Ethiopian grade 12 entrance result

  • Home
  • Ethiopian grade 12 entrance result

Ethiopian grade 12 entrance result Official page of Ethiopian grade 12 entrance result. ምደባ ልለቀቅ ነው፣ ስለዝህ ከወዲሁ የምደባ ውጤት ለማሳየት እናግዛለን።
(2)

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴርየሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስ...
23/04/2024

የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንና ተማሪዎች ልማት ዴስክ ኃላፊ በየነ ተዘራ ለኢፕድ ተናግረዋል፡፡

ከ70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ለ15 ቀናት በኦንላይን፣ በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ለመስጠት እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ጠቁመዋል፡፡

የሪሚዲያል ትምህርት ከታህሳስ ጀምሮ እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም መጨረሻ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ውጤታቸው 30 በመቶ በዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ሒደት እና 70 በመቶ በማዕከል በሚዘጋጅ ፈተና የሚለይ መሆኑን አስረድተዋል፡፡


https://t.me/NEAEAofficial2016

መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.me/global_bank_ref...
13/03/2024

መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል

1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.me/global_bank_referral_bot?start=453803025
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ ዘወትር ቅዳሜ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

 #ማስታወቂያመልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.me/global_...
13/03/2024

#ማስታወቂያ
መልዕክቱን ያጋሩ፣ ከ1ሺህ ብር ጀምሮ ተሸላሚ ይሁኑ!

የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል

1. በመጀመሪያ ቀጣዩን የቦት ሊንክ ይጫኑ፡- https://t.me/global_bank_referral_bot?start=453803025
2. START የሚለውን ይጫኑ፣
3. JOIN CHANNEL የሚለውን ይጫኑ፣
4. ወደ መጀመሪያው ቦት ይመለሱ፣
5. CONTINUE የሚለውን ሲጫኑ የመጋበዣ ሊንክዎን ያገኛሉ፣
6. መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ወዳጅ ዘመድዎ ሼር ሲያደርጉ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በየሳምንቱ ከአንድ ሺ ብር ጀምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ያበረክታል፡፡

ሽልማቱ ዘወትር ቅዳሜ ለተሸላሚዎች ይደርሳል፡፡

ደንብና ሁኔታዎች ተፈፃሚ ናቸው፡፡

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ**************************የግል እና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ...
26/02/2024

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ
**************************

የግል እና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2016 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት መለቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የመውጫ ፈተና ውጤቱን ከዛሬ ጀምሮ ከታች ባለው ሊንክ መመልከት እንደሚቻል ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
https://t.me/NEAEAofficial2016

 #ማስታወቂያለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉየ2016  ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና  ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ ም ጀምሮ  ስለተለቀቀhttps://result.e...
26/02/2024

#ማስታወቂያ

ለሁሉም የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ

የ2016 ዓ .ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና ውጤት ከየካቲት 18/2016 ዓ ም ጀምሮ ስለተለቀቀ

https://result.ethernet.edu.et

ሊንክ ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

ትምህርት ሚኒስቴር!

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም -https://t.me/ethio_moe
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/.../ministry-of-education-ethiopia
በዌብሳይት - www.moe.gov.et ይከታተሉ

 #ማስታወቂያየካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ምለምርምር ጆርናል ባለቤቶችና ለሀገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለምርምር ተቋማት እና ሙያ ማህበራት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር...
22/02/2024

#ማስታወቂያ

የካቲት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ለምርምር ጆርናል ባለቤቶችና ለሀገር ውስጥ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፣ ለምርምር ተቋማት እና ሙያ ማህበራት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በሀገር ውስጥ የሚታተሙ የምርምር ጆርናሎች ጥራትና እይታን ለማሳደግ ሲባል የምዘናና እውቅና አሰራር ስርአት መዘርጋቱ ይታወቃል፡፡

ስለሆነም ከተመሰረተ 3 አመት የሞላቸው ጆርናሎችን የምታስተዳድሩና የእውቅና አሰጣጥ መመሪያ Amended Guideline for Evaluation of Journals Published in Ethiopia No.: Research 01/2019) መስፈርቶችን የምታሟሉ ተቋማት በጆርናሉ ዋና አርታኢ በኩል ይህ ደብዳቤ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ አምስት (15) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ

http://survey.ethernet.edu.et/index.php/888858?lang=en

የተቀመጠውን ቅጽ በመጠቀም እንድታመለክቱ ጥሪ እያደረግን ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ
[email protected]

