WMCC

WMCC AddisWalta - AW
አዲስ ዋልታ
Walta Media and Communication Corporate Who We Are
Walta Media and Communication Corporate S.C.

(WMCC) is a broadcast media company based in Addis Ababa, the political capital of Africa. The company which owns TV and Radio Stations aspires to become a pan African media company currently disseminating information in local and international languages. Walta has built its reputation through covering all aspect of Ethiopia and beyond in its professional news, documentary and programs reporting.

Hard work, commitment to change, sincerity, customer respect, and respect to diversity are the hallmark of our institution. Since the founding of our corporation in 1986, we have been striving to be equipped with state-of-the-art media technology that tailored to the needs of 21 century media landscape. Major Functions
Apart from producing and disseminating professionally crafted news, documentary and programs through our broadcast stations and digital media platforms, our corporation is engaged in top notched research, public relations and event organizing, media training, digital signage, and outdoor advertising. For any inquiry you might have, please do not hesitate to reach out to us through the following contact address. If you wish to visit our head office physically, we are located on Sierra Leone Street/ Debrezeit Road, Behind Commercial Bank of Ethiopia Temenja Yaji Branch. Contacts
Head Office: +251114670303
Fax: +251114670302
Email: [email protected]
Customer Service
Cell: +251944959595
Office: +251114705971
Email: [email protected]
Fax: +251114670302
Documentary
Office: +251114704229
Program
Office: +251114704952
Human Resource
Office: +251114670453
Fax: +251114670302
TV News

Office: +251114707335
Email: [email protected]
Walta FM
Office: +251111552200
Email: [email protected]
Web and Social Media
Office: +251114704139
Walta SMS: 8970
Website: www.waltainfo.com
Facebook Amharic: https://bit.ly/3Ma7QTW
Facebook English: https://www.facebook.com/WMCC-English-108890734710426/
Facebook Arabic: https://bit.ly/3vmjIZR
Twitter Amharic: https://twitter.com/walta_info
Twitter Arabic: https://twitter.com/walta_arabic
YouTube: https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Telegram: https://t.me/WALTATVEth

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በዲያመንድ ሊግ 1 ሺሕ 500 ሜትር ውድድር አሸነፈችሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50:30 ...
20/04/2024

አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በዲያመንድ ሊግ 1 ሺሕ 500 ሜትር ውድድር አሸነፈች

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50:30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች።

በተያያዘ በ2024 የዲያመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በ5 ሺሕ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸንፏል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ርቀቱን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 12:58.96 ስዓት ፈጅቶበታል።

ውድድሩ ለ6 ወራት የሚቆይ ሲሆን አራት አህጉራት በ15 ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።

የፀረ-ሙስና ትምህርትን የስርዓተ ትምህርት አካል ለማድረግ የፖሊሲ ረቂቅ ተዘጋጀሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርትን የስርዓተ ትምህርት አካል ማድረግ ላ...
20/04/2024

የፀረ-ሙስና ትምህርትን የስርዓተ ትምህርት አካል ለማድረግ የፖሊሲ ረቂቅ ተዘጋጀ

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርትን የስርዓተ ትምህርት አካል ማድረግ ላይ ያተኮረ የፖሊሲ ረቂቅ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

ሀገር አቀፍ የፀረ-ሙስና ኮሚሺኖች የትስስር ጉባኤ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ በብሄራዊ የስነ-ምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ረቂቅ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በረቂቁ ላይ የስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትምህርትን የስርዓተ ትምህርት አካል ማድረግ ከፖሊሲው ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ መሆኑ ተነስቷል።

በውይይቱ ላይ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) የትምህርት ተቋማት በትምህርት ፖሊሲያቸው ውስጥ አካተው እንዲያስተምሩ የሚያደርግ ብሄራዊ የሆነ የስነ-ምግባር ግንባታ በትምህርት ሴክተር ውስጥ እንዲገባ ተግባብተን ውይይት ማድረግ አለብን ብለዋል።

ለፀረ-ሙስና ትግል ውጤታማነት ተቋማዊ አቅምን ማሳደግ፣ የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ትምህርትና ስልጠና ተደራሽነት ማስፋት፣ ከአህጉርና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እንዲሁም ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት እና ትስስር ማጠናከር በተጨማሪም ለፀረ-ሙስና ትግል የባለድርሻ አካላትን ትስስር እና ትብብር ማጠናከር ከተቀመጡት የፖሊሲው የትኩረት መስኮች መካከል ናቸው።

