Ethiopia muslim Gallery

  • Home
  • Ethiopia muslim Gallery

Ethiopia muslim Gallery Ethiopian historical gallery

11/04/2024

ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ

ከረመዷን በፊት ወደነበርክበት አመፅና ወንጀል ለመመለስ በማኮብኮብ ላይ ያለህ ወንድሜ ሆይ ! አላህን ፍራ! የረመዳኑ ጌታ የተቀሩት ወራቶችም ጌታ ነው ... አሏህን ፍራ!

ፈጣሪህን በመፍራት የታዘዝከው በዚህ ወር ብቻ አይደለም ... ከፀያፍ ነገሮች መራቅ የእድሜ ልክ ግብ እንጂ የአንድ ወር አላማ አይደለም !

ሁሌም ለአላህ እጅ የሰጠህ ሙስሊም ለመሆን ታገል ...

ረመዷን እስኪወጣ ሣይሆን ሩሕ እስኪወጣ ጌታህን ታዘዝ

وَاعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّى يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮችእንኳን ለ1445ኛው የዒድ ዓልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
11/04/2024

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች
እንኳን ለ1445ኛው የዒድ ዓልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የማይሰግድ ሰው እርድ~~~~~~~~~~~~~~~"ሶላት የማይሰግድ ሰው ያረደውን እርድ መብላት ሐራም ነው" ይላሉ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ። [መጅሙዑል ፈታዋ: 12/45]*ይ...
23/03/2024