በመላክ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
ይህ ማስታወቂያ በ2015 ዓ.ም አራተኛ ዙር ያመለከቱትንና ለዳግም እውቅና አመልክተው ፍተሻው በሂደት ላይ ያሉትን ጆርናሎች አይመለከትም፡። ይሁን እንጂ የግምገማ ውጤቱ እንደታወቀ መስፈርቱን ባለማሟላት እውቅና ለማያገኙ አመልካቾች ሚ/ር መስሪያ ቤቱ ወደፊት በልዩ ሁኔታ የሚያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፤

ማንኛውም አመልካች የሀገር ውስጥ ጆርናሎች ፍተሻ እና እውቅና አሰጣጥ Amended Guideline for Evaluation of Journals Published in Ethiopia No.: Research 01/2019) መስፈርቶችን ማሟላት ይጠበቅበታል፤

ትምህርት ሚኒስቴር

 የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ ።..................................................የካቲት 7/2016 ዓ.ም (ትሚ) የ...
15/02/2024


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ ።
..................................................
የካቲት 7/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞች ምዝገባን በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች የመመዝገቢያ መስፈርቱን በማሟላት በተቀመጠው የጊዜ ገድብ መመዝገብ እንዳለባዉ አብራርተዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም እንደሚከተለው አሳስበዋል።

1. በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ እንዳለባቸው ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ

2. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል

3. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ መቻል

4. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት እንደሚሆን

5. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወረዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች እንደሚከናወን የየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።

የ Grade 12 entrance result መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
https://t.me/NEAEAofficial2016

በዚህ የፌስቡክ ገፅ እና የ (ቴሌግራም) ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ተደራሽ ያድርጉ! አዲስ የከፈቱትን ቢዝነስ ያስተዋውቁ። ለበለጠ መረጃ በውስጥ መስመር 👌
14/02/2024

በዚህ የፌስቡክ ገፅ እና የ (ቴሌግራም) ላይ ምርትና አገልግሎትዎን ተደራሽ ያድርጉ! አዲስ የከፈቱትን ቢዝነስ ያስተዋውቁ። ለበለጠ መረጃ በውስጥ መስመር 👌

 ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀመረ .............................................የካቲት 6/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙ...
14/02/2024


ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች መሰጠት ጀመረ
.............................................
የካቲት 6/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት ጀምሯል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት የተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል የተመደቡ ታዛቢዎችም በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ ጀምረዋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች የሚፈተኑ ሲሆን የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
https://t.me/NEAEAofficial2016

 ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል። የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸውም ተገልጿል ።.........
13/02/2024


ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የፈተና አሰጣጡን ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅ ከዩኒቨርስቲዎች ታዛቢዎች መመደባቸውም ተገልጿል ።.................................................
የካቲት 5/2016ዓ.ም (ትሚ)ሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከነገ የካቲት 6–11 /2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጅና(ፒኤችዲ) የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በ2015 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ በሁሉም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተግባራዊ መደረጉንና በመውጫ ፈተና ማስፈጸሚያ መመሪያ ቁጥር 919/2014 ድንጋጌ መሠረት ፈተናው በዓመት ሁለት ጊዜ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

የሁለተኛ ዙር ፈተናው በ47 የመንግስት ተቋማት በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145 ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች እንደሚፈተኑ ተናግረዋል።

የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ እንዲቻል በሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ታዛቢዎችን መመደባቸውንም ዶ/ር ኤባ ገልጸዋል ።

የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚው ታዛቢዎቹ ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተመለመሉ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-
https://t.me/NEAEAofficial2016

 #ማስታወቂያ1000 Birr (አንድ ሺ ብር) ሽልማት አሁኑኑ!ሁላችሁም ትሸለማላችሁከታች ያለዉን Telegram Bot ሊንክ በመጠቀም በተቀመጠዉ ቅደም ተከተል የቴሌግራም ቻናላችንን ለ50 እና...
10/02/2024

#ማስታወቂያ
1000 Birr (አንድ ሺ ብር) ሽልማት አሁኑኑ!
ሁላችሁም ትሸለማላችሁ

ከታች ያለዉን Telegram Bot ሊንክ በመጠቀም በተቀመጠዉ ቅደም ተከተል የቴሌግራም ቻናላችንን ለ50 እና ከዛ በላይ ሰዎች በመጋበዝ የ1 ሺ ብር ተሸላሚ ይሁኑ!

