ጥልቅ ምክር: ወደ ራስ መመልከት።
ወደ ልቦናችን እንመለስ፤ በጥልቀት ወደ ውስጥ እንመልከት።
ወልድያ ዩኒቨርስቲ ይሄን ተሞክሮ ቢወስድ
የወልድያ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ይሄን ተሞክሮ በመውሰድ ቢሰራበት ለአካባቢያችን ማህበረሰብ ጠቀሜታው የጎላ ነው።
ተከታዩ የአማራ ግብርና ምርምር ተቋም ዘገባ ነው።
¤ ¤ ¤
የደብረብርሃን ግብርና ምርምር ማዕከል በአለም አቀፍ ገበያ ተፈላጊ እና በስጋ ምርቱ ታዋቂ የሆነውን የዶርፐር በግ ዝርያ በማባዛት እና ከሀገረሰብ በጎች ጋር በማዳቀል የስጋ ምርታማነት እንዲያድግ እየሰራ ይገኛል፡፡ በሰው ሰራሽ ዘዴ ጨምሮ በማዳቀል ብዙ አርሶ አደሮች ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ምርምር ማዕከሉ እንደ ሀገር ዋነኛ ንጹህ የዶርፐር በግ ዝርያ የዘር ምንጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
ከሀገረሰብ በጎች ጋር የማዳቀል ስራው የሚሰራው በማዳቀል ዝርያን ለማሻሻል በጥናት በተለዩ አካባቢዎች ላይ ብቻ ሲሆን በመረጣ የዝርያ ማሻሻል ስራ በሚሰራባቸው አካባቢዎች የውጭ ደም ካላቸው በጎች ጋር ሳይዳቀሉ በራሳቸው ዝርያቸውን በመረጣ የማሻሻል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
ቪዲዮውን ይመልከቱ!
“ይህ የምታዩት ገደል የመሠለ ጉድጓድ በወልድያ ከተማ ደብረገሊላ ቴሌ ፊት ለፊት መሐል ፒያሣ የሚገኝ ነው።እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት አደጋ ከመድረሡ በፊት አንድ በሉት ።”
©Corep Corep
አዳጎ ውሃ ልማት ያለው ድልድይም በየቦታው የተቆፋፈረና ለአደጋ የሚያጋልጥልጥ በመሆኑ መፍትሄ ያሻዋል። የመንገድ ስራው ጋር በመነጋገር ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኝ ሊሰራበት ይገባል ስንል ጥቆማችንን እናቀርባለን።
Fikirte Woldesellasie Eskista
ባህሏን አክባሪ ፤ ኩሩ ወሎዬ @Fikirte Woldesellasie
ቆየት ያለ ለወልድያ የተዘፈነ ሸጋ ሙዚቃ !
ልሂድ በወልድያ ባዋጅ መንገሪያው፣
ወንዙ ጥቁር ውሃ፣ መቻሬ ሜዳው፣
ሰው ጠራኝ መሰለኝ አቤት ልበለው፣
የማሽላው አገር አላ ገዶ ነው፣
ጥንቅሹን ወልድያ ምን አበቀለው?
የአላ ገዶ ጥንቅሽ ወልድያ ካለማ፣
በል መርጠህ አምጣልን ለኛም የሚስማማ።
ድምፃዊ፣ ከበደ አሊ
ታዋቂዋ ተወዛዋዥ ኩሪባቸው ወልደማርያም በውዝዋዜ የተሳተፈችበት