የማይሰግድ ሰው እርድ
~~~~~~~~~~~~~~~
"ሶላት የማይሰግድ ሰው ያረደውን እርድ መብላት ሐራም ነው" ይላሉ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ። [መጅሙዑል ፈታዋ: 12/45]
*
ይህንን ሐቅ ተግባራዊ ብናደርገው:–
,
① እራሳችንን ያልተፈቀደ ነገር ከመመገብ እጠብቃለን።
② በየቤታችን፣ በየ ሰርጉ፣ በየ ድግሱ፣ በየ ምግብ ቤቱ፣… ሶላት ለማይሰግዱ ሰዎች ጠንካራ መልእክት እናስተላልፋለን።

23/03/2024

አላህ ሆይ

ካንተ በስተቀር በእውነት የሚገዙት አምላክ የለም፤ለስልጣንህ ተጋሪ የለህም፣ የሰማይ እና የምድር ብቸኛ አስተናባሪ ነህ:: የፍርዱ ቀን ባለቤትህም ነህ::

ጌታችን ሆይ

የፆምነውን ፆም ተቀበለን፣ ያጓደልነውን በእዝነትህ ሸፍንልን፣ መልካም ስራዎቻችን ሁሉ ተቀበለን

ሃያሉ ጌታችን ሆይ

የረመዳን ወር ፆም የፍርዱ ቀን ላይ ለኛ የሚመሰክርልን እንጂ በኛ ላይ የሚመሰክርብን አታድርግብን

አዛኙ ጌታችን ሆይ

በዚህ ባሳለፍነው ረመዳን ወንጀላቸው ሙሉ ለሙሉ ከተማረላቸው፣ ከእሳት ቅጣትም ነጃ ካወጣሃቸው ባሮችህ መድበን

በህይወት ላሉት እና ለሌሉት ምዕመናን በሙሉ ምህረትህን ለግስ፣ ከዚህች አለም እና ከቀጣዩ አለም ፈተናም ጠብቀን

ጌትዬ

ወዳንተ አልቀሰን ተመልሰናል እና ከሰፊው ምህረትህ አቋድሰን:: በወንጀላችን ብዛት ካመጣህብን በላዕ ነጅ አውጣን

አላህ ሆይ

በዲናችን ላይ የመጣብንን ፈተና አንሳልን:: የምዕመናንን ልቦናዎች አስማማ:: በሃቅ ላይ አንድነታችን የሚጠናከር አድርገው:: ዲናችንን ከፍ ለማድረግ እየለፉ ያሉትን ሁሉ ከፍ አድርጋቸው:: ዲናችንን ለማዋረድ የሚጥሩትን ሁሉ አዋርዳቸው:: በማንችለው ፈተና አትፈትነን

ኢላሂ

በህይወት ያሉ ወላጆቻችንን ረጅም እድሜ ከአፊያ ጋር ለግሳቸው:: ሃቃቸውንም ከማጉደል ጠብቀን::

በህይወት የሌሉ ወላጅቻችንንም በሰፊው እዝነትህ አካባቸው:: በልጅነታችን ኖሯቸው ምንም አልከለከሉንም ኣንተም ጀነትህን አትከልክላቸው

አሚን

23/03/2024
12/03/2024

የረመዳን ፆምን የማያበላሹ የህክምና ተግባራት

1, የአይን ጠብታና የጆሮ ጠብታ መድሀኒቶች ፆምን አያበላሹም።

2, የአስም በሽተኞች የሚነፋ መድሃኒታቸውን (Salbutamol puff) እየፆሙ ቢወስዱ ችግር የለውም።

3, ጥርስን ማስነቀል ወይም ጥርስን ማስሞላት ፆምን አያጠፋም።

4, በምላስ ስር የሚደረጉ ኪኒኖች: የልብ በሽታን (MI) ለማከም ... ለሌሎችም በሽታዎች የሚረዱ መድሀኒቶች እስካልተዋጡ ድረስ ፆምን አያበላሹም።

5, ፆመኛ ሰው የደም ምርመራ ለማስደረግ ብሎ ደሙን ቢሰጥ ፆሙ አይፈርስም።

6, በደምስር (IV) ወይም IM የሚሰጡ ምግብን የማይተኩ መድሀኒቶች (ማስታገሻዎች ፣ ክትባቶች ፣ Antibiotics) እንዲሁም ሲቲስካን (CT Scan) ወይም MRI ለመነሳት በደምስር የሚሰጡ መድሀኒቶች (Intravenous contrast) ፆምን አያበላሹም።

7, በበሽታ ወይም በማንኛውም ምክንያት ሳያውቁ ማስታወክ ፆምን አያጠፋም።

8, ሂጃማ (ዋግምት) ፆምን ያበላሻል ወይስ አያበላሽም በሚሉት ሀሳቦች በዑለማዎች (በዲን አዋቂዎች) መካከል ብዙ ሀሳቦች የተሰጠበት ሲሆን ለመጠንቀቅ ያክል በፆም ሰዓታት ዋግምት ከመደረግ ብንቆጠብ የተሻለ ነው። የሂጃማ (የዋግምት) ድንጋጌ በዘመናዊ የህክምና መንገድ ለምንጠቀመው Phelbotomy ይውላል።

9, ነስር ያለበት ሰው በብዛት እንኳን ደም ቢፈሰው ፆሙ አይበላሽም። እየፆመ ያለ ሰው በአደጋ ወይም በሌላ ምክንያት በብዛት ደም ቢፈሰው ፆሙ ላይ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን በዚህ ምክንያት ከታመመና ከደከመ ፆሙን አጥፍቶ መመገብ ይችላል።

