Burji united

Burji united unity for devlopment the power of positive thinking must be to life.

Burji zone land scape.
09/02/2024

Burji zone land scape.

His honour ATO Dange Hido
07/02/2024

His honour ATO Dange Hido

በቡርጂ ከፍተኛ የማዕድናት ክምችት መኖሩ ተገለፀ። ፣ ጥር 27/2016 ዓ.ም በቡርጂ ዞን ከፍተኛ የማዕድናት ክምችት መኖሩን በቡርጂ ዞን የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ...
06/02/2024

በቡርጂ ከፍተኛ የማዕድናት ክምችት መኖሩ ተገለፀ።

፣ ጥር 27/2016 ዓ.ም በቡርጂ ዞን ከፍተኛ የማዕድናት ክምችት መኖሩን በቡርጂ ዞን የሶያማ ዙሪያ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ግና ገለፁ።

ኃላፊው እንደገለፁት ጽ/ቤቱ በውሃ እና በማዕድን ዘርፍ በትጋት እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው ማዕድናቱን በአለኝታ ደረጃ ተለይቶ በጥናት ያልተረጋገጡ እና መኖሩን በጥናት የተረጋገጡ በማለት በሁለት መልኩ ከፍለው አብራርተዋል።

በዚህም መሠረት በጥናት ተለይተው የተረጋገጡ ግሪን ሳፋየር፣ የድንጋይ ከሰል፣ ስሞክኳርቲዝ እና ቤንቶናይት ሲሆኑ ግሪን ሳፋየር የተባለውን የጌጣጌጥ ማዕድን "ዎደ" ማህበር እና "ሠላም" የተባሉ ቡድኖች ለሙከራ በሦስት ወር ውስጥ በተደረገ የማምረት ሂደት ከ182 ሺህ 6ዐዐ በላይ ብር መሸጡን ገልፀዋል።

የድንጋይ ከሰል በጥናት ከተረጋገጡት ውስጥ አንዱ ሲሆን ጴጥሮስ እና ጓደኞቹ ማህበር 11 ሄክታር ቦታ ላይ የማምረት ፈቃድ ተሰጦቶት ለመሬት ባለይዞታ ክፍያ ፈጽሞ በሂደት ላይ መኖሩን ተናግረዋል።

በገምዮ አካባቢ ጥራትና ከፍተኛ ክምችት ያለው የቤንቶናይት ማዕድን እንዳለና ግዛቸው የሚባል አንድ ባለሀብት በ2014 ዓ.ም የቤንቶናይት ማዕድን የማምረት ፍቃድ አውጥቶ ወደ ሥራ ስላልገባ ፈቃዱ ተሰርዞ ሌላ ፍቃድ የጠየቀ ስለሌለ እየጠበቀ ይገኛል።

ሌላው ደግሞ በአለኝታ ደረጃ ተለይቶ በጥናት ያልተረጋገጡ ማዕድናት የብረት ማዕድን፣ ክርስታይል ኦፓል፣ አጌት፣ ፊልድስፓር፣ ብሉ ሳፋየር እና ኢመርላንድ ሲሆኑ በቡርጂ ሌሎችም ማዕድናት ሊኖሩ የሚችሉ አመላካች ነገሮች መኖራቸውን አብራርተዋል።

ኃላፊው በማብራሪያቸው ላይ በአካባቢው የሚገኙ ማዕድናትን በጥናት ለማረጋገጥ በቂ በጀት እንደሚጠይቅ ጠቁመው የዞኑና የወረዳው መንግሥት ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበው በማዕድን ማምረት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሀብቶች፣ ድርጅትችና ማህበራት ቡርጂ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ የሚል ጥሪ አቅርበዋል።

በአጠቃላይ ከጽ/ቤቱ ከአገኘነው መረጃ መገንዘብ የሚቻለው ጽ/ቤቱ ከሚመለከታቸው የክልል እና የፌዴራሉ አካላት ጋር በጥምረት እየሠራ እንደሆነና ቡርጂ ላይ በአለኝታ የተለዩ ማዕድናት ጥልቅ ጥናት ለማድረግ በቂ በጀት ተመድበው በዘመናዊ መሳሪያ ክምችቱን መለየት እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ይቻላል።

በዞኑ በአለኝታ ጥናት ከተገኙት በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ያልተጠቀሱ ከፍተኛ የማዕድን ክምችት ዓይነቶች መኖራቸው ስለተጠቆመ ለማዕድን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

01/02/2024
25/01/2024

የ 4 ኪሎዉን መንግስት መደገፍ የሕልዉናችን ጉዳይ ነዉ!

°°° ❝ለዚህም ነዉ የ 4ኪሎዉን መንግስት እስከችግሮቹ ተቀብለን፣ ሕፀፆችን ለማሻሻል፣ ክፍተቶቹን ለማረምና ለመሙላት ፤ ጅምር ስራዎችን ለማገዝ፤ በሀገር ግንባታ ላይ አሻራችንን ለማሳረፍ፣ በፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የድርሻችንን ለመወጣት መንቀሳቀስ የሚገባን።

የ 4 ኪሎዉን መንግስት በመጠበቃችን የሕልዉና አደጋን ለመግታት፣ ጅምር ስራዎቻችንን ለማጠናቀቅ፣ የተቋም ግንባታችንን ለማፋጠን፣ ሀገራዊ ሚናችንን ለማሻሻል...ብቻ ሳይሆን ማንነታችንን የማይቀበለንን አክራሪ ኀይል ለመመከትም ጭምር መሆኑ እንደሕዝብ መረሳት የሌለበት አጀንዳችን ሊሆን ይገባል።

አሁን ባለዉ ተጨባጭ እንደኀይማኖት የሕልዉናና የማንነት አደጋ ዉስጥ ከሚከተን እክራሪ ኀይል የምንመክተዉ 4ኪሎ ያለዉን መንግስታችን በተጠንቀቅ በመጠበቅ/በመደገፍ••• ነዉ።❞

ሰላም፣ መረጋጋት፣ እድገት፣ ብልጽግና ለሀገራችን ኢትዮጵያ!

11/01/2024

🌍 የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ሙሉ ፕሮግራሞች

📅 እለተ ቅዳሜ ጥር 04 / 2016 ዓ/ም

05:00 | 🇨🇮 አይቮሪኮስት ከ ጊኒ ቢሳው 🇬🇼

📅 እለተ እሁድ ጥር 05 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇳🇬 ናይጄሪያ ከ ኢኳቶሪያል ጊኒ 🇬🇶
02:00 | 🇪🇬 ግብፅ ከ ሞዛምቢክ 🇲🇿
05:00 | 🇬🇭 ጋና ከ ኬፕ ቨርዴ 🇨🇻

📅 እለተ ሰኞ ጥር 06 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇸🇳 ሴኔጋል ከ ጋምቢያ 🇬🇲
02:00 | 🇨🇲 ካሜሮን ከ ጊኒ 🇬🇳
05:00 | 🇩🇿 አልጄሪያ ከ አንጎላ 🇦🇴

📅 እለተ ማክሰኞ ጥር 07 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇧🇫 ቡርኪናፋሶ ከ ሞሪታኒያ 🇲🇷
02:00 | 🇹🇳 ቱኒዚያ ከ ናሚቢያ 🇳🇦
05:00 | 🇲🇱 ማሊ ከ ደቡብ አፍሪካ 🇿🇦

📅 እለተ ረቡዕ ጥር 08 / 2016 ዓ/ም

02:00 | 🇲🇦 ሞሮኮ ከ ታንዛኒያ 🇹🇿
05:00 | 🇨🇩 ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ከ ዛምቢያ 🇿🇲

📅 እለተ ሐሙስ ጥር 09 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇬🇶 ኢኳቶሪያል ጊኒ ከ ጊኒ ቢሳው 🇬🇼
02:00 | 🇨🇮 አይቮሪኮስት ከ ናይጄሪያ 🇳🇬
05:00 | 🇪🇬 ግብፅ ከ ጋና 🇬🇭

