Yealem Tube

Yealem Tube አላማዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርአት የጠበቁ አገልግሎቶችን ለሰው ልጆች ሁሉ ማድረስ ነው

14/11/2022

ሙሉ ስርዐቱን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ
#መዝሙር #ኦርቶዶክስ #ወረብ
https://youtu.be/DJj0KAeal_A

13/11/2022

ምድረ ከብድ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም

13/11/2022

ተፈጸመ ጽጌ በቦሌ መድኃኔዓለም Ethiopin Ortodox Mezmur
Sunscribe and folloe us on Yealem Tube
https://youtu.be/DJj0KAeal_A

12/11/2022
አቡነ  """"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""አረጋዊ ማለት ሽማግለ ወይም የልጅ አዋቂ ማለት ሲሆን አባታቸው ይስሃቅ እናታቸው እድና ይባላሉ::በቈ...
24/10/2022

አቡነ
""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
አረጋዊ ማለት ሽማግለ ወይም የልጅ አዋቂ ማለት ሲሆን አባታቸው ይስሃቅ እናታቸው እድና ይባላሉ::በቈስጥንጥንያ ወይም በሮም በታህሳስ ፲፬ ፫፻፸፭ ዓ.ም ተወለዱ::
በ፲፬ ኣመታቸው ወደ ገዳም ገቡ:: ከአባ ጳኩሚስ እጅ ምንኩስናን ተቀበሉ::ከ፰ ቅዱሳን ጓደኞቻቸው ጋር በ፬፻፷፮ ዓ.ም ወደ ታላቂቷ ሀገር ኢትዮጵያ መጡ::ደብረ ዳሞ የቀድሞ ስሙ ሃሌ ሉያ ይባል ነበር:: ከዚያ ተራራ ስር ማን ያውጣኝ እያሉ ሲፀልዩ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል ዘንዶ ላከለት ዘንዶም ቁመቱ 60 ክንድ ነበር። 30 ክንድ ወደፊት 15 ክንድ ወደ ኋላ ከመሀል ያለው 15 ክንድ ወገባቸው ላይ ተጠምጥሞ ጥቅምት ፲፪ ቀን መልዓኩ ዘንዶውን እያዘዘው ተራራውን ላይ ወጡት::ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በተወለዱበት በ150 ዓመታቸው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ከወጡ በኋላ በሞት ፋንታ በጥቅምት፲፬ ቀን ፭፻፳፭ ዓ.ም #ተሰውረዋል::
የእግዚአብሔር መንግስት በኃይል ስትመጣ እስከያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ አላቸው ማር ፡ 9፡-1-2 ስለዝህ ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ አልሞቱም ተሰውረዋል:: “ የፃድቅ ፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይል ታደርጋለች” ያዕ፡ 5-16፣ ማቴ፡ 10-40፣ መዝ፡ 88-3 መዝ፡67-35
" መዝ.፻፲፩.፮
ለዝህም ነው በየዓመቱ ከተሰወሩበት ጀምሮ ጥቅምት 14 የቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዝክረ በዓል ሆኖ እስከ አሁን እንደሚታዩት በደብረ ዳሞ ገዳም ይከበራል እስከ ዳግም ዕለተ ምፅኣት #ይከበራል።
የአቡነ አረጋዊ በረከት ረድኤት አይለያቹህ አይለየን፣ ለእግዚኣብሔር ክብር ምስጋና ይግባው፣ ዘለአለማዊ ስቡሕ አምላክ ከኛ ጋር ይሁን።ወለተ ተክለሃይማኖት
ወስበሐት ለእግዚአብሔር ይቆየን

https://youtu.be/zfjfCtNCgGQ
22/10/2022

https://youtu.be/zfjfCtNCgGQ

orthodox mezmur,orthodox mezmur 2017,new orthodox mezmur,Mirtnesh Tilahun,mertinesh tilahun,Zemariam,best ethiopian,mezmur tube,orthodox,all mirtnesh tilahun...

22/10/2022

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት ይሆናት ዘንድ ሙሉ ትምህርቱን በዚህ ይከታተሉ Yealem Tube
https://youtu.be/bn-M6Nm_6pE

18/10/2022

#ግዕዝ #ዕዝል #አራራይ በሊቃውንቱ አንደበት
ሙሉውን በዚህ ሊንክ ይመልከቱ
https://youtu.be/01iwyeo3T_8

16/10/2022

አርሴማ ነይ ነይ አርሴማ

💚💛❤️ኢትዮጵያ💚💛❤️👉ኢትዮጵያ ማለት ልዩ ነው ትርጉሙ።➊.ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው። :➋.ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ...
12/10/2022

