የዳሞት ሶሬ ወረዳ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

  • Home
  • የዳሞት ሶሬ ወረዳ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የዳሞት ሶሬ ወረዳ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!!

31/10/2025
‎"በዞኑ በሁሉም መዋቅር የኮሚሽን  ሥራ ተግባራዊ ማድረግ ፣ ለፓርቲ ጥንካሬ ቁልፍ ሚና ይጫወታል" :- አቶ ፃድቁ ፈለቀ‎‎ዳሞት ሶሬ:- ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (ወዞመኮጉ)‎‎የወላይታ ዞ...
30/10/2025

‎"በዞኑ በሁሉም መዋቅር የኮሚሽን ሥራ ተግባራዊ ማድረግ ፣ ለፓርቲ ጥንካሬ ቁልፍ ሚና ይጫወታል" :- አቶ ፃድቁ ፈለቀ

‎ዳሞት ሶሬ:- ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም (ወዞመኮጉ)

‎የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሄደ

‎የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ ስብሳቢ የተከበሩ አቶ ፃድቁ ፈለቀ እንዳስረዱት አዳዲስ የፓርቲ መተዳደሪያ ደንቦችና መመሪያዎች እስከ አባላት ድረስ እንድወርዱና ግልጽነት እንዲፈጠር መደረጉን ተናግረዋል ።

‎የኮሚሽኑ ሥራ ለማሳለጥ የሎጂስቲክ ዕጥረት ለመቅረፍ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመወያየት መፍትሔ እንዲፈለግ በትኩረት እንዲሠሩ አስረድተዋል ።

‎በቀጣይ የኮሚሽን አመራር ሥራ በታቀደው ልክ በየደረጃው አፈጻጸሙን የተሻለ ለማድረግ በዲስፕሊንና በተናበበ ሁኔታ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጡ አጽንኦት ሰጥተዋል።

‎ እንደ ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ማብራሪያ በየደረጃው የኮሚሽን አደረጃጀት ለማጠናከር መሰራቱን፣ የፓርቲ ጤንነትን የማስጠበቅ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱንና ከፓርቲ ጋር በጋራና በተናበበ ሁኔታ ተልዕኮዎች ወደ መሬት እንድወርድ መደረጉን አስረድተዋል ።

‎የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ባሳለፍነው ሩበ ዓመት ውስጥ ተልዕኮውን ሊወጣ የሚችል ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር በሠራው ሥራ አበረታች ስራዎችን ማከናወኑ ጠቁመዋል ፡፡

‎ከጽ/ቤቶች ጋር በቅርብ የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ስርዓት በመዘርጋቱ የአፈጻጸም መቀራረብንና በኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት መካከል ቤተሰባዊ ቅርርብን መፍጠር ስለመቻሉ በገለጻቸው ጠቅሰዋል።

‎የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የኮሚሽኑ መመሪያና ደንብ በግልጽ ተፈጻሚ እንዲሆን የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንደሚረግ አብራርተዋል ።

‎የኮሚሽኑ አመራሮች የፖለቲካ ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ ገንቢ ምከረ ሃሣብ በማቅረብ ተግባራዊነቱን ማጠናከር እንደሚገባ አስረድተዋል ።

‎ በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ አንኳር ጉዳዮችን፣ የተገኙ ውጤቶችና ለቀጣይ ሥራዎች የተወሰዱ ትምህርቶች አስመልክቶ የፓርቲ ጽ/ቤት አመራሮች በተገኙበት ገለጻ በአቶ ወንድማገኝ አበራ ሠነዱ ቀርበዋል ፡፡

‎በግምገማው መድረክ የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን አመራሮች ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ኮሚሽን አመራሮችና የኅብረቱ ኮሚሽን አመራሮች ተሳትፈዋል ።

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው‎‎ዳሞት ሶሬ ፤ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብል...
30/10/2025

‎የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

‎ዳሞት ሶሬ ፤ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም የወላይታ ዞን ብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

‎የወላይታ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ኮሚቴ ስብሳቢ የተከበሩ አቶ ፃድቁ ፈለቀ በገለጻቸውም በየደረጃው የኮሚሽን አደረጃጀት ለማጠናከር መሰራቱን፣ የፓርቲ ጤንነትን የማስጠበቅ ሥራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን ገልፀዋል።

‎አያይዘውም ከፓርቲ ጋር በጋራና በተናበበ ሁኔታ ተልዕኮዎች ወደ መሬት እንድወርድ መደረጉንና አዳዲስ የፓርቲ መተዳደ ሪያ ደንቦችና መመሪያዎች እስከ አባላት ድረስ እንድወርዱና ግልጽነት እንድፈጠር መደረጉን ጠቁመዋል።

‎የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ባሳለፍነው ሩበ ዓመት ውስጥ ተልዕኮውን ሊወጣ የሚችል ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር አበረታች ስራዎችን ማከናወኑ አስረድተዋል ፡፡

‎ከጽ/ቤቶች ጋር በቅርብ የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ስርዓት በመዘርጋቱ የአፈጻጸም መቀራረብንና በኮሚሽኑ አመራሮችና አባላት መካከል ቤተሰባዊ ቅርርብን መፍጠር ስለመቻሉ በገለጻቸው ጠቅሰዋል።

‎የብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና የሥነምግባር ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ አበራ የሩብ ዓመቱ የተከናወኑ አንኳር ጉዳዮችን፣ የተገኙ ውጤቶችና ለቀጣይ ሥራዎች የተወሰዱ ትምህርቶች አስመልክቶ የኮሚሽን አመራሮች በተገኙበት ሪፖርቱን እያቀረቡ ይገኛሉ ፡፡

30/10/2025
ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!
28/10/2025

ጠንካራ ኢንስፔክሽን ለጠንካራ ፓርቲ!