📅 እለተ አርብ ጥር 10 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ ከ ሞዛምቢክ 🇲🇿
02:00 | 🇸🇳 ሴኔጋል ከ ካሜሮን 🇨🇲
05:00 | 🇬🇳 ጊኒ ከ ጋምቢያ 🇬🇲

📅 እለተ ቅዳሜ ጥር 11 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇩🇿 አልጄሪያ ከ ቡርኪናፋሶ 🇧🇫
02:00 | 🇲🇷 ሞሪታኒያ ከ አንጎላ 🇦🇴
05:00 | 🇹🇳 ቱኒዚያ ከ ማሊ 🇲🇱

📅 እለተ እሁድ ጥር 12 / 2016 ዓ/ም

11:00 | 🇲🇦 ሞሮኮ ከ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ 🇨🇩
02:00 | 🇿🇲 ዛምቢያ ከ ታንዛኒያ 🇹🇿
05:00 | 🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ ከ ናሚቢያ 🇳🇦

📅 እለተ ሰኞ ጥር 13 / 2016 ዓ/ም

02:00 | 🇬🇶 ኢኳቶሪያል ጊኒ ከ አይቮሪኮስት 🇨🇮
02:00 | 🇬🇼 ጊኒ ቢሳው ከ ናይጄሪያ 🇳🇬
05:00 | 🇨🇻 ኬፕ ቨርዴ ከ ግብፅ 🇪🇬
05:00 | 🇲🇿 ሞዛምቢክ ከ ጋና 🇬🇭

📅 እለተ ማክሰኞ ጥር 14 / 2016 ዓ/ም

02:00 | 🇬🇲 ጋምቢያ ከ ካሜሮን 🇨🇲
02:00 | 🇬🇳 ጊኒ ከ ሴኔጋል 🇸🇳
05:00 | 🇦🇴 አንጎላ ከ ቡርኪናፋሶ 🇧🇫
05:00 | 🇲🇷 ሞሪታኒያ ከ አልጄሪያ 🇩🇿

📅 እለተ ረቡዕ ጥር 15 / 2016 ዓ/ም

02:00 | 🇳🇦 ናሚቢያ ከ ማሊ 🇲🇱
02:00 | 🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ ከ ቱኒዚያ 🇹🇳
05:00 | 🇹🇿 ታንዛኒያ ከ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ 🇨🇩
05:00 | 🇿🇲 ዛምቢያ ከ ሞሮኮ 🇲🇦

👉 የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ከቅዳሜ ጥር 18 እስከ ማክሰኞ ጥር 21 ይከናወናሉ።

👉 የሩብ ፍፃሜ ጨዋታዎች አርብ ጥር 24 እና ቅዳሜ ጥር 25 ይከናወናሉ።

👉 የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ረቡዕ ጥር 29 ይከናወናሉ።

👉 የደረጃ ጨዋታ ቅዳሜ የካቲት 2 ይከናወናል

👉 የፍፃሜ ጨዋታ እሁድ የካቲት 3 ተከናውኖ የአፍሪካ ዋንጫ በ2018 ተመልሶ እንከሚመጣ ድረስ አፍሪካዊያንን እየናፈቀ ይቆያል።



ጥንቃቄ አይለየን    አቶ ዐቢይ ክንፈ የተባሉ ግለሰብ ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ከተማ ሰዎችን ለማድረስ በኮንትራት ተስማምተው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B36969 ...
10/01/2024

ጥንቃቄ አይለየን

አቶ ዐቢይ ክንፈ የተባሉ ግለሰብ ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ/ም ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ከተማ ሰዎችን ለማድረስ በኮንትራት ተስማምተው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B36969 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪያቸውን እየነዱ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ልዩ ቦታው እንቁላል ፋብሪካ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ተነስተውነበር የተጓዙት፡፡

አቶ ዐቢይ ከሄዱበት ሳይመለሱ መቅረታቸው ያሳሰባቸው ቤተሰቦቻቸው ጉዳዩን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ያሳታውቃሉ፤ ፖሊስም አቤቱታውን ተቀብሎ ክትትሉን ይጀምራል፡፡

በተመሳሳይ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ/ም አቶ ዲልፈታ ደንሰቦ የተባለ ግለሰብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B 21688 አ.አ የሆነ መኪና እያሽከረከረ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሰዎችን ለማድረስ ከሄደበት ሳይመልስ መቅረቱ ለፖሊስ ሪፖርት ይደረጋል፡፡

አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተመሳሳይ ሁኔታ የሁለቱ ግለሰቦች መሰወርና የተሽከርካሪዎቹ ደብዛ መጥፋት የአሽከርካሪዎቹን ቤተሰቦችና ፖሊስን በእጅጉ አሳስቧል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩን የሚከታተሉ የምርመራና የክትትል ቡድን በማደራጀት ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ የአቶ ዐቢይ ክንፈ አስክሬን ሞጆ ከተማ እንዲሁም የአቶ ዲልፈታ ደንሰቦ አስክሬን ከሞጀ ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ ተጥሎ መገኘቱን ያረጋግጣል፡፡

ሁለቱም ግለሰቦች የተለያየ የሰውነት ክፍላቸው ላይ በስለት ተወግተው መሞታቸው እና ከአካባቢው የተገኙ ልዩ ልዩ ማስረጃዎች እንደሚያመለክቱት ወንጀሉ የተፈፀመው በተመሳሳይ ቡድን ወይም ግለሰብ ነው፡፡

አዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚዎች ለማወቅና በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትሉን አጠናክሮ በመጠቀል ባከናወነው ተግባር በሁለቱም ወንጀሎች ቀጥተኛ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎችን እና አንድ በመሸሸግ ወንጀል የተጠረጠረ አንድ ግለሰብን መያዝ ተችሏል፡፡

ወንጀል ፈፃሚዎቹ ትራንስፖርት ፈላጊ መስለው በመቅረብ ሁለቱንም አሽከርካሪዎች በስለት በመውጋት እንደገደሏቸው በምርመራ ተረጋግጧል፡፡

ተጠርጣዎቹ አሽከርካሪዎቹን ከገደሉ በኋላ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3- B 21688 አዲስ አበባ የሆነውን ተሽከርካሪ ወደ ወላይታ ሶዶ በመውሰድ በአንደኛው ተጠርጣሪ ወላጆች መኖሪያ ግቢ ደብቀው ተገኝቷል፡፡

ወንጀል የተፈፀመበት መኪና በግቢያቸው የተገኘው የተጠርጣሪው ቤተሰቦች ተሽከርካሪው ውስጥ የፈሰሰውን የሟች ደም በማጠብ ማስረጃ እንዳጠፉ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B 36969 አ.አ የሆነው ተሽከርካሪ ደግሞ ለአንድ ግለሰብ ተሽጦ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል ወላይታ አካባቢ ሊገኝ ችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ የክትትል ቡድን አባላት ከአዲስ አበባ ሞጆ ፣ ከሞጆ ሀዋሳ ፣ ከሀዋሳ ሺንሽቾ እየተመላለሱ ከፍተኛ ውጣ ውረድ በማስተናገድ እና ውጤት ላይ ለመድረስ ጎዳና ተዳዳሪ መስለው መረጃ እና ማስረጃ ለማሰባሰብ ለበርካታ ቀናት ጎዳና ላይ በማደር ነበር ተጠርጣዎቹን በቁጥጥር ስር ማዋል የቻሉት፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ፣ የብሔራዊ መረጃና መረብ ደህንነት ፣ በኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ፣ በማዕከላዊ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የከንባታ ጠንባሮ ዞን ሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤትና የወላይታ ዞን መምሪያ አመራሮችና አባላት አንዲሁም ለሺንሽቾ ማህበረሰብ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገው ጥረት ላደረጉት ያላሰለሰ ድጋፍ አዲስ አበባ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል።

