አቢሲኒያ ሚዲያ - Abyssinia Media

አቢሲኒያ ሚዲያ - Abyssinia Media Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from አቢሲኒያ ሚዲያ - Abyssinia Media, Media/News Company, 29 Newport Street, Stoke-on-Trent.

እስካሁን ሀያልና አደጉ የሚባሉ አገሮች አንድ መዝሙርና አንድ አርሚ አንድ ሰንደቅ ነው ያላቸው። የተለያየ ክልል እምነት ቋንቋ ግን አላቸው። የኛኮ ወይ እንደሰለጠነው አለም አላደግን፣ ወይም ...
09/12/2022

እስካሁን ሀያልና አደጉ የሚባሉ አገሮች አንድ መዝሙርና አንድ አርሚ አንድ ሰንደቅ ነው ያላቸው። የተለያየ ክልል እምነት ቋንቋ ግን አላቸው። የኛኮ ወይ እንደሰለጠነው አለም አላደግን፣ ወይም ከነሱ ልመናና ባርነት አሎጣን፧ የምንከተለው ሁሉ እነሱ ንቀውና ጠልተው የተውትን ነው። ቢያን የሰው ልጅ የሚኖረውን የተሻሻለ ኑሮ እንኳን ለመኖር አንስማማም። ኢትዮዽያ ውስጥ ስንት ሰንደቅ ስንት መዝሙር እንዳለ ሲታሰብ ይች አገር በመቸው ዘመን ዜጎቿን የተሻለ ኑሮ ማኖር እንደምትች ማሰቡ ከባድ ነው። ለዚህ ሁሉ ችግር ግን በአለማቀፍ የፖለቲካ
መር ወስጥ የተጠላውን የዘር ፖለቲካ የሚሰብኩ ልጆቿ ናቸው እንዲህ የሚያሰቃዮን።

ሱሌማን አብደላ

ሰበር ዜና!የኬኒያው መሪ ኤርትራ አስመራ ገቡ!የደቡብ አፍሪካውን የፌደራል መንግስትና የህወሃት ሃይሎች ስምምነት ተከትሎ ወታደራዊ አመራሮቹ የተገናኑባት ኬኒያ አዲሱ ተመራጭ ዊሊያም ሩቶ በዛሬ...
09/12/2022

ሰበር ዜና!
የኬኒያው መሪ ኤርትራ አስመራ ገቡ!

የደቡብ አፍሪካውን የፌደራል መንግስትና የህወሃት ሃይሎች ስምምነት ተከትሎ ወታደራዊ አመራሮቹ የተገናኑባት ኬኒያ አዲሱ ተመራጭ ዊሊያም ሩቶ በዛሬው እለት ኤርትራ አስመራ መግባታቸውንና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሞቅ ያለ አቀባበል እንዳደረጉላቸው አሳውቀዋል።
ለምን ገቡ የሚለው እስካሁለቱም አካል የተባለ ነገር የለም።

ታግዷል!! በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት መታገዱን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡በከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ...
09/12/2022

ታግዷል!!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት መታገዱን የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በከንቲባ ጽህፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ በአዲስ አበባ ከተማ ከሕዳር 29 ቀን 2015 ጀምሮ ማንኛውም የቋሚ ንብረት ስም ዝውውር አገልግሎት በጊዜያዊነት ታግዷል፡፡

አገልግሎቱ የታገደው በከተማዋ ህገ ወጥነትን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሒደት ውጤታማ ለማድረግ መሆኑን ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ለሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ለሚመለከታቸው አካላትም የተላለፋው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲሆን ትዕዛዝ መሰጠቱን ነው የገለጹት፡፡

(ኤፍ ቢ ሲ)

🙏ኳታር🇶🇦 የገነባችውን ስታዲየም🏟️ማፍረስ ጀመረች‼️👉 ኳታር🇶🇦 ለዓለም ዋንጫ ውድድር ካዘጋጀቻቸው ስምንት ውብ ስታዲየሞች መሀከል አንዱ የሆነውና 40,000 ተመልካችን እንዲይዝ ተደርጎ፤ የ...
09/12/2022