💚💛❤️ኢትዮጵያ💚💛❤️

👉ኢትዮጵያ ማለት ልዩ ነው ትርጉሙ።
➊.ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው።
:
➋.ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
:
➌.ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር አይደለችም።
:
➍.ኢትዮጵያ ማለት ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት።
:
፩."ብሉይ ኪዳን!"
:
➊ኛ).ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው ኢትዮጵያዊው ዮቶር ነው።
:
ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው።
:
አዎ የዮቶር ርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
➋ኛ).አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።
:
ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን ኢትዮጵዊት ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር። እግዚአብሔርም ገሰፃቸው።
:
➌ኛ).አብርሐምን የቀባው የክርስቶስ ምሳሌ የሚባለው የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው።

ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።

➍ኛ).በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
ይህንን ቦታ ምዕራባውያንና አንዳንድ የምሥራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።
:
➎ኛ).ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ /ቤተ-ክርስቲያን/ ውስጥ ነው።

ይህ ቋንቋ ዓለም እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ ልሣን ነው። ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባውያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምሥጢራት ተከትበዋል።

➏ኛ).ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው።
:
የሰው ልጅ ኃጢአትን በመሥራቱ እግዚአብሔር ምድርን በንፍር ውኃ መላት፣ ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
:
➐ኛ). ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት ኢትዮጵያ/ ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው።
:
➑ኛ).የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአቱተ ባሕርያተ ሥጋ ነው።
:
ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች አዳምና ሄዋን ኢትዮጵያዊያን ናቸው ይላሉ።
:
እውነት ነው! ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች። ያች በቁፋሮ የተገኘች የዝንጀሮ አጽም ድንቅነሽ (ሉሲ) ስለተገኘችባት ሳይሆን የእግዚአብሔር የእጁ ሥራ የሆነው አዳም ስለተገኘባት ነው።
:
➒ኛ).ከገነት ከሚመነጩና ገነትን ከሚያጠጡ አራት አፍላጋት/ምንጮች/ ትልቁ ግዮን ኢትዮጵያዊ ነው።
:
ግዮን ከገነት ይመነጭና ወደ ምድር ይፈሳል፣ ከዚያም የኢትዮጵያን ምድር ይከባል። ይህ ወንዝ ጎጃም ውስጥ ሰከላ አካባቢ ግሽ ዓባይ የተሰኘ ቦታ ላይ ነው የሚፈልቀው። ከዚያም ሙሉ ጎጃምን እንደመቀነት ይዞርና ወደ ግብጽ ይፈሳል።
:
➓ኛ).ሞትን ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተወሰደውና አዕምሮውን መቶ በመቶ(100%) የተጠቀመበት ብቸኛው የምድራችን ሰው ሄኖክ/ ኢትዮጵያዊ/ ነው።
:
እስከዛሬ ድረስ አዕምሮውን ሙሉ በሙሉ የተጠቀመ ምድራዊ ሰው የለም። የሰው ልጅ የአእምሮው ልዕልና የሚለካው በምድራዊ እውቀት ሳይሆን በሰማያዊ ጥበብ ነው።
:
ሰው የአዕምሮው ልዕልና (IQ) ሲያድግ ወደ ቅድስና ደረጃ ይሸጋገራል እንጅ ምዕራባዊያን እንደሚሉት በምድራዊ ጥበብና እውቀት አይመላም። ይሄን ደግሞ ያደረገ ብቸኛው ሰው ሐበሻው ሄኖክ ብቻ ነው።
:
➊➊ኛ)ሲኦልም ገነትም የሚገኙት በመልአኩ 15 ክንድ ከምድር ከፍ ብለው ኢትዮጵያ (አፋር ኤርታሌና ጎጃም ጣና አካባቢ በቅደም ተከተል) ነው።
:
በድሮው ወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው አፋር ውስጥ የሚገኘው ኤርታሌ የሚባለው ቦታ የራሱ ሰማያዊ ምሥጢር አለው።
:
እዚህ ቦታ ላይ የሚገኘው እሳተ ገሞራ ወይም የእሳት ባህር ሉሲፈር (ሳጥናኤል) የታሰረበት ቦታ መሆኑን አንዳንድ መዛግብት ላይ ለማንበብ ችያለሁ።
:
አዎ ይህ ቦታ የሲኦል መገኛ እንደሆነና ጎጃም የሚባለው ሀገር ላይ በተለይም ደግሞ ጣና ዙሪያ የገነት መገኛ ናቸው።
:
➊➋ኛ).በዓለም ትክክለኛነቱ የተረጋገጠለት የዘመን ስሌት ያለው ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ (ኢትዮጵያ) ውስጥ ነው።