የግል የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች ተገቢውን ጥንቃቄ

04/01/2024

የሁለተኛ ድግሪ በምማር ወቅት ከ #ሱማሌላንድ በዩኤን ዲ ፒ ስኮላር ተሰጥቷቸው ኢትዮጵያ መጥተው ይማሩ የነበሩ ጓደኞች ነበሩኝ። ስለ ሀገራቸው ሲናገሩ በጣም በኩራት ነበር "ሱማሌ" ባልኳቸው ቁጥር "ሱማሌላንድ" እንድል ያርሙኛል። "ዓለም እውቅና አለመስጠቱን አትመልከት በምስራቅ አፍሪካ የህዝብ ምርጫን ዲሞክራሲያዊ ብቻ ሳይሆን ዲጂታል አድርገን በመምራት እንታወቃለን" ይሉኛል።

በቅርቡ ኢትዮጵያና እና ሱማሌላንድ የወደብ ስምምነት ማድረጋቸው ተሰምቷል ታዲያ ስምምነት ማድረጓቸውን ተከትሎ የሚጠበቁ ምልልሶች ጀምረዋል (የሱማሌ "ግዛቴን ከመውረር ለይቼ አላየውም"፤ የአውሮፓ ህብረት "የግዛት ልዋላዊነት እንዳይረሳ"፤ የግብፅ "የሱማሌ የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ አለሁ" ፤ ወዘተ)።

የኢኮኖሚ ስምምነቶች የጋራ ተጠቃሚነት ከተቻለ ይበልጡን የመጠቀም መርህን የተከተለ ነው። ለምሳሌ፦ ሱማሌላንድ 20ኪ.ሜ ለወደብ የቀረበ የየብስ መሬት ለ50ዓመት መነሻ ኪራይ በመስጠት ከኢትዮጵያ ቀልፍ አጋርነት፤ የሀገርነት እውቅና፤ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚነት፤ የመብራት ሃይል አቅርቦት እንዲሁም ከግዙፍ የመንግስት የልማት ተቋማት ድርሻ የማገኘት ድርድር ሊኖራት ይችላል።

ስለዚህ ድርድሩ በመጪው 50 ዓመት የሚመጡ እድሎች እና ስጋቶችን የደመረ የቀነሰ ረዥም እንደሚሆን ግልፅ ነው። ስምምነት በሚደረስባቸው ጉዳዮች በሙሉ ኢትዮጲያም ልታሸንፍ ሱማሌላንድም ልታተርፍ ለቀጣይ 50 ዓመት አቅጣጫ ቀያሪ ውሳኔ ሊያሳልፉ ነው የሚገናኙት።

ወደብ ለኢትዮጵያ ለኢኮኖሚ ወሳኝ ነው። ይበልጥ በቀጣይ ለማደግ ለሚደረግ ፍጥነት ቀላል ድርሻ አይኖረውም። በተመሳሳይ ከእውቅና እስከ የለማ መሰረተ ልማት ተጠቃሚነት ለሱማሌላንድ ግዙፍ በረከት ነው።

ከ1991ጀምሮ የሱማሌላንድ የእውቅና ጥያቄ በዓለም ሀገራት የሚጣጣለው አንድም የሱማሌን መብት ከመግፋት ጋር በማቆራኘት ሲሆን በዋናነት ግን ራስ ገዝ የሆነ ግዛቶችን በቀላሉ የሀገርነት እውቅና በሰጡ ቁጥር ተመሳሳይ እልፍ ተሰነጣጣቂ ሀገራትን ላለመፍጠር ነው።

በኢትዮጵያ እና በሱማሌላንድ መካከል የተደረሰው ስምምነት ማንን ይበልጥ በዘላቂነት ሊጠቅም እንደሚችል ለማወቅ የስምምነቱ (ምን የመስጠት እና ምን የመቀበል) ጭብጥ በደንብ ሲቀርብ ለመወሰን ይቀላል። በመርህ ደረጃ ግን ሁለቱም እጅግ የሚያስፈልጋቸው ጉዳይ ላይ እንደተገጣጠሙ ይሰማኛል።

እንደዚህ አይነት ስምምነት በወደፊቱ በ2070ዎቹ ሳይቀር ሁለቱ ሀገራት ሊኖራቸው የሚችለውን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ ሳይቀር የሚወስን ነው።

ለሱማሌላንድ የሀገርነት እውቅና ከኢትዮጵያ ሀ ብሎ መጀመር እና በኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኢኮኖሚያዊ አቅም ከፈጠሩ የልማት ድርጅቶች ድርሻ ማግኘትን ከጨመረ ቀላል ጥምቅ አይኖረውም። ለኢትዮጵያ በተመሳሳይ ለመጪው ጊዜ የጦር መንደር ከማግኘት እስከ ነጠላ ክንፍ የወደብ ጥገኝነት (ጅቡቲ) ላይ ለተንጠለጠለው ኢኮኖሚ ሰፊ አማራጭ ማግኘቱ ቀላል ፋይዳ አይኖረውም።
Economist View

ሰበር ዜና! እንኳን ደስ አለን! አላችሁ! ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች!ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች። ጠቅላይ ሚኒ...
01/01/2024

ሰበር ዜና! እንኳን ደስ አለን! አላችሁ!
ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ሆነች!

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር በር ለማግኘት እና ለማልማት የሚያስችላትን ስምምነት ከሶማሊ ላንድ ጋር ፈፅማለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የሶማሊ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ ሁሉን አካታች የሆነውን የጋራ መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በዚሁ መሠረት ለብዙ ዘመናት ወደብ አልባ ሆና የቆየችው ሀገራችን ከሶማሊ ላንድ ጋር ባደረገችው ስምምነት በሊዝ የወደብ ባለቤት መሆን ችላለች።

ኢትዮጵያ የውጪ ብድር ዕዳ መክፈል ያለመቻል አመክንዮ እና ስጋት ምንድን ነው? የተሰጣት የብድር መክፈል ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ቀጣይ ጫና ምንድን ነው?የዓለም አቀፉ የዕዳ ጫና ዝርዝር...
29/12/2023

ኢትዮጵያ የውጪ ብድር ዕዳ መክፈል ያለመቻል አመክንዮ እና ስጋት ምንድን ነው? የተሰጣት የብድር መክፈል ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ቀጣይ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም አቀፉ የዕዳ ጫና ዝርዝር በሚያወጣው ፊች የተሰጣት ደረጃ ከCC ወደ C የመውረዱ ጫና ምንድን ነው?

የዓለም ሀገራት የውጪ ዕዳ የመክፈል አቅም ደረጃ (ከAAA እስከ D) እንዴት ይመደባሉ?

የኢትዮጵያ መንግስት የውጪ ዕዳ ባለመክፈል የሚፈጠርን ጫና ለመቋቋም ምን አይነት ተገማች እርምጃዎች ሊወስድ ይችላል?

በጥልቀት ያለውን ትንታኔ እና መረጃ ከሚከተለው https://youtu.be/OsbhuVpYosw ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ።

የዓለም ሀገራት የዕዳ ክፍያ ሁኔታ ደረጃን እና በየደረጃው ያለውን ትርጓሜ መመልከት ለመትፈልጉ https://t.me/WaseAlpha ላይ pdf አስቀምጫለሁ።

ኢትዮጵያ ተቀምጦ ከአማዞን ዕቃ መግዛት ይቻላል? ዶላር የተጫነበት ኤቲኤም ካርድስ ከየት ይገኛል?-----------------------------------------------------------...
26/12/2023