ኅብረተሰቡ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ የዳኝነት አካል፣ የፍትህ አካላት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ፣ ሚዲያዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት እና የትምህርት ተቋማት ፖሊሲውን የመተግበር ኃላፊነት ያለባቸው መሆናቸው በረቂቁ ላይ ተገልጿል።

የፀረ-ሙስና ተቋማት በነፃነትና ገለልተኝነት ሚናቸውን እንዲወጡ ለማስቻል፣ የሙስና ወንጀል ክስን በብቃት እንዲመሩና የመርታት አቅምን ለማሳደግ፣ የሚዲያና ሌሎች ቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ወቅታዊ መልዕክቶችን ለኅብረተሰብ ግንዛቤ በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ የስነ-ምግባር እና የፀረ-ሙስና ትምህርት በስርዓተ ትምህርቱ ለማካተት ፖሊሲው እንደሚያስፈልግ ነው የተገለፀው።

ማሕሌት መህዲ (ከአዳማ)

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገቡሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገብተዋል፡፡ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላ...
20/04/2024

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገቡ

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ሀዋሳ ገብተዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀዋሳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

በሀገር ደረጃ የተተገበረው የሌማት ትሩፋት ሥራ ያለበትን ደረጃ በሀዋሳ ለመገምገም የክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እና የከተማ አስተዳደር ከንቲባዎችም እየገቡ ነው።

20/04/2024

"አስተውሎት" - በቅርብ ቀን ይጠብቁን!

አየር መንገዱ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው በረራ ሊጀምር ነውሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው...
20/04/2024

አየር መንገዱ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው በረራ ሊጀምር ነው

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ፖላንድ ዋና ከተማ ዋርሶው አራት ሳምንታዊ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል፡፡

ዋርሶው በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኒስኮ) የተመዘገቡ ቅርሶች መገኛ፣ የድንቅ ኪነ ሕንፃዎች ማዕከል እና ታሪክንና ዘመናዊነትን አጣምራ የያዘች በዓለም በቱሪስት መዳረሻነታቸው ከሚጠቀሱ ቀዳሚ ከተሞች አንዷ መሆኗ ይታወቃል።

አየር መንገዱ ወደ ዋርሶው ከሰኔ 9 ጀምሮ በረራ እንደሚያደርግ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡

20/04/2024
የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ይካሄዳልሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ለውጦች ላይ ያተኮረ ...
20/04/2024

የሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር አፈጻጸም ላይ ያተኮረ መድረክ በሀዋሳ ይካሄዳል

ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በሌማት ትሩፋት መርኃ ግብር በተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ለውጦች ላይ ያተኮረ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

በምክክር መድረኩ ለመሳተፍ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል፡፡

በእንስሳትና አሣ ሀብት ልማት ምርትና ምርታማነት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ የተቀረጸው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል።

በመርኃ ግብሩ በዋናነት እንቁላል፣ ዶሮ፣ ማር፣ ወተት እና አሣ ልዩ ትኩረት የተሰጣቸው የልማት መስኮች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕ...
20/04/2024

የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ነው - ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) የጉራጌ ሕዝብ በአንድነት ውስጥ የሚገኘውን ጸጋ ከሕይወት ልምዱ የተገነዘበ ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር የጉራጌ ሕዝብ ስለአንድነት እና አብሮነት አበክሮ ያስተማረና በተግባር ያሳየ አንድነት ኃይል ነው ብሎ የሚያምን መሆኑን አንስተዋል።

ስለሰላም ሳናስብ፤ ስለሰላም ሳንናገር ሰላምን ልንጎናጸፍ አንችልም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጉራጌ ስለሰላም የሚያስተምር፤ በሰላም የሚኖር ሰላምን የሚያስተጋባ ሕዝብ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያን ለመከፋፈል በየዕለቱ ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ለሚያጠፉ ለአትዮጵያ ጠላቶች ጉራጌ አንድነት ኃይል ነው ብሎ ስለሚያምን ኢትዮጵያዊያን ከዚህ ልንማር ይገባል ብለዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ አንድነትን ጠብቀን ለትውልድ ማሻገር እንድንችል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በወልቂጤ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነውሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ...
20/04/2024

በወልቂጤ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው

ሚያዝያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በርካታ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት የለውጡን መንግስት የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰልፍ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

በድጋፍ ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች የፌደራል ፣የክልልና የዞን አመራሮች እንዲሁም የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

19/04/2024

#አጀንዳ+ ፤ የአፍሪካ ቀንድ እና የደኅንነት ስጋቶቹ፣ ከኢትዮጵያ እስከ ሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድ እስከ ሱዳን እና ተያያዥ ጉዳዮች

