Ethiopia Informer

Ethiopia Informer መልካምነት ሕያውነት
(2)

02/12/2023

በአማራ ክልል አምቡላንስ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ንጹሐን ተገደሉ 🚨

01/12/2023

ሶስት አጫጭር የሰበብአዊ መብት ጥሰት መረጃዎች

#ተዋህዶ

የተዋህዶ ምእመናን እና አማራ የሆኑ በግፍ መገደላቸው ተገለጸ✍🏽በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከ 36 የሚበልጡ የተዋህዶ ምእመናን በግፍ መገደላቸው ተገለጸ። ✍🏽የአማራ ማህበር በአሜ...
30/11/2023

የተዋህዶ ምእመናን እና አማራ የሆኑ በግፍ መገደላቸው ተገለጸ

✍🏽በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ከ 36 የሚበልጡ የተዋህዶ ምእመናን በግፍ መገደላቸው ተገለጸ።

✍🏽የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) ደግሞ ጭፍጨፋው ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ አረጋግጧል።

✍🏽ከህዳር 12 2016 ዓ.ም ጀምሮ በኦነግ ታጣቂዎች በመድሃኒአለም እና በሴሮ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን በተፈጸመ ጭፍጨፋ ከ 36 የሚበልጡ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸው ተዘግቧል።

✍🏽በጭፍጨፋው የተገደሉ ሰዎች አስክሬን የሚያሳይ ቪድዮም በሶሻል ሚድያ እየተዘዋወረ ይገኛል።

✍🏽በስፍራው የሚገኙ ምእመናን የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ይገኛሉ።

✍🏽የአማራ ማህበር በአሜሪካ (AAA) “በቀን 12፣ ህዳር 2016 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ቶሌ-ዲገሉ-ቡና ቀበሌ፣ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ኦነግ ሸኔ) ታጣቂዎች ከ18 በላይ የአማራ ተወላጆችን መጨፍጨፋቸውን ከምንጮች አረጋግጧል።” ሲል በሪፖርቱ ገልጿል።

ምንጭ ፡ AAA, Mahibere Kidusan, Dere news, Mereja Tv

ኢትዮጵያ ኢንፎርመር
ህዳር 20, 2016 ዓ.ም
…..*****…..

እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል 🙏🏽 📌ሰከን ብዬ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የተናገሩትን ተመልክቻለው::📌የአማራ ህዝብ በድሮን ሲደበደብ አፋቸውን ዘግተው የሚያዩት ሰውን ለመከፋፈል ግን የፈጠኑ...
21/11/2023

እውነት እና ንጋት እያደር ይጠራል 🙏🏽

📌ሰከን ብዬ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ የተናገሩትን ተመልክቻለው::

📌የአማራ ህዝብ በድሮን ሲደበደብ አፋቸውን ዘግተው የሚያዩት ሰውን ለመከፋፈል ግን የፈጠኑት እኚ የአማራ ቲቪ ጅላንፎዎች ለሴራ እንዲመቻቸው የአባታችንን ሀሳብ ቆራርጠው አቅርበዋል::

📌📌የአባታችንን ሙሉ ሀሳብ ለመረዳት

North Wollo Diocese Media ላይ የቀረበውን የ 1 ሰአት እና

ትናንት ከደሬ ኒውስ (Dere news) ጋር ያደረጉትን የ 30 ደቂቃ ቆይታ መመልከት ያስፈልጋል::

📌በመከላከያ በኩል የተሰራውን ግፍ በድፍረት አጋልጠው ሰዎች በግፍ መረሸናቸውን እና የሱቆችን ዘረፋ ኮንነዋል ቢቻል ጦርነቱን ቢያቆሙ ባይቻል መከላከያ ከባድ መሳርያውን ከቤተክርስቲያኑ እንዲያርቅ ጠይቀዋል:: በምርኮኛ አያያዝ አለም አቀፍ ህግ አክብሩ ብለዋል::

📌የፋኖ ጥያቄ በመንግስት የውንብድ እና የሽብር ቡድን እንዳለው ሳይሆን ልጆቻችን የፍትህ እና የመገፋት ጥያቄ ስላለባቸው የሚጠይቁትን መልሱላቸው ብለው በድፍረት ተናግረዋል:: ፋኖም ከቤተ ክርስቲያን እንዲርቅ ጠይቀዋል:: በደል ያሉትንም አንስተው ኮንነዋል::

