ስለ ድሬ - About Dire

  • Home
  • ስለ ድሬ - About Dire

ስለ ድሬ - About Dire Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ስለ ድሬ - About Dire, Digital creator, .

አርጀንቲና የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነችአርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምት በማሸነፍ የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት...
18/12/2022

አርጀንቲና የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነች
አርጀንቲና ፈረንሳይን በመለያ ምት በማሸነፍ የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
የ22ኛው የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በሉሳይል አይኮኒክ ስታዲየም ተካሂዷል፡፡
በዚህም ፈረንሳይ እና አርጀንቲና መደበኛ ጨዋታውን 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ያጠናቀቁ ሲሆን÷ ተጨማሪ 30 ደቂቃውንም 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፡፡
የፍጻሜ አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የመለያ ምትም አርጀንቲና ፈረንሳይን በማሸነፍ ከ36 ዓመታት በኋላ የዓለም ዋንጫን ማንሳት ችላለች፡፡

የOn-line ስልጠና ተጀመረ  | የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን፤ የተቋሙን የታክስ አስተዳደር የግብር መረጃ አቅርቦት እና ገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ለማዘመን፤ ከCustor Comput...
21/11/2022

የOn-line ስልጠና ተጀመረ
| የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን፤ የተቋሙን የታክስ አስተዳደር የግብር መረጃ አቅርቦት እና ገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ለማዘመን፤ ከCustor Computing plc ጋር በገባው ስምምነት መሰረት፤ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባለሙያዎች የ2ኛ ምዕራፍ የስራ ላይ (on-line) ስልጠና መስጠት ጀምሯል፡፡

ተቋሙ በካፒታል ፕሮጀክት የተያዘውን ስራ ከሃምሌ 1 2014 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልኩ ተሻሽሎ በለማው የኢ-ታክስ መተግበሪያ የታገዘ መደበኛ ስራ ይፋ መደረጉ ይታወቃል፡፡

በዚህ መሰረት የተቋሙን ሰራተኞች የአይቲ እውቀት ለማሳደግ የሚያስችለውን ስልጠና ለታክስ ኦዲት ክፍል ባለሞያዎች መሰጠት ሲጀመር፤ የባለስልጣኑ የኦዲትና ህግ ማስከበር አቶ አክሊለ ታጠቅ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮናስ ጥግነህ ተገኝተዋል፡፡

በቀጣይ ስልጠናው በ3 ዙር መርሃግብር ለሁሉም የገቢዎች ባለስልጣን የሥራ ክፍሎች የሚሰጥ ሲሆን፤ የ2015 በጀት አመት የተግባር ስምሪት ከማዘመን ባሻገር የገቢ መሰረትን ያሳፋል ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ነው

አዎን ጋሽ አብረሃም ሞተ…" The End of An Era " [ግሩም ተበጀ እንደፃፈው] “የሂሳብ ፈተና እንደታደለ … ሂሳብ የማይወደው ተማሪ ሁሉ ወዲያው የመሰለውን አክብቦ ይወጣል፡፡ ክፍሉ ...
21/11/2022

አዎን ጋሽ አብረሃም ሞተ…
" The End of An Era "

[ግሩም ተበጀ እንደፃፈው]

“የሂሳብ ፈተና እንደታደለ … ሂሳብ የማይወደው ተማሪ ሁሉ ወዲያው የመሰለውን አክብቦ ይወጣል፡፡ ክፍሉ ውስጥ አንድ ወይ ሁለት ሂሳብ የሚወዱ ተማሪዎች ሲቀሩ፣ ፈታኝ ተብዬው እነዚህን ተማሪዎች ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያለ ያስቸኩላል፡፡ እኔ እኮ አሉኝ የምላቸው ተማሪዎች እነዚህ 1 ወይ 2 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ይሄን ነገር አቁሙ ብያለሁ - አቁሙ፡፡ ተማሪዎቼን አታስቸኩሉብኝ…”