1 - በቅድሚያ ቀጥሎ
ያለውን ሊንኩን ይጫኑ https://t.me/official_oromia_bank_bot?start=453803025
2 - በመቀጠል Start የሚለውን ይጫኑ
3 - Join Channel የሚለውን ይጫኑ
4 - ወደ ቦቱ ይመለሱ
5 - Continue ሚለውን ተጭነው የመጋበዣ የሼር ምልክት⤴️ ያግኙ
6 - መልእክቱን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ

መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ሰዎች በመጋበዝ አሁኑኑ የ1000 ብር ተሸላሚ ይሁኑ!

አሁኑኑ ሼር ማድረግ፣ ይጀምሩ ቀድመው ያሸንፉ!

 #ማስታወቂያየአንድ ሺ ብር ሽልማት አሁኑኑ!ሁላችሁም ትሸለማላችሁከታች ያለዉን Telegram Bot ሊንክ በመጠቀም በተቀመጠዉ ቅደም ተከተል የቴሌግራም ቻናላችንን ለ50 እና ከዛ በላይ ሰዎች...
09/02/2024

#ማስታወቂያ
የአንድ ሺ ብር ሽልማት አሁኑኑ!
ሁላችሁም ትሸለማላችሁ

ከታች ያለዉን Telegram Bot ሊንክ በመጠቀም በተቀመጠዉ ቅደም ተከተል የቴሌግራም ቻናላችንን ለ50 እና ከዛ በላይ ሰዎች በመጋበዝ የ1 ሺ ብር ተሸላሚ ይሁኑ!

1 - በቅድሚያ ቀጥሎ
ያለውን ሊንኩን ይጫኑ https://t.me/official_oromia_bank_bot?start=453803025
2 - በመቀጠል Start የሚለውን ይጫኑ
3 - Join Channel የሚለውን ይጫኑ
4 - ወደ ቦቱ ይመለሱ
5 - Continue ሚለውን ተጭነው የመጋበዣ የሼር ምልክት⤴️ ያግኙ
6 - መልእክቱን ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ

መልዕክቱን ቢያንስ ለ50 እና ከዚያ በላይ ሰዎች በመጋበዝ አሁኑኑ የ1000 ብር ተሸላሚ ይሁኑ!

አሁኑኑ ሼር ማድረግ፣ ይጀምሩ ቀድመው ያሸንፉ!

 #ማ ስ ታ ወ ቂ ያ https://t.me/NEAEAofficial2016ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉየካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና  ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ...
08/02/2024

#ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

https://t.me/NEAEAofficial2016
ለድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ
የካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የ ድጋሚ (Re-exam) ተፈታኞች በሙሉ የመፈታኛ የይለፍቃል (Password) ከታችበተዘረዘሩት አማራጮች ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. በምዝገባ ወቅት በሞላችሁት email በኩል

2. https://exam.ethernet.edu.et ላይ በመግባት የከፈላችሁበትን Transaction Number በማስገባት እንዲሁም

3. ከተመደባብችሁብት የመፈተኛ ተቋም ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ
• ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች የይለፍቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ወይም ከተመደባብችሁበት የመፈተኛ ተቋም ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን።

• ሁሉም ተፈታኞች የሞዴል ፈተናን እስከ የካቲት 5/2016 ዓ.ም መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ትምህርት ሚኒሰቴር !

የትምህርት ሚኒስቴርን መረጃዎች በሚከተሉት ማስፈንጠሪያዎች ያግኙ፡-

በፌስቡክ
https://t.me/NEAEAofficial2016

 https://t.me/NEAEAofficial2016 ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል። በዚህም በሁለቱም የትምህ...
20/01/2024


https://t.me/NEAEAofficial2016


ትምህርት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም በሚሰጡ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የትምህርት አይነቶች ላይ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህም በሁለቱም የትምህርት መስኮች እያንዳንዳቸው በስድስት የትምህርት አይነቶች ፈተናው እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡

የተፈጥሮ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

የማኅበራዊ ሣይንስ፦
እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚክስ እና ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት

ለሁሉም ክልሎች እና ለሁለቱ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የተፃፈው ሰርኩላር፤ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝግጅትንም ያብራራል።

በዚህም የኢኮኖሚክስ ፈተና ለ2016 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል ብቻ ፈተናው የሚዘጋጅ ሲሆን ሌሎች የትምህርት አይነቶች ከ9-11ኛ ክፍሎች በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት እንዲሁም የ12ኛ ክፍል በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት እንደሚሆን ያትታል።

ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴስት ወደፊት ጥናት ተጠንቶ እስከሚለይ ድረስ በነበረው አሠራር መሠረት ውጤት ተደምሮ የሚገለጽ መሆኑንም ገልጿል።

የፈተና አሰጣጡን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ለወላጆች፣ ለመምህራን እና ለትምህርት ማህበረሰቡ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ከወዲሁ እንዲያውቁት እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።


https://t.me/NEAEAofficial2016

 https://t.me/NEAEAofficial2016ማስታወቂያየመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተ...
16/01/2024


https://t.me/NEAEAofficial2016
ማስታወቂያ
የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉ

ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ስለሆነም በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የምታካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የምትመርጡት ከታች በተገለጸው ማስፈንጠሪያ (Link)
(https://exam.ethernet.edu.et)
ስለሆነ፣ ከጥር 08 እስከ ጥር 15/ 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

አመልካቾች ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር +251 118 13 21 76 ወይም በኢሜይል [email protected] በኩል ድጋፍ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ማሳሰቢያ
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመዉጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የምታካሂዱት እና የአገልግሎት ክፍያ የምትፈፅሙት በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊው የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።


https://t.me/NEAEAofficial2016

 #ማስታወቂያየRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ...
08/12/2023

#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
• የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።

• የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

o Website: https://t.me/NEAEAofficial2016

o Telegram : https://t.me/NEAEAofficial2016

ትምህርት ሚኒስቴር

 #ማስታወቂያየRemedial ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተበ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት...
15/11/2023

#ማስታወቂያ

የRemedial ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ህዳር 12/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡ -

ከታች የተዘረዘሩ ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም የማያስተናግዱ መሆኑን እንገልጻለን።

1. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

2. አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

3. አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

4. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ

5. አርሲ ዩኒቨርሲቲ

6. ኮተቤ የትምህርት ዪኒቨርሲቲ


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ

https://t.me/NEAEAofficial2016

 የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ተለቀቀ**********************የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ጥቅምት 24/ 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3:0...
04/11/2023


የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ተለቀቀ
**********************
የትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ጥቅምት 24/ 2016 ዓ/ም ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ የተለቀቀ በመሆኑ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ፡፡

ውጤቱን በድረ ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስም ብቻ በማስገባት ውጤት መየት እንደሚቻል ከአገልግሎቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

በውጤት ላይ ቅሬታ ካለ በአካል መምጣት ሳያስፈልግ በተመሳሳይ ድረ ገጽ ላይ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ/ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ማቅረብ የሚቻል እና ምላሽም በተመሳሳይ መልኩ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል።

ውጤቱን ለማየት Join ይበሉ

https://t.me/NEAEAofficial2016

 https://t.me/NEAEAofficial2016የ2015 ዓ.ም  12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።==============...
03/11/2023


https://t.me/NEAEAofficial2016
የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቅም ማሻሻያ (Remedial Program) መከታተያ የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።
==============//===================
ጥቅምት 23/2016 ዓ .ም (ትምህርት ሚኒስቴር ) በ2015 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም መከታተያ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የከፍተኛ ትምህርት የአስተዳደርና መሠረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር ) እንደገለጹት በ2016 በግልና የመንግስት ተቋማት የአቅም ማሻሻያ /Remedial Program / የሚከታተሉ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ እንደተፈተኑት የትምህርት ዓይነት ብዛት 30% እና ከዚያ በላይ ሆኗል ።

በዚህም መሠረት በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ለመማር የመቁረጫ ነጥብ የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 255 የተፈጥሮ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 234 መሆኑን አስታውቀዋል።

የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ወንድ ተማሪዎች 218 የማህበራዊ ሳይንስ ለመደበኛና የማታ ሴት ተማሪዎች 200 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 224 ታዳጊ ክልሎች ተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 210 መሆኑን ተናግረዋል።

ታዳጊ ክልሎች የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች መግቢያ 192 ታዳጊ ክልሎች ማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች መቁረጫ180 መሆኑን አመልክተዋል።

አርብቶ አደር አካባቢ የተፈጥሮ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ፆታ 210 መሆኑን ተናግረዋል።

አርብቶ አደር አካባቢ ማህበራዊ ሳይንስ መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ጾታ 180 መሆኑን ገልጸዋል።