📌እኔ ወንድም ከወንድሙ ልጅ ከአባቱ ከዚና ከዝያ ሆኖ ይዋጋ አልልም ብለዋል:: መስቀል እንደያዘ የክርስቶስ ባርያ ሁሉም ልጆቼ ናቸው ያጠፋው ይታረም እንጂ እርስ በርስ ተገዳደሉ አልልም ብለዋል:: ይሄ እንግዲህ ፋኖን ለምንደግፍም መከላከያ ወደ ፊት ለሚልም ለሁለቱም ወገን የሚጎረብጥ ሀሳብ ሊሆን ይችላል::

📌በርግጥ በግሌ ብዙ ያልተመቹኝ ነገር አባታችን ቢናገሩም ግን አባት ናቸውና ማጤን ያስፈልጋል:: ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ንግግር ባንናገር መልካም ነው:: ድል ለፋኖ ስለምንል አባቶችም በፊት ለፊት ወጥተው ድል ለፋኖ ካላሉ ማለት ትንሽ አይከብድም ?:: ብቻ የሀይማኖት አባትነታቸውን ድንበርም ማክበር አለብን ባይ ነኝ::

📌የስጋ አባትህ ቢያስከፋህ ቀና ብለህ አባትህን እንዲ የምትሰድብ ነህን ? ሰድበህም ለሰዳቢ የምትሰጥ ነህን? ከሆንም አንተ አባትህን የማታከብር ባለጌ ልጅ ትባላለህ:: ለስጋ አባታችን እንዲ ከሆንን ለመንፈስ አባቶቻችንስ ? ግን እውነት አባቶቻችንን በዚህ ደረጃ መስደብ ከወዴት ተማርን ?::

📌በዚህ ወቅት እንደ አናቶቻችን እየተፈተነ ያለ የለም:: በሁለት በኩል ሁሌም ጫና አለባቸው:: ወደ አንዱ እንዳያደሉ የነፍስ አባቶች ናቸው:: ለምድር እንዳያስቡ የሰማይም እዳ አለባቸው:: ጫናው ከባድ ነው:: እኛ ያልነውን ብቻ ካላሉ ብለን ለዝያውም ብጹአን ጳጳሳትን ማብጠልጠል ነውር ነው::

📌በርግጥ አባታችን ካነሱት አንጻር የተለየ ሀሳባችንን በጨዋ ደንብ መጠየቅ ተገቢ ነው:: በተለይ መከላከያ በአንድ ብሔር እየተመራ በሌላው ብሔር ላይ በደል መፈጸሙ ተገቢነት እንደሌለው የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በጨዋ ደንብ የሞገታችሁ እያየናችሁ ነውና ትመሰገናላችሁ🙏🏽::

📌ዘመድኩንም እሱ የተተቸበትን ቆርጦ አውጥቶ ሲወርፋቸው ነበር:: እሱም ሲተች ነው የሚውለው ዘመዴም ሰው ስለሆነ ፈጣሪ ስላልሆነ የሰራ ሰው ሊወቀስ ሊገሰጽ ይችላል:: አባታችን እንዴት ይሄን ሊሉ ቻሉ ብሎ አንዳንዴ እራስንም መመልከት እንጂ እኔ ብቻ ልክ ነኝ ብሎ አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ መስጠት ባይኖር መልካም ነው ባይ ነኝ::

በቀረውስ እግዚአብሔር የጎደለንን ሁሉ ይሙላበት በጭንቅ ላሉት ወገኖቻችን እረፍትን ይስጣቸው 🤲🏽

ኢትዮጵያ ኢንፎርመር
ኅዳር 21, 2016 ዓ.ም
…..*****…..

20/11/2023
20/11/2023

አብይ አህመድ በጀርመን ፋሺት ተባለ ተቃውሞ ገጠመው

📌ኢትዮጵያውያን የብልጽግናን መንግስት በተለይም በአማራ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ በመቃወም

በጀርመን በርሊን
በእንግሊዝ ለንደን
በስዊድን ስቶኮልሆም
በኖርዌይ ኦስሎ
በዋሽንግተን ዲሲ እና በሌሎችም የአለም ክፍሎች ድምጽ አሰምተዋል::

📌በጀርመን በርሊን ጠቅላዩ ለስብሰባ በተገኙበት ወቅት ነው ሀገር ወዳዶቹ ተቃውሞ ያሰሙት::

ኅዳር 10, 2016 ዓ.ም
ኢትዮጵያ ኢንፎርመር
Ethiopia Informer
…..*****…..

Indirizzo

Trento

Notifiche

Lasciando la tua email puoi essere il primo a sapere quando Ethiopia Informer pubblica notizie e promozioni. Il tuo indirizzo email non verrà utilizzato per nessun altro scopo e potrai annullare l'iscrizione in qualsiasi momento.

Video

Condividi


Altro Agenzia media/stampa Trento

Vedi Tutte