🙏ኳታር🇶🇦 የገነባችውን ስታዲየም🏟️ማፍረስ ጀመረች‼️

👉 ኳታር🇶🇦 ለዓለም ዋንጫ ውድድር ካዘጋጀቻቸው ስምንት ውብ ስታዲየሞች መሀከል አንዱ የሆነውና 40,000 ተመልካችን እንዲይዝ ተደርጎ፤ የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ የመደወያ ኮድን መሠረት አድርጎ በ974 ኮንቴይነሮች በጊዜያዊነት የተገነባው፤ ለጠቅላላ ግምባታው 717 ሚሊየን ዶላር ወጪ የተደረገበት፤ በዓለም ዋንጫው የውድድር መርሐግብር ላይም፦

ሜክሲኮ🇲🇽 ከ ፖላንድ🇵🇱
ፖርቹጋል🇵🇹 ከ ጋና🇬🇭
ፈረንሳይ🇫🇷 ከ ዴንማርክ🇩🇰
ብራዚል🇧🇷 ከ ስዊዘርላንድ🇨🇭
ፖላንድ🇵🇱 ከ አርጀንቲና🇦🇷
ሰርቢያ🇷🇸 ከ ስዊዘርላንድ🇨🇭
ብራዚል🇧🇷 ከ ደቡብ ኮሪያ🇰🇷 ጋር ያደረጉትን ጨዋታዎችን ያስተናገደው #974 የተሰኘው ስታዲየምን ከትላንት ምሽት ጀምሮ ማፍረስ የጀመረች ሲሆን፤ እነዚህ ኮንቴነሮች ለታዳጊ ሀገራት በእርዳታ ይሰጣል ተብሏል።

ሰበር ዜና!በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን ግጭት ላይ ዋና ተሳታፊዎች “ሸኔ” እና “የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ!የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል በወ...
07/12/2022

ሰበር ዜና!
በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን ግጭት ላይ ዋና ተሳታፊዎች “ሸኔ” እና “የአማራ ታጣቂዎች” ናቸው ሲል ኢሰመኮ ገለጸ!

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞኖች ውስጥ ባጋጠመው ግጭት ዋነኛ ተሳታፊዎች “ሸኔ” እና “የአማራ ታጣቂዎች” መሆናቸውን ገልጿል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት በተለይ በምሥራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖች ብሔር ተኮር በሆኑ ጥቃቶች በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ መፈናቀላቸው እየተገለጸ ይገኛል።
የኢሰመኮ የምርምርና ክትትል ሪጅናል ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታ ለቢቢሲ እንደተናገሩት “በሰላማዊ ሰዎች ላይ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ውስጥ በዋነኝነት እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ቡድን እና የአማራ ታጣቂዎች ዋነኞቹ ተሳታፊዎች ናቸው” ብለዋል።
ኢማድ ግጭቶቹን ተከትሎ ባለፉት ቀናት የደረሰውን የጉዳት መጠን ለማወቅ ማጣራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።
“ሰዎች በማንነታቸው ዒላማ ተደርገው ጥቃት እንደሚደርስባቸው ያሰባሰብናቸው መረጃዎች እና ማስረጃዎች ያሳያሉ” ያሉት የምርምር እና ክትትል ዳይሬክተሩ፤ ከሰሞኑ የተፈጸሙት ጥቃቶች መጠን ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ጨምረው ገልጸዋል።
ባለፉት ቀናት ያጋጠመው ችግር “ከዚህ በፊት ከተፈጸሙት ጥቃቶች ከፍ ያለ ሊሆን እንደሚችል” በተለያዩ መንገዶች ያስባሰቧቸው መረጃዎችን እንደሚጠቁሙም ጨምረው አስረድተዋል።

ነገሮች እንደ ሬት ምርር ቁምጥጥ ብለዋል"ሲኦልን አሳይተን እንመልሳቸዋለን" ሃያላኑወገብ ሰባሪ ሰበር ዜናዎች ከሃያላኑ ጓዳ እንደ ጅረት ፈሷል . . .>ምን እንደያዙ ያልታወቁ የሩሲያ የጦር ...
06/12/2022

ነገሮች እንደ ሬት ምርር ቁምጥጥ ብለዋል
"ሲኦልን አሳይተን እንመልሳቸዋለን" ሃያላኑ
ወገብ ሰባሪ ሰበር ዜናዎች ከሃያላኑ ጓዳ እንደ ጅረት ፈሷል . . .