10, በጤናዋ ላይ ችግር የማያስከትልባት ከሆነ አንዲት ሴት የወር አበባ የሚያስቆም መድሀኒት ተጠቅማ ረመዳንን ብትፆም ችግር የለውም። አንዲት ሴት የረመዳን ቀናት ፆሞችን ፣ ለይለቱል ቀድር ፣ በሀጅና ዑምራ ላይ ያሉ አንዳንድ ተግባራት የመሳሰሉትን ዒባዳዎች እንዳያመልጧት የወር አበባን የሚያስቆም መድሀኒት መጠቀምዋ ጤናዋ ላይ ችግር የማይስከትል ከሆነ ችግር አይኖረውም። ነገር ግን መድሀኒቶቹ የጎኒዮሽ ጉዳት ስላላቸውና ሴቷ ራሷን ተከሉፍ (ራሷን ማስገደድ) ውስጥ ባታስገባ የተሻለ ይሆናል። ኪኒን ተጠቅማ ግን ብትፆምና ዒባዳዎችን ብትተገብር ተቀባይነት አለው።

11, በሴት ማህፀን ወይም ብልት ውስጥ የሚከተቱ የህክምና መሳሪያዎች ፣ ምርመራዎች ፣ መድሀኒቶችና የእርግዝና መከላከያዎች ፆምን አያበላሹም።

[ እነዚህ የረመዳን ፆምን የሚመለከቱ የህክምና ብያኔዎች ቁርዓንና ሀዲስን ብሎም የአራቱ አዒማዎች መዝሀቦችን ተመርኩዘው በዘመናችን ዑለማዎች (የዲን ዓዋቂዎች) የተሰጡና የተጠናቀሩ ናቸው።]

ሼር ያድርጉት ያላወቁትን ያሳውቁ
ዶ/ር መቅሱድ ሸምሱ

12/03/2024
• Today's the best Photo 🌿🥰•🔴 Beautiful                                                                                 ...
12/03/2024

• Today's the best Photo 🌿🥰

•🔴 Beautiful














































27/02/2024
የዘንድሮ እሮመዳን ወር መጋቢት ዉስጥ ይጀምራል ኢነሻአላህ ነብያቺን (ሰ.ዐ.ወ) ምን ብለዋል አንድ ሰዉ ለሌላዉ እሮመዳን መምጣቱን ለመጀመሪ ጊዜ ያሳወቀ እሳት በእርሱ ላይ ሀራም ትሆንበታለቺ...
27/02/2024

የዘንድሮ እሮመዳን ወር መጋቢት ዉስጥ ይጀምራል ኢነሻአላህ ነብያቺን (ሰ.ዐ.ወ) ምን ብለዋል አንድ ሰዉ ለሌላዉ እሮመዳን መምጣቱን ለመጀመሪ ጊዜ ያሳወቀ እሳት በእርሱ ላይ ሀራም ትሆንበታለቺ ብለዋል ሰለዚህ ሸር እናድርግ አላህ ፆም ከሚፁሙት ያድርገንመሀል ያድርገን ያረብ ያረብ ያረብ ያረብ ያረብ ያረብ

11/02/2024
11/02/2024

አቡኬ ከመቀሌ ሰማይ ስር ❤

ኡስታዞቻችን በአፋር መዲና ሰመራ ♥በአፋር የባህል አልባሳት ፍክት ድምቅ ብለው!
28/01/2024

ኡስታዞቻችን በአፋር መዲና ሰመራ ♥
በአፋር የባህል አልባሳት ፍክት ድምቅ ብለው!

በሀላባ ሙተነቂብ ተሸላሚ ተማሪዎች! ማሻአላህ!ኢስላማዊ አለባበስ ለየትኛውም ስኬት ተግዳሮት የማይሆንና የጨዋነት እና የስነ-ስርዐት መገለጫ ነው!ኒቃቧንም ትለብሳለች ፤ ትምህርቷንም ትማራለች!
22/10/2023

በሀላባ ሙተነቂብ ተሸላሚ ተማሪዎች! ማሻአላህ!
ኢስላማዊ አለባበስ ለየትኛውም ስኬት ተግዳሮት የማይሆንና የጨዋነት እና የስነ-ስርዐት መገለጫ ነው!
ኒቃቧንም ትለብሳለች ፤ ትምህርቷንም ትማራለች!

29/09/2023

ሰላት የምትሰግደው
በትርፍ ጊዜ አይደለም
አንዳንድ ጊዜ አይደለም
በፈለከው ጊዜ አይደለም
ሰላት ሁል ጊዜ
በጊዜ
ተጨማሪ ጌዜ ሰጥተህ መሆን አለበት
ምክንያቱም ሞት በየትኛው ጊዜ እንደሚመጣ አታውቅምና ነው። ዶ/ር ዛኪር ናይክ - peace tv amharic ሸይኽ አህመድ ዲዳት

🎈የዛሬውን ለሊት ሁላችንም በኢባዳ እንትጋበት!የዛሬው የረመዳን ለሊት የረመዳን 27ተኛ ለሊት ነው። ይህ ለሊት ደግሞ ለይለቱል ቀድር ይበልጥ የሚከጀልባት ለሊት ነው። በለይለተል-ቀድር ደግሞ ...
17/04/2023

🎈የዛሬውን ለሊት ሁላችንም በኢባዳ እንትጋበት!

የዛሬው የረመዳን ለሊት የረመዳን 27ተኛ ለሊት ነው። ይህ ለሊት ደግሞ ለይለቱል ቀድር ይበልጥ የሚከጀልባት ለሊት ነው። በለይለተል-ቀድር ደግሞ የሚሰራ ዒባዳ ከ1 ሺህ ወራቶች (83 ዓመት) ዒባዳ የሚበልጥ ሲሆን ከነቢዩ (ሰዓወ) ሰሀባዎች ውስጥ፥ ሰይዱና ዑመር(ረዓ)፣ ኢብኑ ዐባስ ፣ኡበይ ኢብኑ ከዕብ፣ ሙዓዊያ፣ ሁዘይፋና ሌሎችም( አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው) ለይለተል-ቀድር 27 ሌሊት ላይ ናት ይሉ ነበር!

በዚህች ለሊት ሁላችንም ለዱኒያችንም ለአኼራችንም ዱዓ ልናደርግ፣ ለሀገራችንም ሆነ ለመላው አለም የሰው ልጆች ዱዓ የምናደርግበት ሊሆን ይገባል::