ኢትዮጵያ ተቀምጦ ከአማዞን ዕቃ መግዛት ይቻላል? ዶላር የተጫነበት ኤቲኤም ካርድስ ከየት ይገኛል?
-------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ተማሪዎች ከውጭ የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) ጋር የተያያዘ ክፍያ መፈጸም ይፈልጋሉ። ውጭ ዘመድ ከሌላቸው እንዴት ይከፍላሉ?
ባሕር ማዶ ጉዞ ሲታሰብ የሆቴል አደራ (Hotel Reservation) ክፍያ ያስፈልጋል። ክፍያው ያለ ካርድ እንዴት ይፈጸም?
አገር ቤት የበረራ ትኬት ቅርንጫፍ ቢሮ የሌላቸው አየር መንገዶች አሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በጭራሽ የሚዳሰስ ቢሮም የላቸውም። ትኬት የሚሸጡት በበይነ መረብ ነው። ከጥሬ ገንዘብ ክፍያ ጋር ፍቺ ከፈጸሙ ቆይተዋል። ኢትዮጵያ ያለ ዜጋ እንዴት ይክፈል?
የተመሰከረለት የሒሳብ አዋቂ ለመሆን የትምህርትና የፈተና ክፍያ በበይነ መረብ ነው የሚካሄደው። የባንክ ሠራተኞች ሳይቀሩ በዚህ ይቸገራሉ።
የውጭ ምንዛሬ እጥረት በሚያንገላታት ኢትዮጵያ ብዙ ሰዎች ከአገር ሲወጡ ራስ ምታት የሚሆንባቸው የዶላር ጉዳይ ነው።
በተለምዶ ክቡ ባንክ የሚባለው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ በ2ኛው ወለል የዶላር ጠያቂዎችን ሰልፍ በየዕለቱ ማየት ብርቅ አይደለም። ለዓመታት ሰልፉ እየረዘመ እንጂ እያጠረ አልሄደም።
ለውጭ አገር አፋጣኝ ሕክምና 30ሺ ዶላር የጠየቀ ታማሚ፣ ለዚያውም በሐኪሞች ቦርድ የተፈረመበትን ደብዳቤ አቅርቦ፣ ከጠየቀው ገንዘብ አንድ እጅን እንኳ አያገኝም።
ባንኮች የዶላር ጥያቄ የሚያቀርቡላቸው ደንበኞችን ዓይን ይሸሻሉ። ጨክነው ከሰጡም ቆንጥረው ነው።
https://bbc.in/48yTs2b

21/12/2023
"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"******ከወደ ጎረቤት ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆኗል። "የኢትዮጵ...
15/11/2023

"የኢትዮጵያውን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ"
******
ከወደ ጎረቤት ሶማሊያ ፑንትላንድ የተሰማው ዜና ፈገግታን የሚጭር ሆኗል። "የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በመምሰሌ የደህንነት ስጋት ስላለብኝ ጥበቃ ይደረግልኝ" ያሉት በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ኢሳቅ አህመድ ሀሰን ጉዳይ በሶማሊያ ሶሻል ሚዲያዎች የእለቱ ሳቅ የሚጭር መነጋገሪያ ሆኗል።

ሰውዬው በሶሻል ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ብቅ ብለው በአፍ ሶማሊ ቋንቋ "አብይን ትመስላለህ እያሉ ህይወቴን አደጋ ውስጥ የከተቱብኝ ሰዎች አሉ። እኔ ሳልሆን አብይ ነው እኔን የሚመሰለው። በዚህ ምክንያት ለህይወቴ ሰለሰጋሁ ያለጠባቂ መንቀሳቀስ አቁሜለሁ።

በዛ ላይ የአባቱ እና አባቴ ስም አንድ ነው። ወደ ኢትዮጵያ የሄድኩት በመለስ ዘመን ነው አሁን መሄድ ብፈልግም ለደህንነቴ ስጋት ስላለብኝ ጠባቂ ያስፈልገኛል።" ብለዋል።

በፑንትላንድ ግዛት የዋኢዮ ወረዳ አስተዳዳሪ ይህን መልእክት ያስተላለፉት ለቀልድ ይሁን የምራቸውን ግን የታወቀ ነገር የለም።

እናንተ ምን አላችሁ? ይመሳሰሉ?
ምንጭ Somali Fast Info. ሶማሊ ፈጣን መረጃ

03/11/2023

መንግስት ሀገር መምራት ስላልቻለ የሚቆጣጠረው ጥቃቅኑን ነገር ሆኗል

እስቲ ብልጽግና ልብ ካለው ( I demand the government of Ethiopia)

📌በአማራ ያዘመተውን ሰራዊት አስወጥቶ የእርስ በርስ ጦርነት ያስቁም ( stop the civil war in Amhara).

📌ንጹሐንን የጨፈጨፉት እና የጦር ወንጀል የፈጸሙትን ለፍርድ ያቅርብ ህገ ወጥ እስር ያቁም (ፍትህ ይስፈን) (serve justice)

📌የህዝቡን የኑሮ ውድነት ያስተካክል (economic improvement)

📌የተቀጣሪዎችን (የመምህራን የዶክተሮች ወዘተ...) ደሞዝ ይጨምር (Salary increment)

📌የመናገር እና የሚድያ ነጻነትን ያክብር ያስከብር (Freedom of speech)

📌ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የሙስሊሙ መስኪድ ማፍረስ እና መግፋት አብያተ ክርስትያናትን አፍርሶ ሆቴል መስራትን አስቁሞ የእምነት ነጻነትን ያክብር ያስከብር (Freedom of religion)

📌የወጣቱን የስራ አጥነት ያስተካክል (Create jobs)

📌የደሀውን ቤት ያፈረሱትን ቀጥቶ ካሳ ይክፈል (Stop demolishing houses of the poor)

📌የፖለቲካ እስረኞችን ጋዜጠኞችንና የማህበራዊ ሚድያ አንቂዎችን ይፍታ (Free political prisoners, journalists and influencers- respect human rights)

📌በሙስና ሀገራችንን እየበዘበዘ ያለውን ሁሉ ለፍርድ ያቅርብ መንግስም ሌብነቱን ያቁም (stop corruption)

📌በአማራ በትግራይ በኦሮምያ በሱማሌ እና በሌሎች ስፍራዎች አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 31 ሚሊየን ወገኖቻችንን ይታደግ ( Resolve IDPs crisis)

📌የህዝብ ሚድያ ለህዝብ ጥቅም ያውቅል የዘር ጥላቻ እና የእርስ በርስ ጦርነትን ከማባባስ ይቆጠብ (Freedom of the press)
…..*****…..

እና ይሄ ሀገራችንን መቀመቅ የከተታት መንግስት ስልጣኑን በሰላማዊ መንገድ ለሚመጥን ሰው ያስተላልፍ (peaceful regime change)

…..*****…..

በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኘው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ፣ ማንኛውም አፍሪካዊ በዚህ ዓመት መጨረሻ ያለ ቪዛ ወደ ግዛቴ መግባት ይችላል አለች ።ማደግና መሰልጠን እንዲህ ነው 🙏 🇰🇪 🙏
29/10/2023

በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኘው ጎረቤት ሀገር ኬንያ ፣ ማንኛውም አፍሪካዊ በዚህ ዓመት መጨረሻ ያለ ቪዛ ወደ ግዛቴ መግባት ይችላል አለች ።
ማደግና መሰልጠን እንዲህ ነው 🙏 🇰🇪 🙏

 ‼️በመምህር [ አበባየሁ ጌታ ] የዩኒቨርስቲ አስተማሪ ከስር ያያዝኩት የ  ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩ...
11/10/2023

‼️
በመምህር [ አበባየሁ ጌታ ] የዩኒቨርስቲ አስተማሪ

ከስር ያያዝኩት የ ውጤት ነው ፤ የዚህ ልጥፍ ዓለማ ራስን ማንቆለጳጰስ ምናምን ሳይሆን ልፋቴ እና የሚከፈለኝ አለመገናኘቱ ሲቀጥል ዩኒቨርስቲ መግባት እና ትምህርት መስቀል ትርጉም አልባነቱን እንዲሁም 12ኛ ክፍል ውጤት ላልመጣላቸው መጽናኛ እንዲሆናቸው ነው።

በአንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ፤ከህይወቴ 17 ዓመት ለመጀመሪያ ድግሪ ሁለት ዓመት ደግሞ ለMasters ድግሪ በአጠቃላይ 19 ዓመታትን ያጠፋሁበት በትምህርት ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም Highschool እና መሰናዶ ጓደኛቼ የነበሩ የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ እና በተለያዩ የሙያ የንግድ እና የመሳሰሉ ነገሮች ላይ የተሰማሩ በአሁኑ ሰዓት የቤት አከራዮቼ ናቸው ፤ ባለመኪና ባለሆቴል ጽድት ያለ ቡቲክ ብቻ ምን አለፋህ በአጠቃላይ ከእኔ እጅግ በጣም በተሻለ የኑሮ ሁኔታ ነው የሚገኙት!😭

በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ ድግሪ የያዘ የዩኒቨርስቲ መምህር የሚከፈለው ደመውዝ ግብር ሳይቀነስ 12,579 ብር ነው ፤ 35% ግብር እንዲሁ የጡረታ ሲወጣ ኪሴ የሚገባው 9956(ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ ስድስት)ብር ነው።

እንግዲህ በትምህርት ደረጃዬ ሲወራልኝ የዩኒቨርስቲ መምህር ነኝ ፤ ሶስተኛ ድግሪዬን ብሰራ እና ዶ/ር አበባየሁ ጌታ ብባል ወደ 16,000 ብር ከታክስ በፊት እና ወደ 13,000 ብር ገደማ ከታክስ በኋላ እጄ ላይ ይደርሳል።

እና ለምንህ ነው ዩኒቨርስቲ ቀረብኝ ብለህ የምትጨነቀው?