የዓይነ ስውራን ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች መቁረጫ ነጥብ በሁለቱም ጾታ ደግሞ 150 መሆኑንም ዶ/ር ሰለሞን ጠቅሰዋል።

ዶ/ር ሰለሞን እንደገለጹት የ2015 ትምህርት ዘመንን ተሞክሮን ከግምት ውስጥ በማስገባት የገጠመውን የውጤት መቀነስ ለማስተካከል በ2016 ትምህርት ዘመን የማካካሻ ትምህርት (Remedial Program) በድጋሚ እንዲተገበር ተወስኗል።

በመቁረጫ ነጥቡ መሰረት የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራሙን የሚከተተሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ በቀጣይ ይካሄዳል።።


https://t.me/NEAEAofficial2016


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ

https://t.me/NEAEAofficial2016

 የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ***የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ምደባን ይፋ አደረገ፡፡በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ...
03/11/2023


የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ
***

የትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ምደባን ይፋ አደረገ፡፡

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ እና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተናውን ወስደው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉም ተገልጿል።

የ 2015 ትምህርት ዘመን የ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱና 30 በመቶ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፤ የማካካሻ ፕርግራም(ሪሚዲያል) ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ነው የትምህርት ሚኒስቴር የገለፀው።

ሰላሳ በመቶ ያመጡ ተማሪዎች በመንግስትና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አማራጮች የማካሻሻ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመቁረጫ ነጥብ መወሠኑን ነው ሚኒስቴሩ የጠቆመው።

በመንግስት ዩኑቨርሲቲዎች የመቀበል አቅምን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ምደባ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 255 ያመጡ፣ ሴቶች 234፣በማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 218 ያመጡ እና ሴቶች ደግሞ 200 ያመጡ መደበኛና የማታ ተማሪዎች፤ ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የማካካሻ ፕሮግራም ተጠቃሚ ይሆናሉ።

በታዳጊ ክልል የተፈጥሮ ሳይንስ ወንዶች 224፣ ሴቶች 210፣ የማህበራዊ ሳይንስ ወንዶች 192 ፣ ሴቶች 180 ያመጡ በመንግስት ተቋማት መግባት ይችላሉ።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል።

Website:
https://t.me/NEAEAofficial2016


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ

https://t.me/NEAEAofficial2016

 #የዩኒቨርስቲ ምደባ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያየተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-1.  1...
01/11/2023

#የዩኒቨርስቲ ምደባ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ አሰራርን አስመልክቶ የተሰጠ ማብራሪያ

የተማሪ ምደባ መስፈርቶች፡-

1. 1000 ለሚሆኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፡- የምደባ ስርዓቱ በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች 1000 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመጀመሪያ የዩኒቨርስቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸው ምደባ የሚካሄድ ይሆናል።

2. ውጤት፡- የምደባ ስርዓቱ እያንዳንዱ ተማሪ ያስመዘገበውን አጠቃላይ ውጤት በምደባ ስርዓት ሂደት ውስጥ መለያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሌሎች ተፈጻሚ የሚሆኑ ህግና ደንቦችን ባልጣሰ መልኩ ምርጫቸውን በመጠበቅ ረገድ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

3. የዩኒቨርሲቲ ምርጫ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የቅበላ አቅም ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ተማሪዎች 46 ዩኒቨርሲቲዎች ለምርጫ ቀርበውላቸዋል፡፡ መረጃው የተሰበሰበው https://portal.etherenet.edu.et ላይ ነው፡፡

4. በተማሪዎች የተመረጡ ተቋማት ያላቸው የትምህርት ፕሮግራሞች ፡- የምደባ ስርዓቱ በተማሪዎች የተመረጡ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የተመረጡት ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራም መሰረት ያደረገ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

5. ጾታ ፡- በተቋማት የጾታ ተዋጽኦን ለመጠበቅ በሚኖረው የምደባ ስርዓት የጾታ ተዋጽኦና ሚዛን እንዲጠበቅ ተደርጓል፣

6. የትምህርት ቤት ተዋጽኦ ፡- የምደባ ስርዓቱ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚመደቡ ተማሪዎችን ተዋጽኦ በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ያግዛል፡፡ይህም ከአንድ ት/ቤት የወጡ ተማሪዎች በአንድ ዩኒቨርሲቲ ወይም ፕሮግራም ውስጥ እንዳይታጨቁ ይደርጋል፡፡