>ምን እንደያዙ ያልታወቁ የሩሲያ የጦር አውሮፕላን ድንበር ላይ አድፍጠዋል
>የአሜሪካ ጦር ያበጠው ይፈንዳ ሲል ለቻይና ጦር ተዘጋጅቻለሁ ብሏል
>ደርባባው ሺ ጂምፒንግ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው ብቅ ብለዋል!

በሆዳቸው ምን አይነት የሞት መላክ እንዳቀፉ ያልታወቁ የሩሲያ ተዋጊ ጄቶች በዩክሬን ድንበር ላይ ሰፍረው አንዲት ትዕዛዝ እየተጠባበቁ መሆኑን ጀርመን ሚዴይ ሜዴይ የአደጋ ጩሕቷን እያሰማች አለቱና የበረዶው ድብ ፑቲን ሌላ እልቂት ሊያወርድ ነው ብላ ከተፍ ስትል የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሹልዝ ወዲያው ቀዝቃዛው የአለም ጦርነትን ለማስጀመር ከበሮ የምትደልቁ ይበቃቿላ ሲሉ አዛውንቱ ጆባይደንን በፊት ጠረባ ብለው ከተፍ ብቅ ብለቃል። ደርባባው ዢ ጂምፒንግ እሳት ለብሰው እሳት ጎርሰው በቁም ሞተናል ሲሉ የአውስትራሊያን ጦር መጣውልህ ብለዋል። የአሜሪካዋን አፈጉባኤ አይተው የአውስትራሊያ ህግ አውጪዎች የቻይናን ማስጠንቀቂያ በካልቾ ጠልዘው የአርማጌዶን መነሻ ወደምትባለው ታይዋን መግባታቸው ታውቋል።

ወዲያ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደረም ያለው የአሜሪካ ጦር ፔንታጎን ራዳር የማያውቀው መልኩን አሳምሮ ሞት የሚተፋ ተዋጊ ጄቱን ከጓዳው መዘዝ አድርርጎ ወደ ደርባባው ሺ ጂምፒንግ አጥለቅላቂው የቻይና ጦር ላይ ዝቷል። ሳልሞት በቁሜ ቻይና በቀጠናው አዛዥ አትሆንም ያለው የአሜሪካ ጦር ቻይናን ለማስቆም ጦሩ መዘጋጀቱን በመግለጽ ውረድ እንውረዱን ከአጭሩ ኪም ኮሪያ ሰርጥ አጠገብ በደቡብ ቻይና ሰርጥ ላይ ይዋጣልን ብሏል። በጥቁር ባሕርና በደቡብ ቻይና ምድር የማትገላገለው ምጥ እንዲህ ሲያደርጋት የባስ አታምጣ እንዲሉት የገሃነሙ ጦርነት ይጀመራል ስትል ለእስራኤል ስለቷን የምታሾረው የአያቶላዎቹ ኢራን ዛሬ የእሳሬል ሰላዮችን ይዛ በገመድ አጠልጥላ መግደሏን ይደርስ ለቴላቩቩ ግልባጩ ለዋሽንግተን ያለችበት ጉድ አሰምታለች። ይሄን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር ከእስራኤል ጦር ጋር የጋራ ወታደራዊ ልምምዱን ወደ ተግባር አውርዶ 1 ኢራንን በመካከለኛው ምስራቅ ምድር ለመግጠም ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱን ተያይዞታል።
>an

አለማድነቅ ይከብዳል የ42 አመቱ መምህር ዶ/ር አብዱልማሊክ በኬራላ ግዛት ወደምትገኘው በመምህራን እጦት ወደ ምትሰቃየው ትንሽ ትምህርት ቤት የሚሄደው በየቀኑ እስከአንገቱ ድረስ በሚያሰምጥ ጭ...
06/12/2022