አብሪሎ

ጋሽ አብረሃም ሞተ…

አስተምሮኛል፤ አብሬውም አስተምሬያለሁ ! የጋሽ አብረሃም ሞት የሆነ ዘመን ማብቂያ ያህል ነው የሚሰማኝ - የሆነ The End of an Era…

የምታውቁት ይገባችኋል - የሆነ የድሬዳዋ ታሪክ ምዕራፍ ነው የተዘጋው…

አብሪሎን መጀመሪያ ያወቅኩት 8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈትነን ክረምት ውስጥ የክረምት ትምህርት ሀይስኩል ስንማር ነበር - 1985 ክረምት !

እንደምገምተው፣ ከሀረር እየመጣ ነበር ከሌሎች ከሀረር እየመጡ ከሚያስተምሩ አስተማሪዎች ጋር የሚያስተምረው፡፡ ከዚያ በፊት አንዱ የሀረርጌ ገጠር ከተማ ሂሳብ ያስተምር ነበር፡፡ እርግጥ ሂሳብ ብቻ አልነበረም የሚችለው - ሁሉንም ጥንቅቅ አድርጎ ያውቃል፡፡ ለዓመታት ማትሪክ እየተፈተነ ሁሉንም ኤ ያመጣ ነበር፡፡ አንዴ እንደውም አራት ኪሎ ሁሉ ገብቶ ነበር - ተመልሶ ወጣ እንጂ…

ትምህርት የምር ይወዳል አብሪሎ…

ሀረርጌ በምትሃቷ ጠልፋ ካስቀረቻቸው በርካቶች አንዱ ነው፡፡ አቤት ሥነሥርዓት ! አቤት ሰው ማክበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሲጨብጥ እንኳ በትህትና እኮ ነው - ቀኝ እጁን በግራ እጁ ይዞ በአክብሮት !!!

የጎንደር ሰው ነው - ድሬ በምትሃቷ ጠልፋ የድሬ ሰው አድርጋው እንጂ…

የአብሪሎን ትህትና ላየ … ከሰሜን ኢትዮጵያ ተወርውሮ ድሬ በስበቷ ምህዋሯ ውስጥ ያስገባችው መሆኑን ሲሰማ ይገባዋል…

የጋሽ አብረሃም ሞት የአንድ ዘመን ማብቂያ ነው - ይህን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡ ሞቱ ገንኖ ባይወራም - ይህን እውነት ግን አንክደውም፡፡

በ1985 ክረምት፣ ከሀረር እየተመላለሰ የክረምት ትምህርት ሲያስተምር ነው የማውቀው ብያችሁ የለ - ከዚያ እንዴት እንደሆነ እንጃ - ድሬዳዋ ጠበሰችው - አስኮበለለችው፡፡
ድሬዳዋ ገባ…

አላውቅም ከዚያም ቀድሞ ድሬዳዋ ገብቶ ይሆናል…

ከዚያ በኋላ ላሉት በርካታ ዓመታት ስመጥር የከተማዋ የሂሳብ አስጠኚ ሆነ፡፡ ቀጣይ ዓመታት የአብሪሎ ዘመናት ነበሩ - The Abrilo Era…

በ1994 ከአለማያ ተመርቄ ስወጣ ደግሞ፣ በዚያ ክረምት መምህራኑ ሁሉ ስልጠና ነው ስብሰባ ግቡ ተብሎ አብሮት ክረምት የሚያስተምር መምህር ሲጠፋ፣ ጋሼ መሰስ ብሎ መጣና ና ፊዚክስ አስተምር አለኝ…

አብሬው አስተማርኩ…
አይ ጋሼ…

አብሪሎ የዋህ ነው - ደግሞም ብልሃቶችም አሉት እኮ

1ኛ እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ የተማርኩበት ከዚራ ትምህርት ቤት ጊቢ ውስጥ ጠረጴዛ እና ወንበር አውጥቶ ለክረምት የሚማሩ ተማሪዎችን መመዝገብ ጀመረ…