እንኳን ደስ ያላችሁ፤ እንኳን ደስ ያለን!!!  !!
28/10/2025

እንኳን ደስ ያላችሁ፤ እንኳን ደስ ያለን!!!

!!

ግላዊ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ትኩረቱ ዉጤቱ ላይ ስለሆነ ሂደቱ ስለሚያስከፍለዉ ዋጋ ግድ አይሰጠዉም፡፡ ሥልጣን አገኝበታለሁ ብሎ ካሰበ ሂደቱ ሀገርን ቢበትን ግድ የለዉም፡፡ እታገልለታ...
27/10/2025

ግላዊ ፍላጎት ላይ የተመሠረተ ፖለቲካ ትኩረቱ ዉጤቱ ላይ ስለሆነ ሂደቱ ስለሚያስከፍለዉ ዋጋ ግድ አይሰጠዉም፡፡ ሥልጣን አገኝበታለሁ ብሎ ካሰበ ሂደቱ ሀገርን ቢበትን ግድ የለዉም፡፡ እታገልለታለሁ የሚለዉን ህዝብ ዋጋ ቢያስከፍልም ቁብ አይሰጠዉም፡፡ ግላዊ ዉጤቱን እንጂ ሂደቱን ከዉጤቱ አንጻር አይመዝንም፡፡

የመደመር መንግሥት ገጽ - 283

‎የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ስምንተኛ የጋራ ምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል‎‎ዳሞት ሶሬ ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም፦‎የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮ...
27/10/2025

‎የብልፅግና የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ስምንተኛ የጋራ ምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል

‎ዳሞት ሶሬ ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ/ም፦
‎የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ክቡር ዶክተር ደስታ ተስፋው በንግግራቸው ኮሚሽኑ አሰራር በማስጠበቅና በብልፅግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ የተሰጠውን ተልዕኮ ከመወጣት አኳያ እያደገ የመጣ አፈፃፀም ማስመዝገብ መቻሉን ጠቅሰዋል።

‎በየወቅቱ መሰል መድረኮችን በመጠቀም፣ የድጋፍና የክትትል ስራዎች በቅንጅት በመስራታቸው የተመዘገበ ውጤት መሆኑን በመግለፅ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ገልፀዋል።

‎የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የኮሚሽኑ ፀሐፊና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ በንግግራቸው የምክክር መድረኩ ዓላማ የኮሚሽኑን እቅድ አፈጻጸም፣ የኮሚሽኑ ሥራዎች አዝማሚያዎች መገምገሚያ እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መግባባት ለመፍጠር ከማገዙም በላይ የልምድ ልውውጥና የአቅም መገንቢያ መድረክ እንደሚያገለግል አንስተዋል።

‎አያይዘውም ኮሚሽኑ እየተጠናከረ እንዲመጣ አመራር በመስጠትና ድጋፍ በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዘዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ አደም ፋራህን አመስግነዋል።

‎በመድረኩ የኮሚሽን አባላት፣ የክልል/ከተማ ኮሚሽን አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎችና ም/ጽ/ቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን የየክልል/ከተማ እና የተጠቃለለ የኮሚሽን ሪፖርቶች ቀርቦ እየተገመገመም ይገኛል።

‎ !!

27/10/2025
25/10/2025

የመደመር መንግስት ዋና ግብ የማይበገር ኢኮኖሚ፣ በታቀደ አግባብ፣ ደረጃ በደረጃ መፍጠር ነው።የማይበገር ኢኮኖሚ የወደፊቱን የሚያሰላ፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶ...
23/10/2025

የመደመር መንግስት ዋና ግብ የማይበገር ኢኮኖሚ፣ በታቀደ አግባብ፣ ደረጃ በደረጃ መፍጠር ነው።

የማይበገር ኢኮኖሚ የወደፊቱን የሚያሰላ፣ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተቋቁሞ እንደ መልካም አጋጣሚ ወስዶ ዕድገቱን ማስቀጠል የሚችል ኢኮኖሚ ነው። ተለምዷዊውን የመንግሥት ቁመና ተላብሶ በፍጥነት በሚለዋወጥ ዓለም ውስጥ አይበገሬ ኢኮኖሚ መገንባት የሚታሰብ አይደለም።

በመሆኑም አንድ ሥርዓት ራሱን ከዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭነት ጋር አጣጥሞ፣ ተወዳድሮና አሸንፎ ለመውጣት የሚጠበቁበት ነገሮች አሉ። ቁመናውን መፈተሽ፣ ማስተካከያዎችን ማድረግና ዝግጁ መሆን ወሳኝ ነው። ይህ የመደመር መንግሥት ቁመና ዕድሎችን በመጠቀምና ሥጋቶችን በመከላከል ግቦቹን ማሳካት እንዲችል ለማድረግ ቁልፍ ነገር ነው።

ኢኮኖሚው የመጪውን ዘመን ፍላጎቶች ማሟላትና ዐቅሞችን በውጤታማነት መጠቀም እንዲችል በመደመር መንግሥት አስተሳሰብ መመራት አለበት።

ምንጭ:- የመደመር መንግስት መፅሐፍ ገፅ 119

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የዳሞት ሶሬ ወረዳ ብልጽግና የኢንስፔክሽንና የስነ ምግባር ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share