ለሊቱን በኢባዳ ማሳለፍ ፣ይበልጥ ወደ አላህ ተናንሰን መቃረብ እና ማሃርታውን መጠየቅ ፤ከአሳማማሚው የጀሀነም እሳትም እንዲታደገን ጌታችንን መማፀን አንዘንጋ

አላህ ለይለቱል ቀድርን ይወፍቀን

ወንጀላችንም ይማረን

16/09/2022

«Qafárim aba!» akak iyyen mari zulmit ibak gabah giirisak nizaam maleh baaxo baysaanamat culeenim tamballe.

Too waqdi sarra "neh mawarisnniton" iyyaanamak yalli (s.w) Addunyâ bagul zulmit giirisak suge mara wagsiisak iyyem ahaak gubal ken kassisna.

قال -تعالى-: (وَنَقُولُ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا ذُوقُوا عَذَابَ النَّارِ الَّتِي كُنتُم بِهَا تُكَذِّبُونَ).[٨]

«Sinni nafsi yuzlume marak girâ digaalay addunyal dirabboysak sugteeni tammoysa keenik inna».

قال -تعالى-: (مَا لِلظَّالِمِينَ مِنْ حَمِيمٍ وَلا شَفِيعٍ يُطَاعُ).[٩]

«Zaalimiin xayi kataysa maliiy, yab kak oggolan
cateyna mali Yallih xaqul.»

قال -تعالى-: (وَمَا لِلظَّالِمِينَ مِن نَّصِيرٍ).[١٠]

«Zaalimiin hebeltô cateynay Yallih digaalá keenik waasa mali.»

قال -تعالى-: (أَلاَ لَعْنَةُ اللّهِ عَلَى الظَّالِمِينَ).[١١]

«Zaalimiinih yan mara Yalli ken yinqibeeh usuk isi Racmatak ken yayxeerem keenil tan.»

قال -تعالى-: (وَقِيلَ لِلظَّالِمِينَ ذُوقُوا مَا كُنتُمْ تَكْسِبُونَ).[

«Zaalimiinik addunyal abak sugten umaanéh galtó tammoysa keenik iyyan.»

قال -تعالى-: (إِنَّ اللّهَ لاَ يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ).[١٤]

«Diggah Yalli zaalimiinih yan maray koroosite mara Awlah haysita tirri mahaa.»

قال -تعالى-: (‌‏ وَقِفُوهُمْ إِنَّهُم مَّسْئُولُونَ‏).[١٥][١٦]

«Madqâ garil ken eyseeda, diggah usun addunyal abeenimik esserimaanahak.»

Yalli zulmik nee cattaay, zaaliimak nee edde catam yallak qaaginna

15/09/2022

ስድስቱ⑥ የተውበት መስፈርቶች ↓

#በህይወታችን ብዙ ጊዜ #ወንጀሎችን እንፈፅማለን። #አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት #እንዳይጠየቅ ተውበት #ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ #መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን #የሚጨነቀው? #እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን #እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን #በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ #ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ።

። እነሱም:-

→1 #ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ ነው ተውበቱን ማድረግ ያለበት። #አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ #የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት አላሟላም፡፡