አለማድነቅ ይከብዳል

የ42 አመቱ መምህር ዶ/ር አብዱልማሊክ በኬራላ ግዛት ወደምትገኘው በመምህራን እጦት ወደ ምትሰቃየው ትንሽ ትምህርት ቤት የሚሄደው በየቀኑ እስከአንገቱ ድረስ በሚያሰምጥ ጭቃማ ወንዝ ውስጥ በመዋኘት እያቋረጠ ነው! በውጤቱም ለአንድም ቀን ቀርቶም ሆነ አርፍዶ አያውቅም!

በቫሌንሲያ ማራቶን አትሌት አመኔ በሪሶ አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች አትሌት አመኔ በሪሶ በስፔን ቫሌንሲያ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች፡፡...
04/12/2022

በቫሌንሲያ ማራቶን አትሌት አመኔ በሪሶ አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች

አትሌት አመኔ በሪሶ በስፔን ቫሌንሲያ በተካሄደው የማራቶን ውድድር አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈች፡፡

በዛሬው የስፔን የቫሌንሲያ ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት አመኒ በሪሶ ርቀቱን በ 2 ሰዓት 14 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመጨረስ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግባ አሸንፋለች።

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ደግሞ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ በመግባት የራሷን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ውድድሩን በሁለተኝነት አጠናቃለች፡፡

ዜና እረፍትየኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን  ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።EOTC
03/12/2022

ዜና እረፍት

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።

EOTC

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን ያሸነፈችጥቁር አፍሪካዊት አገር ካሜሮን ሆናለች። አፍሪካዊያን ዛሬ በካሜሮን ኮርተዋል። አለም አዲስ ታሪክ ፅፏል። የአቡበከር እግር በታሪክ አጋጣሚ በሆነ ደቂ...
03/12/2022

በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ብራዚልን ያሸነፈች
ጥቁር አፍሪካዊት አገር ካሜሮን ሆናለች። አፍሪካዊያን ዛሬ በካሜሮን ኮርተዋል። አለም አዲስ ታሪክ ፅፏል። የአቡበከር እግር በታሪክ አጋጣሚ በሆነ ደቂቃና ሰከንድ ቅፅበት ውስጥ ይችን ታሪክ ሰርቷል።

ሱሌማን አብደላ

ሰበር ዜና!የሩሲያና ቻይና ጦር በኒውክለር ቦምብ ጣይ የታጀበ ግዙፍ ወታደራዊ ልምምድ አደረጉ!ኔቶም እጅግ አስፈሪ የተባለለት የኒውክለር የጦር ልምምድ አድርጓል!ከሰሞኑ የኔቶ ጦር አስደንጋጭ ...
30/11/2022

ሰበር ዜና!
የሩሲያና ቻይና ጦር በኒውክለር ቦምብ ጣይ የታጀበ ግዙፍ ወታደራዊ ልምምድ አደረጉ!
ኔቶም እጅግ አስፈሪ የተባለለት የኒውክለር የጦር ልምምድ አድርጓል!

ከሰሞኑ የኔቶ ጦር አስደንጋጭ የተባለለትን የኒውክለር ጦር ልምምድ ማድረጉን ተከትኮ የሩሲያና ቻይና ጦር የኔቶ ጦር ግዙፍ ሃይል በሰፈረበት ፓስፊክ ሰርጥ ላይ ከሩሲያ የሞት ጓዳ 11ኛው ሰዓት ላይ የሚወጣውን ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ጨምሮ ራዳር አፍዝ አደንግዞቹ የጦር ጄቶችን ያቀፈ ግዙፍ ወታደራዊ ልምምድ ማድረጋቸው ነው የተሰማው። የአሜሪካ ጦር ፔንታጎን ትላንት በሰጠው መግለጫ የቻይና ጦር የኒውክለር ምርቱን ከወትሮ በተለየ ሁኔት እያመረተ መሆኑን ገልጾ ቻይና እስከ 2035 የኒውክለር አየረር ብዛቷን በእጥፍ ልትጨምር እንደምትችልና በዚህም በቀጠናው ላይ ከባድ ስጋት እንደሚፈጠር ጠቁሞ በሕግ አምላክ ብሏል። ይህ በእንዲህ ሳለ አውሮፓ ህብረትና ኔቶ "ፑቲን አጥንት ሰባሪውን ክረምት እንደመሳሪያ እየተጠቀመበት ነው" ሲሉ ዩክሬን በጨለማ መዋጧን በመጥቀስ በጦር ወንጀል ሩሲያ እንድትጠየቅ በመግለጫቸው ጠይቀዋል። በሩሲያ በኩል መፍትሄው ያለው በዩክሬን እጅ ነው የሚል ምላሽ ነው የተሰማው።
>Esube Negn Erase