የጠነከረችና የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አቅደው እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) በቀጣናው የሚስተዋለውን ችግር ቀርፈው የጠነከረችና የበ...
19/04/2024

የጠነከረችና የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት አቅደው እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) በቀጣናው የሚስተዋለውን ችግር ቀርፈው የጠነከረችና የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በውጥን እየሰሩ መሆናቸው ተገለጸ።

የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ከውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ቀንድና በቀጣናዊ ደህንነት ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ትብብርን ማጠናከር ለቀጣናው ውህደት መሠረት የሚጥል መሆኑ በተደጋጋሚ እንደሚነሳና ይህንንም የሚያጠናክር ስራዎች በስፋት መስራት እንደሚጠበቅ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ውይይቱ “ለውስብስብ ጉዳዮች አማራጭ መንገዶችን በመፈለግ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ደህንነትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የተካሔደ ሲሆን ይህን ውጥን እውን ለማድረግ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚኖሩ ሀገራት መተባበርና የጋራ አቋም መያዝ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሀገራት እርስ በእርስ ያላቸው ያልጠነከረ ግንኙነት፣ ሰላም እጦት፣ መፈናቀልና ጦርነት ለዘመናት ችግር ሆነውባቸው መቆየቱ የተገለጸ ሲሆን ይህንን በቀጣናው የሚስተዋለውን ችግር ቀርፎ የጠነከረች የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠር የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በውጥን እየሰሩ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

ለዚህም በቀጣናው ያሉ እድሎችንና ፈተናዎችን በመለየት ዘላቂና አስተማማኝ ከባቢያዊ ሁኔታን በመፍጠር የቀጣናውን አገራት ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችል ውይይትም እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 2023 በጅቡቲ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ትብብሩንም ለማጠናከር የቀጣናው ተወካዮች ሁለተኛ መድረክ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ አካሂደዋል።

በምስራቅ አፍሪካ የሚያጋጥሙ ወቅታዊ ፈተናዎችን ለመሻገር መሰል ውይይቶች ያላቸው ሚና ከፍተኛ እንደሆነና ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም ተገልጿል።

በውይይቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋና የውጭ ጉዳይ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ በቀጣናው የደህንነት ምህዳር ላይ እየታዩ ያሉ ለውጦችና አንድምታቸው፣ የውጭ ኃይሎች በቀጣናው ደህንነት ላይ ያላቸው ሚና ላይ ያተኮሩ የመነሻ ጽሑፎች ቀርበው ውይይቶች ተካሂዶባቸዋል።

19/04/2024

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ጋር የተደረገ ቆይታ

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ባለፉት አምስት ዓመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ባለፉት አምስት ዓመታት ሀብት...
19/04/2024

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ባለፉት አምስት ዓመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር ተገለጸ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ባለፉት አምስት ዓመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር የወቅቱ የኢኒሼቲቩ ሊቀ መንበርና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ፡፡

ሚኒስትሩ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና ዓለም ባንክ ስብሰባ ጎን ለጎን 20ኛውን የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ የመሩ ሲሆን የዓለም ባንክ የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ቪክቶሪያ ክዋክዋ በስብሰባው ተገኝተዋል፡፡

በዋሽንግተን ዲሲ በተካሄዳው ስበሰባ የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ሚኒስትሮች፣ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የዓለም ባንክ ተወካዮች እንዲሁም የጀርመን እና ብሪታኒያ ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በ20ኛው የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ የሚኒስትሮች ስብሰባ የአረብ ባንክ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት፣ የሳዑዲ ልማት ፈንድ፣ የአሜሪካ እና የጃፓን ልዩ መልዕክተኛ በአጋርነት መሳተፋቸውም ተመላክቷል፡፡

አዳዲስ ተቋማት በኢኒሼቲቩ መሳተፋቸውን ያደነቁት ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ኢኒሼቲቭ ባዘጋጀው ህጋዊ ማዕቀፍ ውስጥ ተካተው መደበኛ አጋር እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢኒሼቲቩ ባለፉት አምስት ዓመታት ሀብት በማሰባሰብ ረገድ ስኬታማ እንደነበር አስታውሰው ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ኢንሼቲቭ ሰባት የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በአባልነት አካትቶ በፈረንጆቹ 2019 የተመሰረተ ሲሆን በቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ውህደትን ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