ወዳጄ/ወንድሜ/እህቴ 12 ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት አልመጣልህም?

እሰይ እንኳንም አልመጣልህም! ራስህን ለመቀየር ታትር ፣ አጫጭር ኮርሶችን ከዩቲዩቭ አውርድ ፣ተማር ፣ቪዲዮ ቱቶሪያል ተከታተል ፣ ግራፊክስ እና የመሳሰሉ ገንዘብ ልትሰራ የምትችልባቸው ከምርጥ ኮንተንት ጋር ከመጣህ የዩቲዩብ ስራዎች ብቻ ብዙ ብዙ አማራጮች አሉህ፣ ተስፋ አትቁረጥ! በበሰበሰ ስረዓተ ትምህርት ብዙ ባለድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ባልወሰዱበት ከስር ተጀምሮ ባልተሰራ ስራ እና ሰረዓት ተምረህ መጥተህ መጨረሻ ላይ ብትወድቅ(የመስዋዕት በግ ብትሆን) ብቻህን ተጠያቂ አይደለህም! ራስህን ብቻ አትውቀስ! እልፍ በል! ታገል! እመነኝ ታመሰግነኛለህ!

በተመዘገበው ውጤት ልቡ የደማው የአንተው ከርታታው መምህር ወዳጅህ!

𝐒𝐩𝐞𝐜𝐢𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐧𝐭𝐫𝐢𝐛𝐮𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐢𝐧 𝐓𝐨𝐮𝐫𝐢𝐬𝐦 𝟐𝟎𝟐𝟑Dr. Loko Duba, originally from Japan who turned Borana, is a renowned anthropologist...
01/10/2023

𝐒𝐩𝐞𝐜𝐢𝐚𝐥 𝐂𝐨𝐧𝐭𝐫𝐢𝐛𝐮𝐭𝐢𝐨𝐧 𝐢𝐧 𝐓𝐨𝐮𝐫𝐢𝐬𝐦 𝟐𝟎𝟐𝟑
Dr. Loko Duba, originally from Japan who turned Borana, is a renowned anthropologist. She didn’t only study anthropology but living it! Her appreciation to the deep culture of the Borana earned her a clan status and the name Lookoo Duubaa

Dr. Lookoo Duubaa dhaloonni fi lammiin isaanii biyya Jaappaan tayus, jaalala Oromoof qaban irraa kan ka’e Borantittii tayanii kan hafanii dha. Qorannoo Oromoo hedduminaan gochuun qooda
olaanaa Oromoo keessatti bahaa kan jiranii dha.

📌ለ ብልህ የቡርጂ ወጣቶችውሎህ ምን ይመስላል? ውሎህ የት ነው? ውሎህ ከማን ጋር ነው? ቀን ነግቶ ሲመሽ በሕይወትህ ምን አድስ Value add ታደርጋለህ? ምን ያህልስ በሕይወትህ አድስ ነገ...
28/09/2023

📌ለ ብልህ የቡርጂ ወጣቶች

ውሎህ ምን ይመስላል? ውሎህ የት ነው? ውሎህ ከማን ጋር ነው? ቀን ነግቶ ሲመሽ በሕይወትህ ምን አድስ Value add ታደርጋለህ? ምን ያህልስ በሕይወትህ አድስ ነገር እንድፈጠር ትሻለህ? ምን ያህልስ ትታትራለህ?

ለመሆኑ እነዚህን ጥያቄዎች ራስህን ትጠይቃለህ? ወይስ ውሎ አድሮ የማይቀየረው ተመሳሳይ ሕይወት ተመችቶሃል? እስከዛሬ ካላሰብክበት ለቁጥር የምታክቱ ቀናቶች Comfort zone'ህ ሆነውልሀል ማለት ነው። እዚህ ጋር አንድ ነገር ላስታውስህ በብዙ ነገር የቀደሙን ነጮች ሲተርቱ “Your comfort zone will kill you” ይላሉ። የማይንቀሳቀስ ውሃ ለወባ መራቢያ ምክንያት እንደሚሆነው ሁሉ በድግግሞሽ የተሞሉ ቀናቶች ለተለያዩ ተዳባይ የባህሪ ለውጦች መራባት ምክንያት ላለመሆናቸው ዋስትና አይኖርህም።

ስለዚህ የቡርጂ ወጣት ሆይ ዘመኑ የብልሆችና የፈጣኖች እንጂ የዋዘኞችና የፈዛዞች እንዳልሆነ በመረዳት በ'Survival of the fittest' ዓለም ውስጥ እየኖረ እንዳለ ወጣት 'The fittest' ሆኖ ለመገኘት እራስህን አስታጥቅ። በምን ራሴን ላስታጥቅ ካልከኝ እነሆ በእውቀት (Knowledge ) ራስህን አስታጥቅ። በሙያ/በክህሎት (Skill) ራስህን አስታጥቅ። በምክንያታዊ አስተሳሰብ (Rational thinking) ራስህን አስታጥቅ። በተግባቦት (Communication) ራስህን አስታጥቅ። በዲፕሎማሲ (Diplomacy) ራስህን አስታጥቅ። በትስስር (Network) ራስህን አስታጥቅ። በቋንቋ ችሎታ (Language proficiency) ራስህን አስታጥቅ፤ አፍ ከፈታህበት ቋንቋ በተጨማሪ በትንሹ 4 ቋንቋ ልመድ(Polyglot ሁን) ከሀገር ውስጥ 2 ቋንቋ ለምሳሌ:- አማርኛና Afaan Oromoo ከውጭ 2 ቋንቋ ለምሳሌ:- Englishና 官话(Mandarin/Chinese) ልመድ ምክንያቱም እነኝህ ሁለቱ የዓለምን ኢኮኖሚ የሚዘውሩ ሀገራት ቋንቋዎች ናቸውና። በቀበሌ በወረዳ እና በዞን ከተገደበ አስተሳሰብ ውጣና እንደ ዓለም ዜጋ አስብ፤ እንደ ዓለም ዜጋ ተንቀሳቀስ፤ እንደ ዓለም ዜጋ ተዘጋጅ። በመጨረሻም ዘመኑ የDigital ነውና በDigital knowledge and skill እራስህን አስታጥቅ።



Dawe

May their souls rest in peace
27/09/2023

May their souls rest in peace

ከቡርጂ ዞን ባለስልጣናት እና በኬንያ የቡርጂ ማህበረሰብ አመራሮች ጋር በኤምባሲው ውይይት ተደረገ==================================(ናይሮቢ፤ ኬንያ፣ መስከረም 9 ቀን 20...
21/09/2023

ከቡርጂ ዞን ባለስልጣናት እና በኬንያ የቡርጂ ማህበረሰብ አመራሮች ጋር በኤምባሲው ውይይት ተደረገ
==================================
(ናይሮቢ፤ ኬንያ፣ መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባልና የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በተከበሩ አቶ ማሬ አለማየሁ የተመራ የፌዴራልና የክልል ምክር ቤቶች አባላት እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተ የልዑካን ቡድን ለሥራ ጉዳይ ወደ ናይሮቢ በመጣበት ወቅት በኤምባሲው በመገኘት ከክቡር አምባሳደር ባጫ ደበሌና ዲፕሎማቶቹ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡

በኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ክቡር ጄኔራል ባጫ ደበሌ በአገራችን ልማትና አንድነት ዙሪያ በኬንያ የቡርጂ ማህበረሰብን ለማወያየት የመጣውን የልዑካን ቡድን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በኤምባሲው በመገኘታቸውም አመስግነዋል፡፡

ክቡር አምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ አክለውም የኤምባሲው ዋና ተልዕኮ የአገራችንን ጥቅም በኬንያ ማስጠበቅ እና በኬንያ የሚኖሩ ዜጐቻችንን ጥቅምና መብት ማስጠበቅ እንደሆነ አብራርተው፤ የቡርጂ ማህበረሰብም ለሚያነሳቸው ጉዳዮች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የልዑኩ መሪ እና የቡርጂ ዞን ዋና አስተዳደሪ የተከበሩ አቶ ማሬ አለማየሁ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው፤ የቡርጂ ጂኦግራፊካዊ አቀማመጥ እና የሕዝቡን አኗኗር ገለፃ አድርገዋል፡፡ በዚህም የቡርጂ ማህበረሰብ በተለያዩ አገራት እንደሚኖሩ አንስተው በብዛት በኬንያ እንደሚገኙ በመግለጽ ይህንን በርካታ ማህበረሰባችንን ለአገራችን ልማት አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ኤምባሲው አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡

በመጨረሻም ከተሣታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በክቡር አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ ለአገራችን ሰላምና ልማት የማህበረሰቡ ተወላጆች የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የቡርጂ ዞን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ ብሄር ብሄረሰቦች አንዱ ሲሆን፤ በቅርቡ በተደረገው የክልሉ አደረጃጀት ክለሳ ከልዩ ወረዳነት መዋቅር ወደ ዞን ደረጃ ከፍ ማለቱ ይታወሳል፡፡

 #በእርግጥም እግዚአብሔር በሰፈር የምቀር ሕልም አልሰጠንም። ራዕይ በባህርው ተወልዶ እስክያድግ አድጎም ውጤት እስክያፈራ በየፈርማታው መስዋትነትን ያስከፍላል። ራዕዩን ከጸነስን ዕለት አንስቶ...
17/09/2023

#በእርግጥም እግዚአብሔር በሰፈር የምቀር ሕልም አልሰጠንም። ራዕይ በባህርው ተወልዶ እስክያድግ አድጎም ውጤት እስክያፈራ በየፈርማታው መስዋትነትን ያስከፍላል። ራዕዩን ከጸነስን ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬ መስዋትነት እየከፈላችሁ የመጣችሁ ወገኖቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።

#ከስኬቶቻችን ጥቅቶቹ፣
#ህዝባችንን ከጊዛዊ አስከፍ ኮሮና ቫይረስ በእግዚአብሔር እርዳታ ግንዛቤ በመፍጠር በወቅቱ በማተርያል ድጋፍ ከጎኑ ቆመናል።

#አንድም እናት በህክምና ማሽን እጦት ምክንያት ለሞት መዳረግ የለባትም በምል ጽንሰ ሀሳብ ተነስተን ማህበረሰባችን በቅርበት ተገብ ህክምና እድያገኝ የማሽኖች ግዥና የማህበረሰብ ሆስፕታል ግንባታ ራዕያችን በአንድም በለላም መልኩ ተሳክቶ ዛሬ ላይ በመንግስት ሆስፕታል ማሽኖቹ ግልጋሎት ላይ ይገኛሉ።

#ህዝባችን በአከባቢው በነበረው ረሃብ እንዳይጎዳ ማህበረሰባችን በማስተባበር ክፍውን ጊዜ በመደጋገፍ ወደ እግዚአብሔር ጮሄን ያለንን ተካፍለን አንዳችን ለአንዳችን ፍቅር አሳይተን ይኽው ለዘረ ለድል በቅተናል።

በፍጽሞ አይቻልም ተብሎ ለዘመናት የተፈራውን የዎናካ አያና ክብረ በዓል የይቻላል መንፈንስ በአመራሩ ላይ በመዝራት ይኽው ለተከታታይ አመታት የብሔሩ የማንነት መገለጫ ሆኖ እድከበር መሰረት ካጣሉት አንዱ ለመሆን በባህሉ ዕድገት ዘርፍ የእራሳችንን አሻራ ጥለናል።

#የህዝብ አንድነትን የማጠናከር ስራ የራዕያችን ጽንስ ዛሬ በሞያሌ ኬንያ በአባቶቻችን የ20 ቀን እልህ አስጨራሽ ትግል ፍሬው አይተን እጅጉን ተደንቀናል።

#ህዝብን ለሁለንተናው ለውጥ የማነሳሳት ስራ በዞናችን ከፍተኛ ማስተባበር ከሰሞኑን ሞያሌ ኢትዮጵያ ጀምሮ ማርሰበት ቀጥሎ ናይሮብ ኬንያ ላይ በከፍተኛ ህዝባዊ ማህበል ለውጤት ስበቃ ስናይ ራዕዩ በሁላችን ተሳትፎ እጅጉን እየበለጸገ መሆኑን ስናይ ኖረን በማዬታችን እጅግ ደስ ብሎናል።

#ራይዬ ይቀጥላል ስንል ታጋይ ብሞትም ትግል ይቀጥላልና በትግሉ በቀጥታም በተዘዋዋርም በመሳተፍ ላይ ያላችሁ የማህበረሰባችን አባላት እድሁም ከማህበረሰባችን ውጪ ለማህበረሰባችን ያላችሁን ፍቅር በአንድም በለላም ስትገልጹል የቆያችሁ ወዳጅና አጋር ወገኖቻችን እንኳን ደስ አላችሁ።
Bati jilo

If your dream don't scare You They aren't enough(Mohammed ali)ጃና ቤታ፡፡
20/08/2023

If your dream don't scare You They aren't enough(Mohammed ali)
ጃና ቤታ፡፡

Breaking news burji zone tune rikash kayyo Dr yohannes . Senator mehammed chute ....we unite bright future ...All Ethiop...
19/08/2023

Breaking news burji zone tune rikash kayyo Dr yohannes . Senator mehammed chute ....we unite bright future ...All Ethiopian congratulations 🎉

03/08/2023

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መቀመጫ ዎላይታ ሶዶ መሆኑ ተረጋግጧል። የህዝቡ ጥያቄ ሙሉ በመሉ ባይመለስም መደመጥ መጀመሩ መንግስትን ያስመሰግነዋል።

«. እንደ ኢትዮዽያ ህዝብ በራሱ ላይ ማዕቀብ ጥሎ የሚኖር ህዝብ የለም አሉን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ. »አዎ ገነት ምድር ይዘን የምንሰደድ። ገነት አየር ይዘን በበረሀ የምንቃጠል። ገነት መሬት ኖሮ...
08/05/2023

«. እንደ ኢትዮዽያ ህዝብ በራሱ ላይ ማዕቀብ ጥሎ የሚኖር ህዝብ የለም አሉን ጠቅላይ ሚኒስቴሩ. »

አዎ ገነት ምድር ይዘን የምንሰደድ። ገነት አየር ይዘን በበረሀ የምንቃጠል። ገነት መሬት ኖሮን የምንራብ፣ የአለምን የውሀ ጉድጓድ ደፍነን የምንጠማ፣ ሰፊ አገር ይዘን በዘር የጠበብን ሰዎች ነን። ከሁሉም ከሁሉም የሚያገበግበኝ ውብ እህቶቻችን የልጅነት ውበታቸውን በዘመናዊ ባርነት በአረብ አገር የሚከሰክሱት ነገር ነው። እነዚህ ሁሉ ስህተቶች በፖለቲከኞቻችን የተፈፀመብን መሆኑን እርሰዎም ማወቅ አለባቸው። አዎ ስደት ውርደት ችጋር ጥማት መገዳደል በእርሰዎ የመሪነት ዘመን ብቻ
የተፈጠ አደለም። አሁንም ግን እርሰዎ መሪ ከሆኑ ቡኋላ ሚሊየኖች እየተራቡ፣ መቶሺዎች በዘመናዊ ባርነት እየተሸጡ የመረረውም ተስፋ ቆርጦ በእግሩ በባህር እየተሰደደ የሚኖርባት አገር ናት። በመቶሺ የሚቆጠር ህዝብ የሞተባት በሚሊየን የሚቆጠር ህዝብ የተፈናቀለባት፣ በመቶሺ የሚቆጠር ህዝብ በጭካኔ ቤቱ የፈረሰበት አገር ናት አሁንም ያለችው ኢትዮዽያ።

