03/04/2022
መንግሥት ጽንፋኞች አመለካከት ማጠን አለበት !!
#መንግሥት ሰማያት ሰባክዮች ለምን ይጣላሉ?
#ምድር ጊዚያዊ መኖሪያ ነዉ እንጅ ዘላለማዊ መኖሪያ አይደለም ፡፡
1. መንግስት የመንግስትነት ሚናውን በትክክል መወጣት ሳይችል ሲቀር ህገወጥነትና ስርአት አልበኝነት መንሰራፋቱ የማይቀር ነው። የፖሊስና የመከላከያ ኃይሉ ከወገንተኝነት በፀዳ ጥፋተኞችን ማስታገስ ሳይችል ሲቀር ከዛም አልፎ ለህገወጦች ከለላ ሲሆን ደግሞ አደጋው የከፋ ይሆናል። ህዝብም ፍትሃዊ በመሰለው መንገድ መብቱን፣ ንብረቱንና ሃልውናውን ለማስከበር የየራሱን መንገድ መከተል ይጀምራል። ይህ ደግሞ ሃገራችንን ወደ አደገኛ እርስ በርስ ጦርነት ሊያመራት ይችላል። እናም መንግስት ህዝባዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል። የተበደለ ሁሉ "መንግስት አለልኝ" ሲል በዳይ ሁሉ "መንግስት አለብኝ" ሲል ያኔ ህገ ወጥነት ቦታ ያጣል።
2. ሃገራችን ያለችበትን ተጨባጭ ግምት ውስጥ በማስገባት ህዝባችን የጥፋት ፊታውራሪዎችን ትንኮሳ ጆሮ ሊነሳ ግድ ይላል። ይህንኑ ሲያደርግም ቆይቷል። በሰላም እጦት አትራፊ እንደሚሆኑ የሚያስቡት ወጥመዳቸውን እዛም እዚህም መዘርጋታቸው አይቀርም፤ ህዝብ ግን በሰላም እጦት የመጀመሪያው ተጎጅ ነውና ወጥመዳቸውን ከመበጣጠስ ውጭ የተሻለ አማራጭ የለውም።
3. ኢትዮጵያ ከሌሎች የዓለማችን ሃገራት የተለየች አይደለችም፤ የተፈጥሮ ህጎች በሌሎች ሃገራት ላይ ተግባራዊ እንደሚሆኑት በኢትዮጵያም ላይ ይሆናሉ፤ ለኛ ሲባል የሚታጠፍ ተፈጥሯዊ ስርዓት የለም። ፍትህ መሰርታዊው ህግ ነው። ፍትህ በእጅጉ ሲዛባ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል ዓለማችን በርካታ ምሳሌዎችን አዝላለች። የታሪክ እምብርት የሆኑ ሃገራት ወደ ፍርስራሽ ክምርነት ተቀይረው አይተናል፣ በተፈጥሮ ሃብት የታደሉ ሃገራት የጦርነት አውድማ ሆነው አስተውለናል። "ኢትዮጵያ አትፈርስም" ከሚል እሳቤ ወጥተን የማህበረሰብ ህልውና የሚረጋገጥባቸውን የተፈጥሮ ህጎች እንከተል፤ ያኔ ሃገራችንን ከጥፋት እንታደጋለን፤ ወደ እምርታ ጎዳናም እናመራታለን።
4. የሁሉም ኃይማኖቶች( በተለይም የእስልምናና የኦርቶዶክስ) የኃይማኖት አባቶችና ሰባኪያን በቅርበት የምር መነጋገር ያለባቸው ጊዜ ላይ ደርሰናል። የተጀመሩ ውይይቶች ተጠናክረው ይቀጥሉ። ይህችን ሃገር ለመታደግ የሚጠበቅባችው ቀናኢነት ብቻ ይመስለኛል። የጥላቻ ሰበካዎችን ማስቆም፣ ከፍትህ ጎን በጋራ መቆም፣ የተከታዬቻችውን ስነምግባር ማረቅ፣ ከጭፍን ተከታይነት ይልቅ ምክኒያታዊነትን ዋጋ የሚሰጡ ምእመናን ለማፍራት መትጋት ••• ለነገ የማይባሉ ስራዎች ናቸው። የኃይማኖት ሰባኪያን በወጣቱ አስተሳሰብ ላይ የሚያሳድሩት ተፅእኖ የላቀ ነውና ይህንኑ ተፅእኖ የመፍጠር አቅም ሃገርን ለመታደግ መጠቀም ይኖርባቸዋል።
5. የመገናኛ ብዙሃን የህዝብን ሃሳብ በመዘወር አቅማቸው አቻ አይገኝላቸውም። በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሺህ በላይ ህዝብ ያለቀበት የሩዋንዳው አስከፊ እልቂት መነሻ ለረጅም ጊዜ የተዘራውን የጥላቻ ዘር የለኮሰው አንድ የሬዲዮ ጣቢያ መሆኑን መርሳት የለብንም። እጣ ፋንታችንን እየቀረፁ የሚገኙት ማህበራዊ ሚዲያዎችም በጣቶቻችን ስር ያሉ ናቸው። ዘርና ኃይማኖት ሳንለይ ለፍትህ መቆምን እናስተምርባቸው፣ የምንኖርባትን መርከብ በጋራ የምንጠብቅባቸው መሳሪያዎች እንዲሆኑ እንስራ፣ ነውርን የሚፀየፍ ትውልድ ለመቅራፅ ነውርን ተፀይፈን እናሳይ። በመጨረሻም፣ የሚያደርጉት አያውቅምና ይቅር በላቸው
♥ እግ/ር ሆይ! ህዝባችናንና ሃገራችንን ጠብቅ!