 #አጀንዳ+👉የአፍሪካ ቀንድ እና የደኅንነት ስጋቶቹ፣ ከኢትዮጵያ እስከ ሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድ እስከ ሱዳን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ይዳስሳል ዛሬ ምሽት 3፡00 ይጠብቁን!👇👇https://youtu...
19/04/2024

#አጀንዳ+

👉የአፍሪካ ቀንድ እና የደኅንነት ስጋቶቹ፣ ከኢትዮጵያ እስከ ሶማሊያ፣ ከሶማሌላንድ እስከ ሱዳን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ይዳስሳል

ዛሬ ምሽት 3፡00 ይጠብቁን!👇👇
https://youtu.be/DyumPkXJ5YM?si=MXjO73HZoFMB4PC2

የአማራ ክልል ለ1 ሺሕ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺሕ 460 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ ብርሃ...
19/04/2024

የአማራ ክልል ለ1 ሺሕ 460 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለ1 ሺሕ 460 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ብርሃኑ ጎሽም በሰጡት መግለጫ የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ሚያዝያ 7/2016 ዓ.ም ባካሄደው 6ኛ ዙር 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባ ለሁለተኛ ዙር የሚሰጠውን ይቅርታ ምክንያት በማድረግ በክልሉ የይቅርታ አሰጣጥ ስርዓት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 136/1998 መሰረት ይቅርታ ማድረጉን ገልጸዋል።

ይቅርታ ከተደረገላቸው መካከል ሴቶች 29 መሆናቸውን የገለጹት ኃላፊው ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች የፈጸሙት ወንጀል ይቅርታ የማይከለክል፣ ከተወሰነባቸው የጊዜ ቆይታ ውስጥ አንድ ሶስተኛ፣ አንድ አራተኛና አንድ አምስተኛውን የጨረሱ፣ ከከሳሾቻቸው ጋር እርቅ የፈጸሙ እንዲሁም እድሜያቸውን መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ለሌሎች አርዓያ ሆነው የተለመደ ማህበራዊ መስተጋብራቸውን ጤናማ በሆነ መንገድ ማስቀጠል እንዳለባቸው የተናገሩት ኃላፊው ህብረተሰቡም ይቅርታ ለተደረገላቸው ታራሚዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንዲያደርግላቸው ማሳሰባቸውን የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

ከተማ አስተዳደሩ ከ150 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ተቋማት አስተላለፈሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር...
19/04/2024

ከተማ አስተዳደሩ ከ150 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ተቋማት አስተላለፈ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ150 በላይ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ተቋማት አስተላለፈ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው "ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" በሚል መሪ ቃል በከተማችን የብክለት መከላከል ንቅናቄ ባስጀመርንበት እለት ከ150 በላይ በኤክትሪክ የሚሰሩ በሃገራችን የተመረቱ ሚኒባስ ተሽከርካሪዎችን ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ተቋማት አስተላልፈናል ብለዋል።

በከተማችን ዘመኑ የሚጠይቀውን ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ ተቋሞቻችንን በቴክኖሎጂ እና የተለያዩ አቅርቦቶችን በማሟላት እንዲሁም በማብቃት ላይ እንገኛለን ሲሉም አመልክተዋል።

ከንቲባዋ በአንድ በኩል መሰረተ ልማት እየዘረጋን በሌላ በኩል የአየር ብክለትን እና ሙቀትን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ አገልግሎትን እያሳለጥን ለመኖር ምቹ የሆነች ከተማ የመገንባት ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አክለዋል።

ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉ ተገለጸሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ባለፉት 9 ወራት 2 ቢሊየን 176 ሚሊየን 455 ሺሕ ብር በ...
19/04/2024

ባለፉት 9 ወራት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉ ተገለጸ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ባለፉት 9 ወራት 2 ቢሊየን 176 ሚሊየን 455 ሺሕ ብር በአስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ማዳን መቻሉን የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ሀገር አቀፍ የፀረ ሙስና ኮሚሽኖች የትስስር ጉባኤ ላይ የ2016 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላለከል አገር አቀፍ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ለክልሎች ከ354 ሺሕ በላይ ስልጠናዎች መሰጠቱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ሙስናን በመከላከሉ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተመላክቷል።

በ9 ወራት ውስጥ እንደ ሀገር 1 ሺሕ 451 የጥቆማ መረጃዎችን የመቀበል ስራ መስራቱን የገለጸው ኮሚሽኑ እንደ ሀገር 373 የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጥናት አጥንቶ ከ2 ቢሊዮን 176 ሚሊዮን 455 ሺሕ 388.7 ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውቋል።