እኔ ራቅ ብዬ ተቀምጫለሁ…

ጋሼ ምዝገባ የጀመረው ዛሬ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ጥቂት ተማሪዎች ሊመዘገቡ መጡ፡፡ ወዲያው እየተጯጯሁ እኔንም ቶሎ መዝግበኝ ማለት ጀመሩ…

ገረመኝ ! አሁን ነው ምዝገባው የተጀመረው ምን አጯጯሃቸው አልኩ…

ለማንኛውም ብዬ ቀረብ ብዬ ሳይ - ነገሩ ገባኝ፡፡

አብሪሎ፣ የመጀመሪያውን ልጅ 367ኛ ብሎ ነው የመዘገበው… ቀጣዩን 368፣
ይሄኔ ከእነርሱ በፊት ያ ሁሉ ተማሪ የተመዘገበ መስሏቸው ነው ተማሪዎቹ ቶሎ መዝግበኝ ማለት የጀመሩት - ቦታ እንዳይሞላባቸው !!!

ሂትለርም፣ ናዚ ፓርቲን ሲመሰርት ተመዝጋቢዎችን ለማማለል፣ የመጀመሪያውን ተመዝጋቢ በዚህ መልኩ ነው ያሞኘው ሲባል ሰምቻለሁ…

አይ ጋሼ…

በርህራሄ የሂትለር Opposite፣ በዘዴ ግን አንድ አይነት…

ከዚያ ያው ተማሪ ይጎርፍ ጀመር፡፡ ክረምት አስተማርን - ያላሰብኩትን፣ በጣም ብዙ ብር አገኘሁ፡፡ አብሪሎ ብሩን ሳንከፋፈል የራሱን ድርሻ ወስዶ ጨረሰ…

በየቀኑ፣ ልክ አስተምሮ ሲጨርስ፣ 6 ሰዓት ላይ ብር የሚፈልጡት ሰዎች ይመጣሉ፡፡ ይሰጣቸዋል፡፡ 15 ቀን ሳይሞላ ድርሻውን ወስዶ ጨረሷል…

ግን ደግሞ ሌሎች የሚያስጠናቸው ልጆች ስላሉ ገንዘብ አያጣም፡፡ ገንዘብ አብሪሎ ጋር Currency ነው - ልክ እንደ ኮረንቲ ይፈሳል፡፡ ይመጣል፣ ይሄዳል…

የጋሽ አብረሃም ነገር ሙሉ መጽሐፍ የሚወጣው ነው፡፡ በወጉ ተጽፎ ከጥንካሬ እና ድክመቱ ቀጣይ ትውልድ ቢማርበት እንዴት ሸጋ ነው !!!

የጋሽ አብረሃም የሂሳብ ማስጠናት ስልት፣ ዕውቀትን ብቻ ሽተህ ካልሆነ በቀር ለፈተና አይሆንም፡፡ Set Theoryን ሲያስተምርህ አመቱ ሊያልቅ ይችላል…

ጋሼ በራሱ ዓለሙ ውስጥ ነው…

ድሬዳዋ፣ በተለይ የዛን ጊዜዋ ድሬዳዋ ደግሞ፣ እንዲህ አይነት የተራቀቁ ነፍሶችንም ማስተናገድ የምትችል ቅንጡ ነበረች…

የድሬዳዋ ምትሃት አብሪሎን ጠለፈ፤ የአብሪሎ ዕውቀት እና ጥልቅ ስሜት ደግሞ የድሬን ተማሪዎች ቀልብ ጠብ አደረገ…

ሌላ ሀገር ቢሆን ኖሮ፣ ምን ዕውቀት ቢኖርህ ስልትህ ለፈተና ካልሆነ አይታገስህም፡፡ ድሬዳዋ ግን ሁሉ የተትረፈረፈባት ሀብታም ሀገር ስለነበረች የአብሪሎ አይነቱን ወጣ ያሉትን ለዘመናት አስተናገደች…