7. የውጤት ተዋጽኦ ፡-የምደባ ስርዓቱ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ታሳቢ ያረገ ሲሆን ይህም ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች አንድ ላይ እንዳይመደቡ በማድረግ የተለያየ ችሎታና ተሰጥኦ ያላቸው ተማሪዎችን ቀላቅሎ ለማስተማር ያግዛል፡፡

8. ወሊድን በተመለከተ፡- የምደባ ስርዓቱ እንደ ወሊድ ያሉ ልዩ ሁኔታዎችን ያማከለ ነው፡፡ በመሆኑም በመሰል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመቀጠል የሚቸገሩ ከሆነ ትክክለኛ ለውጥና ድጋፍ የሚደረግ ይሆናል፡፡ መረጃዎቹ የተሰበሰቡት https//student.ethernet.edu.et ላይ ነው፡፡

•አስፈላጊ ማስረጃዎች: - ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የህጻናት የክትባት ካርድ

9. ትክክለኛ የሕክምና ቦርድ ማስረጃዎች፡- በምደባ ወቅት የጤና ችግር ኖሮባቸው ትክክለኛ የሕክምና ማስረጃ ላላቸው ተማሪዎች ምደባው በተለየ መልኩ ሊታይ ይችላል፡፡
• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡ ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና ከህዝብ ጤና ተቋማት የህክምና ምስክር ወረቀት በሶስት ዶክተሮች እና በህክምና ዳይሬክተሩ የጸደቀ።
• የዚህ አይነት መረጃ የተሰበሰበው https://student.ethernet.edu.et በመጠቀም ነው።

10. ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች (identical twins) ፡- በተማሪዎቹ መካከል ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትዮች ካሉ የምደባ ስርዓቱ ከፍተኛ ነጥብ ያገኘው/ችው ተማሪ ከተመደበበት/ችበት የትምህርት ተቋም ቀሪው መንትያ ደግሞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በቀጥታ ይመድባል። የዚህ አይነት መረጃ የተሰበሰበው https://student.ethernet.edu.et ላይ ነው።
• አስፈላጊ ማስረጃዎች፡- ከትምህርት ቤታቸው የድጋፍ ደብዳቤ እና የልደት የምስክር ወረቀት፣

11. የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች:- የምደባ ሲስተ

 በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፋችሁና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ...
20/10/2023



በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፋችሁና በምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ ለምትሹ ተማሪዎች ማመልከቻችሁን በ https://student.ethernet.edu.et በኩል እስከ ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም እንድታመለክቱ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ምንም አይነት ማመልከቻ በአካል #የማይቀበል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ https://t.me/MoE2016

የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ይከናወናል -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ*******************የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታ...
19/10/2023

የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ ይከናወናል -ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ
*******************

የዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምደባ ችሎታና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ የሚከናወን እንጂ በማንም ተጽዕኖ የሚቀየር አይደለም ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።

በ2014 የትምህርት ዘመን በመንግስትና በግል የሪሚዲያል ፈተና ከወሰዱ 145 ሺህ ተማሪዎች መካከል 90 ሺህ ያህሉ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት አስመዝግበዋል።

እነዚህ ተማሪዎች በ2015 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ካመጡት ከ27 ሺህ በላይ ተማሪዎች ጋር ተደምረው በአጠቃላይ ከ117 ሺህ በላይ ተማሪዎች ወደ ተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይመደባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ትናንት ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ የዘንድሮ የተማሪዎች ምደባ ችሎታቸውንና ፍላጎታቸውን መሰረት ባደረገ መልኩ በፍትሐዊነት እንደሚከናወን ገልጸዋል።

ቀደም ሲል በተማሪዎች ምደባ ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችን ታሳቢ በማድረግ ክፍተቶች ተለይተው እንዲስተካከሉ መደረጉንም አብራርተዋል።

በመሆኑም በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ተማሪዎች በችሎታቸውና በፍላጎታቸው መሰረት እንዲመደቡ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የህክምና ክትትል እያደረጉ መሆኑን ትክክለኛ ማስረጃ ከሚያቀርቡ ተማሪዎች ውጪ የዝውውር ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለውም ተናግረዋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ምደባ ለማስቀየር ጥያቄ እንደሚያቀርቡ የተናገሩት ፕሮፈሰሩ የተማሪዎቹ ምደባ በማንም ተጽዕኖ ምክንያት ሊቀየር አይችልም ብለዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩል የሚገለገልባቸው በመሆኑ፤ ማንኛውም አካል ስልጣኑን ተጠቅሞ የተለየ ጥቅም ለማግኘት መሞከር እንደሌለበትም አስገንዝበዋል።