→2 :– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው #የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ወዲያው ሊያቆም ይገባል።

→3 ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡሀላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው #መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።

→ #4 ። ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የእውነት #አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል፡፡

#ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው #ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው #የሰው ወሬ #ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ #አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።

→ #5 ፡፡ይህም ማለት ሞት አፋፍ #ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።

→ #6 ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ወይም ኢስቲግፋርና #ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል፡፡

አላህ ሆይ #ከመሞታችን በፊት ንፁህ የሆነችን ተውበት ወፍቀን።

#ጥራት ይገባው ሰዎችን #ለተውበት የገጠመ #እግሮችንም በመንገዱ #ላይ ያፀና ካንተ ውጭ አስጠጊ #የለኝም ጌታየ በይቅርታህ ከቅጣትን እጠበቃለሁ ብትቀጣኝ በፍትህ ብትምረኝ አንተ ለሱ የተገባህ ነህ። አቤት የተውበተኞች ደስታ በአላህ ፍቅር። አላህ ተውበት አድራጊዎችን ይወዳል #ተጥራሪዎችንም ይወዳል።

#አላህ ሆይ አንተ ጌታየ ነህ ካንተ ውጭ አምላክ የለም ፈጠርከኝም ባሪያህ አድርገህ እኔ የቻልኩትን ያክል #በትዕዛዛቶችህ ላይ ነኝ #ከሰራሃው መጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ በኔ ላይም #በዋልከው ፀጋ እውቅና እሰጣለሁ ወንጀሌንም እናዘዛለሁ ማረኝ!! ካንተ ውጭ ወንጀል የሚምር የለምና።

15/09/2022

መልክት ለሁሉም
አላህን የሚፈሩ ሰዎች ምንኛ የታደሉ ናቸው•
أَلَا إِنَّ أَوْلِيَاءَ اللَّهِ لَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡
الَّذِينَ آمَنُوا وَكَانُوا يَتَّقُونَ

(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡

لَهُمُ الْبُشْرَىٰ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۚ لَا تَبْدِيلَ لِكَلِمَاتِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

ለእነሱ በቅርቢቱ ሕይወትም በመጨረሻይቱም ብስራት አላቸው፤ የአላህ ቃላት መለወጥ የላትም፤ ይህ እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ [yunus 62~64]

إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَعِيمٍ

አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡

فَاكِهِينَ بِمَا آتَاهُمْ رَبُّهُمْ وَوَقَاهُمْ رَبُّهُمْ عَذَابَ الْجَحِيمِ

ጌታቸው በሰጣቸው ጸጋ ተደሳቾች ኾነው (በገነት ውስጥ ናቸው)፡፡ የገሀነምንም ስቃይ ጌታቸው ጠበቃቸው፡፡

كُلُوا وَاشْرَبُوا هَنِيئًا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