ከአብሪሎ አንድ መቼም የማልረሳው ነገር አለ - በተለይ አሁን ላይ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ልነግራችሁ ግድ ይለኛል…

አንድ ጊዜ አብሪሎ ተናድዶ፣ ሌሎች መምህራኖችን ሲወቅስ ሰማሁት…

እንዲህ ይላል አብሪሎ፣ “የሂሳብ ፈተና እንደታደለ … ሂሳብ የማይወደው ተማሪ ሁሉ ወዲያው የመሰለውን አክብቦ ይወጣል፡፡ ክፍሉ ውስጥ አንድ ወይ ሁለት ሂሳብ የሚወዱ ተማሪዎች ሲቀሩ፣ ፈታኝ ተብዬው እነዚህን ተማሪዎች ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ እያለ ያስቸኩላል፡፡ እኔ እኮ አሉኝ የምላቸው ተማሪዎች እነዚህ 1 ወይ 2 ተማሪዎች ናቸው፡፡ ይሄን ነገር አቁሙ ብያለሁ - አቁሙ፡፡ ተማሪዎቼን አታስቸኩሉብኝ…”

አብሪሎን ምን ጊዜም በዚህች ንግግሩ አስታውሰዋለሁ - ምንጊዜም !!!

በዚህ ዓመት እንደታየው፣ ወደፊት፣ ማትሪክ ላይ መኮረጅ የማይታሰብ እየሆነ የሚመጣ ይመስለኛል፡፡ መኮረጅ እንደማይቻል ያወቀ ተማሪ ቶሎ ወረቀቱን ሰጥቶ ሲወጣ ታዲያ፣ ጥቂት ቀለሜ ተማሪዎች ብቻ ናቸው ክፍል ውስጥ የሚቀሩት…

እና … ያኔ … ጥቂት የማይባሉ መምህራን፣ ቶሎ በሉ፣ ቶሎ በሉ ብለው ሳያቻኩሏቸው አይቀሩም ብዬ እፈራለሁ…

ምክንያቱም፣ 3 ሰዓት ለሚፈጀው የሂሳብ ፈተና፣ ሁሉም የመልስ ወረቀቱን ቶሎ ሰጥቶ በሄደበት … 3 ተማሪ ብቻ ሲቀር - የሰለቸው ፈታኝ ቶሎ በሉልኝ ብሎ ያቻኩላቸዋል ብዬ በጣም እፈራለሁ - አዎ እፈራለሁ !!!

በቃልም ባይሆን በመቁነጥነጥ ቶሎ ሰርታችሁ ውጡ ሊል ይችላል ብዬ ስጋት አለኝ - እናም የጋሼ ያቺ ወቀሳ ይሄኔ ትውስ ትለኛለች…



አዎን ጋሽ አብረሃም ሞተ…

የአንድ ዘመን ምዕራፍ #ተዘጋ።
እስቲ ይህን ተንተርሳችሁ የምታውቁትን ጻፉ
ይውጣ ይነበብ ትውስታችሁ…

ስርቆት በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር  | 2 ኩንታል የሚመዝኑ የባቡር መስመር የተለያዩ እቃዎች በግለሰብ ቤት ተደብቀው መገኘታቸውን የምድር ባቡር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።በመምሪያው 1ኛ ሻለቃ ...
21/11/2022

ስርቆት በኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር

| 2 ኩንታል የሚመዝኑ የባቡር መስመር የተለያዩ እቃዎች በግለሰብ ቤት ተደብቀው መገኘታቸውን የምድር ባቡር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በመምሪያው 1ኛ ሻለቃ ሬጅመንት አንድ ሻምበል አራት አዛዥ ኢንስፔክተር አድማሱ አብዱራህማን እንዳሉት በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬና በብድር ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈጸሙ የዝርፊያ ወንጀሎችን ህዝብን ባሳተፈ መልኩ የመከላከል ስራ እየተከናወነ ነው።

