Jah Love Rasta

Jah Love Rasta ልብ ለልብ

10/10/2022

✍️...ስድ ቃላት....!!

ውዴ.......!

ገፅሽን ሳዬው - ፃዳ ንፂት ውሀ
ገጣሚው ልቤን - ጠራው እንደገና
ቃላትን ሰክቼ - ልኳትን ብል ድንገት
ከንፈርሽ ይጣራል....
አውርዶ ሊጥለኝ - ባፍቃሪ ሰው አቀበት...!!

//
ወረድኩት....
ወጣሁት....
//
. .
. .
. .

ወተን ካየንማ - ቁልቁልና አቀበት
እዘልቀው ጀመረ - ባዝማሪ ሰው ቅኝት

//
ተቀበል....
//

" ቢዘርፉበት ቅኔ - ብሶትና መርዶ
ተመልሶ ይመጣል - የሰው ደስታ ሽሮ
ከንፈሯ ተበልቶ - አይኗም ካጠገበ
እሷን እ'ማይመኝ - ሞኝ ሰው የታለ..?!!...."
.
.
.
----//---
አዝማሪው....አንተ ራስህ ተቀበል...!!
//

"....አዝማሪ በቅኔ - ካላት ቆንጆ ሴት
እኔስ ምኔ ሞኝ ነው - ቀምሼ አየሁት....?
በስሜት ሲቃ ውስጥ - ይገጠማል ግጥም
ቃል ሚበላ ከንፈር - እንዴት አርጎ ይጥም...?!
ብወጣው ብወርደው - አላልቅ ቢል ፍቅር
ጠረንሽ ተሰማኝ - አሁንም ከንፈርሽ ስር......"
.
.
.
"...የኔ ቃል ስድ ነው - ገብቷል አንገትሽ ስር
እየማገ ሳበው - ወዝሽ አለው ደምስር
ለሆሳስ ያበዛል - ሲቀምስ የሰው ፍቅር
መዳፌን አዞርኩት - ከፀጉርሽ ሀረግ ስር...."

...........//.........
አያልቅበት የለ.....
የኔ ቃል ተነሳ - ግጥሙን ሰድሮ.......
በጉንጮችሽ ድግስ - ትንሽ ተንፈስ ብሎ
ቃላትን ቀጠለ - አይንሽን አሻግሮ.

ውዴ......
እንዲህ በፍቅር አይን - ያየሽው የልብ እዳ
መናገር አቃተው - ቀልቡን አርጎት ዲዳ
ትንሽ አየሽና - እንደምንም ብሎ
ተደፍቶ አለቀበት - ቃልም እንደቆሎ!!
//
ትኩር ብሎ አየሽና....
//
ደርሶ ቢመስለው - ፍቅር ሚተፋ
የልብን ቀዳዳ - ፈልጎ ሚሰፋ....

//
ድንገት ቢመስለው.....
//

በፍቅር ወደሽው - እንዲ አድርጎ ካየሽ
ባታውቂ ነው ጂ - ጉድ ያስብላል አይንሽ።

ስድ ቃላት....!!

@ኤፍታህ

07/09/2022
29/04/2021

Address

West Wellow

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Jah Love Rasta posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share