«ትሠሩት በነበራችሁት ምክንያት ተደሳቾች ኾናችሁ ብሉ፤ ጠጡም፤» (ይባላሉ)፡፡

مُتَّكِئِينَ عَلَىٰ سُرُرٍ مَّصْفُوفَةٍ ۖ وَزَوَّجْنَاهُم بِحُورٍ عِينٍ

በተደረደሩ አልጋዎች ላይ ተደጋፊዎች ኾነው (በገነት ይኖራሉ)፡፡ ዓይናማዎች በኾኑ ነጫጭ ሴቶችም እናጠናዳቸዋለን፡፡ [አጡር 17~20]

إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُتَّقِينَ

አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና፡፡ [አተውባ 4]

ጌታችን ሆይ!_

አንተን ከሚፈሩት
አንተን ከሚገዙት
አንተን ከማያምፁት
ጥንቁቅ ባሮችህ አድርገን
በእዝነትህም ጀነትን ወፍቀን!

15/09/2022

👉 አደራ አደራ አንብባችሁ ስትጨርሱ ለሌሎችም ሼር አድርጉላቸው

ዋ! በዚህች አለም ባይተዋርነቴ😥

ዋ! በመሞቻዬ ጊዜ አወይ መከራዬ😥

ዋ! በቀብሩስጥ ብቸኝነቴ😥

ዋ! በለህዱስጥ ጭርታዬ😥

አምላኬ ሀጥያቴን ከሰው ጋርድልኝ
ሰዎች ያላወቁትን ክፉ ስራዬ ይቅር በለኝ
የሞት ፍራሽ ላይ ተንጋልዬ የወላጆቼ እጆች አስክሬኔን ሲያገላብጡት!
እባክህ እዝነትህን አትንፈገኝ🤲

ሀጢያቴን ከሰው የጋረድክልኝ ክርዶሽህን እባክህ አታንሳብኝ ጌታዬ🤲

የአስክሬኔን ጫፎች ወዳጅ ዘመዶቼ ከቀኝ ከግራ ይዘውኝ ሲሸከሙት ቻለኝ ታገሰኝ አምላኬ 🤲

እንግዳ ሆኜ ወዳንተ ስመጣ ከሰው ተነጥዬ ቀብሩስጥ ብቻዬን ስሆን ቸርነትህን አትንፈገኝ እባክህን ጌታዬ 🤲
በዚህ በአዲስ ጎጆ ✨በዚህ በአዲስ ጎጆ በማላቀው ሀገር እዘንልኝ አምላኬ🤲

ለባይተዋርነቴ ባንተ ብቻ የምደሰት ባንተ ብቻ የምጸና አድርገኝ ጌታዬ🤲

15/09/2022

ኢማን - ለሕይወት ምሬት ቅመም ነው፣ ለመንገደኛ አጫዋች ነው፣ ለባይተዋር ጓደኛ ነው፣ ለብቸኛ ሰው ወዳጁ ነው፡፡
ኢማን - ግራ የገባዉን ይመራል፣ የተጎዳን ያጽናናል፣ የደከመዉን ያበረታል፡፡
ኢማን - በስደት ዓለም ባልደረባ ነው፣ ለጨለመበት ብርሃን ነው፣ ዕድሜው ለገፋ ምርኩዝ ነው፡፡
ኢማን - ለታጋይ መሣርያው ነው፣ ለደካማ ብርታቱ ነው፣ መላ ለጠፋው መፍትሄ ነው፡፡
ኢማን - የተዘጋን ይከፍታል፣ የጨለመን ያበራል፡፡

14/09/2022

የዑለማኦቹ መልስ

** አንድ ሰው ኢብኑ አልጀውዚ ረሂመሁሏሁ ዘንድ መጣና ‹ተስቢህ ወይንስ ኢስቲግፋር ላድርግ የቱ ይሻለኛል?› አላቸው፡፡
እርሣቸውም ‹ አንድ ሰው ልብሱ የቆሸሸ እንደሆነ ሽቶ ከመቀባት ይልቅ ማጠብ ይሻለዋል፡፡› አሉት፡፡ (ከአላህ ምህረት መጠየቅን አስቀድም፡፡› ማለታቸው ነው፡፡

** ኢማሙ ሻፊዒይ ‹ዓሊም የማያውቀውን ጥያቄ ይጠየቃል ወይ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡
እርሣቸውም ‹ዓሊም የሚያውቀውንም የማያውቀውንም ሊጠየቅ ይችላል፡፡ የሚያውቀውን ይመልሣል፤ የማያውቀውን ይማራል፤ ጃሂል ግን ሲጠየቅ ይቆጣል፤ ለመማርም ዝግጁ አይደለም፡፡› አሉት።

*** ኢማም ሻፊዕይ ‹ በእድሜ ወጣት ሆነው ሣለ ለምን ምርኩዝ ይይዛሉ?› ተብለው ተጠየቁ፡፡
እርሣቸውም ‹ መንገደኛ መሆኔን መርሣት እንደሌለብኝ እራሴን ለማስታወስ፡፡› ብለው መለሱ፡፡

** ኢብኑ ዑመር የሚገዙትም ሆነ የሚሸጡት ነገር ሣይኖር ምን ሊያረጉ ገበያ እንደሚሄዱ ተጠየቁ ‹ ለወንድሞች ሠላምታ ለማቅረብ፡፡› ብለው መለሱ፡፡›

05/09/2022

የውበት ጥግ ኒቃብ

ማሻአላህ

05/09/2022

"ሁሉም ሰው ሞትን ይቀምሳል! ነገር ግን ህይዎትን የሚቀምሷት እጅግ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው"

አላህ መጨረሻችንን ያሰምርልን አሚን በሉ☺️💔🥺

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopia muslim Gallery posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethiopia muslim Gallery:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share