በዚህም የዝርፊያ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በተደረገ ህዝብን ያሳተፈ ኦፐሬሽንም የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት መገልገያ የሆኑና ሁለት ኩንታል የሚመዝኑ እቃዎች በግለሰብ ቤት ተደብቀው መገኘታቸውን ተናግረዋል።

በህብረሰቡ ጥቆማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በሁለት የማዳበሪያ ከረጢት ተደብው የተገኙት እቃዎች በቁጥር 750 የሚሆኑና የተለያየ አገልግሎት ያላቸው መሆናቸውንም ኢንስፔክተሩ አስረድተዋል።

ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና እንዶዴ (k-37) ተብሎ በሚጠራው የባቡር ጣቢያ አካባቢ የተገኙት የባቡር ሃዲዱንና ምሶሶዎቹን አቅፈው የሚይዙ የተለያዩ ብሎኖች፣ ፓዶችና ሌሎች ቁሳቁሶች መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ለጊዜው ከአካባቢው የተሰወሩ የወንጀሉ ፈጻሚ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ክትትል እየተደረገ እንደሚገኝም አዛዡ ተናግረዋል።

የፌዴራል ፖሊስ አባላት የባቡር መስመሩ ከሚያልፍባቸው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀው በተለይ ህብረተሰቡ የሚሰጠው ጥቆማ ዝርፊያውን ለማስቆም ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ እንደሚገኝም ተናግረዋል።

ኢዜአ

 #ድሬዳዋ | በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር፤ 2ኛ ድሉን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ ልምምዱን ቀጥሏል።ከነገ በስቲያ ረቡዕ ህዳር 14 ከቀኑ 10:00 ከመሪ...
21/11/2022

#ድሬዳዋ | በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር፤ 2ኛ ድሉን በሜዳውና በደጋፊው ፊት ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከተማ ልምምዱን ቀጥሏል።

ከነገ በስቲያ ረቡዕ ህዳር 14 ከቀኑ 10:00 ከመሪው ኢትዮጵያ መድን የሚጫወተው ቡድኑ፤ 1 ሰዓት ከ30 የፈጀ ልምምድ ሰሞኑን በተመረቀውና ኤርፖርት አካባቢ በሚገኘው አዲሱ አርቴፊሻል ሜዳ ላይ አድርጓል።

ቡድኑ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር በነበረው ጨወታ በጡንቻ ህመም ምክንያት ከመጀመሪያ አሰላለፍ ወጥቶ የነበረው የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አቤል አሰበ፤ ከህመሙ ሙሉ ለሙሉ በማገገሙ ሙሉ ልምምዱን ሰርቷል።

በኤሌክትሪክ ጨወታ ላይ ተቀይሮ በመግባት ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሙየዲን ሙሳ ልምምድ ላይ ባጋጠመው የቁርጭምጭሚት ወለምታ ያቋረጠ ሲሆን፤ ለእሮቡ ጨዋታ የመድረስ ሁኔታው አጠራጣሪ ሆኗል።

ከዛ ውጭ ሁሉም ተጫዋቾች የዛሬውን ልምምድ በጥሩ ሁኔታ የሰሩ ሲሆን፤ ቡድኑ ነገ ጠዋት ቀለል ያለ ልምምድ በመስራት ለረቡዕ ጨወታ የሚዘጋጅ ይሆናል።

መረጃው ከክለቡ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ ነው።

የከተማ ልማት ዘርፍ ግምገማ  | የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማት ዘርፍ የ2015 በጀት 1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ተገመገመ። በግምገማ መድረኩ የከተማ ልማት ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ ...
19/11/2022

የከተማ ልማት ዘርፍ ግምገማ
| የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ልማት ዘርፍ የ2015 በጀት 1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ተገመገመ።