ይች አገር ከመከራ ወደሌላ መከራ እየተሸጋገረች አሁን ያለነውን ወጣቶች ጭምር ፊዳ እያደረገች እርሰዎ እጅ በሙስኞች የታሰረች ከዚህ ሁሉ አሮንቃ አውጡኝ እያለች የምትጮህ፣ መፍትሄ
ፈላጊ አገር ናት።

አሁንም ቢሆን የተሻለች አገር ለማድረግ የናተንና የፖለቲከኞቻችንን በጎ ህልም ትፈልጋለች። እዚህ ላይ ግን ለሆነው ሁሉ እርሰዎ ብቻ የመፍሄ አካል ይሁኑ አላልኩም። እርሰዎ በቻ ሀላፊነት ይውሰዱ እያልኩኝ አደለም። እርሰዎም እንደ አንድ በችግር የታጠረች አገር መሪ እንደመሆነ ልክ እርሰዎም የሚወስዱት ሀላፊነት እንደለ ግን ማመን አለባቸው።

አጥፊዎቹም መርዘኞቹም ጥሩ ሰሪዎች እኛም እንደ አንድ የሚዲያ ባለሙያ የምንወስደው ግለሰባዊ ሀላፊነት አለን። አገር ቤት ናት የጋራ ቤት የሚሰራ ሰው በሳር አይጣላም እንደሚሉት አረቦች ለዝች አገር ዘላቂ መፍሄ ፈልገን በራሳችን ላይ የጣልነው ማነቋዊ ማዕቀብ ማንሳት፣ ህዝብም እንደህዝብ መሪውም እንደመሪ ፖለቲከኛም እንደ ፖለቲካዊ ሀላፊነቱ የሚዲያ ባለሙያም የራሱን ወሳኝ እርምጃ መውሰድ አለበት።
-
በታሪክ ያለንን ችግር አብረን እንፍታው። በመሬት ይገባኛል የመገዳደል ሞኝ እይታችንን አብረን ሆነን እንፍታው። እርስበርስ ከመጠራጠር፣ ይልቅ የልማት ጦርነት እናውጅ። በሙስና ላይ እስከ
መግደል የሚያበቃ እርምጃ ያለው ህግ እናፅድቅ። በብቃት እንጅ በዘር የተዋቀረ የስልጣን ኩታን እናሶግደው። ሁሉም ብሄር ሙህር አለው። ሁሉም ብሄር ንፁህና ለአገር ተቆርቋሪ አለው። በዝምድናና በዘርየተሳሰረ የስልጣን እርከናችን የትም አያደርሰንም። የለንደን ከተማ ከንቲባ የፓክስታኒ ዜጋ ነው። የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ህንዳዊ ነው። የሚያስፈልገው የተሻለ ራዕይ ሀሳብ እንጅ እምነት ብሄር ወይም ክልል አደለም። ወይም አብላጫ የብሄር መስፈርት አደለም። ስንመሰረት ጀምሮ እስከዚህ ሰአት ድረስ አንዴ የሀይማኖት አንዴ የቡድን አንዴ የመንግስትን አንዴ የግዛትን ጦርነት እየተቀባበልን ነው እዝህ የደረስነው። ሁሉም ስረአቶች በጦርነት ነው የመጡት። ከዚህ ቡኋላ ግን ጦርነት የለለባት አዲሲቷን ኢትዮዽያ ለትውልድ ማስከብ አለብን። ይህ እርምጃ የሚጀምረው ከእርሰዎ ብትረ ስልጣን አሀዱ ብሎ ሲተገበር ነው። ይሄ ህዝብ የሀሰተኞች፣ የፅንፈኞች የሌባ ስረአት ጠባቂዎች በሆኑ ግለሰቦችና መንግስታት እንደፈለገ ሲደረግ የኖረ አሁንም መከራው ያላበቃላት ህዝብ ነው።

አስታውሳለሁ የሳኡዲ የግብርና ሚኒስቴር እናተኮ ብታውቁበት ውሀውንም፣ መኖውንም ስጋውንም፣ ወተቱንም ፣ ማሩንም የቅባት እህሉንም የሰውን ልጅ ፋላጎቶች ሁሉ ለአለም ህዝብ አሟልታችሁ ማቅረብ የነበረባች ህዝቦች እንጅ ለልመና የምትንከራተቱ
ሰዎች መሆን አልነበረባችሁም ብለው ሲናገሩን።

ይህ ሁሉ ግን በራሳችን ላይ ማዕቀብ ጥለን የምንኖር ሰዎች በመሆናችን የመጣብን መከራችን ነው። ከሰላም ይልቅ ለጦርት ፍቅር የወደቅን፣ ከፍቅር ይልቅ ለጥላቻ የተገዛን ከአንድነት ይልቅ ለልዮነት የምንታገል፣ ስራን ከመስራት ይልቅ 6 ሰአት ሰርተን በሱስ ቦታ ላይ ተቀምጠን ፈጣሪን እተቀመጥንበት አምጣልን የምንል ብኩኖች ስለሆንን ነው። አሁንም ነቅተን እናንቃ። ዘመኑ የቴክኖሎጅ ነው አንድ የተሻ ሀሳብ ፈጥረን ተመሳይ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ፍላጎት ያለው ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም በጅ ላይ መረጃ ይወርድለታል። ሰብስቦ መሰረተ ትምህርት ማስተማር ድሮ ቀረ። ለጥፋት ለሀሜት ለጥላቻ ለልዮነት ለበቀል ህዝብን የምናነሳሳበትን ሚዲያ እንደ አባይ ግድብ ድልድይ በአንድ ወጥ ለማደራጀት ከተጠቀምንበት አገራችን ኢትዮዸያ ሆና ልማታችንን ቻይና ማድረግ እንችላለን። ብሄራችን ጎሳችን ቋንቋችን ፍላጎታችን ሁሉ የኛ የሆነ አብሮ የሚቀጥል ማንም ላቀጭጭህ ቢለው ማድረግ የማይችል ሆኖ የተሰራ ነው። ኢትዮዽያ ውስጥ ከዚህ ቡኋላ ማንም ማንንም ማሸነፍ አይችል። የጋራ ጥላታችን ግን ያልተገራው ፖለቲካችንና
ድህነታችን ኋላቀርነታችን ነው። ብሄርና እምነት ከድህነት፣ ከድንቁርና ከስደት ከልመና ከውርደት አያድንም። እንደማያድንም መቶሺ አመታቶችን አብረን ሆነን አየነው። በሁላችንም ብሄርና እምነት ውስጥ ድህነት፣ ረሀብተኝነት ኋላቀርነት አለ። ምንም ቆንጆ የሆነ አንዳችን ከአንዳችን የተሻለ ነገር የለንም።

በመርህ እንተቻለን፣ በመርህ ሀሰብ እንሰጣለን በመርህ እንደግፋለን።

ሱሌማን አብደላ

👉ይሄን መልዕክት ቡርጂን ለማያዉቁ ኢትዮጵያዊያንና መሪዎቿ አድርሱልኝ!!📣〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️"ይህ ከኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሣሙኤል ሩቶ እጅ የሀገሪቱን ቁልፍ ሥልጣን እ...
01/05/2023