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የሚያደርገውን ክትትል እና ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል  የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡***   በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በጦር መሳሪያ ዝውውር በተጠረ...
29/11/2022

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የሚያደርገውን ክትትል እና ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
በተለያዩ ክፍለ ከተሞች በጦር መሳሪያ ዝውውር በተጠረጠሩ ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 9 ሽጉጦች እና በተሽከርካሪ ውስጥ ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ 16 ቦንብ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ከነተጠርጣሪዎቹ ተይዘው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 እና 14 ከህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ጋር በተያያዘ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው ህብረተሰቡ በሰጠው ጥቆማ እና በፖሊስ ክትትል በተጠቀሱት ወረዳዎች ነዋሪ በሆኑ እና በወንጀሉ በተጠረጠሩ 2 ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በተደረገ ብርበራ 5 የተለያዩ ሽጉጦች እና 53 ልዩ ልዩ የሽጉጥ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሚኪሊላንድ ኮንደሚኒየም ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል 4 ሽጉጥ ከ30 መሰል ጥይት እና 1 የእጅ ቦንብ በብርበራ ተይዟል፡፡ በዚህ ወንጀል የተጠረጠሩ 4 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በተለምዶ ፊናንስ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረጉት ክትትል የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 5-01928 አ.አ በሆነ ፒካፕ ተሽከርካሪ አካል ውስጥ ተደብቆ ሲጓጓዝ የነበረ 15 የእጅ ቦንብ ከ3 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በአጠቃላይ 16 የእጅ ቦንብ፣ 9 ሽጉጥ እና 83 የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶችን ከ11 ተጠርጣሪዎች ጋር ይዞ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የገለፀው የአዲስ አበባ ፖሊስ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ላይ የሚያደርገውን ክትትል እና ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ እያስታወቀ ህብረተሰቡ አሁንም አካባቢውን ከፀረ ሰላም ሃይሎች በንቃት እንዲጠብቅ እና ጥቆማና መረጃ በመስጠት ለፀጥታ አካላት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አቅርቧል

Addis Ababa Police

‹‹ለመሆኑ ሰው በአምላኩ የሚረካው መቼ ነው?››በማለት ቢጠይቃቸው፡፡‹‹በበረከቱ ግዜ የሚያገኘውን ደስታ በመከራው ጊዜመግለጥ ከቻለ በርግጥም በአምላኩ ረክቷል ማለትነው››፡፡"አል-ጋዛሊ"
29/11/2022

‹‹ለመሆኑ ሰው በአምላኩ የሚረካው መቼ ነው?››
በማለት ቢጠይቃቸው፡፡
‹‹በበረከቱ ግዜ የሚያገኘውን ደስታ በመከራው ጊዜ
መግለጥ ከቻለ በርግጥም በአምላኩ ረክቷል ማለት
ነው››፡፡

"አል-ጋዛሊ"

ሰበር ዜና!በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናት ተከበቡ "ከባድ ተኩስ ተጀምሯል"ሳይጠበቅ አልሻባብ በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናትን በመክበብ ከባድ ተኩስ ከፈተ!በሶማሊያ ሞቃድሾ በዚህ ሰዓት ባለስ...
27/11/2022