ከገንዘቡ በተጨማሪ መጠኑ 25 ሚሊየን በላይ የሆነ ካሬ ሜትር የሆነ የከተማና የገጠር ቦታ ከሙስና ምዝበራ ለማዳን ተችሏል ተብሏል።

ተቋሙ ከኢንሳ እና መሰል ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመዘርጋት ሙስናን የመከላከል ስራዎችን አጠናክሮ እየሰራ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ የፌደራልና የክልል የፀረ ሙስና ኮሚሸን ኮሚሽነሮችና ምክትል ኮሚሽነሮች ተገኝተዋል።

ማሕሌት መህዲ (ከአዳማ)

የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስ...
19/04/2024

የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮ-ቻይና ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉንና የቻይናው ኮሙኒስት ፓርቲ አጋርነትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ እንደመጣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።

የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት ዛሬ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው።

በውይይታቸውም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማስፋት፣ የሁለቱ ሀገራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን ማስፋት የሚሉት በሰፊው ተዳሰዋል።

ሁለቱ ፓርቲዎች ከዚህ በፊት በተስማሙት መሰረት በትምህርት፣ በስልጠና እንዲሁም በተሞክሮና ልምድ ልውውጥ አብሮ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስምምነት መደረጉን ያስታወሱት ምክትል ፕሬዝዳንቱ በቅርቡ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ የሆኑበት የልኡካን ቡድን ውጤታማ ቆይታ አድረጎ መመለሱም የዚህ ስምምነት አካል እንደሆነ አንስተዋል።

በቀጣይም የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነቶች በተመሳሳይ የስልጠና እና የልምድ ልውውጥ መርኃ ግብሮች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ብልፅግና ፓርቲ ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣዎ ዢዋን በበኩላቸው ኢትዮጵያ የቻይና ጠንካራ ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን ጠቅሰው ይህ ግንኙነት በፓርቲ ለፓርቲም ሆነ በመንግስታዊ ወዳጅነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ከፓርቲው የማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ ሚያዚያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት...
19/04/2024

ምክትል ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ

ሚያዚያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን ስታርት አፕ ኢትዮጵያ አውደ ርዕይን ጎበኙ።

በጉብኝቱ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአውደ ርዕዩ በመጀመሪያ ደረጃ በምርት ሙከራና ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ የጀመሩ ስታርት አፖች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም የተከፈተው ስታርት አፕ አውደርዕይ እስከ ሚያዚያ 20 ለህዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ ይቆያል።

19/04/2024

ተስፈኛ ውሎ...

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ትሰራለች - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ ...
19/04/2024

የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ትሰራለች - ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያ የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና ችግሮች እንዲፈቱ ከወዳጅ አገራትና ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።

በሰላም ዕጦት ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥም አበክራ እንደምትሰራም ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እንደገለጹት ተለዋዋጭ በሆነው ዓለም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟንና ፍላጎቷን መሰረት ያደረገ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን ታራምዳለች።

የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ አልፋና ኦሜጋ ብሔራዊ ጥቅም ነው ያሉት አምባሳደሩ ዲፕሎማሲው ከሀገር ሰላም፣ ልማትና ደህንነት አኳያ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ነው ያነሱት።

በዚህም በተለዋዋጩ ዓለም ውስጥ ኢትዮጵያ የምትወስዳቸው አቋሞች ከራሷ ብሔራዊ ጥቅም አኳያ መዝና እንደሆነ አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስራቅ ጋር ካላት መልክዓ ምድራዊና የህዝብ ለህዝብ ትስስር አኳያ የቀጣናው ቀውስና መረበሽ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ቀጥተኛ አንድምታ እንዳለው ተናግረዋል።

በዚህም የቀጣናው ችግሮች እንዲፈቱና ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ ከአጋር አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እንደምትሰራ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ፖሊሲዋ ለጎረቤት ሀገራት ቀዳሚ ትኩረት እንደምትሰጥ ገልፀው በተለይም ጎረቤት አገራት ቀውስ ለኢትዮጵያ እንደሚተርፍ ተናግረዋል።

በዚህም በሰላም ዕጦት ለሚቸገሩ ጎረቤት አገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር በታሪክ የነበራትን የሰላም ማስከበር ሚና አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ባሻገርም ኢትዮጵያ በቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል የዲፕሎማሲ ስራዎችን ማከናወኗን ገልጸዋል።

የባሕር በርን ጨምሮ ፀጋዎችን አልምቶ በጋራ በመጠቀምና የመሰረተ ልማትና ንግድ ትስስር በማጎልበት የጋራ ዕድገትን ማረጋገጥና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።

19/04/2024

ከ2011 ዓ.ም ማህደር ለትውስታ

19/04/2024

አጓጊውን የድምፃዊያን ውድድር እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ ይጠብቁን!