👉ይሄን መልዕክት ቡርጂን ለማያዉቁ ኢትዮጵያዊያንና መሪዎቿ አድርሱልኝ!!📣
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
"ይህ ከኬንያዉ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሣሙኤል ሩቶ እጅ የሀገሪቱን ቁልፍ ሥልጣን እየተረከበ ያለዉ የቡርጂ ልጅ ነዉ!!
✍️ኬንያ የቡርጂ ልጆችን አቅምና ወኔ ታዉቃለች
በኬንያ ትልቅ ስልጣን ተሰጥቶ አንቱ የተባሉ ሐጅ መሐመድ ጩቴ ቀጥሎ ዛሬ ከወደ ኬንያ አስደማሚ ወሬ ተደምጧልና ጆሮአችሁን ስጡኝ ሲል ለማዉራት መጓጓቴን በማከል ነዉ።

ዛሬ ብቻ ሳይሆን በኬንያ ፓርላማ ጭምር መግባት ለቡርጂ ድንቅም ብርቅም አይደለም ፤ ምድረ ሞያሌ ኬንያን በሐብት ተቆጣጥረዉ የራሳቸዉን ቀበሌ መስርተዉ ወረዳ ሰይመዉና ክፍለ ሀገር አቋቁመዉ የሚኖሩ ቡርጂዎች .............።

በኬንያ ማርሳቢት የተሰየመዉ ማርሳ በሚሉት የቡርጂ ሰዉ እንደሆነ የምናዉቀዉ ስንቶቻችን ነዉ ብዬ ጥያቄ አላነሳም እንጂ መላሹ መአት ነዉ። ናይሮቢን በንግድ ተቆጣጥረዉና ሰፈር መስርተዉ በአስራ ሰባት የባህል ሽማግሌዎች ሚኖሩ ቡርጂዎች ከባለሙያ እስከ አመራር በርካታ የመንግስት ስራ ላይ ተሰማርተዉ ይገኛሉ።

በግምት እስከ 300,000 የሚሆን ቡርጂ በኬንያ በተለያዩ አከባቢዎች እንደሚኖር አንዱ በኬንያ ኮሌጅ የበጠሰዉ ጓዴ ሹክ ብሎኛል። የንግዱን አለም ተቆጣጥረዉ በሌሎች ሥራ እዉቅና እያተረፉ መምጣታቸዉን የሰሞኑ ፕሬዝዳንታቸዉ ሩቶ አዉርቷል የሚል ዜናም ሰምነኛ ወሬ ሆኗል አሉኝ።

ለመንደርደሪያ ይህን ካልኩኝ ዛሬ ከኬንያ እየበረረ የቡርጂን ሰፈር በደስታ ያናወጠዉ ወሬ የሹመት ዜና ነዉ። ከብርጋዴር ጄኔራል ወደ ሜጄር ጀነራልነት ማዕረግ በማደግ የMilitary Intelligence ዋና ዳይሬክቴር ሆኖ ዛሬ የሹመት ደብዳቤ የተቀበለዉ #ሜጄር ጀነራል አብዱልቃድር መሐመድ ቡርጄ የምስራች ዜና ስናሰማ በታላቅ ዜና ነዉ።

ምናልባትም በኬንያ ትልቅ የስልጣን ቁንጮ ላይ የሚገኙ ሀጅ መሐመድ ጩቴና በሚሊተሪ የኢንተሊጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አብዱልቃድር መሐመድ ኢትዮጵያ ብልጥ ከሆነችና በር ከከፈተች መጠቃቀም ይቻል ይሁን????? እናያለና‼️

ናይሮቢ መግቢያ ላይ የሚል ፎቅ እንዳለዉ ሜጄር ጀነራል አብዱልቃድር መሐመድን የሚናዉቅ ስንቶች እንሁን👉???

ወንበሩን ያጽናልህ የወንዜ ልጅ____ #ኬኛ‼️

መልካም ዜናብዙዎቻችን አምርረን ስንጠይቀው የነበረው የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት...
31/03/2023

መልካም ዜና

ብዙዎቻችን አምርረን ስንጠይቀው የነበረው የክልል ልዮ ሀይል የተባለው ወታደራዊ አደረጃጀት መሉ በሙሉ እንዲፈርስ ትዕዛዝ ተላልፏል። ልዮ ሀይሉ ሲፈርስ ወደ መደበኛ መከላከያ ስራዊት የሚቀላቀሉ ሲሆን የቀረው መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ይቀጥላል። ልዮ ሀይሉ የያዛቸውን የስራ ድርሻ ፌደራል ፖሊስና መከላከያ ስራዊት ይረከባቸዋል።

አንድ ፖሊስ ( በፌደራል ፖሊስ ዕዝ የሚመራ)
የኢትዮዽያ መከላከያ ስራዊት ብቻ ሆነው ይቀጥላሉ። ይህ ብልፅግና ከወሰደው አንድ ትልቅ ኢትዮዽያን የመታደግ እርምጃው ነው። እናመሰግናለን። ይች ውሳኔ እንድትወሰን ስትጮሁ ለበረቻሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።

ሱሌማን አብደላ

መንግስት ሀገር ለማፍረስ እየሰራ ነው የአመቱ ምርጥ ቀልድ!!!መቼስ ከወያኔ ጋር በነበረው ጦርነት ሀገር ለማፍረስ ነው የዘመተው እንደማትለን ተስፋ እናደርጋለን።
29/03/2023

መንግስት ሀገር ለማፍረስ እየሰራ ነው የአመቱ ምርጥ ቀልድ!!!
መቼስ ከወያኔ ጋር በነበረው ጦርነት ሀገር ለማፍረስ ነው የዘመተው እንደማትለን ተስፋ እናደርጋለን።

በአማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ከ223 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለአዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወ...
14/03/2023

በአማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች ከ223 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ223 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገለፀ፡፡

የአማሮ ልዩ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሃላፊ ፍፁም አራጋው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ÷ በአማሮ ልዩ ወረዳ ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በልዩ ወረዳው 22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ140 ሺህ 886 በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚፈልጉ ጠቅሰው፥ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳትም በድርቁ ምክንያት መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱትም ነው ሃላፊው የሚናገሩት።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸውንም አስረድተዋል፡፡

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑንም አንስተዋል፡፡

የቡርጂ ሶያማ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሃላፊ ጩሎ ጫንዶ በበኩላቸው፥ በቡርጂ ልየ ወረዳ በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ነው የገለጹት።

ከዚህ ባለፈም ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውንም ጠቁመዋል።

በዚህም ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑን አመላክተዋል፡፡

በመሆኑም በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በሚኪያስ አዬለ


ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

አንዳንዴ ቀልዶች የሰዎችን ስኬት እና ልፋት ይደብቃሉ። ይህ ሰው ገና በልጅነቱ አርባምንጭ አባቱ ጥሎት የጠፋ እና እናቱ የሞተችበት ቤተሰብ ሳይኖረው በብዙ ችግር ውስጥ ልጅነቱን ያሳለፈ ነው።...
01/03/2023

አንዳንዴ ቀልዶች የሰዎችን ስኬት እና ልፋት ይደብቃሉ። ይህ ሰው ገና በልጅነቱ አርባምንጭ አባቱ ጥሎት የጠፋ እና እናቱ የሞተችበት ቤተሰብ ሳይኖረው በብዙ ችግር ውስጥ ልጅነቱን ያሳለፈ ነው። ተርቧል, ማደርያ አቷል። His peers used to bully him. ከሊስትሮነት እስከ ቀን ስራ ድረስ ሰርቷል። ዛሬ ላይ በyoutube እና Tiktok ከ 500,000 በላይ followers አሉት። የተለያዩ seminars ያዘጋጃል የገባውን ለሌሎች ያስረዳል። የተለያዩ ጉዞዎችን ያዘጋጃል። የተለያየ counseling ስራ ይሰራል። he has his own podcast አሁን ደግሞ ቦሌ ላይ ለየት ያለ የመዝናኛ ቦታ እንደከፈተ ሰምቻለሁ። ይህ ለኔ ትልቅ accomplishment ነው።ከምንም ተነስቶ ብዙዎች እየቀለዱበትም ብዙ የህይወት ፈተና ቢያጋጥመውም በአይምሮ የተሻለ ያለውን ለማድረግ የሚለፋ ሰው ነው and I respect that ❤

Address

Soyama, Burji Manyatta
Eastern

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Burji united posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Share

Category


Other Eastern media companies

Show All

You may also like