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ https://t.me/MoE2016

 #ማስታወቂያበ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ)  ለመማር ያ...
19/10/2023

#ማስታወቂያ

በ 2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን በየትምህርትቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፡

 በልዩ ሁኔታ በአዳማ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርሲቲዎች መማር የምትፈልጉ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የማይሰጥ መሆኑን አውቃችሁ ምርጫችሁ ውስጥ በማካተት መመደብ የምትችሉ መሆኑ እናሳውቃለን።

የትምህርት ሚኒስቴር


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ https://t.me/MoE2016

 " ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋየትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች ...
19/10/2023


" ዘንድሮ 164,242 ተማሪዎችን በሬሜዲያል እንቀበላለን " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ በዘንድሮው ዓመት 164,242 ተማሪዎች በአቅም ማሻሻያ (ሬሜዲያል) ፕሮግራም እንደሚታቀፉ አሳውቀዋል።

እንዚህ ተማሪዎች በግልና በመንግሥት ተቋማት የሬሜዲያል ትምህርት የሚከታተሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ፕ/ር ፕርሃኑ ነጋ ምን አሉ ?

- በ2014 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ፦

• ወደ መንግሥት ተቋማት ተመድበው የሬሜዲያል ትምህርት ከተከታተሉት 105,00 ተማሪዎች 63,033 ተማሪዎች አልፈዋል።

• በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ተከታትለው ከተፈተኑት ውስጥ 44,500 ተማሪዎች 27,587 ተማሪዎች አልፈዋል።

በአጠቃላይ ወደ 145,000 ገደማ ተማሪዎች ሬሜዲያል ገብተው በዛው በተቋማቸው ከ30% እንዲሁም ከማዕከል 70% ተፈትነው ከ50% እና በላይ አምጥተው ያለፉት 90,620 ተማሪዎች ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች ዘንድሮ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በ2015 ዓ/ም ብሔራዊ ፈተና ተፈትነው ያለፉት ተማሪዎች 3.2 በመቶ ብቻ ናቸው። እነዚህ ተማሪዎች 27,267 ገደማ ናቸው። በቀጥታ ፌሽማን / አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ።

- በአጠቃላይ በ2014 ዓ/ም ተፈትነው ሬሜዲያል ያለፉና በ2015 ዓ/ም 50 በመቶ አምትጥተው በቀጥታ ያለፉትን ጨምሮ 117,887 ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይሆናሉ። (90,620 ከሬሜዲያል፤ 27,267 ከ2015 ዓ/ም አላፊዎች)

- ዘንድሮ በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡት 191, 509 ተማሪዎች ናቸው። ከነዚህ ውስጥ 164,242 የሬሜዲያል ተማሪዎች ናቸው፤ እነዚህ በግል እና በመንግሥት ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል።


https://t.me/MoE2016


ለፈጣን መረጃ ከFacebook በተጨማሪ የTelegram Channel ቤተሰብ ሁኑ በዝህ ማስፈንጠሪያ https://t.me/MoE2016

ማስታወቂያ -የቅሬታ ምላሽን ይመለከታል። በ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለይ በአካል በመምጣት ቅሬታ ላቀረባችሁ በስልክ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ምላሽ ተሰጥቷል። እ...
17/10/2023

ማስታወቂያ -የቅሬታ ምላሽን ይመለከታል።

በ2015 ት/ት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ለይ በአካል በመምጣት ቅሬታ ላቀረባችሁ በስልክ ወይም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ምላሽ ተሰጥቷል። እየተሰጠም ይገኛል።

በበይነ መረብ(Online) ቅሬታ ያቀረባችሁ ምላሹም በበይነ መረብ የተሰጠ በመሆኑ ከዚህ በፊት ውጤት ባያችሁበት መልኩ በድረ ገጽ eaes.et ላይ ምላሹን ማየት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

በቁጥር የተወሰኑ ቅሬታዎች በምላሽ ሂደት ላይ ያሉ በመሆኑ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን።

የት/ት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት



" ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንዲጠናከር ይደረጋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከታች ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ይጠናከራል አለ።አገልግ...
14/10/2023

" ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንዲጠናከር ይደረጋል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ከታች ጀምሮ የሚሰጠውን ፈተና ይጠናከራል አለ።