ይህ የዘመን ስሌት አጽዋማትና በዓላት የሚከበሩበት ቀመር የቀናት ብሎም የዓመታት ስሌቱ ያልተበረዘና ትክክለኛ ነው።
:
➊➌ኛ).በነብያት እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች የተባለች ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

አዎ ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። መመኪያዋም አለኝታዋም እርሱ ነውና።
:
ይች ሀገር ከፈጣሪዋ ጋር ልዩ ትስስር ያላት የዓለማችን ብቸኛ ሀገር ነች። ፈጣሪ በስጋ የተመላለሰባት ሀገር እስራኤል እንኳን የኢትዮጵያን ያህል ክብር በፈጣሪ ዘንድ የላትም።
:
ለዚህ ደግሞ ማሳያ የሚሆነን ነገር አለ። እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል እስራኤላዊያንን ሲገስጽ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያዊያን ልጆች (ሐበሾች) አይደላችሁም ነበር ያለ። ልብ በሉ! እንደ ኢትዮጵያዊያን!
:
➊➍ኛ).ታቦተ ጽዮን የሙሴ ጽላት የምትገኝባት ሀገር ኢትዮጵያ ነች።
:
በአምላክ ትዕዛዝና ቀመር የተሰራችው ይህቺ ጽላት በጠቢቡ ሰለሞን የንግሥና ጊዜ የደቡብ ንግስት (ንግስተ አዜብ) ወይም የሳባ ንግስት (ንግስተ ሳባ) ተብላ በምትጠራዋ ንግስት ማክዳ ልጅ በቀዳማዊ ምኒልክ አማካኝነት ነበር ወደ ሀገራችን የገባችው።
:
ምዕራባዊያን ይህቺን መመኪያችንን ጽላት ዘሙሴ ለመውሰድ ብዙ ጊዜ ሞክረዋል። ነገር ግን አልተሳካላቸውም፣ አይሳካላቸውምም። ምክንያቱም እነርሱን ትታ በእኛ ምድር በሀገራችን ትኖር ዘንድ በእግዚአብሔር ፍቃድ መጥታለችና ሊወስዷት ቢኳትኑም አያገኟትም።

➊➏ኛ).የዘንዶ ራስ ተቀጥቅጦ ልዩ ምግብ (ጤፍ) ከፈጣሪ የተሰጣቸው ሕዝቦች /ሐበሾች/ ያሉባት ምድር ነች ኢትዮጵያ።
:
አንተም የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጥህ፣ ለኢትዮጵያዊያን ሰዎችም ልዩ ምግብን ሰጠሀቸው ይላል ቅዱስ መጽሀፍ። አስተውሉ! መርምሩም! የእኛ ምግብ አይጥ፣ እባብ፣ አህያ፣ ውሻ ወይም ሌላ የረከሰ ምግብ አይደለም። እንጀራ ነው እንጅ።
:
፪."ሐዲስ ኪዳን!"
:
➊ኛ).የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም በተወለደ ጊዜ በኮከብ እየተመሩ ሄደው የእጅ መንሻ /ገጸበረከት/ ካቀረቡለት (ሰብዐ ሰገል) መካከል የሀበሻው ንጉሥ ባዜን ይገኛል።
:
መድኃኒታችን ሲወለድ መወለዱን በኮኮብ የገለጸላቸው ለእስራኤላዊያን ወይም ለዐረቦች አይደለም። ለሐበሾች እንጅ። ይሄን ክብር ማን አገኘው?
:
➋ኛ).ማኅደረ መለኮት እመብርሃን ድንግል ማርያም በስደቷ ጊዜ በሰላም ኢትዮጵያ ያረፈችባትና በአስራትነት የተሰጠቻት እንዲሁም በተደጋጋሚ በልጇ መስቀል የባረከቻት ቅድስት ሀገር ቅድስት ኢትዮጵያ

👉እንዴት ነው ወደዳችሁት? ከተመቻችሁ በማድረግ ለሌሎች አድርሱ ።

👉እርሶ ያወቁትን እውቀት ሌሎች ያውቁ ዘንድ ቻናላችንን ሼር በማድረግ ጓደኛዎን ይጋብዙ

11/10/2022

እንኳን ለልደታ ማርያም በዓል አደረሰን

05/10/2022

****8**** Dr Rodas Tadesse

+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል + ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል::  ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ  ቃል ጥሎ...
03/10/2022

+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ቅዱስ ገብርኤልhttps://youtu.be/uxHLCCkCX-k  ገብርኤል ማለት ገብረ ኤል፣ የጌታ አገልጋይ፣ የእግዚአብሔር ሠራተኛ፣ ገብረ አምላክ፣ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው።“በባቦች ላይ...
29/09/2022