የዓለም ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳዬሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) እስራኤል በአራን ላይ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃን ተከትሎ በዓለም የነዳጅ ዋጋ 4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ።ሰሞኑን በሁለ...
19/04/2024

የዓለም ነዳጅ ዋጋ ጭማሪ አሳዬ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) እስራኤል በአራን ላይ በወሰደችው የአጸፋ እርምጃን ተከትሎ በዓለም የነዳጅ ዋጋ 4 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለጸ።

ሰሞኑን በሁለቱ አገራት መካከል እየተባባሳ በመጣው ግጭት ምክንያት በዓለም የነዳጅ አቅርቦት ላይ ተፅእኖ ሊያሳድር እንደሚችል እየተገለጸ ነው።

በዚህም ብሬንት የተሰኘው የነዳጅ ምርት አንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ በዓለም ገበያ 90 ነጥብ 54 ዶላር እየተሸጠ መሆኑን ሚንት የተሰኘ የቢዝነስ ነክ መረጃ አቅራቢ ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።

የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት መባባስንና የነዳጅ አምራች አገራት ህብረት የሆነው ኦፔክ አቅርቦት ለመቀነስ መወሰኑ ለዓለም የነዳጅ ዋጋ መጨመር ምክንያት መሆናቸው ነው የተገለጸው።

በሌላ በኩል በወርቅ ዋጋ ላይም ጭማሪ መታየቱ የተገለጸ ሲሆን አንድ ወቄት (28.349 ግራም) ወርቅ የ1 በመቶ ጭማሪ በማድረግ በ2 ሺሕ 422 ዶላር እየተሸጠ መሆኑ ተመላክቷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የብክለት መከላከል ንቅናቄን አስጀመሩሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በ...
19/04/2024

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማዋ የብክለት መከላከል ንቅናቄን አስጀመሩ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ “ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ” በሚል መሪ ሃሳብ በከተማዋ የብክለት መከላከል ንቅናቄን አስጀመሩ።

ተፈጥሮ ለአዲስ አበባ የለገሳትን ውበት ያመናመነውን አሰራር ለመቀየር እና የከተማዋን ሰርዓተ ምህዳር ለማሻሻል የሚረዱ ሜጋ ፕሮጀክቶች በከፍተኛ ርብርብ፣ በልዩ የአመራር ትኩረት እና በአጠረ ጊዜ መፈጸማቸውን ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ከፍተኛ ለውጥ እያመጡ ካሉት ፕሮጀክቶች መካከል ዋነኞቹ ለሞቱት የከተማዋ ወንዞች ትንሳኤያቸውን፤ ለተበከሉት ደግሞ ህክምናን ያበሰረው የአዲስ አበባ ወንዞች ዳርቻ ልማት አንዱና መሰረታዊ ሲሆን በከፍተኛ ፍጥነት እየቀነሰ የነበረውን የከተማዋን የአረንጓዴ ሽፋን የታደገውና ከነበረበት 2.8 በመቶ ወደ 15 በመቶ ያሳደገው የአርንጓዴ አሻራ ማኖር ኢኒሼቲቭ ተጠቃሽ መሆኑን አንስተዋል።

የተሰሩት ስራዎች አዲስ አበባን የቱሪስት መዳረሻና ዓለም አቀፍ የስበት ማዕከል ያደረጓት ቢሆንም አሁንም ድረስ የድምጽ እና የፍሳሽ ብክለት እና አወጋገድ የከተማዋ ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል ነው ያሉት።

በሕግና በአሰራር ችግሩን ለመፍታት ከምናደርገው ጥረት ባሻገር ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት የሚቆይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በመስራት ለውጥ ለማምጣት ንቅናቄውን በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምረናል ብለዋል።

19/04/2024
1600 ዓመታትን ያስቆጠሩ ቅርሶች የሚገኙበት የግል ሙዚየምበሐረር ከተማ የሚገኘው የቀድሞው የተፈሪ መኮንን ታሪካዊ ጫጉላ ቤት አሁን ታሪካዊ ቅርሶች ተሰባስበው የተቀመጡበት የኢትዮጵያውያን፣ ...
19/04/2024