አገልግሎቱ ፤ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የገጠመውን የውጤት ማሽቆልቆል ለመቅረፍ ከታች ጀምሮ የሚሰጠው ፈተና እንደሚጠናከር ይደረጋል ብሏል።

" ለውጤት መቀነስ አንዱ ምክንያት ተማሪዎች በታችኞቹ የትምህርት ደረጃዎች በተገቢው ፈተና እየወሰዱ አለመምጣታቸው ነው " የሚለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " ይህም ተማሪዎች በየደረጃው ማወቅ ያለባቸውን እንዳያውቁ አድርጓል " ብሏል።

ይህ ሁኔታ በስተመጨረሻ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት እንዲያመጡ ማድረጉን አመልክቷል።

ችግሩን ለመቅረፍ ተማሪዎች በተገቢው ምዘና እንዲያልፉ እንደሚደረግ ያሳወቀው አገልግሎቱ ይህንም ለመተግበር በ8ኛ ክፍል የሚሰጠውን ፈተና ከማጠናከር ባለፈ በየትምህርት ቤቶች የሚሰጠውን ምዘና ለማጠናከር ይሰራል ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ግን ሁሉን አቀፍ የማሻሻል ስራዎች እንደሚያስፈልግ እና እንደሚሰራ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኤፍቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል።


https://t.me/Ethiopian_Grade_12EntranceResult

 በሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ተማሪዎችን ሲያስተምሩና ደመወዝ ሲበሉ የቆዩ ግለሰቦች ተፈረደባቸው።ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማሰራት በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበ...
13/10/2023


በሀሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ተማሪዎችን ሲያስተምሩና ደመወዝ ሲበሉ የቆዩ ግለሰቦች ተፈረደባቸው።

ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማሰራት በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ 3 ግለሰቦች ያለ ብቃታቸው እና ያለ ሙያቸው ሲያስተምሩ በመገኘታቸው ክስ ተመስርቶባቸው ውሳኔ ተላለፈባቸው።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ፣
2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ፣
3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ የተባሉት ግለሰቦች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ውስጥ " አንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት " በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ተቀጥረው ያለ ሙያቸው እና ያለ ብቃታቸው ተማሪዎችን ሲያስተምሩ ተይዘው የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

1ኛ ተከሳሽ እዮብ ዲኖ ፦ ከአርባ ምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ #በባዮሎጂ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 10/04 /2011 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያየ የደመወዝ መጠን #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 215 ሺህ 739 ብር ተከፍሎታል።

2ኛ ተከሳሽ ደስታ ዳርጫ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ #በእንግሊዘኛ መምህርነት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከ04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት #በሂሳብ መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 800 ብር ተከፍሎታል።

3ኛ ተከሳሽ በላቸው በየነ ፦ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ኮሌጅ በሂሳብ ትምህርት በዲፕሎማ እንደተመረቀ በማስመሰል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ አዘጋጅቶ ከቀን 04/07/2012 ዓ/ም ጀምሮ በአንዝሬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነት ተቀጥሮ ሲያስተምር ቆይቶ በድምሩ 119 ሺህ 008 ብር ደመወዝ ተከፍሎታል።

ሶስቱም ተከሳሾች ያለሙያቸውና ብቃታቸው ሲያስተምሩ በቆዩባቸው ጊዜያት በተማሪዎች ላይ በገንዘብ የማይተመን እጅግ ከፍተኛ ጉዳት እና በመንግሥት ላይ ባልተገባ መልኩ በተቀበሉት ደመወዝ 455, 755 የሚገመት ብር ጉዳት አድርሰዋል።

ዓቃቤ ህግ በፈፀሙት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማዘጋጀት እና በመገልገል በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ የሙስና ወንጀል ክስ መስርቷል።

የበሉትን ደመወዝም እንዲመልሱ በክሱ ላይ ቀርቧል።

የወልቂጤ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዓቃቤ ህግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች ከበቂ በላይ ናቸው በማለት ሶስቱም ተከሾች ጥፋተኛ ብሏቸዋል።

እያንዳንዳቸው በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እና በ2 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እንዲሁም ያለአግባብ የበሉትን አጠቃላይ 455,755 ብር ለመንግሥት እንዲመልሱ ውሳኔ አሳልፏል።
©tikvah_et

አሁንም ነጥብ እያሳየን 👇👇 Join በማድረግ Reg. Number እና First Name ይላኩልን

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian grade 12 entrance result posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopian grade 12 entrance result:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share