘን ሆነ በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዋና ክፍል ኀላፊ ኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ፀጥታ እያስከበረ በነበረበት ሰዓት በትናትናው ዕለት ከምሽቱ 6፡00 ሰዓት አካባቢ የከተማውን ሰላምና ድህንነት እያስጠበቁ እያለ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመትቶ ለህዝብና ለሀገር ሰላምና ደህንነት ሲሰሩ መስዕዋት ሆነዋል ።

የኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ስርዓተ ቀብር በከፍተኛ ወታደራዊ ስነ-ስርዓት በ12/01/2015 ዓ.ም በአፄ ቴዎድሮስ ክፍለ ከተማ በአየር ጤና ቀበሌ ተፈጽሟል። በቀብር ስነስርዓት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ ፣ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደጀኔ ልመንህ እና የከተማና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

በኮማንደር ዋጋዉ ታረቀኝ ድንገተኛ ህልፈት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቹ መፅናናትን እንመኛለን

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ

ሰበር ዜናዘመነ ካሴ በሕግ ቁጥጥር ስር ዋለበተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ!!በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ምርመራ ምክትል ...
21/09/2022

ሰበር ዜና

ዘመነ ካሴ በሕግ ቁጥጥር ስር ዋለ

በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ዘመነ ካሴ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ ገለፀ!!

በአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን የታክቲክ ምርመራ ምክትል ዘርፍ ኀላፊ ኮማንደር ክንዱ ወንዴ ዘመነ ካሴ በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕግ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተካሔደበት ነው ብለዋል።

በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከግለሰብ ቤት መያዙን ገልጸዋል። የወንጀል ተጠርጣሪው በሕግ ቁጥጥር ሲውል 541 ሺሕ ብር እና ከሌሎች ኤግዚቢቶች ጋር መያዙን ተናግረዋል።

ምርመራው የሚካሔደው በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን አረጋግጠዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል። ኮማንደር ክንዱ ተጠርጣሪው በሕግ ሲፈለግ እንደቆየ ገልጸው እንዲያዝ ለተባበረው ማኅበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል። ማንም ከሕግ ማምለጥ እንደማይችል የተጠርጣሪው መያዝ ማሳያ ነው ብለዋል።

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ከባለቤቷ ጋር ተለያየች!አርቲስት ሰላም ተስፋዬ እና አማኑኤል ተስፋዬ ለ4 አመታት በዘለቀው የትዳር ቆይታ በፍቺ መቋጨቱን ኢትዮፒካሊንክ ዘገበዋል። አርቲስት ሰላም ተስ...
18/09/2022

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ከባለቤቷ ጋር ተለያየች!

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ እና አማኑኤል ተስፋዬ ለ4 አመታት በዘለቀው የትዳር ቆይታ በፍቺ መቋጨቱን ኢትዮፒካሊንክ ዘገበዋል። አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ኑሮዋን ኢትዮጲያ ያደረገች ሲሆን አማኑኤል ተስፋዬ ኑሮውን በሀገረ አሜሪካ አድርጓል። ሁለቱ በትዳር ቆይታቸው 1 ልጅ አግኝተዋል።

Adres

America
RISEETHIOPIA

Meldingen

Wees de eerste die het weet en laat ons u een e-mail sturen wanneer የደጓ ልጅ/Yedeguwa Lij nieuws en promoties plaatst. Uw e-mailadres wordt niet voor andere doeleinden gebruikt en u kunt zich op elk gewenst moment afmelden.

Video's

Delen

Type