1600 ዓመታትን ያስቆጠሩ ቅርሶች የሚገኙበት የግል ሙዚየም

በሐረር ከተማ የሚገኘው የቀድሞው የተፈሪ መኮንን ታሪካዊ ጫጉላ ቤት አሁን ታሪካዊ ቅርሶች ተሰባስበው የተቀመጡበት የኢትዮጵያውያን፣ የውጭ አገር ዜጎችንና ቱሪስቶችን ቀልብም የሚስብ ልዩ ሙዚየም ሆኗል።

ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ እና የተለያዩ እምነቶች እንዲሁም ብሔረሰቦች መገለጫ የሆኑ በ10ሺዎች የሚገመቱ ቅርሶችን አሰባስቦ የያዘ ነው፤ በበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚው በሀረሚያ ዩኒቨርሲቲ የክቡር ዶክትሬት በተበረከተላቸው ውልደት፣ እድገት፣ ትዳር እና ኑሯቸውም በሀረር ከተማ የሆነው አብደላ አሊ ሸሪፍ የመሰረቱት “ሸሪፍ ሙዚየም”።

ከ1600 ዓመታት በላይ ያስቆጠሩ ቅርሶች፣ ከአክሱም ዘመን ጀምሮ መገልገያ የነበሩ ሳንቲሞች፣ የትየለሌ ዓመታትን ህልው መሆን የቻሉ የሃይማኖት መጻሕፍት፣ የነገስታት ሰይፍ እና መሰል የጦር መሳሪያዎች፣ ንጉሳዊያን የተጻጻፏቸው ደብዳቤዎች፣ የተፈረሙ ውሎች እና ሌሎችም እጅን በአፍ የሚያስጭኑ ታሪካዊ ቅርሶችና ሰነዶች በሸሪፍ ሙዚየም ውስጥ በከፍተኛ ጥንቃቄ እና እንክብካቤ ተቀምጠዋል።

በቀደምት ሀረሬዎች የተዘጋጁ በአረብኛ ፊደል በኦሮሚኛ ቋንቋ የተጻፉ ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸው መጻሕፍት፣ በሀረር እናቶች በጥበብ እና በጥንቃቄ የተሳሉ የሃይማኖት መጻሕፍት ሽፋን እንዲሁም ሌሎች ረጅም ዓመታትን ያስቆጠሩ መጻሕፍት በሙዚየሙ ውስጥ እንደልብ ማግኘት ይቻላል፡፡

ሀረሬዎች ይገለገሉባቸው የነበሩ ሳንቲሞች እኛ በዚህ ዘመን ከምናውቃት አምስት ሳንቲም በመጠን 3 እጥፍ የሚያንሱ ሲሆን በአስገራሚ መልኩ በዚች እጅግ ጠባብ ዲያሜትር ባላት ሳንቲም ውስጥ “ነብዩ መሀመድ የአላህ መልዕክተኛ” የሚል ጽሑፍ ታትሞ ይታያል።

ከ1600 ዓመታት በፊት መገበያያ የነበሩትን የአክሱም ሳንቲሞችን ጨምሮ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ያሉ ገንዘቦች እና በምስራቅ አፍሪካ የተለያዩ አካባቢዎችም ግብይት ይፈጸምባቸው የነበሩ ጥንታዊ ገንዘቦች በሙዚየሙ ውስጥ ከአስፈላጊው ገለጻ ጋር በክብር ተቀምጠው ትውልድ ይጎበኛቸዋል፣ ይደነቅባቸዋል፣ ታሪክ ይማርባቸዋል።

ሙሉ ታሪኩን ለማንበብ ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ👇

1600 ዓመታትን ያስቆጠሩ ቅርሶች የሚገኙበት የግል ሙዚየም...

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁ...
19/04/2024

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የኬኒያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላን ህልፈተ-ሕይወት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ ጀኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለሀገራቸውና ለቀጣናው ሠላምና ደህንነት መረጋገጥ የነበራቸው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደነበር አስታውቀዋል።

እሳቸውና ሌሎች ከፍተኛ መኮንኖችን ባጋጠመቸው የሄሊኮፕተር መከስከስ አደጋ ህይወታቸው በማለፉ በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም የተሰማቸውን ሃዘን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጀኔራል ፍራነኪስ ኦሞንዲ ኦጎላ ለኬኒያና ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላበረከቱት አስተዋጽኦና በጎ ሥራ ሁልጊዜ ሲታወሱ ይኖራሉ ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ከኬኒያ ወንድም ህዝቦች ጋር መሆኑን አስረድተዋል።

በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መኮንኖች ቤተሰቦችና ወዳጆች በራሳቸውና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ስም መጽናናትን ተመኝተዋል።