በግምገማ መድረኩ የከተማ ልማት ሚኒስቴር እና የድሬዳዋ አስተዳደር የሚመለከታቸው ተቋማት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ የ1ኪሜ የጎርፍ መከላከያ ግንብ ስራ፤ የ11.5 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና አዲሱ ኬላ ጅቡቲ መንገድ በከፊል አስፋልት ማልበስ ሂደት ለ1500 ሰዎች የስራ እድል መፈጠሩ፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች መካሄዳቸው 2200 ሜትር ዲች ሳምንታዊ የጽዳት ዘመቻ ስራዎች፤ 6 የሙያ ምዘና ጣቢያዎች መቋቋማቸው፤ የሩብ ዓመት የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 85 በመቶ መሰብሰብ መቻሉ በቀረበው ሪፖርት ተመላክቷል፡፡

የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ዑመር ዱአሌ የድሬዳዋን የከተማነት ባህሪያት በማስጠበቅ የከተማ አገልግሎቶችን ለማዘመን አመራሩ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው በሚኒስቴሩ ለሚደረገው ድጋፍና ክትትል አመስግነዋል፡፡

በፌዴራል ከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትሩ ኢንጅነር ወንድሙ ሴታ በበኩላቸው በሪፖርቱ በቀረበው አፈፃፀም በርካታ ክንውኖች እየተሻሻሉ መሆናቸውን እንደተገነዘቡ ገለጸው፤ የከተማዋን የገቢ አቅም ማሳደግና ህገወጥ የመሬት ወረራን መከላከል ላይ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡

ሚኒስትሩ አክለውም የአመራሩን ቁርጠኝነት በማድነቅ ለሌሎች ከተሞች በአርአያነት የሚወሰዱ በርካታ ተሞክሮዎችን ከመድረኩ ማግኘታቸውንም ገልጸዋል፡፡

መረጃው የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ነው

የሚኒስትር ዴኤታው ጉብኝት  | በከተማ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የሚመራ ልዑክ ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎ...
19/11/2022

የሚኒስትር ዴኤታው ጉብኝት
| በከተማ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ የሚመራ ልዑክ ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር በዘርፉ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ጎብኝቷል።

የልዑኩ አባላት በጉብኝታቸው በአስተዳደሩ የመንገዶች ባለስልጣን እየተገነቡ የሚገኙ መንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ምን እንደሚመስል ምልከታ አድርገዋል፡፡

የድሬዳዋ ሽንሌና ድሬዳዋ ባይፓስ የ26 ኪሜ መንገድ ግንባታ፤ በተለይም የመካል ጀብዱ መንገድ ግንባታዎች ላይ አስተዳደሩ በትኩረት ክትትል እያደረገባቸው መሆኑንና፤ የወሰን ማስከበር ስራውም በቅርቡ ተጠናቆ ያለችግር ግንባታውን ለማካሄድ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በመስክ ምልከታው ማጠቃለያ በአስተዳደር እየተሰሩ በሚገኙ የመንገድ ፕሮጀክቶች ላይ በጣም አበረታች ውጤት መታየቱን በከተማ ልማት ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ ገልጸዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ምስጋና  | ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ተሰጣቸው። 31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ በ2014 ዓ.ም የ2ኛ...
19/11/2022

የትምህርት ሚኒስትሩ ምስጋና
| ለድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዕውቅና ተሰጣቸው።

31ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባኤ መጠናቀቅን ተከትሎ በ2014 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ሂደት፤ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ቢሮዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች እና ሌሎች ተቋማት የምስጋና እና እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር ተከናውኗል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በንግግራቸው "ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፈተና ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ወቅት ለጥያቄዎቻችን አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ላደረጉልን ድጋፍ እናመሰግናለን" ብለዋል።

በሌላ በኩል የትምህርትና ፈተናዎች ምዘና አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ፤ በሁሉም ባለድርሻ አካላት በተከናወነው ሁሉን አቀፍ ርብርብና የተቀናጀ ስራ የፈተና ሂደቱን ውጤታማ ማድረግ እንደተቻለ በመግለጽ፤ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልክት አስተላልፈዋል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው

Address


Telephone

+251930552921

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ስለ ድሬ - About Dire posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share