ሰበር ዜና!
በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናት ተከበቡ
"ከባድ ተኩስ ተጀምሯል"

ሳይጠበቅ አልሻባብ በስብሰባ ላይ ያሉ ባለስልጣናትን በመክበብ ከባድ ተኩስ ከፈተ!
በሶማሊያ ሞቃድሾ በዚህ ሰዓት ባለስልጣናቱ በተሰበሰቡበት ከየት መጣ ያልተባለ የአልሻባብ የሽብር ቡድን ቦታውን በመክበብ ከባድ የተኩስ ሩምታ መክፈቱን አልጄዚራን ጨምሮ አለም አቀፍ ሚዲያ በሰበር ዜና ዘግበዋል። በጉዳዩ ላይ ከዚህ በላይ ዝርዝር መረጃ ለመስጠትም አስቸጋሪ ነገር መፈጠሩን ዘገባው ጠቁሟል።

🖋በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል....🖋“ለመሆኑ ...ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”ጃንሆይም ቆፍጠን ባለ አነጋገር ለዛ... “ኢትዮጵያዊነት ኩራትና...
27/11/2022

🖋በአንድ ወቅት የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጠኛ ንጉሱን እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል....

🖋“ለመሆኑ ...ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? ”
ጃንሆይም ቆፍጠን ባለ አነጋገር ለዛ...
“ኢትዮጵያዊነት ኩራትና ትህትና ነው” አሉት።
ጋዜጠኛውም ቢሆን የዋዛ አልነበረምና......
“ይቅርታ ያድርጉልኝና ጃንሆይ ይሄ ሃምብልነስ እና ፕራውድነስ የሚሉት ነገር እርስ በርሱ የሚጣረስ ማንነት አይመስልዎትም?” የሚል ጥያቄ ያስከትላል።

🖋ንጉሱም እንዲህ አሉ .....“አየህ አንድ በጣም ተራ የምትለው ገበሬ ቤት በእንግድነት ብትሄድ ያለውን አብልቶ፤ እግርህን አጥቦ፤ ያጠበውን እግርህን ስሞ፤ አልጋውን ላንተ ለቆ እርሱ ግን መሬት ላይ ይተኛል። በዚያው ልክ በሚስቱ፣ በርስቱና በሃገሩ ላይ ብትመጣበት ደግሞ በግንባርህ ላይ ጥይት ይቆጥርልሃል፤ ስለዚህ አይጋጭም፤ ነገር ግን ይሄንን ነገር ለመረዳት አንተ ራስህ ኢትዮጵያዊ መሆን አለብህ” ነበር ያሉት።

ሰበር ዜና!በሀሰተኛ የሕክምና ት/ት ማስረጃ ተቀጥሮ የኹለት ሰዎች ህይወት ለሞት የዳረገው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺሕ ብር ተቀጣ!የጃዊ ሆስፒታል ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል...
26/11/2022

ሰበር ዜና!

በሀሰተኛ የሕክምና ት/ት ማስረጃ ተቀጥሮ የኹለት ሰዎች ህይወት ለሞት የዳረገው ግለሰብ በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በ5 ሺሕ ብር ተቀጣ!

የጃዊ ሆስፒታል ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው የሀሰት ዶ/ር ጌትነት ወንድ አወቅ የተባለው ተከሳሽ በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሳይማር በሜዲስን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማረ በማስመሰል በሀሰት በተዘጋጀ የዶክትሬት ሰርቲፊኬት የትምህርት ማስረጃ አቅርቧል።
በአብክመ ጤና ቢሮ ከ4/2/2014-4/2/2019 የሚያገለግል የሚል የሀሰት የሙያ ፈቃድ በመያዝ በአብክመ ጤና ቢሮ ሥር ባሉት ሆስፒታሎች በማችንግ ፈንድ ኘሮግራም በ(Junior General Medical practitioner) የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ 50% በማምጣት በደረጃ 14 ብር 9056 እየተከፈለው ሲሰራም እንደነበር ተገልጿል።
በህክምና የእውቀት ችግር ምክንያት በተፈጠረ ስህተት ሟች የተመኝ አምላክ የተባለችውን የ7 ወር ህፃን እና ሟች የኔወርቅ ደሳለው የተባለችውን የ25 ዓመት ወጣት ለሞት የዳረገ መሆኑምን ተመላክቷል።
በፈፀመው የሙስና ወንጀል መንግሥታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ ወይም በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል በዐ/ህግ ክስ ቀርቦበት በቀን 15/3/2015 ባስቻለው ዳንግላ ተዘዋዋሪ ችሎት በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 5,000 መቀጣቱን ከአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያን ዋብ አድርጋ አዲስ ማለዳ ለንባብ አብቅታለች።