ቅዱስ ገብርኤል

https://youtu.be/uxHLCCkCX-k

ገብርኤል ማለት ገብረ ኤል፣ የጌታ አገልጋይ፣ የእግዚአብሔር ሠራተኛ፣ ገብረ አምላክ፣ ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው።
“በባቦች ላይ በገነትም በጻድቃን ላይ በኪሩቤልም ላይ የተሾሙ ከከበሩ መላእክት አንዱ ገብርኤል ነው፡፡”
( ሄኖክ 6፥7)
“በመላእክት ሁሉ ላይ የተሾመ ቅዱስ ገብርኤል ነው።” (ሄኖክ 10፥14)፤

ቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ በጸሎቱ ለታመኑበት ፈጥኖ የሚደርስ በብሉይ እና በሐዲስ ኪዳን በልዪ ልዩ ተልኮዎቹ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፈቃድ በመፈጸም የጸና ሰለሆነ ጥበብ በመግለጽ በማጽናት በማብሰር ከመከራ በማዳን ከእሳት ወላፈን በመታደግ ከአንበሳ መንጋጋ በማትረፍ እና ትዕቢተኞችን በመቅጣት በመገሰጽ እውነተኛ ታዳጊ መልአክ መሆኑን አስመስክሯል።

ሰለስቱ ደቂቅን እንደታደጋቸው እንደተራዳቸው ዛሬም በጸሎቱ ለሚታመኑ ዝክሩን ለሚያደርጉ ድርሳኑን የሚደግሙትን በጸሎት፥ በመዝሙር ፥በቅዳሴ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ክብረ በዓሉን ብናክበር አማላጅነቱን የተሰጠውን ጸጋ ብንመሰክር በበደላችን ምክንያት ከተግባረ ጽድቅ ለተሰደድን ስደተኞች ከባሕረ እሳት ለሰጠምን ኃጥያተኞች የምናመልከው የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር መልአኩን ልኮ የእሳቱን ባሕር ያሻግረናል።

ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምስጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር
እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ የምንሰኝበትን ጸጋ አሰጠን። ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን።

እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን፡፡ የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን
እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን። ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥባቆት ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን።

24/09/2022

እንኳን አደረሰን

"በዓለ ዕረፍቱ ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት"ተክለ ሃይማኖት ማለት ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣  ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ሲሆን የተወለዱት ጽላልሽ ደብረ ኢትሳ ጸጋ አብ እና እግዚእ ኀርያ ...
30/08/2022

"በዓለ ዕረፍቱ ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት"

ተክለ ሃይማኖት ማለት ተክለ አብ፣ ተክለ ወልድ፣ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ማለት ሲሆን የተወለዱት ጽላልሽ ደብረ ኢትሳ ጸጋ አብ እና እግዚእ ኀርያ ከሚባሉ ደጋግ ክርስቲያን ቤተሰቦች ነው።
እሊህ ጻድቅ እግዚአብሔር ለራሱ አገልግሎት የጠራቸው ኅሩይ ስለሆኑበተወለዱ በ3 ቀናቸው እግዚአብሔርን አመሰግነዋል፣ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ካህን ሆነው የሥላሴን መንበር "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” በማለት አጥነዋል፣ ከእነ አባ በጸሎተ ሚካኤል፣ ከእነ አባ ኢየሱስ ሞዓና ከእነ አባ ዮሐኒ ጋር በሐይቅ 10 ዓመት በደብረዳሞ 12 ዓመት ኖረዋል፡፡
ሐዋርያውና ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት በጾምና በጸሎት በመትጋት ወንጌልን በኢትዮጵያ ምድር ዞረው አስተማሩ፣ ሕሙማንን ፈወሱ፣ ተአምራትን አደረጉ፣ በ1267 ዓ.ም ደብረ ሊባኖስን በዓት አድርገው ኖሩ፣ ለ22 ዓመታት ቆመው በመጸለይ የአንድ እግራቸው አገዳ ተሰበረ፣ ደቀ መዝሙርቱ በጨርቅ ጠቅልለው ቀበሩት፡፡
በአንድ እግራቸው ለ7 ዓመት በጸሎት ቆመው ሲጸልዩ ኖረው በ99 ዓመታቸው ነሐሴ 24 ቀን 1290 ዓ.ም አረፉ። ዛሬ የኢትዮጵያ ታላቁ ሐዋርያ ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ቀን የሚከበርበት የከበረ ቀን ነው።
የጻድቁና ሐዋርያው አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎትና ረድኤት አይለየን!
እንኳን አደረሳችሁ!!

Address


Telephone

+251947990542

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Yealem Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Videos

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Videos
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share