የኬንያ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስ ኦሞንዲ ኦጎላ በምዕራብ የአገሪቱ ክፍል ይበሩበት የነበረው ወታደራዊ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ሕይወታቸው ማለፉን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ትላንት ማሳወቃቸው ይታወሳል። ፕሬዝዳንቱ አደጋው ለአገሪቱ “ትልቅ ሐዘን” ነው ማለታቸውም ተገልጿል።

አጓጊው ደሞ አዲስ በመጪው እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ  #በቀጥታ ስርጭት ለእናንተ ለተመልካቾቻችን ተወዳዳሪዎቹን ይዞላችሁ ይቀርባል።በቀጥታ ስርጭትም ዳኞችና ተወዳዳሪዎች በተመልካቾች ድምፅ ...
19/04/2024

አጓጊው ደሞ አዲስ በመጪው እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ #በቀጥታ ስርጭት ለእናንተ ለተመልካቾቻችን ተወዳዳሪዎቹን ይዞላችሁ ይቀርባል።

በቀጥታ ስርጭትም ዳኞችና ተወዳዳሪዎች በተመልካቾች ድምፅ ይዳኛሉ። በዕለቱም በተሰጣቸው ኮድ በ8970 SMS ድምጽ ይስጡ!

ዮሐንስ ወርቁ በA1

አብርሐም ሸዋንቅጣው በA2

አብርሐም ኸይሩ በA4

ማትያስ ደርብ በA5



እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን 🎼🎹🥁🎤🎺🎷🎸🎻

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረችሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) እስራኤል ከኢራን ለተቃጣባት የሚሳኤልና ድሮን ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተገለጸ።እስራኤል ኢስፋሃን በተባ...
19/04/2024

እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ ጥቃት ሰነዘረች

ሚያዝያ 11/2016 (አዲስ ዋልታ) እስራኤል ከኢራን ለተቃጣባት የሚሳኤልና ድሮን ጥቃቶች የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ተገለጸ።

እስራኤል ኢስፋሃን በተባለ የማዕከላዊ አራን አካባቢ ባሉ ወታደራዊ ካምፖች ላይ በድሮኖች ጥቃት መሰንዘሯ ነው የተጠቀሰው።

ይህን ተከትሎ ኢራን የጸረ-ሚሳኤል መከላከያ ማስወንጨፏንና የተተኮሱባትን ሦስት ድሮኖች መታ መጣሏን አስታውቃለች።

ኢስፋሃን የኢራን አየር ኃይል እና የኒዩክሌር ጣቢያ የሚገኝ ከተማዋ ሲሆን በአካባቢው የተሰማው ፍንዳታ ኢራን ያስወነጨፈቻቸው የጸረ ሚሳኤል መከላከያ መሆኑን አገሪቱ ባወጣችው መረጃ ገልጻለች።

የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ የአየር በረራዎች ተስተጓጉለው እንደነበርና በአሁኑ ሰዓት በረራ መጀመሩን እንዲሁም አካባቢው ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሱን የአልጃዚራ ዘገባ አመላክቷል።

በፈረንጆቹ ሚያዝያ 1 ቀን እስራኤል ሶሪያ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ላይ ባደረሰችው ጥቃት 13 ዜጎቿ መገደላቸውን ተከትሎ በእስራኤል ላይ ባሳለፍነው ቅዳሜ 300 ሚሳኤልና የድሮን ጥቃት ማድረሷ ይታወሳል።

ለኢራን ጥቃት እስራኤል አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታ እንደነበርም የሚታወስ ነው።
የሁለቱ አገራት የሰሞኑ ግጭትን ተከትሎ አገራት ዜጎቻቸውን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ እያስጠነቀቁ ነው።

ከስውር ጦርነት አልፎ ወደ ይፋዊና ቀጥተኛ ግጭት ውስጥ የገባው የሁለቱ አገራት የሰሞነኛ ፍጥጫ በቋፍ ላይ የነበረ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ ወደለየለት ጦርነት እንዳይከተው ተሰግቷል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when WMCC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to WMCC:

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share

Our Story

About Walta Information and Public Relations Center S.C. is a private media outlet and Public Relations Center established in 1994. Its major objective is playing significant roles in minimizing the gap of information flow in Ethiopia. Company Overview Walta Information and Public Relations Center S.C. is a private media outlet and Public Relations Center established in 1994. Its major objective is playing significant roles in minimizing the gap of information flow in the country. Accordingly, it has been gathering, organizing, analyzing and disseminating credible, accurate and balanced news and news genres. Besides, it has been providing public relations services since its reorganization, some three years back. The institution has also been contributing an immense role in peace building, democratization and sustainable economic development.