የዓለም ዋንጫ ዕውነታዎች‼️ 👉 ቻምፒዮን ለሆነው አገር የሚበረከተው የመጀመርያው የዓለም ዋንጫ መጠሪያ የጁሊየስ ሪሜት ዋንጫ (Jules Rimet trophy) የሚሰኝ ሲሆን የተሠራውም እ.ኤ....
25/11/2022

የዓለም ዋንጫ ዕውነታዎች‼️

👉 ቻምፒዮን ለሆነው አገር የሚበረከተው የመጀመርያው የዓለም ዋንጫ መጠሪያ የጁሊየስ ሪሜት ዋንጫ (Jules Rimet trophy) የሚሰኝ ሲሆን የተሠራውም እ.ኤ.አ.1930 በፈረንሣዩ የቅርፃ ቅርፅ ባለሞያ አቤል ላፍለር ነው።

👉 የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 1930 የተካሄደ ሲሆን ፈረንሳይ እና ሜክሲኮ የኡራጓይዋ ዋና መቀመጫ በሆነችው በሞንቴቪዲ ተፋልመዋል። በዚህም ፈረንሳይ 4 ለ 1 በሆነ ውጥት አሸነፊ መሆን ችላለች።

👉 የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ግብም የተስተናገደው በዚሁ ተመሳሳይ ጨዋታ ወቅት ሲሆን ግቧን ያስቆጠረውም ፈረንሳዊው ሉሲየን ሎረንት ሲሆን ግቧ የተቆጠረችውም ከፍፁም ቅጣት ምት መስመር ውጭ በቮሊ ነበር።

👉 በ92 ዓመት የፊፋ የዓለም ዋንጫ የውድድር ታሪክ ውስጥ በመክፈቻ ጨዋታ የተሸነፈ አዘጋጅ ሃገር ባይገኝም የኳታር ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ግን በ2022ቱ የመክፈቻ ጨዋታ መጥፎ ታሪክ ለማኖር/ለመፃፍ ተገዷል።

👉 የመጀመሪያው ምንም ግብ ሳያስተናግድ ግጥሚያውን ያጠናቀቀው ግብ ጠባቂ (The first clean sheet) የዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካዊው ጂሚ ዳግላስ ሲሆን ጨዋታውም የ1930ው የዓለም ዋንጫ አሜሪካ ቤልጂየምን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት የረታችበት ነው።

👉 በዓለም ዋንጫ ታሪክ ውስጥ በቀይ ካርድ በመባረር የመጀመሪያ ተጫዋች ሆኖ የተመዘገበው የቺሊው ካርሎስ ካስሴሊ ሲሆን ወቅቱም በ 1974 ነበር።

👉 በአለም የመጀመሪያውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብ በመቀየር የቻለው ሜክሲኮአዊው ማኑዌል ሮሳስ ሲሆን ወቅቱም እ.ኤ.አ. ሰኔ 17 ቀን 1930 ነበር።

👉 የመጀመሪያው ተጨማሪ ሰዓት ታክሎበት የተከናወነ የአለም ዋንጫ ጨዋታ እ.ኤ.አ. ግንቦት 27 ቀን 1934 በኦስትሪያ እና በፈረንሳይን መካከል የተደረገው ነው። ይህ ጨዋታ የጥሎ ማለፍ ፍልሚያ ሲሆን በዚህም ውድድር ኦስትሪያ ፈረንሳይን በጭማሪው ሰዓት 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።

👉 የቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጭት በማግኘት ረገድ ቀዳሚው ስዊዘርላንድ ያዘጋጀችው የ1954ቱ የዓለም ዋንጫ ነው። ይህም እግር ኳስ በዓለም ዙሪያ ዝናው እንዲናኝ ትልቅ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

👉 በ 1970 የተከናወነው የዓለም ዋንጫ ቢጫ ካርዶችንና የተጫዋች ቅያሪን በማስተዋወቅ ረገድ ቀዳሚ ነው። የቢጫ ካርድ ማስጠንቀቂያ ለመቀበል የመጀመሪያው የቀድሞ የሶቪየት ሶሻሊስት ሪፐብሊክ ተጫዋች የነበረው ካኪ አሳሺያኒ ሲሆን ወቅቱም ግንቦት 31 ቀን 1970 እ.ኤ.አ ከሜክሲኮ ብሔራዊ ቡድን ጋር በተደረገ የእግር ኳስ ፍልሚያ ነበር። በዚሁ ተመሳሳይ ጨዋታ ሩሲያዊው ቪክቶር ሴሬብሪያኒኮቭ 46ተኛ ደቂቃ ላይ ተቀይሮ መውጣቱን የዓለም እግር ኳስ የታሪክ ሰነዶች ያወሳሉ። አናቶሊ ፑሳችም የመጀመሪያው ተቀያሪ በመሆን ይታወሳል። የሮማኒያው ስቲቭ አዳማኬም በኒኩላ ራዱካኑ በመተካቱ የመጀመሪያው ተቀያሪ ግብ ጠባቂ ለመሆን በቅቷል።

👉 በመለያ ምት የተጠናቀቀው የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ጨዋታ በፈረንሣይ እና በምእራብ ጀርመን መካከል እ.ኤ.አ. በ 1982 የተከናወነው ነው። ምእራብ ጀርመኖችም በግማሽ ፍፃሜው በመለያ ምት 5 ለ 4 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸው ይታወሳል። በዚህ ጨዋታ ሆርስት ህሩቤሽ የመጨረሻውን የመለያ ምት ወደ ግብነት በመቀር ጀርመንን አሸናፊ ማድረጉ ይታወሳል።

👉 ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉካ ፓግሊውካ በቀይ ካርድ ከሜዳ የተባረረ የመጀመርያው ግብ ጠባቂ በመሆን ይታወሳል። እ.ኤ.አ. ሰኔ 23 ቀን 1994 በተከናወነው የጣሊያን እና የኖርዌይ ጨዋታ ይኸው ግብ ጠባቂ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጪ በእጁ ኳስ በመያዙ ከ21ኛው ደቂቃ በኋላ ከሜዳ ለመውጣት ተገዷል።

👉 የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ወርቃማ ግብ (Golden Goal) ፈረንሳይያዊው ሎረን ብላንክ በሰኔ 28 ቀን 1998 ፈረንሳይ ፓራጓይን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በረታች ወቅት ማስቆጠሩ የሚታወስ ነው።

ኢ.ፕ.ድ

የጃፓን ብሔራዊ ቡድን ተጯዋቾች አለምን ካስደነቀውና በጀርመን ላይ ከተቀዳጁት የ 2 ለ 1 ድል በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ የተጠቀሙበትን መልበሻ ክፍላቸውን እንዲህ አፅድተው ነው የወጡት ‼️(ኢፕ...
24/11/2022

የጃፓን ብሔራዊ ቡድን ተጯዋቾች አለምን ካስደነቀውና በጀርመን ላይ ከተቀዳጁት የ 2 ለ 1 ድል በኋላ በስታዲየሙ ውስጥ የተጠቀሙበትን መልበሻ ክፍላቸውን እንዲህ አፅድተው ነው የወጡት ‼️

(ኢፕድ)

Address

29 Newport Street
Stoke-on-Trent
ST64BU

Telephone

+447931263739

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አቢሲኒያ ሚዲያ - Abyssinia Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to አቢሲኒያ ሚዲያ - Abyssinia Media:

Share